cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ኦርቶዶክስ

ልጄ ሆይ እንዳትሆን መናፍቅ ⛪️⛪️⛪️ ታሪክህንና ሀይማኖትህን እወቅ⛪️⛪️⛪️

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
202
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

የፓስተሩንና የኦርቶዶክሱ ፍጥጫ ~ ፖስተር፦ሰላም ላንተ ይሁን ወንድሜ ኦርቶዶክሱ፦አሜን ለሁላችንም ይሁን እንዴት ነህ ፓስተር ሰሞኑን ጠፍተሃል ፓስተር፦ጠፋሁ አይደል አገልግሎት ላይ ስለነበርኩ እኮ ነው ክብር ለጌታ ይሁን ሀሌሉያ ኦርቶዶክሱ፦አይ ፓስተር አገልግሎት ነው ያልከኝ?የሆነው ሆነና ወደ ዛሬው የመወያያ ርዕሳችን ብንገባ ምን ይመስልሃል ፓስተር፦ደስ ይለኛል ኦርቶዶክሱ፦ጥሩ ደስ ያለህን ሀሳብ ማንሳት ትችላለህ ፓስተር፦ "እናንተ ኦርቶዶክሶች ግን ማርያም ማርያም ማለትን ታበዛላችሁ ቆይ ግን "ምናችሁ ስለሆነች ነው እንዲህ የምታሞጋግሷት??" ኦርቶዶክሱ፦ "እናታችን ስለሆነች።"ነዋ ፓስተር፦ "ማነው እናታችሁ ያደረጋት?" ኦርቶዶክሱ፦ "ልጇ ጌታችን መዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነዋ።" ፓስተር፦ "ደሞ መቼ?" ኦርቶዶክሱ፦ "በእለተ አርብ በቀራንዮ መስቀል ላይ ሆኖ ።" ፓስተር፦ "ደፋሮች ናችሁ!" ኦርቶዶክሱ፦ "እንደት?" ፓስተር፦ "ጌታ ለዮሐንስ እናትህ እችውት አለው እንጅ መቼ ኦርቶዶክሶች እናታችሁ እችውት አላችሁ?" ኦርቶዶክሱ፦"ዮሐንስ እናት አልነበረችውም እንዴ ? ለምን እናትህ እችውት አለው?" ፓስተር፦"በእርግጥ እናት አለው ግን እናቱንም እናቱ እንድትሆንለት ለሱ ብቻ ሰጠው።" ኦርቶዶክሱ፦"ታድያ ለምን "እናትህ" አለው ? በወላጅ እናትህ ላይ እናቴንም ጨምረልሃለው ለምን አላለም?" ፓስተር፦ "በዛን ሰኣት ወላጅ እናቱ አብራው አልነበረችማ።" ኦርቶዶክሱ፦ "አይ ፓስተር ታስቃለህ በጣም! ለመሆኑ 10ቱ ትእዛዛት ለማን ተሰጡ??" ፓስተር፦ "ለሙሴ ነዋ!" ኦርቶዶክሶ፦ታድያ ለሙሴ ብቻ ከተሰጠ ለምን እኛም ትእዛዛቱን እንድንጠብቃቸው ተደረገ??" ፓስተር፦ "የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ስለሆኑ እኛም እንጠብቃቸዋለን!" ኦርቶዶክሱ፦ "መልካም ለሙሴ የተሰጡት 10ቱ ትእዛዛት ለሙሴ ብቻ ተሰተው እንዳሉ እኛ ደሞ አይ የእግዚአብሔር ትእዛዛት ናቸው ብለን ጠበቅናቸው፤ ለመሆኑ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር አይደለምን???" ፓስተር፦ "እግዚአብሔርማ ነው ከፈለክ ጥቅስ ልስጥህ።" ኦርቶዶክሱ፦ "አይ ጥቅሱን እንኳ ተወው እኔምኮ አምንበታለሁ! ያውም ሃያል አምላክ ነው!!" ፓስተር፦ "እና?" ኦርቶዶክሱ፦ "እናማ ለሙሴ 10ቱን ትእዛዛት የሰጠው እግዚአብሔር ነው ብለን አምነን እኛም ትእዛዛቱን ከተቀበልን ታድያ ድንግል ማርያምን ለዮሐንስ የሰጠው ኢየሱስ ክርስቶስም እግዚአብሔር ነው ብለን ለምንድ ነው ድንግል ማርያምን ለዮሐንስ ብቻ ተሰጠች የምንለው?" ፓስተር፦ "የፈለከውን ጠይቀኝ እኔ ድንግል ማርያምን ኢየሱስ ሰቶኛል ብዬ እናቴ አልላትም! " ኦርቶዶክሱ፦ "መብትህ ነው እሽ የጌታዬ እናትስ አትላትም??" ፓስተር፦ "አልላትም" ኦርቶዶክሱ፦ "ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስንም ጌታዬ አትለውም ማለት ነዋ!" ፓስተር ፦ "ለምንድ ነው ማልለው እሱማ ጌታዬ ነው" አልክደውም "ኢየሱስ ጌታ ነው!" ኦርቶዶክሱ፦"እሽ ከ10ቱ ትእዛዛት አንዱ እናትህንና አባትህን አክብር የሚል ነው! ታድያ አንተ የራስህን እናት ሰው ቢያከብርልህ እንደምትደሰት ሁሉ ጌታችንም እናቱን ስታከብርለት እንደሚደሰትብህ አታውቅምን?" ፓስተር፦ "ስለወለደችው አከብራታለሁ" ኦርቶዶክሱ፦ "ምን ብለህ ታከብራታለህ?" ፓስተር፦ ዝም ኦርቶዶክሱ፦ "አንድ አባት ለልጁ የምጣፍጥ ምግብ አዘጋጄለትና በመሶብ አድርጎ አቀረበለት፤ ልጁም እንጀራውን እስክጠግብ በልቶት መሶቧን ወረወራት ። አባቱ "ልጄ ለምን ወረወርካት?" ብሎ ጠየቀው። ልጁም "ምን ታረግልኛለች? እንጀራንስ በላው" አለ። አባቱም "ልጄ ነገ ምናልባት እንጀራ ባይርብህም ግን ችግር ልደርስብህ ይችላል በዛን ጊዜ ይህችን መሶብ ይዜህ ለምስክርነት ከዝህች መሶብ የበላው ሰው ነበርኩ ዛሬ ግን ቸግሮኝ ለልመና ወጣው ትላለህ መሶቧን ሳትይዝ ብትወጣ ግን ማጅራት መቺ ዱርዬ ነህ ብለው ይደበድቡሃል ልጄ ስለዝህም መሶቧ ታስፈልግሃለች" አለው። ልጁም "አይ አባቴ አታስፈልገኝም" ብሎ መለሰለት። ያን ጊዜ አባቱም "ልጄ በስሜ ትጠራ ይሆናል ነገር ግን የኔ ልጅ አይደለህም ያበላችህን ቀኜን ክደሃታልና እኔ በዝህች መሶብ ከብሬ አንተ ግን እሷን ካድካት" አለው። ፓስተር፦ ምን ለማለት ፈልገህ ነው? ኦርቶዶክሱ፦ "አባት የተባለው አብ ነው ፤ እንጀራ የተባለው ወልድ ነው፤ መሶብ የተባለችው ድንግል ማርያም ናት። 'አብ አንድ ልጁን አሳልፎ እስክሰጥ አለሙን እንድሁ ወዶአልና' ተብሎ እንደተፃፈ! ወልድም 'የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ' እንዳለ! ስለድንግል ማርያም 'ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላታል በውስጧ ሰው ተወልዷልና' እንደተባለ። አንተም አብ በልጁ እንድትድንበት ብሰጥህ ዳንኩኝ በቃ ብለህ ለመዳንህ ምክንያትየሆነችውን ድንግልን ካድካት። ርሃብ ባያጋጥምህ እንኳን ለሌላ ችግር ትጠቅምሃለች የተባለው አንተ ሰው ነህ በምትሰራው ኃጢአት ሁሉ ስለእናትህ ብለህ ማረኝ ብትለው ጌታ ይምርሃል እናቱንም አንቺ ታስፈልግኛለሽ አማላጄ ብትላት ሁሉ ሙሉ ይሆንልሃል። አንተ ግን ይህን ሁሉ አልቀበል አልክ። አባት ልጁን በስሜ ትጠራለህ ግን ልጄ አይደለህም እንዳለ አንተም ዛሬ በኢየሱስ ስም ትጠራለህ ነገር ግን የሱ ልጅ አይደለህም አባትህን አንተም ታውቀዋለህ ማን እንደሆነ! ያለ መሶብ እንጀራ እንዳሌለ ሁሉ ያለ ድንግል ማርያምም ክርስቶስ የለም። ፓስተር፦ "ጌታ ምስክሬ ግራ ገብቶኛል" ኦርቶዶክሱ፦ "ለምን ግራ ይገባሃል?" ፓስተር፦ "የጌታዬ እናት እንዳልላት ጌታ ጌታዬ ነው ብፅዕት ብላት ደግሞ የሚቆጣኝ ሌላ ጌታ አለኝ" ኦርቶዶክሱ፦"ለሁለት ጌቶች ነው እንዳ የምትገዛው?" ፓስተር፦ "አይ ለ1 ጌታ ብቻ ነው የምገዛው" ኦርቶዶክሱ፦ "ጌታህ ማነው? የሚቆጣህስ ሌላኛው ጌታ ማን ይባላል??" ፓስተር፦ "እሱ ሚስጥር ነው አይነገርም" ....................................................................... "እመቤቴ ሆይ ! የናቁሽ ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዱልሻል፤ የእግዚአብሔር ከተማ ጽዮንም ይሉሻል"!!!! ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት የሲኦል ደጆች አይችሏትም ቤተክርስቲያን አ.ት.ታ.ደ.ስ.ም! ፀልዩ በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ ሐዋርያት ርትዕት በኅበ እግዚአብሔር! የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር) ቤተክርስቲያን.... መሰረቷ ጉልላቷ እርሱ ነው ሙሽራዋ መስቀል ላይ የሞተው ዛሬም ነገም ያው ነው ለዘላለም አትንገሩን አዲስ ጌታ የለም! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን-ይቆየን።..... ...... @YEHULUUM....
نمایش همه...
+ ያደረግሽው ምንድር ነው? + አዳም ዕፀ በለስን በበላና ክብሩን ባጣ ጊዜ እግዚአብሔር ሲጠይቀው እንዲህ አለ :- ከእኔ ጋር እንድትሆን የሠጠኸኝ ሴት ከዛፉ ሠጠችኝና በላሁ:: ከዚያ በኁዋላ ግን እግዚአብሔር ለሔዋን :- ለምን ዛፉን ብላ ብለሽ ሠጠሽው? አላላትም:: "ያደረግሽው ምንድነው" ብቻ አላት:: እርሱ በሰዎች አስተያየት አይፈርድም:: ሌላው ስለ አንተ የሚለውን ትቶ አንተን ለብቻህ ይጠይቅሃል:: የሰዎችን ግምገማ አይሰማም:: እንደ ሃናንያ "ኸረ ጌታ ሆይ ክርስቲያኖችን ሲያሳድድ ነበረኮ" ቢሉትም ቸል ብሎ ምርጥ ዕቃው ያደርግሃል:: በድንጋይ ልትወገር ይገባታል ሲሉት ክሱን ትቶ ከሳሾቹን ሊከስስ መሬት ላይ ይጽፋል:: ዐሥርቱ ትእዛዛትን በጻፉ ጣቶቹ ዘማዊትዋን ሴት ነጻ ሊያወጣ አፈር ይጭራል:: ሰው ጨካኝ ፈራጅ እንደሆነ ያውቃልና በአዳም አስተያየት ሔዋን ላይ አይፈርድም:: "ያደረግሽው ምንድን ነው?" ብሎ ጠየቃት:: እግዚአብሔር ዛሬም ነፍሳችንን ይጠይቃታል:: ያደረግሽው ምንድር ነው? የአዳምን ክስ ሰምቻለሁ! ሰዎች ስለ አንቺ የሚሉትን አዳምጫለሁ:: አንቺ ግን ንገሪኝ:: ግራውን ሰምቼ አልፈርድም:: ምናልባት ቀኙን ብሰማ ይሻላል የሚል ርኅሩኅ አምላክ ነው:: እኛ የምንፈርድባቸው ሰዎች ሁሉ ቢጠየቁ የሚናገሩት የየራሳቸው የታሪክ ማዕዘን (side of the story) አላቸው:: ስለዚህ እግዚአብሔር አዳምን ሰምቶ አልፈረደም ሔዋንን ጠርቶ ጠየቃት "ያደረግሽው ምንድር ነው?" ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ግንቦት 2 / 2012 ዓ ም አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
نمایش همه...
አንድ ጊዜ ነው አሉ፡፡ አንዱ ባለጠጋ ለአንዱ 'ነዳይ' "ደኅና ገንዘብ" አውጥቶ ይሰጠዋል፡፡ ደኅና ገንዘብ መባሉም በሰጪው ሕሊና ነበር፤ በባለጠጋው ዓይን ጥቂት ብትኾንም ከነዳዩ አንጻር ግን ብዙ እንደ ነበር አስቦአልና፡፡ ታዲያ ለነዳዩ ከሰጠው በኋላ ምስጋና ጠብቆ ኖሮ እንደሚፈልገው ሳይኾን ቀረ፡፡ "ለምን አታመሰግነኝም?" ብሎም ይጠይቀዋል፡፡ ነዳዩም እንዲህ አለው ይባላል፦ "አንተ በሰጠኸኝ ገንዘብ ምናልባት የዕለት ጉርሴን አገኝ ይኾናል፤ አንተ ግን በዚሁ ምክንያት የዘለዓለም ሕይወትን ታገኛለህ፡፡ በሰጠኸኝ ገንዘብ ግፋ ቢል የዓመት ልብሴን እገዛ ይኾናል፤ አንተ ግን የጸጋ ልብስን ትሸምንበታለህ፡፡ ታዲያ ከእኔና ከአንተ ይበልጥ የተጠቀመው ማን ነው? ሊያመሰግን የሚገባውስ ማን ነው - አንተ እኔን ወይስ እኔ አንተን?" በርግጥም መስጠት ማለት መስጠት ሳይኾን መቀበል ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ስጦታና ውኃ አጠጡኝ የሚለን ማን መኾኑንም ብናውቅ፥ እኛ በለመንነው ነበር፥ የሕይወትም ውኃ ይሰጠን ነበርና (ዮሐ.4፥10)፡፡ @aklesyazetewahdo please join_and_share
نمایش همه...
እኔ ለበረከት ዘምርልሻለሁ የክብር ባለቤት አምላኬሽ ልጅሽ ነው የሰጠሽን ክብር ሳልጨምር ሳልቀንስ ሞገስ ሆኖልኛል ስምሽን ማወደስ 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 #አዲስ_መዝሙር 2021 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች #share እናድርግ ! #join_share -------- @dnzema -------- -------- @dnzema -------- -------- @dnzema -------- ✥
نمایش همه...
ማኅቶት_ቲዩብ_Mahtot_Tube_NEW_ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ.m4a5.94 MB
#እናቴ_እመቤቴ እናቴ እመቤቴ የማትጠፊው ከአፌ /2/ በረከቴ አንቺ ነሽ የመስቀል ስር ትርፌ /2/ አምላኬ ሸልሞኝ ለዘለአለም ያዝኩሽ ጌታን የማይብሽ ብሌኔ አደረኩሽ በልቤ ላይ ይፍሰስ የፍቅርሽ ጸዳሉ የሚጣፍጥ ስምሽ መድኃኒት ለሁሉ ተወዳጁን ልጅሽ ጸጋውን ያብዛልኝ እድሜ እስኪፈጸም ለክብርሽ እንድቀኝ #አዝ ነፍሴ እንዳትጎዳ እንዳትቀር ባክና ብርታት ሆኖልኛል የስምሽ ምስጋና እኖራለው ገና ንኢ ንኢ ስልሽ ክብሬ ነሽ ጌጤ ነሽ ከአፍ የማልነጥልሽ #አዝ ሲነጋም ጠራሁሽ ሲመሽም ጠራሁሽ ስዕልሽ ፊት ቆሜ ሰአሊ ለነ እያልኩሽ አሜን የምልብሽ መነጋገሪያዬ የአማኑኤል እናት አንቺ ነሽ ቋንቋዬ #አዝ መች በስጋ ጥበብ ሰው ላንቺ ይቀኛል ከአምላክ ካልተላከ ከፊትሽ ይቆማል አንቺን ማመስገኔ አንቺን ማወደሴ በልቡ ያሰበሽ ፈቅዶ ነው ሥላሴ #አዝ ብዙ ተቀብዬ ጥቂት አልዘምርም ለእናትነት ፍቅርሽ ከቶ ዝም አልልም እኔን በእደ ፍቁርሽ የምትባርኪ ኦ ምልይተ ጸጋ ድንግል ሰላም እለኪ t.me/dnzema #አዲስ_መዝሙር° በሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች #share እናድርግ ! #join_share -------- @dnzema -------- -------- @dnzema -------- -------- @dnzema -------- ✥
نمایش همه...
ማኅቶት_ቲዩብ_Mahtot_Tube_አዲስ_ዝማሬ_እናቴ_እመቤቴ_ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ.m4a7.00 MB
🔔🔔🔔 መዝሙር 🔔🔔🔔 ✅ሊቀ-መዘምራን/ዲን/ ቴድሮስ ዮሴፍ ✟ ናርዶስ ቀጺመታት 🙏ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን🙏 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች #share እናድርግ ! #join_share 👉 @z_tewodros 👉 @z_tewodros 👉 @z_tewodros
نمایش همه...
መዝሙረ ዳዊት5.87 MB
♻️#ሥላሴን_አመስግኑ♻️ 🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟 ስላሴን አመስግኑ /2/ የምድር ፍጥረታት ዘምሩ እልል በሉ 🔆አዝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል ከምንም በፊት ዓለማትን ሁሉ ለፈጠረ ጌታ ምስጋና ይድረሰው ከጠዋት እስከማታ 🔆አ.ዝ ኪሩቤል ሱራፌል የሚያመሰግኑት መላእክት በሰማይ ስሉስ ቅዱስ ያሉት እኛም የአዳም ልጆች እንዘምራለን በሰማይ በምድር እንጠራሃለን 🔆አዝ ብራብ በሥላሴ እጠግባለሁኝ ብጠማም በአምላኬ እረካለሁኝ ስላሴ አምባዬ ክብሬ ናቸውና ሁሌም ይመሩኛል በህይወት ጎዳና @dnzema እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን
نمایش همه...
2020-11-02-13-14-31-100_Tunnel.mp32.10 MB
ሃገር ቅድስት ኢትዮጵያ እግዚአብሔር ዘሃረያ(2) 🙏ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን🙏 ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች #share እናድርግ ! #join_share 👉 @z_tewodros 👉 @z_tewodros 👉 @z_tewodros
نمایش همه...
ሃገር ቅድስት ኢትዮጵያ.mp33.08 MB
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ግንቦት 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✝✞✝ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ✝✞✝ =>በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሐዋርያት ቀጥሎ የቅዱስ አትናቴዎስን ያሕል ስለ ሃይማኖት የተዋጋ ቅዱስ ፈልጐ ማግኘት አይቻልም:: ❖ቅዱስ አትናቴዎስ ማን ነው? +ቅዱስ አትናቴዎስ በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት በዘመነ ሰማዕታት መጠናቀቂያ በ300 አካባቢ(296) እስክንድርያ ግብፅ ውስጥ ነው የተወለደው:: ወላጆቹ አረማውያን በመሆናቸው ክርስትናን አልተማረም ነበር:: +ሕጻን እያለ ለጭዋታ ከቤቱ ሲወጣ የክርስቲያን ልጆች ሃይማኖታዊ ጨዋታ ሲጫወቱ ተመለከተ:: ሊቀላቀላቸው ቢፈልግም ክርስቲያን ባለመሆኑ ከለከሉት:: አትናቴዎስም ክርስቲያን ልሁንና አጫውቱኝ ብሏቸው እሺ ስላሉት ሕጻናቱ ዕጣ ተጣጣሉ:: +ላንዱ ቄስ: ላንዱም ዲያቆን መሆን ሲደርሳቸው ለአትናቴዎስ ፓትርያርክ መሆን ስለ ደረሰው ሌሎቹ ሕጻናት ይሰግዱለት ጀመር:: በአጋጣሚ ሕጻናቱ ይሕንን ሁሉ ሲያደርጉ የወቅቱ ፓትርያርክ ቅዱስ እለ እስክንድሮስ በመገረም ያያቸው ነበርና ለሕጻኑ አትናቴዎስ ትንቢት ተናገረለት:: +ከዚያም የአትናቴዎስ አባቱ ሲሞት ሊቀ ዻዻሳቱ ከእናቱ ወስዶ አጥምቆ: የሚገባውን መንፈሳዊ ትምሕርት ሁሉ በልቡናው ላይ ቀረጸበት:: ከዚሕ በኋላ ዲቁናን ሹሞ አስተምር አለው:: ምንም ሕጻን ቢሆንም ከሊቅነቱ: ከአመላለሱና ከአንደበቱ ጣፋጭነት የተነሳ የሰማው ሁሉ ይደነቅ ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ አድራለችና:: +ቅዱስ አትናቴዎስ ሊቀ ዲቁና በተሾመ ወራት አርዮስ ቤተ ክርስቲያንን በመረበሹ ኒቅያ ላይ 318ቱ ሊቃውንት ሲሰበሰቡ ጸሐፊ አድርገው ሾሙት:: በጊዜውም በዕድሜ የስንት ጊዜ ትልቁ የሚሆነውን አርዮስን ተከራክሮ ምላሽ አሳጣው:: ✝ቅዱስ አትናቴዎስ ከሊቃውንቱ ጋር ሆኖ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: እግዚአብሔር መሆኑን በአደባባይ መሠከረ:: ጸሎተ ሃይማኖትንም ያረቀቀው እርሱ ነው:: +ከዚሕ በኋላ የእስክንድርያ (የግብፅ) 20ኛ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ:: ቤተ ክርስቲያንን በመልካም እረኝነት ለ48 ዓመታት ሲመግብ ብዙ መከራዎችን ተቀበለ:: ለ5 ጊዜ ከመንበሩ አፈናቅለው ወደ በርሃ ሲያግዙት በስደት ከ15 ዓመታት በላይ አሳልፏል:: +በተሰደደባቸው ቦታዎች መከራን እየተቀበለ ያላመኑትን አሳምኗል:: በጎቹ እንዳይባዝኑበት ደግሞ በጦማር (በደብዳቤ) ይጠብቃቸው ነበር:: ዛሬ በሃይማኖተ አበው የምናገኘው ቃለ ሃይማኖት በዚሕ ዘመን የተጻፈ ነው:: +በወቅቱ የነበረው ንጉሥ (ትንሹ ቆስጠንጢኖስ) የአባቱን (ታላቁ ቆስጠንጢኖስን) ዕረፍት ተከትሎ ነገሠ:: +ወዲያውም አርዮሳዊ መናፍቅ ሆነ:: ሃይማኖታቸው የቀና አባቶችንም ያሳድድ ገባ:: ከአበው ቅዱሳን መካከል ግን የዚህ መከራ ቀዳሚው ገፈት ቀማሽ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ አንትናቴዎስ ነበር:: +በተለይ አንድ ጊዜ ንጉሡ ቅዱሱን ወደ በርሃ አግዞ: መናፍቅ ዻዻስ በግብጽ ሹሞ: ብዙ ክርስቲያኖችን በግፍ ሲያስገድል: ቅዱሱን ለ6 ዓመታት አሰቃየው:: የወገኖቹ (የልጆቹን) ስቃይ የሰማው ቅዱስ አትናቴዎስ ግን በድፍረት ወደ ቤተ መንግስት ገብቶ ተናገረው:: +2 አማራጭን አቅርቦ "ወይ ግደለኝና እንደ አባቶቼ ሰማዕት ልሁን: ካልሆነ ግን ወደ መንጐቼ (ምዕመናን) መልሰኝ" አለው:: መናፍቁ ንጉሥም ቢገድለው ብጥብጥ እንደሚነሳ ስለሚያውቅ በስልት ሊያጠፋው ወሰነ:: +ቀዛፊ: መቅዘፊያ: ምግብና ውሃ በሌላት ጀልባ ውስጥ ከቶም ሜዲትራኒያን ባሕር ውስጥ ጣለው:: ድንገት ግን ከሰማይ ጌታችን መላእክቱን አስከትሎ ወረደ:: +ሚካኤልና ገብርኤል ባሕሩን እየቀዘፍ: ሌሎች መላእክት እየመገቡት በዚህች ቀን እስክንድርያ (ግብጽ) አድርሰውት ተሠውረዋል:: ሕዝቡም በታላቅ ሐሴት እየዘመሩ አባታቸውን ተቀብለውታል:: +ሐዋርያዊው ቅዱስ ስለ ኦርቶዶክስ ተዋግቶ: ብዙ ስቃይንም ተቀብሎ በ373 ዓ/ም አካባቢ አርፏል:: ቤተ ክስርቲያን ☞"ሊቀ ሊቃውንት: ☞ርዕሰ ሊቃውንት: ☞የቤተ ክርስቲያን (የምዕመናን) ሐኪም (Doctor of the Church): ☞ሐዋርያዊ" ብላ ታከብረዋለች:: =>አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሊቁ በረከት አይለየን:: በምልጃውም ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን:: =>ግንቦት 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ 2.የባሕታውያን አለቃ ታላቁ አባ ሲኖዳ (ጽንሰቱ) 3.ቅዱስ ዮሐንስ ጻድቅ (ሃብቱን: ንብረቱን: ልብሱን ሳይቀር መጽውቶ ራቁቱን የተገኘ ደግ ሰው ነው) 4.አባ ሐርስዮስ ገዳማዊ =>ወርሐዊ በዓላት 1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ) 2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ 3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ) 4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት 5.አባ ባውላ ገዳማዊ 6.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ) =>+"+ ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዐን ናቸው:: መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና:: ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብጹዓን ናችሁ:: ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ:: ሐሴትም አድርጉ:: ከእናንተ በፊት የነበሩ ነቢያትን እንዲሁ አሳደዋቸዋልና:: +"+ (ማቴ. 5:10) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.