cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ማህበረ ፍኖተ ሕይወት(Mahebere Finote Hiwot)

" ...እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል፣ ነብይን በነብይ ስም የሚቀበል የነብይን ዋጋ ይወስዳል፤ ፃድቅንም በፃድቅ ስም የሚቀበል የፃድቀን ዋጋ ይወስዳል (ማቴ 10፤40-42) ” የሚለውን አምላካዊ ቃል መሰረት በማድረግ ማህበራችን መመስረት ቻለ፡፡ ለበለጠ መረጃ: @fmw1987, @ts121212, @Tsita8

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
399
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
+230 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

"አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኵራት ኾኖ ከሙታን ተነሥቷል።ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኗልና።" 1ቆሮ ፰፭÷፳~፳፩ እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።
نمایش همه...
"እንደ ተናገረ ተነስቷል "መላው የማኅበረ ፍኖተ ሕይዎት አባላት እንኳን አደረሳችሁ
نمایش همه...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ            አሜን ✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን" 📖ቆላስይስ 1፥10-11     ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥              እለተ ቅዳሜ     ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ ይህች በሰሙነ ሕማማት ያለች እለተ ቅዳሜ ልዩ ቀን ናት፤ በዙ ስምም አላት በጥቂቱ እንመልከት 1. ቀዳም ስኡር(የተሻረችው ቅዳሜ) ትባላለች ❖ ምክንያቱም እንደ ቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ በሰንበት እለት የግልም ሆነ የአዋጅ ጾም በፍጹም አይጾምም፤ ውጉዝም ነው፤ ነገር ግን በዚህች የሕማማት ቅዳሜ ይህ ሥርአት ይሻራል ይጾማልም። ❖ ስለዚህ የተሻረችው ቅዳሜ ተባለች፤ በዚህ እለት የሚጾምበት ምክንያት እናቱ እናታችን ድንግል ማርያምና ቅዱሱ ሐዋርያ ዮሐንስ የጌታን ሞት አይተው እስከትንሳኤው ምግብን አልቀመሱም ነበር። ❖ ያን መሠረት በማድረግ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ ከቻልን ከአርብ ጀምሮ ከከበደን ደግሞ ከቅዳሜ ጀምሮ ቀኑን ሙሉና እስከሌሊቱ 9:00 እናከፍላለን እንጾማለን። 2. ለምለም ቅዳሜ ትባላለች ❖ ምክንያቱም በዚህ እለት ጠዋት በቤተክርስቲያን ካህናት ለሕዝበ ምእመናን ለምለም ቀጤማን ያድላሉ፤ ምእመናንም ይህን ቀጤማ በጭንቅላታችን እናስራለን፤ ይህም ምሥጢር ✍"ለኔ ሰላምን ልትሰጠኝ አንተ የእሾህ አክሊል ደፋህ እኔን ልታነግሰኝ አንተ ተንገላታህ የክብር አክሊል ልታረግልኝ የሾህ አክሊል አረክ " ስንል ነው። 3. ቅዱስ ቅዳሜ ትባላለች ❖ ቅዱስ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ሥነ ፍጥረታትን ፈጥሮ ጨርሶ ያረፈባትና የቀደሳት ስትሆን በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ስለሰው ልጅ ሲል በቤዛነት ያደረገውን የማዳን ሥራ ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር አረፈ፥ በነፍሱም ወደ ሲኦል ወርዶ በሲኦል ለ5500 ዘመናት ሲሰቃዩ የነበሩ ነፍሳትን ሁሉ ወደ ዘላለም ረፍት ወስዷቸዋልና ይህች እለት ቅዱስ የሆነች ልዩ እለት ትባላለች። እንበለ ደዌ ወሕማም ፤እንበለ ጻማ ወድካም    ዓመ ከመ ዮም ፤ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ             እግዚአብሔር ለብርሃነ ትንሣኤሁ            በፍስሓ ወበሰላም ✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" 📖ምሳ 1፥33 🙏 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ      ✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን" 📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ                ወስብሐት ለእግዚአብሔር                               ይቆየን
نمایش همه...
نمایش همه...
ስንክሳር ዘወርኀ ሚያዝያ ፳፮

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን ✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"          📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ                ቀናችንን በጸሎት እንጀምር

نمایش همه...
ስንክሳር ዘወርኀ ሚያዝያ ፳፭

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ           አሜን

نمایش همه...
ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር ስለማጠቡ የሊቃውንት ትርጓሜ

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ        አሜን   ✥••••• ●◉ ✞ ◉●•••••✥ ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር ስለማጠቡ የሊቃውንት ትርጓሜ   ✥••••• ●◉ ✞ ◉●•••••✥ ❖ በዕለተ ዐርብ የዓለምን ኀጢአት በደሙ የሚያጥበው ከጎኑ በሚፈሰው ውሃ ዓለምን የሚቀድሰው ጌታችን አስቀድሞ በዕለተ ኀሙስ የደቀ መዛሙርቱን እግር በውሃ በማጠብ ትሕትናን የገለጸበት አስደናቂ ምስጢር የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በመገረም እንዲኽ ብለዋል፡-

نمایش همه...
ሰሞነ ሕማማት ዘእለተ ረቡዕ

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ        አሜን   ✥••••• ●◉ ✞ ◉●•••••✥   ሰሞነ ሕማማት ዘእለተ ረቡዕ   ✥••••• ●◉ ✞ ◉●•••••✥ 📌 ሰሞነ ሕማማት ዘእለተ ረቡዕ ምክረ አይሁድ ይባላል ❖ ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ❖ ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው። ❖ ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል። 📖ሉቃ 22፥1-6 የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል ❖ ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት…

نمایش همه...
ሰሙነ ሕማማት ዘእለተ ማክሰኞ

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ        አሜን   ✥••••• ●◉ ✞ ◉●•••••✥  ሰሙነ ሕማማት ዘእለተ ማክሰኞ   ✥••••• ●◉ ✞ ◉●•••••✥ 📌 ሰሙነ ሕማማት ዘእለተ ማክሰኞ ❖ ሻጮቹን እና ለዋጮቹን ከቤተ መቅደስ ባወጣ ጊዜ ይህንን በማን ኃይል እንዳደረገው የአይሁድ መምህራን ጠይቀውት ነበር፤ ስለ መሆኑም 📖ማቴ 21፥23-27 የጥያቄ ቀን በመባል ይታወቃል ❖ ምክንያቱም ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተ መቅደስ ምክንያት በዚህ ዕለት ስለ ሥልጣኑ በጻሕፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና፡፡ ❖ ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ❓ገበያ መፍታት በማን ሥልጣን ታደርጋለህ፤ የሚል ነበር…