cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Ethio 251 Media

ETHIO 251 is an independent media offering you News, Political Analysis and Information feeds.

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
22 590
مشترکین
+7124 ساعت
+4567 روز
+2 47830 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
ቅምሻ ጎንደር-ታች ጋይንት በደ/ጎንደር ታች-ጋይንት ወረዳ ጌዶዳ በተባለ ቦታ በመከላከያ እና በፋኖ ኃይሎች መካከል ከባድ ውጊያ እየተደረገ ነው። በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ኃይሎች ዋና መሪ ፋኖ ከፍያለው ደሴ  ስለ ውጊያው የሚከተለውን ብሏል። " የመንግስት ኃይል ከአራት አቅጣጫ ከበባ በማድረግ ግንቦት 11/2016 ዓ.ም  ማለዳ 11:45 ውጊያ ከፈተብን። እኛም የመሬቱን አቀማመጥ መሠረት በማድረግ የኃይል ስምሪት አድርገን የተከፈተብንን ጥቃት ሙሉ በሙሉ መክተናል።  በአፀፋዊ ምላሽ በመንግሥት ኃይል ላይ ከባድ ጉዳት አድርሰናል። አሁንም ውጊያው የቀጠለ ሲሆን እስከ አሁን ባለው የዘጠኝ ሰዓታት  ውጊያ 93 በላይ የመንግሥት ኃይል (ወታደር ዐድማ ብተናና ሚሊሺያ) ተገድሏል። ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ቆስለዋል። ሁለት ድሽቃ አራት ብሬል እና በርካታ የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎችን ማርከናል። ከሰዓት በፊት ይህን ያህል ጉዳት ያስተናገደው የብልጽግና መንግሥት   አራት Zu 23 የጫኑ ተሽከርካሪዎችን ከበርካታ ወታደሮች ጋር በድጋሚ እያስጠጋ ነው ሲል ጨምሮ ገልጿል።" ግንቦት 11/2016 ዓ.ም በለጠ ካሳ
نمایش همه...
👍 127 10👏 5😁 2
👍 106 4
21:58
Video unavailableShow in Telegram
ሰበር ዜና! "መንግሥት ፈርሷል፤ ፋኖን ተዋግተን ማሸነፍ አልቻልነም፤ የ51ኛ ክፍለጦር አባላት ነበርን ሙሉ ለሙሉ በዛሬው አውደ ውጊያ ክፍለጦሯ ፈርሳለች" የአብይ አህመድ አገዛዝ ምርኮኛ ሰራዊት በጎንደር ቀጠና ሚካኤል ደብር አካባቢ ከሰሞኑ በተደረገ ውጊያ የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ መብረቅ ክፍለ ጦርና የአማራ ፋኖ በጎንደር አጤዎቹ ክፍለጦር የጋራ ኦፕሬሽን በመስራት የተማረኩ ኃይሎች ከኢትዮ 251 ሚዲያ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ https://t.me/ethio251media
نمایش همه...
👍 132 29👏 11🔥 5😁 4💔 3
በዛሬው ዕለት ለኢትዮ 251 ሚዲያ የደረሰው ጥብቅ መረጃ እንዲህ ይላል፦ ዐቢይ አሕመድ በጦርነት ጉዳዮች እርሱ ባይሳካለትም ሴራ ሲያውጠነጥን ከሚባለው በላይ ሚስጥረኛ ሰው ነው፤ ለራሱ ሰዎች የማይተነፍስባቸው አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው። ሴራው የበሰለ ሲመስለው ለቅርብ ሰዎቹ ያሳውቃል ያኔ ለውስጥ አርበኞች ይደርሳል። የዛሬው መረጃችን ከዚህ ጋር የሚቀራረብ ነው። የሰሜኑ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ዐቢይ አሕመድ "ድሮን እንዳለው" ሚዲያ ላይ አንድም ቀን ተናግሮ አያቅም ነበር፤ በዚህም በወቅቱ ብዙዎቹን የፖለቲካ ኃይሎች የግምገማ ሚዛን አዛብቷል። አሁን ግን ሁኔታዎች ተቀይረዋል። ዐቢይ አሕመድ ግን ሁሌም ራሱን እንደብልጣብልጥ መሪ መቁጠሩን አላቆመም። በትላንትናው ዕለት የመከላከያ ኢንጅነሪንግ የተባለው የዐቢይ አሕመድ ወንበር ጠባቂ በሆነው ሠራዊት የሚመራውን ድርጅት እንደጎበኘ በሚዲያ ታይቶ ነበር። እውነታው ግን ይህ ድርጅት በበጀትና በሰው ኃይል አቅም መዳከም የተነሳ ስራ አቁሞ የከረመ መሆኑ ነው። ይህን ተከትሎ መረጃዎች ስላፈተለኩ ሚዲያ ላይ ሳይወጣ ድርጅቱ እየሰራ ነው የሚል ነገር ለማስወራት ሆነ ብሎ አልሞ ያደረገው ጉብኝት ነው። እውነታው ግን ድርጅቱ 100% ስራ አቁሟል። የተለቀቁ ቪዲዮ ማስተዋል ከቻላችሁ አንድም የሚገጣጠም ብረት ለበስ ታንክ የለም።" ሁሉም በግዥ የመጡ የምስራቅ አውሮፓ አገራት ስሪቶች ናቸው። እነዚህን እያሳየ ያለው ፋኖን እና የኤርትራ መንግሥትን ለማስፈራራት ነው። በነገራችን ላይ በሰኞ የአጀንዳ ፕሮግራማችን "አይቀሬው የዐቢይ አሕመድ ጦርነት በኤርትራ ላይ" በሚል ርዕስ ዘርዘር ያለ በጥብቅ መረጃዎች የተሞላ ፕሮግራም ይዘን እንቀርባለን ከወዲሁ ጠብቁን። ወደሁለተኛው መረጃዬ ሳልፍ… ግንቦት 14 /2016 ሁለተኛ ምዕራፍ ብለው በፋኖ ኃይሎች ላይ በተለያዩ ቀጠናዎች የማጥቃት እርምጃ እንወስዳለን ብለዋል። ፋኖም መከላከያ በተጠጋባቸው ቀጠናዎች ትልልቅ ወጠመድ ቆረጣ እና ደፈጣ ያድርግ። በዋናነት ወሎ እና ጎንደር ቀጠናዎች ታርጌት ተደርገዋል። ጎጃም ዕዝ ዳግም የቋሪት ቀጠናን የመቆጣጠር እቅድም አቅምም አደራጅቷል ይሄን ነገር ተጠቅመን አከርካሪውን እንምታ በማለት ከፍተኛ ጸረ ማጥቃት ልምምድ ብርሸለቆ ላይ ተጀምሯል። በተጨማሪም ከፍተኛ የሆነ ከቦታ ቦታ የሎጀስቲክ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሆነ ለኢትዮ 251 ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመላክታል። የሎጀስቲክ እንቅስቃሴውም "ወንዝ ማዶ" በማለት ሲሆን በክረምቱ ይሁን በአሁን ሰዓት እንደልብ መሳሪያ ማንቀሳቀስ በማይቻልባቸው ቦታዎች ሽፋን የሚሰጥ መድፍ ጨምሮ ሞርተር እና ዲሽቃ እያስቀመጡና እያንቀሳቀሱ እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ ያመላክታል። የተቀመጡት መሳሪያ ለማሸሽ ስለማይመቹ gps እንዲገጠምላቸው አዘዋል በተጨማሪም ለአየር ጥቃት እንዲመች አድርገው ነው የሚያስቀምጡት ። በግንቦቱ ውጊያ ሸዋ ላይ የተለየ እንቅስቃሴ አይኖርም የሚል ውሳኔ ወስነዋል ነገር ግን ይሄ መረጃ አሾልከው አስወጥተው ውጊያ ሊከፍቱ ይችላሉ የሚል መረጃም ደርሶናል። ለማንኛውም ግን ፋኖ ሁሌም ቢሆን ፋኖ በራሱ እቅድ ይመራ ይላል መረጃው የሸዋ ቀጠና ምክንያቱም ቀጠናው ውስብስብ ነው ይሄ ቀጠና ብቻውን መመታት ያለበት ነው ብለዋል። የአብይ አህመድ አገዛዝ አንድ ሪፓርት ላይ አድማ ብተና ከፋኖ ጋር ግጭት የገቡት በትግራይ ውጊያ ጊዜ ፋኖ መንገድ ጠብቆ ልዩ ሃይሉን መቷል የሚል ተመልክቻለሁ። ይሄ ነገር ፍጹም ውሸት እንደሆነ በ ውጊያ በነበሩ ፋኖ አመራሮ እንደዚህ አይነት ግድያ ማን ሲፍጸም እንደነበር የፋኖ ኃይሎች መግለጫ ቢሰጡበት መልካም ነው። ሌላ ተጨማሪ መረጃ የሚሊሻ እርሻ እንዲያርሱ የኦሮሞ ባለሃብቶች ወደ አማራ ክልል እንዲገቡ በእነ ሽመልስ አብዴሳ ውሳኔ ላይ ተደርሷል። ወደ አማራ ክልል የኦሮሞ ባለሀብቶች ትራክተር የሚመጣ ከሆነ በመረጃና ደህንነቱ ጥናት ያስደርግና እንደሚኒሻው ንብረት የእነዚህ ባለሀብቶች ንብረትም መወረስ እንዳለበት መረጃውን ያደረሱን ምንጮች ገልጸዋል። በተመሳሳይ መረጃ የእነ አረጋ ከበደ የዞንና የወረዳ አመራር በውጊያ ላይ እያሉ በፋኖ ጥይት የተሰው ሚሊሻዎችን መሬት ላልሞቱ ሚሊሻዎች እያደለ እንደሚገኝ ለኢትዮ 251 ሚዲያ የደረሰው ጥብቅ መረጃ ያመላክታል። https://t.me/ethio251media
نمایش همه...
👍 84 5🔥 2🙏 2🐳 2
Photo unavailableShow in Telegram
ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ከቃሊቲ  እስር ቤት! እስር ቤት ውስጥ ሆኜ ብዙ የዩቱብ ሚዲያዎቻችን ተዘጉ ሲባል እየሰማሁ ነው። ሁሉም ለማለት በሚያስችል ሁናቴ የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል የሚዘግቡ ሚዲያዎች ናቸው። እነገሌ እየሠሩ ነው? ብለን እስር ቤት ያለነው ሰዎች ስንጠይቅ "ሠሞኑን ጠፍተዋል ተዘግቶባቸው ይሆናል ። ባለፈውም  አስራ አንደኛ ነው  አስራ አምስተኛ  ጊዜ ተዘግቶባቸው ነበር አሁንም ይሄው መንግስት አዘግቶባቸው ይሆናል የማናያቸው"   የሚል ነው የምናገኘው ምላሽ። በእየለቱ ሲዘጋብን ተከታትሎ ሰብስክራይብ አድርጎ እንድንነሳ ከማድረግ ይልቅ "ሰሞኑን ጠፍተዋል ። የሉም " በሚል እየሰለቸ ነው። መሬት ላይ ወርደው ባሩድ እያሸተቱ የሚዘግቡት ሳይደክሙ ተከታትሎ ሰብስክራይብ ማድረግ መታከቱ ያሳዝናል። ፋሺስቱ ደግሞ ይህንኑ ስልቹ መሆናችንን  እና በእልህ ተባብረን የምንደጋገፍ  አለመሆናችንን በመረዳት የዲጅታል ወታደር አዘጋጅቶ እያዘጋ ከዩቱብ ላይ እንድንጠፋ እያደረገን ነው ። በጦር ሜዳ ሽንፈት የተጋተው አቢይ አህመድ ወደ ሚዲያ የዲጂታል ጦርነት ዞሯል።  ትክክለኛ መረጃ የሚያቀብሉ እና መሬት ካለው ፋኖ ባልተለየ ህዝቡን የሚያነቁ ሚዲያዎች ላይ ነው  ያነጣጠረው። ታዲያ እንደት ይህንን ሁሉ በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር ለቴክኖሎጂ እጅግ የቀረበ ህዝብ እያለን ያአልተማረ ካድሬ ስብስብ የዲጂታል ወታደር ሆኖ ለመፋለም ሲመጣ ለምን እናፈገፍጋለን ? ወንድሞቻችን ደምና አጥንታቸውን እየከሰከሱ እኛ አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ሰብስክራይብ እና ላይክ ማድረግ እንደት እንቦዝናለን ? ይህ አድራጎት ቀላል ሊመስል ይችላል። ጠላት ግን ይህንን በማድረግ ሁላችንንም ከህዝባችን እየለየን ነው። አንዳንዶቻችን ሰብስክራይብ  ላይክ እና ሸር አድርጉ ሲባል ከገንዘብ ጋር የሚያይዙት አሉ። ስህተቱ  ይሄ ነው።  ጠላትም በተደጋጋሚ ማስቆምና መቆጣጠር የማይችለውን ጋዜጠኛ ወይም የዩቱብ ቻናል "ከዩቱብ በሚገኝ ገንዘብ" በሚል ያሸማቅቃል። በዚህ ጉዳይም  ምላሽ ከመስጠት  ይልቅ ችላ ስለምንል  ሠውም ከዩቱዩብ ገንዘብ በቁና  የሚታፈስ እየመሠለው የዩቱብ ሸቃዮች እያለ ይከተላል። አብይ አህመድ ግን ከውጭ ሳይቀር የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎችን ቀጥሮ ከዚያም አለፍ ሲል የዩቱብ ካምፓኒ ሰራተኞች ጋር በመመሳጠር ጋዜጠኞቻችንን እና አንቂዎቻችንን ከህዝብ ጋር እንዳይገናኙ  ብዙ ሚሊዮን ዶላር እያፈሰሰ ነው። ጦርነቱ ሁለት አለም ላይ ነው እየተካሄደ ያለው ። አንዱ መሬት ላይ ሌላው ሳይበር ላይ። መሬት ላይ ያለውን በቆራጥ የአማራ ልጆች መስዋትነት ጠላት በሀይል እየተመታ ነው። ልክ እንደ ጉንዳን በሁሉም ቦታ ቁንጥጫው በዝቶበት የሚሆነውን አጥቷል። በሳይበር ጦርነት ግን ይህንን ህዝብ ይዘን ያለምንም ደም መፍሰስ እና ላብ አንድት ደቂቃ ብቻ ሰብስክራይብ  ሸር እና ላይክ ባለማድረግ ጋዜጠኞቻችን : ህዝብን የሚያነቁ እና እንቁ ምሁራኖቻችን ሀሳባቸውን የሚያቀርቡበት የዲጂታል ሚዲያ ቻናል እየተመናመነ ነው። በመሆኑም ጠላት አምርሮ እየሄደበት ካለው መንገድ አንጻር እኛ በቀላሉ መቀልበስ የምንችለውን ስራ እየሰራን ባለመሆኑ ይህንኑ የሳይበር ጦርነት በርተተን ያለመታከት መመከት አለብን። ከእንግድህ በዃላ የሚዘጋ ሚዲያ ሳይሆን እንደ አዲስ ሌሎች ጋዜጠኞች እና  አክቲቪስቶች የሚቀላቀሉበትን ሚዲያ መክፈት እና እንዳይቸገሩ መደገፍ ይኖርብናል።  የአማራ ድምፅ ሚድያ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ከቃሊቲ  እስር ቤት https://t.me/ethio251media
نمایش همه...
👍 130 10👏 9
Photo unavailableShow in Telegram
ሰበር መረጃ-ወሎ የአማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ በ ሐይለኛ ትንቅንቅ እያደረገ ይገኛል። በተኩለሺ፣ በአባሆይ ጋራ እና በወንዳች የአማራ ፋኖ በወሎ ምስራቅ አማራ ፋኖ አሳምነው ከፈለጦር  የጠላትን ጦር እየለበለቡት ይገኛሉ። በበለጠ ሸጋው  የሚመራው የአሳምነው ክፍለጦር  በተኩለሺ፣ በአባሆይ ጋራ እና በወንዳች   ከጧት ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰዓት የጠላትን ኃይል እያርገበገቡት ይገኛሉ። ሰሞኑን የአማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ ከአገዛዙ ሐይል ተሰልፈው የአማራን ህዝብ ሲያሰቃዩና ሲወጉ የነበሩ የአድማ ብተና የልዩ ሀይል እና የሚልሻ  ታጣቂወችን የተሐድሶ ስልጠና ሰጥቶ ወደ ዕዙ መቀላቀሉ ይታወሳል። እነዚህ ሐይሎች የአማራ ፋኖ በወሎ  እያደርገ  ባለው የህልውና ተጋድሎ ተሰልፈው የእስከዛሬ በደላቸውን የሚያካክስ ጀብድ እየፈፀሙ እንደሆነም ከስፈራው ለማረጋገጥ ተችሏል። በዚህም ለወታደራዊ ስትራቴጅክ ቦታ አመች የሆንችውን ወንዳችን አስለቅቆ ወደ ሙጃ እየገሰገሰ ይገኛል። በዛሬው የውጊያ ውሎ እንደተለመደው ከከባድ እስከ የነብስ ወከፍ መሳሪያዎች፣ ከከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች እስከ ተራ ወታደሮች ተማርከዋል ተብሏል። ሙት እና ቁስለኛውን የወሎ ተራሮች ይመስክሩት። https://t.me/ethio251media
نمایش همه...
👍 110 20👏 9🔥 4 1
نمایش همه...
የቀይ ቦኔቶቹ ሚስጢርና በፋኖ የተማረኩት ሰራዊቶች ኑዛዜ | 251 Zare | 251 Agenda | Ethio 251 Media

👍 42
Photo unavailableShow in Telegram
መረጃ-ጎንደር የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ በአራቱም አቅጣጫ ሐይለኛ ትንቅንቅ እያደረገ ይገኛል። በአርማጭሆ፣በመተማ እና በወገራ ጀግኖች የጠላትን ጦር እየለበለቡት ይገኛሉ። በሻለቃ ሲሳይ አሸብር የሚመራው የጎቤ ክፍለጦር በአርማጭሆ፣በሻለቃ ባሻ ስጦታው የሚመራው የጎንደሬ በጋሻው ክፍለጦር በወገራ-ኪንፋዝ በገላ፣የአጣናው ዋሴ ብርጌድ በመተማ  አቸሬና ጋጄ  ከጧት ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰዓት የጠላትን ኃይል እያርገበገቡት ይገኛሉ። ሰሞኑን የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ከጠላት ሐይል ተሰልፈው ወገንን ሲወጉ የነበሩ ታጣቂወችን የተሐድሶ ስልጠና ሰጥቶ ወደ ዕዙ መቀላቀሉ ይታወሳል። እነዚህ ሐይሎች በአራቱም ማዕዘን እየተደረገ ባለው የህልውና ተጋድሎ ተሰልፈው የእስከዛሬ በደላቸውን የሚያካክስ ጀብድ እየፈፀሙ እንደሆነም የአማፋኖ ጎንደር ዕዝ ዋና አዛዥ ሻለቃ ሐብቴ ወልዴ አስታውቋል። በዛሬው የውጊያ ውሎ እንደተለመደው ከከባድ እስከ የነብስ ወከፍ መሳሪያዎች፣ከከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች እስከ ተራ ወታደሮች ተማርከዋል ብሏል። ሙት እና ቁስለኛውን የአርማጭሆ መተማና ወገራ በርሐወች ይቁጠሩት ያለው ሻለቃው መረጃው እስከተሰጠበት ሰዓት ድረስ ጦርነቱ እንደቀጠለ እና የሐይል የበላይነቱ እንደተለመደው በነበልባሉ ፋኖ እጅ እንደሆነ አብራርቷል። መረጃው የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ነው።
نمایش همه...
👍 88 25🔥 12
03:56
Video unavailableShow in Telegram
የአማራ ፋኖ በጎጃም ዕዝ ቋሪት ገረመው ወንዳወቅ ብርጌድ አመራር ከሆነው ፋኖ በለጠ አብርሃም ጋር የተደረገ ቆይታ
نمایش همه...
👍 36
09:03
Video unavailableShow in Telegram
የአማራ ፋኖ በጎንደር ዕዝ ዋና አዛዥ አርበኛ ሀብቴ ወልዱ ጋር የተደረገ ቆይታ
نمایش همه...
35👍 12