cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

የእግዚአብሔር ህልውና

እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም የሚፈፅም የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ ሐዋ13÷22 የሞተላቸውን አስደስተው የሞቱ ምንኛ የታደሉ ናቸው፡

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
164
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

❝የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው #የኃጢአትም_ኃይል_ሕግ ነው።❞ — 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥56 "ፀጋን መስበክ ሀጢአትን ያበረታታል።"የምትሉ ይህንን ቃል አስተውሉ። ሀጢአት ጉልበት የሚያገኘው ሕግ ሲሰበክ እንጂ ፀጋ ሲበሰር አይደለም። በመሠረቱ ሀጢአት(የሥጋ ሥራ) ባለመበረታታት አይቆምም፣በመበረታታትም አይስፋፋም። የሀጢአት እውቀት አዕምሮ ላይ እስካለ ድረስ ሥጋ የአመፃ የጦር ዕቃ ሁኖ ማገልገሉንና ሀጢአትን(የሥጋ ሥራን) መግለጡ አይቀርም። እንግዲህ ይህ እንዳይሆን መፍትሄው፦ ነፍስን በእግዚአብሔር ቃል ዕውቀት በማደስ ሥጋን የጽድቅ የጦር ዕቃ ሆኖ እንዲያገለግል ማድረግ ነው። ❝ሕግ እስከ መጣ ድረስ ኃጢአት በዓለም ነበረና ነገር ግን ሕግ በሌለበት ጊዜ ኃጢአት አይቈጠርም።❞ — ሮሜ 5፥13
نمایش همه...
...መንፈሳዊ ጥንካሬ “በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥” — ኤፌሶን 3፥16-17 ------------------------------------------------------------ ✍ አንድ ቀን እንቁላል እና ድንች የፈላ ውሃ ውስጥ ይገባሉ። ከቆይታም በኋላ ሲወጡ የሚያስደንቅ ነገር ሆነ ፤ ድንቹ ከፈላ ውሀ ውስጥ ሲወጣ ጥንካሬውን ቀንሶና ለዞ ሲወጣ በተቃራኒው ደግሞ እንቁላሉ እጅጉን ጠንክሮ ከፈላው ውሃ ወጣ። አንድ ሰው ስጋዊ ጥንካሬን ለማግኘት ቀን ከሌት ስፓርት እንደሚሰራው እንዲሁ መንፈሳዊ ጥንካሬን ለማምጣት ብዙ ስራ ይጠበቅብናል። “ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥8 #ስጋዊ_ጥንካሬ_እንዳለ_ሁሉ_መንፈሳዊ_ጥንካሬም_እንዲሁ_አለ!! ሴጣን በጣም ትንሽ የሚባሉ ችግሮች ክርስቲያኖችን የሚጥልበት ዋናው ምክንያት መንፈሳዊ ጥንካሬ ላይ ትኩረት ባለመስጠታቸው ነው። መጠንከር ማለት ስንወለድ ያልነበረን እጅ ይኖረናል ማለት ሳይሆን ስንወለድ የተሰጠንን እጅ በልምምድና የተለያዩ ትናንሽ ነገሮችን በመያዝና በመሸከም ውስጥ የምንደርስበት ደረጃ ነው ፤ ለዚህም ነው ህፃን ልጆች ምንም እንኳ እንደ ማንኛውም ሰው እጅ እና አምስት ጣት ቢኖራቸውም እቃ ከሰጠናቸው ግን መሸከም ስለማይችሉ ያመልጣቸዋል ምክንያቱም የመሸከም አቅም የላቸውም። 💎 ክርስቲያንን ጠንካራ እንዲሆን ከሚረዱት ነገሮች መካከል በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኘውን ማንነት መረዳት በዋናነይ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው ሲሆን ሌላው ጥንካሬ የሚሰጠን ነገር መከራ ነው፡፡ የትኛውም መከራ ለእናንተ ወደሚቀጥለው ክብር መሻገሪያ ድልድይ ነው። “በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሰከረ፥ በምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር።” — 1ኛ ጴጥሮስ 1፥11 #መከራ_ለጊዜው_ያደክማል_የኃላ_ኃላግን_ጥንካሬ_ሆኖ_ይገለጣል። https://t.me/Glory_to_God_in_Ethiopia
نمایش همه...
የእግዚአብሔር ህልውና

እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም የሚፈፅም የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ ሐዋ13÷22 የሞተላቸውን አስደስተው የሞቱ ምንኛ የታደሉ ናቸው፡

❝አላቸውም፦ ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ።❞ — ማርቆስ 4፥24 ጌታ ያለ ምክንያት ይህንን አልተናገረም።አንድ ነገር ከመሰማት አልፎ ዐዕምሮ ላይ የመጫን እድል ካገኘ ዕምነት ይሆናልና ነው። ❝እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው።❞ — ሮሜ 10፥17 በመንፈሳዊ ዐለም እምነት ዋነኛ መሣሪያ ነው። በመንፈሳዊ ዐለም ያለ በረከት በምድር ላይ የሚገለጠውም ሆነ የሚገደበው በእምነት ነው። እግዚአብሔር በህይወታችን የሚሠራው እንደ እምነታችን መጠን እንጂ በችሎታው ልክ አይደለም። ❝እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን #ከምንለምነው ወይም #ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው።❞ — ኤፌሶን 3፥20 ልመናችን(ጥያቄአችን) በዕምነታችን ልክ ይገደባል፤እምነታችን ደግሞ በሕይወታችን የእግዚአብሔርን ሥራ ይገድባል። ❝በዚያም በጥቂቶች ድውዮች ላይ እጁን ጭኖ ከመፈወስ በቀር፥ ተአምር ሊያደርግ ምንም አልቻለም። ስለ አለማመናቸውም ተደነቀ። በመንደሮችም እያስተማረ ይዞር ነበር። ❞ — ማርቆስ 6፥5-6 እንግዲህ በወቅቱ ኢየሱስ መፈወስ አቅቶት ሳይሆን የሰዎች አለማመን እንዳይፈወሱ አድርጎአቸዋል። ዛሬም ከእግዚአብሔር ዘንድ የታቀደልንን ኑሮ በምድር በሙላት እንዳንኖር እምነታችን ገደብ ያደርግብናል። እግዚአብሔር በምድር ላይ ያሉትን መልካም የሆኑ ነገሮች ሁሉ የፈጠረው ለሰው እንጂ ለራሱ አይደለም።ዛሬ እየሆኑ ያሉትን መልካም ያልሆኑ ነገሮችን ተመልክተን ❝እግዚአብሔር ነው መዓት ያመጣ።❞ ማለት አንችልም ምክንያቱም “ ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤” — ገላትያ 6፥7 ሆኖ እንጂ እግዝአብሔር በሰው ልጆች ላይ መከራና ስቃይ የሚያመጣ ሁኖ አይደለም። ያንን ያስተማረን ሐይማኖት እንጂ ቃሉ አይደለም። ቃሉማ የሚለን 👉🏽❝ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።❞ — ኤርምያስ 29፥11 ስለዚህ ሐይማኖት ያስተጋባብንንና የሚያስተጋባብንን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ይሁንልን። ❝እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።❞ — ሮሜ 10፥17
نمایش همه...
❝የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው #የኃጢአትም_ኃይል_ሕግ ነው።❞ — 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥56 "ፀጋን መስበክ ሀጢአትን ያበረታታል።"የምትሉ ይህንን ቃል አስተውሉ። ሀጢአት ጉልበት የሚያገኘው ሕግ ሲሰበክ እንጂ ፀጋ ሲበሰር አይደለም። በመሠረቱ ሀጢአት(የሥጋ ሥራ) ባለመበረታታት አይቆምም፣በመበረታታትም አይስፋፋም። የሀጢአት እውቀት አዕምሮ ላይ እስካለ ድረስ ሥጋ የአመፃ የጦር ዕቃ ሁኖ ማገልገሉንና ሀጢአትን(የሥጋ ሥራን) መግለጡ አይቀርም። እንግዲህ ይህ እንዳይሆን መፍትሄው፦ ነፍስን በእግዚአብሔር ቃል ዕውቀት በማደስ ሥጋን የጽድቅ የጦር ዕቃ ሆኖ እንዲያገለግል ማድረግ ነው። ❝ሕግ እስከ መጣ ድረስ ኃጢአት በዓለም ነበረና ነገር ግን ሕግ በሌለበት ጊዜ ኃጢአት አይቈጠርም።❞ — ሮሜ 5፥13
نمایش همه...
ከአንደበታችን የሚወጡ ቃላቶች.... ✍ የምንኖረው የተናገርነውን እንደሆነ ስንቶቻችን እናውቃለን? ሕይወታችን በሙሉ የሚመስለው ንግግራችንን ነው፤ ውድቀት የምንናገር ከሆነ ስኬትን አንኖርም ፤ ፍርሃትን የምንናገር ከሆነ የድፍረት ሕይወት መኖር አንችልም ፤ በተገላቢጦሽ ደግሞ ስኬትን የምናወራ ከሆነ ሳይሳካልን አይቀርም ፤ መበርታትን ተናግረን መድከም አንችልም። “ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚወድዱአትም ፍሬዋን ይበላሉ።” — ምሳሌ 18፥21 ከአንደበታችን የሚወጡ ቃላት ሕይወታችን ምን እንደሚመስል አና ምን እየመሰለ እንደሚሄድ ያሳያሉ። ብዙዎቻችን ስለምንናገረው ነገር አስበን አናውቅም ፤ ምክንያቱም መናገር ለጊዜው ዋጋ የሚያስከፍል አይመስለንም። ብዙዎቻችን የማንችለው ስለማንችል ሳይሆን እንደማንችል ስለምናምንና በአንደበታችን ስለምንናገር ነው ፤ ስለዚህ ስንናገር አልችልም ፤ አይሆንም ፤ ይህ ነገር ከባድ ነው ፤ እጠላዋለሁ ፤ ደብሮኛል የሚሉ ቃላቶችን ማስወገድ አለብን። “አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል።” — ያዕቆብ 3፥6 #በጌታ_አምነን_የምንናገራቸው_ነገሮች_ግን_ሕይወታችንን_ጠፍረው_ይይዙታል!!! “ሰው ከአፉ ፍሬ መልካምን ይበላል፤ ”. ምሳሌ 13፥2 ነገሩ እንዲህ ከሆነ የምንናገረውን በሙሉ በቃሉ መሰረት እንናገር።
نمایش همه...
ራእይ ያላቸው ሰዎች የኖሩትን እንጂ ያልኖሩት ታሪክ አይነበብላቸውም! “ራእይ በሌለበት ሕዝብ መረን ይሆናል፤ ሕግን የሚጠብቅ ግን የተባረከ ነው።” — ምሳሌ 29፥18 የሕይወት ትርጉም የሚገኘው እና ከመረን ሕይወት የምንድነው ከፈጣሪያችን ጋር በመገናኘት እና እርሱ ለእኛ ያለውን ራእይ በመረዳት ብቻ ነው። ለዚህም ነው ራእይ ያላቸው ሰዎች ለሕይወታቸው ጣዕምና ትርጉም የሚያገኙት። ማወቅ ያለብን ነገር በምድር ላይ እኛ የምንሞላው ቦታ እንዳለ ነው። ብዙ ሰው ትርፍ የሚሆነው የራሱ ያልሆነ የሰው ቦታ ላይ ስለሚገኝ ነው። ለዛም ነው የእርሱ ያልሆነ የሰው ታሪክ እንዲነበብለት የሚሆነው። ትርጉም የሌለው ሕይወት ኖረን የእኛ ያልሆነ ታሪክ እንዳይነበብልን እግዚአብሔርን በጸሎት ቀርበን እንዲህ ብለን እንጠይቀው; ◇ የእኔ ቦታ የት ነው? ◇ ለእኔ ሕይወት ያለህ እቅድ ምንድን ነው? ◇ እኔ ፍጻሜ ያለው ልጅ እንደሆንኩ አውቃለው ◇ ሳትፈጥረኝ ታውቀኛለህ ለምን ፈጠርከኝ? እኛ የተፈጠርንበት አላማ በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ ሚስጥር ሆኖ ተቀምጧል ለዛም ነው እግዚአብሔር ጋር መጥተን የተፈጠርንበትን አላማ መጠየቀ ያለብን። እግዚአብሔር ደግሞ ይመልስልናል! ስሙ ይባረክ
نمایش همه...
ከጀግንነት መገለጫዎች አንዱ! “የምትሞትለት ዓላማ ከሌለህ የምትኖርለት ዓላማ የለህም ማለት ነው” ይሉናል አንዳንድ በነገሩ ያሰቡበት ሰዎች፡፡ ነገ ሕይወትን እስከመክፈል ድረስ ራሳችንን የሰጠንለት ዓላማ፣ ዛሬ ሕይወትን እንድናጣጥማት የማድረግ ጉልበት አለው፡፡ እንደየተሰማራንበት መስክ በርካታ የጀግንነት መገለጫዎች አሉ፡፡ ከሁሉም የጀግንነት መገለጫዎች አንዱና ለሕይወት ይህ ነው የማያባልን ጣእም የሚሰጣት ጀግንነት፣ ምንም ነገራችንን ከመክፈል የማንመለሰልትን ዓላማ መያዝና ለዚያ መኖር፣ ለዚያ ደግሞ መሞት ነው፡፡ ምንም ነገር ቢያስከፍለንም ከእኛ ለበለጠ ራእይና ዓላማ እስከመኖርና “ስንጀግን” ለዚያ ነገር ጊዜያችንን፣ ጉልበታችንን፣ ገንዘባችንን . . . አስፈላጊ ከሆነም ሕይወታችንን እንሰዋለን፡፡ ጊዜያችሁን እስከመሰዋት የምትኖሩለት ነገር ምንድን ነው? ሕወታችሁን እስከመሰዋት ድረስ የምትሩለትስ ነገር ምንድን ነው? ብዙ ሰዎች በየእለት ኑሯቸው ስልችት የሚላቸውና ባዶነት የሚሰማቸው ከዚህ አይነቱ “ጀግንነት” ውጪ ሕይወትን ለመኖር ስለሚሞክሩ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች በኑሯቸው ደስ የሚላቸውና ሙሉነት የሚሰማቸው ይህንን አይነት “ጀግንነት” ስላዳበሩና ጊዜያቸውንም ሆነ ሕይወታቸውን እስከመክፈል ድረስ የሚኖሩለትን ነገር ስላገኙት ነው፡፡ የጀግንነቶች ሁሉ ጀግንነት ምንም ነገር ለመክፈል የተዘጋጀንለትን ዓላማ ማግኘትና እስከሞት ድረስ ለዚያ መኖር!
نمایش همه...
ብዙ እየተሰማችሁ ነው/ብዙ እየደከማችሁ ነውን❓❓🤔 ይህንን ስሙ🎤📣📣……… 🏋‍♂🏋🏋‍♂ስፖርተኞችን ስንመለከት ስፖርት ሲሰሩ ህመም ሚሰማቸው ቦታ ለይ ቱንች ያወጣሉ💪 እንደውም ሚሰሩት ስፖርት ለ እጅ ቱንቻ ሆኖ እጃቸውን ካልተሰማቸው ልክ አይደለም የ ሰራውት ብለው ያስባሉ ✔️ልክ እንዲሁ፨፨፨፨👇👇👇 ☑️ያባተ ልጆች ስትፀልዩ ድካም እየተሰማችኁ ነው??? መፅሐፍ ቅዱስ ስታነቡ📖📖 ድካም ይሰማቹሃል??? 🔑🔑ይየ ሚያሳየው እናንተ ምትሄዱበት መንገድ ልክ እንዳልሆነ ሳይሆን ድካማችሁ ሊበረታ መሆኑንና ለ ፀሎት🧎🧎‍♀ እንደ ምትበረቱ ነው መፅሃፍ ቅዱስ ለ ማንበብ አቅም/ሃይል💥💥 እንደምታገኙ ነው 🚨ስለዚ መቼም ፀሎት እንዳታቆሙ ልታድጉበት📈📈 ልትበረቱበት ነው ድካም ሚሰማችሁ ልክ የሆነ መንገድ ስለ ምትሄዱ ነው መቼም እንዳታቆሙ ታድጉበታላችሁ ትበረታላችኁ መፀለያችኁን🤲 መፅሃፍ ቅዱስ📖 ማንበባችኁን ቀጥሉ የሆነ ጊዜ ራሳችኁን ከ ጌታ ጋር በጣም ትሩ ህብረት ያለው/ያለት ሆናችሁ #ታገኙታላችኁ🏆🏅 ተባረኩ
نمایش همه...