cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

12+1th

🅰👉 @ethio_ake

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
198
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

#MoE #ይፋዊ የትምህርት ሚኒስቴር የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን ጊዜ #ይፋ አድርጓል። ሚኒስቴሩ ፤ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 30/2015 ዓ.ም ድረስ #በመንግስት_ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል ብሏል። ዩኒቨርሲቲዎችም ያላቸውን ስራ በማጠናቀቅ ከሐምሌ15/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
#MoE #ይፋዊ ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርሲቲ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከሐምሌ 03/2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ #በይፋ አሳውቋል። ሚኒስቴሩ የዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ይሰጣል ብሏል። የ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃን በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ፈተናውን እንደሚወስዱም ገልጿል። በ2014 ዓ.ም የህግ መውጫ ፈተና ተፈትነው ማለፊያ ነጥብ ያላስመዘገቡ ተማሪዎችም በዚሁ ጊዜ ፈተናውን የመንግስት ዩኒቨርሲቲ የመፈተኛ ማዕከላት ውስጥ መውሰድ ይችላሉ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተናን ለመሥጠት የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያደርግ መቆየቱ አስታውሷል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
የ6ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና " ከ75 ሺ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎችን የሚኒስትሪ ፈተና ለማስፈተን ዝግጅት እየተደረገ ነው " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠውን የ6ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ተማሪዎችን ለማስፈተን የዝግጅት ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋቃ። የቢሮው የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የሠጡት ቃል ፦ - በአዲስ አበባ ከተማ በግል እና በመንግሥት ትምህርት ቤቶች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙ ከ75 ሺህ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማስፈተን ዝግጅት እየተደረገ ነው። - ከቢሮ እስከ ትምህርት ቤቶች ድረስ ተማሪዎቹን ለፈተና የማዘጋጀት ሥራ እየተሠራ ይገኛል። - ተማሪዎች የሚኒስትሪ ፈተና ከመፈተናቸው አስቀድሞ የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ ሞዴል ፈተናዎችን በማዘጋጀት በወሩ እንዲወስዱ ተደርጓል። ለፈተናው የተለያዩ አጋዥ መጽሐፍትንም አንብበው እንዲዘጋጁ እና እንዲፈተኑ እየተደረገ ነው። - በአማርኛ ቋንቋ የሚፈተኑ አራት እንዲሁም በአፋን ኦሮሞ የሚፈተኑ አምስት የትምህርት ዓይነት ፈተናዎች የሚወስዱ ይሆናል። በዚህ መሠረትም ፦ 👉 የሒሳብ፣ 👉 የአካባቢ ሳይንስ፣ 👉 አማርኛ፣ 👉 አፋን ኦሮሞ እና እንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነቶች ይሰጣሉ። - ምዝገባው የሚካሄደው በኦንላይን ሲሆን የተመዘገቡ ተማሪዎች የተመዘገቡበትን የስም እና ዕድሜ ስህተት እንዳይኖር ማረጋገጥ እና ማስተካከል ይችላሉ። - በየክላስተሩ ላሉ ትምህርት ቤቶች ወጥ በሆነ መልኩ ስልጠና በመስጠት ትምህርት ቤቶች ራሳቸው ፈተናዎችን እንዲያወጡ እና እንዲፈተኑ ይደርጋል። - በአዲሱ ሥርዓት ትምህርት በየምዕራፉ ማጠናቀቂያ ላይ ለተማሪዎች ፈተና ይሰጣል። ለዚህም አንደኛ ምዕራፍ የሚባለው ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል ያለው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ሲሆን ሁለተኛ ምዕራፍ የሚባለው ከሰባት እስከ ስምንተኛ ክፍል ነው። - የመጀመሪያ ምዕራፍ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚያጠናቅቁት ስድስተኛ ክፍል ላይ ስለሆነ የሚኒስትሪ ፈተናው ተማሪዎች ከታች ጀምረው ራሳቸውን እያነጹ እንዲመጡ የሚያደርግ ነው። የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ አንጻር ከፍተኛ ጥቅም አለው። - የመማሪያ መጽሐፍት በሚፈለገው ልክ ሀገር ውስጥ አለመገኘት እና በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ከውጭ የሚመጡ መጽሐፍት የመዘግየት ሁኔታ አለ። - የሚኒስትሪ ፈተና የሚሰጥበት ቀናት የሚወሰነው በአገር አቀፍ ደረጃ ቢሆንም እንደ ቢሮ #ከሰኔ አጋማሽ በኋላ ለመስጠት ዝግጁ ነን። #ኢፕድ
نمایش همه...
#Update #UAE በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ሙሉ ስኮላርሺፕ መስጠቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መናገራቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወስደው ከግማሽ በላይ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች ውስጥ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች እውቅና በሰጡበት ወቅት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተማሪዎቹ " እንኳን ደስ ያላችሁ " ካሉ በኋላ የተሰጣቸውን ፈተና በአግባቡ መስራት በመቻላቸው " ኢትዮጵያን የሚያግዙ 273 ተማሪዎች ተገኝተዋል በዚህም ደስታ ይሰማናል" ብለዋል፡፡ ተማሪዎቹ እጅግ ዘመናዊ በሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉና ለኢትዮጵያ እና አፍሪካ የሚደርሱ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ተማሪዎቹ በርትተው ተምረው ሀገራቸውን ሳይረሱ የሚጠቅሙ እንዲሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል። ዶ/ር ዐቢይ ሁሉም ተማሪ ጥበብን እንዲሻ እና ሀገሩን ለመለወጥ እንዲሰራ ጠይቀዋል፤ በተለይ " ለእውነት የቆመ ተማሪ ነገ ሃገሩን ይለውጣል፤ እናንተ የላቀ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎችም እውነትን የምትሹ መሆን አለባችሁ እንደዛ ሲሆን ደግሞ ሀገርን የምትገነቡ ትሆናላችሁ " ብለዋል። #ኤፍቢሲ
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#AAU አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን 5 ሺህ 100 አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ መቀበል ጀምሯል፡፡ ዩኒቨርሲተው በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአገር አቀፍ ደረጃ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ 5 ሺህ 100 ተማሪዎችን ከዛሬ የካቲት 15/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይቀበላል፡፡ ከአዲስ ገቢ ተማሪዎቹ መካከል 3 ሺህ 51 በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተመደቡ መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ዲን ሽብሩ ተመስገን (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን በአገር አቀፍ ደረጃ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር በ11 ዩኒቨርሲቲዎች መመደባቸው ይታወቃል፡፡
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
የእጩ ፍሬሽማን ተማሪዎች ወይም የአቅም ማሻሻያ(Remedial) ፕሮግራም ትምህርት የተማሪዎች ምደባ በዚህ ሳምንት ምናልባት ነገ ወይም ከነገ ወዲያ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። ፨ትክክለኛውን ቀን አላሳወቀም ▬▬▬▬▬▬▬▬
نمایش همه...
#Update ለ 2015 የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች እስካሁን ጥሪ ያደረጉ ዩኒቨርሲቲዎች 🔭 ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ - የካቲት 13 - 14. 🔭 ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ - የካቲት 15 - 16. 🔭 ድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ - የካቲት 20-21. 🔭 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ - የካቲት 15 - 16 🔭 ባህር ዳር ዩንቨርስቲ - የካቲት 20 - 22 🔭  ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ Online ምዝገባ የካቲት 20-26. (  የመግቢያ ቀንየካቲት 27-28 ) 🔭 ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ወደ ግቢ መግቢያ ቀን የካቲት 20/2015 እና 21 ▬▬▬▬▬▬▬▬
نمایش همه...
የካቲት 11 ቀን 2015   ማስታወቂያ   በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2015 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ   በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2015  የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡ የካቲት 15 ቀን እና የካቲት 16 ቀን 2015 ዓ.ም በየተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓሶች በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ያሳውቃል፡፡ በተጨማሪም ተማሪዎችም ለምዝገባ ስትመጡ 1ኛ - የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውንና ፎቶ   ኮፒ፣ 2ኛ - ስምንት ጉርድ ፎቶግራፍ፣ 3ኛ - ብርድልብስና አንሶላ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ መምጣት እንዳለባችሁ ያስታውቃል፡፡ ➢ በተጠቀሱት ቀናት ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚመጡት ተማሪዎች በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣ በላም በረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች በመገኘት ዩኒቨርስቲው የትራንስፖርት አገልግሎት ያቀርባል፡፡ ፡ ➢ ከተገለጸው ቀን በፊት ለሚመጡ ተማሪዎች ምንም ዓይነት አገልግሎት ዩኒቨርስቲው አይሰጥም፡፡ ➢ ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርስቲውን ድረገጽ https://portal.aau.edu.et/ ወይም www.aau.edu.et ማየት የሚቻል ሲሆን ➢ ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉትና ስለ ዩኒቨርስቲው ገለጻ የምታገኙት የካቲት 17 ቀን 2015 ዓ.ም መሆኑን ያሳውቃል፡፡ ➢ ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የመኝታ አገልግሎት ለማግኘት የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል 12ኛ ክፍል በተፈተናችሁበት ቁጥር በመጠቀም https://portal.aau.edu.et ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ ➢ በተለያየ ምክንያት ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2015 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ ከየካቲት 15 እስከ የካቲት 17 2015 ዓ.ም እንድታመለክቱ እናሳውቃለን፡፡   አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ                                                             ሬጅስትራር
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
የጥሪ ማስታወቂያ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አዲስ የመጀመሪያ ዓመት ለተመደባሁ ተማሪዎች በሙሉ በ2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ዓመት አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ 👉የካቲት 13 እና 14/2015 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በዩኒቨርስቲው በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እንገልፃለን፡፡ ማሳሰቢያ 1. በማስታወቂያው ከተገለፁት ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን፣ 2. ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲው ሲመጡ ሊይዟቸው የሚገቡ፡- • የ8ኛ ክፍል ሠርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ • ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ • የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣ • የግል አልባሳት (ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና ስፖርት ትጥቅ “ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት”
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
የጥሪ ማስታወቂያ አዲስ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች በሙሉ፣ በዋቸሞ ዩንቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ለአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ከየካቲት 15-16/2015 ዓ.ም እንዲሁም ለሬሜዲያል (Remedia) የተመደባችሁ ከየካቲት 21-22/2015 ዓ.ም ድረስ የሚከናወን ሲሆን በReadmission እና withdrawal ምክንያት የወጣችሁ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከየካቲት 17-18/2015 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ማሳሰቢያ፣ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲመጡ የሚከተሉትን ይዛችሁ መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡ 1ኛ. የመሰናዶ (12ኛ) ክፍል ያስፋችሁበት ሰርተፍኬት፣ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት እና የ8ኛ ክፍል ካርድ፤ 2ኛ. የሌሊት አልባሳት፣ 3×4 ጉርድ ፎቶ ግራፍ ብዛት 8 እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ መምጣት እንዳለባችሁ እያሳሰብን፤ ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን። ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት
نمایش همه...