cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ማህተቤ እምነቴ

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
549
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

✝✞✝ ወበዛቲ ዕለት ተወልደ አብ ክቡር አረጋዊ፡ ወሰማዕተ ጽድቅ አቡነ ታዴዎስ ዘጽላልሽ፡፡ በዚህች ዕለት ኢትዮጵያዊው ፃድቅ አቡነ ታዴዎስ ተወለዱ ✝✞✝ ✝ #አቡነ_ታዴዎስ_ዘጽላልሽ ✝ ✝ትውልድ ሀገራቸው ጽላልሽ (ዞረሬ) ነው። አባታቸው ሮማንዮስ እናታቸው ማርታ ይባላሉ። አባታቸው ሮማንዮስ ቄስ ነው። የአቡነ ተክለ ሃይማኖት አጎት ናቸው። በእናታቸው ማኅፀን ሳሉ በጽላልሽ ረሀብ ፀንቶ ነበር። እሳቸው ግንቦት ፳፫ ቀን በመንፈቀ ሌሊት በልብሰ ብርሃን ተጠቅልለው ተወለዱ። ቤታቸው በበረከት ተመላ። ለሀገሬው ዝናብ ዘንቦለት ህዝቡ ከፃድቁ እናትና አባት የተመፀወቱትን ከፍለው ዘሩ። አቡነ ታዴዎስ በተወለዱ በ፵ ቀናቸው ሐምሌ ፪ ቀን ሲጠመቁ የተዘራው እህል አንድ ሳይቀር አፍርቶ ተገኝቷል። ዕድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስ ለሊቀ ካህናቱ ለሕይወት ብነ ሰጥተዋቸው ሲማሩ አደጉ። አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዳሞት (ወላይታ) ተሻግረው መተሎሚን አስተምረው “በእግዚአብሔር ቸርነት በአንተ ፀሎት መተሎሚን በሃይማኖት ወልጄዋለሁ። በምግባር አሳድጌዋለሁና እህትህን ይዘህ በቶሎ ና፤” ብለው ላኩባቸው። እህታቸው ትቤጽዮን ትባላለች። የመተሎሚን ወንድም ዝግናን አግብታ አባ ኤልሳዕን ወልዳለች። ከባሏ ተጣልታ ነበርና እሷን ከባሏ አስታርቀው እሳቸው አቡነ ተክለሃይማኖትን እያገለገሉ ፱ አመት ኖረዋል። በኋላ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ አባ በጸሎተ ሚካኤል ሲሄዱ እሳቸውም ወደ ጽላልሽ ተመልሰው ስለነበር አፄ ይኩኖ አምላክ እንድትመክረኝ እንድትገስፀኝ ከቤቴ ተቀመጥ ብለው ከቤተመንግስት አስቀመጣቸው። ሰይጣን ለፀብ ለምቀኝነት አያርፍምና ጠላ ቤቷን ክፉ የሚገድል ሽታ አሸተታትና ሞተች። አባ ታዴዎስ ወንዝ ገብተው ሲፀልዩ ሙቷ ተነሥታለች። ከዚህ በኋላ ውዳሴ ከንቱ ይሆንብኛል ብለው ወደ ደብረ ሊባኖስ ተመለሱ። አቡነ ተክለሃይማኖት ወደ ጽጋጋ (ጅጅጋ) ሂድ አሏቸው። ለምን ቢሉ? አባ አኖሬዎስ ሄደው ሲያስተምሩ ያገሬው ሰዎች ደብድበው አስረዋቸው ነበርና እሳቸውን ለማሰወፈታት ነበር። የአካባቢው ንጉስ መዩጥ ይባላል። በነፋስ ሰረገላ ተጭነው ሄደው ከፊቱ ወርደው ሲቆሙ ደንግጦ ከሰማይ መላእክት ነህ ወይስ ከሰው ወገን? ቢላቸው። እኔ ከሰው ወገን ነኝ አሉት። ክርስትናንም አስተማሩት ጋኔን ከእሳት ላይ ጥሎት ሲሰቃይ የሚኖር ልጅ ነበረው አድነውለታል። ይህን አይቶ አምኖ ሕዝቡም እንዲያምኑና ክርስትናን እንዲቀበሉ አዋጅ ነገረ። እንደ ሐዋርያው ታዴዎስ ፳፭ ግመል በመርፌ ቀዳዳ በተአምራት አሳልፈው በማሳየታቸው አፍጃል የሚባል ያንድ ባለጠጋ ልጅ በምትሐት እንደሚያደርጉት አድርጎ በመናገሩ ከግመሎቹ አንዲቱ ረግጣው ሞተ፤ ይህን ሙሳ የሚባል ልጅም በተቀበረ በሦስተኛው ቀን «አልዓዛርን ከሙታን በአስነሳው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ልጄ ና ተነስ» ብለህ ይህንን መቋሚያዬን ወስደህ ከመቃብሩ ላይ አኑር ብለው በአፍጃል ሰጥተውት እንዳሉት ቢያደርግ አፈፍ ብሎ ተነስቷል። ይህን አይተው ህዝቡ ሁሉ አምነዋል። ከዚህ በኋላ ሙሳን ሙሴ ብለው ሊቀ ካህናት አድርገው ፲፪ አብያተ ክርስቲያናት አሳንፀው አኖሬዎስን ይዘው ተመልሰዋል። አቡነ ተክለሃይማኖትም ከንጉሱ ተማክረው ሊቀካህናት ዘጽላልሽ ብለው ሾመዋቸዋል። ንጉስ ዓምደ ጽዮን ፍቅረ ዝሙት አድሮበት የአባቱን ቅምጥ ቢያገባት ሄደው ገሰፁት። በዚህ የተናደደች የንጉሱ ሚስት የኋሊት አሳስራ ከጥልቅ ገደል አሰጣለቻቸው። በዚህ ጊዜ የመቶ ሃያ አመት አረጋዊ ነበሩ። የታዘዘ መልአክ ገብረ እግዚአብሔርና ውቢት የተባሉ ደጋግ ሰዎችን አስነስቶ ስጋቸውን ወስደው ከበዓታቸው ቀብረው የተሰጣቸውንም ቃል ኪዳን በዳግማዊ አፄ ዳዊት ዘመን በህዝቡ ፊት መስክረዋል። ንጉስ ዳዊትም ዜና ገድላቸውን አጽፈዋል፤ ስጋቸውንም ወደ ከተማቸው በክብር አፍልሰው በተቀደሰ ስፍራ አኑረውታል። የፃድቁ አባታችን እረድሄት በረከት ይደርብን አሜን!!! (Sisay Poul እንደጻፈው - ነፍሱን ይማር) https://t.me/mahitebiemnetie
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
††† እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመገለጥ በዓል (ደብረ ምጥማቅ) በሰላም አደረሳችሁ ††† ††† ደብረ ምጥማቅ ††† =>የአርያም ንግሥት: የሰማይና የምድር እመቤት: የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚሕች ዕለት በምድረ ግብፅ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች:: +ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ: +ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብፅና ኢትዮዽያ በተሰደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ: ከዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ አርፎ ነበር:: ቦታውን ባርኮ ለዘለዓለም ያንቺ መገለጫ ይሁን ብሎም ቃል ኪዳን ገብቶላት ነበር:: +ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት ቤት ሆነ:: እመቤታችንም በልጇ ፈቃድ ግንቦት 21 ቀን አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላት መጣች:: +በዚያ ሕዝበ ክርስቲያንም: አሕዛብም ተሰብስበው ለ5 ቀናት ከእመ ብርሃን ጋር ይሰነብታሉ:: እንግዲህ ልብ በሉት:- እንኩዋን የአርያም ንግስት: የአምላክ እናቱ እመቤታችንን ይቅርና በዚሕ ዓለም ሰይጣን ቤቱ ያደረጋቸውን: የመዝናኛው ኢንዳስትሪ ዝነኛ ሰዎችን ለማየት የዘመናችን ሰው እንዴት እንደሚቸኩል:: +እመቤታችንን በአካል መመልከት አይደለም ስሟን መጥራት ነፍስን ከሥጋ መለየት የሚችል ጣዕምና ደስታ አለው:: ባይሆን ይሔ ለሚገባውና ላደለው ብቻ ነው:: +የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር የሚቆዩባቸው ቀናት የዘለዓለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባቸው ናቸው:: ፈልገው የሚያጡት: ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም ነገር አልነበረም:: ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታት: ደናግል: መነኮሳት: መላዕክትና ሊቃነ መላእክት ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበርና:: እመ ብርሃንም እየመላለሰች ትባርካቸው ነበር:: +እነዚያ እርሷን ያዩ ዐይኖች: በፊቷ የቆሙ እግሮች ክብር ይገባቸዋል:: 5ቱ ዕለታት ሲፈጸሙ ሕዝቡ እመቤታችንን በዕንባ ይሰናበቷታል:: እመ ብርሃንም በብርሃን መስቀል ባርካቸው ከቅዱሳኑ ጋር ታርጋለች:: ††† አባ መርትያኖስ ††† =>አባ መርትያኖስ በበርሃ ከ68 ዓመታት በላይ በቅድስና የኖሩ አባት ናቸው:: ሰይጣን እርሳቸውን ፊት ለፊት ተዋግቶ መጣል ቢያቅተው በዝሙት በተለከፉ ሴቶች ያስቸግራቸው ነበር:: +አንድ ቀን አንዷ ሽቶ አርከፍክፋ በዝሙት ልትጥላቸው ብትል እግራቸውን እሳት ውስጥ ጨምረው እግራቸው እየተቃጠለ በሚወጣው ጠረን አጋንንትን አርቀዋል:: እሷንም በንስሃ መልሰው ለቅድስና አብቅተዋታል:: ጻድቁ ከፈተና ለመራቅ በ108 ሃገራት 108 በዓቶች የነበሯቸው ብቸኛ አባት ናቸው:: ††† ለአባት እናቶቻችን የተገለጠች እመቤታችን ለእኛም በረድኤት ትገለጽልን:: ጣዕመ ስሟ በአንደበታችን: ጣዕመ ፍቅሯ በልባችን ይደርብን:: ††† =>ግንቦት 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅድስት ደብረ ምጥማቅ (የእመቤታችን መገለጥ) 2.አባ መርትያኖስ ጻድቅ (በዝሙት ላለመሰናከል እግራቸውን በእሳት ያቃጠሉ አባት) 3.ቅዱስ አሮን ሶርያዊ 4.ቅዱስ አሞጽ ነቢይ =>ወርኀዊ በዓላት 1.አበው ጎርጎርዮሳት 2.አቡነ ምዕመነ ድንግል 3.አቡነ አምደ ሥላሴ =>+"+ የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ:: ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው:: ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው:: በሁዋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ . . . በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ:: በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ:: ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ:: +"+ (መዝ. 44:12-17) ወስብሐት ለእግዚአብሔር https://t.me/mahitebiemnetie https://t.me/mahitebiemnetie
نمایش همه...
✝✝✝ ተአምሪሁ ለጻድቅ አቡነ ዓቢየ እግዚእ - - - ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም:: አሜን:: ✝✝✝ ☞ከበዙ ተአምራቱ አንዱን፡- =>ጻድቁ #አባ_ዓቢየ_እግዚእ በገዳማቸው #ተንቤን (መረታ) ሳሉ አንዲት መበለት መጥታ "አባቴ! የምጠጣውን ጸበል ባርከህ ስጠኝ?" አለቻቸው:: ጻድቁም በውሃው ላይ ጸሎትን አድርሰው : በመስቀላቸው ባርከው ሰጧት:: +ወደ ባልንጀራዋ ስትደርስ ግን ሐሳቧን ቀየረችና "ልጠጣው" ብላ የተቀበለችውን ማይ (ጸበል) ልትጠመቅበት (ልትጸበልበት) ወሰነች:: ባልንጀራዋንም "በላዬ ላይ አፍሺልኝ" ስትል አዘዘቻት:: +ባልንጀራዋም "እሺ" ብላ ልታፈስላት (ልትጸብላት) በፋጋ (ግማሽ ቅል) ያለውን ጸበል አነሳች:: ልታፈሰው ስትዘቀዝቀው ግን ከሆነው ነገር የተነሳ 2ቱም ደነገጡ:: ጸበሉ የረጋ ደም ወደ መሆን በቅጽበት ተለውጧልና:: +ፍጹም ፍርሃት የወደቀባቸው ሴቶቹ እየተሯሯጡ ወደ አባ ዓቢየ እግዚእ በዓት ደረሱ:: ከውጭ ሆነውም "አባ! አባ! የሰጠኸን ጸበልኮ የረጋ ደም ሆነ" አሏቸው:: ጻድቁም እንዳላዋቂ "ምን አጠፋችሁ?" ሲሉ ጠየቁ:: +"አባታችን! ምንም አላጠፋንም:: ብቻ አፍሺልኝ ብየ ስሰጣት እንዲህ ሆነ" ስትል አንዷ መለሰች:: ጻድቁ ግን በየውሃት "ልጆቼ! ሁሌም : 'ምንም አላጠፋንም' አይባልም:: ሰው ሆኖ የማይበድል የለምና:: + . . . አንቺም ልጄ! እኔን ያልሺኝ 'የምጠጣው ጸበል ስጠኝ' ነበር:: ግን ልትጸበይበት ወደድሽ:: ስሕተትሽ ከዚህ ይጀምራል:: (የቅዳሴ ጸበል ለመጸበል አይሆንምና) ¤በዚያ ላይ "አልቦ ዓቢይ ኃጢአት ከመ ወልጦ ቃል . . . ከውሸት በላይ ከባድ ኃጢአት የለም::" (ዮሐ. 8:44) + . . . በተጨማሪ ደግሞ ያለ ስልጣኗ እህትሽን 'አጥምቂኝ' አልሻት:: ስለነዚህ ነገሮች ጸበሉ ተለውጦባቹሃል" ብለው ወደ ጸበሉ በመስቀል አማተቡ:: "እፍ" ሲሉትም የረጋ ደም የነበረው ማይ ወደ ጸበልነቱ ተመለሰ:: ይህንን ያዩ ሴቶቹ በግንባራቸው ተደፍተው ለጻድቁ ሰገዱ:: =>ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም:: አሜን:: <<< በበዓሉም (ግንቦት 19 ቀን) ጐንደር በሚገኘው ቤተ መቅደሳቸው ተገኝተን እናክብራቸው ! >>> <<< ከጻድቁ በረከት አይለየን !! >>> ✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞ https://t.me/mahitebiemnetie https://t.me/mahitebiemnetie
نمایش همه...
++"+ በተኩላና በእባብ ላይ ትጫማለህ:: አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ:: በእኔ ተማምኗልና አስጥለዋለሁ:: ስሜንም አውቁዋልና እጋርደዋለሁ:: ይጠራኛል እመልስለትማለሁ:: በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ:: አድነዋለሁ: አከብረውማለሁ:: ረጅም እድሜንአጠግበዋለሁ:: ማዳኔንም አሳየዋለሁ:: +"+ (መዝ. 90:13-16) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/mahitebiemnetie https://t.me/mahitebiemnetie
نمایش همه...

✝እንኳን አደረሳችሁ✝ 💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠 /ማቴ ፫:፫/ 🔷ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!! ❇️ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)❇️ " 🔶ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::🔸 አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/mahitebiemnetie https://t.me/mahitebiemnetie
نمایش همه...
††† እንኳን ለታላቁ የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ††† ††† ሊቁ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ጽድቅ ከቅድስና : ድርሰት ከጥብቅና የተሳካለት አባት ነው:: "ኤዺፋንያ" ማለት የመለኮት መገለጥ ሲሆን "ኤዺፋንዮስ" ማለት ደግሞ ምሥጢረ መለኮት የተገለጠለት ማለት ነው:: ቅዱስ ኤዺፋንዮስ የተወለደው ክርስቶስን ከሚጠሉ አይሁዳውያን ቤተሰቦች ቤተ ገብርኤል ውስጥ ነው:: ቤተሰቦቹ ከአንድ አህያ በቀር ምንም የሌላቸው ድሆች ነበሩ:: በዚያ ላይ በልጅነቱ አባቱ በመሞቱ ከእናቱና ከአንዲት እህቱ ጋር በረሃብ ሊያልቁ ሆነ:: ሕጻኑ ኤዺፋንዮስ በአህያው እንዳይሠራ አህያው ክፉ ነበርና ሊሸጠው ገበያ አወጣው:: ፊላታዎስ ከሚባል ክርስቲያን ጋር ለግዢ ሲደራደሩ አህያው የኤዺፋንዮስን ኩላሊቱን ረግጦት ለሞት አደረሰው:: በዚህ ጊዜ አብሮት ያለው ክርስቲያኑ በትእምርተ መስቀል አማትቦ አዳነው:: በፈንታው ግን አህያው ሞተ:: ሕጻኑ ኤዺፋንዮስ እያደነቀ ሔደ:: ከቆይታ በኋላ ሀብታም አጎቱ ገንዘቡን አውርሶት በመሞቱ ገና በ16 ዓመቱ ባለጠጋ ሆነ:: ያቺ ገበያ ላይ ያያት ተአምር ግን በልቡ ውስጥ ትመላለስ ነበር:: አንድ ቀን ደግሞ ሉክያኖስ ከሚባል ክርስቲያን ጋር ሲሔዱ ነዳይ አገኙ:: ባለጠጋው ኤዺፋንዮስ አለፈው:: ያ ድሃ ክርስቲያን ግን የለበሳትን አውልቆ መጸወተው:: በዚሕ ጊዜ መልዐኩ መጥቶ የብርሃን ልብስ ሲያለብሰው ኤዺፋንዮስ ተመለከተ:: ኤዺፋንዮስ ጊዜ አላጠፋም:: ከእህቱ ጋር በክርስቶስ አምኖ ተጠመቀ:: ሃብት ንበረቱን ግማሹን መጸወተ:: በተረፈው ደግሞ መጻሕፍትን ገዝቶ ወደ አባ ኢላርዮን ገዳም ገባ:: በዚያም መናንያኑ እስኪያደንቁት ድረስ በፍጹም ትጋትና ቅድስና ተጋደለ:: በጸሎቱ ዝናም አዘነመ : ድውያንን ፈወሰ : ብዙ ተአምራትንም አደረገ:: እግዚአብሔር ደግሞ ለሌላ አገልግሎት ሽቶታልና በቆዽሮስ ደሴት ላይ ዻዻስ ሆኖ ተሾመ:: ብሉይ ከሐዲስ የወሰነ ሊቅ ነውና ብዙ መጻሕፍትን ተረጎመ:: በሺሕ የሚቆጠሩ ድርሳናትን ደረሰ:: በአፍም በመጽሐፍም ብሎ መናፍቃንንና አይሁድን ምላሽ በማሳጣቱ ቤተ ክርስቲያን "ጠበቃየ" ትለዋለች:: ከደረሳቸው መጻሕፍት መካከል "ሃይማኖተ አበው ዘኤዺፋንዮስ : መጽሐፈ ቅዳሴውና አክሲማሮስ (ስነ ፍጥረት)" ዛሬም በቅርብ ይገኛሉ:: ሊቁ ቅዱስ ኤዺፋንዮስ በመልካም እረኝነትና በሚደነቅ ቅድስና ተመላልሶ በ406 ዓ/ም ዐርፏል:: እድሜውም 96 ዓመት ያህል ነበር:: ††† አምላካችን ከቅዱሱ ሊቅ በረከት ያድለን:: ††† ግንቦት 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ) 2.ቅዱስ ኢላርዮን ገዳማዊ 3.አባ ሉክያኖስ ጻድቅ 4.ቅዱስ ፊላታዎስ ክርስቲያናዊ ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት) 2.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ) 3.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ 4.አባ ገሪማ ዘመደራ 5.አባ ዸላሞን ፈላሢ 6.አባ ለትጹን የዋህ ††† "የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል:: እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው:: እኛ ግን የማይጠፋውን:: ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም:: ነፋስን እንደሚጐስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም:: ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጐሰምሁ አስገዛዋለሁ::" ††† (1ቆሮ. 9:25) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
نمایش همه...
🎁🎁🎁የትናንት የDaily Lottery እድለኛ ዕጣ ቁጥር 27 ሁኗል።🎁🎁🎁 እንኳን ደስ አለህ
نمایش همه...
🎁🎁🎁የትናንት የDaily Lottery እድለኛ ዕጣ ቁጥር 11 ሁኗል።🎁🎁🎁 እንኳን ደስ አለህ
نمایش همه...
ሰላም ሰላም የDaily Lottery channel ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ Daily Lottery ከአንድ ዓመት በላይ በታማኝነት እና በቅንነት ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል በመሆኑም አንዳንድ የአጨዋወት ማስተካከያዎችን ያደረግን መሆኑን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው። እነሱም እንደሚከተለው የተገለፁት ናቸው። በመጀመርያ የዕጣ ቁጥር ይሰጣችኋል የዕጣ ቁጥራችሁን በሁለት መንገድ ማግኘት ይቻላል በመጀመሪያ መግዛት የሚፈልጉትን ዕጣ መጠን ያህል ከብር አስር (10birr) ጀምሮ መግዛት ይኖርባችኋል ። ይህንም 1ኛ. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000382874092 2ኛ. በቴሌብር 0918981642 ማሳሰቢያ ዕጣውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሆነ የምትገዙት transaction code screenshots መላካችሁን እንዳትረሱ። እንዲሁም ዕጣውን የምትገዙት በቴሌብር ከሆነ ከቴሌ የሚላክላችሁን ማረጋገጫ ሜሴጅ(SMS) screenshot እንስተው ይላኩ። በቻናሉ ያላችሁን ሀሳብና አስተያየት በዚህ ያጋሩን 👉👉 @Englizu 👉👉 @Englizu 👉👉 @Englizu ምንጊዜም ቢሆን የዕለቱ እድለኛ transaction በቻናላችን የሚለጠፍ ይሆናል።
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.