የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
رفتن به کانال در Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
نمایش بیشتر4 374
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
4 374
#በእንተ_ልደቱ_ለእግዚእነ_ኢየሱስ_ክርስቶስ
🌾🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾🌾
፩. #በኮከብ_መጽኡ
በኮከብ መጽኡ(፪) ሰብአ ሰገል
ለአማኑኤል(፬) ይስግዱ ለአማኑኤል
፪. #ቤዛ_ኩሉ
ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ(፪)
ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ(፬)
የዓለም ሁሉ መድኀኒት ዛሬ ተወለደ(፪)
የዓለም ሁሉ መድኀኒት ዛሬ ተወለደ(፬)
፫. #አንፈርዐጹ
አንፈርዐጹ ሰብአ ሰገል(፪)
አምኃሆሙ አምጽኡ መድምመ(፪)
፬. #አንፈርዐጹ
አንፈርዐጹ ሰብአ ሰገል ረኪቦሙ ህፃነ ህፃነ(፪)
ዘተወልደ ለነ(፬) ህፃነ ዘተወልደ ለነ
፭. #በቤተልሔም_ተወልደ
በቤተልሔም ተወልደ(፪) አማኑኤል
እምዘርአ ዳዊት (፬) ተወልደ አማኑኤል
፮. #ተወልደ_ኢየሱስ
ተወልደ ኢየሱስ በቤተልሔም(፪) ዘይሁዳ በቤተልሔም
አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ(፪) በቤተልሔም
፯. #ወወለደት
ወወለደት ወልደ ዘበኩራ(፪)
መንጦላዕተ ደመና ሠወራ(፬)
፰. #ለዘተወልደ
ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል ምንተንብሎ ናስተማስሎለመድኀኒነ
አርዌ ገዳምኑ አንበሳ ወሚመ(2) ከራድዮን
፱. #ስብሐት_ለእግዚአብሔር
ስብሐት ለእግዚአሔር በሰማያት(፪)
ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብዕ ሃሌሉያ(፫)ሃሌ(፪)ሉያ
፲. #አማን_በአማን
አማን በአማን(፪) መንክር(፪)
መንክር ስብሐተ ልደቱ(፬)
እውነት በእውነት(፪) ድንቅ ነው (፪)
ድንቅ ነው የጌታ ልደቱ(፬)
፲፩. #ይትፌስሃ
ይትፌስሃ አድባረ ጽዮን ወይትሀስያ አዋልደ ኢትዮጵያ
እስመ ተወልደ ብኁተ ልደት መድኀኔዓለምበኢየሩሳሌም መድኀኔዓለም
፲፪. #ዮም_ሰማያዊ
ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል
ርዕይዎ ኖሎት (፪)አእኮትዎ መላእክት(፪)
፲፫. #ወእንዘ_ትፈትል
ወእንዘ ትፈትል(፪)ወርቀ ወሜላተ አስተርአያ ገብርኤል ግብተ
ወይቤላ(፪) እስመ ረከብኪ ሞገሰ በሀበ እግዚአብሔር
፲፬. #ወእንዘ_ትፈትል
ወእንዘ ትፈትል/፪/ ወርቀ ወሜላት
አስተርአያ ገብርኤል አስተርአያ ለማርያም
፲፭. #ለድንግል
ለድንግልገብርኤል አብሰራ
ሚካኤል/፪/በክነፍ ጾራ/፪/መንጦላዕተ ደመና ሠወራ
፲፮. #ሊቀ_መላእክት
ሊቀ መላእክት ገብርኤል ዘአብሠራ ለድንግል
ኃያል ኃያል/፬/ ሰዳዴ ሳጥናኤል ኃያል ገባሬ ኃይል
፲፯. #መጽአ_ከመ_ይቤዙ
መጽአ ከመ ይቤዙ ዓለም
የሀበነ ሰላመ ጋዳ ያበውዑ ቁርባነ
፲፰. #በጎለ_እንስሳ
በጎለ እንሰሳ
በጎለ እንሰሳ ተወልደ አማኑኤል
፲፱. #ብርሃን_ዘመፅአ
ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም(፪)
ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም(፬)
፳. #ኢየሱስ_ክርስቶስ
ኢየሱስ ክርስቶስ መፅአ ውስተ ዓለም
በብርሃኑ ንዑ ናንሶሱ
፳፩. #መድኀኒነ
መድኀኒነ ተወልደ ነዋ መድኀኒነ ተጠምቀ ነዋ(፪)
ይዕዜኒ ለሰላም ንትልዋ(፬)
፳፪. #ኢየሩሳሌም_በሆን
እንደ ዮሴፍ ወይ እንደ ሰሎሜ በሆን
ኢየሩሳሌም(3) በሆን አምላክ ሲወለድ ባየን
እንደ እረኞች ወይ ሰብአ ሰገልን በሆን
ኢየሩሳሌም(3) በሆን አምላክ ሲወለድ ባየን
፳፫. #በጎል_ሰከበ
በጎል ሰከበ በአፅርቅት ተጠብለለ
ቤዛ ከሉ ዓለም(፪)ዮም ተወልደ
በበረት ተኛ በጨርቅም ተጠቀለለ
የዓለም መድኀኒት(፪) ዛሬ ተወለደ
፳፬. #እም_ሰማያት
እም ሰማያት ወረደ ወእማርያም ተወልደ(፪)
ከመይኩን ቤዛ(፪) ለኩሉ ዓለም ለብሰ ሥጋ ማርያም
ከሰማያት ወረደ ከድንግል ማርያም ተወለደ
እንዲሆነን ቤዛ(፪)ለዓለሙ ሁሉ ተዋሐደየማርያምን ሥጋ
፳፭. #የምስራች
የምስራች ደስ ይበለን(፪)
የዓለም መድኃኒት ተወለደልን
ምስራች ደስ ይበለን
የምሥራች ደስ ይበለን(፪)
ጌታችን ተወልዶ አይተነው መጣን(፪)
ንጉሥ ሄሮድስ ይህን ሲሰማ
ፈልጋችሁ አምጡት በቀን በጨለማ(፪)
ሰብአ ሰገል እንደታዘዙት
በኮከብተመርተው ህፃኑን አገኙት(2)
ሰገዱለት ከመሬት ወድቀው
ወርቅዕጣን ከርቤውንም ሰጥተው(2)
፳፮. #ይኸው_ተወለደ
ይኸው ተወለደ የዓለም መድኃኒት(3)
እሰይ ተወለደ የዓለም መድኃኒት(3)
ትንቢት ተናገሩ ነቢያት በሙሉ(3)
አምላክ ቀዳማዊ ይወርዳል እያሉ(3)
ሰብአ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ(3)
የእስራኤል ንጉሥ ተወልዷል እያሉ(3)
ሰብአ ሰገል እጅ መንሻ ይዘው(3)
ወርቅ ዕጣን ከርቤውን ገበሩለት ሰግደው(3)
ህፃናት እንሂድ ከልደቱ ቤት(3)
ውኃው ሆኗልና ማርና ወተት(3)
በሶርያ ታየ ፈጣሪ እንደእነግዳ(3)
ብስራተ ልደቱን ለሁሉ ሊያስረዳ(3)
፳፯. #ሳርቅጠሉ_ሰርዶው
ሳር ቅጠሉ ሰርዶ ሰንበሌጥ ቄጤማው
በዚያች ቀን በዚያች ወር ለምለም የነበረው
በእልልታ ዘመሩ በደስታ ተውጠው
ጌታ መወለዱን የምስራች ሰምተው
እልል በይ ቤተልሔም ሃሌ ሃሌሉያ
የፍቅር የሰላም ነሽና ገበያ
የታደሉ እረኞች ያደሩ በትጋት
ብርሃን ሆነላቸው በእኩለሌሊት
ጥሪ ተደርጎለት ከሰማይ ሰራዊት
ለመመልከት በቃ የጌታውን ልደት
እረኝነት ትንሽ የወራዳ ግብር
ብሎ ሰው በልማድ ደንግጎ ነበር
አምላክ የመረጠው መሆኑን እረኛ
ክርስቶስ ሲወለድ ተረዳነው እኛ
የተነበዩለት ነቢያት በሙሉ
ጌታ ተወለደ የምስራች በሉ
ሰውን በመውደዱ ሰማያዊው ንጉስ
ይኸው ተወለደ እኛን ለመቀደስ
የሩቅ ምስራቅ ሰዎችሰብአ ሰገል ሰምተው
ሊሰግዱለት መጡ በኮከብ ተመርተው
ዕጣንና ከርቤ ወርቁንም አመጡ
እንደየስርአቱ እጅ መንሻ ሰጡ
ስለተወለደ መድኅን የእኛ ተስፋ
በደል ተወገደ ኃጢያትም ጠፋ
፳፰. #አንቺ_ቤተልሔም
አንቺ አንቺ ቤተልሔም የይሁዳ መሬት
በአንቺ ተወለደ የዓለም መድኃኒት
ለአዳም ክብር ሲሻ ቤተልሔም
ለሁሉም ሰላም ”
ዛሬ ተወለደ ”
ከድንግል ማርያም ”
እጅ መንሻ አቀረቡ ቤተልሔም
የምሥራቅ ነገሥታት ”
በከብቶች በረት ”
ተኝቶ ላገኙት ”
እሥራኤል ሕዝቤን ቤተልሔም
የሚጠብቃቸው ”
ከአንቺ ይወጣል ብሎ ”
እንደ ነገራቸው ”
፳፱. #እሰይ_እሰይ_ተወለደ
እሰይ እሰይ ተወለደ (፪)
ከሰማየ ሰማያት ወረደ (፪)
ከድንግል ማርያም ተወለደ
እሱ ባይወለድ እሰይ እሰይ
ቸሩ አባታችን ”
መች ትገኝ ነበረ ”
ገነት ምድራችን ”
ብርሃን ወጣላቸውእሰይእሰይ
ለመላ ሕዝቦቹ ”
በጨለማ ጉዞ ”
እንዲያ ሲሰላቹ ”
እንደ ጠል ወረደ እሰይ እሰይ
ከሰማይ ወደ እኛ ”
ወገኖቹን ሊያድን ”
ከኃጢአት ቁራኛ ”
እግዚአብሔር አብ ላከ እሰይ እሰይ
አንድያ ልጁን ”
እርሱ ወዷልና ”
እንዲሁ ዓለሙን ”
፴. #አዳምን_ያልተወው
አዳምን ያልተወው እንደተሰደደ
እሰይ የምሥራች ዛሬ ተወለደ (፪)
አምላካችን መድኃኒታችን
ተወለደ ለነፃነታችን(፪)
አዳምን ያልተወው እንደ ተጨነቀ
እሰይ የምሥራች ዛሬ ተጠመቀ (፪)
አዳምን ሊጠራ የመጣው ሙሽራ
በገሊላ መንደር ለሠርግ ተጠራ(፪)
ሠርግ ቤት እንዳለ በክብር ተቀምጦ
የወይን ጠጅ ሆነ ውሃው ተለውጦ (፪)
እጅግ ያስደንቃል የጌታችን ሥራ
በገሊላ መንደር ይህን ተአምር ሠራ (፪)
ጌታችን አንድ ቀን ያደረገው ተአምር
ሲያስደንቅ ይኖራል ይህን ሁሉ ፍጡር (፪)
4 374
#የሱራፊ_ማዕጠንት_የአምላክ_እናት
☞✞በቅዱሳት መጻሕፍት ምስጢር የተራቀቁ ቀደምት ሊቃውንት ቅድስት
ድንግል ማርያምን ዮሐንስ ባያት በመላእክት እጅ በተያዘች የወርቅ ማዕጠንት መስለዋት አስተምረዋል (ዮሐ ፰፥፫‐፬)፡፡
☞✞ይኸውም የሥነ ፍጥረት መጻሕፍት እንደሚያስረዱን ልዑል እግዚአብሔር
ከሰራዊተ ሩፋኤል ኻያ አራት ሊቃናትን መርጦ በመንበረ መንግሥት ዙሪያዋን
ክንፍ ለክንፍ አያይዞ አቁሟቸዋል፤ “ወሰመዮሙ ለእሙንቱ ካህናተ ሰማይ
ወወሀቦሙ ማዕጠንታተ ዘእምወርቀ እሳት ወአክሊላተ ብርሃን ዘእምጳዝዮን
ወአብትረ ዘከተማሆን መስቀል ወአልበሶሙ አልባሰ ክህነት ዘሕብሩ መብረቅ” ይላል እነዚኽን ስማቸውን “ካህናተ ሰማይ” ሲላቸው የእሳት ወርቅ ጽና አስያዛቸው፤ የብርሃን አክሊል ጳዝዮን ከሚባል የብርሃን ዘውድ ደፋላቸው፤
ማኅተሙ መስቀል የኾነ የብርሃን ዘንግን አስያዛቸው፤ ሕብሩ መብረቅ የመሰለ
የብርሃን ካባ ላንቃ አልብሷቸዋል።
☞✞ዮሐንስም በራእ ፬፥፬‐፭ ላይ “በዙፋኑ ዙሪያም ኻያ አራት ዙፋኖች ነበሩ
በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ኻያ አራት ሊቃናት ተቀምጠው ነበር” ብሏል፡፡
☞✞ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በአክሲማሮስ ላይ “ወይወፅእ እምውስተ ማዕጠንቶሙ
መብረቅ ወነጐድጓድ ወፀዓዕ ዘመዐዛሁ ሠናይ ወይቤሎሙ እግዚአብሔር
ለካህናቲሁ ጸሎተ ኲሎሙ ቅዱሳን ይኩን ውስተ ማዕጠንትክሙ ከመ ይዕርግ
ኀቤየ” እንዳለው፤ እነዚኽ ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ በአንድ ላይ ባጠኑ ጊዜ
ከማዕጠንታቸው የሚወጣው ጢስ መልኩ መብረቅ፤ ድምፁ ነጓድጓድ፤ መዐዛው መልካም የኾነ ሲኾን የጻድቃን ጸሎት፣ የሰማዕታት ገድል፣ የደጋግ ሰዎች
ምግባር በእናንተ ማዕጠንት እየታጠነ ወደኔ ይድረስ ብሏቸዋል፤ “ወይገለብቦ
ለሰማይ ወለአርያም ጢሰ ዕጣኖሙ ዘመዐዛሁ ሠናይ” ይላል ዛሬ በክረምት
ተራራውን ኮረብታውን ጉም እንደሚሸፍነው እንደሚጋርደው ኹሉ ካህናተ ሰማይም የሚያጥኑት ማዕጠንት ጽርሐ አርያምን መንበረ መንግሥት ይሸፍናል፡፡
☞✞ዮሐንስ በራእዩ “እንስሶቹም በዙፋን ላይ ለተቀመጠው ከዘላለምም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው ለርሱ ክብርና ውዳሴ ምስጋናም በሰጡት
ጊዜ ኻያ አራቱ ሊቃናት በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ ጌታችንና አምላካችን ሆይ አንተ ኹሉን ፈጥረኻልና ስለ ፈቃድኽም ኾነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኀይልም ልትቀበል ይገባኻል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ” በማለት እንደተናገረ ኪሩቤል በቀኝ ሱራፌል በግራ ካህናተ ሰማይ ዝቅ ብለው ክንፍ ለክንፍ ገጥመው ቁመው አምላካቸውን ያመሰግናሉ (ራእ ፰፥፱-፲፩)፡፡
☞✞ቅዱስ ዮሐንስም በራእዩ የቅዱሳንን ጸሎት መልአኩ በወርቅ ማዕጠንቱ
በርሱ እጅ ወደ እግዚአብሔር ፊት እንዳወጣው በምእ ፰፥፫-፬ “ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ኹሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ” በማለት ምዕራገ ጸሎት የሚደረግባት የጥናዋን ምስጢር ገልጽዋል፡፡
☞✞በመኾኑም የቅዱሳኑ ኹሉ ጸሎት በመልአኩ እጅ በወርቅ ጥናዋ አማካይነት ቅድመ እግዚአብሔር እንደደረሰ ኹሉ በተመሳሳይ ፍሕመ መለኮትን ፱ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ በተሸከመች አማናዊት ማዕጠንት በኾነች በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የጸለይነው ጸሎት ኹሉ እውነተኛ ፈራጅ ወደኾነው ወደ አምላካችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚቀርብ ነውና ሊቃውንት ቅድስት
ድንግል ማርያምን ዮሐንስ ባያት በመላእክት እጅ በተያዘች የወርቅ ማዕጠንት መስለዋታል፡፡
☞✞ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ከዚኽ ተነሥቶ በአንቀጸ ብርሃን መጽሐፉ ላይ፦
“ናስተማስለኪ ኦ እግዝእትነ በማዕጠንት ዘወርቅ ዘውስተ እደዊሆሙ ለሊቃነ
ካህናት ሰማያውያን እለ ይከውኑ ጸሎተ ኲሎሙ ቅዱሳን ወመሃይምናን እምዲበ
ምድር በውስተ ማዕጠንቶሙ ከማሁ በስእለተ ስምኪ ያዐርጉ ስእለቶሙ ለደቂቀ ዕጓለ እመ ሕያው ውስተ ማኅደረ ሥሉስ ቅዱስ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ወታስተስርዪ ኀጢአተ ሕዝብኪ ተበውሐ ለኪ እምአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ከመ ትኩኒ ተንከተመ ለውሉደ ሰብእ ለሕይወት ዘለዓለም”
☞✞(እመቤታችን ሆይ የቅዱሳንና የምእመናንን ኹሉ ጸሎት በማዕጠንታቸው ከምድር ወደ ሰማይ በሚያሳርጉ በሰማያውያን የካህናት አለቆች እጆች ውስጥ ባለ የወርቅ ማዕጠንት እንመስልሻለን፤ እንዲኹም ስምሽን በመጥራት የሰው ልጆችን ልመና ወደ ልዩ ሦስት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያሳርጋሉ፤ የወገኖችሽን ኀጢአት ታስተሰርዪ ዘንድ ከአብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ተፈቅዶልሻል፤ ለሰው
ልጆች የዘላላም ሕይወት ድልድይ ትኾኚ ዘንድ) በማለት በምልጃዋ በተሰጣት
ቃል ኪዳን ጸሎታችንን ኹሉ ወደ ሥላሴ የምታደርስልን አማናዊት ማዕጠንትነቷን
መስክሯል፡፡
☞✞ከሊቃውንት ውስጥ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ ማዕጠንተ ሱራፊነቷን ሲገልጹ፦
☞✞“ዐቢይ ውእቱ ተአምር ጸግዮትኪ በድንጋሌ ወፈርዮትኪ በንጽሕ ቊርባነ አምልኮ መጥለሌ ማዕጠንተ ሱራፊ ዘወርቅ ወጽዋዐ ኪሩብ ዕንቈ ቢረሌ
አልቦ ጸሎት ወአልቦ ትንባሌ እንበሌኪ ማርያም ዘየዐርግ ሉዓሌ” (በድንግልና መፅነስሽ በንጽሕናም የሚያለመልም የአምልኮ ቊርባንን መውለድሽ ታላቅ ድንቅ ተአምር ነው፤ የሱራፊ የወርቅ ማዕጠንት ቢረሌ የሚባል የኪሩብ የዕንቊ ጽዋ ማርያም ያላንቺ ወደላይ ወደ ፈጣሪ የሚያርግ ልመናም ምልጃም የለም) በማለት በርሷ ምልጃ እውነተኛ ፈራጅ የኾነው ልጇ ልመናችንን የሚቀበልልን እውነተኛዋ የሱራፊ ማዕጠንት መኾኗን ሲመሰክሩ፤
☞✞ዳግመኛም በዚኹ መጽሐፋቸው ላይ፦ “ከመ ጼና ልብስኪ ወጼና አንፍኪ ወመዐዛ አፉኪ ቦኑ እምነ ጽጌያት ዘገነት ዘበውስተ ገዳም ይጼኑ ተአምረ ቊርባን ማርያም ለኪሩብ ጢሰ ዕጣኑ ማየ ልብንኑ ሰሊኆትኑ መዐዛ ዚኣኪ ዘይመስል መኑ” (እንደ ልብስሽ እንደ አፍንጫሽ እንደ አፍሽ መዐዛ በገነት በበረሓ ከአሉት አበባዎች እንደዚያ የሚኾን አለን? የለም፤ ኪሩብ የሚያቀርባት የዕጣን ጢስ ማርያም፤ የነጭ ዕጣን ልባንጃ ውሃ ነውን? ወይስ ሰሊኆት የተባለ ሽቱ? የአንቺን መዐዛ የሚመስል ማንኛው ነው?) በማለት የመዐዛ ንጽሕናዋን ነገር መዐዛቸው
በሚያስደንቅ ነገራት በመመሰል “ኪሩብ የሚያቀርባት የዕጣን ጢስ ማርያም”
በማለት የምልጃዋን ነገር አስተምረዋል፡፡
"ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ"
🙏ምዕራገ ጸሎት ማዕጠንተ ሱራፊ ድንግል ሆይ ጸሎታችንን ኹሉ ወደ ልጅሽ
መንበር አሳርጊልን፡፡🙏
4 374
#የአምላክ_እናት_ውበት_በቅዱስ_ቴዎዶጦስና_በቅዱስ_ፕሮክልዩስ
☞✞ሰላምታ የተገባሽ ምልእተ ጸጋ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና፤ አንቺ
የተባረክሽ ነሽ (ሉቃ ፩፥፳፰)፤ ከሴቶች ኹሉ በእጅጉ የተዋብሽና በጣሙኑ
የተቀደስሽ ነሽ፤ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው፤ ከኹሉም በላይ ቅድስት የኾንሽ
ሆይ የተከበርሽና መልካም ነሽ፤ ጌታ ከአንቺ ጋር የኾነ ውዳሴ የተገባሽ ሆይ
ተወዳዳሪ የለሽም፣ ከሞገስ በላይ የኾንሽ ሆይ ኹሉ የተትረፈረፈልሽ
እግዚአብሔር ያከበረሽ ነሽና ምስጋና ኹሉ ይገባሻል (ሉቃ ፩፥፵፱)፨
☞✞የእግዚአብሔር ማደሪያው፤ መለኮት የጠበቀሽ የተከባከበሽ ሀብት ነሽ፤
በአንቺም ውስጥ በኀጢአት ውስጥ መፅነስን ወይም በኀጢአት ውስጥ
መውለድን በጭራሽ አላውጅም፤ በዚኽ ፈንታ የሔዋንን ሐዘን እንዲበቃ ያደረገው
ደስታን አምጥቼያለኊ እንጂ፤ በአንቺ የመከራ ፅንስን ወይም ሕማመ ወሊድን
ፈጽሞ አላውጅም፨
☞✞ንጽሕት፣ ድንግል፣ ነውር የሌለባት፣ ያለነቀፋ የኾነች፣ ምንም ያልነካት፣
ሕጸጽ የማይገኝባት በሥጋም በነፍስም ቅድስት፣ በእሾኽ መኻከል እንደበቀለች
የሱፍ አበባ ናት (መሓ ፪፥፩)፤ የሔዋንን ክፋት የማታውቅ፣ የሴትነት የፈቲው
ጠባይ ያልታየባት፣ ከመፅነሷ በፊት ለፈጣሪ የተለየች፣ የቤተ መቅደስ እንግዳ፣የሕግ ደቀ መዝሙር የኾነች፣ በመንፈስ ቅዱስ የተቀባች፣ የመለኮትን ጸጋ እንደ ልብስ የተጎናጸፈች ናት” [ቅዱስ ቴዎዶጦስ (†፫፻፫ (303) ዓ.ም]
“ያለ ስሕተት ከርሷ ተገኘ፤ ርሷንም ያለነውር እንድትኾን አደረጋት፤
እንዲኹም ማርያም የዐዲስ ፍጥረት ሰማያዊ ምልክት ምሕዋርን ኾነች፤
በዚኽም ምሕዋር የጽድቅ ፀሓይ ለዘላለም ያበራል፤ ርሷንም የኀጢአት ጨለማ ፈጽሞ አላያትም፨
ከእግዚአብሔር እናት የምትበልጥ ታገኝ እንደኾን ሰው ሆይ ፍጥረቱን ኹሉ
በሐሳብኽ ዞረኽ እይ፤ ዓለምንና ውቅያኖሶችን ኹሉ ዙር፤ አየሩን ኹሉ መርምር፤ ሰማያትን ጠይቅ፤ የማይታዩትን ኀይላት ኹሉ ዐስብ፤ በድንቅ የሚመስላት ካገኘኽ መርምር ርሷ ብቻ ከቃላት በላይ የኾነች መንገድ ናት፤ መርዓዊ ሰማያዊ ባለበት በሠርግ አዳራሽ በማሕፀኗ ውስጥ ፍጥረት ኹሉ በፊቱ በመፍራትና
በመንቀጥቀጥ የሚንበረከኩለትን ያሳደረች ናት”(ፕሮክልዩስ ዘቁስጥንጥንያ (†፬፻፵፮ (446)።
ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
•✞ የአምላክ እናት ሆይ እንወድሻለን ዘመናችንን ሁሉ ባርኪልን አሜን ✞•
4 374
#እንደ_አናንያ
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
•••
✔ለምሳሌ አንድ አሣ አስጋሪ ሰው መርምህናም ( ማር ምህናም፤ ቅዱስ ምህናም ማለት ነው) እርዳኝ እያለ ሲጠራ ‹‹ወበጊዜሃ መጽአ ኅቡረ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወቅዱስ መርምሕናም ተፅኢኖሙ ዲበ አፍራሲሆሙ...›› ተብሎ እንደተገለጸው ቅዱስ ጊዮርጊስም አብሮ ተገልጾ እንደረዱት የሚነግር ተአምር በገድለ ጊዮርጊስ ተአምሩ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ግን በዋናነት ሊገለጽ የሚችለው በገድለ መርምሕናም እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡ ስለዚህ በቅዱሳን ዘንድ አንዱ ብቻ ነው እንጂ ሌሎቹ የሉም የሚያስብል ታሪክም ድርጊትም የለም፤ ሊኖርም አይችልም፡፡ ልዩነት ያለ የሚመስለን መገለጦችን የምንረዳበት ሒደት አነስተኛ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
✔ይህ ከሆነ ታዲያ በሠለስቱ ደቂቅ የድኅነት ታሪክ ውስጥ ቅዱስ ገብርኤል ጎልቶ ለምን ይወጣል? በዓል ሆኖ የሚከበረው ለቅዱስ ገብርኤል፤ በሥዕልም ላይ አራተኛው ተብሎ በናቡከደነጾር የተገለጸው ሰው የቅዱስ ገብርኤል ሥዕል ሆኖ የሚሣለው ለምንድን ነው?
✔ይህም የሆነበት ምክንያት ዝም ብሎ ወይም በአጋጣሚ አይደለም፡፡
እግዚአብሔር ሥጋዌውን አስቀድሞ የገለጸው መላእክትንም በሰው አምሳል እንዲገለጹ በማድረግም ጭምር ነው፡፡ ለምሳሌ ለሙሴ መጀመሪያ የተገለጠለት በዚሁ መንገድ ነበረ፡፡ ‹‹የእግዚአብሔርም መልአክ በእሳት ነበልባል በእሾህ ቍጥቋጦ መካከል ታየው እነሆም ቍጥቋጦው በእሳት ሲነድድ ቍጥቋጦውም ሳይቃጠል አየ›› / ዘጸ 3፤2/ ተብሎ ተጽፏልና፡፡ ይህም ግን ነገረ ተዋሕዶን የሚስረዳ
የምስጢረ ሥጋዌ መገለጥ ነው፡፡
እግዚአብሔር ራሱን በመላእክት አምሳል ሲገልጥ ደግሞ ቅድሚያውን ስፍራ የሚይዘው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ምክንያቱም ገብርኤል ማለት
ቃለ እግዚአብሔር እንዲሁም ሰውና አምላክ ማለት ስለሆነ ነው፡፡ እመቤታችንን ሊያበስር የተላከውም በዚሁ ምክንያት ነው፡፡
✔ስለዚህ እግዚአብሔር ለናቡከደነጾር ሥጋዌውን ‹‹ አራተኛ ሰው አያለሁ››
እስኪል ድረስ ሰውነቱን በመገለጥ ያሳየው ከሦስቱ ሊቃነ መላእክት
ይህን ምስጢር በስሙም በተልእኮም ቅዱስ ገብርኤል የተሸከመው በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህም ሦስቱም ሊቃነ መላእክት በጠባቂ መላእክትነታቸውና ረቂቃን ኃይላት በመሆናቸው ቢኖሩም እግዚአብሔር ሊገልጠው ለፈለገው ታላቅ ምስጢር ተስማሚ የሆነውን (ራሱ ገብርኤል መሆኑ ትርጉምና መልእክት ያለው ነውና) መልአክ በአምሳ ወሬዛ ኀየል ወይም የነገሥታትን ልጅ በሚመስል መንገድ የንጉሠ ሰማይ ወምድር የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ ምሳሌ ሆኖ እንዲገለጽለት አደረገ፡፡
በዓሉ ለእርሱ የተሠጠውና ሥዕሉ የእርሱ የሆነበት ምክንያትም ይኸው ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም ቅድሰት ተዋሕዶ ይህን ሁሉ ምስጢር እንዲህ ባለ ታላቅ ሥርዓተ በዓል እንዲከበር በሥዕልም እንዲታይ በማደረግ ነገረ ሠጋዌውንም የሕጻናቱን ተጋድሎም የመላእክቱንም ጠባቂነት ስትገልጽበትና ስታስረዳበት ትኖራለች፡፡
✔መጽሐፍ ቅዱስን በምልዓት መረዳት ያለው በእውነተኛው የሐዋርያትና የሊቃውንት ትምህርት ትውፊትና ሥርዓተ አምልኮ ጸንታ በምትኖረው ቅድስት ተዋሕዶ ነው፡፡
የሊቀ መላዕክት የቅዱስ ገብርኤል፡የቅዱሳን መላእክት ጥበቃና ልመና ረድኤትና በረከት አይለየን።
••• ተፈፀመ •••
4 374
••• በእያንዳንዱ ነገራችንና ፈተናችን ላይ ወደ እግዚአብሔር እያመለከቱ የሚጠብቁን የሚያድኑን የሚያስፈርዱልን ወይም የሚያስፈርዱብንም እነርሱ ናቸውና፡፡
✔እንደናቡከደነጾር ያለውን አስፈርደውበት አውሬ አድርገው ሣር
ያስግጡታል፤ እርሱም ራሱ አንድ ቅዱስ ጠባቂ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ ብሎ አሁንም አረጋግጧል /ዳን 4 ፤13/፡፡ እንደ ሔሮድስ ያለውን ደግሞ ‹‹ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያን ጊዜ የጌታ መልአክ መታው በትልም ተበልቶ ሞተ›› /ሐዋ 12 ፤23/ ተብሎ እንደተጻፈው አስፈርደው ይቀስፉታል፡፡ እንደ ዳንኤል፤ ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ዮሴፍ፣
ሠለስቱ ደቂቅ ያሉትን ደግሞ ያድኗቸዋል፡፡ ‹‹... እርሱ ከአዳኝ
ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና። በላባዎቹ ይጋርድሃል፥
በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል። ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥ በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም። በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ ወደ አንተ ግን አይቀርብም። በዓይኖችህ ብቻ
ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ብድራት ታያለህ። አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ። ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም። በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ
እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል። ... ›› /መዝ 90 / ተብሎ ተጽፏልና፡፡
✔ጠባቂ መላእክቶቻቸው የሚያድኗቸው ቢሆንም በራእዩ የታየው አንድ ሆኖ ሳለ ሦስቱ ተደርገው በሦስት ድርሳናት ለምን ተገለጸ የሚል ጥያቄም ልናነሣ እንችላለን፡፡ እንዲህ ያሉትን ምስጢራት መረዳት የምንችለው በቅዱሳት መጻሕፍት ያሉትን ተመሳሳይ ታሪኮችና ይህ የሚሆንበትን ምክንያት ስናውቅ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል የጌታችንን ትንሣኤ አስመልክቶ አራቱም ወንጌላውያን
መዝግበውልናል፡፡ አራቱም የመዘገቡበት መንገድ ግን ተቃርኖ ባይኖረውም ልዩነት አለው፡፡ አበይት ልዩነቶቹ ሦስት ነገሮች ላይ ናቸው፡፡ የተገለጹት መላእክት ቁጥር ላይ፤ የመጡት ሴቶች ማንነትና ሴቶቹ የመጡበትን ሰዓት በተመለከተ የአዘጋገብ ልዩነት አለ፡፡ ለዛሬው
ለጉዳያችን ቅርበት ያለው የመላእክቱ ብዛት ላይ እናተኩር፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ ‹‹እነሆም፥ የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ። መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ። ጠባቆቹም እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ እንደ ሞቱም ሆኑ። መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው። እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ
አውቃለሁና፤ እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ። ፈጥናችሁም ሂዱና። ከሙታን ተነሣ፥ እነሆም፥ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል በዚያም ታዩታላችሁ ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሩአቸው /ማቴ 28 ፤2-7/ ሲል ይገልጻል፡፡
✔ማርቆስ ደግሞ ‹‹ወደ መቃብሩም ገብተው ነጭ ልብስ የተጎናጸፈ ጎልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ፤ ...›› /ማር 16 ፤5/ ይላል፡፡
✔ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ ‹‹እነርሱም በዚህ ሲያመነቱ፥ እነሆ፥ ሁለት ሰዎች የሚያንጸባርቅ ልብስ ለብሰው ወደ እነርሱ ቀረቡ ›› /ሉቃ 24 ፤4/ ይለናል፡፡
✔ቅዱስ ዮሐንስም ብዙ ነገር ስለ ትንሣኤው ካተተ በኋላ ‹‹ ማርያም ግን እያለቀሰች ከመቃብሩ በስተ ውጭ ቆማ ነበር። ስታለቅስም ወደ መቃብር ዝቅ ብላ ተመለከተች፤ ሁለት መላእክትም ነጭ ልብስ ለብሰው የኢየሱስ ሥጋ ተኝቶበት በነበረው አንዱ በራስጌ ሌላውም
በእግርጌ ተቀምጠው አየች /ዮሐ 20 ፤ 11-12/ ሲል መዝግቦልናል፡፡
✔እነዚህን አገላለጾች ስናያቸው የአዘጋገብ ልዩነት ቢታይባቸውም ቅራኔና የእውነታ ልዩነት ግን የላቸውም፡፡ ማቴዎስና ማርቆስ ስለ አንድ መልአክ
ማነጋገር ቢገልጹም ሌላ መልአክ እንዳልነበረ ግን አላመለከቱም፡፡ እንዲያውም ማቴዎስና ማርቆስ የመዘገቡልን ስለ አንድ መልአክ ይሁን
እንጂ ሁለቱም የመዘገቡት ግን ስለተለያዩ መላእክት ነው፡፡ ማቴዎስ ከመቃብሩ ወጭ ድንጋዩን አንከባሎ ስለተቀመጠው ዘግቦ ከመቃብሩ ውስጥ በቀኝ በኩል (በራስጌ ወይም በግርጌ) ስላለው አልመዘገበም፡፡ ማርቆስ ደግሞ ውስጥ ከገቡ በኋላ ስላለው መዝግቦ በውጭ በኩል ስላለው ወይም የመቃብሩ ድንጋይ ላይ ስላለው አልመዘገበም፡፡ ሁለቱም ግን ሌላውን መልአክ አልነበረም አላሉም፤ ‹‹የለም›› በሚያሰኝ መንገድም አልገለጹም፡፡ ሉቃስና ዮሐንስ ደግሞ ሁለቱንም መኖራቸውንና በግርጌና በራስጌ መሆናቸውን ገለጹልን፡፡ ስለዚህ
ሁሉም ትክክል ናቸው፡፡ የተለያዩና የማይቃረኑ የተባለው ለዚህ ነው፡፡
ይህም ቢሆን በተዘገበው መንገድ ስለተገለጹት መላእክት ይናገራል
እንጂ በትንሣኤው ዕለት ስለነበሩት መላእክት አጠቃልሎና ዘግቶ
አይናገርም፡፡ የነበሩትን መላእክትም ሁለት ብቻ ነበሩ ማለት ፍጹም
ስሕተት ላይ ይጥላል፡፡
✔ወንጌላውያኑ በዚህ በመላእክቱም ቁጥር ሆነ በሌሎቹ ጉዳዮች
የተለያዩትስ ለምንድን ነው ስንል ደግሞ አንድ መሠረታዊ መልእክት እናገኛለን፡፡ ይኸውም ስለመላእክቱ የተለያየ ዓይነት መገለጥ የገለጹት ለተለያዩ ሰዎች በትንንሽ የጊዜ ልዩነት የታየውን መገለጥና ለአንዳንዶችም በተቀራራቢ ግን በተለያየ ጊዜ የተገለጠውን
ስለመዘገቡ ነው፡፡ ለምሳሌ ቅዱስ ዮሐንስ መቅደላዊት ማርያም መመላለሷ ከማሳየቱም በላይ ለእርሷ የተደረገውን የአንድ ጊዜ መገለጥ ብቻ ነው የነገረን፡፡
ሉቃስ ደግሞ ለሌሎች ሴቶች የተደረገውን (ምክንያቱም ተመላልሰው
ያዩም አንድ ጊዜም ያዩ አሉ፤ ብዙ ታሪኮች በውስጡ አሉና) እያሉ ከነጊዜው ስለመዘገቡ እንጂ አንዱን ነጠላ ድርጊት ለያይተውና አሳሰተው መዝግበው አይደለም፡፡ በዚህ መሠረት ቀስ ብሎና በዚህ ጽሑፍ መጀመሪያ ክፍል ላይ እንዳየነው ከመንፈስ ቅዱስ መገለጥ
ተሰጥቷቸውና በጊዜው የነበረውን እውነተኛውን ትውፊት ከሐዋርያትና
ከነበሩት ሰምተው ከተረጎሙት ሳይረዳ ልክ እንደዚያ ርኩሳን እንደተባሉት እንስሳት ሳያመሰኳ ወይም እውነታውን ሳይቆነጥጥ ወይም እንደ አሳዎቹ ሐዋርያት የእምነት መከላከያ ጋሸ (ቅርፊት) እና ምስጢራትን የሚረዳበት ክንፈ ጸጋ ሳይኖረው በአመክንዮ (ሎጂክ) ብቻ እረዳለሁም አስረዳለሁም ቢል ይሳሳታል፡፡
✔ስለዚህ የሠለስቱ ደቂቅ ድኅነትን በተመለከተ በድርሳነ ገብርኤል ላይ
ገብርኤል ተብሎ በድርሳነ ሚካኤል ላይ ሚካኤል ተብሎና በድርሳነ ሩፋኤል ላይ ሩፋኤል ተብሎ መገለጹ ከላይ በወንጌል እንዳየነው ያለ ትውፊቱን ለያይቶ መዘገብ እንጂ ተቃራኒ ነገር አይደለም፡፡በዚሁ መሠረት ሦስቱን ሕጻናት አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤልንም ያዳኗቸው ጠባቂ
መላአክቶቻቸው ናቸው፡፡ እነዚህም ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ሩፋኤል ናቸው፡፡ ልክ ሥላሴ ለአብርሃም በተገለጹለት መንገድ ሦስት ሆነው ከሦስቱ ጀርባ ቆመው መታየት ነበረባቸው ካላልን በቀር ከጥንት ጀምሮ በተላለፈው ትውፊት ሦስቱ መላእክት የሦስቱ ሕጻናት ጠባቂ መላእክት ነበሩ፡፡ እንኳን ሰዎቹ ሦስት ሆነው ይቅርና አንድም ሰው ቢሆን ሦስትና ከዚያ በላይ መላእክት ሊገኙ ይችላሉ፡፡ ዮናታን ወልደ ሳዖል ‹‹በብዙ ወይም በጥቂት ማዳን እግዚአብሔርን አያስቸግረውምና›› /1ኛ ሳሙ 14 ፤ 6/ እንዳለው በአንድም በብዙ ማዳንም የእግዚአብሔር ፈቃድና ምስጢር እንጂ የማነስና የመብዛት
ጉዳይ አይደለም፡፡ እንዲህ ያለው ነገር እንኳን በመላእክት ቃል ኪዳን ተቀብለው በሚያማልዱና በሚያድኑ ሰማዕታትና ቅዱሳንም ታሪክ ላይ በተደጋጋሚ የተገለጸ መሆኑን ከተለያዩ ገድላት መረዳት ይቻላል፡፡
••• #ይቀጥላል •••
4 374
#ሠለቱ_ደቂቅን_ያዳናቸው_ማን_ነው?
❖በድርሳነ ገብርኤል ላይ ገብርኤል ተብሎ በድርሳነ ሚካኤል ላይ ሚካኤል ተብሎና በድርሳነ ሩፋኤል ላይ ሩፋኤል ተብሎ መገለጹ ምሥጢሩ ምን ይሆን?
“ታዲያ ሠለስቱ ደቂቅን ያወጣቸው ማን ነው?” ለሚለው የተሐድሶዎች ጥያቄ በመ/ር ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ የተሰጠ መልስ፦
✔መጀመሪውንም መጽሐፍ ቅዱሱ ገብርኤል ነው አይልም፡፡ መጽሐፍ ቅዱሱ የሚለው የሚከተለውን ነው፤
‹‹የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ አማካሪዎቹንም፤ ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን? ብሎ ተናገራቸው። እነርሱም፦ ንጉሥ ሆይ፥ እውነት ነው ብለው ለንጉሡ መለሱለት። እርሱም፦ እነሆ፥ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል ብሎ መለሰ›› /ዳን 3 ፤ 24 -25/ ፡፡
✔በዚህ ገለጻ መሠረት አራተኛውን ያየው ንጉሡ ናቡከደነጾር ነው፡፡
እርሱም አየሁ ያለው አራተኛ ሰው ነው፡፡ የጨመረበት ቢኖር አራተኛው የአማልክትን ልጅ ይመስላል የሚለውን ነው፡፡ ለመሆኑ አራተኛውን ሰው እርሱ ብቻ ለምን አየ? ሌሎቹ ለምን አላዩም? አንደኛው የጥያቄው ቁልፍ ምስጢር ያለው እዚህ ላይ ነው።
✔እውነቱን ለመናገር ይህ ሰው ጥንቱንም ሠለስቱ ደቂቅን ወደ እሣት
የጣለው ራሱን ምስል አቁሞ ለምስሉ ሕዝቡን በማሰገድ ራሱን አምላክ አድርጎ ሊያስመልክ ነበር፡፡ ታዲያ ራሱንና እርሱን የመሰሉትን አምላክ አድርጎ የሚቆጥር ከሆነ የሚያየውን አራተኛውን ሰው ‹‹የእኛን ልጅ ይመስላል ወይም እኛን ይመስላል›› ለምን አላለም? ከዚያ ይልቅ አርቆ ሌሎች አማልክትን የሚያመልክ አስመስሎ ‹‹የአማልክትን ልጅ›› ይመስላል ያለበት ምስጢር ምንድን ነው? ይህን ያለበት ምክንያቱ ያየው ነገር አራተኛው አካል ከህልውና ያለው በዘር በሩካቤ የተወለደ ሰው እነርሱ ሳያዩት እሳቱ ውስጥ ገብቶ ሳይሆን ነገሩ መገለጥ ስለሆነ ነው፡፡
✔በብሉይ ኪዳን ከተገለጹት ታላላቅ ሦስት የእግዚአብሔር መገለጦች
ውስጥ አንዱ ይህ የሠለስቱ ደቂቅ የድኅነት ታሪክ ነው፡፡ ➊አንደኛው በመምሬ የአድባር ዛፍ ሥር እግዚአብሔር ለአብርሃም በሦስት ሰዎች አምሳል የተገለጠው መገለጥ ነው / ዘፍ 18/፡፡ ➋ሁለተኛው ደግሞ አሁንም እግዚአብሔር ለአባታችን ለያዕቆብ
በጎልማሳ አምሳል ተገልጾ ሲታገለው ያደረበት ታሪክና ያዕቆብንም መጀመሪያ ‹‹ካልባረከኝ አልለቅህም›› ከተባረከ በኋላም ‹‹እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሰውነቴም ድና ቀረች ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል ብሎ ጠራው›› /ዘፍ 32 ፤ 25 - 32/ ያሰኘው መገለጥ ነው፡፡ ➌ሦስተኛው ይህ ለባቢሎኑ አላዊ ንጉሥ ሠለስቱ ደቂቅን ወደ እቶን እሳት በጣለበት ወቅት ያደረገው መገለጥ ነው፡፡
✔ሦስቱም መገለጦች የሚያመሳስሏቸው ሁለት ጠባያት አሏቸው፡፡ የመጀመሪያው በሦስቱም ጊዜ እግዚአብሔር በሰው መልክና አምሳል መገለጡ ሲሆን ሁለተኛውና ዋናው ደግሞ ቃለ እግዚአብሔር በሥጋዌ (ሰው በመሆን) ተገልጦ ለሰው ፍጹም ድኅነት የሚሰጥ መሆኑን አስቀድሞ በምሳሌ መግለጽ ነው፡፡ መሠረታዊ መልእክቱ ደግሞ አምላክ ሰው ከሆነ በኋላ የሚያድነው የተስፋውን ዘር እሥራኤልን ብቻ ሳይሆን አሕዛብንም ጭምር መሆኑን ለማሳየትና አሕዛብም የሥጋዌው ነገር ቀድሞ የተገለጸው ለእሥራኤል ብቻ ስለሆነ እኛ ልናምንበት
አይገባም እንዳይሉ ለዚህ ደንዳናና ጫካኝ ናቡከደነጾርም ጭምር ገለጸለት፡፡ የእነ ነነዌ ታሪክም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሆኖ የተቀመጠውና
እግዚአብሔር ለአሕዛብም ድኅነት ይፈጽም እንደነበር የተዘገበው
እግዚአብሔር የእሥራኤል ብቻ ሳይሆን የሁሉም አምላክ የነበረ መሆኑን ራሱ ብሉይ ኪዳንም ምስክር እንዲሆን ነው፡፡ እነዚህን የመሰሉ ሌሎች ታሪኮችና ምሳሌዎችም በብዛት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ፡፡ ስለዚህ የዚህ በሠለስቱ ደቂቅ ድኅነት ውስጥ የታየው መገለጥ ዋናው ምስጢሩና መልእክቱም የአካላዊ ቃልን ሰው ሆኖ መገለጥና አዳኝ
መሆኑንን በሐዲስ ኪዳንም እንደ ሠለስቱ ደቂቅ እሳትና ስለት፣ ሰይፍና ጎራዴ፤ እስራትና ግርፋት የሚቀበሉትን ሰማዕታት ሁሉ የሚያድናቸው እርሱ መሆኑን መግለጽ ነው፡፡
✔ታዲያ ዋናው መልእክቱና ምስጢሩ ይህ ከሆነ ገብርኤልም ሆነ ሌሎቹ
መላእክት ለምን አዳኑ ይባላሉ? በቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት
መሠረት ለሰዎች ከጊዜያዊና ምድራዊ አደጋና ሰዎች ከሚያመጡባቸው መከራ ድኅነት ሲደረግላቸው ድኅነታቸውን
የሚፈጽሙላቸው ቅዱሳን መላእክት ማለትም ጠባቂ መላእክቶቻቸው
ናቸው፡፡ ምንም አንኳ ይህ መሆኑን አንዳንድ ጊዜ በግልጽ አንዳንድ
ጊዜ ደግሞ በምስጢር ቢገለጽም የእግዚአብሔር መላእክት
ከሚጠብቋቸው ሰዎች ተለይተው አያውቁም፡፡ ለምሳሌ በሐዋርያት ሥራ ላይ ቅዱስ ያዕቆብን ያስገደለው ሔሮድስ ቅዱስ ጴጥሮስንም ለመግደል ባሰረው ጊዜ በዚያ ወቅት ሊሞት እግዚአብሔር ስላልፈቀደ መልአኩ እንዲያድነው አድርጓል፡፡ ‹‹እነሆም፥ የጌታ መልአክ ቀረበ በቤትም ውስጥ ብርሃን በራ፤ ጴጥሮስንም ጎድኑን መትቶ አነቃውና። ፈጥነህ ተነሣ አለው።
ሰንሰለቶቹም ከእጁ ወደቁ። መልአኩም። ታጠቅና ጫማህን አግባ አለው፥ እንዲሁም አደረገ። ልብስህንም ልበስና ተከተለኝ አለው። ወጥቶም ተከተለው፤ ራእይንም የሚያይ ይመስለው ነበር እንጂ በመልአኩ የሚደረገው ነገር እውነት እንደ ሆነ አላወቀም።
የመጀመሪያውንና የሁለተኛውንም ዘብ አልፈው ወደ ከተማ ወደሚያወጣው ወደ ብረቱ መዝጊያ ደረሱ፤ እርሱም አውቆ ተከፈተላቸው፤ ወጥተውም አንዲት ስላች አለፉ ወዲያውም መልአኩ ከእርሱ ተለየ። ጴጥሮስም ወደ ልቡ ተመልሶ፦ ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንደ አዳነኝ አሁን በእውነት አወቅሁ አለ /ሐዋ 12፤ 7 -11/ ተብሎ እንደተጻፈ ሙት ላነሣውና ስንት ተአምራት ላደረገው ቅዱስ ጴጥሮስ አሁን ግን ይህን ሁሉ የሚያደርግለት መልአኩ ነው፡፡ ይህ መልአክ የቅዱስ ጴጥሮስ ጠባቂ መልአክ እንደሆነ ብዙ ሊቃውንት በትርጓሜያቸው አስተምረዋል፡፡
✔በዚሁ ታሪክ ላይ ‹‹ጴጥሮስም የደጁን መዝጊያ ባንኳኳ ጊዜ ሮዴ የሚሉአት አንዲት ገረድ ትሰማ ዘንድ ቀረበች፤ የጴጥሮስ ድምፅ መሆኑንም ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሣ ደጁን አልከፈተችም፥ ነገር ግን ወደ ውስጥ ሮጣ ጴጥሮስ በደጅ ፊት ቆሞ እንዳለ አወራች። እነርሱም፦ አብደሻል አሉኣት። እርስዋ ግን እንዲሁ እንደ ሆነ ታስረግጥ ነበር። እርሱም፦ መልአኩ ነው አሉ›› / 13-15 / ተብሎ እንደተጻፈው ውስጥ የነበሩት ጴጥሮስ አይሆንም ‹‹መልአኩ›› ነው ያሏት እርሱን ሊመስልሽ የሚችለው ጠባቂ መልአኩ ነው ለማለት ነበር፡፡ ይህም የሆነው በጥንት ክርስቲያኖች ዘንድ የጠባቂ መላእክት ጥበቃና መገለጥ በሰፊው ይታወቅ ስለነበረ ነው፡፡
✔በመጽሐፈ ጦቢትም ላይ ቅዱስ ሩፋኤል ሰው መስሎ ለጦብያና
ለቤተሰበው እንዲሁም ለራጉኤልና ለቤተሰቡ ቀድሞ ጸሎታቸውን
በማሳረግ በኋላም ከፈተናቸው በማዳንና ሕይወታቸውን በመባረክ ተገልጾ አይተነዋል፡፡
✔እነዚህ ሁለት ታሪኮች የሚያሰረዱን ጠባቂ መላእክት በድሕነታችን ውስጥ ትልቅ ስፋራ የሚሰጣቸውና በርግጥም እነርሱ የሌሉበት ድኅነት የሌለ መሆኑን ነው፤ ልዩነቱ በአንዳንዶቹ ታሪኮች ላይ መገለጣቸው በአንዳንዶቹ ላይ ደግሞ ተገልጠው ለሰው አለመታየታቸው ብቻ ነው፡፡
✔ጌታችንም በወንጌል ‹‹ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና›› /ማቴ 18 ፤10/ ያለው ስለ ጠባቂ መላዕክቶቻችን ነው፡፡
••• #ይቀጥላል•••
4 374
#ገብርኤል_ማን_ነው?
🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾
#ገብርኤል ማለት “ እግዚእ ወገብር” - የእግአብሔር አገልጋይ ማለት ነው።
ፍጥረታት መፈጠር በጀመሩበት በዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን
ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወራቸው መላእክትም “ መኑ ፈጠረነ፡ ማን ፈጠረን ” ሲሉ ዲያብሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሎ መላእክት በተረበሹ ጊዜ “ የፈጠረንን
አምላካችን እስክናውቅ በያለንበት ጸንተን እንቁም ” ብሎ ያረጋጋቸው መልአክ
ነው። በዚህም ምክንያት ጌታ “ በእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም ”
እንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል። ከዚህም በኋላ ደጋግ ሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድ ሆኗል።ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡
በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ በክርስቲያኖች ዘንድ ይወደዳል፡፡ ምክንያቱም ያዘኑትን ለማጽናናት የምሥራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን ይላካልና፡፡
#ይህ_ቅዱስ_ገብርኤል_ነው
ሳጥናኤል ሥላሴን በካደ ጊዜ መላእክትን በቃሉ ያጽናናቸው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ፤የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ
👉*ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡*
ዳንኤልን ከአናብስት ያዳነው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነቸው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ወደ ዘካርያስ የተላከ የዮሐንስን ልደት ያበሰረ
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ወደ ዮሴፍና ወደ ኒቆዲሞስ የተላከ
👉*ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡*
ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ሰብአ ሰገልን በኮከብ ምልክት የመራቸው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ድንግል ማርያምና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ
👉* ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
የብርሃን ራስ ወርቅ የተቀዳጀ
👉*ገብርኤል ነው፡፡*
የአሸናፊና የኃይል መልአክ
*ገብርኤል ነው፡፡*
ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ
*ገብርኤል ነው፡፡
🙏"የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃና ረድኤት አይለየን"🙏
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
#ታኅሣሥ_19
ዮሐንስ ኤጲስ ቆጶስ ወገብርኤል ሊቀ መላእክት፡፡
#ዘቅዳሴ
#2ኛ_ተሰሎ_1:6-ፍጻሜ፡ወርቱዕሰ ይትፈደዩ በኀበ እግዚአብሔር"መከራ የሚያጸኑባችሁ እነዚያ በእግዚአብሔር ዘንድ ፍዳቸውን ይቀበሉ ዘንድ ይገባል፡፡.................
.........................................................የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእናንተ ላይ ይከብር ዘንድ እናንተም በእርሱ ትከብሩ ዘንድ እንጸልያለን፡፡"
#ይሁዳ_1:20-ፍጻሜ፡ወአንትሙሰ አኃዊነ ሕንጹ"ወንድሞቻችን ሆይ እናንተ ግን በተቀደሰች ሃይማኖት ራሳችሁን እነጹ በመንፈስ ቅዱስም ጸልዩ፡፡....................................................................................................አሁንም እስከ ዘለዓለም ድረስ በጌታችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኀይልም ሥልጣንም ይሁን፡፡አሜን፡፡"
#የሐዋ_ሥራ_7:30-35፡ወተፈጺሞ 40 ዓመት"አርባ ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ በበረሃ በደብረ ሲና የእግዚአብሔር መልአክ በቁጥቋጦ መካከል በእሳት ነበልባል ታየው፡፡............................
........................................................በግብጽ ያሉትን የወገኖቼን መከራ ማየትን አይቻለሁ ጩኸታቸውንም ሰምቻለሁ ላድናቸውም ወርጃለሁ አሁንም ና ወደ ግብጽ ሀገር ልላክህ፡፡"
#ምስባክ
በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ
ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ
ወእገኒ ለስምከ፡፡
#ትርጉም
በመላእክት ፊት እዘምርልሃለሁ
ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ በስምህ ሁሉ፡፡
#መዝ_137:1-2
#ወንጌል
#ሉቃስ_1:11-21፡ወአስተርአዮ መልአከ እግዚአብሔር"የእግዚአብሔር መልአክም በዕጣን መሠውያው በስተቀኝ ቆሞ ታየው፡፡...................
........................................................አሁንም በጊዜው የሚሆነውንና የሚፈጽመውን ነገሬን አላመንኸኝምና ይህ እስኪሆን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ መናገርም ይሳንሃል፡፡"
#ቅዳሴ፡ዘእግዝእትነ፡፡(ጎሥዓ)
