fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

رفتن به کانال در Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

کانال Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 15 948 مشترک است و جایگاه 5 316 را در دسته دین و مذهبی و رتبه 2 234 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 15 948 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 21 اکتبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 408 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 1 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 25.79% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 10.92% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 4 113 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 1 742 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 29 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 22 اکتبر, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته دین و مذهبی تبدیل کرده‌اند.

15 948
مشترکین
+124 ساعت
+1627 روز
+40830 روز
آرشیو پست ها
#ታኅሣሥ_12_የአቡነ_ሳሙኤል_በዓለ_ዕረፍት ✤✤ #ፀሐይ_ማር_አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_(#ዘገዳመ_ዋሊ_) ✤✤ ፠ በሃገራችን በኢትዮጵያ በብቸኝነት በጌታችን የተመሠረተው ገዳመ ዋልድባ፤ ኋላ በአሕዛብ ጠፍቶ ነበርና በ13ኛው ክፍል ዘመን እንደ መሶብ ከፍ አድርገው በ4ቱም አቅጣጭ በ4 ወንዞች (በሰሜን ተከዜ፥ በምስራቅ እንስያ፥ በምዕራብ ዛሪማ ፥ በደቡብ እንዞና ወይቦ) ዙሪያውን ከልለውና አጥረው ያስባረኩ አባት ናቸው፡፡ ፠ አዲስ አበባና አካባቢውን ከ700ዓመታት በፊት በአንበሳ እየተጓጓዙ በስብከተ ወንጌል እርሻነት፥ በሥነ ምግባር ማለስለሻነት ያረሱ አባት ናቸው፡፡ ፠ ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን፣ ወላዴ መምህራን ወሊቃውንት የኾኑ ናቸው፤ ይህንንም ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በ40ቀን ዕረፍታቸው በመካነ መቃብራቸው ተገኝተው መልክዓቸውን ደርሰውላቸዋ፤ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል በማኅሌተ ጽጌ ድርሰታቸው አውስተዋቸዋል፤ እንዲሁም በርካታ ቅዱሳን ደራስያን በየድርሰታቸው አንስተዋቸዋል፡፡ #ክቡር_መምህር፥ #የከበረ_መምህር፤ #መልአክ_ዘበምድር፥ #የምድር_መልአክ፤ #ካህን_ወድንግል፥ #ካህንና_ድንግል፤ #ፍጹም_ንጹሕ_ወልዑል፥ #ፍጹም_ንጹሕና_ልዑል፤ #ትጉህ_ወኅሩይ፥ #ትጉህና_ኅሩይ_የተመረጠ)፤ #ብእሴ_እግዚአብሔር፥ #የእግዚአብሔር_ሰው፤ #ለባሴ_ንጽሕና፥ #ንጽሕናን_የተላበሰ፤ #ወለብሰ_ብርሃናዌ፥ #ብርሃንን_የለበሰ፤ #ዘፈጸመ_ገድሎ_በሠናይ፨ #ገድሉን_በመልካም_ተጋድሎ የፈጸመ፨/ገድለ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ/ ፠ ከረድአቸው አባ ብንያሚና፤ ከጓደኞቻቸው ከአባ አንበስ ዘሐዘሎና ከአቡነ ዘርዐ ቡሩክ ጋር በመኾን በወቅቱ ከነበሩት ርዕሰ አበው አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘንድ ለመባረክ ወደ ዝቋላና ምድረ ከብድ የመጡና በረከትን የተቀበሉ ከሰሜን እስከ ደቡብ ኢትዮጵያ ያስተማሩ ናቸው፡፡ ፠ አናታቸው በሥጋ ሞት በሕፃንንታቸው ቢለይዋቸውም፤ በሕፃንነታቸው ጌታችን አውራ ጣቱን አትብቷቸዋል፡፡ ‹‹እንዘ ይተግህ ለጸልዮ ወያስተበርክ ለስኢል፤ መንኰብያቲሁ አጠበዎ ወልደ ማርያም ድንግል፡፡ ሳሙኤል፥ ሳሙኤል፥ ሳሙኤል ዘዋልድባ መነኮስ ኀያል፡፡›› /እንዲል ነግሥ/ ፠ የተከዜ ወንዝ ሞልቶ የማያሻግራቸው ቢሆን ውሃውን በትዕምርተ መስቀል ባርከው በአንድ እጃቸው መጽሐፍ ፥ በአንድ እጃቸው መብራት እንደያዙ ወደ ወንዙ ገብተው መብራቱ ሳይጠፋ መጽሐፉም ሳይበላሽ ተሸግረዋል፡፡ ፠ ገባሬ ተዓምራት ወመንክራት የኾኑ፤ ⴲ ዝናብ በኾነ ጊዜ ዝሆኖች መጥተው እንደ ጥላ የሚያስጠልሉት፤ ‹‹ሳሙኤል አቡነ ሠረገላ ጸሎት፤ ጊዜ ርደቶሙ ለዝናማት፤ ዘከለሉከ ነጌያት፡፡›› እንዳለ መጽሐፈ ሰዐታት፤ ⴲ ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ (ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት) ጋር መንበረ ጸባዖትን ለ12 ዓመታት አጥነዋል፤ በዚህም በጎንደር ደባርቅ አካባቢ የመሠረቱት ገዳማቸው አብ ጠራ(ህ) በሚል ተሰይሟል፡፡ ......................................የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ‹‹ሳሙኤል አቡነ ትሩፈ ምግባር፤ ዐምድ ጽኑዕ ፀወነ ሃገር፤ ወመልአክ ዘበምድር፡፡›› እንዲል መጽሐፈ ሰዐታት፣ ⴲ በዋልድባ ምድር ላይ ቀድሞ ውኃ የለም ነበርና፤ ፸ የሚጠጉ ምንጮችን በተለያዩ ቦታዎች አፍልቀዋል፡፡ ⴲ ቅዳሴ ማርያምን ወደ መሃል ሃገር ያመጡ፤ ⴲ ቅዳሴ ወውዳሴ ማርያምን ሲደግሙ ከመሬት ክንድ ከስንዝር ያህል ከፍ የሚሉ፡፡ ⴲ በአናብስት ዘባን ላይ የሚጫኑ፤ መጻሕፍቶቻችውንም በአናብስት ላይ የሚጭኑ፡፡ ⴲ እመቤታችን ነጭ ዕጣን (ስለ ምዑዝ ክህነታቸው) እንዲሁም ዕንቊ (ስለ ንጽህናቸው፣ ቅድስናቸውና ድንግልናቸው) የሰጠቻቸው። ⴲ በሰኔ 21 ቀን በቀደሱበት ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑ አንድ ክንድ ከስንዝር ከምድር ለቆ እንደ ደመና በአየር ላይ ቆሞ የታየላቸው፡፡ ⴲ ውኃውን ወደ ኀብስት የቀየሩና ከነ ደቀመዛሙርቶቻቸው የተመገቡ፤ ‹‹ሶበ አተቦ ለማይ በቅዳሴኪ እንዘ ይጼሊ፤ ረሰዮ ኅብስተ ጽጌ ሃይማኖት ሳሙኤል ዘሐቅለ ዋሊ፡፡ ምሕረተ ወፍትሐ ለተአምርኪ እኅሊ፤ ሥረዪ ኀጢአትየ ወዕፀብየ አቅልሊ፤ አስመ ኵሎ ገቢረ ማርያም ትክሊ፡፡›› /ማኅሌተ ጽጌ/ ‹‹ …አርአዮሙ ለመምህራን ዐበይተ ኀይላተ፤ እንዘ ይገብር ተአምረ ወመንክረ በኀበ ተአኵተ፥ ወለማይኒ ረሰዮ ኅብስተ፡፡›› /ማኅሌተ ጽጌ/ የምንኵስና ተወረዱም፤ አባት አባትን ሲወልድ፤ መምህር መምህርን ሲተካ፥ ቅዱስ ቅዱስን ሲያፈራ፥ ገዳም ገዳምን ሲወልድ ነውና ቅሉ፤ የምንኵስና ተዋረዱም፤ ፠ ….. ፀሐይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አቡነ መድኃኒነ እግዚእን፤ ፠ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ 7ቱን ከዋክብት /ፀሐይ አቡነ ሳሙኤልንና ሌሎች ቅዱሳንን/፤ ፠ ከ7ቱ ከዋክብት አንዱ ፀሐይ አቡነ ሳሙኤል ደግሞ ደቀ መዛሙርቶቻቸውን (አባ ተሥፋ ሐዋርያትን፥ አባ ዘሩፋኤልን፥ አባ ብንያሚን፥ አባ በኪሞስን፥ …… ሌሎች እልፍ አእላፋት መነኰሳትን አምንኵሰዋል፣ ሊቃውንትን አስተምረዋል፤ መምህራንና ደራስያንን ተክተዋል ….፤ በዚህም ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን ፥ ወላዴ መምህራን ወሊቃውንት አባ ሳሙኤል በመባልም ይታወቃሉ፡፡ #አቡነ_ሳሙኤል_፤ በአኵስም ከተማ አካባቢ በ1295 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ አባታቸው እስጢፋኖስ እናታቸው ዓመተ ማርያም ይባላሉ፡፡ በአኵስም ጽዮን ከነበሩት መምህራን ከፊደል ጀምረው የቅዱስ ያሬድን ጸዋትወ ዜማና ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን ተምረዋል፡፡ ወላጆቻቸው በልጅነታቸው በሞት ተለይተዋቸዋል፡፡ ከወላጆቻቸው ሞት በኋላ ወደ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘንድ ሔደው ደብረ በንኰል ገዳም ገቡ፡፡ በዚህም ገዳም እያገለገሉ በወቅቱ ከነበሩት ሊቃውንት የብሉያትና የሐዲሳትን ትርጓሜ እንዲሁም ሥርዐተ ምንኵስናን ተምረው ከገዳሙ አባት በአቡነ መድኃኒነ እግዚእ እጅ ከሌሎች 11ድ ወንድሞቻቸው ጋር አብረው መነኰሱ፤ ቆባቸውም እንደ አቡነ አረጋዊ የድንጋይ ቆብ ነበር፡፡ በዚህም ገዳም እህል ሳይበሉ ቅጠል ብቻ እየተመገቡ ይኖሩ ነበር፡፡ እግራቸው እስኪያብጥም ድረስ ይሰግዱ ነበር፡፡ **ኋላ ወደ ጣና ገብተው ከቆብ ወንድማቸው ከአቡነ ያሳይ ጋር ለ12 ዓመታት በሱባኤ ቆዩ፤ **በስተመጨረሻም ጌታችን ወደ መሠረተውና በመሃልም ጠፍ ሆኖ ወደ ነበረው ብዙ ቅዱንን፣ መምህራንን፣ ሊቃውንትንና መናንያንን ወደ ወለዱበት ዋልድባ ገዳም ገብተው ለ70 ዓመታት ያህል ከዚህ ዓለም በምናኔ ተለይተው፣ ግርማ ሌሊቱን፥ ፀብአ አጋንንቱን ፥ ድምፀ አራዊቱን፥ የሌሊቱን ቊር፥ የቀኑን ሐሩር ታግሠው፣ ረሃቡንና ጽሙን ችለው፣ መላ ዘመናቸውን በጽድቅ ጎዳና ተጕዘው በ1395ዓ.ም ታኅሣሥ 12 ቀን በዋልድባ አቴና ገዳም ዐርፈዋል፡፡ #ባርከኒ አባ እንሣእ ጸሎተከ፤ በእንተ ሰላማ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ አባ ሳሙኤል ባርከኒ እንሣእ በረከተከ፨ /ጸሎተ መሐረነ አብ/ #በታኅሣሥ ፲፪ በበዓለ ዕረፍታቸው ጊዜም፤ ሮም በጴጥሮስና በጳውሎስ ዕረፍት እንዳለቀሰች፤ ቅድስት ገዳማቸው ገዳመ ዋልድባ (ዋሊ) አልቅሳለች፨ ‹‹በከየት ወለሀወት ገዳምከ በሞትከ ዮም፤ ሃሌ ሉያ፥ ሃሌ ሉያ፥ ሃሌ ሉያ፤ ምድረ ዋልድባ ቅድስት ሰሚዓ ዜና ሞትከ፤ እንዘ አንተ ሰብእ ምድራዊ ወመልአክ ተሠመይከ፤ ካህነ አርያም ሳሙኤል መንበረ ሥላሴ ዘአጠንከ፤ አንበሳ ወነምር ይሰግዱ ለከ፤ ወይልህሱ ጸበለ እግርከ፤ ዕንቈ ወዕጣነ ማርያም አምጽአት ለከ፤ በቅዳሴሃ ሶበ ጸለይከ፤ በከየት ወለሐወት ገዳምከ።>> እንዲል ዚቅ፨ (ሥርዐተ ማኅሌቱን ላልደረሰው ያድርሱ)

#የመስቀል ወረብ (በቀራንዮ መካን ….) ፤ በደብረ ሰላም ሊቃውንት በዩቲዩብ ገጻችን ያድምጡ:: https://youtu.be/2QR7BR2Emg8

#ታኅሣሥ_12_የአቡነ_ሳሙኤል_በዓለ_ዕረፍት_ከሚከበርባቸው_ቦታዎች_ዋናዎቹ፤ ✤✤1. በሁሉም #የዋልድባ_ገዳም_ክፍልች_ (በውስጡ ባሉት 3ት ገዳማት፣ የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት፣ ጸሎት/ስዕል/ ቤቶች፣ የአትክልት ቦታዎችና ሞፈር ቤቶች)፤ እነዚህም፤ 1.1. ዋልድባ አብረንታንት መድኀኔ ዓለም ገዳም **1.2. ዋልድባ ዳልሽህ ገዳም (ዋልድባ ዳልሽህ አባ ሳሙኤል ገዳም) **1.3. ዋልድባ ሰቋር ገዳም (የኪዳነምሕረት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስና የመድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን) **1.4. በዋልድባ አቴና (መቃብረ ሳሙኤል)፤ ሌሊቱንና ቀኑን ሙሉ ጧፍ እየበራ ገድላቸው እየተነበበ **1.5. በዋልድባ አባ ናፃ የአቡነ ተሥፋ ሐዋርያት ገዳም **1.6. በዋልድባ ደንደሮቃ ቅዱስ ሚካኤል ገዳም **1.7. በዋልድባ ማይ ለበጣ ቤተ እግዚአብሔር **1.8. በዋልድባ ማይጋባ ቅዱስ ሚካኤል ገዳም **1.9. በዋልድባ ደለሳ ቆቋ አቡነ አረጋዊ ገዳም **1.10.በዋልድባ ማይ ሃርገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም **1.11. በዋልድባ ዕጣኖ ማርያም ገዳም **1.12. በዋልድባ ዋልቅስ ኪዳነ ምሕረት **1.13. በዋልድባ አምብላ አቦ **1.14. በዋልድባ ስር ባሉ የስዕል ቤቶችና የአትክልት ቦታዎች (…..) ✤2. በተወለዱበት በርዕሰ አድባራት ወገዳማት አኵሱም ጽዮን ማርያም፤ ✤3. ምንኵስናን በተቀበሉበት በደብረ በንኰል አቡነ መድኀኒነ አግዚእ ገዳም፤ (ሽሬ አጠገብ) ✤4. በቆብ ወንድማቸው በአባ ያሳይ መንዳባ መድኀኔ ዓለም ገዳም፤ (ጎርጎራ ፥ ጣና) ✤ 5. በቆብ አያታቸው በአቡነ ተክለሃይማኖት ደብረ ሊባኖስ ገዳም በውዳሴና በቅዳሴ (በደብረ ሊባኖስ ቅዳሴ በየቀኑ በማይቀደስበት፤ በዓመት ውስጥ ጥቂት ቀናት ብቻ በሚቀደሱበት ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የቅዳሴ ቀናቸው ከማይታጎሉ አንደኛውና ዋነኛው የአቡነ ሳሙኤል በዓለ ዕረፍት ነው) ፠፠ 5. አቡነ ሳሙኤል በመሠረቷቸውና ባስፋፏቸው ገዳማት፤ ✤5.1 #በደብረ_ዐባይ_አቡነ_ሳሙኤል_ገዳም_ /ሽሬ (እንዳባጉና) አጠገብ/ (#በኢትዮጵያ_የቅዳሴ_ዘደብረ_ዐባይ_ትምህርት_ዋና_ማስመስከሪያ)፤ እጅግ ደማቅ በኾነ ኹኔታ፡፡ ✤5.2 #በአብጠራ_(አብጠራህ) #አቡነ_ሳሙኤል_ገዳም_ /ጎንደር ፥ ደባርቅ/ (ከጎንደር ከተማ 100 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ የሚገኝ) ✤5.3 #በደብረ_ገነት_አቡነ_ሳሙኤል_ገዳም_ /አዲስ አበባ አቃቂ አጠገብ፥ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ያለበት ጋር/) በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ✤5.4 #በጎንደር_አዘዞ_አባ_ሳሙኤል_፡፡ ✤✤6. በተጨማሪም በስማቸው በታነጹ አብያተ ክርስቲያናት ይከበራል፤ ለአብነትም፤ በአዲስ አበባ በስማቸው በብቸኝነት በታነጸው #በቦሌ_ቡልቡላ_ምስካበ_ቅዱሳን_አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_ገዳም #በአዲስ_አበባ_ወረገኑ_ቅዱስ_ሚካኤል_እና_ጻድቁ_አቡነ_ሳሙኤል_ #በአዲስ_አበባ_ሲምሲ_ሚካኤል_(በድርብነት) #በታጠቅ_በዓለ_ወልድ_ቤ.ክ (በድርብነት ይከብራል) ፤/ ወደ መናገሻ መንገድ ሲሄዱ) #በአንጓ_ቀርነጃ_ታላቅ_ሴራ_ሳሙኤል_ #በነቀምቴ_አቡነ_ሳሙኤል_ #በዩኤስ_አሜሪካ_ቨርጂንያ_ሐመረ_ብርሃን_ቅዱስ_አባ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_ገዳም_ #ባርከኒ አባ እንሣእ በረከተከ በእንተ ሰላማ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አባ ሳሙኤል/፫/ ባርከኒ እንሣእ በረከተከ፡፡ ከቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/ Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

#በቤተክርስቲያናችን_በር_ላይ_ለጥፈን_የነበረው_ባነር_በአስተዳደሩ_መመመርያ_ሰጪነት_በመውረዱ_ምክንያት_ስብሰባው_ቀርቶ_ነው_ወይ_ብላችሁ_ለጠየቃችሁን_የአካባቢ_ወጣቶች በሙሉ በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃ
+1
#በቤተክርስቲያናችን_በር_ላይ_ለጥፈን_የነበረው_ባነር_በአስተዳደሩ_መመመርያ_ሰጪነት_በመውረዱ_ምክንያት_ስብሰባው_ቀርቶ_ነው_ወይ_ብላችሁ_ለጠየቃችሁን_የአካባቢ_ወጣቶች በሙሉ በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል አብያተ ክርስቲያናት አጥቢያ የምትገኙ ወጣቶች ቅዳሜ 10/04/2013 ዓ.ም የዘንድሮውን የጥምቀት በዓል በደመቀ ሁኔታ ለማክበር የተጠራው ስብሰባ የተጠበቀ ነው፡፡ ሰንበት ት/ት ቤቱ በየዓመቱ የጥምቀትን በዓል የአካባቢውን ወጣት እያስተባበረ በዓሉን በሰላም እና በፍቅር እንደሚያከብር ይታወቃል፡፡ስለሆነም በዘንድሮውም ዓመት በቤተክርስቲያናችን በር ላይ ለጥፈን የነበረው ባነር በአስተዳደሩ መመመርያ ሰጪነት በመውረዱ ምክንያት ስብሰባው ቀርቶ ነው ወይ ብላችሁ ለጠየቃችሁን የአካባቢ ወጣቶች ስለ ጥምቀት በዓል ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ የተጠራው ስብሰባ የተጠበቀ መሆኑን እንገልጻለን::

#ታኅሣሥ 7/2012 ዓ.ም. #ለመጀመሪያ_ጊዜ_የቅዱስ_ያሬድ_ዜማ_በቤተ_ክርስቲያናችን_አገልግሎት_የተጀመረበትን በማስመልከት፤ ‹‹#የዜማ_ቀን_ክብረ_በዓልን_›› #በደብረ_ይባቤ_ቅዱስ_ያሬድ_ቤ/ክ #ለመጀመሪያ_ጊዜ_ክብረ_በዓሉ_ታቦቱ_ወጥቶ_መክበሩን እናስታውሳለን_፡፡ አነሆ ዘንድሮም👉👉 አሑድ #ታኅሣሥ_11_በ2013 ዓ.ም ለሁለተኛ ጌዜ ታቦተ ሕጉ ወጥቶ ይከብራል 👉👉#በዓሉ_ግን_ታኅሣሥ_7_ነው፡፡ (አድራሻ፤ ጎተራ ከአጎና ሲኒማ ከ,ወደ መስቀል ፍላወር በሚወስደው መንገድ፡፡) ፠ (#ቅዱስ_ያሬድን_ያልዘከረ_ኢትዮጵያዊ_ምኑን_ኢትዮጵያዊ_ኾነ!?) ፠ (#ቅዱስ_ያሬድን_ያልዘከረ_ካህን_ምኑን_ካህን_ኾነ!?) ፠ (#ቅዱስ_ያሬድን_ያልዘከረ_ሰንበት_ተማሪ_ምኑን_ሰንበት_ተማሪ_ኾነ!?) ፠ ጥዑመ ልሳን፤ ፠ የሱራፌል አምሳያ፤ ፠ የቤተ ክርስቲያን እንዚራ፤ ፠ የቤተ ክርስቲያን ብርሃን፤ ፠ መዓርዒረ ዜማ፤ ፠ ካህን (ካህነ ስብሐት) ፠ ማኅሌታይ፤ ፠ መዘምር ዘበድርሳን፤ ፠ ሊቅ (ርእሰ ሊቃውንት) ፠ ዓርከ ሊቃውንት፤ ፠ ደራሲ፤ ፠ የመጽሐፍ መምህር፤ (ብሉያትንና ሐዲሳትን የሊቃውንትንም መጻሕፍት አስማምቶ የተረጐመ) ፠ ባለቅኔ (የቅኔ ጀማሪ)፤ ፠ የቤተክርስቲያን ጌጧና መሠረቷ ሕይወቷና እስትንፋሷ ፠ ልዑለ ስብከት፤ ፠ ሰማዕት፤ ፠ ባሕታዊ፤ ፠ መናኝ ፠ የዜማ አባት፤ ፠ የኢትዮጵያ ብርሃን፡፡ ፠ አንደበቱ ጣፋጭ (ጥዑም) የኾነ:: ፠ እግሮቹ በመልካም መንገድ የሚጓዙና ወደ መልካም መንገድ የሚያስጕዙ ፠ ልቡናው የቅድስና ማኅደር የኾነ:: ፠ ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ የኾነ:: ፠ አእምሮው የመጠቀ፤ ፠ ድርሰቱ የተራቀቀ፤ ፠ እስከ አርያም ተነጥቆ ዕፁብ ድንቅ ምሥጢራትን የተመገበ፤ …… ማን እንደርሱ:: …... •፠ሃሌ ሉያ ንዑ ንትፈሣህ በመኃልይሁ፤ ወንንግር ለካህን ውዳሴሁ፤ ከመ ሱራፌል ለያሬድ ክላሁ፤ ለክርስቶስ ሰበከ ትንሣኤሁ፤ ማኅበረነ ይባርክ በእዴሁ፡፡ •፠ሶበ ኤዶምሃ መሠጥዎ፥ ግናየ ትንሣኤ መልዕዎ፤ ለያሬድ ካህን አስተብፅዕዎ፡፡ የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔዓለምና ደ/ትጉሃን ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት፡፡ Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

#ታኅሣሥ_6_የአርሴማ_ቅድስት_ወሰማዕትና_የእርሷ_ማኅበርተኞች_ድል_አድራጊዎች_27_ሰማዕታት_ሥጋቸው_በክብር_የፈለሰበትና_ቤተ_ክርስቲያኗ_ቅዳሴ_ቤት_የተከበረበት_ዕለት ነው፡፡ 1ኛ. አርሴማ፤ ቅድስት ወሰማዕት ኃያል ተጋዳሊት 2ኛ. ኢያሚኖስ፤ ጸሎትን የሚያሳርግ ካህን 3ኛ. አፍጢኖስ፤ ከብዙዎች የተመረጠ 4ኛ. በርቲኖስ፤ ጻድቅና ቸር 5ኛ. ጢሞና፤ በመላላክ ሥራ አገልጋይ የኾነ 6ኛ. ጢሞዓና፤ ተአጋሽና ጸዋሚ 7ኛ. ዘኬዎስ፤ ከከበሩ የከበረ 8ኛ. እስጢፋኑ፤ ተጋዳይና የበደሉትን ይቅር ባይ 9ኛ. አርሞና፤ ከጎልማሶች ይልቅ ደም ግባቱና መልኩ ያማረ 10ኛ. ኪርያኮስ፤ ሥጋውን ያላረከሰ ንጹሕ 11ኛ. አንጥያኮስ፤ ቡሩክ የኾነ የአቡሪ ልጅ 12ኛ. ያዕቆብ፤ የእግዚአብሔር ታማኝ የኾነ 13ኛ. ቡራኬሌስ፤ በሰው ዘንድ ተወዳጅ የኾነ 14ኛ. አስቂርያቆስ፤ ክርስቶስን የሚወደው 15ኛ. አስኪርያኖስ፤ ባለሟል የኾነና ግርማው የሚያስፈራ 16ኛ. ሚርያኖስ፤ ፊቱና መልኩ ደስተኛ የኾነ 17ኛ. ትትግርጦስ፤ ወደ ንስሐ የተመለሰ 18ኛ. ያስቲኖስ፤ የሚፈርድና የሚበይን 19ኛ. ጥልያኖስ፤ ያላመኑ ሰዎችን የሚገስጽ 20ኛ. ዑልያኖስ፤ የዚህ ዓለም ጥበብ መምህር የኾነ 21ኛ. ጴርቅላስ፤ በስም አጠራርና በሽምግልና መልካም የኾነ 22ኛ. ኬብያኖስ፤ ተጋዳይ የኾነ 23ኛ. ጴጥሮስ፤ የጠራ የባሕርይ ዕንቊ 24ኛ. ጰኵንዮስ፤ የሮምያ ሹም 25ኛ. ሐናንያ፤ የዋህና ሽንገላ የሌለው 26ኛ. ሐሊባኖስ፤ ጾምና ጸሎትን የሚወድ 27ኛ. ኤስያኖስ፤ በመንፈስ ቅዱስ ጎልማሳ የኾነ 28ኛ. ኤልያብ፤ በረኛና የሰማዕት መጀመሪያ፡፡ ሰላም ለዘአዕረፉ ምስሌኪ ፳ወ፯ቱ ሰማዕታት፤ ረድኤቶሙ ትረድ ላዕሌየ ዘምስለ ብዙኅ ምሕረት፡፡ ወኀበ ሀለወ ስሞሙ ምስለ ስምኪ ቅድስት፤ ዓዲ ኢይቅረብ አርሴማ ሕማመ ብድብድ ወሞት፤ በኵሉ አዝማን ወበኵሉ ዓመታት፡፡ የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔዓለምና ደ/ትጉሃን ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ፡፡ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w https://t.me/medihanaelem