cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Art of life

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
143
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ግንቦት 20 አይቀርም #ከሲሳይ Azusa ጋ #ወጣቶች በመንፈስ ሚሰክሩበት ቀን #ወጣቶች ከእስራት ሚፈቱበት ቀን🔥 #ወጣቶች በአምልኮ ሚፈሱበት ቀን🔥 #የታመሙ ሰዎች ሚፈወሱበት ቀን🔥 #ኢየሱስ ብቻውን ሚከብርበት ቀን🔥 🔥ከጠዋቱ 2:00-9:00🔥 #አድራሻ:- ከመገናኛ CmC Taxi ይዛቹ ሴንቸሪ ሞል ጋ መውረድ ከዛ ሚቀበሏቹ ልጆቹ አሉ #House of Christ ቸርች👇👇👇👇👇👇 🚨Photo FB ላይ Post አድርጉት😍🚨🚨
نمایش همه...
ስላደክ ነው💪💪💪💪 ልጅ እያለክ የሚያሳስብክ ወንዝ ይህ ነበረ የሚያስጨንቅክም ይህ እራሱ ነበር ስታድግ ግን " አባይ" ሆነ አየህ ችግርህ እለት እለት እያደገ ከመጣ አንተም አድገሀል ማለት ነው እርግጠኛ ሆኜ ልንገርህ የማታልፈው ፈተና የለም ሁሉም በአቅምህ እና እንዳቅምህ መጥቷል ተጋፈጠው @Artlifewith
نمایش همه...
#ለጊዜው #ሞት #ሞቷል 💀💀💀💀💀💀💀 "ለሁሉ ጊዜ አለው " ሲለኝ ሰለሞን አላግጬ ነበር ደግሜ ቃሉን "ለሁሉ ጊዜ አለው ካልከኝ ሰለሞን ሞት የሚሞትበት ጊዜው መች ይሁን?" እያልኩኝ እያሾፍኩ ቀልጄ ነበረ አሁን ግን ሲገባኝ ቃሌም ተቀየረ መወለድ ማደጉ ማርጀቱ መሞቱ በሰላም ተወጥቶ በሰላም መግባቱ ሁሌም አይቀጥልም ይቆማል በወቅቱ ምክንያቱም ተነግሯል "ሁሉም በሰዓቱ " በተለምዶ ህይወት እየኖርን ሳለን ሰማዩ ተቀዶ ድምፅን እንሰማለን ድምፁ አዲስ ነው እጅጉን አስፈሪ ሁሉም ግን ያውቀዋል በምድር ላይ ኗሪ ሲጠብቅ የኖረ ተንበርክኮ ይሰግዳል ሲጠበቅ የኖረም በምሬት ያለቅሳል ድንገት በዚህ ቅፅበት ምድሩ ይፈርሳል ሰማይ ዝቅ ብሎ ልጆቹን ያነሳል በልጁ አምኖ ልጅነት የገባው በፅድቅ ለመኖር አጅጉን የተጋው ይሄን ቀን ለማየት ከልቡ የጓጓው ከዘላቂ ህይወት ጋር ይከፈላል ዋጋው በምድር ህይወቱ እጅግ ያላገጠ የከበረውን ቃል ንቆ የረገጠ በሰፊ ጎዳና ተዝናንቶ ለሄደው ለትንሿ አለም ትልቁን ለካደው ድንገት....ቀኑ ይጨልማል የፀፀት መዓቱ በላዩ ይዘንባል "ምነው ባደመጥኩኝ" እያለ ያነባል ታድያ ምን ያደርጋል..... ድምፁ የሚያስፈራው ፊቱ የሚያበራው ብዙ መላዕክትን ከጎኑ የሰራው ልጆቹን ያቅፍ እና ወደላይ እየወጣ ቃልን ይናገራል እንባው እየመጣ "ጊዜ ነበራችሁ እኔን የማድመጫ ከጨለማው አለም እሮጦ የመውጫ ነገር ግን ደንድኖ ውስጣችሁ ጨከነ በማይረባው ነገር ልባቹ ባከነ አሁን ጊዜ ረፍዷል.... ምህረቴ ተነስቶ ከዚህ አለም ሄዷል ከዚህ በኋላ ሲቃ ከዚህ በኋላ ጩኸት ጊዜው የጥልቁ ነው የሚፈነጭበት" ብሎ እንደተናገረ ከእይታ ይጠፋል የጭፍሮች አለቃ ከጥልቁ ይተፋል ለዘመናት በእስር የቆየው አለቃ ተንገብግቦ ይወጣል ልጆቹን ሊያደቃ "አንዴት ቆየሽ ምድር እንዴት ቆየሽ ሀጥያት ሚናገረኝ የለም አሁን በዚህ ሰዓት ውዶቹ ልጆቼ እንደምን ቆያቹ ጓጉቼ ነበረ በአይኔ እስካያቹ" ብሎ እያጓራ ከት ብሎ ይስቃል ጭፍራው ተከትሎት ከእርሱ ጋር ያደምቃል በምድር ሚኖረው ህዝብ እያለቀሰ ለጭፍሮች አለቃ እንባ አፈሰሰ ምህረትን ለማያውቅ ምህረት መጠየቁ የማይታሰብ ነው መች ይሄን አወቁ ልብሳቸውን ቀደው ምድርን ሲቧጥጡ በፍርሀት ማዕበል ተንጠው ሲዋጡ ለጭፍሮች ደስታ ለሰዎች በሽታ አእምሮ ያላቀደው የምድር ላይ ዋይታ እነሆ "ሀ" ተብሎ ስቃይ ተጀመረ አለቃ ተብየው ሰው እየወረወረ ከአይኖች እንባ ሳይሆን ደም እየፈለቀ መንገዱን መሳቱን ሁሉም ሰው አወቀ በረፈደ ሰዓት ለንስሀ ቢሮጥ "ይቅርታ" እያለ ወገቡ እስኪቆረጥ ፊቱንም ቢቧጭር ደረቱን ቢደቃ ጩኸቱ ከንቱ ነው ጊዜው ስላበቃ ሰይጣን ተደስቶ ከልቡ ይስቃል ክቡሩ የሰው ልጅ ከእግሩ ስር ወድቋል መከራ መሸከም እጅግ ሲከብዳቸው ሞት የሚሉት ነገር ወድያው ታወሳቸው እግሮችም ፈጠኑ ወደ ሞት ጎዳና ከዚህ በላይ ስቃይ አይኖርም አሉና "ይሄን አለም ትቼ ወደላይ ሮጣለው ከማየው መከራ ሲዖል እመርጣለው" ቃላቸው ነበረ የእነሱ ድስኮራ ቃልኪዳን የገቡት ከታላቅ ሞት ጋራ ከእነሱም መካከል አንደኛው እሮጦ ሊጠፋ ወሰነ ኤሌትሪክ ጨብጦ ልፋ ቢለው እና ቢያደርገው ቀውላላ ሞት የሚሉት የለም ከጭፈራ ሌላ ሌላኛዋም ሄደች..... ከታላቅ አፋፍ ላይ ራሷን ወረወረች ይሄን አለም ትታ ጥላ እንደሄደችው ተቀበለኝ ብላ አይኗን ጨፈነችው ከደቂቃዎች በኋላ አይኗን ስታበራ ንቅንቅ አላለችም ከዚያ ከመከራ በቀጣይ የመጡት አንድ አዛውንት ናቸው መከራው ሳይመጣም ሞቱ ሚያምርባቸው ትልቅ ካራ ቢጤ ይዘው በእጃቸው በሆዳቸው ላኩት አፍጦ አይናቸው ካራው በሆድ ገብቶ በጀርባቸው ወጣ ከልብ ተማፀኑ ነፍሳቸው እንድትወጣ መሬት በርከክ ብለው ትንሽ አቃሰቱ ሚሞቱ መስሏቸው በጣም ተደሰቱ ነገር ግን ከየት ይምጣ ሞት ሚሉት ገላጋይ ቢፈለግ ቢዳሰስ ምድርና ሰማይ እድሜ ዘመናቸው እየሸሹት ኖረው ዛሬ ግን...ቢፈልጉት የለም ከመሬት ቆፍረው ግማሹ ይሮጣል በረኪና ይጠጣል አንዳንዱ ተቻኩሎ በእሳት ይቀልጣል ሌላኛውም መጥቶ ለሞት ዜማ ያዜማል በአሳዛኝ ቅላፄ እንደዚህም ይላል "ሞት ሆይ ከየት አለህ የትስ ትገኛለህ ድምፅህን አሰማን መቼ ትጣራለህ? ያለህበት ቦታ ፈጥኜ መጣለሁ እዚህ አለው በለኝ ወድያው እሮጣለሁ " ይህን ሁሉ ሰምቶ አለቃው ይስቃል የሰው ልጅ ሞት አጥቶ በመከራው ደቋል የሰይጣን ልፋቱ የላቡ ውጤቱ አጅግ ተደሰተ ይሄን በማየቱ ቀን ተሌት ሳይተኛ ተንኮል በማሰቡ አብዛኞቹ ሰዎች በእጁ ስር ገቡ አሁን ተደስቷል ጥሙም በጣም ረክቷል የሲኦል ሙሽራን በእጥፉ አፍርቷል ብቻውን አየገባም ወደ ጨለማው ቤት ስቃዩን ሚጋራ እጅጉን በዝቶለት ሲዖል ጋር ሳይደርሱ አዲስ ሲዖል ፈጥሮ ይፍለቀለቅ ጀመር በሰው እንጉርጉሮ የአንበጣ መንጋ ከያሉበት ወጡ መቼ በዚህ አበቃ ተጨመረ ጊንጡ የሰውን ልጅ አንቀው ደም እየመጠጡ ታይቶ ማይታወቅ መከራን አመጡ ሰለሞን አልዋሸም ለሁሉም ጊዜ አለው ሞት እንኳን ይሞታል ይኸው እምላለው አይኖቹን ጎልጉሎ እንባ እየዘራ ድረስልኝ ቢልም ፈጣሪን ቢጠራ አምላክም አይመልስ ፈፅሞ አይራራ በተሰጠው ሰዓት ተግቶ ስላልሰራ ጥርስ ሟፏጨቱ ሲቃውም በርትቷል እጅግ ቢፈለግም ለጊዜው #ሞት #ሞቷል @Artlifewith @Artlifewith @Artlifewith ✍✍✍@Besuerasu
نمایش همه...
ሰላም ሰላም የ #art of life ቻናል ተከታታዮቻችን እንደምናችሁ እኔ በጣም ደህና ነኝ ሰሞኑን በተለያዩ ምክንያቶች ወደ እናንተ ሳንመጣ እርቀን ነበር ለዚህም ከልብ የሆነ #ይቅርታ🙏🙏🙏🙏🙏🙏 በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን አሁን ከበፊቱ ለየት ባለ መልክ የተለያዩ ግጥሞችን መንፈሳዊ ልብ ወለዶችን ይዘንላችሁ ቀርበናል በቅርቡ ደግሞ #ለጊዜው #ሞት #ሞቷል የተሰኘው የመጨረሻ ዘመን የሚያሳይ እንዲሁም ደግሞ #ከዳግም #ምፅአት በኋላ አለም ምን ትመስላለች የሚለውን መልስ የያዘ ግጥም ወደ እናንተ ይደርሳል ያልተቀላቀላችሁን በፍጥነት ተቀላቀሉን 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @Artlifewith @Artlifewith @Artlifewith 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
نمایش همه...
🌼🌼 #አዲስ አመት 🌼🌼 አሮጌው ተረስቶ አዲሱ ሲመጣ በአደይ አበባ ምድር አጎጥጉጣ 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 ሰማይ ማኩረፍ ትቶ ፀሀይ ስትወጣ ይሄኔ ይባላል "አዲስ አመት መጣ" እውነት ነው መጥቷል አዲሱ አመት እኛ ግን አልሄድንም ዛሬም ወደፊት ቀንና ማታ ብርድና ሙቀቱ ሲፈራረቁብን ሁሌም በየወቅቱ እዛው ነው ያለነው ሳናንስ ሳንበዛ የህይወትን ብርሀን አርገ ነው ደብዛዛ ታድያ ምን ፈየደ የአዲሱ መምጣት እኛ ካልተጓዝን ካልሄድን ወደ ፊት ታድያ ምን ጠቀመ "እንኳን አደረሰህ! እንኳን አደረሰሽ!" ብሎ መናገሩ እኛ ሰምጠን ሳለ አመት መሻገሩ የምድርን ለውጥ አይተን ስናደንቅ ውስጣችን አርጅቶ ፈራርሰን ስንወድቅ ለምን ተዘመረ ተብሎ "እንቁጣጣሽ" እኔ ሳልራመድ "እንኳን ደህና መጣሽ!" የማይሆን ነገር ነው እጅግ አስቸጋሪ ውስጥሽ አዲስ ሳይሆን ለአዲስ አትዘምሪ እጅግ አስቸጋሪ የማይሆን ነገር ውስጥህ አዲስ ሳይሆን ለአዲስ አትዘምር የአዲስነት #ፍቅር የመለወጥ እሳት ፈንድቶ ሲወጣ እሱ ሳይደርስብህ አንተ ነህ ምትመጣ አምና እንዲመጣ በክብር ተጠምተን ዘንድሮ ላይ ስንደርስ ረገጥነው አውጥተን አንተ ግን አዲስ ሁን ፍፁም አትረገጥ አዲሱ ሳይመጣ ቀድመኸው ተለወጥ ሁለት አዳዲሶች ሚገናኙ ለታ ምድር ትዘላለች በፍቅር በርትታ እግዜርም ይስቃል አዲስ ነገር አይቶ የመፍጠሩ አላማ እቅዱ ተሳክቶ በአዲስ ማንነት መልካም አዲስ አመት 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 ✍በሱፍቃድ ደርጉ (ቤቢ) 😎😎😎😎😎😎😎😎 😎😎😎😎😎😎😎😎 @besuerasu @besuerasu @besuerasu 😎😎😎😎😎😎 😎😎😎😎😎😎 4:14 ዕለተ አርብ 01/012013
نمایش همه...
ዛሬ ሁሌ እያለ እየመሰለ የማይደገም ተመልሶ የማይመጣ ለአንድ አፍታ ለቅፅበት ታይቶ ዳርቻ ከሌለው ከዘላለም ጠፈር ገብቶ የሚሰወር በትናንትና በነገ መሀል የተሸነቆረ "እንቁ" ነው 💎 💎💎💎💎💎💎 💎💎💎💎💎💎 @Artlifewith @Artlifewith @Artlifewith 💎💎💎💎💎💎 💎💎💎💎💎💎
نمایش همه...
በምድር ላይ ስትኖር እንደሞተ ሰው ኑር ያኔ ለመኖር የሚያጓጓህህ ለመሞት የሚያስፈራህ አንዳች ነገር የለም 👌👌👌👌👌👌👌 @Besuerasu 👌👌👌👌👌👌👌
نمایش همه...