cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

🇨🇬 ደጉ ሳምራዊ (ኢትዮጵና ቅድስት ቤተክርስቲያን )

#ደጉ_ሳምራዊ የተገፊዎች ድምፅ ነው!!! -ህዳር 2-2013 ዓ.ም @Ethio_Betecrstian ለአስተያየትዎ ➧➧ @gebretsadik24_bot ላይ ቢጽፉልን ከእኛ ጋር ይደረሳል።

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 466
مشترکین
-124 ساؚت
-57 عوز
-2730 عوز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

የጻድቃኗ ማርያም፥ በክርስቶስ ቀኙ፥ የምትቀመጪ፣ የልጅሽ ልጅ እኔ፥ ኀጢአቴ ገድቦሽ፥ ወደ እኔ ባትመጪ፣ ክፋቴ ከልሎሽ፥ ከኖርሽበት ቤቴ፥ ምንም ብትወጪ፣ በመንፈስ ነይና፥ በልቤ ምጥማቅ ላይ፥ ከሩቅ ተገለጪ። (ኤፍሬም የኔሰው ) @Ethio_Betecrstian
نمایش همه...
ከአዳም ጎን ሞት ተገኘ ከክርስቶስ ጎን ሕይወት ተገኘ። የአዳም ጎን አጥንት ለአዳም ሚስቱ እንደሆነች በጌታም ደም ቤተ ክርስቲያን ተመሠረተች።
نمایش همه...
"ሰይጣንም የአንቺን ምስጋና ወሬ ሲሰማ በብስጭት ጥርሱን ያፏጫል፤ የምስጋናሽ ወሬ በእርሱ ዘንድ መራጃ ነውና እራሱን ይቆርጠዋል፡፡ ከስምሽ አጠራር የተነሣ መብረቅ በኃይል ሲጮህ እንደ ሰማ ሁሉ ይደነግጣል፡፡ አንቺ ከተወለድሽ ጀምሮ ፈጽሞ ዕረፍት አላገኘም፡፡ በአንቺ ታመመ በልጅሽም ተጨነቀ በአንድ ልጅሽ መስቀል ሥቃይ አገኘው፡፡ ከፍጡራን ወገኖች ሁሉ ይልቅ ሰይጣል አንቺን ይጠላል፡፡" #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
አማን በአማን አማን በአማን ተወልደት አማን በአማን አማን በአማን/፪ ጊዜ/ ተወልደት እመ ብርሃን ተወልደት እመ ብርሃን/፪ ጊዜ/
نمایش همه...
ክርስቶስን መውደድ እንዴት? (በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) አንድ በጣም የምንወደው እንግዳ ወደ ቤታችን ሲመጣ እጅግ በጣም ከመደሰታችን የተነሣ የምናደርግለት ኹላ ሊጠፋብን ይችላል፡፡ እንደምንወደው፣ እንደናፈቀን እንነግሯለን፡፡ ከዚያም በላይ የሚወደውን እናቀርብለታለን፡፡ ባይኖረን እንኳን ስላላቀረብንለት እናዝናለን፡፡ ያለንን፣ ቤት ያፈራውን ግን እናቀርብለታለን፡፡ ስለምንወደውና ስለናፈቀን ርሱን የሚያስከፋ ነገር ምንም አናደርግም፡፡ ብናደርግም ወዳጃችንን ኾን ብለን ለማስከፋት ብለን የምናደርገው አይደለም፡፡ እንወዷለን የምንለው እንግዳችንን ትተን ሌላ ሥራ አንሠራም፡፡ በቃላት ብቻ እወድኻለኁ ብንለው፥ ነገር ግን በተግባር እንግዳችንን መውደዳችን ባንገልጥ ግን እንግዳችን ያዝንብናል፡፡ ከቃላችን በላይ ተግባራችንን ስለሚያይም እንደምንወደው ብንነግረውም አያምነንም፡፡ መውደድ የቃላት ጨዋታ ሳይኾን በተግባር የሚገለጥ ነውና፡፡ ልክ እንደዚኹ ፍጹም ሰው ኾኖ፣ ባሕሪያችንን ባሕርይ አድርጐ ወደ እኛ የመጣውን ክርስቶስን እንደምንወደው እየተናገርን፥ ነገር ግን በተግባር የምናሳዝነው ከኾነ መውደዳችን ትክክለኛ መውደድ አይደለም፡፡ ብንወደው ኖሮ ልክ ከላይ እንደገለጥነው እንግዳችን የሚበላ ነገርን እናቀርብለታለን፡፡ የክርስቶስ መብሉስ ምንድነው? እርሱ እራሱ እንዲኽ ሲል ነግሮናል፡- “የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው” /ዮሐ.4፡34/፡፡ ተርቦ ስናየው የሚበላ ነገርን እንስጠው፤ ተጠምቶ ስናየው የሚጠጣ ነገርን እንስጠው፤ ርሱም ይቀበለናል፡፡ የሚቀበልንም ስለሚወደን ነው፤ ከማንወደው ሰው ስጦታን አንቀበልምና፡፡ ስጦታችን ትንሽ ሊኾን ይችላል፤ ነገር ግን አፍቃሪያችን ነውና ስለ ስጦታችን ታናሽነት አልቀበላችኁም አይለንም፡፡ ስጦታችን በርሱ ዘንድ ትልቅ ነው፡፡ በስንፍና አንያዝ እንጂ ስጦታችን አምስት ሳንቲምም ልትኾን ትችላለች፤ ርሱ ግን ወዳጃችን ነውና አምስት ሳንቲም ናት ብሎ ስጦታችንን አያቃልላትም፡፡ እንደ ድልብ ስጦታ አድርጎ አምስት ሳንቲሟንም ይቀበልልናል እንጂ፡፡ ስጦታችንን የሚቀበለው ድኻ ስለኾነ አይደለም፡፡ ስጦታችንን የሚቀበልልን ስለ ስጦታችን ታላቅነት ሳይኾን ስለ ልቡናችን ኀልዮት (intention) ነው፡፡ ስለዚኽ ስንሰጥ ክርስቶስ ስለተቀበለን ትንሽዋንም ስጦታችንን ይቀበል ዘንድ በቤታችን ታዛ ስለገባ ልናመሰግነው ይገባል፡፡ እውነተኛ ሐሴት ማለትም ይኸው ነው፤ በመቀበል ሳይኾን በመስጠት የምናገኘው፡፡ ወደ ቤታችን፣ ወደ ሕይወታችን የመጣው ለእኛ ሲል ነው፡፡ ነፍሱን አሳልፎ ለሞት የሰጠው ለእኛ ሲል ነው፡፡ ፍቅሩ ግን እዚኽ ላይ አላበቃም፡፡ አኹንም እኛ ጋር እየመጣ ነው፡፡ ሐዋርያው “ስለ ክርስቶስ መልእክተኞች ነን” ብሏል /2ኛ ቆሮ.5፡20/፡፡ ስለዚህ ተርበውና ተጠምተው ወደ እኛ የሚመጡት ሰዎች የክርስቶስ መልእክተኞች ናቸው ማለት ነው፡፡ የንጉሡን መልእክተኛ፡የሚያባርር ታድያ ማን ሞኝ ነው? ነገር ግን ብዙዎቻችን ሞኞች ኾነናል፡፡ የነገሥታት ንጉሥ የክርስቶስ መልእክተኞችን እያባረርናቸው ነውና፡፡ ክርስቶስን እንወድኻለን እያልን በተግባር ግን እናባርረዋለን፡፡ ከዚኽ የበለጠ ምስኪንነት ከወዴት ይገኛል? ክርስቶስን በቃል እወድኻለኁ እያሉ በተግባር ግን ርሱን ማባረር የማይጠቅም ብቻ ሳይኾን የሚጐዳን ጭምር ነው፡፡ እንኪያስ ተወዳጆች ሆይ! ክርስቶስን በቃልም ገቢርም እንውደደው፡፡ በታላቁ እንግዳችን በክርስቶስ ደስ መሰኛታችንን በተግባር እንግለጠው፡፡ ይኽን እንድናደርግ ርስቱንና መንግሥቱንም እንደ ቸርነቱ እንዲያወርሰን እኛን በመውደዱ ወደ እኛ የመጣው ደግሞም የሚመጣው ክርስቶስ ይርዳን አሜን!!! @Ethio_Betecrstian
نمایش همه...
🌾እ 🌾ን 🌾ኳ 🌾ን ለ ብ ር ሃ ነ ❤️ ❤️ ❤️ ❤️ 🌹ት🌹 🌺🌺 🌺🌹 🌹🌸 🌸🌸 በሰላም❤️ን❤️አደረሳችሁ 🌲 ሳ 🌷 🌲 ኤ🌷 🌲ው🌷 🌲፡፡🌷 ለሁላችን 🌹🌹🌹መ🌸 🌳ል🌸 🌳ካ🌸 🌳ም🌸🌹🌹 በዓል 🍁🍁 🌷ኦ🌿 🌷ር🌿 🌷ቶ🌿 🌷ዶ🌿 🌷ክ🌿 🌷ስ🌿 💐ተ🌾 💐ዋ🌾 💐ህ🌾 💐ዶ🌾 🌹🌹🌹🌹🌹🌹 💐 ❤️ በሀገር🌺 🌸 💐ው❤️ 🌺ው🌸 💐ስ❤️ 🌺ጭ🌸 💐ጥ❤️ 🌺 ም🌸 💐ም❤️ 🌺 ያ🌸 🌺 ላ🌸 🌺ች 🌸 🌺 ሁ🌸 በ❤️ ስ❤️ ደ🌸🌸🌸🌸 ትበጎዳና በአልጋ 💐በ 💐ጭ 💐ን🌺🌺🌺🌸 💐ቅ በ መ ከ ራ🌸 🌷 በ 🌹ያ 🌷ዱ 🌹ላ 🌷ር 🌹ች 🌷 በ 🌹ሁ❤️❤️ 🌷ዋ 🌹መ በ 🌸 🌷 ሻ 🌹ል ዓ🌸 🌹ካ ም ል🌺 🌸🌺🌺 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 @Ethio_Betecrstian 🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ንጹሐት የሆኑ እግሮችህን አቅፋቸው ዘንድ ስጠኝ። ከእርሳቸውም የሕይወት መዓዛ አሸት ዘንድ፤ ከዐይኖቼ በሚፈስ ዕንባ አርሳቸው ዘንድ፤ በራሴ ጸጉርም አሻቸው ዘንድ ኃጢአትህ ተፍቆልሃል፤ በሰላም ሂድ ትለኝ ዘንድ፤ ይህንን ስለ ተቀደሰው ስምህም በሕይወት መጽሐፍ ይጻፍ ትለኝ ዘንድ ተቀደሰው ስምህ ያለዋጋ ስጠኝ። የደቀ መዛሙርትህን እግር ያጠብህ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከኃጢአቴና ከበደሌ እጠበኝ። በላዬም የንስሐ ውኃን እርጨኝ፤ ከበረድ እጅግ እነጻ ዘንድ። ግብረ ሕማም ዐምዳዊው ስምዖን ድርሳን 
نمایش همه...