cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

💦EVA TV💧

ኢየሱስ የሚለው ስም ልዩ ትርጉም አለው ለኔማ ስጠራው ስደጋግመው ኑ አብረን እናገልግል #ቴዎሎጂ ነክ መጻሕፍት #መዝሙሮች #አጫጭር መልእክቶች #ፀሎትና መገለጥ ትንቢቶች #ከኢየሱስ ጋር ወደፊት ነው በጎ ወታደር ሁሉ ይቀላቀለን። https://www.youtube.com/@Buze7

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
2 479
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+77 روز
+19930 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
ፍርስራሽ የሆነና ደካማ ሸክላ የሆነ ሰውነታችን ዛሬ በኢየሱስ ስም ሃይል እየበረታ ይሔዳል። እርሱ የሚጤሰውን ጧፍ ያነዳል ለቅጥቅጡ ሸንበቆ ብርታት ይሆናል በርቱ ተፅናኑ። t.me/eva_ch7
نمایش همه...
3
Photo unavailableShow in Telegram
ተወዳጁ ዘማሪ አዉታሩ ከበደ ቁጥር 7ቱን የዝማሬ አልበም ሊለቅ ነዉ። "ከ9 አመታት በኋላ የ7 ቁጥር አልበሜ በመንፈስ ተጠምቆ ለቅዱሳን በረከት ላልዳኑ የኢየሱሰን አዳኝነት ለማብሰር ተጠናቋል" ሲል ዘማሪዉ ገልጿል። የምትፅልዩልኝ,በነገር ሁሉ ከጎኔ ያላችሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ። በሁላችሁ እጅ ላይ በቅርቡ የሚደርስበትን ቀን አሳውቃለው የዘማሪዉ መልዕክት ነዉ።
نمایش همه...
👏 2
نمایش همه...
💦EVA TV💧

Boost this channel to help it unlock additional features.

Photo unavailableShow in Telegram
20🥰 2
ረጅም ተጉዘሃል ዛሬ ያለህበትና የጉዞህ መነሻ መሃል በጣም ሰፊ ርቀት አለ። ከዓመታት በፊት የህይወት አቅጣጫህ ሙሉ በሙሉ ከዛሬው የህይወት መንገድህ የተለየ ነበር። ማደግና መቀየርህ ያንተ ሁነኛ መንገድ ቢሆንም ለውጥህ ግን የዛሬ ስፍራህ እንደሚያደርስህ እርግጠኛ አልነበርክም። ተስፋ መቁረጥ ትችል ነበር፣ በእንቅፋቶችህ መሰናከል ትችል ነበር፣ በሰዎች ትቺትና ዘለፋ ማቋረጥ ትችል ነበር፣ ባለብህ የገንዘብና የጊዜ እጥረት ሃሳብህን እንደ ሃሳብ ብቻ መተው ትችል ነበር። ነገር ግን የጉዙህ እርዝማኔም ሆነ በየመሃሉ የሚያጋጥምህ መሰናክል እንቅፋት እንዲሆንህ አልፈቀድክምና ዛሬ ያለህበት ቦታ መድረስ ችለሃል። ማንም በምቾት መሃል ተጉዘህ እንደመጣህ ሊያስብ ይቸላል፣ ማንም ነገሮች አልጋ በአልጋ እንደነበሩ ሊያስብ ይችላል፣ ማንም ሁሉ ተመቻችቶልህ፣ ሁሉ ተዘጋጅቶልህ የመጣህ ሊመስለው ይችላል። እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው። ሰው የማያውቀው ብዙ መሰናክሎችን አልፈሃል፣ ለሰው ብትነግረውም የማይረዳህን የግል ጉዳይ ተወጥተሃል፣ ከዚህም በላይ አንተም ሆንክ ብዙ ሰው የሚያውቀው የግል ፈተና ነበረብህ ነገር ግን አልፈሀው መጥተሃል። ይሔንን ሁሉ ያደረከውም እራስህን በተግባር ስለምትወደው ነው። ረጅም ተጉዘሃል! ብዙ መጥተሃል፣ ብዙ ወርደሃል፣ ለዛሬው መዳረሻህ ብዙ ጥረሃል፣ ብዙ ትተሃል፣ ከብዙ ሰው ተራርቀሃል። የከፈልከው ዋጋ አለ፣ ያወጣሀው ወጪ አለ፣ የተወጣሀው ከባድ ሃላፊነት አለ፣ የተሻገርከው ብዙ መሰናክል አለ። ጥረትህ እስከምን እንደነበረ አንተ ታውቃለህ፣ ምንያህል እንደታገልክ አንተ ታውቃለህ፣ ምንያህል መሱዋዕት እንደከፈልክ ካንተ የተሰወረ አይደለም። ፍረሃት ቀላል ስሜት አይደለም፣ ጭንቀት፣ ተስፋ ማድረግ፣ ትዕግሥት፣ ፅናት፣ ወጥነት፣ ዲሲፕሊን፣ እራስን መግዛት፣ ለአላማ መፋለም እያንዳንዳቸው ቀላል ነገሮች አይደሉም። ከባድ ስለሆኑ ብቻ ሌሎች ሰዎች እንኳን ሊካፈሉህ አይችሉም፣ ለወዳጆችህ ማካፈል አትችልም፣ የቅርብ ሰዎችህ ሊያግዙህ ቢፈልጉ እንኳን ማድረግ አይችሉም። እያንዳንዶቹ የግል ስሜቶች ያንተ የግል የቤት ስራዎችህ ናቸው፤ የምትጋፈጣቸው አንተ እራስህ ብቻ ነህ። ሞክረህ ሞክረህ፣ ተጉዘህ ተጉዘህ፣ መጥተህ መጥተህ ማቆም ትችል ነበር ነገር ግን አላቆምክምና ዛሬ ቀና ብለህ ለመራመድ በቅተሃል፣ ዛሬ ብዙዎች የሚመኙትን የሰውነት አቋም መገንባት ጀምረሃል፣ ዛሬ ብዙዎች ሊወዳጁት የሚፈልጉት ብርቱ ሰው ሆነሃል። ክፍያህ ምንያህል እንደጣርክ አመልካች ነው፤ የመጨረሻው መዳረሻህ የተወጣሀውን ሃላፊነት የሚያሳይ ነው። አዎ! ቆራጥ ብቻ አልነበርክም የተግባር ሰውም ነበርክ፣ ታጋሽ ብቻ አልነበርክ የትዕግስትህን ምክንያትም ታውቅ ነበር፣ አዋቂ ብቻ አልነበርክም ይልቅ ጥበብንም ተላብሰሃል። ፅናትህ ድንቅ ነበር፣ ተነሳሽነትህ ያስገርማል፣ ውስጣዊ ፍላጎትህ ግሩም ድንቅ ነበር። እራስህን መሆንህ ከምንም በላይ ጠቅሞሃል፣ የተግባር ሰው መሆንህ ማንነትህን ቀይሮታል፣ ውስጣዊ አቅምህን በሚገባ መረዳትህ ፅኑ አድርጎሃል፣ ለውጥን አለመፍራትህ፣ ላመንክበት አላማ እራስህን መስጠትህ ከፍታህን ጨምሮታል፣ ለቁጪት እድል አለመስጠትህ ከምታስበው በላይ ብርቱና መንፈሰ ጠንካራ አድርጎሃል። ትናንትህን አስታውስ፣ ጅማሬህን ወደኋላ ተመልከት፣ መነሻህን አስተውል። የዛሬው ስኬትህ ትልቁ ቁልፍ ከምንም በላይ መነሻህ እንደሆነ እወቅ። "ባልጀምር ምን ይፈጠር ነበር?" ብለህ ጠይቅ። በእርግጠኝነት የዛሬው ህይወትህ ምኞት ብቻ ይሆን ነበር። #ሼር t.me/eva_ch7 t.me/eva_ch7
نمایش همه...
6
Photo unavailableShow in Telegram
የቀጠለ..... #ይህችን_ሴት_አትሁኝ 11. እጆችሽን በፍቅር ያሻሽሻል በቀልዱ ያስቅሻል 12. አይኖችሽን በፍቅር አይን ተመልክቶ ፈገግታ ይመግብሻል 13. ብዙ ትውውቅ ያላቹ ያህል ተሰማሽ 14. ክፍል እንድትይዘ ጠየቀሽ ተስማማሽ 15. ምቾት እንዲሰማሽ አደረገ 16. በፍቅር በስሱ ከንፈርሽን መሳም ጀመረ 17. ትክክል አለመሆኑ ቢገባሽም ደስታ ተሰምቶሻል 18. በእርጋታ ወደ አልጋ ወሰደሽ 19. ለመቃወም አቅሙን አጣሽ 20. ሌለዉ ቢቀር መከላከያ ለመጠቀም ሀሳብ አቀረብሽ 21. በስሜት ጦፎ ሰለነበር ሊሰማሽ አልቻለም 22. ፍልሚያውን ወደድሽው እርካታም አገኘሽ 23. ከፍሪጅም ቀዝቃዛ ዉሀ አምጥቶ እራሱ አጠጣሽ 24. የሚያሳይሽ ክብር እጅጉን ማረከሽ 25. ራስሽን እድለኛ አርገሽ ቆጠርሽ 26. የምትፈልጊውን ወንድ እንዳገኘሽ ተሰማሽ 27. ልብሰሽን ለባበስሽ 28. ወደ ቤት አቅፎ ሸኘሽ 29. ጉንጮችሽን ስሞ የደሰታ ጊዜ ማሳለፉን ገለፀልሽ 30. ለጉዞሽም ገንዘብ በእጅሽ አስጨበጠሽ 31. ከልብሽ ፈገግ በማለት ነገ እንገናኝ ፍቅር አልሽው 32. እሱ ግን መልስ አልሰጠሽም 33. በደስታ ፈገግ እንዳልሽ ተጉዘሽ እቤት ደረሰሽ 34. በሰላም እቤት እንደደረሽ ሜሴጅ ላክሽለት 35. online ቢሆንም መልስ አልመለሰልሽም 36. ግራ ተጋብተሽ ድጋሜ ፃፍሺለት 37. አሁንም መልስ የለም 38. ከደቂቃዎች ብሀላ ስታይው ቴሌግራም ላይ ብሎክ ተደርገሻል 39. ብሎክ መደረግሽ ታወቀሽ 40. ቀናት ሳምንት ወራት አለፉ 41. ህመም ይሰማሽ ጀመር ድካም ክብደት መቀነስ.. 42. ወደ ሆስፒታል በመሄድ ምርመራ አደረግሽ 43. ከቆይታ ቡሀላ ነርሶ ውጤት ይዛ መጣች 44. HIV ፖዘቲቭ እና እርጉዝ እንደሆንሽ ተነገረሽ 45. እንዴት??? 46. ከእውነቱጋ ተጋፈጥሽ 47. ጭንቀት ነገሰብሽ በፍርሀት ተዋጥሽ 48. ተስፋ ቢስነት ስሜት አልባነት ተሰማሽ 49. ሞት ወደ አንቺ መቃረቡ ተሰማሽ 50. ሁኔታዎች ወደ ኃላ ተመልሰው ብታድሻቸው ተመኘሽ 51. ግን ምን ዋጋ አለው እረፍዶል 52. ወደ ሰማይ በማንጋጠጥ ፀሎት አደረስሽ😢😥😥🙏 • ይህችን ሴት አትሁኝ • በስሜት አትመሪ • በሀቡት በንዋይ ሰውን አትመዝኚ • ሴት ልጅሽ እንድትሆንልሽ የምትመኚውን አይነት ሴት ሁኚ የመፅሐፍ ቅዱሷን የተባረከችውን ሴት ሁኚ። . . . ለሴቶች የሚሆን ምክር ያንብቡት።አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያድርጉ 👇👇👇👇👇👇👇👇 t.me/eva_ch7 👆👆👆👆
نمایش همه...
💦EVA TV💧

ኢየሱስ የሚለው ስም ልዩ ትርጉም አለው ለኔማ ስጠራው ስደጋግመው ኑ አብረን እናገልግል #ቴዎሎጂ ነክ መጻሕፍት #መዝሙሮች #አጫጭር መልእክቶች #ፀሎትና መገለጥ ትንቢቶች #ከኢየሱስ ጋር ወደፊት ነው በጎ ወታደር ሁሉ ይቀላቀለን።

https://www.youtube.com/@Buze7

👍 8
ጊዜ ተራማጁ ጊዜ ልቡ❤ ይመታል ድው...ድው እያለ                                                ይቆጥራል፤ ጊዜ እግሩ ይራመዳል የኮቴውን ድምፅ እያሰማ መንገዱን ይጓዛል። ሰሚው አካል ግን ጆሮው ያለው ግን፤ ወዴት እንደሚሄድ አቅጣጫውን አቶ ግራ በመጋባት ሁሉንም እረስቶ ጉንጩን ደገፍ አርጓል ውስጡ ኦና ሆኖ፤ በራሱ ይነጉዳል ባሻው ይከንፋል ጆሮ ዳባ ብሎ። ይሄ ቢያርደውም ሆድ ቢያብሰው አባ ሆይ ተነሳ ጌዜን ሊጠቁመው ልጄ አትድከም አትልፋ ህይወት ለሌለው ሲሄድ አይነግርህም ጊዜ ጣረ ሞት ነው። ድንገት ይመጣና ድንገት ያልፍሃል፤ ከልብ ከቀረብከው ከልቡ ይወድሃል። ድንገት ካለፈህ ዞሮ አያይህም ጊዜ ተራማጅ ነው ቆሞ አይጠብቅህም። ስትወደው ውድ ነው ብትይዘው ክቡር ነው ጊዜን እንቁ ነው። ገጣሚ ባሮክ t.me/eva_ch7
نمایش همه...
👍 4 3
Photo unavailableShow in Telegram
#አስተማሪ_ምክር ለሴቶች #ይህችን_ሴት_አትሁኝ 1. በቴሌግራም ሀይ አለሽ 2. ሳትመልሺ ወደ profilu አቀናሽ 3. አለባበሱም ሆነ አቁዋሙ ያምራል 4. በድጋሜ ሀይ አለሽ 5. አሁን ግን በደስታ መለሽለት 6. መልክት መለዋወጥ ተጀመረ.. 7. በአካል ለመገናኘት ቀጠሮ ተያዘ 8. ጥሩ ልብስ ለበሰሽ ሽቶ ተቀብተሽ አምሮብሸ ሄድሽ 9. ወድ የሆነ መዝናኛ ቦታ ወሰደሽ 10. ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ ጀመራቹ ይቀጥላል..... @eva_ch7
نمایش همه...
👍 4👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ቢሾፕ ዴቭ ለሸዋፈራው ያወጣው ስም 👉""ሰይጣን ፈራው"" *** የተወደደው ወንድማችን ሰይጣንፈራው በማህበራዊ ድረገፅ በሚጣፍጥ አንደበት በፍፁም ትህትና ለሰው ልጆች ሁሉ መዳን የሚሆነውን የዳንበትንና ነፃ የወጣንበትን የምስራቹን ቃል ወንጌል ጌታ ኢየሱስን በስልጣን በመስበክ ማህበራዊ ድረገፅን ለንትርክና ለስድድብ ሳይሆን ለወንጌል ስርጭት ተጠቅሞበታል::ወንድማችን በእውነት ተባርከሀል:: ከዚህ በሁዋላ ስለስሙ ብትሰደብ ብትነቀፍ የወንጌል ማህበርተኛ በመሆንህና የኢየሱስን ስም ስትጠራ ሰይጣን ስለሚቃጠልና ስራው ስለሚፈርስበት ነውና ደስ ይበልህ እኔም ከዚህ በሁዋላ ሸዋፈራው ደሳለኝ ሳይሆን "ሰይጣንፈራው ደሳለኝ"ብዬሀለው ሸዋማ ይውደድህ ምንበወጣው የሚፈራህ አምላኩን ይፍራ እንጂ::   “ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ “                                ዮሐንስ 1:12 https://t.me/eva_ch7 https://t.me/eva_ch7
نمایش همه...