cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Haděř Tubê 😍ከአሺቆች መንደር

👉 የቻናሉ አላማው 👌ኦሪጂናል የቂብላ ሀድራወች 👌እንዲሁም ደርሶች 👌የአሪፎች ቂሶወች የቆዩ እና አዳዲስ  ሀድራወችን👏 ለእናንተ እያደረስን በሶፈአ የምንጓረፍ ይሆናል ከእኛ ጋር ሁኑ🤗 le astayete #in box me @lovesmylife8 ❤❤hadera tube on muaz ne....🙌🙌

نمایش بیشتر
أثيوبيا10 995زبان مشخص نشده استدین و مذهبی92 832
پست‌های تبلیغاتی
263
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ይነበብ ✍️ከYe Dro Sew  ከጊዜ ወደጊዜ ሀሪማዎች ላይ የሚታዩ ዘግናኝ የ አደብ ጥሰቶችን አንስተህ ስታወራ የተለመደ አስቂኝ አባባል አለ.. አባባሉ ትክክል ቢሆንም ሰዎች ለነፍሲያቸው ምቾት ሲጠቀሙበት ማየት እጅግ ያስቃል.. <<ቦታው ጠባቂ አለው አንተ አትጠብቀውም😎>> ይሉሀል...የአላህ ቤት መስጂድ ጠባቂ ስለሌለው ነው አደብ ያስፈለገው?..መካ እና መዲና በመቶዎች በሚቆጠሩ ታጣቂ ወታደሮች የሚጠበቁት ጠባቂ ስለሌላቸው ነው?.. ይሄ ነፍሲያ ምቾቷ እንዳይነካባት የምትፈጥረው ማታለያ ነው.. እንደ መስጂዶች እና ሀሪማዎች ጠባቂ የሚያስፈልጋቸው ሴንሴቲቭ ቦታዎች የሉም..እኛ ለቦታው በሰጠው ሀያዕ እና ክብር ልክ ነው  የምንሰራው ኢባዳ ቀቡሊያው የሚመዘነው.. ድቤ ደብድቦ ለመምጣት አይደለም መውሊድ ተብሎ ወደ ሀሪማዎች የሚኬደው..ጫት በልቶ ለመምጣትም አይደለም..ደጋግ ቀዲሞቹ እነዛ ትላልቆቹ አብሬት ለመድረስ 50 ኪሎ ሜትር ሲቀራቸው ለክብሩ ጫማቸውን አውልቀው ከፈረሳቸው ላይ ወርደው በባዶ እግራቸው ነበር ይሚጏዙት.. ከረጀብ እስከ ረጀብ በናፍቆት የሚጠብቁት..የኑር ሀሪማ ነው.. ቀዲሞቹ መጥተው ያለንበትን ሀለት አይተው ቢሆን ኖሮ እጅግ ባፈሩ ነበር..አንድ ሰው ያጫወተኝን ልንገራቹሁማ. የሆኑ ሰዎች አብሬት ሀሪማ ሄደው ዘይረው ተመለሱና አባቴ ዘንድ ለዚያራ ገቡ..አብሬት ላይ ስለነበራቸው ቆይታ እያጫወቷቸው አወል ሶፍ ላይ  ከሸኾቹ ክፍል አጠገብ ተቀምጠው እንደነበር አጫወቷቸው.በዚህ ጊዜ አባቴ እጅግ ደነገጡ.. <<ከሸኾቹ ክፍል ከመጋረጃው አጠገብ ተቀመጣቹህ?>> ትክ ብለው እያዯቸው ደጋግመው ጠየቋቸው...አዎ ሀጂ እዛው ጋር ነበርን ብለው መለሱ....ይሄኔ አባቴ በትካዜ ወደ ድሮው ዘመን ተመልሰው እንዲህ አሉ..<<አይ ጊዜ..በፊት እዛ ቦታ ላይ ይቀመጡ የነበሩ ሰዎችን ባያቹህ..አሁን የናንተ መጫወቻ ሆነ?>> ብለው እምባ አቀረሩ.... ሰዎቹ ባንዴ ድንጋጤ ወረራቸው.. ወዳጆቼ ትላልቅ ሸኽነት የወጡ ብቁ የጠሪቃ ሼኾች ሳይቀሩ ጥምጣማቸውን ፈተው አንገት የደፉበት ሀሪማ ነው..ጉራጌ ናቸው ብላቹህ በዋዛ አትዯቸው..ተው ያከበራቹህ መስላቹ አትናቋቸው.. ተናጋሪ እና ታዛቢ የለም ብላቹህ ተው እባካቹህ የተከበረውን ቦታ አታዋርዱ..ብዙዎች የባከኑበት ቦታ ነው.... አንዲት እንኳ ፈን ሳትቀር በብቁ አሊሞች ይቀራበት የነበረበት ስፍራ ነው.. ለይለን ወነሀር በኢባዳ የሚኖሩ ሚስጊን ባሮች የሚኖሩበት ሀሪማ ነው..ቀልብ ከመድረቅ በላይ መጠረዝ ያለ እንዳይመስላቹህ.. አንድ ሰው ከደጋጎች ቤት ሲባረር ቀልቡ ነው የሚደርቀው.. እንጂ ሌላ ተዐምር የለም.. ሀሪማቸው ስንገባ ውለታ እየዋልንላቸው አናስመስለው.. ወይንም ከነ አካቴው ይቅርብን. ፊልም እንደሚሰራ ሰው ለቀረፃ የምንሄድ..እዛ ሀሪማው ላይ ያልተገቡ ወራዳ ስራዎችን የምንሰራ ክብረ ቢሶች አደብ እናድርግ!!. ሀያዕ ለራሳችን እንጂ ለሌላ ለማንም አይጠቅምም.. ሲጀመር ወላጆቻችን የት እንደምንሄድ አውቀው ፈቅደው ሲልኩን ብቻ እንሂድ..የደጋጎች ሀሪማ መዝናኛ ቦታ አይደለም..ከቤተሰብ ሸሽቶ አሸሸ ገዳሜ የሚባልበት የስክስታ ቦታ አይደለም..ይልቁንስ ከወላጆቻችን ጋር የሚያቃርብ ከአላህ ጋር ያለንን ሀላቃ የሚያሳምር..ቦታ ነው. አዋቂዎች እንሁን..አንሞኝ...ስሜታችንን ሳንገራ ሀሪማዎች ቤት ገብተን አናጨቅየው.. https://t.me/haderatubeonmuaz
نمایش همه...
Haděř Tubê 😍ከአሺቆች መንደር

👉 የቻናሉ አላማው 👌ኦሪጂናል የቂብላ ሀድራወች 👌እንዲሁም ደርሶች 👌የአሪፎች ቂሶወች የቆዩ እና አዳዲስ  ሀድራወችን👏 ለእናንተ እያደረስን በሶፈአ የምንጓረፍ ይሆናል ከእኛ ጋር ሁኑ🤗 le astayete #in box me @lovesmylife8 ❤❤hadera tube on muaz ne....🙌🙌

#ትኩረት_አድርግ( 2 ) 💭 ሴቶች እንደወንዶች ቢሆኑ ኖሮ ሕጳናት በደስታ እየቦረቁ አያድጉም ነበር ( አቡ መሕዲ ) 🧡 @ikhlasstudents™||ikhlas Tube 🧡
نمایش همه...
የ1444ኛው የረጀብ ወር በሂጅራ አቆጣጠር የ1444ኛው የረጀብ ወር ጨረቃ ዕለተ እሁድ 14-05-2015 ፀሀይ ከጠለቀች በኋላ ሸሪዓዊ በሆነ መንገድ መታየቱ ተረጋግጦልናል። በመሆኑም በሸሪዓዊ ህግ መሠረት ዕለተ ሰኞ 15-05-2015 በሂጆራ አቆጣጠር የ1444ኛው የረጀብ ወር መጀመሪያ ይሆናል። https://t.me/haderatubeonmuaz
نمایش همه...
Haděř Tubê 😍ከአሺቆች መንደር

👉 የቻናሉ አላማው 👌ኦሪጂናል የቂብላ ሀድራወች 👌እንዲሁም ደርሶች 👌የአሪፎች ቂሶወች የቆዩ እና አዳዲስ  ሀድራወችን👏 ለእናንተ እያደረስን በሶፈአ የምንጓረፍ ይሆናል ከእኛ ጋር ሁኑ🤗 le astayete #in box me @lovesmylife8 ❤❤hadera tube on muaz ne....🙌🙌

نمایش همه...
Haděř Tubê 😍ከአሺቆች መንደር

👉 የቻናሉ አላማው 👌ኦሪጂናል የቂብላ ሀድራወች 👌እንዲሁም ደርሶች 👌የአሪፎች ቂሶወች የቆዩ እና አዳዲስ  ሀድራወችን👏 ለእናንተ እያደረስን በሶፈአ የምንጓረፍ ይሆናል ከእኛ ጋር ሁኑ🤗 le astayete #in box me @lovesmylife8 ❤❤hadera tube on muaz ne....🙌🙌

በሻሻው ሸይኻችን ሸይኽ ዐብዱሏህ አል ሀረሪይ ከዛሬ 60 አመት በፊት… ሸይኽ ሙሐመድ ሱብሒ የተባሉ የሶሪያ ታላቅ ዐሊም እንዲህ ይላሉ:"ሸይኽ በድሩዲን አልሐሰኒይ ከሞቱ በኃላ የሐዲስ ሊቅ የሆነ ሙስጦለሕ የሚያቀራን ፍለጋ ያዝን እኔ፣ሸይኽ ሙሐመድ ሪያድ አል ማሊሕ(በደማስቆ የሚታወቁ ዓሊም ናቸው) እና በደማስቆ የአልጃሚዕ አል ኡመዊይ ኢማምና ኸጢብ የሆኑት ሸይኽ ዐብዱረዛቅ አልሐለቢይ ለአልባኒይ(ወሀቢዩ) መልስ ለመስጠት በሐዲስ ጠንካራ የሆነን የሱፊይ ሸይኽ መፈለግ ያዝን ምክንያቱም የሸይኽ በድሩዲን አልሐሰኒይን ሞት ተከትሎ ወሀቢዩ አልባኒይ ይጎራ ይበጣጠስና የሐዲስ እውቀት እንዳለው መጣራት በመጀመሩ ነበር።" በዚህ ጊዜ በሶሪያ ውስጥ የሐዲስ እውቀት ያለው ሰው ያፈላልጋሉ ሰዎችም ወደ ግብፅ እንዲሄዱ ያመላክቷቸዋል።ተነስተው ወደ ግብፅ አመሩ ታላላቅ ዑለሞችን አገኙ ሐዲስ የሚያቀራን የሐዲስ ሊቅ እንፈልጋለን በማለት ጥያቄ ሲያቀርቡ እንዲህ የሚል ምላሽ አገኙ:"እናንተ ከሻም ሀገር ወደኛ ትመጣላችሁን?እናንተ ጋር እኮ የሻም ሀገር ሙሐዲስ አለ።የተከበሩት የሐዲስ ሊቅ ዓሊሙ ሸይኽ ዐብዱሏህ አል ሀረሪይ እያሉላችሁ እኛ ጋር ትመጣላችሁን?" እነዚህ የሻም 3 ዑለሞች ስለ ሸይኽ ዐብዱሏህ አል ሀረሪይ ሶሪያ መግባት ገና አልሰሙም ነበር።የት እንደሚያገኟቸው በመጠየቅ የሽኽ ዐብዱሏህ አል ሀረሪይ በሶሪያ ውስጥ መገኛቸው አል ቀይመሪያ የምትባል ቦታ እንደሆኑ ተነገራቸው።ከዚያም ተመለሱና ሸይኽ ዐብዱሏህ ካሉበት ቦታ ደረሱ ተገናኙም።ሰለተከሰተው ነገር ለሸይኽ ነገሯቸው።ሐዲስ ፈትሑል ባሪንና ተድሪበራዊን ለመቅራት እንደሚፈልጉም ነገሯቸው።ሸይኽም እንዲህ አሏቸው:"ከፈጅር በፊት አንድ ሰአት ቀድማችሁ ኑ" እነሱም ከዚህ ውጭ ሌላ ጊዜ የለዎትም? በማለት ጠየቁ ሸይኽም "እኔ የሰዎችን ዐቂዳቸውን በማስተካከል ላይ ተወጥሬያለሁ ሰዎችን ዐቂዳ በማስተማር ተወጥሬያለሁ"በማለት ምላሽ ሰጡ እነሱም ተስማሙ። ሁለቱ ተድሪበራዊን ሸይኽ ዐብዱረዛቅ ደግሞ ፈትሑልባሪን ይዘው ከሸይኽ ጋር ተቀመጡ።ሸይኽ የሐበሻ መሻይኾች የሚቀመጡትን አይነት አቀማመጥ እጃቸውን አጣምረው ወደ ግድግዳው ገደፍ በማለት አይናቸውን ጨፍነው ቁጭ አሉ።መቅራት ጀመሩ ሶስቶቹ ኪታብ ይዘው ሸይኽ ዐብዱሏህ ኪታብ ሳይዙ በሒፍዝ እንዲህ ነው የሚቀራው እንዲህ ነው እያሉ ማስቀራት ማብራራት ጀመሩ።ኪታቡ ላይ በህትመት ጊዜ ያለተፃፉ የነበሩ ሸይኽ ግን በሒፍዛቸው እዚህ ጋር ይህ ቃል ጎሏል ይህ ቃል የለም አስገቡበት እያሉ በሒፍዝ ያስተካክልሏቸውም ነበር። እኒህ ነበሩ ሸይኻችን በሐዲሱም በተውሒዱም በሁሉም ፈኖች የጥልቅ እውቀት ባልተቤት……ሌት ተቀን ዐቂዳ ዐቂዳ………ምክንያቱም መሰረት ሳይቆም እንዴት ተብሎ ጣሪያ ይሰራል? ስንቶች በፊቅህና በሐዲስ በሌሎች ፈኖች ተወጠርን ብለው ህብረተሰቡ ዐቂዳውን በደንብ ሳይማር በመቅረቱ ሰበብ ዛሬ በወሀቢያ በኩል የምናየው ፍዳ ግልፅ ማሳያ ነው።ሰይዳችን ገና ለአቅመ አዳም ለመድረስ የደረሱ ህፃነትን ሳይቀር መጀመሪያ ተውሒድን ነበር የሚያስተምሯቸው።ተቀዳሚውና በላጩ እውቀት እሱ ስለሆነ።አሏህን እና መልእክተኛውን በሚገባ ሳያውቅ እንዴት ወደሌላ ይኬዳል? ተውሒድን ተማሩ አስተምሩ ባላችሁ ጊዜያት በሙሉ ሳትሰስቱ ተማሩ አስተምሩ…ለምን ለ 1 ደቂቃ አይሆንም ሰዎችን የማስተማር እድሉን ካገኛችሁ ተውሒድን አስተምሩበት።ከኩፍር አስጠንቅቁ።በመልካም እዘዙ ከመጥፎ አስጠንቅቁ። መልካም ኸሚስ https://t.me/hamid_al_ashariy https://t.me/hamid_al_ashariy
نمایش همه...
(Hamid Al_ashariy

ለማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ በዚህ ልታደርሱኝ ትችላላችሁ @Sodrudin

Photo unavailableShow in Telegram
አንድ የሁዲይ ገበያ ላይ ዘይት በመቸርቸር ላይ ነው። ልብሱ በሚሸጠው ዘይት አማካይነት ተዝርክርኮ ቆሽሿል። ፀሀይ በተደጋጋሚ የደበደበው ፊቱ ገርጥቷል። በዚህ ሁኔታ ዘይቱን በመቸርቸር ላይ ሳለ በግዜው የሙስሊም ዳኞች መሪ የነበሩት ኢብኑ ሐጀር በበርካታ ሰዎች ተከበው እና እጅግ ያማረ ልብስ ለብሰው በውብ ፈረስ ሲያልፉ ተመለከታቸው። ዘይቱን ከሚቸረችርበት መደቡ ብድግ ብሎ የኢብኑ ሐጀርን የፈረስ ልጓም ያዘ። ወደ እሳቸው ሽቅብ እየተመለከተም፦‹‹አንቱ መሪ ሆይ! ነብያችሁ ዱንያ የካፊር ጀነት ናት፤ የሙስሊም ደግሞ እስር ቤቱ ናት ብለዋል። ታድያ እርሶ ምን አይነት እስር ቤት ውስጥ ኖት እኔስ ምን አይነት ጀነት ውስጥ ነኝ?›› ሲል ጠየቃቸው። እሳቸውም፦‹‹እኔ አኪራ ላይ ከተዘጋጀልኝ የጀነት ድሎት አንፃር አሁን ያለሁበት ሁኔታ እስር ቤት ነው፤ አንተም አኪራ ላይ ከተዘጋጀልህ የጀሀነም ቅጣት አንፃር አሁን ያለህበት ሁኔታ ድሎት ላይ ነህ›› ብለው በመጣበት መለሱት። ምንጭ፦ فيض القدير በቻናላችን በሚሰጡ ትምህርቶች ተሳታፊ ለመሆን ይህን ይጫኑና ጆይን ይበሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/hamid_al_ashariy https://t.me/hamid_al_ashariy
نمایش همه...
ሱልጣኑል አውሊያእ በመባል የሚታወቁት አብዱልቃዲር አልጀይላኒይ ደረሳዎቻቸውን አስከትለው በባግዳድ ከተማ መሀል እየተዟዟሩ ነው። ህዝቡ በሙሉ አይን ሊያያቸው እሚፈራቸውን እኒህን ሸይክ አንድ ሰካራም ከመንገድ ዳር ጭቃ ላይ ወድቆ፦‹‹አንተ አብዱል ቃዲር›› ሲል ተጣራ። ዞር ብለው ሲያዩ በስካር ተዝረክርኮ ልብሱ የጨቀየን ሰው ተመለከቱ። ሰውዬውም እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦‹‹አላህ ይሳነዋል እንዴ!›› ሸይኩ፦‹‹አይሳነውም›› ብለው ፈገግ አሉ። ሰካራሙም፦‹‹ቆይ አላህ ይሳነዋል?›› ብሎ ዳግም ጠየቀ። ሸይኩም፦‹‹ኧረ አይሳነውም!›› ብለው ፈገግ አሉ። ሰካራሙም፦‹‹አላህ ይሳነዋልን?›› ሲል ዳግም ጠየቀ። ይህን ግዜ ሸይኩ እያለቀሱ ሱጅድ አደረጉ'ና፦‹‹አዎን! አላህ ቻይ ነው! ቻይ አይሳነውም›› አሉ። ከዝያም ተማሪዎቹ ይህን ሰካራም ተሸክመው ወስደው እንዲያጥቡት እና ልብሱንም እንዲቀይሩለት አዘዟቸው። ግና ተማሪዌቹም እንዲህ ሲሉ ጠየቁ፦‹‹የሰውዬው ጥያቄ እና የርሶ ምላሽ ግራ አጋብቶናል፤ ፍቺው ምን ይሆን?›› ጀይላኒም እንዲህ ሲሉ ያብራሩ ጀመር፦‹‹-መጀመርያ አላህ ይሳነዋልን ብሎ የጠየቀኝ አላህ ይቅር ሊለኝ ይሳነዋል ወይ ማለቱ ነው። -ሁለተኛ ላይ አላህ ይሳነዋልን ብሎ የጠየቀኝ በአንተ ቦታ እኔን ማድረግ ይሳነዋል ወይ ማለቱ ነው። ሶስተኛ ላይ አላህ ይሳነዋልን ብሎ የጠየቀኝ ፤ አላህ አንተን በኔ ቦታ ሰካራም ማድረግ ይሰነዋል ወይ ማለቱ ነው። አይሳነውም ብዬ ያለቀስኩትም ለዝያው ነበር›› ብለው እያለቀሱ መለሱላቸው። ቀደሰሏሁ ሲረሁ! ምንጭ፦ حلية الأولياء وطبقات الاصفياء በቻናላችን በሚሰጡ ትምህርቶች ተሳታፊ ለመሆን ይህን ይጫኑና ጆይን ይበሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/hamid_al_ashariy https://t.me/hamid_al_ashariy
نمایش همه...
(Hamid Al_ashariy

ለማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ በዚህ ልታደርሱኝ ትችላላችሁ @Sodrudin

«ነገ ላይ የምትጠለልበትን ዛፍ ዛሬ ትከለው!» የስኬት ምስጢር ይኸው ነው! ግልፅና አጭር ነው! ለጉዞው በቅጡ መዘጋጀት።… ሳይታክቱ መትጋት። መሥራት፤ መሥራት። መልፋት። መታገል… ከስህተት መማር።… ተስፋ ሳይቆርጡ መንገዱ ላይ መዘውተር። ከሁሉም በላይ ደግሞ የአላህን ተውፊቅና እርዳታ መለመን! አላህ ሆይ! ያሰብነውን አሳካልን። ከተመኘነው በላይ አውለን! https://t.me/hamid_al_ashariy
نمایش همه...
(Hamid Al_ashariy

ለማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ በዚህ ልታደርሱኝ ትችላላችሁ @Sodrudin

نمایش همه...
ያጀማል_መዙሐረል_ጀማል_የዳንዩ_ሳኒ_ሀድራ_መንዙማ_hadra_menzuma_.m4a11.88 MB
نمایش همه...
_የሸህ_ጫሊ_ሀድራ_በሚያምረው_ድመፁ_ሸህ_መሀመድ_አወል_ሀምዛ_ሲያንጎራጉረው.mp32.45 MB