cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ኪዳነምህረት እናታችን

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ መዝሙሮች ፣የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ እና ወረባቶችን አንዲሁም ትምህርቶች ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። “ልጄ ሆይ፥ ወደ ጥበቤ አድምጥ፤ ጆሮህን ወደ ትምህርቴ መልስ፥” ምሳሌ ፭፥፩

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
152
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ለእመ ኮነ ሕንጸተ ቤተ መቅደስ በሰንበት (መስከረም ፲፮) መዝሙር ሐነጽዋ (በ፮/ሥ) ሐነጽዋ ለቤተ ክርስቲያን ወሣረርዋ በመንፈስ ቅዱስ እንተ ተሐንጸት በእደ ካህናት ወተቀደሰት በአፈ ጳጳሳት ወተዓተበት በማይ ዘውኅዘ እምገቦሁ አመ ሕማማቲሁ ለሰማይ አቅዲሙ ፈጠሮ ወበምድር ተከለ ደብተራ ቀደሳ አብ ወማኅደሮ ረሰያ። ትርጕም፦ ቤተ ክርስቲያንን በመንፈስ ቅዱስ ሠሯት አነጿት በካህናት እጅ ታንጻለችና በጳጳሳት አፍ ተቀድሳለችና በሕማሙ ጊዜ ከጎኑ በፈሰሰ ውኃ ከብራለችና። አስቀድሞ ሰማይን ፈጠረ በምድርም ድንኳንን ተከለ አብ ቀደሳት ማደሪያው አደረጋት። የዕለቱ ምንባባት ፩ቆሮ ፫፥፩ - ፲፰፤ ራእይ ፳፩፥፲ - ፍ፤ ግብ ፯፥፵፬ - ፶፩፤ የዕለቱ ወንጌል፦ ዮሐ ፲፥፳፪ - ፍ፤ ቅዳሴ፦ ዘእግዚእነ፤ የዕለቱ ምስባክ፦ ደብረ ጽዮን ዘአፍቀረ፤ ሐነጸ መቅደሶ በአርያም፤ ወሣረራ ውስተ ምድር ዘለዓለም። መዝ ፸፯፥፷፰፤ ትርጕም፦ የወደደውን የጽዮንን ተራራ፤ መቅደሱን በአርያም ሠራ፤ ለዘለዓለም በምድር ውስጥ መሠረታት። ምሥጢር፦ የጽዮንን ተራራ የወደደ እሱ ነው አንድም የእመቤታችንን ሥነ ውበት ለተዋሕዶ የወደደ እሱ ነው፤ መመስገኛው የምትሆን ቤተ መቅደስን በልዕልና ሠራት አንድም ማደሪያው የምትሆን እመቤታችንን በልዕልና ፈጠራት፤ በዚህ ዓለም ለዘለዓለም አጽንቶ ሠራት አንድም እመቤታችንን በንጽሕና በቅድስና አጸናት። ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇 •➢ ሼር // SHARE
نمایش همه...
በስምአም ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አአዱ አምላክ🙏🙏 በአቃቂ ቃሊቲ በፋንታ ፈለገ ብርሀን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስታን የንግስ በአል መስቀረም 21/1/2014ዓ .ም በታላቅ ሁኔታ ይከበራል በዚህ እለት የቤተ ክርስቲያኑ የተመሰረተበት ስለሆነ እርሶም መተወ የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ በልኡል እግዚአብሔር ስም እንጠይቆታለን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 💒💒💒💒💒⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ✝️✝️✝️✝️
نمایش همه...
ከቁጥር ተርፈን ለንስሃ ዕድሜ ተጨምሮልን ፫፻፷፭ ቀን ልኖር ተዘጋጀን ሀገራችን ከማቅ ለማውጣት እግዚኦ ለምንልበት ለዚች ቀን ለዐዲስዋ ብርሃን ጅማሮ 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 መልካም አዲስ ዓመት 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 አዲስዓመት መልካምአዲስዓመት መልካም አዲስዓመት መልካም አዲስዓመት መልካም አዲስዓመት መልካም አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመትአዲስዓመትአዲስዓመት አዲስዓመትአዲስዓመትአዲስዓመት አዲስዓመት መልካምአዲስዓመት መልካምአዲስዓመትአዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት መልካም አዲስዓመትአዲስዓመት መልካምአዲስዓመት አዲስዓመት ዓመት አዲስዓመት መልካምአዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመትአዲስዓመት መልካም አዲስ ዓመት መልካም አዲስ ዓመት መልካም አዲስ ዓመት መልካም አዲስ ዓመት መልካም አዲስ ዓመት መልካም አዲስ ዓመት መልካም አዲስ ዓመት መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን 🌼🌼 መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን 🌼🌼 መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን 🌼🌼 መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን 🌼🌼 አዲስ ዓመት አዲስ ዓመት አዲስ ዓመት አዲስ ዓመት አዲስ ዓመት አዲስ ዓመት አዲስ ዓመት 🌼ነገ ለሳምንቱ ለወሩ ለዓመቱ ደምሮን ያድርሰን 🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 መልካም አዲስ ዓመት ብሎ አምላካችን እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም አሸጋገራችሁ ይበለን ከነ መላ ቤተሰቦቻችን ። ዐዲሱን ዓመት እግዚአብሔርን በማመስገን መጀመር ዓመቱን ሙሉ በበረከትና በምስጋና እንድንኖር ያደርጋልን። 🌼🌼🌼 🌼🌼🌼 🌼🌼🌼 🌼🌼🌼 🌼🌼🌼 ዮሐንስ መክብብ 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼
نمایش همه...
ውድ የኪዳነምህረት እናታችን ቤተሰቦች እንካን ለዛሬው ከሊቀ መላእክት ሶስተኛ ለሆነው ቅዱስ ሩፋኤልለተሾመበት እና ለከበረበት እለት ጳጉሜ 3 ታላቅ በአል አደረሳችሁ ‹እኔ ሩፋኤል ነኝ›› 👉ከሰባቱ ሊቃነ መላእክትም ከቅዱስ ሚካኤልና ከቅዱስ ገብርኤል ቀጥሎ በሦስተኛ ደረጃ ሊቀ መላእክት የሆነው ቅዱስ ሩፋኤል የተሾመበትና የከበረበት ዕለት ጳጉሜ ሦስት ታላቅ በዓል ነው፡፡ 👉በመጽሐፈ ስንክሳር እንደተጻፈው ሐዋርያት የቅዱስ ሩፋኤልን ክብሩን ያስረዳቸው ዘንድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በለመኑት ጊዜ ከሦስተኛው ዓለም ውስጥ የመላአክት አለቆች ቅዱስ ሚካኤልን ቅዱስ ገብርኤልን እና ቅዱስ ሩፋኤልን እንዲመጡ አዘዛቸው፤ እነርሱም መጥተው በታላቅ ደስታ ለክብር ባለቤት ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰገዱ፡፡ 👉ጌታችንም ቅዱስ ሩፋኤልን እንዲህ አለው፤ ‹‹የክብርህን ገናናት የባልንጀሮችህንም ልዕልናቸውን እንዲያውቁ ለሐዋርያት ንገራቸው፡፡›› ያንጊዜም ለጌታችን ሰገደ፤ እንዲህም አላቸው፤ ‹‹ደገኛው የመላእክት አለቃ ሚካኤል ለሁሉም መላእክት አለቃቸው ነው፤ ስሙም ይቅር ባይ ይባላል፡፡ ሁለተኛም የመላክት አለቃ ገብርኤል ይባላል፤ የስሙም ትርጓሜ አገልጋይም ጌታም የሆነ የዓለሙ ሁሉ እመቤት የሆነች አምላክን የወለደች ቅድስት ድንግል ማርያምን ያበሠራት ነው፡፡ የእኔም ስሜ ሩፋኤል ነው፡፡ ይህም ደስ የሚያስኝ ቸር መሐሪ ቅን የዋህ ማለት ነው፡፡ እኔም ኃጢአተኞችን በእግዚአብሔር ዘንድ አልከሳቸውም፤ ከኃጢአት በንስሓ እስኪመለሱ ስለ ቅንነቴ በእነርሱ ላይ እታገሣለሁ እንጂ፤›› 👉በሃያ ሦስቱ የመላእክት ነገደ ሠራዊት ላይ እግዚአብሔር የሾመኝ እኔ ሩፋኤል ነኝ፤ እግዚአብሔር አብን ይቅር ባይ ልጁን አጽናኝና አዳኝ የሆነ መንፈስ ቅዱስን እናመሰግነው ዘንድ፤ በደብረ ጽዮን በሚደረገው የሺህ ዓመት ተድላ ደስታ የክብር ጽዋን በሚሰጣቸው ጊዜ ለቅዱሳኖቹ በጎ ነገርን እንድንሰጣቸው ያዘዘኝ ሩፋኤል እኔ ነኝ፡፡ ደግሞም በዚህች ቀን ከዕፀ ሕይወት ዐጽቅ ወስጄ ለተመረጡ ክርስቲያኖች በእጄ እንድንሰጣቸው እግዚአብሔር ያዘዘኝ ሩፋኤል እኔ ነኝ፡፡የሰማያት መዛግብትም ከእጄ በታች ተጠብቀው የሚኖሩ እኔ ሩፋኤል ነኝ፡፡ እኔም እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ እከፍታቸዋለሁ፤ እዘጋቸዋለሁም፡፡ 👉"በምድር ሰው ባልንጀራው ስለ ስሜ በጎ ነገር ቢያደርግ እኔ ከመከራው በችግሩ ረዳዋለሁ፤ ወይም የሹመቴን ነገር የሚጽፍ ወይም ከቅዱሳን ጋራ ስሜን የሚያስብ ወይም በስሜ ለቊርባን የሚሆነውን የሚሰጥ ወይም በበዓሌ ቀን ምጽዋትን የሚሰጥ ይኸውም እግዚአብሔር በሊቃነ መላእክት ክብር የሾመኝ ያከበረኝ ጳጉሜን ሦስት ቀን ነው፡፡ ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት እስከማስገባው በብርሃን ሠረገላ እኔ እሸከመዋለሁ፡፡ በምድር ላይ ከቶ እንደርሱ ያለ የማይገኝ መዐዛው እጀግ ጣፋጭ በሆነ ሽቱ ነፍሶቻቸው እርሱን በማሽተት ደስ እንዲላቸው አደርጋለሁ፡፡ ሐዋርያት ሆይ በእግዚአብሔር ፊት እስክትቆሙ እጠብቃችሁ ዘንድ ከእኔ ርዳታ ሹ፡፡›› 👉የዚህ የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ ሩፋኤል ተአምራቶቹ ብዙ ናቸው፡፡ በተከበረች በጳጉሜን ሦስት የጦቢትን ዓይን ያበራና የራጉኤልን ልጅ ተቆራኝቷት ከነበረው ጋኔን ያላቀቃት ይህ መላእክ ነው፣ዳግምም በጳጉሜ ሦስትም ቅዱስ ሩፋኤልም በግብጽ ሀገር የምትገኘውን በአንድ ዓሣ አንበሬ ላይ የታነጸችውን ቤተ ክርስቲያኑን ዓሣ አንበሬው እንዳይገለብጣት ያጸናበትም የተአምር ዕለት ነው። በዚህ ዕለት ቀላያተ ምድር ሁሉ በመልአኩ በበትረ መስቀሉ ይባረካሉ። ስለዚህም ስለ እኛ ይማለድልን ዘንድ የበዓሉን መታሰቢያ ልናደርግ ይገባል፡፡ በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን! ምንጭ:- ድርሳነ ሩፋኤል፣ መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ጳጉሜን
نمایش همه...
#ቅዱስ_ሩፋኤል ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥ #ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇 •➢ ሼር // SHARE ቅዱስ ሩፋኤል ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲኾን፤ ሩፋ ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው፤ ሄኖክም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ይለዋል (መጽሐፈ ሄኖክ 6፥3)። ይኽ መልአክ በራማ ሰማይ ያሉ ነገደ መናብርትን የሚመራቸው ነው፡፡ ነገደ መናብርት ያላቸው ቅዱስ ሩፋኤል የሚመራቸው በራማ ሰማይ የሚኖሩ ነገደ መላእክት ናቸው፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ “ወለዳግም ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ መናብርት ወሊቆሙ ሩፋኤል እሉ እሙንቱ እለ ይቀልል ሩጸቶሙ እምነፋስ ወእለ ይጸውሩ ወላትወ መብረቅ ወኲናተ እሳት ዘይነድድ ወአንበሮሙ በዳግሚት ሰማይ” ይላል በራማ ሰማይ የሚገኘውን ኹለተኛውን ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፤ እነዚኽም ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ በራማ በኹለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ከሚመራው ከዚኽ ነገድ 24ቱ ካህናተ ሰማይ ወጥተዋል፡፡ አባ ጊዮርጊስም በሰዓታቱ ላይ፡- “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጽርሐ አርያም ማኅፈዱ መካነ ትጉሃን ዐጸዱ ካህናተ ሰማይ ቅዉማን በዐውዱ አክሊላቲሆሙ ያወርዱ ቅድመ መንበሩ እንዘ ይሰግዱ ይርዕዱ ወኢይዝብጦሙ ሶበ ይበርቅ ነዱ” (ጽርሐ አርያም አዳራሹ፤ የትጉሃን መኖሪያ ቦታው የሚኾን እግዚአብሔር ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ተብሎ በአንድነት በሦስትነት ይመሰገናል፤ ካህናተ ሰማይ በዙሪያው ይቆማሉ፤ በዙፋኑ ፊት እየሰገዱ አክሊሎቻቸውን ያወርዳሉ፤ እሳትነቱ (ባሕርዩ) በሚበርቅ፣ ወገግ በሚል ጊዜ እንዳይመታቸው ይንቀጠቀጣሉ) ይላል ሊቁ እንደጠቀሰው በዕለተ እሑድ ሥሉስ ቅዱስ ሰባቱን ሰማያት ፈጥረዋል፤ ከዚያም ልዑል እግዚአብሔር በዕለተ እሑድ ሰባቱን ሰማያት ከፈጠረ በኋላ ሊቁ በአክሲማሮስ እንደገለጸው ከቅዱሳን መላእክት መኻከል፡- “ወእምዝ ነሥአ እግዚአብሔር እምሰራዊተ ሩፋኤል ፳ወ፬ተ ሊቃናተ ወአቀሞሙ ዐውደ መንበሩ፤ ወሰመዮሙ ለእሙንቱ ካህናተ ሰማይ ወወሀቦሙ ማዕጠንታተ ዘእምወርቀ እሳት ወአክሊላተ ብርሃን ዘእምጳዝዮን ወአብትረ ዘከተማሆን መስቀል ወአልበሶሙ አልባሰ ክህነት” ይላል ከሰራዊተ ሩፋኤል ፳፬ት ሊቃናትን መርጦ በመንበረ ስብሐት በመጋረጃዋ ውስጥ ዙሪያዋን ክንፍ ለክንፍ ገጥሞ አቁሟቸዋል (ሕዝ ፩፥፲፩-፲፪)፤ ቊጥራቸውን ኻያ አራት ማድረጉ በኻያ አራቱ ጊዜያት ጸልየው ሌላውንም ራሳቸውንም ጠብቀው ዋጋቸውን ተቀብለው የሚኖሩ በመኾናቸው ሲኾን እነዚኽንም መላእክት “ካህናተ ሰማይ” ሲላቸው የእሳት የወርቅ ጽና ሲያሲዛቸው የብርሃን አክሊል ጳዝዮን የሚባል የብርሃን ዘውድ ደፍቶላቸዋል፤ የብርሃን ዘንግ ማኅተሙ መስቀል የኾነ ሲያሲዛቸው የብርሃን ካባ ላንቃ ሕብሩ መብረቅ የመሰለ አልብሷቸዋል ( ራእ ፬፥፬-፭፤፲-፲፩)። እነዚኽ ሰማያውያን ካህናት በአንድ ላይ ባጠኑ ጊዜ ዛሬ በክረምት ጊዜ ጉም ተራራውን እንደሚሸፍነው ከማዕጠንታቸው የሚወጣው ጢስ መልኩ መብረቅ፣ ድምፁ ነጐድጓድ፣ መዐዛው መልካም የኾነና ጽርሐ አርያም፣ መንበረ መንግሥት የተባሉትን የብርሃን ሰማያት የሚሸፍንና የሚጋርድና ከጢሱ ጋር የቅዱሳን ጸሎት ዐብሮ ወደ እግዚአብሔር ፊት ይወጣል፤ “ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሠዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሠዊያ ላይ ለቅዱሳን ኹሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ” እንዳለ ዮሐንስ በራእዩ (ራእ ፰፥፫-፭)፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በአክሲማሮስ ላይ፦ “ወቦ ኪሩቤል ይቀውሙ በየማን በአምሳለ ቀሳውስት ወሱራፌል ይቀውሙ በአምሳለ ዲያቆናት ወድኅሬሆሙ ካህናተ ሰማይ ወቦ እልፍ አእላፋት ወትእልፊተ አእላፋት መብረቅ ወነጐድጓድ ወሠረገላሆሙኒ ምሉኣነ አዕይንት” እንዳለ ኪሩቤል በቀኝ ሱራፌል በግራ ከፍ ብለው ካህናተ ሰማይ ክንፍ ለክንፍ ገጥመው በስተኋላቸው ሲታዩ በሰማይ ውዱድ ዙሪያ እልፍ አእላፋት መብረቅ፣ ነጐድጓድ፣ ሠረገላ፣ እንደ መስታየት ብሩህ የኾነ ሲኖርበት እነዚኽ ቅዱሳን መላእክትም ሳያቋርጡ “ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ እግዚአብሔር” እያሉ ፈጣሪያቸውን በአንድነቱ በሦስትነቱ ያመሰግኑታል (ራእ ፬፥፰)፡፡ ሊቁ ቅዱስ ባስልዮስም ስለነዚኽ ቅዱሳን መላእክት ሲገልጽ “ወኲሎሙ ሰራዊተ መላእክት እለ ይቀውሙ ቅድሜሁ ይጸርሑ ወይባርክዎ ለእግዚአብሔር…” (በፊቱ የሚቆሙ የመላእክት ሰራዊትም ኹሉ ጩኸው ያመሰግኑታል፤ የመላእክት አለቆችም ለማይታይ ለባለዚኽ ስም ዘንበል ብለው ይሰግዳሉ፤ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑና የሚዘምሩ ዙፋኑን የሚሸከሙ አርባዕቱ እንስሳ ጩኸው ያመሰግኑታል፤ ዕጣንን የተመሉ የወርቅ ማዕጠንት በእጆቻቸው ያለ ኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ይኸውም የቅዱሳን ጸሎት ነው እስከ ዘላለሙ ሕያው በኾነው ፊት የሚቀበለው መሥዋዕት አድርገው ወደ ላይ ያሳርጋሉ) በማለት የቅዱሳንን ጸሎት ቅድመ እግዚአብሔር በማዕጠንታቸው ለማሳረግ የተመረጡት መላእክት ኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይ መኾናቸውን አስተምሯል፡፡ ይኽ መልአክ ጦቢትን የተራዳ መልአክ ነው፤ ይኽ ጦቢት ዐሥሩ ነገድ በ፯፻፳ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ሲማረኩ ዐብሮ የተማረከ ጻድቅ ሰው ነው፤ ይኽ ሰውን በመርዳት በደግነቱ የታወቀው ጦቢት ከመንገድ ወድቆ የተገኘ በድን ቀብሮ፤ በዚያው ሌሊት ከቅጥሩ አጠገብ ፊቱን ተገልጦ ተኝቶ ሳለ አዕዋፍ ትኩስ ፋንድያ ዐይኑ ላይ ጥለውበት እንደ ብልዝ ያለ ወጥቶበት ዐይኑ ጠፋ፤ ሚስቱም ባለማስተዋል “አይቴ ውእቱ ምጽዋትከ ወጽድቅከ” (በጐነትኽ ምጽዋትኽ ያዳነኽ ወዴት ነው?) በማለት በተናገረችው ጊዜ ዐዝኖ ሞትን ተመኘ (ጦቢ ፪፥፲፬)፡፡ ያን ጊዜ መልአኩ ሩፋኤል ርሱንና ባሎቿ ስለሞቱባት ቤተሰቦቿ ያንቋሽሿት የነበረችውን የራጉኤል ልጅ ሳራን ለማዳን ተልኮ በመምጣት አስቀድሞ በርሷ ላይ ዐድሮ ባሎቿን ይገድልባት የነበረውን ጋኔን አስወጥቶ የጦቢት ልጅ ጦብያ እንዲያገባት አድርጓል፤ በዚኽም “ፈታሔ ማሕፀን” ተብሏል፡፡ በኋላም ወደ ጦቢት በመኼድ ረዥም ዘመን የታወረ ዐይኑን አብርቶለት “አነ ውእቱ ሩፋኤል መልአክ አሐዱ እምነ ሰብዐቱ ቅዱሳን መላእክት” (ከሰብዐቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሩፋኤል እኔ ነኝ) ብሏቸው ተሰውሯል (ጦቢ ፲፪፥፲፭)፡፡ ✍በመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ የቅዱስ ሩፋኤል ረድኤት በረከት ይደርብን አሜን 🙏 ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥ •➢ ሼር // SHARE// ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━@kedeyeenate━━━━━━━━━━━━━━━
نمایش همه...
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

✞ በየጊዜው አዳዲስ መንፈሳዊ ➢ ፅሁፎች ➢ መዝሙሮች ➢ ኦርቶዶክሳዊ መልእክቶች ➢ መንፈሳዊ ነገሮችን ሁሉንም ለማግኘት ከፈለጉ ተቀላቀሉን ✞ ❑• @Z_TEWODROS •❒ ➢ ሁሉም እንዲያነበው SHARE ያርጉ ! እናመሰግናለን ! • እንዲሁም ግሩፓችንን የኪዳነምህረት ልጆች ይቀላቀሉ ❤! • @kidanameherat16 •

convert_1599462692202.mp33.65 MB
​​​​ጳጉሜን ጳጉሜን የሚለው ስያሜዋ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ጭማሪ ማለት ነው፡፡ በግእዝ ተውሳክ ማለት ሲሆን ተውሳክ ማለት ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ “ወሰከ - ጨመረ” ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ ሌሎች ሀገሮች ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ያደርጓታል፡፡ ይኸውም ይታወቅ ዘንድ እኛ የወርን ቁጠር 30 ስናደርግ እነርሱ 31 ብለው የሚቆጥሩት ወር አላቸው፡፡ ይኹን እንጂ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ሳያደርጉ የዓመት ተጨማሪ አድርገዋታል፡፡ ጳጉሜን በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ትመጣለች፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ በዘመነ ዮሐንስ መግቢያ ጳጉሜን ስድስት ቀን ትሆናለች፡፡ በዚህም ሀገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ /Thirty months of sunshine/ በመባል ትታወቃለች፡፡ ጳጉሜን ስድስት በምትሆንበትም ጊዜ ጾመ ነቢያት /የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈትቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡ በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜን ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው። ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዎች ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፥2-7፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋት በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡ ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲ 8፥2፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡ ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡ የጳጉሜን ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብባትም ወር ነች፡፡ ይህም ጳጉሜን የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር
نمایش همه...
✍️✍️✍️ ❝አትገረምም!❞ ***** አየህ አገልግሎት ገደብ የለውም! ዕድሜ፣ ቦታ፣ ስራ፣ ትዳር፣ ሁኔታ፣ ሌላውም ምክንያት አይገድበውም። ይህን መልዕክት የምትመለከተው ወንድሜ ሆይ ያኔ በልጅነት ሰንበት ትምህርት ቤት ያሳለፍከውን ጊዜ አስብ፤ መልዕክቱን የምታነቢውም እህቴ፣ ያን የማይረሳ የአገልግሎት ዘመን አስቢው! ዝማሬ ለመቆም፣ መዝሙር ለማጥናት፣ ያሬዳዊ ዝማሬን አጥንቶ ለማቅረብ፣ ድራማ እና ጭውውት ለመስራት፣ አልባሳት ለብሶ ለመዘመር፣ በየበዓላቱ በአልባሳት ደምቆ ቄጤማ እና ዘንባባ ይዞ በየከተማው እየዘመሩ ለመሄድ፣ በየወርሃዊ የዝክር መርሐግብሮች ላይ ጸበል ጸድቅ ለመቃመስ፣ በየልቅሶው ቤት አጽናኝኝ እመአምላክ እያሉ እየዘመሩ ሐዘንተኞችን ለማጽናናት፣ የታመሙትን ድውይ ነኝ አንተ አድነኝ እያሉ እየዘመሩ በሽተኞች በሽታቸውን እንዲረሱ ለማድረግ፣ በየሰርጉ ላይ መርአዊ ሰማያዊ እያሉ ለማጀብ፣ በየንግሱ ታቦታቱን በአልባሳት አሸብርቆ ለማጀብ ያለህን ፍቅር እና ፍላት ቅናት እና መነሳሳት አስበው ወንድሜ። እስኪ ትዝ ይበልሽ እህቴ! ዛሬስ? ዛሬማ ትልቅ ሆንና! መንግስት ሰራተኞች ደመወዝተኞ ሆንና! ዛሬማ ጊዜ የለንማ፣ ትላልቆች ሆነን አግብተን ወልደን ከበድና፣ ዛሬማ ዕድሜያችን ገፍቶ አልባሳት ለብሶ ማገልገል ያሳፍረናላ፣ ጡረታ ወጣና! ያሳዝናል። ግን የቤተክርስቲያን ፍቅር እና አገልግሎት በእውቀት ለገባው ምንም ነገር ላለማገልገል ምክንያት አይሆነውም። ብዙዎች መንፈሳዊው እውቀት ላይ ደካሞች ስለሆኑ ተበተኑ። የገባቸው ግን ምንም አይገድባቸውም። ልክ እንደኚህ አባት! ለአባታችን ረዥም እድሜ ከጤና ጋር ያድልልን! / በአንዲት ቅድስት ቤተክስቲያን እናምናለን // ወስብሐት ለእግዚአብሔር
نمایش همه...
#ደብረ_ታቦር ደብረ ታቦር ከገሊላ ባሕር በምዕራባዊ በኩል 10 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ተራራ ሲሆን፤ ከፍታው ከባሕር ወለል በላይ 572 ሜትር ይሆናል፡፡ በዚህ ተራራ ላይ ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን እንደሚገልጽ ምሳሌና ትንቢት ተነግሯል፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በትንቢቱ “#ታቦርና #አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል” ብሎ የተናገረው ትንቢት እንዲፈጸም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራቱን በዚህ ተራራ ላይ ገልጧል /መዝ. 88፥12/፡፡ በዘመነ መሳፍንት ባርቅ ሲሣራን ከነሠራዊቱ ድል ያደረገው በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ነው፡፡ ምሳሌነቱም ባርቅ የጌታችን ሲሣራ ደግሞ የአጋንንት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር ክብሩን በመግለጥ በአይሁድ እያደረ አምላክነቱን እንዲጠራጠሩ ያደረጋቸውን አጋንንት ድል የማድረጉ ምሳሌ ነው /መሳ. 4፥6/፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን በቂሳርያ “የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?” ብሎ ከጠየቃቸው ከስድስት ቀን በኋላ #አዕማድ ተብለው የሚጠሩ ሦስቱን ሐዋርያት ይዞ ወደ ረጅም ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ በፊታቸውም ተለወጠ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ፡፡ እነሆም #ሙሴና #ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው፡፡ ቅዱስ #ጴጥሮስ መልሶ ጌታችን ኢየሱስን ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፡፡ ብትወድስ በዚህ #ሦስት ዳስ እንስራ አንዱን ለአንተ አንዱን #ለሙሴ አንዱን #ለኤልያስ አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፡፡ ከደመናውም በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት የሚል ድምፅም ተሰማ፡፡ ሐዋርያት ይህንን ሰምተው የጌታችንን መለኮታዊ ክብር አይተው በፊታቸው ወደቁ እጅግ ፈርተው ነበር፡፡ ጌታችንንም ተነሡ አትፍሩም አላቸው፡፡ በዚህ መልኩ አምላክነቱን ገለጠላቸው /ማቴ. 17፥1-10/፡፡ ፠፠፠ #አዕማደ_ሐዋርያት_(#ጴጥሮስ፣ #ያዕቆብና #ዮሐንስ )#ለምን_ተመረጡ "አዕማደ ሐዋርያት ተብለው የተጠሩት #ጴጥሮስ፣ #ያዕቆብና #ዮሐንስ ናቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ጴጥሮስ፣ ዮሐንስና ያዕቆብን “አዕማድ ሐዋርያት” እያለ ጠርቷቸዋል /ገላ. 2፥9/፡፡ ስያሜውን ያገኙበት ዋናው ምክንያት የኢየሩሳሌምን ቤተ ክርስቲያን በሓላፊነት ያስተባብሩ ስለነበረ ነው፡፡ ከዚህን በተጨማሪ ጌታችን በኢያኢሮስ ቤት ልጁን ሲፈውስ፣ በጌቴ ሴማኒ ሲጸልይና በደብረ ታቦር ምስጢረ መለኮቱን ሲገልጥ ከእሱ ስላልተለዩና ይዟቸው ስለሔደ ነው /ማር.5፥37-43/፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሦስቱ ደቀ መዛሙርት የተመረጡበትን ምክንያት ሲያትቱ እንዲህ ብለዋል፡፡ ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ሹመት፣ ሽልማትና ክብር ፈላጊዎች ነበሩ፡፡ ከዚህ ሃሳብ እንዲወጡ ከብልየታቸው እንዲታደሱ ለይቶ አውጥቷቸዋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለድኅነተ ዓለም የመጣው በሕማማቱ በሞቱ ቤዛ የሚሆነን አምላክ “ልሰቀል ነው” ባላቸው ጊዜ “አይሁንብህ” ብሎት ነበር፡፡ እንዲህ ያለው ሃሳብ የጠላት እንጂ የሰው ልጆች ሊሆን አይችልም ከሞቱ በቀር ድኀነት ሊያስገኝልን የሚችል የለምና፡፡ ደቀ መዝሙሩ ግን ከሞተ ክብሬ ምንድን ነው ብሏልና “አይሁንብህ” አለ፡፡ /ማቴ. 16/ በሌላም ስፍራ እንዲሁ “ሁሉን ትተን ተከተልንህ እንግዲያስ ምን እናገኝ ይሆን?” በማለት ይጠይቃል፡፡ /ማቴ.19/፡፡ ጌታ ግን ዋጋችሁ #ሰማያዊ #ክብራችሁ ዘላለማዊ ነው ሲል እስከ ፍጹማን መዓርግ /ነጽሮተ #ሥሉስ ቅዱስ/ አድርሶ ብርሃነ መለኮትን ገልጦ ተስፋውን ነገራቸው፡፡ ሁለቱ ወንድማማች ደቀ መዛሙርትም እናታቸውን ልከው ሹመት ሽልማት መዓርግ ለምነዋል፡፡ ስለዚህም ጌታችን በደብረ ታቦር “በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው ነገር” ስለሞቱ እንዲነጋገሩ አደረገ፡፡ ሞቱ እርግጥ ሆነ ማለት ነው፡፡ አባቱም “ኦሆ በልዎ ለክርስቶስ”፤ እሺ በሉት እርሱን ስሙት ሲል፡፡ ሞቱ እርግጥ በመሆኑ ከልባቸው እንዲጠፋ መርጦ ወደ ቅዱስ ተራራ ይዟቸው ወጥቷል፡፡ “እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም” እንዲል /ሚል 3፥6/ በእርሱ ዘንድ ወረት የለም፡፡ አስቀድሞ ከተዓምራቱ ከምሥጢሩ አይለያቸውም ነበርና ብርሃነ መለኮትን ለማየት አበቃቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ለማወቅ፣ ለመማር፣ ለመጠየቅ ያሳዩት ትጋት ምስጢር ተገልጦላቸዋል፡፡ ይህ ምስጢር ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት ተገልጦ የሚቀር አይደለም፡፡ እስከ ዓለም ፍፃሜ እግዚአብሔር ለመረጣቸው ሲገለጥ፣ በመረጣቸውም ሲነገር የሚኖር ነው፡፡ደቀ መዝሙሩ ጴጥሮስ “አልክድህም አልተውህም” የሚለው /ማቴ. 26፥35/ ቢወድደው አይደለምን? ፍቅሩን መግለጡ ለክብር አብቅቶታል፡፡ ሁለቱ ደቀ መዛሙርትም “ጽዋዬን ልትጠጡ አትችሉም” ቢላቸውም /ማቴ. 20፥22/ አንዳችን በቀኝ ሌላችን በግራ ሆነን አብረንህ እንሞታለን ሲሉ በምስጢር ለምነዋል፡፡ ሞታቸውን ከሞቱ ጋር መደመራቸው ፍቅራቸውን መግለጣቸው ነው፡፡ ፠፠፠ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like
نمایش همه...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.