cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ቅድሚያ ለተውሂድ ተውሂድ የነብያቶች ጥሩ ነው!!

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:– «የደስታ ሰዎች ብሎ ማለት እነዛ የተውሒድ ሰዎች ናቸው።» (مجموع فتاوى 18/56) ይሄ ቻናል የሰለፊያ ኡለሞች ሙሐደራ እና ደርስ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ። ,https://t.me/joinchat/AAAAAFG6nVbtrMK-0XJ3uw

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
235
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
-830 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ከዚክሮች ሁሉ በላጩ ቁርአን መቅራት ነዉ። «መቅራት ካልቻልክ በትኩረት አድምጥ!!»        = https://t.me/skatnYefelgeYeselfochnmengedYcet
نمایش همه...
AUD-20230506-WA0007.mp32.70 MB
📘 ማስታወቂያ ለእውቀት ፈላጊዎች 📌 እንደሚታወቀው ሁዘይፈቱል የማን የቁርአን ሂፍዝ እና የተርብያ ማዕከል ከነባር ተማሪዎች በተጨማሪ በበጋ በኦንላይን መርሃ ግብር ተመዝግበው በመርከዙ የሚሰጡትን ትምህርቶች ለመከታተል ለሚፈልጉ አድስ ተማሪዎች ምዝገባ ስለጀመርን የምንፈልገው ተማሪ ውስን ስለሆነ ቀድማችሁ እስከ መስከረም 1/2016 ዓ.ል ድረስ ትመዘገቡ ዘንድ ለመግለፅ እንወዳለን። 💻 በመርከዙ የሚሰጡ ትምህርቶች ➦ ቃዒደቱ ኑራንያ ለጀማሪዎች ተጨማሪ የድጋፍ ማጠናከሪያ ከመስጠት ጋር ➦ቁርአን በነዞር መቅራት ለሚፈልጉ ➦ ቁርአን በሂፍዝ መቅራት ለሚፈልጉ ➦ ለኪታብ ጀማሪዎች👇          በመጀመሪያ ጀረጃ በቅደም ተከተል         📚 መትን ኡሱሉ ሰላሰህ         📚 መትን ቀዋዒዱል አርበዓ              📚 መትን ነዋቂዱል ኢስላም         📚 መትን አቂደቱ አልዋሲጥያህ         📚 መትን አርበዒን አነወዊያህ         📚 መትን ሹሩጡ ሶላት                📮 ማስታወሻ ➊. ሒፍዝ ለመቅራት የምትመዘገቡ ተማሪዎች መጀመሪያ የተጅዊዳችሁ ሁኔታ ከታየ በኋላ ነው። ➋.ቁርአን በነዞር እና በሒፍዝ ለምትቀሩ ተማሪዎች ለተጅዊዳችሁ ማጠናከሪያነት ይረዳችው ዘንድ የተለያዩ የተጅዊድ ኪታቦች ጎን ለጎን ይሰጣሉ። ➌.የተጅዊድ ኪታቦቹ የሚሰጡበት ሰአት ቁርአን ከምቀሩበት ክፍለ ጊዜ ውጭ ነው። ➍.በመርከዙ የሚሰጡትን የቁርአን እና የቃዒደቱ ኑራንያህ ትምህርቶች ሳይሰላቹ በጥሩ ሁኔታ ተከታትለው ተከታታይ ፈተናቸውን ከ100% አመርቂ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች መርከዙ የምስክር ወረቀት ይሰጣል። ➎.ለኪታብ የምትመዘገቡ ተማሪዎች በምትቀሩት ኪታቦች ላይ እያንዳንዱ ፈስል (ክፍል) ከተጨረሰ በሗላ ፈተና ስለሚኖረው አስፈላጊውን ሙራጅአ ሳትሰላቹ የምታደርጉ ተማሪዎች መሆን አለባችሁ። ኪታቡ ሲጠናቀቅ መጨረሻ ላይ ውጤታችው ከ 100% ተደምሮ ይሰጣችሗል። 👁‍🗨 የሚመዘገቡ ተማሪዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርት ❶. ሰአት አክባሪ መሆን ❷. የሚሰጠውን ት/ት ሙራጅዓ ማድረግ ❸.ትምህርቱ በሚሰጥበት ማስታወሻ መያዝ ❹.ትምህርቱን ከጀመሩ ያለ ምክንያት አለማቋረጥ ❺.በፈተና ጊዜ ራስን ችሎ መስራት (አለመኮረዥ) 👁‍🗨 ትምህርቱ የሚሰጥባቸው ሚዲያዎች ❶. በቴሌግራም live Stream ❷.በ ZOOM Meeting ➦ይህንን መጠቀም ለማይችሉ ተማሪዎች ሌሎች ሁኔታዎች ይመቻቻሉ። ♦️ትምህርቱ የሚሰጥበት ሰአት ተማሪዎች ተመዝግበው ሲጨርሱ እንደሚመታቸው ወቅት ታይቶ ክፍለጊዜው ይወጣል። 👁‍🗨 ለመመዝገቢያ አድራሻዎች@Abu_Huzeyfah5@Abu_Tesnim5 👉 ወደ ቻናላችን ለመቀላቀል 👇 🌏t.me/Merkezhuzeyfetulyeman 👉 ወደ ግሩፓችን ለመቀላቀል 👇 🌏 t.me/Huzefetulyemanqurancenter
نمایش همه...
መርከዝ ሁዘይፈቱል የማን የቁርአን ሂፍዝ እና መሰረታዊ የሸሪዓ እውቀት ማዕከል ( GROUP)

🖊በዚህ ግሩፕ 👇 ➦የተጅዊድ ትምህርት ያላቸው ተከታታይ ፁሁፎች ➦ አጫጭር የተጅዊድ ኪታቦች ➦ የቁርአን የሀድስ እንድሁም የቀደምት ምክሮች ➦ የቁርአን ሀለቃ ትምህርቶች ➦ ተጅዊድን ለማወቅ አጋዥ የሆኑ የተለያዩ ቪድዮ እና ፎቶዎች ➦ ለተጅዊድ ጠቃሚ የሆኑ ጥያቄ እና መልሶቻቸው ➦ አጫጭር የቁርአን ቲላዋዎች ይለቀቁበታል። 📝 ለመመዝገብ @AbuHuzeyfah123_bot or @Abu_Huzeyfah5

🔀 የተጅዊድ ትምህርት ክፍል - ስምንት ⭕️ የኑን ሳኪና እና ተንዊን ህግጋቶች ❶) ኢዝሀር ➨ኢዝሀር ማለት በቋንቋ ደረጃ ግልፅ ማድረግ ማለት ሲሆን በተጅዊድ ምሁራኖች አገላለፅ ደግሞ ከኑን ሳኪና እና ተንዊን በኋላ የኢዝሀር ፊደላቶች በመምጣታቸው ምክንያት ኑን ሳካናዋን ወይም ተንዊኑን ያለ ጉና ግልፅ አድርጎ ማንበብ ማለት ነው። ➨ ለኑን ሳኪና እና ተንዊን የኢዝሃር ፊደላቶች ስድስት ሲሆኑ አጠቃላይ ከጉሮሮ የሚወጡ ፊደላቶች ናቸው። እነርሱም፦ أ ه ع ح غ خ ናቸው። ወይም 👇 أخي هَاكَ عِلماً حازَهُ غَيْرُ خَاسِرٍ በሚለው አረፍተ ነገር ውስጥ በቃሎቹ መጀመሪያ መጀመሪያ ላይ የሚገኙት ፊደላቶች ናቸው። ➨ እነዚህ የኢዝሀር ፊደላቶች እያንዳንዳቸው ከኑን ሱኩን ጋር በሚመጡ ጊዜ 12 ሁኔታዎች እና ከተንዊን ጋር በሚመጡበት ጊዜ 6 ሁኔታዎች በድምሩ 18 ሁኔታዎች አሏቸው። ➨ለዚህም ምክንያቱ በክፍል ሰባት ላይ ስለ ኑን ሱኩን እና ተንዊን ልዩነት ስናብራራ ከልዩነታቸው ውስጥ አንደኛው መለያቸው ኑን ሱኩን በቃል መካከል እና በቃ መጨረሻ ላይ መምጣት የምትችል ስትሆን ተንዊን ግን በቃል መጨረሻ ላይ ብቻ እንደምትመጣ አይተናል። ⭕️ ስለዚህ ኑን ሱኩን በቃል መካከል ላይ ስትመጣ ከስድስቱ የኢዝሀር ፊደላቶች ጋር 6 ሁኔታ ይኖራታል። ➙ምሳሌ፦ ኑን ሱኩን በቃል መካከል ከሀምዛ ጋር ስትመጣ👇 [ يَنأَوْنَ ] ⭕️በቃል መጨረሻ ላይ ስትመጣ ደግሞ ከስድስቱ የኢዝሀር ፊደላቶች ጋር አሁንም 6 ሁኔታ ይኖራታል። ➙ምሳሌ፦ ኑን ሱኩን ከሀምዛ ጋር በቃል መጨረሻ ላይ ስትመጣ👇 [مَن أَمَنَ ] በድምሩ ኑን ሱኩን ከኢዝሀር ፊደላቶች ጋር 12 ሁኔታዎች ይኖራታል ማለት ነው። ⭕️ በአንፃሩ ተንዊን ደግሞ በቃል መጨረሻ ላይ ብቻ ስለምትመጣ ከስድስቱ የኢዝሃር ፊደላቶች ጋር ሊኖራት የሚችለው 6 ሁኔታ ብቻ ነው። ➙ምሳሌ ፦ ተንዊን ከሀምዛ ጋር በቃል መጨረሻ ላይ ስትመጣ 👇 [ رَسُولٌ أَمِينٌ ] 🔷ስለዚህ በአጠቃላይ ኑን ሱኩን እና ተንዊን ከኢዝሀር ፊደላቶች ጋር (12+6) =18 ሁኔታዎች ይኖራቸዋል ማለት ነው። ማስታወሻ 🔷 በአጠቃላይ ኢዝሃር በአራት ይከፈላል። እነርሱም ፦ 1) ኢዝሃሩል ሀልቅይ 2) ኢዝሃር አሽ-ሸፈውይ 3) ኢዝሃሩል ቀመርይ 4) ኢዝሃሩል ሙጥለቅኢዝሃሩል ሀልቂይ ➦ በኑን ሳኪና ተንዊን ህግ ከኑን ሱኩን ወይም ከተንዊን በሗላ የሀልቅ (የጉሮሮ) ፊደላቶች በመምጣታቸው ምክንያት ኑንሳኪና እና ተንዊን ኢዝሃር (ግልፅ) ተደርገው ይነበባሉ። ◍ይህ አይነት ግልፅ ማድርግ ኢዝሃሩል ሀልቂይ ይባላል። ❷ ኢዝሃር አሽ-ሸፈውይ ➦ በሚም ሳኪና ህግ ከሚም ሱኩን በኋላ ከ ባ (ب) እና ከሚም (م) ፊደላቶች ውጭ ቀሪ 20 ስድስት ፊደላቶች ሲመጡ ሚም ሱኩንን በሸፈታን (በሁለት ከንፈሮች) ግልፅ አድርገን እናነባታለን። ◍ ይህ አይነት ግልፅ ማድረግ ኢዝሃር ሸፈውይ ይባላል። ❸ ኢዝሃር ቀመርይ ➦ ከላመል አል (ላመል መእሪፋህ) በሗላ የቀመርያ ፊደላቶች በሙምጣታቸው ምክንያት ላም ሱኩኗ ኢዝሀር (ግልፅ) ተደርጋ ትነበባለች። ◍ ይህ አይነት ግልፅ ማድረግ ኢዝሃር ቀመርይ ይባላል። ❹ ኢዝሃር ሙጥለቅ ➦ በኑን ሳኪና እና ተንዊን ህግ ኑን ሱኩን እና የኢድጋም ፊደላቶች የሆኑት ኑን (ن) እና ዋው (و) በአንድ ቃል ሲመጡ ኑን ሱኩኗ ኢዝሃር (ግልፅ) ተደርጋ ትነበባለች። ◍ ይህ አይነት ግልፅ ማድረግ ኢዝሃር ሙጥለቅ ይባላል። ይቀጥላል............. አንሻ አላህ ‼️ ✍️አቡ ሁዘይፋህ ኢብኑ ሙሃመድ ሰኔ 9 /2015 E.C ዙል ቀኢዳህ 27 /1444 H. ሰኔ 16 /2023  G.C ክፍል ሰባትን ለማግኘት 👇 https://t.me/Merkezhuzeyfetulyeman/294 🔀 ሌሎችም ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ሸር አድርጉት   👉 ወደ ቻናሉ ለመቀላቀል 👇 🌏https://t.me/Merkezhuzeyfetulyeman 👉 ወደ ግሩፑ ለመቀላቀል 👇 🌏https://t.me/Huzefetulyemanqurancenter 📝  ተመዝግባችሁ መማር የምትፈልጉ ካላችሁ በነዚህ አድራሻዎች አሳውቁኝ👇       መመዝገቢያ አድራሻ@Abu_Huzeyfah5@AbuHuzeyfah123_bot
نمایش همه...
مركز حذيفة اليمان لحفظ القران الكريم والمبادئ الشرعية 📚መርከዝ ሁዘይፈቱል የማን የቁርአን ሂፍዝ እና መሰረታዊ የሸሪዓ እውቀት ማዕከል 🖊በመርከዙ የሚቀሩ የቂርአት አይነቶች 👇 ❶ ቃዒደቱ ኑራንያህ ❷ ቁርአን በነዞር (በእይታ) ❸ ቁርአን በሂፍዝ ❹ የተጅዊድ ኪታቦች 📒 ተመዝግበው ለመቅራት @AbuHuzeyfah123_bot ወይም @Abu_Huzeyfah5 ይጠቀሙ https://t.me/Huzefetulyemanqurancenter
نمایش همه...
መርከዝ ሁዘይፈቱል የማን የቁርአን ሂፍዝ እና መሰረታዊ የሸሪዓ እውቀት ማዕከል ( GROUP)

مركز حذيفة اليمان لحفظ القران الكريم والمبادئ الشرعية 📚መርከዝ ሁዘይፈቱል የማን የቁርአን ሂፍዝ እና መሰረታዊ የሸሪዓ እውቀት ማዕከል 🖊በመርከዙ የሚቀሩ የቂርአት አይነቶች 👇 ❶ ቃዒደቱ ኑራንያህ ❷ ቁርአን በነዞር (በእይታ) ❸ ቁርአን በሂፍዝ ❹ የተጅዊድ ኪታቦች 📒 ተመዝግበው ለመቅራት @AbuHuzeyfah123_bot ወይም @Abu_Huzeyfah5 ይጠቀሙ

03:43
Video unavailableShow in Telegram
طلب العلم سهل ميسور فضيلة الشيخ صالح بن عبدالله بن حمد العصيمي https://t.me/Mohammed_Siraj_Al_Kemissie
نمایش همه...
10.93 MB
ተከታታይ ፁሁፍ የሰሀቦች ታሪክ ክፍል 4 የሀንዘላህ ኢብኑ አቢ ዐምር ረደላሁ አንህ ታሪክ ይህማ ኢብኑ ነፈውል ነው እርሱ የተከበረ ሲሆን መላ ቤተሰቡም የተከበሩ ናቸው አለ :: ከዛም በዘክዋን ኢብኑ ዓብድ ቀይስ በድን አጠገብ ሲደርሱ አቡ ዓምር  ይህ ከመሪዎቻቸው አንዱ ነው አለ:: በመጨረሻ ሀንዘላህ ኢብኑ አቡ ዓምር የወደቀበት ቦታ ደረሱ እርሱም ከሐምዛ ኢብኑ ዓብድል ሙጦሊብና ከዐብደላህ ኢብኑ ጀሕሽ ጐን ነበር የወደቀው:: አቡ ዓምር አል_ፋሲቅ የልጁን አስክሬን ሲመለከት በጣም ነበር ያዘነው ሁኔታውን ያስተዋለ አቡ ሶፍያን ይህ ሰው ማን ነው ሲል ጠየቀው እሱም ይህማ እዚህ ካለው ሰው ሁሉ ለእኔ ተወዳጁ ነው ይህ የኔ ልጅ ሐንዘላህ ነው አለው:: ከዚያም ተንበርክኮ ልጁን በሀዘኒታና በርህራሄ እያስተዋለ ልጄ ሆይ ከመሞትህ በፊት ከሙሐመዲ እንድትርቅ መክሬህ ነበር በአላህ እምላለሁ አንተ ለአባትህ ታላቅና ተወዳጅ ነበርክ የተከበረና ፀባይህ የተዋበ ነበርክ በመጨረሻም ከተከበሩ ጎደኞችህና ባልደረቦችህ ጋር ወደክ አለ:: ይህን ካለ በሆላ አቡ ዐምር ወደ ሐምዛ እያስተዋለ እንዲህ አለ ሐንዘላህና ማናቸውንም የሙሐመድ ተከታዮች አላህ የሚመነዳቸው ከሆነ አንተንም ይመነዳሀል አለ::  ከዛም ወደ ቁረይሽ ተዋጊዎች ፊቱን መልሶ እንዲህ በማለት ጮኸ _ የቁረይሽ ሰዎች ሆይ _ ከእናተ ውስጥ ማንም ቢሆን የሐንዘላህን በድን እንዳይቆራርጥ በማለት ተናገረ:: ምንምኳ ከናተም ሆነ ከእኔ ጋር መእምነት አንድ ባይሆንም  በእርሱ አካል ላይ አንዳች ተንኮል እንዳትፈፅሙ አስጠነቅቃችሁ አለሁ አለ:: የሐንዘላህን ሰውነት መላእክት አጠቡ ጦርነቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የአላህ መልእክተኛ ﷺ  ለተከታዮቻቸው የሐንዘላህን በድን መላእክ እዳጠቡት ካበሰሯቸው በኋላ  ሰለሁኔታው ባለቤቱን ጠይቋት አሏቸው ተከታዮቻቸውም ወደ ባለቤቱ ሄደው ነቢዩ ﷺ የሐንዘላህን በድን መላእክት በሰማይ በመሬት መካከል በብር ሳፋ ላይ አድርገው እንዳጠቡት ገልፀውልናል ምን የተለየ ያስተዋልሽው ለገር አለ በማለት ጠየቋት? እርሷም እንዲህ አለች ወደ ጂሃድ ሲሄድ ጁኑብ አካላዊ ንፅህና ሳይኖረው እንደሆነ ነበር አለች:: እርግጥ  ነው የተወሰነውን የሰውነቱን ክፍል ታጥቧል ሆኖም ግን ሁሉንም አካሉን አልታጠበም ነበር አለች:: ይህ ነው እንግዲህ ከሚወዳት ባለቤቱ ጋር ከሰዐታት በፊት ጋብቻ ፈፅሞ ለመታጠብኳ ጊዜ ሳያገኝ ወደ ጂሃድ የገሰገሰው የሐንዘላህ መጨረሻ:: መላእክት በሰማይና በምድር መካከል በብር ሳፋ ላይ አድርገው ያጠቡት መሆኑ አያስደነግጥም ::ይህን ሰው ሰለ መሰሉ ፍፁም ምእምናን አላህ ሲገልፅ እንዲህ ይላል :: ﴿انّٓ الله شْتَرَیٰ مِنٓ لْمُوْۡمِنِينَ أَنفُسهُمْ وَأَمْوٰٓلَهُمْ بِأَنَّ لَهُمْ لْجَنَّةَ﴾التوبة :١١١ አላህ ከምእምናን ነፍሶቻቸወንና ገንዘቦቻቸወን ገነት ለእርሱ ብቻ ያላቸው በመኾን ገዛቸው ::__(አት ,ተውባ : 111) ፊአመኒላህ በቀጣይ ታሪክ እሰከምንገናኝ🌱🌱🌱
نمایش همه...
ስኬትን የፈለገ የሰለፎችን መንገድ ይከተል

አዋቂዎች አይደለንም አህለል ቢደአ ግን አይሸውደንም []~ ሰለፍያ~[] የልባሞች እምነት የጀግኖች ጎዳና መመሪያሽ ቁርአን የነቢዩ ሡና በሀቅ የተካብሽው መጠለያ ቤቴ ከጥመት መሸሻ ብርሀነ-ንጋቴ ሁሌም የበላይ ነሽ ኢስላሜ ድምቀቴ መንሀጀ-ሠለፍ ወሠጢያ እምነቴ!! @umu_Anes_Aselefly_botአስተያየት ካለወት👌

https://t.me/skatnYefelgeYeselfochnmengedYcet

ተከታታይ ፁሁፍ  የሰሀቦች ታሪክ ክፍል 3 ↪️ የሀንዘላህ ኢብኑ አቢ ዐምር ረደላሁ አንህ ታሪክ የቀጠለ 💫 ሐንዘህ መሳሪያወን እንደታጠቀ ወደ ነቢዩ ﷺ ገስግሶ ሲደርስ ተዋጊወቻቸወን በጦር ግንባር እያደራጁ አገኛቸው:: የቁረይሽ የጦር አለቆች የተወሰኑ ባሮችንና የሐበሻ ሰዎችን በአቡ  ዐምር  አል_ፋሲቅ ዙሪያ ሆነው ከጥላት ጥቃት እንዲከላከሉለት መድበውለት ነበር :: በዚህ ሁኔታ ላይ የነበረው አቡ ዐምር ከተዋጊወቹ ሰልፍ ወደ ፊት እመር ብሎ በመውጣት ሕዝቦቹን እንዲህ እያለ መጣራት ጀመረ እናተ የአውስ ነገድ ሰዎች ሆይ እኔ አቡ ዐምር ነኝ በፍጥነት ከሙሀመድ ጉራ ወጥታችሁ ወደዚህ እንድትመጡ እሻለሁ አለ:: ♾ የእነርሱ መልስ ደግሞ እንዲህ የሚል ሆነ_ የማችኛችንም አይን አንተን በማየት አይደሰትም ፋሲቅ አሉት :: ይህንን የሕዝቦቹን መልስ እንደሰማ እኔ ከተለየኋቸው በሆላ  ሕዝቦቸ በሰይጣናዊይ ሁኔታ ላይ ወድቀዋል አለ:: ልጁ ሐንዘላህ ኢብኑ ዐምር አባቱን መግደል ይችል ዘንድ ነቢዩ ﷺ. ፍቃድ እንዲሰጡት ጠየቃቸው :: ሁኖም ግን የእዝነት ነቢይ በመሆናቸው ያን እንዳደርግ አልፈቀዱለትም:: ውጊያው ሲጋጋም ሐንዘላህ ወደ መሀል በመጋለብ የቁረይሾች  ወደ ሆነው አቡ ሶፍያን ኢብኑ ሐርብ በቀጥታ ገሰገሰ:: በዚያ ግልቢያውም አቡ ሶፍያንን ሊገድለው ቀርቦ ነበር ::ሆኖም ግን አላህ የሰማዕትነትን ደረጃ ሊያጎናፅፈው እነሆ ፍቃዱ ሆነ:: ወደ አቡ ሶፍያን በተጠጋበት ቅፅፈት ሸዳድ ኢብኑ አል አስወድ አይቶት ኖሮ ኃይለኛ ነት ሰለሰነዘረበት ተሰዋ:: አቡ ሶፍያንም ከዚያ መዓት በማምለጥ ከቁረይሽ ጎደኞቹጋ ጋር እስኪቀላቀል ድረስ ፈረሱ አልጋበት ነበር:: አባትና  ልጅ ----------------- ✍በእሑድ ጦርነት ኢብኑ ቀሚዐህ ነቢዩ ﷺ መገደላቸወን እየጮህ ይለፈልፍ ነበር  ይህን ያደረገው ሙሰአብ ኢብኑ ኡመይርን ረደላሁ አንህ በገደለ ጊዜ ነበር ነቡዩን ﷺ  የገደለ መስሎት ሰለነበር ነው :: እንደሚታወቀው ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ከሚመስሉ ሰዎች ውሰጥ ሙሰአብ ረደላሁ አንህ አንዱ ነበርና:: ጦርነቱ እንደተጠናቀቀም አቡ ሶፍያንና አቡ ዐምር አል_ ፋሲቅ በጦሩ አውድ ላይ የወደቁትን ሰዎች ለማየት በተለይም ደግሞ የነብዩ  ﷺ አስክሬንን ለማገኘት ፍለጋቸወን ቀጠሉ:: በዚያ  ሁኔታ የኻሪጃል ኢብኑ ዘይድ ኢብኑ  አቡ ዙሃይረን በደንብ ተመለከቱ:: አቡ ዐምር አል_ፋሲቅ አቡ ሶፍያን! ይህን ሰው ታውቀዋለህን አለው ? አለ የለም አላውቀወም በማለት መለሰለት:: ይህኮ  ኻሪጃህ ኢብኑ ዘይድ ኢብኑ አቡ ሁዘይር ነው አለ:: ከዚያም የዐባስ ኢብኑ ነዲላህን አስክሬን እንዳዩ አሁንም ይህንስ አታውቀውምን ? አለ አቡ ዐምር አል _ፋሲቅ:: አላውቀውም አለ አቡ ሶፍያን ይህማ ኢብኑ ነፈውል ነው እርሱ የተከበረ ሲሆን በላ ቤተሰቡም የተከበሩ ናቸው አለ::
نمایش همه...
ስኬትን የፈለገ የሰለፎችን መንገድ ይከተል

አዋቂዎች አይደለንም አህለል ቢደአ ግን አይሸውደንም []~ ሰለፍያ~[] የልባሞች እምነት የጀግኖች ጎዳና መመሪያሽ ቁርአን የነቢዩ ሡና በሀቅ የተካብሽው መጠለያ ቤቴ ከጥመት መሸሻ ብርሀነ-ንጋቴ ሁሌም የበላይ ነሽ ኢስላሜ ድምቀቴ መንሀጀ-ሠለፍ ወሠጢያ እምነቴ!! @umu_Anes_Aselefly_botአስተያየት ካለወት👌

https://t.me/skatnYefelgeYeselfochnmengedYcet

ተከታታይ ፁሁፍ የሰሀቦች ታሪክ ክፍል 2 🌱 የሀንዘላህ ኢብኑ አቢ ዐምር ረደላሁ አንህ ታሪክ የቀጠለ✍✍✍ ነቢዩም ﷺ ይህ እውነት አይደለም : አንተም ሆንክ ሌሎች መስሎችህ በኢብራሂም ሃይማኖት ላይ ብዙ የፈጠራ ነገሮችን ጨምራችሆልና አሉት :: አቡ ዐምር በዚህ ጊዜ ከእኛ ውሰጥ ውሸታሙ ሰው ብቻወንና ከሰዎች ተነጥሎ ይሙት አሉ :: ነቢዩም ﷺ አሚን አሉ ↪️ አቡ ዐምር እንዲህ አለ_  አንተን ሊዋጉ የተዘጋጁ ህዝቦችን ካገኘሁ ከእነርሱ ጋር እቀላቀላለሁ አለ:: ከነዚህ የሁለቱ ሰዎች ንግግር በሆላ ነቢዩ ﷺይህን ሰው አቡ ዐምር አል ፋሲቅ አመፀኛው አቡ ዐምር በማለት ጠሩት:: ይህ ከሆነ በኋላ አቡ ዐምር አል ፋሲቅ ሃምሳ የሚሆኑ የአውስ ጐሳ አባላትን አስከትሎ  ከመዲና ወደ መካ ጋለበ :: እዚያ እንደደረሰ የቁረይሽ ሹማምነትን ሰብስቦ የአውስ ጐሳ አባላት የእርሱን ትእዛዝ እንዲሰሙ ነቢዩን ﷺ ጥለው ወደ እርሱ እንደሚመጡና ከእርሱ ፍቃድ እንደመይወጡ አረጋገጠላቸው :: ከዚያ በሆላም ቁረይሾች በበደር ቀን የደረሰባቸወን ውርደት የሚበቀሉበት ቀን  እንደተቃረበ እየተናገረ ለውጊያ ሲያነሳሳቸው ቆየ:: የሐንዘላህ ጋብቻ ይህ በእንዲህ እያለም ልጁ ሐንዘላህ ኢብኑ አቡ ዐምር ረደላሁ አንህ ኋላ ላይ በመዲና ውሰጥ የታወቀውን የምናፍቃን ዋና አለቃ የአብደላህ ኢብኑ ኡብይ ኢብኑ ሰሉልን ልጅ ጀሚላህ ቢንት ዐብደላህ ኢብኑ  ኡብይ ኡብኑ ሰሉልን አገባ::   እርሷን ባገባበት ቀን ማግስት ጧት ላይ ለጂሃድ ጥሪ ሲደረግ አዳመጠ:: ከዚያም ወደ ነቡዩﷺ ሄደና ለሊቱን ከርሷ ጋስ ማሳለፍ ይችል ዘንድ እንዲፈቅዱለት ጠየቃቸው ከዚያም በሆላ እንደነጋ መሳሪያወን ታጥቆ ወደ ነቢዩ ﷺ ገሰገሰ:; 🔂. የኡሑድ ጦርነት ሐንዘላህ ወደ ኡሑድ ጦርነት ለመሄድ መወሰኑን ባለቤቱ ካወቀች በሆላ ከዘመዶቿ ውስጥ አራት የሚሆኑትን በመጥራት ሐንዘላህ ከሷ ጋር የጋብቻ ሥርዐቱን በሚገባ መፈፀሙን እንዲያውቁ አደረገች :: ይህን ለማድረግ የወሰነችወም በህልሟ ሰማዩ ክፍት ሁኖ ሐንዘላህ ወደዚያ ሲመጥቅና ሰማዩም ሲውጠው ሰላየች ነበር :: በዚህም የተነሳ ሐንዘላህ በዚህ ውጊያ ሰማዕት (ሸሂድ) እንደሚሆን አምና ነበር ; ሰለሆነም እርሱ በሕየወት የመይቆይ ከሆነና በግንኙነታቸው ወቅት ፀንሳ ከሆነ ይህንኑ እንደመሰክሩላት ነበር ዘመዶቿን የማስጠራቱ ሚስጠር:: ይቀጥላል ኢንሸ አላህ ስህተት ካለኝ ስህተቴን ረሙኝ 🌱✍✍✍✍
نمایش همه...
ስኬትን የፈለገ የሰለፎችን መንገድ ይከተል

አዋቂዎች አይደለንም አህለል ቢደአ ግን አይሸውደንም []~ ሰለፍያ~[] የልባሞች እምነት የጀግኖች ጎዳና መመሪያሽ ቁርአን የነቢዩ ሡና በሀቅ የተካብሽው መጠለያ ቤቴ ከጥመት መሸሻ ብርሀነ-ንጋቴ ሁሌም የበላይ ነሽ ኢስላሜ ድምቀቴ መንሀጀ-ሠለፍ ወሠጢያ እምነቴ!! @umu_Anes_Aselefly_botአስተያየት ካለወት👌

https://t.me/skatnYefelgeYeselfochnmengedYcet

↪️ የሰሀቦች ታሪክ  ክፍል 2 የሐንዘላህ ኢብኑ አቢ ዐምር ረደላሁ አንህ ታሪክ ሙሉ ስሙና የዘር ሀረጉ እንደሚመለከተው ተጠቅሷል ሐንዘላለ  ኢብኑ አቢ ዐምር ኢብኑ ሳፊ ኢብኑ ማላክ ኢብኑ ኡመያህ ኢብኑ ዱባኢያህ ዘይዲ ኢብኑ ዐወፍ ኢብኑ ማሊክ ኢብኑ አል አውሰ አል አንሷሪይ ይባላሉ :: ይህ ሰም በአጭሩ ሲጠቀስ ደግሞ ሐንዘላህ ኢብኑ አቢ ዐምር አር ራሂቡ አል አንሷሪይ አል አውስ በመባል ይታወቃል :: አቡ ዐምር አር ራሂብ  እና ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሐንዘላህ ኢስላምን የተቀበለው  ነብዩ  ﷺ ወደ መዲና በመጡበት ጊዜ ነበር:: አባቱ አቡ ዐምር ኢብኑ ሳፊ በመዲና የአውስ ጐሳ ውሰጦ የተከበረ ሰው የነበረ ሲሆን  ከአይሁዲ ጋርም ቅርርብ ነበረው :: አቡ ዐምር ይህንኑ ቀረቤታወን በመንተራስ አይሁዳዊያንን ይመጣል ሰለሚባለው የመጨረሻ ነቢይ ባሕሪና ሁኔታ ይነግሩት ዘንድ መጠየቅ ያዘወትር ነበር:; ♦️በሌላ አጋጣሚ አቡ ዐምር ወደ ሻም (ታላቋ ሶሪያ) ጉዞ ባደረገበት ጊዜም ከተኢማ አይሁዲ ጋር ተገናኝቶ ነበር :: እንዲሁም  በዚያው ሰለ  ክርስቲያኖችን አግኝቶ መበፀሀፍቶቻቸው ነቢዪ ዒሳ ኢብኑ መርየ አለይሂ ሰላም } ይመጣል ስለተባለው ነብይ የተናገረው ነገር ምን እንደሆነ ሲጠይቃቸው  የሚያውቁትን ሁሉ ነገሩት ከዚያም ወደ ሀገሩ እንደተመለሰ ከሱፍ የተሰራ ልብሱን ካጠለቀ በሆላ እንዲህ አለ~ እኔ በነቢዩ ኢብራሂም ሀይማኖት ላይ እፀናለሁ የሚመጣወንም ነቢይም ከሚጠባበቁት ነኝ አለ 🔂 ይህ ሁሉ አጋጣሚና ሁኔታ የሚያሳየው አቢ ዐምር አር _ራሂብ  ነቢዩን  ﷺ  ለመከተል የመጀመሪያው ሰው እንደሚሆን ነበር :: ይሁን እንጂ አቡ ዐምር የነቢዩን  ﷺ   መምጣት እንደሰማ በእርሳቸው ለማመን ቀዳሚ አልሆነም ልጁ ሐንዘላህ ኢስላምን መቀበሉን ከሰማ በኋላ  እውነተኛወን የእምነቱን ምስክርነት (ሸሀዳ) በመስጠት የእርሳቸው ተከታይ ከመሆን ይልቅ ግልፅ ባልሆነ ምክንያት ከሚጠሏቸውቻ በቅናት ከሚመለከቷቸው ሰዎች ግንባር ቀደሙ ሆነ:: ነቢዩ ﷺ ወደ መዲና ተሰደው በሄዱበት ጊዜም አቡ ዐምር ወደ እርሳቸው ሄደና ሙሐመድ ሆይ ! ምንዲነው ይህ አድስ ሀይማኖት አላቸው ? እርሳቸወም ይህማ የኢብራሂም ሃይማኖት ነው አሉት አቡ ዐምርም እኔ ከዚል ሃይማኖት ላይ ነኝ አለ:: ይቀጥላል ኢንሸ አላህ✍✍✍✍ ስህተት ካለው ስሀተቴን ረሙኝ @umu_Anes_Aselefly_bot
نمایش همه...
ስኬትን የፈለገ የሰለፎችን መንገድ ይከተል

አዋቂዎች አይደለንም አህለል ቢደአ ግን አይሸውደንም []~ ሰለፍያ~[] የልባሞች እምነት የጀግኖች ጎዳና መመሪያሽ ቁርአን የነቢዩ ሡና በሀቅ የተካብሽው መጠለያ ቤቴ ከጥመት መሸሻ ብርሀነ-ንጋቴ ሁሌም የበላይ ነሽ ኢስላሜ ድምቀቴ መንሀጀ-ሠለፍ ወሠጢያ እምነቴ!! @umu_Anes_Aselefly_botአስተያየት ካለወት👌

https://t.me/skatnYefelgeYeselfochnmengedYcet

♨️ በሙሓዶራው የተወሱ ነጥቦች √ የሰለፎች አቋም በሀሜት ላይ √ የሀሜት ሰበቦችና ምክንያቶች √ የመጥፎ ጓደኛ ተፅእኖ https://t.me/skatnYefelgeYeselfochnmengedYcet
نمایش همه...
02 ሀሜትና መዘዙ.mp34.94 MB
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.