cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

የልቤ ድርሰት የብዕር ጠብታ

Well come😊 ✍ትኩረት ነጥቦች ፩ ፦ግጥም ፪፦ድርሰት ፫፦ፍልስፍና ፬፦ስዕል ፭፦ሙዚቃ ፮፦ስሜት ፯፦ፎቶ ✍አላማ ~> በዚህ ቻናል አዳማጭ ያጡ ልቦችን እናንኳኳለን ከዝምታው አለም እንዲወጡ ፣ የልባቸውን ድርሰት የብዕራቸዉን ጠብታ እንዲያጋሩ ፣ የዉስጥ እረፍት እንዲያገኙ እና ወደ ወደፊት ህልማቸው አንድ እርምጃ እንዲጠጉ ማድረግ ነው። inbox @amanytz የሁሉም ሰው ልብ ደራሲ ነው!!❤

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 997
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-127 روز
-6230 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
. . ቤተሰቦች🤗 #4 ሳለኝ ብላቹህ ከላካቹህልኝ መካከል እንሆ ጀባ..🤲 join and share @YelbeDrset @YelbeDrset 👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨 inbox me @aman116 👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
. . ቤተሰቦች🤗 #3 🖤🖤🖤🖤R.I.P🖤🖤🖤🖤 join and share @YelbeDrset @YelbeDrset 👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨 inbox me @amna116 👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ሳለኝ ብላቹህ ከላካቹህልኝ መካከል እንሆ ጀባ..🤲
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ቤተሰቦች እንደምን ሰነበታቹህ?🤗 ስለጠፋሁ ይቅርታ!🙏 ሳለኝ ብላቹህ ከላካቹህልኝ መካከል እንሆ ጀባ..🤲 ይሄንን ስዕል ጨምሮ አብዛዋቻቹህ የላካቹህልኝ ፎቶ ጥላና ብርሃኑ በደንብ እማይለይ ስለሆነብኝ ከላካቹህልኝ መካከል አምስት(5) ብቻ መርጨ በሚቀጥሉት ቀናት ሰርቼ እማቀርብላቹህ ይሆናል..!!🙏🙏🙏
نمایش همه...
ቤተሰቦች🤗 ለስዕል ብላቹህ የላካቹህልኝ ፎቶ ከቀጣይ ስድስት ቀናት በኋላ መስራት እንደምጀምር ልነግራቹህ እወዳለሁ። ይህ ለምን ሆነ ብትሉ ሌላ ቦታ ስለሆንኩ እና ወደ ቤቴ መመለስ ስላልቻልኩ ነው። እንደተመለስኩ በየቀኑ አንድ አንድ እያደረኩ እሰራላቹኀለው።🙏 በትግስት ጠብቁ!😊🙏 join and share @YelbeDrset @YelbeDrset 👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨 inbox me @amna116 👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨
نمایش همه...
ቤተሰቦች🤗 ለመሳል ፎቶ የላካቹህልኝ አባላት በትግስት እንድትጠብቁ እጠይቃለሁ! ፎቶ ያላካቹህ አባላት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት መላክ ትችላላችሁ! እና ፎቶው ቀረብና ጠራ ያለ ቢሆን መልካም ነው። በላካቹህበት ሰዓት መሰረት እንደየ ፎቶው ጥራት ስዕሉ ይሰራና ይላክላቹሃል።✌️😊 ደህና እደሩ!😴 ፎቶ ለመላክ 👉@aman116 join and share @YelbeDrset @YelbeDrset 👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨 inbox me @amna116 👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨
نمایش همه...
እንደምን አላቹህ? ቤተሰቦች🤗 የሰሞኑን የስዕል ስራዎቼን ተጋበዙልኝ!😊🙏 ከዛሬ 14/10/2024 ዓ.ም እስከ 16/10/2024 ዓ.ም ምሽት 4 ሰዓት ደረስ እሚቆይ Free Package ስለምሰጥ ፎቶ በመላክ በነፃ ማሳል ትችላላቹህ!! ፎቶ ለመላክ 👉@aman116 join and share @YelbeDrset @YelbeDrset 👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨 inbox me @amna116 👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨👨‍🎨
نمایش همه...
አባቴ ከማውቃቸው ሰዎች ሁሉ ምስኪኑ ሰው ነው። አባቴ ዝምተኛ ነው። ዝምተኛ ነው ስል እነዚህ ማውራት እየቻሉ ምናባቱ ብለው እንደሚተውዉት ሰዎች አይደለም። እሱ የሚያወራው ነገር የለውም። ይኸው ነው። አባቴ እወንድሜ ቤት ከተማ ይመጣና ብዙ ቀን መቆየት አይችልም። ከተማ ይጨንቀዋል። እሱ የሚወደው አፈር፤ ሳር፣ ቅጠል፣ ከብቶች፣ ሰማዩና መሬቱ የሚገናኙበትን አድማስ ማየት። በቃ። አባኮ ጭምት ከመሆኑ የተነሳ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ልጆቹን በስማችን አይጠራንም ነበረ። ስሜን ስለማያውቀው ነው ወይስ መጥራት ያፍራል? እያልኩ የማስብበት ወቅት ነበረኝ። ከፈለገኝ ዝም ይልና “አቡሽ” ይለኛል😂 Not anymore tho. Now he calls me by my name, አዳም ይለኛል። የኔ አባት ይሄ ሁላ ዘመን ሲፈራረቅበት እንዴት አድርጎ በዝምታ እንደሚያሳልፈው አላውቅም። ትንሽ አረቄ ከጠጣ ብቻ ይጫወታል። እንደኔ ጭንቅላቱ አልኮሆል አይችልለትም። ሁለት ከጠጣ በቃ። እናቴ ትናደዳለች ከዛ። ራስህ አይችልምኮ ለምን ትጠጣለህ ብላ ትቆጣዋለች። ገንዘብሽን ጨረስኩብሽ አይደለም? ይላል። አልነካብሽም ሁለተኛ ይላል። እኔ እስቃለሁ። ብቸኛው ድምጹን ከፍ አርጎ የሚያወራበት ሰዓት ያን ጊዜ ነው። 'አባ የምሥራቅ በር’* ሰዓት አያስርም። ስልክም አይጠቀምም። ምን ሊያደርግለት። ዝም ብሎ ማረስ፣ መዝራት፣ ማረም፣ መኮትኮት፣ ማጨድ፣ መውቃት.... ካመት እስካመት። በቃ። ድንገት ትዝ ባለኝ ቀን ስለሱ አስብና ያሳዝነኛል። ከገበሬው ማህበረሰብ ውስጥ ስለሚገኝ መንግሥትና እግዜር እየተቀባበሉ ደባ ይሠሩበታል። ከገበሬም ዝምተኛ እና ጭምት ስለሆነ ዘመናይ ነን ባዮች፣ እንዳቅማቸው ዘምናኖች በየሄደበት ብልጫ ይወስዱበታል። ኧረ ምን ላድርግህ ጌትዬ! አሁን አሁን ብዙ ጊዜ ስለማንገናኝ አልፎ አልፎ ስንገናኝ ያወራኛል። እንደሩቅ ሀገር ሰው ይጠይቀኛል ብዙ ነገር። የመጣልኝን መልስ እሰጠዋለሁ። ብዙ ጊዜ በሙሉ ዐይኑ አያየኝም። ካየኝ እፈራዋለሁ። “ይሄን ሁላ ፍቅር ተቀብዬ ምንድነው የማደርገው? ይ'ገባኛልን?” እላለሁ። አየው አየውና ለቅሶ ይከጅለኛል። ከግር እስከራሱ የሚዳሰስ ምንዱብ ነው። ስለሱ ሳስብ ጎልቶ ትዝ የሚለኝ ነገር ኩታራ ሆኜ ለበዓላት ገንዘብ ካላመጣህ ብዬ ልቡን የምሰቅለው ነገር ነው። አምጣ እለዋለሁ። የለኝም ይለኛል። አለቅሳለሁ። ነገ እሰጥሃለሁ ይለኛል። አልሄድለትም ካጠገቡ። የማይቀር ሲሆንበት ከኪሱ በፌስታል የተቋጠሩ ሳንቲሞች ያወጣል። አሥር ሳንቲሞች፣ አምስት ሳንቲሞች፣ ስሙኔ ሳንቲሞች፣ ሽልንግ ሳንቲሞች... አሥር አሥር ሳንቲሞቹ ብዙ ጊዜ አዳዲስ ነበሩ ለምን እንደሆነ አላውቅም። ከአሥር ሳንቲሞቹ ውስጥ መርጬ እወስድበታለሁ። አባቴን እንዴት እንደምወደው አስብና መልሼ እወደዋለሁ በዛ ጊዜ። ልጅ ሆኜ ካባቴ ጋር ነው የምተኛው። ለሊት ለሊት ሁሌ ሽንቴን እሸናበታለሁ። ለሊት ለሊት ሁሌ እየተነጫነጨ ይቀሰቅሰኛል። ስነቃ አልጋው ሽንት ብቻ ሆኖ አገኘዋለሁ። ቆይ ነገ ገና ሳልሸናው ነው የምነቃው እላለሁ። በሚቀጥለውም ቀን ከሸናሁት ወዲያ ነው የምነቃው። ያን ሳስታውሰው “እንዴት አይሰለቸውም?” እላለሁ። እሱ ቻይ ነው። ጭምት እዝጋቤል። ይኸ ኃይሉ የተባለ Country man ከራሱ ጋር የሚኖር ሰው ነው። በዓለም ፊት የሞተ፤ ዓለምም በሱ ፊት የሞተች። አጠገቤ ሆኖ ሩቅ እንዳለ ይመስለኛል። ጋሼ ኃይሉን ትክ ብለው የተመለከቱት እንደሆነ፡ አምላክ እስቲ ጉዳችሁን ልይ ብሎ በአንድ ጥቁር ኮስማና ሰውዬ አቋም ሆኖ የሚያደርጉትን ሁላ በዝምታ እየታዘበ ያለ ይመስላል። አይ የሱ ሥራ... *አባ የምሥራቅ በር - ከበውቀቱ ስዩም “ላባቴ” ግጥም ላይ የተወሰደ ሀረግ @YelbeDrset @YelbeDrset inbox @aman116
نمایش همه...
. . #ለእግዜር_የተላከ_ደብዳቤ! . . እንደምነህ እግዜር ሰማይ ቤት እንዴት ነው እመጣለሁ ብለህ ቆየህሳ ምነው? እኛማ... ለእልፍ አዕላፍ አለቃ ማመልከቻ ፅፈን፣ ለወፈ ሰማይ ህዝብ መድረክ ላይ ለፍፈን፣ ፆለት ቤታችንን እኛው ላይ ቆልፈን፣ የምድር አተካራ ህግጋቱን አልፈን ደብዳቤ ላክንልህ፤ አይንህን ካየነው ሁለት ሺህ ዘመን እንደቀልድ አለፈ የመምጣትህ ተስፋ እየኮሰመነ መቅረትህ ገዘፈ... እንደውም እንደውም... "በእመጣለሁ ተስፋ ሁለት ሺህ ዘመን ገትሮን ከጠፋ፣ በቀጠሮው ሰአት መምጣት ከተሳነው፣ እግዜር አበሻ ነው" እያሉ ያሙሃል... እኔ ምን አውቃለሁ... አመስግነው ሲሉ እልልታ የማቀልጥ፣ ቃሉን ስማ ሲሉኝ...ሰባኪው እግር ስር በደስታ እምቀመጥ፣ 'እግዚኦ! በሉ' ሲባል...እንባዬን የማፈስ፣ ሃሌ ሉያ ሲሉኝ...በሳቅ ልቤ 'ሚፈርስ፣ ምናምኒት እውቀት ውስጤ ያልፀደቀ፣ እንበረከክበት ጉልበቴ ያለቀ፣ እኔ ምን አውቃለሁ... ግን አንተ ደህና ነህ? ከምር እንደሚያሙት ምፅአት ቀረ እንዴ? የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ አትከፋም አንዳንዴ! የሆነስ ሆነና ሰማይ ቤት እንዴት ነው? አብረሃም ሰላም ነው...? እዛስ ቤት ገነባ ዛሬም በድንኳን ነው? እኛማ ይሄውልህ... በቤት ኪራይ ችንካር እየተሰቀልን፣ "ኤሎሄ" እንላለን ጎጆ እንድትጥልልን.... ወደላይ ገነባን ወደጎን አሰፋን፣ ወደላይም ከላይ ወደጎንም ከጎን እንደጉድ ተገፋን... ቤት ለእንግዳ ማለት ጭራሹኑ ጠፋን!! አባታችን ሙሴ እንዴት ነው ለክብሩ፣ ውቂያኖስ መክፈያው ደህና ናት በትሩ? እኛማ ይሄውልህ... እንጀራ ፍለጋ ባህር ስናቋርጥ፣ የተስፋዋን ምድር አሸዋ ሳንረግጥ፣ የትም ውሃ በላን የትም አሳ ላሰን፣ ንገርልንና በትሩን ያውሰን... እናልህ እግዜር ሆይ... ከተስፋዋ ምድር ወደሌላ ተስፋ አለን እየኳተን መሄጃው ሲገርመን መመለሻ መንገድ መቆሚያ ቦታ አጥተን...! ላባታችን ሙሴ እንደምትልልን.. "የመሄድ ዘመን ነው ባህር የመሻገር ዱላህን ላክልን" ብሎሃል በልልኝ... "ሰማይ ቤት እንዴት ነው? ዳዊትስ ደህና ነው? ዛሬም ይዘምራል? ዛሬም ይፎክራል? ሰላም ነው ጠጠሩ? ሰላም ናት ወንጭፉ? እዛስ አቅል ገዛ ጎሊያድ ተራራው ጎሊያድ ግዙፉ? እልፍ አዕላፍ ጎሊያድ ከቦን ሲደነፋ፣ ወንጭፉን ጠቅልሎ ምነው ዳዊት ጠፋ? ብሎሃል በልልኝ!! ለረከሰ ጠጠር ለሞላ ወርዋሪ፣ "ወንጭፍህን ስጠው ለዚህ ታሪክ አውሪ" ብለህ እዘዝልን...!! እንዴት ነህ ጌታ ሆይ? ሰማይ ቤት እንዴት ነው? የሙሴ አልጋ ወራሽ እያሱ ሰላም ነው? ያቆማትን ፀሃይ ግቢ ቢላት ምነው? ያው እንደምታውቀው፣ አስራ ሶስት ወራት ነው ፀሃይ የምንሞቀው ኧረ ፀሀይ በዛ፣ኧረ ፀሀይ በዛ የመጣው ወር ሀሉ ፀሀይ እያዘለ፣ የተሾመው ሁሉ "ፀሀይ ነኝ" እያለ የአስራ ሶስት ወር የግዜር ፀሃይ፣ የአስራ ሶስት ወር የሰው ጀምበር፣ ባቃጠላት ምድጃ አገር፣ ምን ታምር ሊኖር ይችላል ፀሀይ ሁኖ እንደመፈጠር ኧረ እግዜር በናትህ በጭንቅ አማላጇ፣ ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ፣ ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና፣ ሙቀት ገደለና! እናልህ እግዜር ሆይ ማጣፊያው አጥሮናል፣ ስም ያለው ሞኝ ነው ሁሉም ይጠራናል ጳውሎስ ሲሉን...አቤት ጴጥሮስ ሲሉን...ወይዬ ይሁዳ ሲሉንም አቤት እንላለን፣ ስማችንን ሸጠን...ሰላሳ ጭብጨባ እንቀበላለን ተወው የኛን ነገር...ሰማይ ቤት እንዴት ነው.... ሄዋንስ ደህና ናት? ያው የልጅ ልጆቿ በእግሯ ተተክተው የፍሬው ሲገርምህ ግንዱንም አንክተው ለፍጥረተ አዳም ባይኑ ያገምጡታል፣ ሰይጣንም ደህና ነው ኑሮ ተስማምቶታል... ሰውን ለማሳሳት ላይ ታች ማለት ትቷል፣ ሳይጠራው የሚጎርፍ ህዝብ በዝቶለታል...!! ኧረ እግዜር በናትህ በጭንቅ አማላጇ፣ ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ፣ ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና፣ ሙቀት ገደለና!!! ✍️አሌክስ አብርሃም join and share @Yelbedrset @Yelbedrset ✍✍✍✍✍✍ inbox me @aman116 ✍✍✍✍✍✍
نمایش همه...
# የጓደኛዬ ኑዛዜ ክፍል 1 ቅዱሳን መካናትን በኢየሩሳሌምና አካባቢው ለመሳለም ከባለቤቱ ጋር እስራኤል ሄዶ እንደተመለሰ ጓደኛዬ ደወለልኝና፦ “ ደኅና መጣችሁ ? እንዴት ነበር ጉዟችሁ? ስለው “አየኋት እኮ! ገሊላ ባሕር ዳር ቆማ አየኋት !”አለኝ በደስታ ሲቃ። ቀጠለና “ሀገረ ሕይወት ፣ ብሔረ ቅዱሳን ለመግባቷ ጥርጥር የለኝም፤ የጌታዬ ምህረት በዛልኝ!” አለኝ። “ምንድን ነው የምታወራው ? ማንን ነው ገሊላ ባሕር ዳር ቆማ ያየሃት ?” አልኩት ነገሩ ግራ አጋብቶኝ። ይልቅስ “ አሁን ተሎ ላግኝህ ”አለኝና ቤቴ መሆኔን ስነግረው “መጣሁ መጣሁ ” አለና ስልኩን ዘጋው። የቤቴ በረንዳ ላይ ወንበር አውጥቼ እንደተቀመጥን፦ “መጀመሪያ እንዴት እንዳየኋት ልንገርህና ማን መሆኗን ኃላ እነግርሀለሁ ። ለብዙ ጊዜ ልነግርህ እየፈለኩ ያልነገርኩህ የኑዛዜ ታሪክ አለኝ” አለ። የሄደበትን የጉብኝት ዝርዝር ከመንገር ይልቅ ሌላ ግራ የሚያገባ ጉዳይ ቢመዝም ጉጉት የሚጭር ስለሆነ፦ “በል እሽ በመሰለህ መልኩ ተርክልኝ ” አልኩት በትኩረት ለማዳመጥ መዘጋጀቴን በሚያሳይ መልክ ሁለመናዬን ወደ እርሱ አዙሬ። “እንዴት መሰለህ !ሌሊቱንና ረፋዱን የትንሳኤን በዓል በኢየሩሳሌም ካከበርን በኋላ ከሠዓት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተወልዶ ወደ አደረገበትና የማስተማር ሥራውን ወደ ጀመረበት ወደ ገሊላ አውራጃ ተጓዝን። ገሊላ ጥብርያዶስ ደርሰን ሆቴል ገብተን አረፍ አልን። ወደ 12 ስዓት አየሩ ቀዝቀዝ ሲል ከባለቤቴ ጋር ተያይዘን ወደ ጥብርያዶስ ዳርቻ ሄድን። እንደምታውቀው የጥብርያዶስ (የገሊላ ) ባሕር ክርስቶስ በጀልባ እየተመላለሰ ፣ ደቀመዛሙርቱን ያስጨነቀውን የባሕሩን ሞገድ የገሰፀበት ፣ ጴጥሮስ ተጠራጥሮ ሊሰጥም ሲል ያወጣበት ፣ በቃሉ ብዙ ዓሣ የተጠመደበት ፣ አብዛኞቹ ሐዋርያት የተጠሩበት ባሕር መሆኑን ማሰብ ልዩ መንፈሣዊ ሀሴት ያጎናፅፋል ። ይህንን እየተነጋገርን በባሕሩ ዳር ትንሽ እንደተጓዝን አንዲት እስራዔላዊት ወጣት ፊቷን ወደ ሀይቁ አዙራ በእጆቿ የጸሎት መጽሐፏን ይዛ ከፊት ወደኋላ ጎንበስ ቀና እያለች እንደ አይሁድ ልማድና ፀሎት ታደርሳለች። ወጣትነቷ ፣ ዘመናዊ አለባበሷ ፣ በባዶ እግሯ ቆማ መጸለይዋ ተዳምሮ ልዩ ትንግርት ነበር። ከእኔ ይልቅ ባለቤቴ በተመስጦ ታያት ነበር። "አየህ ይህች ልጅ ወጣት ናት፣ ዘመናዊ ናት። በዚህ በሠለጠነ ዓለም የተገኘች ባትሆንም ሃይማኖት አልረሳችም አለች በአድናቆት ። "እውነት አልሽ። እስራኤል ሃይማኖትን ከሥልጣኔ ጋር በአግባቡ ያጋባች ሀገር ናት። የጥንካሬዋም ምንጭም ማንነቷን ማክበሯ ነው። ይሁዲነት የትም አገር ይኖራል ። እስራኤል ግን ያለይሁዲነት የለችም። ይህ በወጉ ተረድተዋል' አልኳት። ባለቤቴ ቀጠለችና በስሜት ሆና፦ 'በሚቀጥለው ጊዜ ልጆቼን አምጥቼ ይህን ምሥጢር እንዲረዱ ማድረግ አለብኝ። ሃይማኖትን ጠብቆ፣ ማንነትን አክብሮ መሰልጠንና መዘመን እንደሚቻል መረዳት አለባቸው ። ያለችንን ትንሽ ገንዘብ ከማውረስ ይልቅ ይህን ባሳያቸው ለራሳቸውም ለሀገርም ኃላፊነቴን ተወጣሁ ማለት ነው' አለች። ግሩም ሀሳብ ነው!' ብያት በባሕሩ አቅራቢያ እየተዘዋወርን ውሃውን እየቀዳን ራሣችን ላይ እያፈሰስን በሀሴት አምሽተን ወደ ሆቴላችን ተመለስን። “እሺ ከዚያስ?” አልኩት ታሪኩ አልያዝልህ ቢለኝ። "ከሌሎች ተጓዦች ጋር ራታችን ተመግበን ፈጣሪን አመስግነን ወደ የክፍላችን ሄደን ተኛን። ብዙም ሳልቆይ ደስ ብሎኝ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰደኝ። ከባለቤቴ ጋር በአድናቆት ጎንበስ ቀና እያለች ጸሎት ስታደርስ ያየናት ወጣት ትመስለኛለች ። ልክ ምሽት ላይ እንዳየናት ጸሎቷን ቀጥላለች ።ቆይታ በትከሻዋ በኩል ወደኋላ የወረደው ወርቃማ ፀጉሯ ተቀይሮ አጠር ያለ የሀበሻ ፀጉር መሰለ። ቀጥ ብለው የቆሙት የእግሮቿ ባት የቆዳ ቀለም ከፈረንጅ ሊጥ መሰል ቆዳ ወደ ጠይም የሀበሻ ቆዳ ቀለም ሲቀየር ታየኝ። ድንገት ዞር ስትል በዚያች በአንዲት በጭቃና እንጨት በተሠራች ክፍል ተጥላ የነበረችው <ሰናይት> ናት። join and share @YelbeDrset @YelbeDrset
نمایش همه...