cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

አግናጥዮስ

@አግናጢዎስ

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
344
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ጥቅምት 22 የቅዱስ ሉቃስ በዓለ ዕረፍት በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ❤ ቅዱስ ሉቃስ ቊጥሩ ከ72ቱ አርድእቱ ውስጥ ሲኾን በግሪክ ቋንቋ ሉቃስ ማለት ብርሃን የሚሰጥ ማለት ሲኾን በግብሩ ደግሞ “መበሥር” (አብሣሪ) ተብሏል፤ ምክንያቱም ቅዱስ ገብርኤል ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም ተልኮ አምላክን እንደምትፀንስ ያበሠራትን ብሥራት የጻፈ ነው። ❤ ይኽ ወንጌላዊ ከሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት በስሙ የተጠራለት ወንጌልንና የሐዋርያት ሥራን ጽፎልናል፤ ይኽ ወንጌላዊ የመጀመሪያ ሙያው ሐኪም (የሕክምና ዶክተር) ነበር፤ በኋላ ግን የነፍስ ሐኪም እንዲኾን ክርስቶስ መርጦታል፤ ቅዱስ ጳውሎስም “የተወደደው ባለ መድኃኒቱ ሉቃስ ዴማስም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል” በማለት የሕክምና አዋቂነቱን መስክሮለታል (ቆላ 4፡14)። ❤ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደምንረዳው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ለመጀመሪያ ጊዜ የጌታን የስቅለቱን ሥዕል እንደሣለ በተመሳሳይ መልኩ ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕል የሣለ ነው። በወንጌሉ ላይ እመቤታችን ጌታን በቤተልሔም መውለዷን የጻፈው ሉቃስ ጌታን እንደታቀፈች አድርጎ በ60 ዓ.ም. የሣላት ሲሆን የነገረ መለኮት ምሁራን The original “iconographer,” responsible for writing the first icon of the Blessed Virgin Mary ይሉታል። ❤ ከኢትዮጵያ ሊቃውንቱ አንዱ የመልክአ ሥዕል ደራሲም ይህንን ሲጠቅስ፡- “ሰላም ለሥዕልኪ እንተ ሠዐላ በእዱ ሉቃስ ጠቢብ እምወንጌላውያን አሐዱ” (ከወንጌላውያን አንዱ ዐዋቂ ሉቃስ በእጅ ለሣላት ለሥዕልሽ ሰላምታ ይገባል) ብሏል። ❤ ይኽቺም ቅዱስ ሉቃስ የሣላት የእመቤታችን ሥዕል ከላይዋ ላይ ዘይት እየፈሰሰ፤ ወዝ እየወዛ ብዙ ተአምራትን ትሠራ ነበር። በሰማዕታት ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች በመከራው ሰዓት በሚደበቁበት ግበበ ምድር (ካታኮምብ) ዋሻ ግድግዳ ላይ ቅዱስ ሉቃስ እንደሣላት እያስመሰሉ የእመቤታችንን ሥዕሏን ይሥሉ ነበር፡፡ ❤ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ላይ እንደምናነብበው "መራሒተ ፍኖት" Hodigitra "She who Shows the Way"፣ "ርኅርኅት ድንግል" Eleusa "Virgin of Tenderness" በመባል የሚታወቁና ሌሎች የእመቤታችንን ሥዕል እንደሣለ ይነገራል። ❤ በ460 ዓ.ም. ያረፈው የንጉሥ ቴዎዶስዮስ 2ኛ ሚስት ኢውዶኪያ “መራሒተ ፍኖት” ተብላ የምትጠራውን ቅዱስ ሉቃስ የሣላትን ሥዕል ከቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ለንጉሥ አርቃዴዎስ ልጅ ለፑልቼሪያ ልካላት ነበር፤ ቅዱስ ሉቃስ በዘመኑ ሰባት የእመቤታችንን ሥዕል የሣለ ሲኾን የተለያዩ ጥንታውያን ሀገራት ውስጥ ሲገኙ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጥንታውያን ገዳማት ውስጥ ቅዱስ ሉቃስ የሣላቸው የእመቤታችን ሥዕላት በተለያየ ጊዜ እንደመጡ ይነገራል (Cormack, Robin (1997) Painting the Soul, Icones, p.46)፡፡ ❤ ይኽ ቅዱስ ሉቃስ ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ በሰማዕትነት በሮሜ ካረፉ በኋላ ርሱ ወደዚኽች ሀገር ገብቶ ወንጌልን ሲሰብክ ጣዖታት ይደቅቁ ነበር፤ ካህናተ ጣዖታቱም አማልክታቸው እየረገፉ መውደቃቸውን ሲመለከቱ በንዴት ልብሳቸውን ቀድደው ጠጒራቸውን ይነጩ ነበር፤ ከዚያም ወደ ንጉሡ ኔሮን ኼደው ነገሩት፤ ርሱም ይኽነን በሰማ ጊዜ ተበሳጭቶ ባስቸኳይ ተይዞ እንዲመጣ አዘዘ፤ ❤ ሉቃስም ከዚኽ ዓለም መውጫው እንደ ደረሰ በመንፈስ ቅዱስ ዐውቆ ወደ ባሕር ዳርቻ በመኼድ ዓሣ ያጠምድ የነበረውን አረጋዊ ጠራው፤ ርሱም በሉቃስ ላይ ያደረውን ጸጋ እግዚአብሔር ባየ ጊዜ በእግሩ ሥር ወድቆ ሰገደ፤ ርሱም ከወደቀበት አንሥቶ መጻሕፍቱን በመስጠት “ዕቀብ እሎንተ መጻሕፍተ እስመ እማንቱ ይበቊዓከ ወያበጽሓከ ውስተ ፍኖተ እግዚአብሔር” (ወደ እግዚአብሔር መንገድ መርተው ያደርሱኻልና እሊኽን መጻሕፍት ጠብቃቸው) ብሎታል፡፡ ❤ ከዚያም በወታደሮች ተይዞ በንጉሥ ኔሮን ፊት ቈሞ ስለ ክርስቶስ አምላክነት መሰከረ፤ ንጉሡም በብስጭት የቅዱስ ሉቃስ ደም እንደ ውሃ እስኪፈስስ ድረስ እንዲገረፍ አደረገ፤ ከቅዱስ ገብርኤል ብሥራት በመዠመር ወንጌልን የጻፈውን የቀኝ እጁን እንዲቈረጥ አዘዘ። ❤ በቈረጡት ጊዜም “ኦ ንጉሥ አእምር ከመ ኢንፈርህ ሞተ ዝንቱ ዓለም ወዘንተ ብሂሎ ነሥኣ ለምትርት እዴሁ ዘየማን በፀጋማይ እዴሁ ወአስተላጸቃ ውስተ መካና ወኮነት ድኅንተ ከመ ቀዳሚ” ይላል (ንጉሥ ሆይ እኛ የዚኽን ዓለም ሞት እንደማንፈራ ዕወቅ፤ ነገር ግን የጌታዬንና የፈጣሪዬን ኀይሉን ታውቅ ዘንድ አሳይኻለኊ) ካለው በኋላ ብሥራተ ድንግልን የጻፈባት ሥዕሏን የሣለባት የተቈረጠች የቀኝ እጁን በግራ እጁ አንሥቶ ከተቈረጠችበት ቦታዋ ላይ አገናኝቶ እንደቀድሞዋ ጤነኛ አድርጓታል። ይኽነንም አይተው 477 ሰዎች አምነዋል፤ ከዚያም ንጉሡ ከቅዱስ ሉቃስ ጋር ራሳቸው እንዲቈረጥ አዝዞ ጥቅምት 22 የምስክርነትን አክሊል ተቀዳጅተዋል፡፡ ❤ ኢትዮጵያዊው ሊቅ አርከ ሥሉስም ይኽነን በዐርኬው ላይ ሲገልጽ፦ ✍️ “ሰላም ለሉቃስ እንተ ረትዐ ልሳኑ ወንጌለ መለኮት ይጽሐፍ እምእለ ብዙኃን ወጠኑ ከመ ያርኢ ኀይለ ቅድመ ኔሮን ወተዐይኑ አስተላጸቃ ወሌለያ ለምትርት የማኑ እስመ ላዕሌሁ ተሰውጠ ለክርስቶስ ሥልጣኑ” (ብዙዎች ሊጽፉት የዠመሩት ከመኾኑ የተነሣ የመለኮትን ወንጌልን ይጽፍ ዘንድ አንደበቱ ለቀና ለሉቃስ ሰላምታ ይገባል፤ በኔሮንና በሰራዊቱ ፊት ኀይልን ያሳይ ዘንድ የተቈረጠች ቀኝ እጁን ለያት መልሶም አጣበቃት በርሱ ላይ የክርስቶስ ሥልጣን ተጨምሯልና) በማለት ጽፎታል፡፡ ቅዱስ ሉቃስ ሆይ ቅዱስ ወንጌልን በጻፈው እና የአምላክን እናት ሥዕሏን በሣለው እጅኽ እንድትባርከን እንለምንኻለን፡፡ ለአስተያየት 👉 @kokuha_haymanot_bot ይጠቀሙ 💚 @kokuha_haymanot 💚 💛 @kokuha_haymanot 💛 ❤️ @kokuha_haymanot ❤️
نمایش همه...
አባ ዮሐንስ ሐፂር ትምህርቶች የጠላቱን ከተማ ለመቆጣጠር የዘመተ ንጉሥ አስቀድሞ የውኃውን መንገድ ይዘጋል ፣ የእህሉንም መግቢያ ይይዛል። ያንጊዜ ጠላቶቹ ይራባሉ ይጠማሉ። በመጨረሻም እጃቸውን ይሰጣሉ። የነፍስን ፆር ለማሸነፍም በተመሳሳይ መንገድ መጠቀም ይገባል። አንድ ሰው በጾምና በረኃብ ከጸና የነፍሱ ጠላቶች ይዳከማሉ። ✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟ እኔ በትልቅ ዋርካ ሥር የተቀመጠንና አራዊት ሊጣሉት የመጣን ሰው እመስላለሁ። ሊቋቋማቸው እንደማይችል ከተረዳ ሸሽቶ ወደ ዛፉ በመውጣት ነፍሱን ያድናል። በእኔም የተፈጸመው ይኼው ነው። በበዓቴ ተቀምጬ ክፉ ሐሳቦች ሊቃወሙኝ ሲመጡ ፣ ልቋቋማቸው እንደማልችል ባወቅኹ ጊዜ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ሸሽቼ እመሸጋለሁ። በዚያም ከጠላቶቼ ፍላፃ እድናለሁ። ✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟ መለወጥ የምትፈልግ ነፍስ በተመለከተ አባ ዮሐንስ እንዲህ አለ፦ በአንዲት ከተማ ውስጥ ብዙ ወዳጆች የነበሯት አንዲት አመንዝራ ሴት ነበረች። ከገዥዎቹ አንዱ ቀረባትና "መልካም ሴት ለመሆን ቃል ግቢልኝና አገባሻለሁ" አላት። እርሷም ቃል ገባችለትና ተጋቡ። ወደ ቤቱም ወሰዳት። የቀድሞ አፍቃሪዎቿ ያቺን ሴት ፈለጓት። እርስ በእርሳቸውም "ያ ልዑል ወደ ቤቱ ወስዷታል ፤ ወደ ቤቱ ብንሄድ ይቀጣናል። ነገር ግን በጓሮ በኩል እንሂድ ፣ ለእርሷም እናፏጭላት፥ የፉጨቱን ድምጽ ስትሰማ ከድርሱ ወርዳ ወደኛ ትመጣለች፤ በዚህም ያለ ችግር እናገኛታለን" ተባባሉ። ወደ ቤቷም ጓሮ ተጉዘው ያፏጩ ጀመር። እርሷ ግን የፉጨቱን ድምጽ ስትሰማ ጆሮዎቿን ደፈነች። ወደ ውስጣዊው እልፍኝም ገባች። በሩንም ጥርቅም አድርጋ ዘጋች። ይህች ሴት የእኛ ነፍስ ምሳሌ ናት። ወዳጆቿ የተባሉም ፈተናዎቿ ናቸው፣ ገዥ የተባለውም ክርስቶስ ነው፣ እልፍኝ የተባለውም ዘለዓለማዊው ቤት ነው። እነዚህም የሚያፏጩት ክፉዎች አጋንንት ናቸው፣ ነገር ግን ነፍስ ሁልጊዜም በክርስቶስ አምባነት ትሸሸጋለች። ✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟ አባ ዮሐንስ ልቡናው ከእግዚአብሔር ጋር ስለነበረ ምድራዊ ነገሮችን ይዘነጋ ነበር። አንድ ቀን አንድ ወንድም ቅርጫት ሊወስድ ወደ አባ ዮሐንስ በአት መጣ። አባ ዮሐንስም ምን ፈልጎ እንደሆነ ጠየቀው። ያም ወንድም "ቅርጫት ፈልጌ ነው" አለው። አባ ዮሐንስ ወደ በኣቱ ተመለሰና ዘንግቶት ወደ ሽመና ሥራው አመራ። ጥቂት ቆይቶ ያ ወንድም አንኳኳ አባ ዮሐንስም ወጥቶ "ምን ፈልገህ ነው?" አለው። "ቅርጫት ስጠኝ ብየህ ነበር" ሲል መለሰለት። ተመልሶ ወደ በኣቱ ሲገባ ልቡናው በሰማያዊ ነገር ስለተመሰጠ ዘንግቶት ወደ ሽመና ሥራው እንደገና ገባ። ለሦስተኛ ጊዜ ያ ወንድም ሲያንኳኳ አባ ዮሐንስ ተመልሶ መጣና "ምን ፈልገህ ነው?" አለው። "ቅርጫት ስጠኝ ብየህ ነበር" አለና መለሰለት። አባ ዮሐንስም እጁን ይዞ እየጎተተ ወደ በኣቱ አስገባውና "ቅርጫት ከፈለግህ ያዝና ሂድ፣ በእውነቱ እንዲህ ላሉት ነገሮች እኔ ጊዜ የለኝም" አለው። ✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟ አንድ ቀን አንድ ሰው ወደ አባ ዮሐንስ ሐጺር በኣት መጣና ሥራውን እያየ ያመሰግነው ጀመር። አባ ዮሐንስ ዝም አለውና ገመድ መሥራቱን ቀጠለ። እንግዳውም እንደገና ወሬውን ቀጠለ ፣ አባ ዮሐንስም ጸጥ አለው። ለሦስተኛ ጊዜ እንግዳው ወሬ ሲያበዛ "አንተ ወደ በኣቴ በመግባትህ እግዚአብሔር ወጥቶ ሄደ" ብሎ ተናገረው። ✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟ አባ ዮሐንስ እንዲህ አለ፦ "የብሕትውናን ኑሮ በከተማ ውስጥ የሚኖር አንድ ሽማግሌ ነበረ። ያ ሰው በከተማው ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠውና ባለዝናም ነበር። አንድ አረጋዊ አባት ከማረፉ በፊት ያንን ሰው ሊያየው እንደሚፈለግ ለዚያ ሰው ጥሪ ደረሰው። ያም ሰው በቀን ከተጓዝኩ ሰዎች ስለሚከተሉኝ ለኔ የተለየ ክብር ይሰጡኛል ብሎ አሰበ። ስለዚህም በሌሊት ሰው ሳያየው ለመጓዝ ወሰነ። በመሸ ጊዜም አሁን ማንም አያየኝም ብሎ ተነሣና ጉዞ ጀመረ። ነገር ግን ሁለት መላእክት ታዝዘው ፣ መብራት ይዘው መንገዱን ይመሩት ነበር። ይህንን የተመለከቱ የከተማው ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ ፣ መላ ከተማው ያንን የመላእክት ብርሃን እያየ ከኃላ ተከተለው። ከክብር በሸሸ ቁጥር የበለጠ ክብርን አገኘ። በዚህም "ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል ፤ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ከፍ ይላል።" የሚለው የወንጌል ቃል ተፈጸመ (ሉቃ. ፲፬፥፲፩)። የአበው በረከት ይደርብን linkun በመጫን ይቀላቀሉን ላልደረሰዉም ያድርሱልን... 💚💚👇👇👇👇👇👇👇💚💚 💛💛👉@Theophoross👈💛💛 💜💜👉@Theophoross👈💜💜 💖💖👉@Theophoross👈💖💖 💞💞👆👆👆👆👆👆👆💞💞
نمایش همه...
🌼የአዲስ አመት ስጦታ ከ EBS ቴሌቪዥን!🌼 ለ ቴሌግራም ቻናላችን ተከታይዎች! ባልነው መሰረት የያጋሩና ይሸለሙ ውድድር አሸናፋቻችን በአስገራሚ ስጦታዎች ለመሸለም ተዘጋጅተናል! የእንኳን ደስ አላችሁ ebs tv world wide!! 🌻 1ኛ ዘመናዊ አውቶሞቢል ለ 100 እድለኞች 🌻 2ኛ የባጃጅ ተሽከርካሪዎች ለ 150 እድለኞች 🌻 3ኛ ዘመናዊ ስማርት ስልኮች ለ 3000 ባለ እድሎች! ያስተውሉ ዕጩ ለመሆን መጀመርያ በጥንቃቄ ያንብቡ ለመሸለም ይህንን መንገድ ተከተሉ 1.መጀመርያ ከታች ባለው ማስፈንጠርያ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇👇 https://t.me/joinchat/AAAAAEyYjxQN-gzb9nxfEw 2.በመቀጠል ለ 50 ወዳጅ ዘመድዎ ይህን መልዕክት በፍጥነት ሼር ( Forward) ያድርጉ 3.እስከ መስከረም 10 ድረስ የሽልማቱ አሸናፊ ይሁኑ ! መልካም እድል! አሸናፊዎቹ በ ebs tv worldwide የቴሌግራም ቻናላችን ላይ የምንገልፅ ይሆናል ይቀላቀሉን 👇👇 https://t.me/joinchat/AAAAAEyYjxQN-gzb9nxfEw GOOD LUCK # EthiopianNewYear መልካም አዲስ አመት t.me/ebstvworIdwide
نمایش همه...
መልካም አዲስ ዓመት አዲስዓመት መልካምአዲስዓመት መልካም አዲስዓመት መልካም አዲስዓመት መልካም አዲስዓመት መልካም አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመትአዲስዓመትአዲስዓመት አዲስዓመትአዲስዓመትአዲስዓመት አዲስዓመት መልካምአዲስዓመት መልካምአዲስዓመትአዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት መልካም አዲስዓመትአዲስዓመት መልካምአዲስዓመት አዲስዓመት ዓመት አዲስዓመት መልካምአዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመትአዲስዓመት መልካም አዲስዓመትአዲስዓመት መልካም አዲስዓመትአዲስዓመት መልካም አዲስዓመትአዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት መልካም አዲስዓመትአዲስዓመት መልካም አዲስዓመትአዲስዓመት መልካም አዲስዓመትአዲስዓመት
نمایش همه...
†✝† እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ሕንጸተ ቤታ (ሕንጸታ) በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †✝† †✝† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✝ †✝† በዓለ ሕንጸታ †✝† †✝† በዚሕች ቀን : በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን በአምላክ እናት ስም ታንጻለች:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን "ሑሩ ወመሐሩ ኩሎ አሕዛበ" (አሕዛብን ሁሉ ሒዱና አስተምሩ) /ማቴ. 28:19/ ባላቸው ቃል መሠረት ዓለምን በወንጌል ያርሷት ዘንድ በዕጣ ተካፍለዋታል:: የሰው ልጅ ድኅነቱ የሚፈጸመው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበል ነውና (ዮሐ. 6:56) አበው ሐዋርያት ቁርባንን በተመረጡ ሰዎች ቤት እያዘጋጁ ቀድሰው ያቆርቡ ነበር:: በመጀመሪያ በጽርሐ ጽዮን: ቀጥሎም በተለያዩ ሰዎች ቤት እንዲሕ ይከናወን ነበር:: ለጸሎት ሥራ ደግሞ አንዳንዴ ምኩራበ አይሁድን ይጠቀሙ ነበር:: እየቆየ ሲሔድ ግን ከአሕዛብ ያመኑ ሰዎች ቁጥር እጅጉን በዛ:: በተለይ ቅዱስ ጳውሎስ ያሳመናቸው ለጸሎት እያሉ ወደ ጣዖት ቤት መግባት አመጡ:: በዚሕ ምክንያት መምሕራን ሕዝቡን "ካመናችሁ በኋላ እንዴት ወደ ጣዖት ቤት ትገባላችሁ?" ቢሏቸው "እኛ ምን እናድርግ! የምንጸልይበት እንደሆን የለን" ሲሉ መለሱላቸው:: ነገሩ ሲያያዝ ከደጋጉ ሐዋርያት ጳውሎስና በርናባስ ደረሰ:: ወዲያውኑ አንዳንድ ወንድሞች "ለምን አናንጽም" ብለው ነበር:: ቅዱስ ጳውሎስ ግን "ሊቀ ሐዋርያቱ ሳይፈቅድ አይሆንም" አለ:: (ለዚሕ ነው ዛሬም ሊቀ ጳጳስ ካልፈቀደ ቤተ ክርስቲያን የማይታነጸው::) ከዚያ ቅዱሳን ጳውሎስና በርናባስ ሐዋርያቱ ወዳሉበት ሔደው ነገሩን ለቅዱስ ጴጥሮስ አስረዱ:: ሊቀ ሐዋርያቱም "የጌታችን ፈቃዱ መሆኑን እናውቅ ዘንድ ተያይዘን ሱባዔ እንግባ" ብሎ አዋጅ ነገረ:: በዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድ ልብ ሱባዔ ገቡ:: በሱባዔአቸው መጨረሻም ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግርማ ወደ እነርሱ ወረደ:: ሁሉንም ሐዋርያት በደመና ጭኖ ፊልጵስዩስ አደረሳቸው:: ከከተማ ወጣ ብሎ ባለ መሬት ላይም "ቤተ ክርስቲያንን በእናቴ ስም አንጹ" ብሎ አዘዛቸው:: ለቅዱስ ጴጥሮስም ሦስት ዓለቶችን ሰጠው:: እነዚያን መሬት ላይ ተክሎ : ጌታችን ቆሞለት : ሐዋርያቱ እየተራዱት : ግርምት የምትሆን ሦስት ክፍል ያላትን የመጀመሪያዋን ቤተ ክርስቲያን በ52 ዓ/ም በዚህች ቀን አንጿል:: ¤ቤተ ክርስቲያኗን ነገ ጌታችን ቀደሳት የምንል ነንና ይቆየን:: ††† አምላካችን የድንግል እናቱን ፍቅር : የተቀደሰች ቤቱን ጸጋ : የቡሩካን ሐዋርያቱን በረከት ያሳድርብን:: ††† ሰኔ 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 2.ቅድስት ቤተ ክርስቲያን 3.ቅዱሳን ሐዋርያት 4.ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ (ዕረፍቱ) ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት (ሰማዕት) 2.ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር 3.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ 4.ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ) 5.አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና 6.ቅድስት ሳድዥ የዋሒት ††† "በድካም: አብዝቼ በመገረፍ: አብዝቼ በመታሠር: አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት: ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው::" ††† (፪ቆሮ. ፲፩፥፳፫-፳፰) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
نمایش همه...
ምክረ አጋንንት በቅዱስ አቡነ ዮሴፍ ዘላስታ 👉 ልጹም ትላለህ ፤ ተው አትጹም ይልሃል!አንተም ትተወዋለህ። 👉 ልመጽውት ትላለህ ፤ ተው አትመጽውት ይልሃል። አንተም ትተወዋለህ። 👉 ንስሐ ልግባ ትላለህ ፤ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ያለንስሐ ትሞታለህ። 👉 ልቁረብ ትላለህ ፤ ገና ነህ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ሳትቆርብ ትሞታለህ 👉 ላስቀድስ ትላለህ ፤ ተው ትንሽ ተኛ ይልሃል። አንተም ሳትሄድ ታረፍዳለህ። 👉 ጸበል ልግባ ትላለህ ፤ ጤነኛ ነህ ይልሃል። ገዳም ልባረክ ልሂድ ትላለህ ፤ ተው ስራን ስራ ይልሃል፡፡ አንተም ሳትሄድ ስትቆጭ ትኖራለህ። 👉 አስራት በኩራት ልስጥ ትላለህ ፤ ተው አትስጥ የለህም ይልሃል። አንተም ትተወዋለህ። 👉 በአንድ ልወሰን ትላለህ ፤ ተው ቆንጆዎቹ ያልፉሃል ይልሃል። አንተም በዝሙት ትወድቃለህ። #በመጨረሻም_የተወሰነልህ_ግዜ_ያልቃል። ነፍስህን አጋንንት እንደ ኳስ እየተቀባበሉ ይወስዷታል። #ልጠጣ ስትል ፤ ጠጣ ይልሃል። ያሰክርሃል። #ልዝፈን ስትል ፤ዝፈን ይልሃል። ያስጨፍርሃል! #ልስረቅ ስትል ስረቅ ይልሃል። ያሰርቅሃል! #ልጣለው ስትል ተጣላ ይልሃል። ያጣላሃል። #ልዋሽ ስትል ዋሽ ይልሃል። ያስዋሽሃል! ስጋዊ ተድላን ይሰጥሃል። ይመችሃል፡ስጋህ ወፍሮ ፣ ቀልቶ ፣ ወዝቶ በጓደኞችህ ‹ ተመቸህ እኮ ! › ያስብልሃል። አንተም ደስ ይልሃል! በዛው ትገፋበታለህ። 👉 #ሃሳብህ ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ቀርቶ ወደ ጅምናዝየም ቤት መሔድ ይሆናል። 👉 #ሃሳብህ ሁሉ የተመጣጠኑ ምግቦችን መመገብ ይሆናል። ሃሳብህ ሁሉ ሳውና ባዝ ፣ ስቲም ቤት ፣ማሳጅ ቤት ሂደህ መታሸት እና መዝናናት ይሆናል። 👉 #እግርህ ሁሉ ወደ ሲኒማ ቤት ፣ ወደ ናይት ክለብ ቤት ፣ ወደ ሆቴል ቤት ፣ ወደ ግሮሰሪ ቤት ፣ ወደ ሱፐር ማርኬት ፣ ወደ ምናምን ቦታ ይሆናል። 👉 በእነዚህ ሁሉ ስጋህ ሲመቸው 🌠 ቁሞ መጸለይ ይደክምሃል። 🌠 መስገድ ያቅትሃል። 🌠 መጾም ይከብድሃል። 🌠 ቤተክርስቲያን ለመሄድ ይጨልምሃል። 🌠 ስጋህ በአጋንንት መረብ ይጠመዳል። 🌠 ደም ብዝት አስይዞ ሴት ያዝልሃል። ደም ብዛት አሲይዞሽ ወንድ ያዝልሻል። 🌠 የነርቭ በሽታ አስይዞ መቆምና መሄድ ያስቅትሃል። 🌠 ስኳር በሽታ አሲይዞ ከጾም ይከለክልሃል። 🌠 ጨጓራ በሽታ አስይዞ ጾምን ይከለክልሃል። 🌠 #ምላስህ እግዚአብሔርን ማመስገንን ሳይሆን ዘወትር ስለ በሽታህ እንድትዘምር ያደርጋታል። #በጣም ብዙዎች ሃብት ሞልቷቸው በሽተኛ ያደርጋቸዋል። ገና ከጥዋቱ እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትለው ቢሄዶ ኖሮ ፤ እንደ አብርሃም ፣እንደ ይስሐቅ እና እንደ ያዕቆብ በምድር ሃብታም እንደ ሆኑ ሁሉ በሰማይም እንደ ቅዱሳኑ የገነት ባለቤት በሆኑ ነበር። #ሰይጣን ክፉ ነው! ሃብታሙን በሽተኛ ፣ ድሃውን ደግሞ ጤነኛ አድርጎ አምላክን ወቃሽ ያደርገዋል።እንዲህ እንዲህ እያለ የመሰናበቻ ጊዜ ይደርሳል። በኃጢአት የዳበረው ስጋችን አፈር ነውና በቅጽበት እሬሳ ተብሎ ወደ አፈር ይገባል። ነፍስ ግን እያዘነችና እየተፀፀተች ወደ ሲዖል ትወረወራለች። #የምናያቸው ቆንጆ ሴቶች ፣ የምናያቸው ቆንጆ ወንዶች ፣ የምናየው የልኳንዳ ስጋ ፣ የምናየው መጠጥና ምግብ ሁሉ ያምረናል። ስጋችን ያሸንፈናል፥ ነፍሳችን ትሸነፋለች። ለገነት ተፈጥረን ለሲዖል እንሆናለን። 👉 ወገኖቼ ይህ ዘመን ከባድ ነው። ገዳም ገብተህ እንዳትመንን ዓለም እንደ ወለላ ማር ትጣፍጥሃለች። 👉 በዓለም ሆነህ ስጋህን እንዳታቸንፍ ጓደኞችህ ፣ ቤተሰቦችህ ፣ ጎረቤቶችህ ፣ ዓይኖችህ ፣ ጀሮዎችህ ፣ ምላስህ ፣ እግርህ ፣ እጅህ ፣ ልብህ እንቢ ይሉሃል። በምድር ትሸነፋለህ ፤ በሰማይም ትሸነፋለህ። መጨረሻህ ገሀነም ይሆናል። 🙏 ራሳችንን በመንፈሳዊ አይን ብንመለከተው ባዶ ነን! ጽድቅ የሌለን ፣ ስም ብቻ የተሸከምን በኃጢአት የተሞላን አህዛብ ነን። 🙏 ሁላችንም ወደ እግዚአብሔር ተመልሰን ንስሃ ካልገባንና ወደ ቅዱስ ቁርባኑ ካልቀረብን መጨረሻች ገሃነም እንደሚሆን አፌን ሞልቼ እናገራለሁ። ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ! 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur
نمایش همه...
አንድ ሰው መጥቶ ለአንድ ቅዱስ አባት ጥያቄ አቀረበለት ፦ "ተአምር መሥራት እፈልጋለሁ ፣ እንዴት ላድርግ?" ቅዱሱ አባት መለሰለት፦ "አንድን ሰው ወንጌል እንዲያነብ ካስተማርከው ዓይን አበራህ ማለት ነው። ድሆችን እንዲረዳ ካስተማርከው ሽባውን አዳንክ ማለት ነው ።ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ እንዲችል ካደረግህ አንካሳውን ፈውሰኻል። ሙት ማንሣት ከፈለግህ ደግሞ ንስሓ እንዲገባ አድርገው ያኔ የሞተ ሰውን አስነሥተሃል ማለት ነው በል ሒድና ተአምር ሥራ!" ★ ★ ★ ለልጆቻችን ክርስቶስ ማን እንደሆነ እኛ ካልነገርናቸው ዓለም ክርስቶስ ያልሆነውን ሁሉ ይነግራቸዋል። ★ ★ ★ ኃጢአተኞች በሌላ ኃጢአተኛ ላይ ከእነርሱ ለየት ያለ ኃጢአት ስለ ሠራ ይፈርዱበታል ፣ ወይም ተመሳሳይ ኃጢአት ቢሠራም ይፈርዱበታል። ★ ★ ★ አባታችን ሆይ እንዴት ትላለህ? እንደ ልጅ ካልኖርህ እንዴት "አባት" ትለዋለህ? ሌላውን ጠልተህ ራስ ወዳድ ከሆንክ እንዴት አባት "አችን" ብለህ በአንድነት ትጠራዋለህ? ምድራዊ ነገር ብቻ እያሰብህ እንዴት "በሰማያት የምትኖር" ትለዋለህ? ልብህ ከእርሱ ርቆ በአንደበትህ ብቻ እየጠራኸው "ስምህ ይቀደስ" እንዴት ትለዋለህ? ሥጋዊና መንፈሳዊውን እየቀላቀልህ "መንግሥትህ ትምጣ" ለምን ትለዋለህ? መከራን በጸጋ የማትቀበል ከሆነ "ፈቃድህ ይሁን" ለምን ትላለህ? ለራስህ ሆድ እንጂ ለተራቡት ግድ የማይሰጥህ ከሆነ ለምን "እንጀራችንን ሥጠን" ትላለህ? በወንድምህ ላይ ቂም ይዘህ "እኛም የበደሉልን ይቅር እንደምንል" እንዴት ትላለህ? የኃጢአትን አጋጣሚዎች ሳትሸሽ "ወደ ፈተና አታግባን" እንዴት ትላለህ? ክፉን ለመቃወም አንዳች ሳታደርግ "ከክፉ አድነን" እንዴት ትላለህ? ጸሎቱን ከልብህ ሳትሰማውስ እንዴት አሜን ትላለህ? © ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ linkun በመጫን ይቀላቀሉን ላልደረሰዉም ያድርሱልን... 💚💚👇👇👇👇👇👇👇💚💚 💛💛👉@Theophoross👈💛💛 💜💜👉@Theophoross👈💜💜 💖💖👉@Theophoross👈💖💖 💞💞👆👆👆👆👆👆👆💞💞
نمایش همه...
نمایش همه...
Yhnn ye hywet metshaf tegabezulgn wud yegziabher seboch
نمایش همه...
አንድ ሰው መጥቶ ለአንድ ቅዱስ አባት ጥያቄ አቀረበለት ፦ "ተአምር መሥራት እፈልጋለሁ ፣ እንዴት ላድርግ?" ቅዱሱ አባት መለሰለት፦ "አንድን ሰው ወንጌል እንዲያነብ ካስተማርከው ዓይን አበራህ ማለት ነው። ድሆችን እንዲረዳ ካስተማርከው ሽባውን አዳንክ ማለት ነው ።ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ እንዲችል ካደረግህ አንካሳውን ፈውሰኻል። ሙት ማንሣት ከፈለግህ ደግሞ ንስሓ እንዲገባ አድርገው ያኔ የሞተ ሰውን አስነሥተሃል ማለት ነው በል ሒድና ተአምር ሥራ!" ★ ★ ★ ለልጆቻችን ክርስቶስ ማን እንደሆነ እኛ ካልነገርናቸው ዓለም ክርስቶስ ያልሆነውን ሁሉ ይነግራቸዋል። ★ ★ ★ ኃጢአተኞች በሌላ ኃጢአተኛ ላይ ከእነርሱ ለየት ያለ ኃጢአት ስለ ሠራ ይፈርዱበታል ፣ ወይም ተመሳሳይ ኃጢአት ቢሠራም ይፈርዱበታል። ★ ★ ★ አባታችን ሆይ እንዴት ትላለህ? እንደ ልጅ ካልኖርህ እንዴት "አባት" ትለዋለህ? ሌላውን ጠልተህ ራስ ወዳድ ከሆንክ እንዴት አባት "አችን" ብለህ በአንድነት ትጠራዋለህ? ምድራዊ ነገር ብቻ እያሰብህ እንዴት "በሰማያት የምትኖር" ትለዋለህ? ልብህ ከእርሱ ርቆ በአንደበትህ ብቻ እየጠራኸው "ስምህ ይቀደስ" እንዴት ትለዋለህ? ሥጋዊና መንፈሳዊውን እየቀላቀልህ "መንግሥትህ ትምጣ" ለምን ትለዋለህ? መከራን በጸጋ የማትቀበል ከሆነ "ፈቃድህ ይሁን" ለምን ትላለህ? ለራስህ ሆድ እንጂ ለተራቡት ግድ የማይሰጥህ ከሆነ ለምን "እንጀራችንን ሥጠን" ትላለህ? በወንድምህ ላይ ቂም ይዘህ "እኛም የበደሉልን ይቅር እንደምንል" እንዴት ትላለህ? የኃጢአትን አጋጣሚዎች ሳትሸሽ "ወደ ፈተና አታግባን" እንዴት ትላለህ? ክፉን ለመቃወም አንዳች ሳታደርግ "ከክፉ አድነን" እንዴት ትላለህ? ጸሎቱን ከልብህ ሳትሰማውስ እንዴት አሜን ትላለህ? © ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ 🔸@memher_eshetu ✍Comment @DnDawitsol
نمایش همه...