cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

#Selemen

እዚ ቻናል ላይ የተለያዮ ልብ ወለድ ስለፍልስፍና የተለያዮ መፅሀፎች ይለቀቃሊ። እና ምን ትጠብቃላቹ Joyen bela @Abnet2020

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
179
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
ተመራጭ ሳይክሎች ይዘንላቹ መተናል ሚሸጥ ነው ሳይክል መግዛት ምትፈልጉ contact አርጉኝ fixd Bricu 15.000 ብር ነው 0942166520 የሳይክል መሸጫ Chanal ይከፈት ምትሉ ከልጅ እስከ አዋቂ
نمایش همه...
😘ብቀላ😘 🔥ክፍል 38 📚ደራሲ ማሪኮሪሊ ቬንዳታ ✍ አዘጋጅ elu jaz ፣ ፣ ፣ ሳኩበት፡፡....... «አንተን ደስ ካለህ እቃውን ማምሻህን አደራጀው ግን የእመቤቲቱ አገልግሎት ይበቃኛል ከእንግዲህ አንተ ማሰብ የለብህም የአቨሊኖ ገዞህ ከዚህ ሁሉ በላይ ለኔ ብልጫ ያለው ነው ። ደግሞ የምታደርስልኝ መልእክት ኣለ ።» አንዲት ትንሽ የተቆለፈች የብረት ሳጥን አዘጋጅቶ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጦ አሳየሁት «ይህን ይዘህ እንድትሄድ ።» የውስጥ ስሜቱን መቋቋም እንዳቃተው ይታየኛል ። ሥራዬን ሁሉ ፈርቷል ። ደስተኛ እንዳልሆንኩ አውቋል ።እኔም ትእግስት እያጣሁበት ሄድኩ ። በመጨረሻው «የምትነግረኝ ካለ ንገረኝ» አልኩትና ። እጄን በፍርሃት ተጭኖ «ይቅርታ ያድርጉልኝ ባላዩኝ ሰዓት ሁሉ እኔ ኣዮት ነበር ። በውስጥዎ ሀዘን አለ ደሙ ወርዶ የማያባራ ቁስል በልቦ ውስጥ አለ ። እንዲህ ያለው ሀዘን ሞትን እንደሚያስከትል የታወቀ ነው ። እባክዎ ኣብሬዎት ልቆይ ጌታዬ ይፍቀዱልኝ ። ፊትዎን ለምጄዋለሁ፡፡ ለኝህ ትልቅ ሴት ወይዘሮም ያለዎት ፍቅር ለልቦ ደስታን አልሰጠውም ። ሰርጉን በተጠጉ ቁጥር ሀዘኖ እየከበደ ነው የሄደው ዛሬ ዛሬ ደግሞ ሌቱን ሙሉ ይጽፋሉ ። በመኝታ ሰዓትዎ ሁሉ ይጽፋሉ እና እንዲህ ልቦ በሀዘን መሰባበሩን እያየሁ እንዲህ ብቸኛ መሆንዎን እያወቅሁ እንዴት እኔ ከሊላ ጋር መደሰት እችላለሁ?>> እንደጅረት ውሀ እየተከታተለ የሚወርደውን ቃሉን ለማቆም እጄን ጨብጠው የያዙኝንእጆቹን እያላቀቅሁ <<የተቆጣሁ እንዳይመስልህ» በእርጋታ መንፈስ ኣልኩት ነገር ግን ከመጠን በላይ ስላሳሰብኲህ አዝናለሁ ለእኔ ኣታስብ ። ነገ የለፋሁበትን ሁሉ አገኛለሁ ። የመጨረሻው ደስታዬም ይኸው ነው ። ስለዚህአትጠራጠር ራስህን አታስጨነቅ የተለመደ ቅንነትህን አትንፈገኝ ። ባልኩህ ሰዓት ሹልክ ብለህ ሲኞራሞንቲ ዘንድ ድረስልኝ» ብዩ ትስሻውን መታመታ አደረኩት «በል ይልቅ ስለሰርጌ ቀን ብለህ ፊትህ ፈገግ ይበል ያለዚያ ሊላን አታገኝም>> አልኩት ። «ሌላው ከኣንተ የምፈልገው ደግሞ በፍጹም እንዳትከተለኝ ነው ። መታመንና ቅንነት አስፈላጊ ናቸው ግን እኔ ደግሞ ከአንተ ዛሬ የምፈልገው መታዘዝን ነው ። ፍጹም ታዛዥነትህ ያስፈልገኛል ተኝቼ ወይም ነቅቼ ሳለሁ በግሌ መሆን ኣለብኝ ። አንተም የራስህን እኔም ያሻኝን መሥራት አለብኝ ። ገባህ ቪንቼንዞ?» አዎን ገባኝ ጌታዬ» ሲል በልቡ ውስጥ ነገር እንደተምታታ በፊቱ ላይ ፈገግታ መጣ። «ስለድፍረቴ ይቅርታ ያድርጉልኝ» አለኝ፡፡ «ለምኑ ነው ይቅርታው? ከልብህ ስለወደድከኝ? እንደምትወደኝ አውቃለሁ።አሁን ግን እኔ ከአንተ የምፈልገው ትእዛዜን እንድትፈጽም ነው። ትእዛዜን ደግሞ ብትቀበለኝ የዘለዓለም ጓደኛሞች ነን፡፡ ከመጠን በላይ መውደድ ደግሞ ይቅርታ የሚያስጠይቅ አይደለም ።» «ትእዛዞን እፈጽማለሁ ።» «ይህን የብረት ሳጥን ነው ሲኞራ ሞንቲ የምሰጥ?>> «አዎን በእጅዋ እንድትሰጣት እስክመጣ እርስዋ ዘንድ ይቀመጥ።»ፊቱ በአንድ ጊዜ ፈካ፡፡ «ወዲያው ሊላን አይቼ እጠግባታለሁ ።» እንደማፈር ብሎ እቃዬን ሊያደራጅ ገባ ። ራት ላይ ተቀምጨ ጠራሁትና የጣሊያን ምርጥ ወይን ጠጅ በሁለት ብርጭቆ ቀድቼ በአንደኛው ውስጥ እንቅልፍ የሚያመጣ ፈሳሽ ጠብ ኣድርጌ ቪንቼንዞን እንዲጠጣ ጋበዝኩት ። እኩል አንስተን ግጥም አድርገን ጠጣን ። ራት የቀረበበትን ገበታ ኣነሳስቶ ፊት ለፊት እያዛጋ እንዲጠርግ የሰጠሁትን ካፖርቴን ይዞ መኝታው ክፍል እንደገባ ቀረ ። የማነብ መስዬ መጽሐፍ ገልጬ ለእኩል ሰዓት ጠብቄ ክፍሉ ብገባ እንቅልፍ ይዞት ሔዶአል ። የእንቅልፍ መጠጡ ጭልጥ አድርጐ ወስዶታል ። ሊከተለኝ በማይችልበት አይነት በእንቅልፍ አስሬ ያን ሌሊት መፈጸም ያለበትን ጉዳይ ለማከናወን ማንነቴን እንዳይታወቅ ተጠማጥሜ በጭለማ ወጣሁ በሙታን መንደር የማዘጋጀው ስላለ ኣንድም ፍጡር ሳያየኝ ገሰገስኩ ቪንቼንዞን ያጠጣሁት ለአራት ሰዓት ያህል በተኛበት እንደሚይዘው ስለማውቅ ድብቅ የሙታን መንደር ሥራዬን እንደጻዕረ ሞት ያለስጋት አከናውንኩ ። በእርግጥ ብዙ ሰዓት ፈጀብኝ ። ሥራዬን ስጨርስ የሙታን አጽም አጥንቴ መቅኖ ውስጥ የተሰካ ያህል ተሰማኝ ። በረደኝ ጥርሴን እስኪነዝረኝ አንቀጠቀጠኝ፡ ያሰብኩት እንደምንም ተጠናቆ ተፈጸመ ። ለመጨረሻው ትራጀዲ ወይም ኮሚዲ መድረኩ ሁሉ ተዘጋጀ፡፡ ሥራዬን ጨርሼ ዝናብና ጐርፍ አልፈ ቤቴ ስገባ ቪንቼንዞ ኣሁንም እንደተኛ ነው ። ነቅቶ ጠብቆኝ ፊቴንና መንፈሴን ቢያይ ኖሮ በጣም ይደነግጥ ነበር ። ፊቴን እኔው ራሴ በመስታወት ብመለከተው ሰቀጠጠኝ አንድ ሽበቱ የተመሰቃቀለ ዓይኑ የጉድ ተከታታይ የመሰለ ጨካኝ መጻጉዕ እመስላለሁ ። ልብሴ በዝናብ ሾቆአል እጅና ጥፍሬ መቃብር ብቻውን ሲጎደፍር አድሮ የነጋበት ይመስላል ። ጫማዎቼ በጭቃ ከብደዋል፡፡ ጠቅላላ ሁኔታዬ አንድ አሲቃቂ ተግባር ፈጽሜ የመጣሁ ይመስላል ። ንጋት እየተጠጋ የሠርጌ ማለዳ እየመጣ ነው፡፡ የተለመደ ቦታዬ ተቀምጬ ሳነብ ቪንቼንዞ እየተጨናበሰ ወጣና «እስከአሁን ድረስ ምን ጉድጓድ ዋጠህ ቪንቼንዞ»ብዬ ቀለድኩበት ። «እኔ እኮ ወይንጠጅ ኣለመድኩም አልኮሉ ነው መሰለኝ እንቅልፍ ይዞኝ ጭልጥ አለ ጌታዬ» አለ ።ማንም ሳያየኝ ባዘጋጀሁት የድብቅ ሥራ እየተኩራራሁ ጥቂት አንቀላፋሁ፡፡..... ✨ ይቀጥላል..... ሀሳብ አስተያየት Any Comment @Poul_Fuye ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @FuyeEhsutin ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
نمایش همه...
ሁሌም የሴቶች ዶርም ድረስ መጥቶ ሸኝቶኝ ሲመለስ ባለማመን ያዩታል። <<ሔለን ግን ሙድ እየያዝሽብን ነዋ! ያን ሁሉ ወንድ ያባረርሽው ይሔ ፉንጋ ጋር ለመሆን ነው?>> ትላለች አንደኛዋ። <<እስኪ ተያት ምን ታውቂያለሽ? ራቁቱን ያዬችው እሷ!>> ብላ ሌላኛዋ ታሽካካለች። እኔም አስከፋናት ብለው እንዳይደብራቸው እስቅላቸዋለሁ። ዋና ምክኒያቴን ከሚያውቁብኝ የጠረጠሩት እውነት እንደሆነ እንዲሰማቸው ባደርግ ይሻለኛል። ለሰው ባይመስልም ፉንጋው የፀሎቴ መልስ ብቻ ሳይሆን ጨለማ ክፍል ውስጥ ያገኘሁት ሻማዬ ነው። <<ሔሉዬ ሌላ ቅፅል ስም ጠፍቶ ነው 'ሻማዬ' የምትይኝ?>> ይለኛል። <<ሻማዬ ካላልኩህ ችቦዬ ነው የምልህ...የቱ ይሻልሀል?>> <<አይ ሻማው ይሁን በቃ!>> ይላል እየተቅለሰለሰ። አንዲት ፀበል ለፀበል የምትመላለስ ታላቅ እህት አለችኝ። ሰዎች መንፈስ ይዟት ነው እያሉ ያወራሉ። እኔ ግን ባሏን ፈትታ ከመጣች ቡኃላ የዘመድ አዝማዱን ወሬ አትችለው ብላ እንዳበደች አውቃለሁ። ከዛ ጊዜ ጀምሮ ፀሎቴ አንድና አንድ ብቻ ነው። <<ጌታ ሆይ የምወደውን ሳይሆን የሚወደኝን ስጠኝ!>> ለዛ ነው ሻማዬ የፀሎቴ መልስ ነው የምለው። የመጀመሪያ ቀን ሰውነቱ በላብ ተጠምቆ፣ እጁ እየተንቀጠቀጠ፣ መተንፈስ አቅቶት እየቃተተ ሲጠይቀኝ እንደማገባው ወስኜ ነበር። የግቢውን ወንዶች ሁሉ መልሼ እሱን የጠበስኩት እነሱ እንደሚሉት የተለዬ ነገር አግኝቼበት አይደለም። ሪስክ መውሰድ ስለማልችል ነው። የፈሪ ሰው ጥቅም?...ቀድሞ አያጠቃም! ግቢ ውስጥ በኔ ምክኒያት ያልደረሰበት ግፍ የለም። ለሁሉም ታዋቂ ካፕሎች ቅፅል ስም ሲሰጡ እኛን ማን ቢሉን ጥሩ ነው? "beauty and the beast" ሆሆ! ተረባውን ችሎ አለፍ ሲል ደግሞ መምህራኖች ግሬድ ያበላሹበታል። ጉልበተኞች ዱላ የቀላቀለበት ማስፈራሪያ ያዘንቡበታል። ዘበኞች እንኳን ባቅማቸው ያዋክቡታል። ሁሉም እንደየስልጣኑ ይበድለዋል። <<ሻማዬ ከዚህ በላይ እንድትጎዳ አልፈልግም>> ስለው <<ቀላል ነው ብዬ አልዋሸሽም። ሽልማቴ አንቺ እንደሆንሽ ሳስበው ግን 'ኧረ ያንሰኛል ጨምራችሁ ምቱኝ' ልላቸው ሁላ ያምረኛል!>> እያሳዘነ ያስቀኛል። ገፍተው ገፍተው ለራሱ ያለውን አመለካከት እንዳወረዱበት የገባኝ የአመቱ መጨረሻ ላይ ነው። እሱ ተመራቂ ስለነበር ቀጣይ አመት እንደማንገናኝ ገብቶት እያለቀሰ መጣ። <<አንተም ስራ ልታገኝ የምትችለው እዚሁ አዲሳባ ነው። እኔም እዚሁ ነው የምማረው! ምን የተለዬ ነገር ተፈጠረና ነው የምታለቅሰው?>> <<አንድ ነገር ብቻ ቃል ግቢልኝ!>> አለ አሁንም እያለቀሰ! <<እሺ ምንድን ነው?>> <<እስክትመረቂ ድረስ የፈለግሽው ወንድ ጋር ሁኚ! ከዛ ቡኃላ ግን ተመልሰሽ ወደኔ ልትመጭ ቃል ግቢልኝ!>> ምንም አላልኩትም። በቆመበት ጥዬው ሔድኩ። ምን ባደርገው ነው ሊተማመንብኝ የሚችለው? እኔስ በዚህ ደረጃ ከሚወደኝ ወንድ ውጭ ሌላ ምን እፈልጋለሁ? ከሶስት ቀን ቡኃላ የሻማዬን ልብ ያረጋል ብዬ ያሰብኩትን ትልቅ ውሳኔ ወሰንኩ። ሲያዬው አዲስ እንደተወለደ ህፃን ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ጀመረ። ለነገሩ እኔም ከዛ ያነሰ ግብረመልስ አልጠበኩም። ይሔንን ፊት ለዘላለም እንዳይጠፋ አድርጌ ጀርባዬ ላይ ተነቅሼለት ለቅሶ ሊበዛብኝ ነው? የሚያስቀው እንራራቃለን ብዬ ፊቱን ተነቅሼለት ሌክቸረር ሁኖ እዛው ግቢ ቀረ። የሚያሳዝነው ደግሞ ተማሪዎች በገቡ በመጀመሪያው ሳምንት ሁሉም ስለታቱዬ አወቁ። የፈሪ ትልቁ ችግር.....ምርኮኛ አያያዝ አይችልም! <<ለማን ተናግረህ ነው?>> ብዬ ሳፈጥበት...አብሮት ሌክቸረር ለሆነ ሰቃይ ጓደኛው ብቻ መናገሩን ነግሮ ይቅርታ ጠየቀኝ። እኔም ከተያዙ ቡኃላ መንፈራገጥ ጥቅም የለውም ብዬ ተውኩት። የግቢው አየር ባንድ ጊዜ ተገለበጠ። ሻማዬ የግቢው ቁጥር አንድ ተፈላጊ ወንድ ሆኖ ቁጭ አለ። እኔ ደግሞ ስወጣ ስገባ የተረባ መለማመጃ ሆንኩ። አንዴ ወጣቶች ተወራርደው አስገድደው ልብሴን ገልጠው፣ ታቱዬን ካዩብኝ ቡኃላ ከሀዘን የወጣሁበት ቀን ትዝ አይለኝም። ሻማዬ ሊጠብቀኝ ቀርቶ ቶሎ ቶሎ ሊያገኘኝ ራሱ ጥረት አያደርግም። እኔ ነኝ የምደውልለት። እንዲያውም አልናገርም ብዬ እንጂ አልፎ አልፎ የግቢው ታዋቂ ሴቶች ከቢሮው ሲወጡ አያለሁ። በአንድ ወቅት ሊነካኝ ከብዶት ሲንቀጠቀጥ የነበረ ሰው፤ ዛሬ መዳፉ ላይ ሲያገኘኝ ጨብጦ ሊያፈርጠኝ ሲዳዳ ባዬው...ለመረዳት ከበደኝ። የሆነ ቀን ጉዳዩን ጨራርሰን እንደተቀመጥን <<ሰሞኑን መድሀኒት ስትጠቀሚ አላይሽም! ሌክቸረር ሆነ ብለሽ ልታረግዥብኝ ነውዴ?>> አለኝ። በዚች ንግግሩ ታሪኬን ቀዬረው። ትምህርቴን አቋርጨ አዲስ ህይወት ጀመርኩ። ስሜንም ቀየርኩ። ታቱዬን ሙሉ ጥቁር አድርጌ "ብላክ ሆል" ነው እያልኩ መንገር ጀመርኩ። ሰላም ያለው ህይወት ለመኖር የነበረኝ አንድ አማራጭ ነበር። ሁሉንም ሰው ከህይወቴ አስወጥቼ ልጄን ማሳደግ። የዚያኔ እንደዛ ባለኝ ሰዓት ፀባዩ ሲስተካከል እነግረዋለሁ እያልኩ ያረፈድኩባት ፅንስ ነበረችኝ። አሁን አሁን ሳስበው ታሪኬ ረጅም ይመስላል እንጂ አጭር ነው። ይቺው ናት ውጣ ውረዴ! ልጄን እስካሳድግ ድረስ ሁለት ጊዜ ብቻ ነው ከቤተሰቦቼ ጋር የተገናኘሁት። እነሱም እምብዛም ሊያዩኝ አይፈልጉም። መላቀቅ ነው! ይቅሩብኝ ከነምላሳቸው! ምላስ ሽሽት ነው ነው ኑሮዬ! አልፎ አልፎ ስር እንዳይሰድ አድርጌ የወሲብ ግኑኝነት እጀምራለሁ። እነሱም ስለኔ ትንሽ ማወቅ ሲጀምሩ ጥያቸው ዲዲዲዲዲዲ! በዚህ ርዕስ ላይ ከማወራ ይሻለኛል። ልጄ በኔ መልክ ባባቷ ጭንቅላት በመውጣቷ ያገኛት ሁሉ ይወዳታል። እኔም በሷ እየተፅናናሁ እኖራለሁ። በቃ። ይሔን ሁሉ ቁጭ ብዬ የማስበው ዛሬ <<አባቴ ማነው?>> ብላ ጠይቃኝ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ሩጨ የማላመልጣት ሰው ገጠመችኝ። የመመለስ ግዴታ እንዳለብኝ አውቃለሁ። ግን እንዴት ነው የአ'ምሮ በሽተኛ ሳላደርጋት ስለአባቷ ልነግራት የምችለው? ተረት ላድርገው ይሆን? እምብዛም የማይንቁት...እምብዛም የማያደንቁት የ'ንደኔ አይነቷ ኖርማል ሰው ህይወት እንዴት ነው የሚተረተው? <<ተረት ተረት>> <<የመሰረት>> <<በድድሮሮሮሮ ጊዜ አንዲት ሔለን የምትባል ከብርጭቆዋ ጋር ጨለማ ክፍል ውስጥ የምትኖር ልዕልት ነበረች>> <<እእእሽ>> <<ሁሌም ሌቦች ብርጭቆዬን ይሰርቁብኛል ብላ ስለምትሰጋ ጨለማው ያስፈራት ነበር። ከዛ አንድ ቀን ምን ብታገኝ ጥሩ ነው?>> <<ምን?>> <<ሻማ! በጣም ደስ አላት። ሻማዋን አብርታ እያዬች ደስ አላት። ይቺ ሻማ እስካለች አልሰጋም ስትል አሰበች። ሻማዋ ግን እጠፋለሁ ብላ ትሰጋ ነበር። ንፋስ በመጣ ቁጥር ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ ይላል። ልዕልቷም ሻማዋን ከንፋስ ለማስጣል ብላ አንድ የሞኝ ውሳኔ ወሰነች!>> <<ምን አደረገች?>> <<በብርጭቆዋ ሸፈነቻት።>> <<ከዛስ?>> <<ከዛማ ሌባ ይገባል ብላ በር በሩን እያዬች ከኋላዋ ቃቃቃቃቃቃ የሚል ድምፅ ተሰማት። ደንግጣ ስትዞር የምትሳሳላት ብርጭቋዋ ናት። ንፋስ መቋቋም አቅቷት ልትጠፋ የነበረችው ሻማ በሙቀቷ ብርጭቆዋን ሰንጥቃባታለች። ልዕልቲቱ አዘነች። ውሀ አጣጯ ቢመጣም ውሀ መጠጫ እንደሌላት እያሰበች አለቀሰች! አለቀሰች!..>> እያለ የሚቀጥል ተረት! ታሪኩን ከወደዳችሁትና እንደዚ አይነት አጫጭር ታሪኮችን እንድንፅፍላችሁ ከፈለጋችሁ በLike ግለፁልን።😊👍👍
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
#ችግርህን_በየቀኑ_በአንድ_ፐርሰንት_አባብስ ዛሬ ላይ ጥቂት ገንዘብ መቆጠብ ብትችል አሁኑኑም ሚሊየነር አትሆንም፡፡ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ጂም ብትሰራ በአካል ቅርፅህ ላይ ምንም ለውጥ አታይም፡፡ ዛሬ ምሽት ፈረንሳይኛ ቋንቋን ለሶስት ሰዓታት ብታጠና የቋንቋው ተናጋሪ አትሆንም፡፡ ጥቃቅን ለውጦችን ለማምጣት እንሞክራለን፡፡ የለውጡን ውጤት ቶሎ ማየት ስለማንችል ግን ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለሳለን፡፡ መጥፎው ነገር ደግሞ ይህ የለውጡ ውጤት የሚታይበት ፍጥነት እጅግ ዘገምተኛ መሆን ለመጥፎ ልማዶች እንድንመቻች የሚያደርገን መሆኑ ነው፡፡ ዛሬ ምሽት ቤተሰቦችህን ተወት አድርገህ ስራ ላይ ብታሳልፍ ይረዱሃል፡፡ ሥራህን የምትጨርስበት ሰዓት ለነገ ብለህ ብታሳድረው ለዚህ የሚሆን ጊዜ “ነገ” ላይ አይጠፋም፡፡ በዚህ መንገድ አንዲትን ውሳኔ መተው ብዙም ከባድ ነገር አይደለም፡፡ በየቀኑ ችግሮቻችንን በ1% እያባባስን፣ መጥፎ ውሳኔዎችን እየደጋገምን፣ ትንንሽ ስህተቶችን እየሰራን እና ጥቃቅን ምክንያቶችን እያበጀን ከሄድን ግን ድምር ውጤታቸው እጅግ የገዘፈ እና የከፋ ይሆናል፡፡ ብዙውን ጊዜ በሕይወታችን ውስጥ ለትልቅ ችግር የሚዳርጉንም እዚህም እዚያም የምንሰራቸው ችግሮቻችንን በ1% የማባባስ ስራዎቻችን ድምር ውጤቶች ናቸው። #የልማድ_ኃይል_ATOMIC_HABITS መጽሐፍ * ቤተሰብ ይሁኑ Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/ Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#የለየልን_ደደብ_እንደሆንን_ይሰማናል! ብዙ ሰዎች መሆን አለብን ብለው ያሰቡትን ያህል ባለመሆናቸው ራሳቸውን ያለማቋረጥ ይቀጣሉ። ራሳቸውን በራሳቸው ተሳዳቢዎች ይሆናሉ፤ ሌሎች ሰዎችንም ተጠቅመው ራሳቸውንም ይበድላሉ። ነገር ግን ራሳችንን ከምንበድለው በላይ ማንም ሊበድለን አይችልም፡፡ ይህን እንድናደርግ የሚያደርገን፣ ተኮናኝ የሚያደርገን ውስጣዊ ዳኛችንና የእምነት ስርዓታችን ነው። ብዙ ሰዎች ባሎቻቸው፣ ሚስቶቻቸው፣ እናቶቻቸው ወይም አባቶቻቸው እንደበደሏቸው ሲናገሩ እንሰማለን፡፡ ነገር ግን ከዚህ በበለጠ ሁኔታ ራሳቸውን በራሳቸው እንደበደሉ አያውቁም። በራሳችን ላይ የምንፈርድበት መንገድ ከሁሉም ዳኝነት የከፋው ዳኝነት ነው። በሰዎች ፊት ስህተት በሰራን ቁጥር ስህተቱን ለመካድና ለመደበቅ እንሞክራለን፡፡ ነገር ግን ብቻችንን ስንሆን ተሸክመነው የምንዞረው ዳኛ ያበራየናል፤ የጥፋተኝነት ስሜቱም በጣም ጠንካራ ነው፡፡ ከዚያም የለየልን ደደብ፣ በጣም መጥፎ፣ ወይም ከናካቴው የማንረባ ፍጡር የሆንን ያህል ይሰማናል፡፡ ራሳችንን ከመበደል ለመውጣት ደግሞ ውስጣዊ ዳኛችንን ማስተካከል አለብን፡፡ ግን እንዴት? የሕይወት ፍልስፍና መጽሐፍ እንዴት እንደምንችል ያስተምረናል፡፡ #የሕይወት_ፍልስፍና መጽሐፍ * ቤተሰብ ይሁኑ Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/ Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#በውስጣችሁ_ያለው_በዓለም_ካለው_ይበልጣል፡፡ ከታዋቂ የግሪክ ገዳማት ከአንዱ አበምኔት ጋር አስደሳች ውይይት አድርጌ ነበር፡፡ እርሳቸውም ለህይወታቸው ጠንካራ ትርጉም የሰጠው “በውስጣችሁ ያለው በዓለም ካለው ይበልጣል፡፡” የሚለው የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅስ እንደሆነ ነገሩኝ፡፡ ቀጥሎም፣ “በማንነቴ ጥልቀት ውስጥ እግዚአብሔር በጥበቡ እና በኃይሉ እንደሚኖር መገንዘቤ ለእኔ እምነት እና ዋስትና ይሰጠኛል። ችግሬን እንዴት መፍታት እንደምችል ብርሃን ወይም ግንዛቤ ስጠይቅ አዲስ ግንዛቤ ወይም ሀሳብ በውስጤ ይፈነጥቃል፤ እናም በችግሩ ውስጥ እንኳን የእግዚአብሔር ብርሃን በአእምሮዬ ውስጥ ያለውን ጨለማ ሲያስወግድ እመለከታለሁ፡፡” ብለውኝ ነበር፡፡ እኝህ አባት የሕይወትን ምስጢር እና የሕይወትን የሀብት ምንጭ አግኝተውታል፡፡ ስለያቸውም፡- “እውነት ማለት የምናሰብው፣ በስሜታችን የምንዳስሰው፣ ምናብ እና እምነታችን እንጂ በገሀዳዊው ዓለም የምናየው ነገር አይደለም፡፡” ሲሉ ነግረውኝ ነበር፡፡ አበመኔቱ የተናገሩት ነገር ሁሉም የስነአእምሮ ተማሪዎች የሚያውቁት እውነታ ነበር፤ ይህም ማለቂያ የሌለው ጥበብና ሀብት በውስጣችን እንጂ ከእኛ ውጭ እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ እስቲ ዛሬ ሀብት ያለው አእምሮህ መጽሐፍ እንደሚለው በውስጤ ያለው በአለም ካለው ይበልጣል ስንል እንዋል። መልካም ቀን! #ሀብት_ያለው_አእምሮህ መጽሐፍ * ቤተሰብ ይሁኑ Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/ Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#የእኔ_አእምሮ_ውስጥ_ያለው_ሀብት በቅርቡ #ሀብት_ያለው_አእምሮህ የሚል አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ ማዋላችንን ምክንያት በማድረግ #አእምሯችን_ውስጥ_ያለውን_ሀብት መግለጽ የቻለ ይሸለማል፡፡ብለንም በፌስቡክ ገጻችን አወዳድረን ነበር፡፡ ከአንድ እስከ ሶስት የወጡትና የገንዘብና የመጽሐፍ ተሸላሚዎች መካከል 1ኛ የወጣው አእምሯችን ውስጥ ያለውን ሀብት የገለጸው እንደሚከተለው ሲሆን ደረጃውን ያገኘውም 83 ላይክ በማግኘት ነው። #የእኔ_አእምሮ_ውስጥ_ያለው_ሀብት ይለናል፡፡ *** ሀብት ማለት ገንዘብ፤ ቤት፤ ንብረት፤ መኪና...ብቻ አይደለም ለምሳሌ ጤና፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ ደስታ....ሀብቶች ናቸው፡፡ አንዱ ያለ አንዱ ትርጉም አይሰጡም እነዚን በህይወታችን ለማግኘት እነዚህን ወሳኝ ነገሮች ሚዛናዊ ማድረገ አለብን... 1, መንፈሳዊ ህይወት 2, ማህበራዊ ህይወት 3, ጤና 4, ስራ የእነዚህን ሚዛን ከጠበቅን ህይወታችን የተሻለ ይሆናል ። የኔ አእምሮ ውስጥ ያለው ሀብት ይሄ ሀሳብ ነው። *** አሸናፊ Natnael Nigussie #ሽልማት 700 ብር እና አንድ መጽሐፍ በዚሁ አጋጣሚ በፌስቡክ ገጻችን ሁሌም ስለምናወዳድር፣ ይከተሉን፣ ይወዳደሩ፣ ይሸለሙ!! #ሀብት_ያለው_አእምሮህ መጽሐፍ በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡ * ቤተሰብ ይሁኑ Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/ Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#አእምሮ_ማለት_እውቀት_ማለት_ነው በቅርቡ #ሀብት_ያለው_አእምሮህ የሚል አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ ማዋላችንን ምክንያት በማድረግ #አእምሯችን_ውስጥ_ያለውን_ሀብት መግለጽ የቻለ ይሸለማል፡፡ብለንም በፌስቡክ ገጻችን አወዳድረን ነበር፡፡ ከአንድ እስከ ሶስት የወጡትና የገንዘብና የመጽሐፍ ተሸላሚዎች መካከል 2ኛ የወጣው አእምሯችን ውስጥ ያለውን ሀብት የገለጸው እንደሚከተለው ሲሆን ደረጃውን ያገኘውም 75 ላይክ በማግኘት ነው። #አእምሮ_ማለት_እውቀት_ማለት_ነው ይለናል፡፡ *** #አእምሮ_ማለት የግዕዝ ቃል ሲሆን እውቀት ማለት ነው:: አእምሮአችን ውስጥ ያለው ሀብት የአውቀት ጥርቅም(ሀሳብ) ሲሆን በFormal ትምህርት ቤት ብቻ ሳይሆን በአካባቢያችን የምናገኘው አውቀትም ይኖራል:: እንደ ሰዉ አተገባበረር ይለያይ አንጂ ሁሉም ሰው የአእምሮ ሀብቱ እውቀቱ ነው፡፡ እውቀት የአእምሮአችን ሀብት ነው!!! *** አሸናፊ Astu Man #ሽልማት 350 ብር እና አንድ መጽሐፍ በዚሁ አጋጣሚ በፌስቡክ ገጻችን ሁሌም ስለምናወዳድር፣ ይከተሉን፣ ይወዳደሩ፣ ይሸለሙ!! #ሀብት_ያለው_አእምሮህ መጽሐፍ በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡ * ቤተሰብ ይሁኑ Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/ Telegram- https://t.me/teklu_tilahu
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.