cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ሀላል ትዳር❤️

..................ፍቅርን.......................... በትዳር ውስጥ ..................ፈልጉ።......................... ትዳር የእውነተኛ ፍቅር መገኛ 💝ተዘወጅ በነቢዬ ሱና ሀላል ትዳርን ላይ ላለዎት የትኛውም አስተያየት እና ጥቆማ @abuyaa6

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
409
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

የፀሐይ ግርዶሽ ወቅት የሚሠገድ ሠላት (ሠላቱል ኩሱፍ) ለአላህ ብለው ሼር ያድርጉ —————————————————— የፊታችን ሠኔ 14 (እሁድ ዕለት) ጠዋት የፀሐይ ግርዶሽ በሐገራችን እንደሚከሠት ተተንብዮ ፣ ህዝቡ በጉጉት እየጠበቀ ይገኛል። እስልምና "እምነት" ብቻ ሳይሆን የሕይወት መንገድ (way of life) ነው የሚባልበት አንዱ ምክንያት ፣ ሙስሊም የሆነ ማንኛውም ግለሰብ: እንደ መብላት እና መጠጣት ካሉ ዕለታዊ ክንውኖች ጀምሮ ፣ እንደ ፀሐይ ግርዶሽ እስካለው እጅግ ያልተለመደ (rare) ክስተት ድረስ ያሉ በህይወት ዘመኑ የሚያጋጥሙትን ተፈጥሯዊ ክስተቶች በሙሉ ከተቀረው የዓለም ህዝብ (በአላህ እና በነብዩ መሐመድ /ሰአወ/ ካላመነው) በተለየ ሁኔታ፣ በምን መልኩ ከአምልኮ ጋር እያቀናጀ ማካሄድ እንዳለበት ከፈጣሪው የተደነገገለት መመሪያ ያለው በመሆኑ ነው። የፀሐይ ግርዶሽ በአንድ አካባቢ አንድ ጊዜ ከተከሠተ እዚያው ቦታ ላይ ዳግም ለመከሠት እስከ 400 ዓመታትን ሊፈጅ እንደሚችል የዘርፉ ምሁራን ያስረዳሉ። በዚህም መሠረት ለአብዛኞቻችን የመጪው እሁድ ክስተት በሕይወት ዘመናችን የመጀመሪያችንም የመጨረሻችንም ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። በዚህ ልዩ አጋጣሚ ታዲያ በሕይወት ዘመናችን ደግመን ልንሠራው የማንችለውን፣ አባቶቻችን እና አያት – ቅድመ አያቶቻችን የመተግበር ዕድል ያላገኙትን በርዕሴ ላይ የጠቀስኩትን ልዩ የሡና ተግባር ሳንተገብር እንዳያልፈን ልጠቁም እወዳለሁ። የፀሐይ ግርዶሽ ሠላት አሠጋገድ: ——————————————— የሠላቱ ወቅት:– የፀሐይ ግርዶሽ ሠላት የሚሠገደው የግርዶሹ ክስተት ከጀመረ አንስቶ እስከሚጠናቀቅ ባሉት ሠአታት ውስጥ በተመቸን ወቅት ሲሆን፣ በጀመዓ መስገዱ ይበልጥ የተወደደ ነው። ያለመታደል ሆኖ በሱናው መሠረት እንደ ጁምዓ ሠላት በመስጊዶቻችን ተሠባስበን በአንድ ኢማም መስገድ ባንችልም በየቤታችን በጀመዓ መስገድ ይቻላል። አሠጋገድ:— ሠላቱ ሁለት ረከዓ ሆኖ፣ እያንዳንዱ ረከዓ ሁለት ሩኩዕ እና ሁለት ቂረዓት ይኖረዋል። ማለትም : መጀመሪያ ሠጋጁ እንደሌላው ሠላት ከውዱዕ በኋላ ወደቂብላ በመዞር አንድ ተክቢራ አድርጎ ወደ ሠላት ይገባል። የመክፈቻ ዚክር፣ ሱረቱል ፋቲሃ እና ተጨማሪ (ከተቻለ ረጅም) ሱራ ይቀራል። ከዚያም ሩኩዕ ያደርግና በሩኩዕ ወቅት የሚደረገውን ዚክር ያስረዝማል። "ሠሚዓላሁ ሊመን ሀሚደህ" ብሎ ከተነሳ በኋላ እንደሌላ ሰላት ወደ ሱጁድ በመሄድ ፋንታ በድጋሚ ፋቲሃን እና ሌላ ረጅም ሱራ ይቀራል። ሲጨርስ ሩኩዕ ያደርግና ረጅም ዚክር ያደርጋል። "ሠሚዓላሁ ሊመን ሀሚደህ" ብሎ በአንድ ረከዓ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ከሩኩዕ ከተቃና በኋላ ወደ ሱጁድ ያመራል። እንደሌላ ሰላት ሁለት ሱጁዶችን አድርጎ ወደ ሁለተኛው ረከዓ ይነሳል። ሁለተኛውን ረከዓ ልክ እንደመጀመሪያው ረከዓ አይነት ሁለት ሩኩዕ እና ሁለት ቂያም ያለው አሠጋገድ ይሠግድና ወደ ሱጁድ ያመራል። በስተመጨረሻም ተሸሁድ ተቀምጦ ያሠላምታል። የፀሐይ ግርዶሽ ሠላት ከጨረቃ ግርዶሽ ሠላት የሚለየው ፣ በቀን የሚሠገድ በመሆኑ ድምፅ ከፍ ሳይደረግ ቁርአን የሚቀራበት መሆኑ ነው። ለሌሎች ሼር በማድረግ የዚህ ልዩ ሱና አጅር ተካፋይ ይሁኑ። መተግበሩም እንዳያመልጦት!!! @zewjeti ============[[[ @zewjeti
نمایش همه...
sticker.webp0.25 KB
ከማግባትዎ በፊት ማወቅ ያለበዎት 10 ነገሮች
ባል ቢዋሽስ
ሚስት ብትዋሽስ
ይህንን ሳያውቁ እንዳያገቡ
sticker.webp0.25 KB
"ሀፍሲ" ክፍል አስር ጸሐፊ፦ ኑዕማን ኢድሪስ ... ከተያዘላቸዉ ሆቴል ክፍሉ ዉስጥ አልጋዉ ላይ ተንጋሏል። በአይኖቹ ልሙጥ የሆነዉነን ጣራ እየተመለከተ ነገሮች ሁሉ በጽሁፍ ተቀምጠዉ እያነበባቸዉ እስኪመስል ድረስ ተመስጧል። ኡስማን ብዙ ሀላፊነት አለበት። ሁሉንም ሀላፊየቶች ግን የስራ ጫና፤ የነገራቶች መደራረብ ሳይበግሩት ሁሉንም በብቃት ይወጣል። አሁን ይበልጥ ያሳሰበዉ ግን የሀፍሲ ጉዳይ ነዉ። በጣም ብዙ እየጠበቃት ነዉ። ከዛሬ ነገ መልስ ትሰጠኛለች። ፈቃደኛ ሆና አብረን እንሆናለን እያለ ሚያስበዉ ነገር የሌት ህልሙ፤ የቀን ቅዠቱ ብቻ እንደሆነ እየተሰማዉ ነዉ። "ልጅ በልጅነት ነዉ!" ያሉት የሸኽ አጃኢቡ ምክር በህሊናዉ በተደጋጋሚ እያቃጨለ ነዉ። አልሳካለት ብሎ እንጂ ቶሎ አግብቶ በወጣትነት የልጅ አባት ቢሆን ምኞቱ ነዉ። "ስለዚህ መወሰን አለብኝ" ብሎ አሰበ። ዛሬ ስለሷ የሚያስብበት የመጨረሻ ቀን ነዉ። ዉሳኔዎቹ ሸኽ አጃኢቡ ይዘዉ በሚመጡት መልስ ይወሰናል!። በዚህ መሃል ስልኩ የንዝረት ድምጽ አሰማ። "ሄሎ ሃዩ..." የጀመዓቸዉ አባል የሆነችዉ ሀያት ናት። ከሰላምታዉ በኃላ ሃያት እራት ልጋብዝህ ብላዉ ከአልጋዉ ተነሳ። ሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል ከምሽቱ 1:30 ... ሀፍሲና ዴቭ ክብ ወደሆነዉ ጠረንጴዛ አመሩ። ዴቭ ቀደም ብሏት ተራመደና ወንበሩን ሳብ አድርጉ እንድትቀመጥ ጋበዛት። ሀፍሲ ነገሮችን ቶሎ ተረጎመቻቸዉ። "እሱም ይወደኛል!" ብላ አሰበች። እንደዚህ አይነት ተንከባካቢ ባል የማግባት ፍላጓቷ የቆየ በመሆኑ ዴቭ ዛሬዉኑ ደግሶ ቢያገባት ተመኘች። "እኔምልሽ ሀፍሲ..." አላት። ከሀሳቧ እንደመንቃት እያለች "ወይዬ ዴቭ" አለችዉ። "ራት ግብዣዉ ምንን በማስመልከት ነዉ?" ብሎ ጠየቃት። "ምንም እንዲሁ ነዉ! ግን ከእራቱ በኃላ ምነግርህ ነገር አለ" ብላ መለሰችለት። ድፍረቷ ገርሟታል። "እሺ ደስ እንዳለሽ..." አለና ቀጠል አድርጎ "... ታዉቂያለሻ ሀፍሲ ሁሌም ቆንጆዬ ነሽ የዛሬዉ ደግሞ የተለየ ነዉ!" ብሎ እንደማድነቅ አደረገ። ሀፍሲ ዉስጧን የደስታ ስሜት አጥለቀለቀዉ። በዴቭ ቆንጆ ነሽ መባል ለሷ ትልቅ መታደል ነዉ። "እሱም ቢሆን ለኔ ስሜት አለዉ!" ብላ አሰበች። በነገራቶች ሁሉ "እሱ እንደሚያፈቅራት!" ብቻ ነዉ ማሰብ የምትፈልገዉ። ዴቭ ያወራታል ነገር ግን ሀፍሲ ምንም ነገር እየመለሰችለት አይደለም። ከእራቱ በኃላ እንደምታፈቅረዉ ልትነግረዉ ነዉ። በጣም ፈርታለች ተንበርክካ "ታገባኛለህ" ብላ እንደመጠየቅ ያክል ዉስጧ ተሸብሯል። "እዚ ሆቴል ብዙ ግዜ መጥቻለሁ። አንድም ቀን ግን ከምወዳት ልጅ (ከፍቅረኛዬ) ዉጭ ሌላ ሴት ጋር መጥቼ አላዉቅም" አላት። ሀፍሲ አይኗ ፈጠጠ፤ ደነገጠች። መርዶ እንደተነገረዉ ሰዉ በቀይ ፊቷ ላይ ድንጋጤ ታክሎበት ሊፈነዳ የደረሰ ቲማቲም መሰለ። "ማለት ፍቅረኛ አለክ?" ብላ ጠየቀችዉ። . . . ሸኽ አጃኢቡ 2:00 ሰአት ሲሆን የዒሻ ሶላታቸዉን ሰግደዉ አጠናቀቁ። ብዙ ጊዜ መሸት አድርገዉ የመስገድ ልምድ ስላላቸዉ እንደለመዱት ቢያደርጉ ደስ ይላቸዉ ነበር። ነገር ግን ዛሬ ከሀፍሲ ጋር ቀጠሮ ስለያዙ በጊዜ ሰገዱ። ...ኡስማንና ሀያት መኪና ዉስጥ ሁነዉ ለስላሳ አዝዉ እያወሩ ነዉ። ሃያት ኡስማንን በስስት አይን እያየችዉ ተስለመለመች። "ሃዩ ልትነግሪኝ የምትፈልጊዉ ነገር አለ?" አላት። ዉስጧ የሆነ ነገር እንዳለ ሁኔታዋ ያሳብቅባታል። ፊቷ አይደብቅም - ያስታዉቅባታል። "አ....ዎ የሆነ ነገር ልነግርህ እፈልጋለሁ ግን ፈራሁ" አለችዉ። ኡስማን ሀሳቡ ሌላ ቦታ ስለሆነ፤ ምኞቱ ሀፍሲ ብቻ ስለሆነች ሀዩ ፊት ፍራሀቷን እንጂ ፍቅሯን ማንበብ አልቻለም። የአይኖቿን መስለምለም እንጂ ለሱ ያላትን ዉዴታ ከፊቷ መረዳት አልቻለም። አይናችን ብቻ ያለ ልብ ማስተዋል ቢችል ኡስማን የሀዩን ፍቅር በተረዳ ነበር። ነገር ግን ሀሳቡ፤ ምኞቱና ፍላጎቱ ሌላ ቦታ ነዉ። "አትፍሪ ሃዩ ንገሪኝ!" ብሎ እንደ ማደፋፈር አደረጋት። "አይ ኡስሚ ነገ ስራችንን በጊዜ ከጨረስን ወደ አዲስ አበባ እንመለሳለና?" ብላ ጠየቀችዉ። "አዎ ሀዩቲ እንመለሳለን" "ከቻልክ እኔና አንተ ብቻ አብረን እንሂድ የምነግርህ ነገር አለኝ!" ብለዉ የጀመረችዉን ለስላሳ ሳትጨርስ ከመኪና ወረደች። ... "ፍቅረኛ አለክ?" የሀፍሲ ጥያቄ ነበር። ዴቭን ወደደችዉ እንጅ ስለዴቭ ምንም ነገር አታቅም። እሱም ስለራሱ ለመናገር ደፍሮ አያዉቅም። ካሳለፈዉ የህይወት ታሪኩ የሚወደዉ አንድም ነገር የለም። ምክንያቱም ዴቭ እስልምናን ከመቀበሉ በፊት ከዩኒቨርሲቲ ጀምሮ በጣም ሚወዳት ፍቅረኛ ነበረችዉ። ፍቅረኛዉን በጣም ነዉ የሚወዳት፤ የትኛዋንም ሴት ከሚያስበዉ በላይ ስለ ሀና ሲያስብ ዉስጡን ሀሴት ይሰማዋል። ከሀና ጋር ብዙ ነገር አብረዉ አሳልፈዋል። እስልምናን ከተቀበለ አንድ አመት እየሆነዉ ቢሆንም ሀናን ሳያስባትና ሳይደዋወሉ ዉለዉ አያድሩም። ሁሌም ወደ እስልምና ጥሪ ያደርግላታል። አብረዉ እንዲሆኑና እሱ የሚከተለዉን ሀይማኖት ተከትላ አግብቷት አብረዉ ቢኖሩ ደስታዉ ወደር የለዉም። ምክምያቱም ዴቭ ከሀና ልጅ አለዉ። የዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪ እያሉ ለመዉለድ ተስማምተዉ እጅግ በጣም ከሚወዳትና ከሚያፈቅራት ሴት የአብራክ ክፋይ አግኝቷል። ... ሀፍሲ ፊቷ ላይ የድንጋጤ ስሜት ቢታይባትም ዴቭ ቀለል አድርጎ "አዎና እስልምናን ከተቀበለች አገባታለሁ። ልጃችንንም አብረን እናሳድጋለን!" አላት። ሀፍሲ ራሷን መቆጣጠር አልቻለችም። ሰዉነቷ ተንቀጠቀጠ። ተብረከረከች። አይኗቿ ተቀያየሩ። ከደቂቃዎች በፊት የነበረዉ ዉበት ወደ አስፈሪነት ተቀየረ። ያዘዙትን ራት ሳይበሉ ምንም ቃል ሳታወጣ ከተቀመጠችበት ተነስታ እየተንገዳገደች ወደ በሩ አመራች። "ምን ሆንሽ ሀፍሲ?" ብሎ ከተቀመጠበት ተነስቶ ተከተላት። ወደ ዉጭ ከወጣች በኃላ ወደ መኪናዋ ሩጫ በቀረዉ ፈጥነት ተራመደች። ያሰበችዉንና ያቀደችዉን ሳትነግረዉ በነገራት አስደንጋጭ ዜና ራሷን መቆጣጠር አቅቷት ወደ ሻሸመኔ በፍጥነት ማሽከርከር ጀመረች። ክፍል አስራ አንድ ይቀጥላል..... .................. @nuiman_veiw ...................
نمایش همه...
ሜካፕ የሴት ልጅ ውበቷን እንጂ አኽላቋን አያሳምርላትም😕 📩 @zewjeti
نمایش همه...
1441ኛው የረመዳን ፆም አርብ ይጀመራል! በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ታላቅ ቦታ ያለው የረመዳን ፆም የፊታችን አርብ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዬች ጠቅላይ ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት ሃላፈ ዑስማን አደም ለኤፍ ቢ ሲ እንደተናገሩት ጨረቃ ዛሬ ረቡዕ ባለመታየቷ ፆሙ የሚጀመረው አርብ መሆኑን ገልፀዋል። ፆሙ አርብ የሚጀምር በመሆኑ ሀሙስ ምሽት የተራዊህ ሰላት የሚጀመር ይሆናል። ምንጭ፦ ፋና ብሮድካሲትንግ @liverpool_125
نمایش همه...
ለአላህ ብላችሁ ሸር አድርጉት መርዳት የሚፈልግ 0900222334
نمایش همه...
3.77 MB
ለጥንቃቄ ይህንን መልእክት ለሌላውም በማዳረስ ሌሎችም ከቫይረሱ ራሳቸውን እንዲከላከሉና እንዲጠበቁ እናድርግ! ኮሮና ቫይረስን በመጨነቅ እና በመፍራት ሳይሆን በእውቀት መራመድ ያቆመዋል! . በውሃን ቻይና በኮሮና ቫይረስ የተፈጠረውን ወረርሽኝ ለመዋጋት በስፍራው ከሚንቀሳቀስ ግብረሃይል ጋር ለመስራት ከተሰማራ ወጣት ተመራማሪ የተገኘና ኮሮና ቫይረስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ እንዴት ከሰው ወደሰው እንደሚተላለፍ እንዴት በዕለት ተዕለት የህይወት እርምጃ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ማስቆም እንደሚቻል የተሰጠ መረጃ! - ኮሮና ቫይረስ የአፍንጫ እርጥበት እና አክታ የሚያስከትል ሳል ያለው አይደለም፡፡ በተቃራኒው አፍንጫ የማያረጥብ እና ደረቅ ሳል የሚያስከትል በመሆኑ በቀላሉ ልንረዳው የምንችለው ነው፡፡ - ቫይረሱ ከ26-27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያለውን ሙቀት መቋቋም የማይችል በመሆኑ ይሞታል፡፡ ስለዚህ እንደ ሻይ፣ ሾርባ ፣ ትኩስ ውሃ ...ወዘተ ያለትን ትኩስ ነገሮች በየቀኑ ደጋግሞ መጠጣት ቫይረሱን ይገድበዋል፡፡ ትኩስ ነገሮችን መጠጣት ደግሞ ከባድ አይደለም፡፡ - በጣም የቀዘቀዘ ውሃ አትጠጡ፣ የበረዶ ኩቦችን ወይም አመዳይ/Snow አትመገቡ! - የምትችሉ ሁሉ የጸሐይ ሙቀት ተቀበሉ፡፡ - ኮሮና ቫይረስ ከ400-500 ናኖሜትር ዳያሜትር ርዝመት ያለው ትልቅ ቫይረስ በመሆኑ ለመከላከል የሚያስፈልገው ጭምብል ወይም ማስክ በተለየ መንገድ የተሰራ መሆን የለበትም፡፡ ማንኛውንም አይነት ጭምብል መጠቀም ይቻላል፡፡ - በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች በሚገኙባቸው ተቋማት የሚያክሙ የጤና ባለሙያዎች ግን የተለዩ የመከላከያ መንገዶችን መጠቀም አለባቸው፡፡ - አንድ በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ከፊት ለፊታችሁ ከ3 ሜትር ርቀት ላይ ቢያስነጥስ ቫይረሶቹ ወደ ምድር የሚወድቁ በመሆናቸው በቫይረሱ ተጠቂ አትሆኑም፡፡ - ቫይረሱ ብረትነት ባላቸው ገጾች/አካሎች ላይ ካረፈ በኋላ ለ12 ሠዓታት በህይወት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ ከብረት የተሰሩ እንደእጀታዎች፣ በሮች፣ የቤት ዕቃዎችን፣ የአውቶቡስ የባቡር ወይም የትራም መደገፊያ እጀታዎችን ወይም ምሰሶዎችን ከነካችሁ በኋላ እጃችሁን በደምብ በሳሙና መታጠብ ይገባል፡፡ - ቫይረሱ በልብስ እና በጨርቆች ውስጥ ተሰግስጎ ከ6-12 ሰዓታት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ መታጠብ የሚችሉትን ልብሶች በሙሉ ዘወትር በምንጠቀምባቸው ሳሙናዎች ብናጥባቸው ቫይረሱን ይገድለዋል፡፡ በየእለቱ መታጠብ የማይችሉ ልብሶችን ጸሐይ ላይ ብታሰጧቸው ቫይረሱን የጸሐይ ሙቀት ይገድለዋል፡፡ . በቫይረሱ የመጠቃት ምልክቶች ምን ምንድን ናቸው? 1. ቫይረሱ መጀመሪያ መቀመጫውን ጎሮሮ ላይ በማድረግ የጉሮሮ ብግነት እና የጎሮሮ ድርቀት ስሜት ያስከትላል፡፡ ይህ የህመም ስሜት ከ3-4 ቀን በሰው ላይ ሊቆይ ይችላል:: 2. ቫይረሱ በመተንፈሻ ቱቦ ውስጥ ያለውን እርጥበት በመጠቀም ወደትራኪያ ከወረደ በኋላ መቀመጫውን ሳምባ ውስጥ ያደርጋል፡፡ ሳምባን በማጥቃት ኒሞንያ/ የሳምባ ብግነት ያስከላል፡፡ ይህ ምልክት የሚታይባችሁ ሁሉ በፍጥነት ወደ ህክምና ሂዱ!! . በቫይረሱ ላለመያዝ ምን ማድረግ ይገባል? 1. የቫይረሱ ስርጭት በአብዛኛው ቀጥታ ከንክኪ ጋር የተያያዘ ሲሆን ቫይረሱ ያረፈባቸውን ቁሳቁሶች እና ልብሶች ወዘተ... መጠቀም ዋነኛ መተላለፊያው መንገዱ ነው፡፡ ይህም ማናቸውንም ነገር ከነኩ በኋላ በተደጋጋሚ እጅን በደምብ መታጠብ ዋነኛ መከላከያ መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡ 2. ቫይረሱ በሰው እጅ ላይ በሕይወት መቆየት የሚችለው 10 ደቂቃ ያህል ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአስር ደቂቃዎች ውስጥ ብዙ ነገር ሊከናወን ይችላል፡- አይንን ማሸት፣ አፍንጫን መንካት፣ ጣቶችን ወደ አፍ መውሰድ ወይም [እንደ ጥፍር የመመጥመጥ ክፉ ልማድ] ቫይረሱን በቀላሉ ወደ ጉሮሮ እንዲሄድ ሊያደርገው ይችላል፡፡ 3. ስለዚህ ለራሳችሁና ለባልንጀራችሁ (ለሌላው ሰው) ደህንነት ስትሉ በጣም በተደጋጋሚ እጆቻችሁን ታጠቡ፡፡ 4. አፍ እና ጉሮሮን ጸረ-ተሕዋስ መድሀኒቶችን በመጠቀም መጉመጥመጥ ቫይረሱን ሊያስወግድ ወይም ወደ ጉሮሮ የሚሄዱትን መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡ አፍን መጉመጥመጥ ወደ ጉሮሮ ወደ ትራኪያ አልፎም ወደ ሳምባ ቫይረሱ የሚያደርገውን ጉዞ ሊያግደው ወይም ሊቀንሰው ይችላል፡፡ 5. የኮምፒውተራችሁን ኪ-ቦርድ እና ማውዝ በጸረ- ተህዋስ በሚገባ አጽዱ፡፡ (ከሳይንስ ማሕደር) ይህንን መልእክት ለሌላውም በማዳረስ ሌሎችም ከቫይረሱ ራሳቸውን እንዲከላከሉና እንዲጠበቁ እናድርግ!
نمایش همه...
አሏህ ሚስቶቻችሁንም / ባሎቻችሁንም እንዲሁም ልጆቻችሁን ሷሊህ ያድርግላችሁ ለሚስቶቻችሁ የትኛውን ቃል ትጠቀማላችሁ ? የኔ ሴትዮ 🙄🙄 ?? የኔ ሚስት 😍😍 ?? የኔ ጎደኛ 🤔🤔 ?? ጥያቄ ? 🤔🤔🤔 በሶስቱ ቃሎች መሀል ያለው ልዩነት ምንድን ነው ሴት ሚስት ጎደኛ ? መልስ : ሴት : በአንድ ወንድና ሴት መሀል የአካል መቀራረብ ኖሮ ነገር ግን የአስተሳሰብና የውዴታ መገጣጠም ከሌለ " ሴት " የሚለውን እንጠቀማለን ። ሚስት : በሁለቱ መሀል የአካል መቀራረብ ኖሮ በተጨማሪ በአስተሳሰብና በፍቅር መገጣጠም ካለ " ሚስት " እንላለን ﻗﺎﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ : ‏( ﺍﻣﺮﺃﺓ ﻧﻮﺡ ‏) የኑህ ሴት ‏( ﺍﻣﺮﺃﺓ ﻟﻮﻁ ‏) የሉጥ ሴት የኑህ ሚስት ወይም የሉጥ ሚስት ብሎ አልጠራቸውም ምክኒያቱም በመሀላቸው የእምነት ልዩነት ስለነበረ !!! ሁለቱም ነብያቶች የነበሩ ሴቶቹ ግን ያላመኑ ነበሩና ሁለቱንም ሴት በሚል ጠቀሳቸው ። የፊርዓውንን ሚስት እንደዚሁ " ሴት " በሚል አወሳት ምክኒያቱም እሷ በአሏህ አንድነት ስታምን እሱ ደግሞ በክህደቱ ቀጠለ ስለዚህ " ሴት " እንጅ ሚስት አላለም ። በሌላ ቦታ ደግሞ ቁርአን " ሚስት " የሚለውን በእምታቸውና በአካል የተዛመዱትን ሲያወሳ እንመልከት ስለ አባታችን አደም ቁርአን እንዲህ አለ : ( ﻭﻗﻠﻨﺎ ﻳﺎ ءاﺩﻡ ﺍﺳﻜﻦ ﺃﻧﺖ ﻭﺯﻭﺟﻚ ﺍﻟﺠﻨﺔ ‏) አዳም ሆይ! አንተም ሚስትህም በገነት ተቀመጡ ። ነብያችንን ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም በተመለከተ ደግሞ : ‏( ﻳﺎ ﺃﻳﻬﺎ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﻗﻞ ﻷﺯﻭﺍﺟﻚ ‏) አንተ ነብይ ሆይ ለሚስቶችህ እንዲህ በላቸው በመሀላቸው የእምነትም ሆነ የፍቅር የአካል መወዳጀት ስለነበር " ሚስት " በሚል አወሳ ። ሰይዲና ዘከሪያ ዓለይሂ ሰላም ሚስታቸው በእምነትም በአካልም በፍቅርም ተወዳጅተው እያለ እሳቸው ግን " ሴት " የሚለውን ቃል ተጠቅመው ነበር ቁርአን እንዲህ ይነግረናል ﻳﻘﻮﻝ الله تعالى : ‏( ﻭﻛﺎﻧﺖ ﺍﻣﺮﺃﺗﻲ ﻋﺎﻗﺮﺍً ‏) ሚስቴም መካን ነበረች ምክኒያቱ ደግሞ ባለመውለዷ በመሀላቸው ችግር እንዳለ ለማመላከት ጭንቀታቸውን ወደ አሏህ አቤቱታ እያቀረቡ ስለነበር ። ነገር ግን አሏህ ከሷ ልጅ ከሰጣቸው በሃላ ቁርአን ላይ እንዲህ ተቀምጦ እማገኘዋለን „ فقال الله تعالى ‏( ﻓﺎﺳﺘﺠﺒﻨﺎ ﻟﻪ ﻭﻭﻫﺒﻨﺎ ﻟﻪ ﻳﺤﻴﻰ ﻭﺃﺻﻠﺤﻨﺎ ﻟﻪ ﺯﻭﺟﻪ ‏). ጥሪውን ተቀልን ምላሽም ሰጠነው የህያ የሚባል ልጅም ሰጠነው " ሚስቱንም" እንድተወልድ አደረግን ይላል አቡ ለሀብ ቤት አለመግባባት መኖሩን አሏህ አጋልጧለረ ﻓﻘﺎﻝ ﺗﻌﺎﻟﻰ : ‏( ﻭﺍﻣﺮﺃﺗﻪ ﺣﻤﺎﻟﺔ ﺍﻟﺤﻄﺐ ‏) ሴትዮዋም እንጨት ተሸካሞ ናት በሁለቱ መሀል ምንም አይነት መጣጣም አለመኖሩን ለማሳየት !!! ባልደረባ ( ጎደኛ ) በባልና ሚስት መሀል የአስተሳሰብ ብሎም የአካል መወዳጀት ሲጠፋ ቁርአን ጎደኛ ( ባልደረባ ) የሚለውን ይጠቀማል አሏህ ብዙ ቦታ ላይ በቂያማ ቀን ክስተት ላይ ባልደረባ የሚለውን ቃል ይጠቀማል قال تعالى : ‏( ﻳﻮﻡ ﻳﻔﺮ ﺍﻟﻤﺮﺀ ﻣﻦ ﺃﺧﻴﻪ ﻭﺃﻣﻪ ﺃﺑﻴﻪ ﻭﺻﺎﺣﺒﺘﻪ ﻭﺑﻨﻴﻪ ‏). ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን ከናቱም ከአባቱም ከባልደረባውም ከልጁም አስፈሪ ቀን በመሆኑ ሁላቸውም በራሳቸው ጉዳይ በመጨነቅ የአካልም ሆነ የመተሳሰብ ሁኔታው ስለተቋረጠ ﻓﺴﺒﺤﺎﻥ ﺍﻟﻠﻪ الذي أنزل هذا الكتاب المعجز والذي قال فيه في سورة االإسراء - الآية 88 (قُل لَّئِنِ اجْتَمَعَتِ الْإِنسُ وَالْجِنُّ عَلَىٰ أَن يَأْتُوا بِمِثْلِ هَٰذَا الْقُرْآنِ لَا يَأْتُونَ بِمِثْلِهِ وَلَوْ كَانَ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ ظَهِيرا.) جعلنا الله جميعاً ممن يقولون: (رَبَّنَا هَبْ لَنَا مِنْ أَزْوَاجِنَا وَذُرِّيَّاتِنَا قُرَّةَ أَعْيُنٍ وَاجْعَلْنَا لِلْمُتَّقِينَ إِمَاما ) أعجبتني فتمنيت لكم الفائدة فنقلتها لكم . t.me/zewjeti 🌺 ሁሉም ነገር ላይመለስ ይጎዛል … ዱዓ ሲቀር በምኞት ልከሀው ስጦታ ይዞ ይመለሳል …💐 ያ አሏህ ንግግሬ የደረሰቻቸውን ሁሉ በቀልባቸው ውስጥ ደስታን ሙላላቸው, ያንተን ፍቅርና ውዴታ ለግሳቸው አንተን የወደደን ሁሉ ውዴታንም ጭምር ወፍቃቸው, አምላኬ ሆይ ወዳንተ የሚያቃርብ ማንኛውንም ስራ እንዲሰሩ አግራላቸው, በምድርህ ላይ የተረጋጉ ሆነው እንጅ አይጎዙ እዝነትህ በየትም ሆነው ይከተላቸው ጭንቀታቸውን አንሳላቸው መልካሙን ነገር ሁሉ አግራላቸው ያ ረብ !!!
نمایش همه...
ሀላል ትዳር❤️

...................ፍቅርን.......................... በትዳር ውስጥ ..................ፈልጉ።......................... ትዳር የእውነተኛ ፍቅር መገኛ 💝ተዘወጅ በነቢዬ ሱና ሀላል ትዳርን ላይ ላለዎት የትኛውም አስተያየት እና ጥቆማ @Abuyabot

یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.