HiTech
رفتن به کانال در Telegram
HiTech | Learn. Fix. Create. 📱💻🎨 Your Ethiopian tech hub! We teach: ✅ Smartphone Repair ✅ Laptop & Chip-Level Repair ✅ Graphics & Motion Design ✅ Coding & Web Development ✅ Tools, Tips & Tech Reviews Join the HiTech family — grow your skills & build
نمایش بیشتر1 704
مشترکین
+324 ساعت
+167 روز
+2330 روز
آرشیو پست ها
1 704
🔴 ዲሲ ፓወር ሰፕላይ (DC Power Supply) በኤሌክትሮኒክስ እና በሞባይል ስልክ ጥገና ስራ ላይ በጣም አስፈላጊ ከሆኑ የምርመራ መሣሪያዎች አንዱ ነው።‼️
⛔️ ባጭሩ ዲሲ ፓወር ሰፕላይ ማለት ከግድግዳ የሚመጣውን ተለዋዋጭ የኤሌክትሪክ ኃይል (AC - Alternating Current) ወደ ቋሚና ቁጥጥር ወደሚደረግበት ቀጥተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል (DC - Direct Current) የሚቀይር መሣሪያ ነው።
⛔️ በስልክ ጥገና ላይ ይህ መሣሪያ እንደ " ባትሪ" (Mock Battery) ሆኖ ያገለግላል። ስልኩን ያለ ባትሪ በራሱ በፓወር ሰፕላዩ አማካኝነት በማስነሳት ስልኩ ያለበትን የሃርድዌር ችግር በቀላሉ ለመለየት ያስችላል።
1️⃣ . ዲሲ ፓወር ሰፕላይ ለምን ይጠቅማል? (ጥቅሞቹ)‼️
🟠 የስልክ ባትሪን ተክቶ ለማስነሳት፦ ባትሪው ሙሉ በሙሉ የሞተ ወይም የተበላሸ ስልክ ሲመጣልህ፣ ስልኩ ራሱ ይሰራል ወይስ አይሰራም የሚለውን ለማረጋገጥ በፓወር ሰፕላዩ ኃይል በመስጠት ማስነሳት እንችላለን።
🟠 የኤሌክትሪክ ሾርት (Short Circuit) ለመለየት፦ በማዘርቦርዱ ላይ የኤሌክትሪክ መስመር መተላለፍ (ሾርት) ካለ፣ ስልኩን ሳታበራው ገመዱን ስታገናኝ ብቻ ከፍተኛ አምፔር (Current) በመሳብ ሾርት መኖሩን ወዲያውኑ ያሳውቀሃል።
🟠 የስልኩን በሽታ ለመለየት (Diagnosis)፦ ስልኩ ሲበራ የሚስበውን የኤሌክትሪክ መጠን (Ampere Reading) በማየት ችግሩ የፓወር አይሲ (Power IC)፣ የሶፍትዌር (Boot loop) ወይስ የሲፒዩ (CPU) መሆኑን መለየት ይቻላል።
🟠 የሞቱ ባትሪዎችን ለመቀስቀስ (Battery Boosting)፦ ሙሉ በሙሉ ቮልቴጃቸው ወርዶ ቻርጀር እምቢ ያሉ ባትሪዎችን በከፍተኛ ቮልቴጅ በመምታት መልሶ ህይወት ለመስጠት ያገለግላል።
