cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

✟...ገድለ ቅዱስን...✟

" ዝምታ ሃይማኖትን ትጠብቃለች ምግባርም ወደ ሰማያት ታወጣለች "

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 529
مشترکین
+124 ساعت
-17 روز
-1830 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

💥💥💥💥💥💦💦💦💦💦💦💥💥💥💥💥 #እንኳን_ለጌታችን_መድኅኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_በዓለ_ትንሳኤ_በሰላም_አደረሳችሁ   ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤       በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤            አሰሮ ለሰይጣን፤                አግዐዞ ለአዳም፤                     ሠላም፤                        እምይዕዜሰ፤                              ኮነ፤                                  ፍስሐ ወሰላም፡፡ "ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም:: 'የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል: በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ግድ ነው' እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደተናገረ አስቡ::"  (ሉቃ. ፳፬፥፭-፰)       #_ትንሣኤ_ዘክርስቶስ_የክርስቶስ_ትንሳኤ ☞  ሦስት መዓልት እና ሦስት ሌሊት በመቃብር? ☞  ሦስት መዓልት እና ሦስት ሌሊት የሞላው እንዴት ነው? ☞  እንዴት ተነሣ? ☞  ለምን በአዲስ መቃብር ተቀበረ? ☞  እንዴት በዝግ መቃብር ተነሣ? ☞  መቃብሩን ማን ከፈተው?       ጌታችን  አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድኅነተ ዓለምን በመስቀል ላይ ከፈጸመ በኋላ በአካለ ሥጋ ወደ መቃብር ወረደ ÷ ይኸውም በመቃብር ፈርሶ በስብሶ መቅረትን ሊያስቀርልን ነው፡፡ በአካለ ነፍስ ደግሞ ወደ ሲኦል ወረደ÷ ይኸውም በሲኦል ለነበሩ ነፍሳት ነፃነትን ይሰብክላቸው ዘንድ ነው፡፡ መለኮት፥ በተዋሕዶ፥ ከሥጋም ከነፍስም ጋር ነበረ፡፡ ለዚህ ነው፥ መቃብር ሥጋን ሊያስቀረው ያልቻለው፤ ሲኦልም ነፍስን ማስቀረት አልተቻለውም፡፡ ቅዱስ ዳዊት፡- « ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተዋትም» ያለው ይኽንን ታላቅ ምሥጢር በትንቢት ቃል ሲናገር ነው፡፡ መዝ ፲፭÷፲፡፡ ሐዋርያው  ቅዱስ ጴጥሮስም፡- «ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር (ወደ አብ÷ ወደ ራሱና ወደ መንፈስ ቅዱስ) እንዲያቀርበን፥ እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት (ስለ ሰው ልጆች ኃጢአት ተላልፎ በመሰጠት) ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ (በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ለየ)÷ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ÷ (ያን ሥጋ ነፍስ እንድተለየችው መለኰት አልተለየውም)÷ በእርሱም ደግሞ (መለኰት በተዋሐዳት ነፍስ) ሄዶ በወኅኒ ለነበሩት ነፍሳት ሰበከላቸው፤» ብሏል። ✞ #ሦስት_መዓልት_እና_ሦስት_ሌሊት_በመቃብር✞ ጌታችን በከርሰ መቃብር የቆየው ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት ነው፡፡ «ሥጋዬ ደግሞ በተስፋ ታድራለች፤» የሚለው ቃለ ትንቢት የሚያረጋግጥልን ይኽንኑ ነው፡፡ መዝ ፲፭፥፱፡፡ ምሥጢራዊ ትርጉሙም «ወደ መቃብር የወረደ ሥጋዬ በተስፋ ትንሣኤ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት በመቃብር አደረ፤» ማለት ነው፡፡ ተስፋ ትንሣኤውም በተዋሕዶ ከሥጋ ጋር ወደ መቃብር የወረደ መለኰት ነው፡፡ ነቢዩ ሆሴዕም፡- «ኑ÷ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰብሮናልና÷ (በሞተ ሥጋ ላይ ሞተ ነፍስን ጨምሮ የፈረደብን እርሱ ነው)÷ እርሱም ይፈውሰናል፤ (መርገመ ሥጋን መርገመ ነፍስን አስወግዶ ከሞት ወደ ሕይወት ያሸጋግረናል)፤ እርሱ መትቶናል÷ እርሱም ይጠግነናል፡፡ ከሁለት ቀን በኋላ ያድነናል፤ በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል፡፡» በማለት ትንሣኤ ክርስቶስ በሦስተኛው ቀን መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ሆሴ ፮÷፲፪፡፡ ይልቁንም ጌታችን ራሱ በመዋዕለ ሥጋዌው፡- ከሽማግሌዎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ፥ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀመዛሙርቱ በግልጥ ነግሯቸዋል፡፡ ማቴ ፲፮÷፳፩፡፡ በገሊላም ሲመላለሱ፡- «ወልደ ዕጓለ እመሕያው ክርስቶስ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጥ ዘንድ አለው÷ ይገድሉትማል÷ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል፤» ብሏቸዋል፡፡ ማቴ ፲፯÷፳፡፡ ጻፎችና ፈሪሳውያንም ምልክት በጠየቁት ጊዜ፡- «ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል÷ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም፡፡ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ፥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደነበረ÷ እንዲሁ የሰው ልጅ (ወልደ ዕጓለ እመሕያው ክርስቶስ) በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል፡፡» ብሏቸዋል፡፡ ማቴ ፲፪፥፴፰-፵። ✞ #ሦስት_መዓልት_እና_ሦስት_ሌሊት_የሞላው እንዴት_ነው?  ✞ ጌታ በከርሰ መቃብር የቆየው ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት ነው፡፡ ይኽንንም ለመረዳት ዕብራውያን ዕለታትን እንዴት እንደሚቆጥሩ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ እኛ በሀገራችን የሌሊቱን ሰዓት መቁጠር የምንጀምረው ከዋዜማው ከምሽቱ አንድ ሰዓት ነው÷ የቀኑን ሰዓት መቁጠር የምንጀምረው ደግሞ ከማለዳው አንድ ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ የሌሊቱ ሰዓት የሚያ ልቀው ከማለዳው አሥራ ሁለት ሰዓት ሲሆን፥ የቀኑ ደግሞ ከምሽቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ሲሆን ነው፡፡ የቀኑም የሌሊቱም ሰ ዓት ተደምሮ ሃያ አራት ሰዓት ይሆናል፡፡ ሁሉም ሰዓት ዕለቱን ይወክላል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው እሑድ ዕለት ከሃያ አራቱ ሰዓ ት በአንዱ ቢወለድ እሑድ ተወለደ ይባላል÷ ቢሞትም እሑድ ሞተ ይባላል፡፡ ዕለቱ በሚጀምርበትም ሰዓት ሆነ፥ በሚያልቅ በት ሰዓት፥ ድርጊቱ ቢፈጸም ያ ሰዓት እንደ አንድ መዓልትና እንደ አንድ ሌሊት ይቆጠራል፡፡ አውሮፓውያን አንድ ብለው ሰዓት መቁጠር የሚጀምሩት በእኛ አቆጣጠር ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ነው፡፡ እስከ ሃያ አራት ይቆጥሩና በእኛ አቆጣጠር ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ሲሆን ይጨርሳሉ፡፡ ሃያ አራት ሰዓት ሲሆን ዜሮ ይሉና እንደገና አንድ ብለው መቁጠር ይጀምራሉ፡፡ በሌላ አነጋገር ከሌሊት እስከ ሌሊት ይቆጥራሉ፡፡ አሜሪካውያን ደግሞ በእኛ ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ሲሆን አንድ ብለው ይጀምሩና በእኛ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ሲሆን አሥራ ሁለት ብለው ይጨርሳሉ፡፡ ከዚያም በእኛ አቆጣጠር ከቀኑ ሰባት ሰዓት እንደገና አንድ ብለው ይጀምሩና በእኛ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ሲሆን አሥራ ሁለት ብለው ይጨርሳሉ፡፡ ዕብራውያን ግን ዕለትን መቁጠር የሚጀምሩት ከዋዜማው ማለትም በአውሮፓውያን ከአሥራ ሰባት ሰዓት÷ በአሜሪካውያን ከአምስት ሰዓት (P.M.) ÷ በእኛ ደግሞ ከምሽቱ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ድረስ ሃያ አራት ሰዓት ቆጥረው አንድ ቀን ይላሉ፡፡ ከላይ እንደተገለጠው እያንዳንዱ ሰዓት የዕለቱን መዓልትና ሌሊት ይወክላል፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ከመስቀል ወርዶ የተቀበረው ዓርብ ቅዳሜ ከመግባቱ በፊት ነው፡፡ ዓርብ ዕለቱ የሚጀምረው ከዋዜማው ሐሙስ በእኛ አቆጣጠር ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ ስለዚህ ጌታ የተቀበረው በዓርብ ሃያ አራት ሰዓት ክልል ውስጥ በመሆኑ እንደ አንድ መዓልትና ሌሊት ይቆጠራል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ዓርብ ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ቀን አሥራ አንድ ሰዓት ያለው ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ ቅዳሜ ከቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ጀምሮ እስከ እሑድ ቀን አሥራ አንድ ሰዓት ያለው ነው፡፡ ከዚህ በኋላ የሰኞ ምሽት ይገባል፡፡ ጌታ የተነሣው በሦስተኛው ቀን እሑድ መንፈቀ ሌሊት ነው።
نمایش همه...
የሰሙነ ሕማማት ማክሠኞ በዚህ ዕለት አምላካችን ለጥያቄዎች በሙሉ መልስ የሰጠበት እና በስፋት ያስተማራቸው ትምህርቶች የሚታሰቡበት ዕለት ነው። ፩. የጥያቄ ቀን ትባላለች። በዚህ ዕለት አምላካችን ስለ ሥልጣኑ በካህናት አለቆችና በሕዝብ አለቆች"በምን ሥልጣንህ እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን የሰጠህ ማነው?"(ሉቃ፳:፩-፵፩) የሚል ጥያቄ ለፈተና የተጠየቀበት ዕለት በመሆኑ የጥያቄ ቀን ትባላለች፡፡ ጥያቄዎቹ በቁጥር አምስት ናቸው። እነዚህም:- ፩. ሥልጣኑን የተመለከተ ጥያቄ ቀርቦለታል። (ሉቃ፳:፪) ለክፋት የቀረበ ጥያቄ በመሆኑ ጥያቄውን በጥያቄ መልሶታል። ፪. በወይን አትክልት መስሎ ጥያቄ አቅርቦላቸዋል። (ሉቃ፳:፱)ይህ ምሳሌ በቀጥታ ከእነርሱ ጋር እንደሚገናኝ ተረድተውም ነበር። ፫. ግብርን የተመለከተ ጥያቄ ቀርቦለታል። (ሉቃ፳:፳፪) ይህንንም በድንቅ ጥበቡ የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ብሎ መልሶላቸዋል። ፬. ትንሣኤ ሙታንን የተመለከተ ጥያቄ ቀርቦለታል። (ሉቃ፳:፴፫) ከጋብቻ ጋር በተገናኘ ምድራዊ አስተሳሰብ ሰማያዊውን ኑሮ አውርደው ለጠየቁት ለሰዱቃውያን ከሞት በኋላ እንደ መላእክት ያለን ኑሮ የመኖር ዕድል እንዳለው የሰው ልጅ መልሶላቸዋል። ፭. ክርስቶስን የዳዊት ልጅ ለምን ይሉታል የሚል ጥያቄ አቅርቦላቸዋል።(ሉቃ፳:፵፩) መልስ ላጡበት ጥያቄ ራሱ በመመለስ እርሱ የዳዊት ጌታ መሆኑን አስተምሯቸዋል። ፪. የትምህርት ቀን ትባላለች። በዚህ ዕለት ደቀ መዛሙርቱን ሰፊ ትምህርትን ስለ መጨረሻው ዘመን ምልክቶች አስተምሯቸዋልና የትምህርት ቀን ተብላ ትጠራለች። (ሉቃ፳:፵፬-፵፯) ያስተማራቸው ትምህርቶች ፩. የአምልኮ መልክ ካላቸው ተጠንቀቁ ፪. ታይታን ከሚወዱ ተጠንቀቁ ፫. ለራሳቸው ክብርን ከሚሰጡ ተጠንቀቁ ፬. የባልቴቶችን ገንዘብ ከሚበሉ ተጠንቀቁ ፭. በምክንያት ጸሎት ከሚያረዝሙ ተጠንቀቁ ሌላው በግብረ ሕማማት ካህናት በዚህች ዕለት ስለሚያከናውኗቸው ስራዎች እንዲህ ተብሎ ተገልጿል:-"ከዚህ በኋላ በከበረች ቤተክርስቲያን ማክሰኞ ከሌሊቱ መጀመሪያው ሰዓት ካህናት ይሰብሰቡ። ተዘከሮ እግዚኦ የሚለውን የዳዊት መዝሙር ወአሰሰልኩ ዕለተ እስከሚለው ድረስ ጸልዩ። ውዳሴ ማርያምም የቀዳሚትን ይድገሙ።" ግብረ ሕማማት (ገጽ፪፻፴፪) የመዝሙረ ዳዊት ምንባባት በ፩ ሰዓት (መዝ፴፬:፬-፭) በ፫ ሰዓት (መዝ፻፲፰:፻፶፬) በ፮ ሰዓት (መዝ፲፯:፲፯) በ፱ ሰዓት (መዝ፳፬:፩) በ፲፩ ሰዓት (መዝ፵፬:፮)
نمایش همه...
✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱስ "ስምዖን ዘአርማንያ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ +*" ቅዱስ ስምዖን ሰማዕት "*+ =>ቅዱስ ስምዖን የአርማንያ ሰው ቢሆንም ሰማዕትነትን የተቀበለው በሃገረ ፋርስ (በአሁኗ ኢራን አካባቢ) ነው:: ፋርስ ከ1ኛው መቶ ክ/ዘ እስከ ተንባላት (መሐመዳውያን) መነሳት (7ኛው መቶ ክ/ዘ) ድረስ ባለው ጊዜ ብዙ ሰማዕታት ለክብር በቅተውባታል:: +ብዙዎቹ የዚያው (የፋርስ) ዜጐች ሲሆኑ ጥቂቶቹ ደግሞ የተሰዉት ከሌላ ሃገር መጥተው ነው:: ፋርሳውያን አብዝተው ፀሐይን ያመልኩ ነበርና ክርስቲያኖቹን የሚያሰቃዩት ይህቺውን ፍጡር እያመለኩ እንዲንበረከኩ ነበር:: +ቅዱስ ስምዖንም ከፋርስ ግዛቶች በአንዱ ኤዺስ ቆዾስነትን (እረኝነትን) ተሹሞ ነበርና የመከራው ተሳታፊ ሆኗል:: በጊዜው ክርስትና እንደ ዛሬው "ሠርግና ምላሽ" አልነበረምና ቅዱስ ስምዖን (እረኛው) እና 150 የሚያህሉ ልጆቹ (መንጋው) ስለ ክርስቶስ ፍቅር ብዙ ሆነዋል:: +በእምነታቸው ጸንተው በመገኘታቸውም እንዲገደሉ ተወስኖባቸው 151ዱም ተሰውተዋል:: =>አምላከ ሰማዕታት በጽናታቸው አጽንቶ ከበረከታቸው ይክፈለን:: =>ሚያዝያ 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ስምዖን ሰማዕት (አርማንያዊ) 2."150" ቅዱሳን ሰማዕታት (የስምዖን ማሕበር) =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት 2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት 3.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ 4.አቡነ ስነ ኢየሱስ 5.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም =>+"+ እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ: ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::+"+ (ዕብ. 6:10-13) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
نمایش همه...
ባለማወቅሽ ነው” እያለ ረገማት፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም የገባው ሰለ ደኅንተቷ ሊያሳስባት ፈልጐ ነው፡፡ በማያወላዳ መንገድ ንጉሧና መድኃኒቷ እንደሆነ ገለጸላት፡፡ ወደ ራሷ ተመልሳ ጸጋዋን እንድትቀበል የልቧን ድንዳኔ ትታ እርሱን እንድትሰማ አስጠነጠቃት፡፡ ግን አልተጠነቀቀችም፡፡ ለጊዜው በክብር ተቀበለችው፡፡ ከጥቂት ቀን በኋላ ግን ተወችው፤ በመስቀል ላይ ሰቀለችው፡፡ የደኅንነቷን ቀን ማወቅ ተሳናት፡፡ በዚህም ደግሞ ከብዙ ዓመታት በኋላ መዓት ወረደባት፡፡ ይህ የሚያሳዝን የኢየሩሳሌም ሥራ የእኛም ሥራ ነው፡፡ ኢየሱስን መድኃኒታችንን መቀበል አንፈልግም ወይም ተቀብለን በኃጢአታችን ከእኛ እንዲርቅ እናደርገዋለን፡፡ በቅዱስ ቁርባን ወደ እኛ ሲመጣ በደስታ እንቀበለዋለን፡፡ ትንሽ ቆየት ብለን ደግሞ እናዋርደዋለን፡፡ ከእርሱ ጋር እንጣላለን፡፡ ከኃጢአት ጋር ጓደኝነት እንይዛለን፡፡ በኃጢአት ስንወድቅ እርሱን እንደገና እንሰቅለዋለን፡፡ ኢየሱስ እኛን “አቤት በዚህ ቀን ለደኅንነትህ የሚደረገውን ብታውቅ ኖሮ …፣ ይህ ሁሉ ከዓይንህ ተሰውሮብሃል ማወቅን አልፈለግህም፡፡ ይህን እወቅ ግን አንድ ቀን …” እያለ አዝኖ ይፈርድብናል፡፡ ይህንን በማሰብ ሲመጣና ሲናገረን እምቢ አንበለው አናባርረው፡፡ በኋላ እርሱ ቂም ይዞ እምቢ እንዳይለና እንዳያባርረን ደኅንነታችንን ራሳችን አናጥፋት፡፡ በዚህ ዕለት ፀበርት /ዘንባባ/ እየተባረከ ለሕዝብ ይታደላል ይኽንን በመያዝ ዕለቱ የፀበርት እሑድ ይባላል፡፡ታሪኩ በአራቱም ወንጌላት ውስጥ ይገኛል፡፡ √ማቴ.21፡4 √ ማር.11፡1-10 √ሉቃ.19፡28-40 √ዮሐ.12፤15       • የሆሣዕና መዝሙር፡- - ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ ሀገረ እግዚአብሔር ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት ነሢኦሙ አዕፁቀ በቀልት እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ተፅዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበሐሴት ይሁቦሙ ኃይለ ወሥልጣነ        • የሆሳዕና የቅዳሴ ምንባባት         ( ዕብ.8÷1-ፍጻ. ) ከተናገርነውም ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፡፡ እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፤ እርስዋም በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር የተተከለች ናት፡፡        (1ኛ ጴጥ.1÷13 ) ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና ነቅታችሁ ኑሩ፤ ኢየሱስ ክርስቶስም ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ፡፡       ( ሐዋ.8÷26-ፍጻ. ) የእግዚአብሔር መልአክም ፊልጶስን ተናገረው፤ እንዲህም አለው÷ “በቀትር ጊዜ ተነሣና በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያወርደው በምድረ በዳው መንገድ ሂድ፡፡” ተነሥቶም ሄደ፡፡   • የሆሣዕና ምስባክ የቅዳሴ    ( መዝ.80÷3 ) ንፍሑ ቀርነ በዕለት ሠርቅ፡፡ በእምርት ዕለት በዓልነ፡፡ እስመ ሥርዓቱ ለእስራኤል ውእቱ“     ትርጉም፦ በመባቻ ቀን በታወቀችው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤ ለእስራኤል ሥርዐቱ ነውና÷ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ ነውና፡፡    (ወይም መዝ.80÷2 ) እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሓተ፡፡ በእንተ ጸላዒ፡፡ ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ፡፡“       ትርጉም፦ ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፡፡ ስለ ጠላት÷ ጠላትንና ግፈኛን ታጠፋው ዘንድ፡፡      • የሆሣዕና ወንጌል የቅዳሴ   ( ዮሐ.12÷1-11 ) ፋሲካ ከሚውልበት ከስድስተኛው ቀን አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ......          • የሆሣዕና ቅዳሴ              - ቅዳሴ ዘጐርጐርዮስ
نمایش همه...
Henok: መንፈሳዊ ጉባኤ: ❖ ❖ ❖ የዐቢይ ፆም ስምንተኛ ሳምንት።     💦💦💦💦💦"ሆሣዕና" ❖ ❖ ❖ ሆሣዕና ማለት በዕብራይስጡ  ‹‹ሆሼዕናህ›› የሚል ሲሆን እባክህ አሁን አድን ማለት ነው፡፡ መድኃኒት ማለትም ነው፡፡ ከጌታችን ዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡ ሆሣዕና፡--  የተባለበት ምክንያት ጌታ “ሆሣዕና በአርያም” እየተባለ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት ዕለት የሚታሰብበትና የሚዘመርበት በመሆኑ ነው፡፡ የሆሣዕና ሥርዓት ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ዕለቱ ፍጻሜ ድረስ የተለየ አገልግሎት አለው፡፡        ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው። ሆሣዕና አስቀድሞ ካለው ረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን እንደሆነ ይታወቃል። ይህን ስም በዚሁ ሰንበትና በዋዜማዎቹ ዕለታት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‘ሆሣዕና በአርያም’’ ‘ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት’’ ‘ዕለተ ሆሣዕናሁ አርዓየ… ‘ ወዘተ. በማለት ሆሣዕና የሚለውን ቃል ቅዱስ ያሬድና ሌሎችም አባቶች በየቦታው እየጠቀሱና እየተዘመረለት በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁኔታ እየተረከ ስለሚዘምር ይህ ሰንበት በጌትነትና በክብር በውዳሴና ቅዳሴ ሆሣዕና በአርአያም እየተባለ በሽማግሌዎችና በሕፃናት አንደበት በድንጋዮችም ልሳን ሳይቀር እየተመሰገነ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በከብር ሲገባ ለሰጣቸው ለተቀደሰ ሰላሙና ፍቅሩ መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሌላ ቀን እንደ ተራ ሰው ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ይገባ ነበር፡፡ በዚህ ቀን ግን የአይሁድ ንጉሥ ሆኖ በክብር ገባ፡፡ ከቢታንያ ተነሥቶ ደብረ ዘይት ሲደርስ ከሐዋርያቱ ሁለቱን በቤተፋጌ ሰው ተቀምጦባት የማያውቅ ውርንጭላ እንዲያመጡለት ላካቸው፡፡ “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሒዱ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁም አምጡልኝ፡፡ ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ“ አላቸው፡፡ ማቴ.21፡1-17 ወደ ቤተፋጌም ሄደው አህያዪቱን አገኙአት፡፡ ሲፈቱአትም ሳለ ባለቤቶቹ መጡባቸውና አስቆሟቸው፡፡ እነርሱም ኢየሱስ እንደፈለጋት ነገሩአቸው፡፡ ባለቤቶቹ ይህንን ሲያውቁ ተውአቸው፡፡ ሐዋርያትም የአህያዪቱን ውርንጭላ ፈትተው ወደ ኢየሱስ ወሰዱ፡፡ አጠገቡም ሲደርሱ ልብሳቸውን በአህያዪቱ ውርንጭላ ላይ አንጥፈው ኢየሱስን አስቀመጡት፡፡       አህዮች በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ታሪክ አላቸው፡፡ የበልአም አህያ የመልአኩን ክብር ለመግለጥ አፍ አውጥታ ተናግራለች- ዘሁል22+28 ፤ ጌታችን በተወለደ ጊዜ አህዮች ከከብቶች ጋር በበረት እስትፋሳቸውን አሟሙቀውታል ፣ የሆሣዕና እህዮች ከሁሉ ተመርጠው አምላካችን ተቀምጦባቸዋል፡፡ ለምን የተዋረዱትን አህያዎች መረጠ ? 1. ትሕትናን ለማስተማር የትሕትና ጌታ መሆኑን ለመግለጽ ነው እንጂ ደመና አዞ ነፋስ ጠቅሶ በእሳት መንኮራኩር ላይ የሚረማመድ አምላክ ነው ነገር ግን የመጣው ለሰው ልጅ ትህትናን ሊያስተምር ነውና በአህያ ተቀመጠ 2. ትንቢቱን ለመፈጸም ትንቢት- ‹‹ አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በዪ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሁትም ሁኖ በእህያም በውርንጭላቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል ሰረገላውንም ከኤፍሬም ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም ያጠፋል›› ብሎ ዘካርያስ ትንቢት ተናግሮ ነበርና ለመፈጸም ነው ዘካ 9+1 3. ምሳሌውን ለመግለጽ ምሳሌ- ቀድሞ ነቢያት ዘመነ ጸብእ ከሆነ በፈረስ ተቀምጠው ዘገር ነጥቀው ይታያሉ ዘመነ ሰላም ከሆነ በአህያ ተቀምጠው መነሳንስ ይዘው ይታዩ ነበርና ጌታችንም ዘመነ ሰላም ነው ሲል በአህያ ተቀምጦ መጥቷል፡፡ 4. ምሥጢሩን ለመግለጽ ምሥጢር- በአህያ የተቀመጠ ሸሽቶ አያመልጥም አሳዶም አይዝም እሱም ካልፈለጋችሁኝ አልገኝም ከፈለጋችሁኝ አልታጣም ሲል በአህያ ተቀምጦ መጥቷል √ አህያ የእስራኤል ምሳሌ ፤ ውርንጫላይቱ የአሕዛብ ምሳሌ አህያይቱ ቀንበር መሸከም የለመደች ናት እስራኤልም ሕግ መጠበቅ ለምደዋልና ፤ ውርንጫላይቱ መሸከም አለመደችም አሕዛብም ሕግ መጠበቅ አለመዱምና √ አህያ የኦሪት ምሳሌ ፤ ውርንጫይቱ የወንጌል ምሳሌ አህያ ቀንበር መሸከም እንደለመደች ኦሪትም የተለመደች ሕግናትና ውርንጫላይቱ ቀንበር መሸከም አለመደችም ወንጌልም ያልተለመደች አዲስ ሕግ ናትና √ በሁለቱም ላይ መቀመጡ ኦሪትንም ወንጌልንም የሰራሁ እኔ ነኝ ሲል ነው √ በአህያይቱ ላይ ልብሳቸውን አንጥፈውለታል:: ልብስ በአካል ያለውን ነውር ይሸፍናል አንተም ከባቴ አበሳ ነህ ሲሉ √ በአህያዋ ላይ ኳርቻ ሳያደርጉ ልብስ አንጥፈውለታል ኮርቻ ይቆረቁራል ልብስ አይቆረቁርም የማትቆረቁር ሕግ ሠራህልን ሲሉ ነው። √ ስለምን ልብሳቸውን አነጠፉለት ቢባል ? በእዩ ልማድ ነው፡፡ እዩ የተባለው ሰው በእስራኤል ላይ ሲነግሥ እስራኤል ልብሳቸውን አንጥፈውለት ነበረና በዚያ ልማድ አንጥፈውለታል √ እኩሌቶቱ ደግሞ ዘንባባ አንጥፈውለታል ።     * ለምን ዘንባባ ያዙ ቢባል፦ ዘንባባ እሾሃም ነው ፤አንተም የኃይል የድል ምልክት አለህ ሲሉ፤ አንድም  ዘንባባ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ አይበላውም አንተም ባህርይህ አይመረመርም ሲሉ፤አንድም ዘንባባ ረጅም /ልዑል/ ነው አንተም ባሕርይህ ልዑል ነው ሲሉ ዘንባባ ይዘው ተቀብለውታል፡፡     * የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፦ ቴምር ፍሬው አንድ ነው አንተም ባህርይህ አንድ ነው ሲሉ፡፡አንድም፤ ቴምር ልዑል/ረጅም/ ነው አነተም ልዑለ ባህርይ ነህ ሲሉ፡፡ አንድም፤የቴምር ፍሬው በእሾህ የተከበበ ነው በቀላሉ መለቀም አይቻልም ፤የአንተም ምስጢር አንተ ካልገለጠከው አይመረመርም ሲሉ ነው፡፡      * የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፦ ወይራ ጽኑዕ/ ጠንካራ/ ነው አንተም ጽኑዓ ባህርይ ነህ ሲሉ፤ አንድም ወይራ ለመስዋዕት ይሆናል፤ አንተም መስዋዕት ትሆናለህ ሲሉ፤ አንድም ወይራ ዘይቱ ለመብራት ይሆናል አንተም የዓለም ብርሃን ነህ ሲሉ ይህንን ይዘው አያመሰገኑ ተቀበሉት፡፡     * ልብሳቸውንም ማንጠፋቸው፦ እንኳን አንተ የተቀመጥክባት አህያ እንኳን መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ልብሳቸውን አነጠፉለት፡፡ እነዚያ ያላመኑ አይሁድ ለተቀመጠባት አህያ ይህንን ያህል ክብር ከሰጡ፤ በድንግልና ጸንሳ ለወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምን ያህል ክብር ልናድረግለት ይገባን ይሆን?፡፡ “የጽዮን ልጅ ሆይ አትፍሪ እነሆ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል” ዘካ.9፡9 የሚለው የዘካርያስ ትንቢት ተፈጸመ፡፡ ሕዝቡም ኢየሱስ በመምጣት ላይ እንዳለ ሲያውቅ ሊቀበለው ወጣ፡፡ አንዳንዶች ያልፍበት በነበረ መንገድ ልብሳቸውን እንዳንዶቹ ደግሞ የዘንባበ ዝንጣፊ ያነጥፉ ነበር፡፡ ከፊትና በኋላ ያሉት ደግሞ “ሆሳዕና በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ” እያሉ በታላቅ ድምፅ ይጮሁ ነበር፡፡ ኢየሱስ በሕዝቡ እልልታና ደስታ ታጅቦ ሲገባ ተጠንቅቀው ይታዘቡትና ይመለከቱት የነበሩ ፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርቱን ዝም እንዲያሰኛቸው ተናገሩት፡፡ እርሱም ሕዝቡ ዝም ቢል ድንጋዮች እንደሚጮኹ አስታወቃቸው፡፡ ኢየሱስ ኢየሩሳሌምን ሲያያት አለቀሰላት፡፡ “አንቺ ኢየሩሳሌም ለሰላምሽ የሚያስፈልገውን ነገር ምነው አውቀሽ ቢሆን ኖሮ አሁን ግን ይህ ነገር ከዓይንሽ ተሰውሮብሻል ጠላቶችሽ በዙሪያሽ እንደ አጥር ከብበው በዚህም በዚያም አንቺን የሚያስጨንቁበት ጊዜ ይመጣል… ምክንያቱም እግዚአብሔር ሊያድንሽና ሊጐበኝሽ የመጣበትን ጊዜ
نمایش همه...
✞✝✞ ሚያዝያ 18 ✞✝✞ ✞✝✞ እንኩዋን ለጻድቅና ሰማዕት "አባ ዼጥሮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✝✞ *+" ጻድቅና ሰማዕት አባ ዼጥሮስ "+* =>ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ (መስዋዕትነት) ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው:: +ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው:: +እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ! በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም:: +እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ: የሚረግሟችሁን መርቁ: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ" ብሎናልና:: (ማቴ. 5:44) ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል:: +በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና:: ❖ቅዱስ አባ ጴጥሮስም ከዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች አንዱ ነው፡፡ በዚያ የመከራ ዘመን (3ኛው መቶ ክ/ዘ) ግብፅና ሶርያ በብዙ መከራ ውስጥ ሳሉ በርካታ ቅዱሳን ተሰውተዋል፡፡ በተለይ በግብፅ ደግሞ ብዙ ንጹሐን አበውና ቅዱሳት አንስት መከራውን ታግሠው ለክብር በቅተዋል፡፡ ❖ከእነዚሁ አንዱ የሆነው አባ ጴጥሮስ ገና ከልጅነቱ ጣዕመ ክርስትናን የተማረው ከአሳዳጊው (ከአክስቱ) ነበር፡፡ በፍፁም ልቡ የሚወደው ወንድም እና ባልንጀራም ነበረው፡፡ ስሙ ደግሞ አባ ብሶይ ይሰኛል፡፡ ሁለቱም በበጎ ምግባር ተኮትኩተው ፡ ዓለምንም ንቀው በርሃ ገብተው ፡ በጾም በጸሎት ተወስነው ብዙጊዜ ኑረዋል፡፡ ❖በመከራው ዘመን ደግሞ ክርስቶስን ስላመለኩ ብቻ ተከሰው ታስረዋል፡፡ ተገርፈው ተደብድበዋል፡፡ ጭንቅ ስቃይንም በትእግስት አሳልፈዋል፡፡ በፍጻሜውም አባ ጴጥሮስ በዚህች ቀን ተሰውቶ ለክብር አክሊል በቅቷል፡፡ ወዳጁና ወንድሙ ቅዱስ ብሶይም በክብር ገንዞ ቀብሮታል፡፡ =>አምላከ ሰማዕታት ከጸናች ገድላቸው ፡ ከበዛች ትእግስታቸው ፡ ከፍጹም በረከታቸው ያሳትፈን፡፡ =>ሚያዝያ 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ አውሳብዮስ ሰማዕት 2.አባ ዼጥሮስ ሰማዕት 3.ሰማዕታተ ጠርሴስ =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ 2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን) 3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ 4.ማር ያዕቆብ ግብፃዊ =>+"+ በድካም: አብዝቼ በመገረፍ: አብዝቼ በመታሠር: አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት: ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው:: +"+ (2ቆሮ 11:23) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
نمایش همه...
✞✞✞ እንኩዋን ለታላቁ ነቢይና ሰማዕት "ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ +*" ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ "*+ =>ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6) *የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር:: *ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ በስተእርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው:: *ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው:: *የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በሁዋላ ሰኔ 30 ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል:: *ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ:: *እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 (5) ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7) ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት:: *ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ ድንግል ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ:: *ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በኋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ25 (23) ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም:: *ከዚህ በኋላ 30 ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጀን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" (ሉቃ. 1:76) ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና:: *ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና:: *ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ: ለንስሃም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ6 ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነልብሱ የያዘ ፈጣሪ 'አጥምቀኝ' ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው:: *"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "መጥምቀ መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ7 ቀናት አሠረው:: *በዚህች ቀንም ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: (ማቴ. 3:1, ማር. 6:14, ሉቃ. 3:1, ዮሐ. 1:6) *ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በኋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት ደብረ ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: ቅዱሳን ሐዋርያትበኋላ በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት:: *ከዚሕ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት:: በመላው ዓለም ለ15 ዓመታት ስትሰብክ ኑራ በዚህች ቀን ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች:: =>" አስማተ-ዮሐንስ መጥምቅ/ የመጥምቁ ዮሐንስ ስሞች" 1.ነቢይ 2.ሐዋርያ 3.ሰማዕት 4.ጻድቅ 5.ካሕን 6.ባሕታዊ/ገዳማዊ 7.መጥምቀ መለኮት 8.ጸያሔ ፍኖት (መንገድ ጠራጊ) 9.ድንግል 10.ተንከተም (የብሉይና የሐዲስ መገናኛ ድልድይ) 11.ቃለ አዋዲ (አዋጅ ነጋሪ) 12.መምሕር ወመገሥጽ 13.ዘየዐቢ እምኩሉ (ከሁሉ የሚበልጥ) ❖ጌታችን መድኃኔ ዓለም የመጥምቁ ዮሐንስን ምትረት አስቦ ይቅር ይበለን:: ጸጋውን: በረከቱንና ክብሩንም ያሳድርብን:: ❖ሚያዝያ 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት (ጸዐተ ነፍሱ) 2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ (ከ318ቱ ሊቃውንት) 3.ቅዱስ አጋቦስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት) 4.ቅድስት እለእስክንድርያ ሰማዕት 5.አቡነ አቢብ ጻድቅ ወርኃዊ በዓላት 1 ቅዱስ ሚናስ 2 .ቅዱስ ማርቂርቆስ ለእሙ ኢየሉጣ 3 ቅድስት ዕንባ መሪና 4 ቅድስት ክርስጢና 5 ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ++"+ ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . . . ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችሁአለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላቹሃለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም. . . ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ:: ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው :: የሚሰማ ጀሮ ያለው ይስማ:: +"+ (ማቴ. 11:7-15) ❖ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ❖
نمایش همه...
††† እንኳን ለአባ መክሲሞስ ሊቀ ዻዻሳት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† አባ መክሲሞስ ሊቀ ዻዻሳት ††† ††† "ዻዻስ" ማለት "አባት - መሪ - እረኛ" ማለት ነው:: በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ በሐዲስ ኪዳን የመንፈሳዊ ስልጣን ደረጃዎች በጥቅሉ 3 ናቸው:: እነሱም *ዲቁና: *ቅስና: *ዽዽስና ሲሆኑ በሥራቸው ወደ 9 ያህል ክፍሎች አላቸው:: ከእነዚህም ከፍተኛው ስልጣን ዽዽስና ነው:: ዽዽስና ማለት የክርስቶስን መንጋ እንደ ባለቤቱ አድርጐ መጠበቅ ማለት ነው:: ሥልጣኑ በምድር "ሸክም" : "ዕዳ" ሲሆን በሰማይ ግን "ክብር" ነው:: ማንም በሥጋው ላይ ካልጨከነ በቀር ዽዽስናን አይመኝም:: ቅዱስ ዻውሎስ "ሠናየ ግብረ ፈተወ - ማንም ዽዽስናን ቢመኝ መልካም ሥራን ተመኘ" (1ጢሞ. 3:1) ማለቱን ይዞ "ሹሙኝ" ማለት ወደ ማይጠፋ እሳት የሚያስጥል ከባድ ውሳኔ ነው:: ምክንያቱም አንድ ክርስቲያን የሚጠየቅ በራሱ ኃጢአት ሲሆን አንድ ካህን ደግሞ ስለ ልጆቹ ይጠየቃል:: የከፋው ግን የዻዻሱ ነው:: አንድ ዻዻስ ቢጾም ቢጸልይም እንኩዋ ለድኅነቱ በቂ አይደለም:: ምክንያቱም በመንበሩ ላይ ያስቀመጠው መንጋውን እንጂ ራሱን እንዲያድን አይደለምና:: ጌታ እንዳለ መልካም እረኛ "ይሜጡ ነፍሶ ቤዛ አባግኢሁ - መልካሙ እረኛ ስለ በጐቹ ቤዛ ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ ነው::" (ዮሐ. 10) ስለዚህም ክህነት (ዽዽስና) ሐዋርያዊ አገልግሎት: ከባድም ኃላፊነት ነው:: አባቶቻችን ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው ሐዋርያውያን ታላላቅ የዽዽስና መንበሮችን መሥርተው: ትምሕርቱን ከነ ወንበሩ አስተላልፈዋል:: ከእነዚህ መንበረ ዽዽስናዎች 4ቱ የበላይ ናቸው:: ††† እነዚህም:- *የቅዱስ ዼጥሮሱ የሮም: *የቅዱስ ዮሐንሱ የአንጾኪያ: *የቅዱስ ማርቆሱ የእስክንድርያና *የቅዱስ ዻውሎሱ የኤፌሶን መናብርት ናቸው:: እነዚህ መንበሮችም ከክርስቶስ ዕርገት እስከ 443 (451) ዓ/ም {ጉባኤ ኬልቄዶን} ድረስ በአንድነት ቆይተው ተለያይተዋል:: ከእነዚህ መናብርት መካከል የእስክንድርያው (የግብጹ) እና የአንጾኪያው (የሶርያው) ዛሬም ድረስ በተዋሕዶ እምነት የጸኑ ናቸው:: የእኛ ቤተ ክርስቲያንም ሐዋርያዊት እንደ መሆኗ ሐዋርያትን መስለው: ሐዋርያትን አህለው የተነሱ አበው ዻዻሳትን በየጊዜው በበዓላት ታስባለች: ታከብራለች:: በተለይ ደግሞ የእስክንድርያና የአንጾኪያ በርካታ አባቶችን እናከብራለን:: እነርሱ ለቀናች ሃይማኖትና ለመንጋው ሲሉ ብዙ መከራን በአኮቴት ተቀብለዋልና:: ከእነዚህም መካከል አንዱ አባ መክሲሞስ ነው:: አባ መክሲሞስ የእስክንድርያ (ግብጽ) 15ኛ ፓትርያርክ ሲሆን በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ቤተ ክርስቲያንን ለ15 ዓመታት አገልግሏል:: ቅዱሱ ከልጅነቱ ጀምሮ ምስጢረ ሃይማኖትን የተማረ ሲሆን መናኝ ሰው እንደ ነበርም ይነገርለታል:: በደቀ መዝሙርነትም ለአባ ያሮክላ (13ኛው ሊቀ ዻዻሳት) እና ለአባ ዲዮናስዮስ (14ኛው ሊቀ ዻዻሳት) በትህትና አገልግሏል:: ዲቁናና ቅስና ሹመት ያገኘውም በዚህ ጊዜ ነው:: ፓትርያርክ ሆኖ ከተመረጠ በሁዋላም ምዕመናንን በአፍም : በመጣፍም ብሎ አስተምሯል:: በዚህም መንጋውን ከተኩላ የመጠበቅ ተግባርን ከውኗል:: በተለይ ደግሞ ዓለማቀፍ መናፍቃን የሆኑትን ማኒንና ሳምሳጢን ተዋግቷል:: ትግሉም ተሳክቶ መናፍቃኑ ተወግዘዋል:: ቅዱሱ አባት አባ መክሲሞስ (ማክሲሙስ) ከዚህም የሚበልጥ ብዙ በጐ ሥራ ሠርቶ በበጐ ዕረፍት በዚህች ቀን ዐርፏል:: ††† አምላከ ቅዱሳን ስለ አባቶቻችን ብሎ ለመንጋው የሚራራ እረኛን ይስጠን:: ከቅዱሱ በረከትንም ይክፈለን:: ††† ሚያዝያ 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አባ መክሲሞስ ሊቀ ዻዻሳት ††† ወርሐዊ በዓላት 1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል) 2.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ 3.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ 4.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው) 5.አባ ስምዖን ገዳማዊ 6.አባ ዮሐንስ ጻድቅ 7.እናታችን ቅድስት ነሣሒት ††† "ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ዻዻሳት አድርጎ ለሾመባት: ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ:: ከሄድሁ በሁዋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ:: ስለዚህ 3 ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቁዋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ::" ††† (ሐዋ. 20:28) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✝✝✝
نمایش همه...
በአንድ ወቅት አንድ መንፈሳዊ አባት ከነበሩበት ቦታ ወደ በረሃ መሰደድ ግድ ሆነባቸው። ከቅዱስ መጽሐፋቸው ሌላ ሦስት ነገሮች ነበሯቸው። እነሱም፦ ቅዱስ መጽሐፉን በጨለማ ወቅት ለማንበብ የሚጠቅማቸው ኩራዝ ፣ጎህ ከመቅደዱ በፊት ከእንቅልፍ የሚቀሰቅሳቸው አንድ አውራ ዶሮ እና ለመጓጓዣነት የሚገለገሉበት አንድ አህያ ነበሩ። አንድ ቀን ምሽት ከጉዞ የተነሣ በጣም ስለ ደከሙ እኚህ መንፈሳዊ አባት ወደ አንድ መንደር ቀርበው ማደሪያ ቢጠይቁም መንደርተኛው ፈቃደኛ ባለመሆኑ ማንም አላሳደራቸውም። ስለዚህም ከመንደሩ አቅራቢያ አንድ ጉድጓድ ያገኙና በዚያ ውስጥ ገብቶ ለማደር በመወሰን ገብተው አደሩ። እንደ ወትሮው ቅዱስ መጽሐፋቸውን ለማንበብ ኩራዛቸውን ቢለኩሱትም የነበረው ብርቱ ነፋስ አጠፋባቸው። ስለዚህም ለመተኛት ጋደም እንዳሉ ተኩላ መጥቶ አውራ ዶሮዋቸውን፣ አንበሳም አህያቸውን በሉባቸው። የተደራረበ ጉዳት ስለደረሰባቸው ሽማግሌው እርዳታን በመሻት ወደዚያ መንደር ቢመለሱ ዘራፊ ሽፍታዎች የመንደሩን ነዋሪዎች በሙሉ ገድለው ንብረት ዘርፈው ዖና መንደር ሆኖ አገኙት። ሽማግሌው ይህን ሁሉ ባጤኑ ጊዜ እግዚአብሔር ምን ያህል መልካም ነገርን እንዳደረገላቸው አስተዋሉ። በዚያች ምሽት በመንደርተኞቹ በአንዱ ቤት ቢያድሩ ኖሮ የዘራፊዎች ሰለባ ሆነው ሊገደሉ በቻሉ ነበር። ቀንዲላቸውንም ነፋስ ባያጠፋው የብርሃኑ ወጋገን እዚህ ጋር ሰው አለ በማለት ለሽፍታዎቹ ያሳብቅ ነበር። አውራ ዶሮአቸውና አህያቸውም ባይበሉ ኖሮ ከሽፍታዎቹ ተደብቀው ማደር ባልቻሉ ነበር።” እግዚአብሔር ከክፉ ነገሮች ውስጥ መልካም ነገር ማውጣት የሚችል አምላክ ነው።" 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ስለዚህ እንዲህ በሉ፦ "የሚደርስብኝ ፤ የሚገጥመኝ ፈተናና መከራ ሁሉ አምላኬ ሆይ ለበጎ ታደርግልኛለህና አመሰግንሐለሁ" አሜን 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
نمایش همه...
†††  እንኳን ለአባ ይስሐቅ ጻድቅ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† አባ ይስሐቅ ጻድቅ ††† ††† ጻድቁ ግብጻዊ ሲሆኑ የነበሩት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: በጊዜው ዝነኛ ከነበሩት ከታላቁ አባ ዕብሎ (ቅዱስ ዕብሎይ) ተምረዋል:: መማር ብቻ ሳይሆንም ለ25 ዓመታት ያለ መታከት በተልዕኮ አገልግለዋል:: በእነዚህ ጊዜያትም ትሕርምትን : ተጋድሎን : ትምህርተ ቅድስናንና ሌሎች አስፈላጊ መንፈሳዊ ስንቆችን ሰንቀዋል:: በመታዘዛቸው በምድር አበውን : በሰማይ እግዚአብሔርን አስደስተዋል:: በዚህም ከእግዚአብሔር ጸጋውን : ከአበው ምርቃትን አትርፈዋል:: ጊዜው ደርሶም ታላቁ ዕብሎ ሲያርፉ አባ ይስሐቅ በዓት ለይተው ደንበኛውን ተጋድሎ ጀምረዋል:: አምላካቸውን ለማስደሰትና በቅድስና ለመዝለቅም የአርምሞ ሰው ሁነዋል:: ለሚገባው ነገር ካልሆነ በቀር አያወሩም:: ምላሽም አይሰጡም:: "ለምን?" ሲባሉ 1."ለሁሉም ጊዜና ቦታ አለው::" 2."ሰው በከንቱ በማውራቱ ከጸጋ እግዚአብሔር ይርቃል" ይሉ ነበር:: አባ ይስሐቅ የክርስቶስ መድኃኒታችንን ሕማማት ለማዘከር ሁሌ ያነቡ (ያለቅሱ) ነበር:: ቅዳሴ ሲያስቀድሱ እጃቸው የሁዋሊት ታስሮ ነበር:: ቅዱሱ ሰው ለአዝማናት እንዲህ ተመላልሰው በመልካም ዕርግና ያረፉት በዚህ ቀን ነው:: ††† አምላከ ቅዱሳን ከበረከታቸው አይለየን:: ††† ሚያዝያ 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አባ ይስሐቅ ገዳማዊ (የታላቁ ዕብሎይ ደቀ መዝሙር) 2.አባ ገብርኤል ሊቀ ዻዻሳት ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ 2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ 3.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ 4.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ 5.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ) 6.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት 7.ቅዱስ ዕፀ መስቀል ††† "የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ: የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ በእግዚአብሔር አብ ተወደው: ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ: ምሕረትና ሰላም: ፍቅርም ይብዛላችሁ:: ወዳጆች ሆይ! ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኩዋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ::" ††† (ይሁዳ. 1:1) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
نمایش همه...