cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

የሰበታ መ/ሠ/ቅ/ገብርኤል ቤተክርስቲያን ፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት ⓵⓽⓼⓪ዓ.ም⛪️

ይህ ቻናል የሰበታ መካነ ሠላም ፍሬ-ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት የቴሌግራም ገፅ ነው። ከ1980 ዓ.ም ጀምሮ⛪️ ⏯በዚህ ገፅ👇 ⏺ ትምህርቶች ⏺ መልዕክቶች እና ⏺ የሰንበት ትምህርት ቤታችን የስራ እንቅስቃሴ ለፍ/ሃ/ሰ/ት/ቤት አባላት የሚደርሱበት ነው ለአስተያየት እና ሃሳብ ለመስጠት ይህንን ሊንክ 👉🏻 https://t.me/+hq8Lt_LJfeRlOTNk ይጠቀሙ.

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
387
مشترکین
-124 ساعت
+17 روز
+830 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

"የተራበውን ማብላት፥ የተጠማውንም ሰው ማጠጣት የሞተ ሰውን ከማስነሣት ይበልጣል፡፡" 👉ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
نمایش همه...
1
ውድ በሁለተኛው ዙር ለ12ኛ ክፍል ለተፈጥሮ ሳይንስ (natural science)ፈተና ወደ ዩኒቨርስቲ እየገባችሁ ላላችሁ አባሎቻችን ሰንበት ትምህርት ቤታችሁ  መልካም ምኞቱን ይገልፅላችኃል።         👉እንደ ከዚህ ቀደሙ ሰንበት ትምህርት ቤታችሁን እንደምታስጠሩ ተስፋ አለን 👉ሁላችንም አባላት ለወንድም እህቶቻችን እግዚአብሔር እንዲረዳቸው ሰላም ለኪ እና አቡነ ዘበሰማያት እንድንደግምላቸው በእግዚአብሔር ፍቅር እናሳስባለን 🌟የአባቶቻችን የአብርሃም ፥ የይስሐቅ ፥ የያዕቆብ አምላክ ማስተዋሉን ፥ ጥበቡን ፥ አእምሮውን ያድላችሁ። እመ አምላክ ከፊታችሁ ትቅደም።🙏                 መልካም ፈተና መልካም ዕድል
نمایش همه...
🙏 2
#ቅድስት_ሥላሴ - (#ሐምሌ_7) ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡ የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡ አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡ በዚያው ዕለትም የይስሃቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የመረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡ ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ ዘፍ 18፡1-25፣ ሮሜ 4፡-3፡፡ ቀትር ሰዓት ላይ በድንኳኑ ደጅ ተቀምጦ እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር ታየው ተነጋገረው፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዐይኑን አራምዶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ላይ ቆመው አያቸው፣ ወደ እርሱም ሲወርዱ አይቶ ፈጥኖ ሄዶ ከሰግደላቸው በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ…›› እያለ በትሕትና በመጋበዝ ወደ ድንኳኑ አስገብቶ በሚገባ ጋበዛቸው፡፡ ‹‹በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፣ ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡ ያች ሥላሴ የገቡባት የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ሁሉ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋዋን ለመዋሐድ የማደራቸው ምሳሌ በመሆኑ አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ናት፡፡ ሉቃ 1፡35፡፡ እግዚአብሔርም አብርሃምን የዛሬ ዓመት ልጅ እንደሚወልድ ነግሮት በዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል፡፡ ሁለቱ ሰዎች ከአብርሃም ድንኳን ወጥተው ወደ ሰዶም ወደ ገሞራ ሄዱ፣ አብርሃምም ይሸኛቸው ዘንድ አብሯቸው ሄደ፡፡ የሄዱትም ሁለቱ ሰዎች አብና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዱ ወልድ በአብርሃም ቤት ቀርቷል ይኸውም ከቤተ አብርሃም ሰው እንደሚሆን ለማጠየቅ ነው፡፡ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፡፡ እግዚአብሔርም የሚሠራውን ሁሉ ከአብርሃም አይሠውርም ነበርና የሰዶምን የገሞራን ጥፋት ነገረው፡፡ አብርሃምም ይቅር እንዲላቸው አብዝቶ ለመነላቸው፡፡ ሥሉስ ቅዱስን የአብርሃሙ ሥላሴን በምግባር በሃይማኖት ሆነን እናገለግል ዘንድ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን! 👉ስንክሳር ዘተዋሕዶ ፌስቡክ ገጽ የተወሰደ
نمایش همه...
🙏 1
አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር፤ ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር! ኹልጊዜ ተማር። ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር። ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ። ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም። ስለዚህ ተማር! ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለህ። ይህች የንስሓ በር ትኾንልሃለች፡፡ አንድ ቀን ወደ ንስሓም ትመራሃለች። 👉ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
نمایش همه...
4
“መድኅን ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ሚስት ያፈቅራታል፤ እንደ ልጅ ይወዳታል፤ እንደ አገልጋዩ ያሳድራታል (ይመግባታል)፤ እንደ ድንግል ልጁ ይጠብቃታል፤ እንደ አትክልት ሥፍራው ይከልላታል፤ እንደ አካሉም ይንከባከባታል።  እንደ ራስ ኾኖ ይመግባታል፤ እንደ ሥር ኾኖ ያሳድጋታል፤ እንደ እረኛ በለመለመ መስክ ያሰማራታል፤ እንደ ሙሽሪት ያገባታል፤ እንደ ታራቂ ይቅር ይላታል፤ እንደ በግ ይሠዋላታል፤ እንደ ሙሽራ በውበቷ ይማረካል፤ እንደ ባልም ደግሞ ረዳት ይኾንላታል።" 👉ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ©ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
نمایش همه...
1
"ነገር ኹሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን ! !! አንድ አንዴ በሕይወታችን ምንም የማይጠቅሙ ነገሮችን ልንመርጥ እንችላለን ።የሚያስፈልገንና የማይጠቅመን ግን መንፈስ ቅዱስ ሲመርጥልን  ነው።" አደጋና ስጋት ፡በሽታና ስቃይ ፡እጦትና ችግር ፡ራብና ጥማት ፡ኅዘንና ትካዜ ፡የሌለው ሕይወት እጅግ ጠቃሜ እንደ ኮነ አድርገን እናስባለን ነገር ግን ይህን የሌለው ሕይወት ኹሉ ጠቃሜ ላይኾን ይችላል ። እንደ ራሳችን ሓሳብ ሳይኾን እንደ እግዚአብሔር ሓሳብ ስንጓዝ ግን ነገር ኹሉ ለበጎ ነው ። ነገር ኹሉ ሲባልም በእኛ እይታ በጎ ነው የምንለው ብቻ አይደለም ፡ ክፉ ነው የምንለውም ጭምር እንጂ።እንደ እግዚአብሔር ሓሳብ ስሆን ማግኘትም ማጣትም ፡ጤንነትም በሽታም ለበጎ ነው። እግዚአብሔር ለእኛ መልካም የሚያደርግልን በጎ ነው ብለን በምናስበው ነገር ብቻ አይደለም። እጅግም ክፉና አስቸጋሪ መስለው ከሚታዩን ኹኔታዎችም ለእኛ ለልጆቹ እጅግ የሚደንቅና በጎ ነገርን ማድረግ ይችልበታል። 👉በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 
نمایش همه...
2👍 1
ውድ በመጀመሪያው  ዙር ለ12ኛ ክፍል የሶሻል ሳይንስ ፈተና ወደ ዩኒቨርስቲ እየገባችሁ ላላችሁ አባሎቻችን ሰንበት ትምህርት ቤታችሁ  መልካም ምኞቱን ይገልፅላችኃል።         👉እንደ ከዚህ ቀደሙ ሰንበት ትምህርት ቤታችሁን እንደምታስጠሩ ተስፋ አለን 👉ሁላችንም አባላት ለወንድም እህቶቻችን እግዚአብሔር እንዲረዳቸው ሰላም ለኪ እና አቡነ ዘበሰማያት እንድንደግምላቸው በእግዚአብሔር ፍቅር እናሳስባለን 🌟የአባቶቻችን የአብርሃም ፥ የይስሐቅ ፥ የያዕቆብ አምላክ ማስተዋሉን ፥ ጥበቡን ፥ አእምሮውን ያድላችሁ። እመ አምላክ ከፊታችሁ ትቅደም።🙏                 መልካም ፈተና መልካም ዕድል
نمایش همه...
11🙏 5
#ሰኔ_30 #መጥምቁ_ቅዱስ_ዮሐንስ ሰኔ ሠላሳ በዚች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ መጥምቁ ዮሐንስ ተወለደ። ይህም በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለእግዚአብሔር ልጅ የሰገደው ነው። ይህም በመድኅን ክርስቶስ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው። በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች። ዘመዶቿና ጐረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለርስዋ ደስ አላቸው። በስምንተኛውም ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት። እናቱ ግን አይሆንም ዮሐንስ ይባል አለች። ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም አሏት። አባቱንም ጠቅሰው ማን ሊባል ትወዳለህ አሉት። እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ይባል ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ። ያን ጊዜም አንደበቱ ከድዳነት ተፈትቶለት ተናገረ እግዚአብሔርንም ፈጽሞ አመሰገነው። ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም የልዑል ነቢይ እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ። ሰብአ ሰገልም መጥተው ከሔዱ በኋላ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃኑ ዮሐንስ ለሄሮድስ ነገሩት እንዲገድሉትም ጭፍሮችን ላከ ጭፍሮችም ወደ አባቱ ዘካርያስ መጡ ሕፃኑንም ከእርሱ ፈለጉት አባቱም አንሥቶ በትከሻዎቹ ተሸክሞ ወደ ቤተ መቅደስ ከእርሱ ጋራ እንዲሔዱና ሕፃኑን ከዚያ እንዲወስዱት ወታደሮችን ለመናቸው። ከዚህም በኋላ ሕፃኑን በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኖረውና ከዚህ ራሳችሁ ተቀብላችሁ ውሰዱት አላቸው ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው። ጭፍሮችም ባላገኙት ጊዜ አባቱ ዘካርያስን ገደሉት። ሕፃኑ ግን አድጎ ለእስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ኖረ። የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ ጥርጊያውንም አስተካክሉ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እነሆ ብሎ ኢሳይያስ የተናገረለት ይህ ነው። ሚልክያስም ስለሱ እንዲህ አለ። በፊትህ ጐዳናዬን አስተካክሎ የሚጠርግ መልእክተኛዬን እኔ እሰዳለሁ። ራሱ መድኃኒታችንም ስለርሱ ሲናገር ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጠው የለም ብሏል። ይህ የእግዚአብሔርን ልጅ በአጠመቀውና የማትዳሠሥ ራሱን በዳሠሠው ጊዜ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት የሚል የአብን ቃል ሰምቷልና። ዳግመኛም ክብር ይግባውና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀመጥ አየ። እኛም መድኃኒታችን እንዲምረንና ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ፡፡ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱም እኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። 👉#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.