cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

አምደ ሃይማኖት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
226
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-27 روز
-930 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

የጽጌ_፯ኛ_ዐመት_፮ኛ_ሳምንት_ወረብ_ክበበ_ጌራወርቅ_.mp33.48 MB
የጽጌ_፯ኛ_ዐመት_፮ኛ_ሳምንት_ወረብ_ናሁ_ተፈጸመ_.mp33.07 MB
የጽጌ_፯ኛ_ዐመት_፮ኛ_ሳምንት_ወረብ_ተመየጢ_.mp32.18 MB
የጽጌ_፯ኛ_ዐመት_፮ኛ_ሳምንት_ወረብ_ኢየሐፍር_ቅድመ_ስዕልኪ_.mp32.91 MB
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ምስባክ ዘሳድሳይ ሳምንት ወበዓለ ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ፣ ወኢዮብ ጻድቅ፣ ወአቤል" #ተፈጸመ_ማኅሌተ_ጽጌ" 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ምንባባት፦ ቆላ፡ ፩÷፩-፲፪ ያዕ፡ ፩÷፩-፲፫ ግብ:ሐዋ ፲፫÷፮-፲፮ ማቴ ፳፩÷፴፫-ፍ:ም ምስባክ፦ ወይከዉን ከመ ዕፅ እንተ ትሁብ ኀበ ሙኀዘ ማይ፣ እንተ ትሁብ ፍርሃት በበጊዜሃ፣ ወቆጽላኒ ኢይትነገፍ። ትርጉም፦ እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች ይከናወንለታል፣ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፣ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል። መዝ ፩÷፫ ቅዳሴ፦ዘእግዝእትነ
نمایش همه...
🌹✣ይነበብ✣🌹 "ኢየኀፍር ቀዊመ ቅድመ ሥዕልኪ ወርኀ ጽጌ ረዳ አመ ኀልቀ፤ ዘኢየኀልቅ ስብሐተ እንዘ እሴብሐኪ ጥቀ" "የአበባ ወር ባለቀ ጊዜ የማያልቅ ምስጋናን በእጅጉ እያቀረብኹልሽ በሥዕልሽ ፊት ለመቆም አልፈራም/አላፍርም/" በአምላክ ቸርነት በእመቤታችን ምልጃ ዘመነ ጽጌውን ጀምረን ልንጨርስ ይኸው አንድ ሰንበት ብቻ ቀረችን! አንድም በህይወት ጫና አንድም በመንፈሳዊ ዝለት እስካሁን የነበሩትን እሁዶች በቤተክርስቲያን አድረን እንደ ሊቃውንቱ እመአምላክ ሆይ መልካሟ ርግቤ ሆይ ፀዓዳ በመለኮቱ ቀይሕ በትስብዕቱ የተባለውን ልጅሽ መድኃኔዓለምን ይዘሽ አቅፈሽ ሊቃነ መላእክቱን ደስተኛውን ገብርኤልን ርኅሩኁን ሚካኤልን አስከትለሽ ከኀዘኔ ታረጋጊኝ ዘንድ ወደኔ ነይ ለማለት አልታደልን ይሆናል! ሰው ቢሆን አቴንዳንስ ይዞ ከ6ቱ እሁዶች አንዱን ብቻ መጥተሃልና እኩል በረከት አይሰጥህም ይልህ ይሆናል፤ ሰይጣንም ቢሆን መጀመሪያ ግድ የለህም ደክሞሃል ጠዋት ትሄዳለህ ብሎ ሊያዘናጋህ ይሞክራል እሱን እንደምንም ካለፍከው አምስቱን እሁድ ተኝተህ አድረህ አሁን አንዷን ሄድክ አልሄድክ ምን ልትጨምር ብሎ ተስፋ ሊያስቆርጥህ ይጣጣራል፤ ጓደኞችህ ካልጠፋ ቀን ጠፍተው የሰነበቱት ጭምር ቅዳሜ ማታ ካልተገናኘን መቃብሬ ላይ እንዳትቆም ሊሉህ ይችላሉ፤ አንተ ግን ይሄን ሁሉ አልፈህ ለተፈጠርክበት ዓላማ መቆም መቻል አለብህ እርሱ ምንድነው ካልከኝ ምስጋና ነው! ቸሩ መድኃኔዓለም ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ደህና መጣህ ነው እንጂ ለምን መጣህ እንዴት መጣህ እስካሁን የት ነበርክ የሚለን አምላክ አይደለም እና ግድ የላችሁም የዛሬዋ አዳራችን በመቅደሱ ይሁን! ምናልባት ዛሬ አስራ አንደኛው ሰዓት ላይ መጥቼ ምን አገኛለሁ የሚል ካለ አንድ የመጽሐፍ ታሪክ ብቻ ላንሳ:- ማቴ 20: 1-7 ስለ ወይን ቦታው አትክልት ሰራተኞች አቀጣጠር የሚናገረው ታሪክ ላይ ያ የወይኑ ባለቤት ከ3 ሰዓት ጀምሮ ፤በ6፤በ9፤በ11 ሰዓት እየወጣ ሰራተኞችን እንዳመጣ ክፍያ ግን ለሁሉም ተመሳሳይ አንድ ዲናር እንደሰጣቸው ይናገራል:: ምስጢሩ 3 ሰዓት የተባለው ከ7-20 ያለው የሰው ዓመት ፤ 6 ሰዓት የተባለው ከ20-40፤ 9 ሰዓት የተባለው ከ40-60፤ 11 ሰዓት የተባለው ከ60-80 ያለው ነው። ሃይማኖት ሳይማሩ ምግባር ሳይሰሩ ኖረው በየትኛውም ሰዓት/3፣6፣9፣11/ ግን ሃይማኖት ተምረው ምግባር ሰርተው ቢያርፋ በአንድ ዲናር የተመሰለች መንግስተ ሰማያትን ሁሉም እኩል ይወርሳሉ ሲለን ነው። እና እኛም በ11ኛው ሰዓት ላይ በመጨረሻው የዘመነ ጽጌው ሰንበት መጥተን ከሊቃውንቱ ጋር ስናመሰግን ብናድር በ3ሰዓት ከመጡት ጋር እኩል በረከትን እንደምናገኝ መጽሐፍ ይነግረናል። እሊያህ የወይን ቦታው ሰራተኞች ሳይቀጠሩ በፊት ለምን ስራ ፈታችሁ ቆማችሁ ሲባሉ የሚቀጥረን አጣን ብለው ነበር እናንተም የሚጠራን አጣን የሚጋብዘን አጣን እንዳትሉ ይኸው አስቀድሜ አክብሬ ጠራኋችሁ! የማታ ሰው ይበለን 🌹✣🌹 ተፈጸመ! ማሕሌተ ጽጌ ዲያቆን ኤፍሬም አበበ ኅዳር 01/2016 ዓ.ም #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘን_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.