cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። በዚህ ቻናል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶችን መዝሙሮችን እንዲሁም ምክሮችን ያገኙበታል። ክርስቲያናዊ ሕይወትዎን ያዩበታል.......

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
658
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+17 روز
-930 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
                        †                         🕊  💖                     💖  🕊 [  መንፈሳዊ ብርታት እንዴት እናግኝ !  ] 🕊                         †                         [ ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል ! ] ❝ እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው ፤ የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል ፤ እግዚአብሔርም ይመስገን። ❞ [ መዝ . ፷፰ ፥ ፴፭ ] [  💖  መ ን ፈ ሳ ዊ ብ ር ታ ት 💖  ]                    ]      [      🕊    ምክረ ቅዱሳን   🕊 🕊 [ በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ] †                       †                        † 💖                    🕊                     💖
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
🕊 [ እንኳን ለታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥጋቸው ለፈለሰበት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን። ] በዚህ ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥጋቸው ፈልሷል:: ይሕ የተደረገው ጻድቁ ከረፉ ከ፶፮ [56] ዓመታት በኋላ ነው:: በዕለቱም ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተፈጽመዋል:: [ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሥላሴን በማመን ተተከለ [ ተገኘ ]። በማስተዋል ስሙት ፣ በጸጥታ እና በርጋታም ሆናችሁ አድምጡት። በጌታው የሠርግ ቀን [ በዕለተ ምጽዓት ] በመከራው ከሚገኘው ደስታ ትሳተፉ ዘንድ ፣ የነፍስ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ብላችሁ መጥራት ይቻላችሁ ዘንድ በመገዛት ፣ በማኅሌት እና ኅሊናን በመሰብሰብ በዐሉን አክብሩ። ] [ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ] ሰዳዴ ጽልመት አባታችን ቅዱስ ተክለሐይማኖት ❝ አንተ የደከምክበት ያ መልካም አዝመራ እንክርዳድ ሞላበት ተክለ አብ ቶሎ ና አውሬው ሰልጥኖብን ተፍገምግመናል ኪዳን የሚጠብቅ አባት ያስፈልጋል፡፡ ❞ †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
نمایش همه...
                        †                         [  🕊  ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ  🕊  ] እንኳን የዓለም ሁሉ መምህር ለሆነ ለቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። 💖 " ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በስደት ዘመኑ የደረሰበትን መከራ በቃላት አከናውኖ ለመግለጽ አይቻልም። ለሦስት ወራት ያህል በእግሩ በጨካኝ ወታደሮች እየተንገላታ ያደረገው የቅጣት ጉዞ ሰውነቱና ጤንነቱ ከትኅርምትና ከተጋድሎ ብዛት ለተጎዳውና ለተዳከመው አባት የቀስ በቀስ [ አንድ ጊዜ በመግደል ያልተፈጸመ ] ሰማዕትነት ነበር። በዚህ የስደት ዘመኑም ቢሆን በጣም ብዙ ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ መልሷል። በአርማንያ ሲያልፍ በሰማዕቱ በቅዱስ ባሲሊቆስ ቤተ ክርስቲያን ጸሎት አደረሰ። በዚያው ሌሊት ድል አድራጊው ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ባሲሊቆስ በራእይ ተገለጠለትና " ወንድሜ ዮሐንስ ሆይ ፣ ነገ አብረን እንሆናለንና አይዞህ" አለው። ... በማግስቱ ወታደሮቹን በዚያው በቅዱስ ባሲሊቆስ ቤተ ክርስቲያን ይቆይ ዘንድ ቢጠይቃቸውም ከለከሉት። እንደተለመደው ገና ሳይነጋ የስደቱን ጉዞ ጀመረ። ነገር ግን ብዙም ሳይሄዱ ስለታመመ ወደተነሱበት ቤተክርስቲያን መመለስ ግድ ሆነባቸው። ካህናቱ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን ነጭ አለበሱት። እርሱም ነጭ መጎናጸፊያውን ለብሶ ከቅዱስ ምስጢር [ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ] ተቀብሎ ወዲያው ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። " ከአንደበቱ ላይ የነበረው የመጨረሻ ቃል የሁል ጊዜ ምስጋናው ፦ " ስለ ሁሉም ነገር ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን " የሚለው ነው። † ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው :- - ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ - አፈ በረከት - አፈ መዐር [ ማር ] - አፈ ሶከር [ ስኩዋር ] - አፈ አፈው [ ሽቱ ] - ልሳነ ወርቅ - የዓለም ሁሉ መምሕር - ርዕሰ ሊቃውንት - ዓምደ ብርሃን [ የብርሃን ምሰሶ ] - ሐዲስ ዳንኤል - ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ [ እውነተኛው ] - መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ - ጥዑመ ቃል - - - " እግዚአብሔር ሆይ ፣ እንዲህ ያለውን ቅዱስ አገልጋይህንና ባለሟልህን እንዳውቀው ስለፈቀድህልኝ አመሰግንሃለሁ።" እንዲሁም ግንቦት ፲፪ [ 12 ] እናታችን ርሕርሕቷ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በዚሕ ቀን ስሟን ለጠራና መታሠቢያዋን ላደረገ የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብላለች:: [      💖   እንኳን  አደረሰን   💖    ] †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
نمایش همه...