cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

👍ⓢⓜⓐⓡⓣ 🤛advertize👓 offcial page👍

✍ለማነኛውም ጥያቄ እና ትእዛዝ በሚቀጥለው ስልክ ይደውሉ 0911516527(በህሬ ለመስታወቅያ ሾል በሚቀጥለው አድራሻ [email protected] በመግባት የሚፈልጉትን ዲዛይን ይላኩ ✍more think ከፎቶ የምንሰራው ሸርዓዊ(ኢስላማዊ በሌላ አማርኛ ባለጉዳይ ብቻ የምናስተናግድ መሆኑን ስንገልፅ ከትልቅ አክብሮት ጋር ነው ✍ ከህትመት ማነኛውም አይነት ✍📈↗️አልከሶ ከተማ

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
131
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

የረቀቁ ሀሳቦች ⚜️ሕይወትን በተሻለ መንገድ ለመረዳት ወደ "3" ቦታዎች መሄድ አለብህ 1. መቃብር 2. ሆስፒታል 3. እስር ቤት "በመቃብር ስፍራ" ላይ ህይወት ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ትገነዘባለህ:: "በሆስፒታል" ውስጥ ከጤና በላይ ምንም ነገር እንደሌለ ትገነዘባለህ:: "እስር ቤት'' ሆነህ ነፃነት በጣም ውድ ነገር እንደሆነ ትገነዘባለህ። ⚜️ " የሆነን ሰው መሆን እየተመኘህ በሄድክ ቁጥር የዛ ሰው ኮፒ ስብእና እንጂ የራስህ የሆነ ማንነትና እውቀት እንዲሁም ተጽዕኖ አይኖርህም! ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ልትጥለው የሚገባው ነገር እንደ እገሌ መሆን እፈልጋለሁ ወይም እንደ እሱ እሆናለሁ የሚለውን አባዜ ነው ። አንተ ማንንም ለመምሰልም ሆነ ማንንም ለመሆን አልተፈጠርክም ። አንተ አንተ ነህ እገሌም እገሌ ነው ። " ⚜️"ሰው ላይ እንድትፈርድ የሚያስቸኩልህ ባህሪ የሚያሳየው ሁሉንም ሰው ከአንተ በታች ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት ነው። አንድ ሰው ልእለ ሰብነት (ታላቅነት) ላይ ለመድረስ ታላቅ ንቃት ይጠይቃል። ከውስጣችሁ ካለው ተራራ ጫፍ መውጣት ይጠበቅባችኋል። ይህ ደግሞ አስቸጋሪ ይመስላል።ስለዚህ ቀላሉና ርካሹ መንገዱ ራሳችሁን የበላይ ለማድረግ ከመጣር ይልቅ ....ምንም ድካም የማያስፈልገው ሌሎችን የበታች አርጎ መቁጠር ነው። ለዛ ነው ሰው ላይ ለመፍረድ የምትቸኩለው። ሌላው ላይ ለመፍረድ የምታደርገው ጥረት አንተ የተሻልክ እንደሆንክ ለማሳየት ያለህን ፍላጎት ያረጋግጣል። " ⚜️"በሁሉም ነገር አዲስ መንገድ ፈልጉ።በየዕለቱ አዲስ ነገር መፈለጋችሁን ስትቀጥሉ ህይወታችሁ ልብ አንጠልጣይ፣አስደናቂ ይሆናል። ህይወት አይሰለቻችሁም። አንድ ነገር ለማውቅ ሁልጊዜ ጉጉ ሁኑ።ሁልጊዜ ከማወቅ ከመመርመር ከማግኘት ፣ከመፈለግ ጫፍ ስትደርሱ ንቃታችሁ ይበልጡን ይጨምራል ። 👇👇👇👇
نمایش همه...
👉ታላቅ የምስራች ለፓስፖርት ፈላጊያን በሙሉ ✍️ እነሆ አዲስ አበባ ወይም እሩቅ መሄድ ቀረ አልያም ደሞ ከእንግልት ሊገላግሎት ብቅ ብሏል ባገርኛው 👉የፌደራል ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ባወጣው አዋጅ መሠረት የኢሚግሬሽን እና የዜግነት ጉዳይ መምሪያ በ2020 ጀምሮ በተከሰተው COVID 19 ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው መመሪያ መሰረት ፓስፖርት በየአቅጣጫችሁ ባለ ኢንተርኔት ቤት መመዝገብ እንደሚቻል መግለጫ ተሰጥቶን ነበር እናም ይህን በማሥመልከት ድርጅታችን ➛ስማርት ፎቶ እና ማተሚያ ቤት (ኃ.የተ.የግ.ማ) ከወሳኝ ኩነት ዋና መ/ቤት ባገኛው ፎርማት እና ፈቃድ መሠረት እነሆ ስራ ጀምረናል ይምጡ ይመዝገቡ ፓስፖርትዎትን ይያዙ ያለአላማ አየሰደዱ ከኣለስፈላጊ እንግልት እና ወጪ እራሶን ይጠብቁ *ፓስፖርት ለመመዝገብ ሲመጡ መያዝ የለቦትን መስፈርት በጥንቃቄ ይከታተሉ 👉የታደሰ መታወቂያ እና ጉርድ ፎቶ 👉የልደት መረጃ እና ከፖሊስ ድጋፍ ደብዳቤ 👉ለህፃናት እና ለተማሪዎች አገልግሎት ሲስተሙን አስካሚለቀቅልን ድረስ ከቻሉ መታገስ ወይም head office በኣካል በመቅረብ apllay ማድረግ የክፍያ ሁኔታ 👉 32 page ፓስፖርት 600 የኢትዮ ብር 👉64 page ፓስፖርት 2180 የኢትዮ ብር 📜ልብ ይበሉ ክፍያውን የሚፈፅሙት በባንክ ሲሆን ከተመዘገቡበት ቢሮ ማለትም የተመዘገቡበት ቁጥር ይዘው ወደ ንግድ ባንክ ሄደው ይከፍላሉ ➛smart digtal studio and advertising center /Alkeso አድራሻችን አልከሶ ንግድ ባንክ ፊት ለፊት ባለው ማስታወቂያ ቤት ስልካችን,,,09-11-51-65-27//09-15-66-71-51 ቴሌግራም ላይ ከፈለጉን @kumrel711 ብለው ይፈልጉን ✍️ምንግዜም ስራ ላይ ✍️ ለወዳጆ ዘመዶ ያጋሩ @smart711 እናመሰግናለን !!
نمایش همه...
➛የቀጠለ አዕምሮ ጥሩ ሎሌ ሲሆን፣ ግን ደግሞ አመለ ሸጋ ጌታ አይደለም አዕምሮህን በማይጠቅሙ ነገሮች ላይ እንዲያተኩር ካደረከው አላሰለጠንከውም ማለት ነው:: ዊንስተን ቸርችል "የታላቅነት ዋጋ በእያንዳንዱ አስተሳሰብህ ላይ ኃላፊነት መውሰድ ነው!!” ብሏል አስታውስ አዕምሮ ልክ እንደ ሌሎቹ የሰውነታችን ጡንቻዎች ነው::በአግባቡ ከተጠቀምክበት ይጠነክራል አልያም ይላሽቃል።” “ የእጅህ ጡንቻ እንዲጠነክር ከፈለግክ ልታለማምደው ይገባል፡፡ የእግርህን ጡንቻዎችም ልታጠነክራቸው ከፈለግክ አስቀድመህ ልታሰለጥናቸው ይገባል፡፡ አዕምሮህንም እንዲሁ እንዲሰራ እስከፈቀድክለት ድረስ፣ ተዓምራትን ይሰራል፡፡ እንከን የሌለው ጤና እና ንቃትን ይፈጥራል፡፡ በአግባቡ ከተንከባከብከው ተፈጥሯዊ ወደሆነው እውነተኛ ብቃቱ ይመለሳል፡፡ ሌላው ቀርቶ እውን እንዲሆንልህ የምትፈልገው ራዕይ እንኳን ተፈጻሚ እንድታደርገው ያግዝሃል። የሩቅ ምስራቅ የሲቫና ሊቃውንቶች አንዲት ልዩ አባባል አለቻቸው፡- "የህይወት ገደብ የአዕምሮ የፈጠራ ውጤት ነው ::” ይላሉ ✍️ሮቢን ሻርማ #behree ሌላውን ለማስተማር በቅንነት #ሼር አድርጉ 🤸‍♀️🤸‍♀️ just join and share your family @smart711
نمایش همه...
ትርጉም ያለው ህይወት መኖር "የህይወት ገደብ የአዕምሮ የፈጠራ ውጤት ነው።" ህይወትህን በሙሉነት ለመኖር አእምሮህን ከማይጠቅሙ ሀሳቦች ልታፀዳው ይገባል።በአእምሮህ አፀድ ውስጥ ልትተክለው ያሰብከውን ተክል መምረጥ አለብህ። በውበት ከተሸለመ አጸድህ አእምሮ ውስጥ በአረም እና በቁጡቋጦ ሲሞላ ማየት የለብህም። ብሎም ጠቃሚና የተጣራ መረጃ ብቻ እንዲገባ መቆጣጠር ይኖርብሃል። የማሰብ ችሎታህ የሚጎለብተው በልምምድ ነው። አብዛኛው ሰው የአዕምሮውን የተትረፈረፈ ጉልበት አያውቀውም፡፡በጣም አሳቢ የሚባለው ሰው እንኳን፤ የሚጠቀመው አንድ መቶኛውን የአዕምሮ አቅም ነው። አንድ ዓይነት ነገር ብቻ የሚያስቡ ሰዎች፤ በአሉታዊ የአዕምሮ ልማድ ውስጥ ይዘፈቃሉ፡፡ የአዕምሮህ ሙሉ አትኩሮት ሊሆን የሚገባው ህይወትህን የተሻለ ሊያደርግ በሚችል ነገር ላይ እንጂ በትላንትናው ላይ አይደለም:: ጥቂቶች ስለፍቅር ግንኙነታቸው መፍረስ አሊያም ስለሚገጥማቸው የገንዘብ ችግር ይጨነቃሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ መልካም ስላልነበረው የልጅነት ጊዜያቸው አሁን ላይ ቆመው ያስባሉ፡፡ እንዲሁም ሌሎቹ በማይጠቅማቸው ጥቃቅን ነገር ላይ በሀሳብ እየቆዘሙ ይናውዛሉ ፣ አልያም የሥራ አጋሮቻቸው የሚሰጣቸውን ትችት በማብሰልሰል አዕምሯቸው ይህንነ ነገር ብቻ እንዲያውጠነጥን ይፈቅዱለታል። በውስጣችን ያልተነካ ሀይል አለ። ግቦቻቸውን የሚቀዳጁት ሰዎች ከሌሎቹ ሊለዩ የሚችሉት አሊያም የበለጠ ደስተኛ የሚሆኑት ይህንኑ ሀይል አንጥረው በማወቅ መጠቀማቸው ነው። ለአንድ ታላቅ ዓላማ አሊያም ስላልተለመደ እቅድ ስታውጠነጥን ፣ አስተሳሰብ እስራቱንን ይሰብራል። አዕምሮ ከነበረበት ይልቃል። ንቃተ ህሊናህ በየአቅጣጫው ይንሰራፋል። ያኔ ራስን በአስደሳች ዓለም ውስጥ ታገኘዋለህ::
نمایش همه...
LIVING IN BALANCE... 🔆ህይወት ውስጥ ትልቁ ቁምነገር ትክክለኛውን መጠን ማግኘት ነው። መድሃኒት በትክክለኛው መጠን ፈውስ ነው ሲበዛ ግን መርዝ ነው ይገላል። ወይን በትክክለኛው መጠን ለልብ ደስታ ለመንፈስ ፍስሐ ነው ሲበዛ ግን ስካር ነው ያጠፋል። 💡በሕይወት ውስጥ ሁሉም ነገር እንዲህ ነው። ማንኛውም ነገር ቢሆን ከመጠን በላይ ሲሆን አጥፊ ነው። እና የሚሻለው የምትጠቀምበትን ያክል ብቻ እወቅ፡፡የሚያጠግብክን ያክል ብላ የሚያረካህን ብቻ ጠጣ ሁሉን ነገር ማጣት ሰቀቀን ቢሆንም ሁሉን ነገር ማግኘትም እዳ ይሆናል ፡፡ምንም አለማወቅ ባዶነት ቢሆንም ሁለን ማወቅ ደግሞ ሸክም ይሆናል፡፡ 🔆ሰውነት ምሥጢር ፣ ሰው መሆን ረቂቅ ነው፡፡ በመሸጥ ብቻ ነጋዴ አይኮንም፡፡ በመግዛትም ጭምር እንጂ ፡፡ በመቀበል ብቻ ባለጠጋ የሆነ የለም፡፡ መስጠትንም ጨምሮ እንጂ፡፡ መኖርን ምሉዕ የምናደርገው ሁለት ተቃራኒዎችን በሚዛን በመከወን ነው፡፡ እንባም ሳቅም፣ ደስታም ኀዘንም ፣ መስጠትም መቀበልም ፡፡ መሙላትም መጉደልም። ሲጠቃለል ፣ ሕይወት ኅብረ ቀለሟ ያማረ ቀስተ ደመና ነች @smart711🏃‍♂️🏃‍♂️🏃‍♂️
نمایش همه...
የመኖር ጥበብ!! 💚የመኖርን ጥበብ በእጅጉ የሚሻ አንድ ሰው ወደ አንድ ታላቅ ጠቢብ ዘንድ ይሄዳል። ግራ መጋባት የሚታይበት ይህ ሰው ጠቢቡ ጋር እንደ ደረሰ የጥያቄ መዕት ያወርድበታል። ጠቢቡም ሰው ሁሉንም ጥያቄ በጥሞና ይሰማ ነበር። " የመኖርን ጥበብ አውቅ ዘንድ ካንተ ዘንድ መጣው። ቢቻልህስ ንገረኝ።" አለው። 💛ጠቢቡም ሰው እንዲ ሲል መለሰለት። "በ አንድ ወቅት ሰው ሁሉ የሚገረምበት አንድ ትልቅ ከመስታወት የተሰራ ትልቅ ቤት ነበር። ሁሉም ጥበብን የሚሻ የሚሄድበትና ጥበብን የሚማርበት። እናልህ ሁለት ሰዎች ይሄን ሰምተው ወደዛ ቤት ይሄዳሉ። ሁለቱም እጅግ የተለያዩ ናቸው። አንዱ ደስተኛ ተጫዋች ቅለል ያለ ህይወት የሚመራ ሲሆን ሁለተኛው በአንፃሩ ንዴታምና ብስጩ፥ ህይወትንም መክበድ የሌለባትን ያህል አክብዶ የሚያይ ነበር። ❤️ወደ መስታወት ቤት ሲደርሱ ደስተኛው ሰው ቀድሞ ገባ። ወደ ቤቱም ሲገባ በጣም ተማረከበት። ፊታቸው እጅግ የበራ፥ ህይወትን በእጅጉ የሚያጣጥሙ አይላፍ ህዝብ ተመለከተ። ከበፊቱም በላይ እጅግ ተደስቶም ከመስታዎት ቤቱ ወጣ። ውጪ ቆሞ ላለው ለሌለኛው ሰውም ያየውን ነገረው። 💚እጅግ ብስጪ ንዴታሙ ሰውም ወደ መስታዎት ቤቱ ገባ። ያጋጠመውም ነገር ከበፊቱ እጅግ የተለየ ነበር። አእላፍ ደስታ የራቃቸውንም ሰዎች ተመለከተ። ቤቱን ከመውደድ ይልቅ ጥላቻ ሞላበት። እጅግ በተበሳጨ ቁጥር ቤቱ ውስጥ ያሉትም አእላፍ ሰዎች ብስጭታቸው ይጨምር ነበር። እሱ የሚያደርገው እያንዳንዱን ነገር እነርሱ በእጥፍ ይመልሱለት ነበር።" አለ ጠቢቡ ሰው። 💛ቀጥሎም "አየህ ሁለቱ ሰዎች ያዩት ነገር ሌላ ነገር ሳይሆን የራሳቸውን ምስል ነው። መስታወቱ የራሳቸውን ምስል መልሶ እያሳያቸው ነበር። እዚም ምድር ላይ የተለየ የመኖር ጥበብ የለም። አንተ የሆንከውን አከባቢህ ይሆንልሀል። ደስታን ከሰጠኸው እጥፍ አርጎ ይመልስልሃል። ፍቅር ከሰጠኸው አትርፍርፎ ላንተም ይሰጥሀል። ጥበቃ ካረክለት እርሱም መልሶ ይንከባከብሃል። ደግ ስትሆንለት ደግነት ታገኛለህ። ❤️ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንደሚባለው ሰው በ አሉታዊ ሀሳብ ተብትቦ ደግ ነገርን ከሰው ይጠብቃል። እየገደለ መኖርን ይፈልጋል። እያደማ መዳንን ይሽል። እየሱስ ይሄን ባንድ አርፍተ ነገር " የዘራኸውን ታጭዳለህ። " በማለት ገልፆታል። "ሊደረግልህ የምትፈልገውን አንተ ለሰው አድርግ ይላል።" ደግሞም እንዲህ ይባላል " አለም ላይ ማየት የምትፈልገውን ነገር አንተ ደግሞ እርሱን አርግ።" 💚አዎ ሰው ነገሮችን ሁለት ጎን እንዳላቸው ሳያቅ ይኖርና በመጨረሻም ይጎዳል። አሸናፊነትን እንጂ በሌላ ጎን ያለውን ሽንፈትን አይረዳውም። ህይወትና ሞት ፥ ደስታና ሀዘን ፤ መግደልና መሞት ፥ መውደድና ጥላቻ...... ወዘት የአንድ ነገር ሁለት ጎኖች ናቸው። አንዱን ብቻ ስንረዳ የእውነትን ግማሽ ተረዳን ማለት ነው። ሁለቱንም ስንረዳ ግን ሁሉም ይገባናል። ሀዘንን ለመሸሽ በሌሎች ሀዘንን አናመጣም። መውደድን ለማቆየት ሌሎችን አንጠላም። 💛ነገር ግን ተቃራኒ የሌለው አንድ ነገር አለ። እርሱም በ እ/ር ተመስሏል። ይህ ተቃራኒ የሌለው አቻም ያልተገኘለት ነገር ፍቅር ነው። ፍቅር ጊዜን ጠብቆ የማይከዳ የተፈጥሮ ሀብት ነው። ገፅ በረከት ስጣታም ነው። ፍቅር ስንሰጥ ሁሉንም በሁሉ ውስጥ እናገኛለን። ❤️ለዚህ የመኖር ጥበብ በጥቅሉ ያለ ቅድመ ሁኔታ ማፍቀር ነው። የሰው ልጅ ደጋግሞ ከመስማቱ ያልተገበረው ነገር ግን የሰለቸው ቃል። ሰው ተቃራኒ ያለውን ፍቅር ይዞ ይጎዳል። ፍቅር ይበለው እንጂ ይሄ በፍቅር ስም የሚነግድ ሌላ አይነት ስሜት ነው። ግዜን ጠብቆ ወደ ጥላቻ የሚሄድ ፍቅር ፍፁም ፍቅር አይባልም ። ፍፁሙን ፍቅር እሻ"!!! 🌹➛behredin jemal
نمایش همه...
አዋዋልህ ሕይወትህን ይወስናል!! አዋዋልህ የህይወትህ መገለጫ ነው፡፡ አንዲቷን ቀን የምታሳልፍበት መንገድ የዘመናት ሕይወትህን ይወስናል፡፡ ዛሬ የምትሠራው ነገር የወደፊት ሕይወትህን ይፈጥራል፡፡ የምትናገራቸው ቃላት፣ የምታፈልቀው ሐሳብ፣ የምትመገበው ምግብ እንዲሁም የምትወስዳቸው እርምጃዎች እጣ ፈንታህን ይወስናሉ፣ ማንነትህንና ሕይወትህን ይቀርፃሉ፡፡ ትናንሽ ውሳኔዎች በጊዜ ሂደት ግዙፍ ውጤት ያስከትላሉ። ‹‹ትርጉም አልባ» እለት የሚባል ነገር የለም፡፡ እያንዳንዳችን ለታላቅነት የሚያበቃ ጥሪ አለን፡፡ እያንዳንዳችን በውስጣችን ታላቅ ኃይል አለ፡፡ እያንዳንዳችን በዙሪያችን በሚገኙ ሰዎች፣ ሁናቴዎችና ነገሮች ላይ ተጽእኖ ማድረግ እንችላለን። በውስጣችን የሚገኘውን ይህን ኃይል ለማጎልበት ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ ይበልጥ ተግባራዊ ስናደርገው የበለጠ ይጎለብታል፤ ብርቱ ይሆናል። ይሄን ኃይል ይበልጥ ስትጠቀምበት ይበልጥ ልበ-ሙሉ፤ በራስህ የምትተማመን ትሆናለህ፡፡ ከእኛ መካከል ይበልጥ ስኬታማ የሆኑት ሰዎች ከተቀረነው የተለየ ስጦታ ያላቸው አይደሉም፡፡ ወደ ታላቁ ሕይወት ሲጓዙ በየእለቱ ጥቂት ደረጃዎችን በትክክለኛው አቅጣጫ የሚራመዱ ናቸው፡፡ . ቀናት ወደ ሳምንታት፣ ሳምንታት ወደ ወራት ይሸጋገራሉ. . . ሳይታወቃቸው የተለየ» ተብሎ ከሚታወቅ ሥፍራ ይደርሳሉ፡፡ ✍️በህረዲን ጀማል
نمایش همه...
ብረቷ ሴት!! የዛሬ 36 ዓመት ገደማ ከኮሌጅ ተመርቃ የ 22 ዓመት ልጅ እያለች "WJZ-TV" የሚባል የቴሌቪዥን ጣብያ ውስጥ በዜና አንባቢነት ተቀጥራ ትሰራ ነበር። በወቅቱ በዛ ቴሌቭዥን ጣብያ በእድሜ ትንሿ እና ብቸኛዋ ጥቁር አሜሪካዊ ዜና አንባቢ ነበረች። ነገር ግን "....ለቴሌቪዥን የሚሆን መልክ የለሽም! ብዙም አትመስጪም! ተመልካች ሳቢም አይደለሽም! ፀጉርሽ ሉጫ አይደለም! ብቃትሽም ቢሆን እምብዛም ነው! በተደጋጋሚ ዜና ስታነቢ ቃላቶችን በተሳሳተ መንገድ ስትጠሪ ታዝበናል!...." ብለው የቴሌቪዥን ጣብያው አመራሮች በመጀመርያ ከስራ ዝቅ (Demote) እንድትደረግ ያደርጉና ከዛም ከስራ ገበታዋ ያባርሯታል። በሚገባ ውሃ፣ መብራት እና መፀዳጃ ቤት እንኳን የሌለው ቤት ውስጥ ያደገችው፣ ነጮችን በቤት ሰራተኝነት ከሚያገለግሉት አያቷ ጋር ልጅነቷን ያሳለፈችው፣ እጅግ በጣም ስኬታማ ከሆነች የቤት ሰራተኛ (Maid) ነው የምትሆነው ተብሎ በቤተሰቦቿ የተተነበየላት፣ በገዛ አጎቷ እና በዘመዶቿ ወዳጆች አካላዊ እና ፆታዊ ጥቃቶች የደረሰባት፣ ገና በ 9 ዓመቷ በአሰቃቂ ሁኔታ የተደፈረችው፣ ድጋሚ በ 14 ዓመቷ ተደፍራ፣ አርግዛ ከዛም ልጇ "premature" ስለነበረ የሞተባት፣ በግፍ አትችይም ተብላ ከቴሌቪዥን ዜና አንባቢነት የተባረረችው "Oprah Winfrey" ዛሬ ላይ "የቴሌቪዥን ቶክ ሾዋ ንግስት(Queen of television talk shows)" በሚል ቅፅል ስም ነው የምትጠራው አባዬ! የሷን ያህል በቲቪ "Talk show" ዘርፍ ስኬታማ የሆነ ማንም ሰው የለም። ለወደፊትም ይኖራል ማለት ከባድ ነው! ምክንያቱም "ሚልየነር" ሳይሆን "ቢልየነር" ሆናበታለች! ሴትየዋ 2.7 ቢልዮን ዶላር ብቻዋን ታወጣለች! አሜሪካ ብትሄድ ብቸኛዋ ጥቁር ሴት ቢልዮነር እሷ ናት። በ "University of Pennsylvania" "History 298: Oprah Winfrey, the Tycoon" የሚባል ኮርስ እንደሚሰጥ ታውቃለህ አባዬ? ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች "ኦፕራ እንዴት ሃብታም ልትሆን ቻለች?" የሚለውን ይመረምራሉ ስልህ!😀 በነገራችን ላይ በጣም የምትታወቅበት "The Oprah Winfrey Show" ለ 25 ዓመታት ከ "September 8, 1986" እስከ "May 25, 2011" የተላለፈ ሲሆን በአሜርካ የቴሌቪዥን ታሪክ ትልቅ የተመልካች "rating" ያለው እንደሱ የለም! "Oprah" የመጀመርያዋ የራሷ ሾው አዘጋጅም ፕሮዲውሰርም መሆን የቻለች ተዓምረኛ ሴት ናት። ዛሬ ላይ በተለያዩ የቴሌቪዥን ጣብያዎች ላይ የምታያቸው የ "Talk show" ፕሮግራሞች የተገለበጡት ከሷ እና ከ "David Letterman" ነው! ሁሉም ማለት በሚቻል ደረጃ! ለ 25 ዓመታት የተላለፈው "The Oprah Winfrey Show" "4561" ክፍሎች (Episodes) አሉት! Who does that?😳 እነዚህን ክፍሎች አውርደህ በቀን እንኳን አንድ ክፍል ብታይ በ 12 አመት ነው የምትጨርሰው! አባዬ እንዳትሞክረው!😀 "Oprah Winfrey" ድንቅ፣ ጠንካራ፣ ብርቱ፣ ዐርዓያ፣ ተምሳሌት፣ ጀግና፣ ሃብታም እና ለብዙ ዜጎች ስራ ፈጣሪ በመሆንዋ በ 2013 የሃገሪቷን ከፍተኛ የክብር ሽልማት(Presidential Medal of Freedom) በወቅቱ የሃገሪቷ ፕሬዝዳንት ከነበሩት "Barack Obama" የተቀበለች ሴት ናት። በነገራችን ላይ ምን ያህል ተፅህኖ ፈጣሪ እንደሆነች የምታውቀው በ 2008 የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ 1 ሚልዮን የሚሆኑ መራጮች ድምፃቸውን ለ "Barack Obama" እንዲሰጡ ያደረገች ሰው መሆንዋን ስታውቅ ነው። በመጨረሻም አንድ ገጠመኟን ላጋራችሁ እና ልውጣ! "Oprah Winfrey" እጅግ በጣም ሃብታም ከሆነች በኃላ በአንድ አጋጣሚ ወደ "Switzerland" ታቀናና ውድ ውድ የቅንጦት ቦርሳዎች የሚሸጡበት ሱቅ ውስጥ ትገባለች። ከዛም ቦርሳዎቹን ስትመለከት አንድ የተሰቀለ ቦርሳ ቀልቧን ይስበዋል። በወቅቱ ሱቅ ውስጥ ያለችውን ሻጭ "...ያንን ቦርሳ አሳይኝማ!...." ስትል ትጠይቃታለች። ልጅቷም "...አንድ አሮጊት ሴት ሲጀመር ተሳስታ ይሆናል እንጂ እንደዚህ አይነት ሱቅ ውስጥ ልትገባ አትችልም! በዛ ላይ ጥቁር ናት! አሰብኩት እኮ አንዲት ጥቁር ሴት መሰረታዊ ፍላጎቷን አሟልታ የ 38 ሺህ ይሮ ቦርሳ ስትገዛ?!" ትልና "...ይቅርታ እሱ ይወደድብሻል !...ሌላ ርካሽ ቦርሳዎች አዛ ጋር አሉልሽ እነሱን ማየት ትችያለች!..." ትላታለች!😳 አባዬ! አይደለም ቦርሳውን የቦርሳውን አምራች ኩባንያ እንደ ቀልድ መዥለጥ አድርጋ መግዛት የምትችለው "Oprah" ዘረኝነትን ሚልየነር ወይም ቢልየነር ስለሆንክ/ስለሆንሽ የሚጠፋ ነገር ሳይሆን ለረጅም ግዜያት የሰዎች አመለካከት ላይ በመስራትን የሚጠፋ ነው ትላለች! "....Surround yourself with only people who are going to lift you higher!..." ➛𝔀𝓻𝓲𝓽𝓽𝓮𝓷 𝓫𝔂 𝓫𝓮𝓱𝓻𝓮𝓭𝓲𝓷 𝓳𝓮𝓷𝓪𝓵 🙏መልካም ምሽት🙏
نمایش همه...
ከታላላቅ ሰዎች ድንቅ አባባሎች ➛አዘጋጅ smart ህትመት "በምስጋና የተከፈተ ዘመን አስደሳች ነው፤ በፀሎት የተከፈተ ቀን መልካም ነው፤ በእምነት የሆነ ኑሮ ረፍት ነው፤ በይቅርታ የሆነ ጉዋደኝነት ዘላቂ ነው፤" ✍️አቡነ ሺኖዳ "ህልምና ምኞት በሌላቸው ሰዎች መሃል ታላቅ ከመሆን ይልቅ፣ህልምና ምኞት ባላቸው ሰዎች መሀል ደካማ መሆንን እመርጣለሁ፡፡” ✍ካህሊል ጅብራን “በሕይወት ውስጥ የተለመዱ ነገሮችን ባልተለመደ መንገድ ስታከናውን የዓለምን ቀልብ ትቆጣጠራለህ፡፡” ✍ ጆርጅ ዋሺንግተን "መጠጥ ቤቶች እብደት በጠርሙስ የሚሸጥባቸው ቦታዎች ናቸው" ✍️ሶቅራጥስ በገንዘብህ የጥቅም ጓደኞችን ልታፈራ ትችላለህ በውበትህ የስሜት ጓደኞች ልታፈራ ትችላለህ በእምነትህና በስነምግባርህ ግን.. የህይወት ጓደኞችን ታፈራለህ። ✍️unknown "ሁላችንም የሰራናቸውን ስህተቶች ለምን እንደፈፀምናቸው በቂ ምክንያት ለመስጠት እና ለማስረዳት የምንጠቀምበት ሀይል፣ትክክለኛ ነገሮችን ለመስራት ከምናውለው መብለጡ አስገራሚ ነው፡፡" ✍️ካህሊል ጂብራን "መፍራት ያለብህ ቀስ ብለህ ማደግህን ሳይሆን ከአለህበት ቁመህ እንዳትቀር ነዉ፡፡ተራራን ከቦታ ወደቦታ የሚያንቀሳቅሰዉ ሰዉ ትንንሽ ድንጋዮችን ያለመታከት የሚያጓጉዝ ሰዉ ነዉ፡፡" ✍️ቻይናውያን Join: ➛written by behredin jemal
نمایش همه...
አስሩ የስኬት መርሆች ... አስሩ የስኬት መርሆች በአለማችን ላይ ስለስኬት ከተጻፉ መጻሕፍት ውስጥ ቁጥር አንድ እንደሆነ የሚነገርለት የ “Thinkand Grow rich” ደራሲ ናፖሊዮን ሂል፤ ምንም እንኳን የምንፈልጋቸው ነገሮች ቢለያዩም ሁላችንንም ለስኬት የሚያበቁ ድንቅ መመሪያዮችን በመጽሃፉ አስፍሯል። : ☞እናም እኛንም በመረጥነው የህይወት ጉዞ ላይ ከረዳን ብዬ አስሮቹን የስኬት መርህዎች ኸርል ናይቲንጌል ካሰናዳው ላይ እንዲህ አቀናብሬ አቅርቤያቸዋለው። ~ 1."ፍላጎት(Desire)!" : ☞የመጀመሪያው ደረጃ ፍላጎት ነው። ከልብ የመነጨ ፍላጎት፤ፍላጎታችንን እንደ ዘር ልናየው እንችላለን። ፍሬ እንደሚያፈራ አምነን የምንዘራው ዘር። ዛሬ ዘርተነው ዛሬውኑ ፍሬ የሚሰጠን ተክል የለም። : ☞ፍላጎታችንም ልክ እንደ በቆሎ ወይም ማንኛውም ዘር ዛሬ ተዘርቶ በቂ ውሃ፤ በቂ ጸሃይ፤ በቂ እንክብካቤ ፤ካገኘ በኋላ በግዜው የሚያሽት ነው። : ☞የምንፈልገውን ነገር ጥርት ባለ መልኩ ማወቁ ይጠቅመናል። : ☞ለመረጥነው ነገር ምን ያህል ፍላጎት እንዳለን ለማወቅ የምናደርጋቸውን ነገሮች መቃኘት ያስፈልገናል። : ☞ከምንም በላይ በውስጣችን ያለው የትዕግስት መጠን ፍላጎታችን ምን ያህል እንደሆነ ያስረዳናል። : ❀ለምሳሌ ሰዓሊነት ፍላጎቱ የሆነ ሰው ባይከፈለው እንኳን ስዕል መሳሉን አያቆምም። : ☞አላማ ብለን ለመረጥነው ነገር በቀላሉ ሊገደብ የማይችል ፍላጎት ሊኖረን ይገባል። : ☞ጥልቅ ፍላጎት ማለት ወደ ኋላ እንዳናፈገፍግ የመመለሻውን ድልድይ እንደማቃጠል ያህል ነው። ~ 2."እምነት(Faith)!" : ☞እምነት አላማችን የሚገነባበት መሰረት ነው። የምንፈልገው ነገር ምንም ይሁን ምን እምነት ከሌለን ነዳጅ የሌለው መኪናን ለመንዳት እንደመሞከር ይሆንብናል። : ☞ደግነቱ እምነት በመጀመሪያ ባይኖረንም፤ በሂደት ልንገነባው የምንችለው ጥበብ ነው። : ☞ለአይምሮዋችን ቀና የሆኑ ነገሮችን በመመገብ እምነትን በሂደት ማዳበር ይቻላል። : ☞የምንፈልገውን ነገር ለማግኘት እምነት እጅግ ወሳኝነገር መሆኑን መዘንጋት የለብንም። : ☞ማርቲን ሉተር ኪንግ ስለ እምነት ደስ የሚል አባባል አለው ” እምነት ማለት ሙሉውን ደረጃ እስከየት እንደሚደርሰን ባናውቅም እንኳን የመጀመሪያውን ደረጃ መውጣት ነው” ይላል። ~ 3."እራስን ማሳመን-Auto Suggestion (አውቶ ሰጀሽን)!" : ☞አይምሮዋችን እውነት ብሎ የሚቀበለው ነገር ደግመን ደጋግመን የምንመግበውን ነው። : ☞እዚህ ላይ ይህንን በደንብ የሚያስረዳ አንድ ታሪክ ትዝ አለኝ። : # ታሪኩ እንዲህ ነው:- : <ሁለት ውሾች የነበሩት አንድ ሰው ነበር።አዘውትሮ እኒህን ውሾች አደባባይ እየወሰደ እንዲደባደቡ ያደርግ ነበር። ታዲያ ተመልካቾቹ የትኛው ውሻ በእለቱ እንደሚያሸንፍ ሲጠይቁት “በደንብ የምመግበው ውሻ ነው” ሲል መለሰላቸው። >> : ☞ሁላችንም ውስጥ ሁለት ዉሾች አሉ:- : ✔ የመልካም እና የክፋት፤ : ✔ የልማት እና የጥፋት፤ : ✔ የእውቀት እና የድንቁርና፤ : ✔ የውድቀት እና የድል ውሾች። : ✔ የበላይ ሆኖ የሚመራን ውሻ ዘወትር የምንመግበው ነው። : ☞ለዚህ ነው ናፖሊዮን ሂል “አውቶ ሰጀሽን”ወይም ለራስ መልካም ነገሮችን ደጋግሞ በመንገር አይምሮዋችንን ወደፈለግነው መንገድ መምራት እንደምንችል የሚነግረን።መንገር ብቻም ሳይሆን የሚያሳስበን! ~ 4."በአንድ ነገር ላይ እራስን የተካኑ ማድረግ(ስፔሻላይዝድ ኖውሌጅ)!" : <“Mastermind group- associate with men who know what you want to specialize in” ልንሰማራበት በመረጥነው ወይም ፍላጎት ባለን ሙያ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን መተዋወቁ እና ቅርርብ መፍጠሩ ወሳኝ ነገር ነው።> : ጊዜያችንን የምናሳልፈው ከነማን ጋር ነው? : የምናውቃቸው ሰዎች ወይም ጓደኞቻችን ለምንፈልገው ሙያ የሚያግዙን ናቸው? : ☞ለምሳሌ፦ ፡ ✔ ፕሮፌሰር ለመሆን ፍላጎት ያለው ሰው በተቻለው መጠን ዩንቨርሲቲ አካባቢ ካሉ ሰዎች ጋር ግንኙነቱን ቢያዳብር ይጠቅመዋል። : ✔ ተዋናይ መሆን የሚመኝ ሰው እራሱን ከቲያትር መድረክ አካባቢ ማራቅ የለበትም። : ☞ሁላችንም የምንማረው ቀድመውን ካወቁት ነውና፤ የምንፈልገውን ነገር በቅጡ የሚያውቁ ሰዎችን ማወቁ ይጠቅመናል 5."ነገሮችን በህሊናችን መሳል!" : ☞“Imagination- It’s the workshop, the impulse. men can create what he can imagine. what the mind conceives it achieves”. ሁሉም ነገር ሃሳብ ነበር። ምንም ነገር እውን ሆኖ ከማየታችን በፊት በአንድ ሰው አይምሮ ውስጥ የተጠነሰሰ ሃሳብ ነበር። : ☞የምንፈልገውን ነገር እውን ሆኖ ከማየታችን በፊት በህሊናችን መሳል ትልቁ የስኬት ሚስጥር እንደሆነ ብዙዎች የተስማሙበት ነው። : ☞አላማችን ቁልጭ ብሉ በህሊናችን ከታይን ለጉዞዋችን ትልቅ ጉልበት አገኘን ማለት ነው። ምክንያቱም የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እንደሚሳካ አይምሮዋችን እየነገረን ነው። ~ 6."እቅድ ማውጣት-Organized planning!" : ☞እቅድ ማውጣት ጊዜን በአግባቡ እንድንጠቀም ከማድረጉም በላይ፤ በአንድ ጊዜ አንድ ደረጃ እየወጣን ጉዞዋችን አድካሚ እንዳይሆን ያደርግልናል። ፡ ☞እቅድ ስናውጣ ነገሮች ሳይደራረቡብን ቀስ በቀስ ወደ ግባችን እንደርሳለን። ፡ ☞እቅድ ስናወጣ ግን እራሳችንን በሚያጨናንቅ እና ካልፈጸምነው የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማን በሚያደርግ ሁኔታ ሳይሆን፤ ከጊዜያችን ፤ ከባህሪያችን እንዲሁም ከማንነታችን ጋር የሚስማማ እቅድ ነው ማውጣት አለብን። ምክንያቱም ሌላው ያቀደበት መንገድ ለኛ ላይስማማ እና ከግባችን ላያደርሰን ስለሚችል። ~ 7."ውሳኔ-Decision!" : ☞“lack of decision is the top reason for failing. if you make a decision its worth sticking toit. don’t let others opinion to sway you” .የሰው ልጅ ውድቀት አንደኛው መንስዔ የውሳኔ ማጣት ነው። አንድ ሰው ምንም ያህል እምቅ እውቀት ቢኖረው፤ ምንም ይህል የሚያስደንቅ ሃሳቦችን ማመንጨት ቢችልም ውሳኔ መወሰን ካልቻለ ግን አቅሙ ሁሉ ከውስጡ አይወጣም። ፡ ☞ውሳኔ በማጣት የተነሳ ብዙ ሙዚቃዎች ሳይሰሙ፤ ብዙ መጽሐፎች ሳይጻፉ፤ ብዙ ግኝቶች ሳይገኙ፤ ወደ መቃብር ይወርዳሉ። ፡ ☞በሁላችንም ውስጥ ለኛ ብቻ የተሰጠ ስጦታ አለ፤ ይህን ስጦታ ግን አውጠን ሌሎች እንዲያዩት ማድረግ የምንችለው ውሳኔ መወሰን ስንችል ብቻ ነው። ፡ ☞የምንወስነው ምንድን ነው ካላችሁ፤ መልሱ የምንወስነው መሆን የምንፈልገውን ነው። ~ 8."ጽናት-(Persistence)!" : ☞“the power of will. This quality distinguishes the success from the failure. it’s a state of mind and can be cultivated”. ውሳኔ ብቻውን አቅም የለውም። ውሳኔያችን ባህሩን አቋርጦ ከአላማችን ዳርቻ እንዲደርስ የሚያደርገው ሃይል ጽናት ነው። ብዙዎⶭችን የተለያዩ ውሳኔዎችን እዚህና እዚህ እንወስናለን ነገር ግን ጽናት ኖሮን አንገፋበትም። : ☞ለዚህ ነው ናፖሊዮን ሂል የወድቀት እና የስኬት ዋናው መለያ ጽናት ነው ያለው። : ✔ለምሳሌ ከመጠጥ ሱስ መላቀቅ የሚፈልግ ሰው መቶ ጊዜ ለማቆም ቢወስንም ከውሳኔው ጋር ጽናት ካልተደመረበት በቀር ውሳኔው ብቻውን ምንምዋጋ የለውም። : ☞ስለዚህ በውስጣችን ያለውን የጽናት መጠን መፈተሹ እጅግ ወሳኝ
نمایش همه...