cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

🇪🇹Ethiopia🇪🇹🇪🇹 News🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

True Breaking News

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
Advertising posts
153مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ከረመዳን ጾም በኋላም መልካምና በጎ ነገር ማድረጉን እንዲያስቀጥል ተጠየቀ ----------------------------------- ግንቦት 05/2013 (ዋልታ) - የደብረታቦር ከተማ ሙስሊም ማኅበረሰብ የ1 ሺህ 442ኛውን ኢድአልፈጥር በዓልን በቴዎድሮስ አደባባይ በሶላትና በእስላማዊ ትምህርቶች አክብሯል፡፡ በእለቱ በእንግድነት የተገኙት የደብረታቦር ከተማ ከንቲባ መሰረት ወንዴ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እስልምናና ክርስትና ሃይማኖቶች ለበርካታ ዓመታት አብረው ተከባብረው የኖሩ መሆናቸውን አስታውሰዋል። ይህንን መልካም እሴት ላቆዩን አባቶቻችን ክብር ይግባቸዋልም ብለዋል፡፡ ከንቲባው እስልምና ማለት ሰላም ማለት መሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያ ከተጋረጠባት ችግር እንድታልፍ ሕዝበ ሙስሊሙ ዱኣ (ጸሎት) እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡ በበዓሉም የሶላት ሥነ ሥርዓትና ሌሎች አስተምህሮዎች ተከናውነዋል፡፡ በበዓሉ ለሕዝበ ሙስሊሙ ሃይማኖታዊ ትምህርት የሰጡት የሃይማኖቱ ዳኢ (አስተማሪ) ሸህ አብዱል ሃዲ ሁሴን ከእስልምና መሰረቶች ውስጥ አንዱ ጾም መሆኑን ጠቅሰው በጾም ወቅት እዝነት፣ መረዳዳት፣ ያለው ለሌለው ማካፈልና በጎ ስራ መስራት ከፈጣሪ ጋር የሚያስታርቅ ነው ብለዋል፡፡ ሙስሊሙ ማኀበረሰብ ከሮመዳን ጾም በኋላም መልካምና በጎ ነገር መስራትን አጠናክሮ በመቀጠል ከአላህ ምንዳውን ለማግኘት ሃይማኖቱን መኖር እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ (ምንጭ፡- አሚኮ)
نمایش همه...
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለኢድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረችሁ መልዕክት አስተላለፉ ------------------------- ግንቦት 05/2013 (ዋልታ) -ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለ1ሺህ 442ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢድ ዓልፈጥር በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ፕሬዚዳንቷ በትዊተር ገጻቸው ላይ ለመላው ሙስሊም ኢትዮጵያውያን እንኳን ለኢድ አል ፈጥር በዓል በደህና አደረሳችሁ ብለዋል። በዓሉን በቤታቸው ለማክበር ዕድሉን ያላገኙትን ወገኖቻችንን በማስታወስ ፣ በመደገፍና ያለንን በማካፈል ልናከብር ይገባል ብለዋል ። በዓሉ የሰላምና የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡
نمایش همه...