cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ETV.News

@etv_newss (tikvah news)

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
8 056
مشترکین
+124 ساعت
+67 روز
+10330 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#Kenya በጎረቤት ኬንያ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 188 ደርሷል። ካለፈው መጋቢት ጀምሮ በደረሰው አውዳሚ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 188 መድረሱን የሀገር አስተዳደር ሚኒስቴር አሳውቋል። እስካሁን ያልተገኙ በርካታ ሰዎች መኖራቸውም ተገልጿል። በኬንያና ሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች በተከታታይ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ የብዙ ሰዎች ህይወት እየጠፋ ሲሆን የከፍታ ቦታዎች መናድም ነዋሪዎችን ካለመጠጊያ አስቀርቷል፡፡ መንገዶችን ድልድዮችን እና ሌላም የመሰረተ ልማት አውታሮችን ውድሟል። #VOA @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
በአዲስ አበባ ከተማ የወጣው የመሬት ሊዝ  ጨረታ ተራዘመ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ  ፤ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ በሌሎችም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል። በዚህም ከሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 24/2016 ዓ/ም ድረስ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ሲከናወን ቆይቷል። ነገር ግን የጨረታ ሰነድ ሽያጩ ከ28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 09/09/2016 ዓ/ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት መራዘሙ ተነግሯል። ተጫራቾች ፦ - የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ፣ - ሲፒኦ፣ - የግንባታ አቅም ማሳያ ማስረጃ፣ - ሰነዱን ለመግዛት በቴሌ ብር የከፈሉበት ስሊፕ - ሌሎች መያያዝ ያለባቸዉ እና በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን በመጨመር የጨረታ ሰነዶችን በኤንቨሎፕ በማሸግ ግንቦት 09/2016 ዓ/ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አከባቢ ኤም ኤ (MA) ህንፃ ላይ በሚገኘው የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ተብሏል። ጨረታው ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 12/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ ለተከታታይ 9 የስራ ቀናት በቦሌ ክ/ከተማ አስተደዳር አዳራሽ  እንደሚከፈት ተገልጿል። የጨረታው ዝርዝር👇 https://t.me/tikvahethiopia/87112 @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" ' እኔ ሰርቂያለሁ ስሜን ግን ለጥፏል ' የሚል ይምጣና ይክሰሰኝ ካሳውን እንከፍላለን "  - አቶ አቤ ሳኖ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ከዋልታ ቴሌቪዥን ቆይታ አድርገው ነበር። በዚህም ወቅት ፥ መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ/ም በሲስተም ችግር ምክንያት በተፈጠረው እክል ተዘርፎ የተወሰደውን ባንኩ ገንዘብ  እያስመለሰ መሆኑንና ከ801 ሚሊዮን ብር የቀረው 25 ሚሊዮን ብር መሆኑን ገልጸዋል። በዕለቱ 30 የባንኩ ሰራተኞች በግብይት ላይ መሳተፋቸውን ተከትሎ አሁን ላይ ከስራ ታግደው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን ገልጸዋል። በሌላ በኩል ፥ ባንኩ በምን የሕግ አግባብ ነው ሰዎች ነጻ ሆኖ የመገመት መብታቸው ተጥሶ ፎቷቸው የተሰራጨው ? የሰዎችን ምስል ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዴት አሰራጨ በሚል ተጠይቀዋል። አቶ አቤ ፤ " እኛ ዛሬም ድረስ ወንጀለኛ ናቸው የሚል ቃል አልወጣንም። ይሄን ገንዘባችንን ወስደዋል መልሱ ነው ያልነው መውሰዳቸውን 101% እናውቃለን " ሲሉ ገልጸዋል። " ዛሬ ያለንበት ሁኔታ እና መጀመሪያ ላይ የነበረው ይለያያል። እሁድ የነበረው ታሪክ ' ባንኩ ማን ብር እንደወሰደበት አያውቅም ' የሚል ነው በተለይ ሶሻል ሚዲያ ላይ ሲቀለድ ነበር እኛ ግን ' እናውቃለን መልሱ ስንል ' ነበር ምላሹ ' አያውቅም ' የሚል ነበር በኃላ 1 ሳምንት ሰጠን በተደጋጋሚ አስጠነቀቅም እንዲመልሱ ከዛ ስም እና ፎቷቸው እዲወጣ ወደማድረጉ ገባን " ብለዋል። " ምስል አታሰራጭ የሚል በህገ-መንግስቱ አልተገለጸም። ሲቀጥል 15 ሺህ ሰው በኮንቬንሽናል ህግ ሊፈታ የሚችል ችግር አይደለም " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " naming and shaming የሚል ህግ አለ ገንዘብ የወሰደውን ሰው ስሙን አውጥቶ ያያችሁት ንገሩትና ይመልስ ነው ያልነው " ብለዋል። " ነጻ ሆኖ የመገመት መብቴ ተነክቷል " የሚል ካለ ይክሰሱንና ካሳ ይጠይቁ ሲሉ ገልጸዋል። አቶ አቤ " ' እኔ ሰርቂያለሁ ስሜን ግን ለጥፏል ' የሚል ይምጣና ይክሰሰኝ ካሳውን እንከፍላለን " ሲሉ ተናግረዋል። " ያደረግነው ነገር በተወሰነ ደረጃ ወቀሳ ሊቀርብበት የሚችል ነገር ነው። ለችግሩ መፍትሄ ግን ያደረግነው ብቻ ነበር። ነገሩ ከህግም ከፖሊስም አቅም በላይ ነው ይሄን ሁሉ ሰው ማሰር አይችሉም፤ ፍርድ ቤት ይሄን ሁሉ ሊዳኝ አይችልም። የህግ ጥያቄ ቢነሳም ትክክለኛው መፍትሄ ያደረግነው ብቻ ነበር እሱንም አማራጭ ስላልነበረን ነው ያደረግነው ያን ማድረጋችን ህዝቡ እንዲያውቀው ሆኖ የወሰደው ሁሉ ተሰልፎ መጥቶ መለሰ " ብለዋል። " ገንዘቡ የህዝብ ነው እያስመለስን የቀረው ከ801 ሚሊዮን ብር 25 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው ፤ የማሰባሰቡ ስራ 96.8 በመቶ ደርሷል " ሲሉ አሳውቀዋል። " ምንም እንኳን ልጆች ቢያጠፉም ወላጆች መጥተው አርመዋልና የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ጨዋ ነው ፤ አሁንም አዋቂ አለ ፣ የሚያስትምር አለ፣ ሽማግሌ አለ፣ ጨዋ ወላጅ አለ ማለት እፈልጋለሁ " ሲሉ ለቴሌቪዥን ጣቢያው ተናግረዋል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
እነ ቀሲስ በላይ ክስ እስኪመሰረትባቸው በእስር ይቆያሉ። የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በነ ቀሲስ በላይ መኮንንና ሌሎች 2 ተጠርጣሪዎች ላይ የክስ መመሥረቻ 15 ቀናት ፈቅዷል። በሀሰተኛ ሰነድ ከአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ከ6 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ለማውጣት ሙከራ አድርገዋል ተብለው የተጠረጠሩትና በቁጥጥር ስር የዋሉት ቀሲስ በላይ መኮንንና 2 በወቅቱ አብረዋቸው የነበሩ ግለሰቦች ዛሬ ለ3ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። በዚህም ፍርድ ቤት ለዐቃቤ ሕግ 15 ቀናት የክስ መመስረቻ ፈቅዷል። ተጠርጣሪዎች ክሱ እስኪመሰረት ድረስ ባሉበት ማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ፍርድ ቤት አዟል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር በዓሉን ምክንያት በማድረግ እስከ 25% ቅናሽ የተደረገባቸውን ማራኪና ውብ የመመገቢያ ጠረጴዛዎቻችንን በመግዛት ልዩ የአብሮነት ጊዜ ያሳልፉ! የዘመናዊነት ተምሳሌት! አድራሻችን፦ 1. ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251 995 27 2727 / +251 911 51 6843 2. ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251 957 86 8686 3. ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251 993 82 8282 👉 Telegram:  https://t.me/yonatanbt_furniture 👉 Facebook:  https://www.facebook.com/profile.php?id=100087238034736 👉 TikTok: https://www.tiktok.com/@yonatanbtfurniture 👉 Instagram: https://www.instagram.com/yonatanbtfurniture/
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ጸሎተ_ሐሙስ ጸሎተ ሐሙስ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች ተከብሯል። በአዲስ አበባ ፒያሳ ልደታ ማርያም ካቴድራል የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነኢየሱስ ሱራፌልን ጨምሮ ካህናት፣ ደናግላንና ምዕመናን በተገኙበት መሥዋዕተ ቅዳሴና የቅባ ቅዱስ ቡራኬ ተካሂዷል። Photo Credit - FBC & Emdiber Catholic Secretariat @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ማኅብረቅዱሳን በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ዛሬ ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት መወሰዳቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዘግቧል። የሁለቱም አገልጋዮች የመኖሪያ ቤት መፈተሹም ተገልጿል። በአሁኑ ሰዓት ሜክሲኮ ፌዴራል ፓሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ይገኛሉ የተባለ ሲሆን የተያዙበት ምክንያት እንዳልታወቀ የቴሌቪዥን ጣቢያው ገልጿል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ  ሊቀ ማእምራን ብርሃኑ ተክለ ያሬድ በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12:00 በፌዴራል ፖሊስ " #ለጥያቄ_ይፈለጋሉ " በሚል ከቤታቸው ተወስደው መታሠራቸውን ቤተሰቦቻቸው መናገራቸውን ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ዘግቧል። ቀደም ብሎ ፥ የሰንበት ት/ ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ከቤታቸው በጸጥታ ኃይል መወሰዳቸውና ቤታቸው ላክ ፍተሻ መደረጉን የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን መዝገቡ ይታወሳል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ጸሎተ_ሐሙስ የሕፅበተ እግር ስነ ሥርዓት ተከናወነ። ዛሬ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክሃይማኖት መሪነት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የሕፅበተ እግር ስነ ሥርዓት ተከናወነ። በስነ ሥርዓቱ ላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ቆሞሳት ፣ ካህናትና በርካታ ምዕመናን ተገኝተው እንደነበር ከቤተክርስቲያኗ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተገኘው መረጃ ያሳያል። Photo Credit - TMC @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " የ4 ሰዎች አስክሬን ከተለያየ ቦታ አውጥተናል። ...‘13 ሰዎች በጎርፍ ተወሰዱ’ የሚለው ትክክለኛ መረጃ አይደለም " - አቶ ንጋቱ ማሞ ከቀናት በፊት “ ሰዓሊተ ምህረት ጀርባ ያድሩ የነበሩ 13 የጎዳና ተዳዳሪ ልጆች በጎርፍ ተወስደው ሕይወታቸው እንዳለፈ አካባቢው ላይ ተነግሯል ” ሲሉ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። በስፍራው የእሳት አደጋ ሠራተኞች ፣ ዋናተኞች፣ የፌደራል ፓሊስ አባላት ተገኝተው አስክሬን ለማውጣት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደተመለከቱ የገለጹ ሲሆን ፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ስለጉዳዩ የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ሥራ አመረራር ኮሚሽንን ጠይቋል። የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ በሰጡት ምላሽ፤ “ ባለፈው እንደገለጽነው የ4 ሰዎች አስከሬን አውጥተናል። ‘13 ሰዎች በጎርፍ ተወሰዱ’ የሚለው ትክክለኛ መረጃ አይደለም። ጥቆማ ከሆነ ሊሆን ይችላል ” ብለዋል። “ ምክንያቱም በየትኛውም ጉዳይ ሕይወቱ ያለፈ ሰው ቢኖር ወይ እሳት አደጋ ወይ ፓሊስ ነው የሚያነሳው፤ በግለሰብ ደረጃ አስከሬን አንስቶ ቀብር ያለ አይመስለኝም ” ነው ያሉት። “ በቦታው ነበርን ግን ይሄ አሁን የተጠቀሰው ቁጥር (13) አስከሬን አልተገኘም። ያገኘነው 4 አስከሬን ነው ” ያሉት አቶ ንጋቱ ፣ 4ቱን አስክሬን ለፓሊስ አስረክበናል ሲሉ አስረድተዋል። 4 አስክሬን የት አካባቢ ነው የተገኘው ? ለሚለው ጥያቄ፣ “ ሰዓሊተ ምህረትም፤ ከተለያዩ ቦታም ነው የገኘነው። ጎዳና ተዳዳሪ ይሁኑ፣ እዛው አካባቢ ነዋሪ ይሁኑ እኛ መረጃ የለንም። ፓሊስ ነው የሚያረጋግጠው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። “ አሁን የሚሉት ጥቆማ ትክክለኛነቱ የሚረጋገጥ ከሆነ ከፓሊስ ጋር ሆነን ፍለጋ እናካሂዳለን። አንዳንድ ጊዜ ጥቆማ ትክክል አይደለም የሚል መደምደሚያ ላይኖር ይችላል” ሲሉ ተናግረዋል። ጎርፉ ተቋማትን ጨምሮ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን፣ በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለው ኑሯቸውንና እንቅስቃሴያቸውን ወንዝ አካባቢ ባደረጉ ሰዎች እንደሆነ፣ ማህበረሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ፣ አደጋ ከደረሰም በ #939  የኮሚሽኑ ስልክ በፍጥነት ደውለው እንዲያሳውቁ አስገንዝበዋል።  #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
نمایش همه...