cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ሐያእ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሰይጣንን እርምጃዎች አትከተሉ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች የሚከተል ሰው (ኀጢአትን ተሸከመ)፡፡ እርሱ በመጥፎና በሚጠላ ነገር ያዛልና፡፡ በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ ከናንተ አንድም ፈጽሞ ባልጠራ ነበር፡፡ ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያጠራል፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡ ኑር:21 Any comment @Haayhabot ላይ ያገኙናል

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
206
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ለውዷ እህቴ ውድ ምክር ፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦ በመጽሐፉ ውስጥ መርየምንም ከቤተሰቧ ወደ ምሥራቃዊ ስፍራ በተለይች ጊዜ (የሆነውን ታሪኳን) አውሳ፡፡ فَاتَّخَذَتْ مِن دُونِهِمْ حِجَابًا فَأَرْسَلْنَا إِلَيْهَا رُوحَنَا فَتَمَثَّلَ لَهَا بَشَرًا سَوِيًّا ከእነሱም መጋረጃን አደረገች፡፡ መንፈሳችንምም (ጂብሪልን) ወደርሷ ላክን፡፡ ለእርሷም ትክክለኛ ሰው ሆኖ ተመሰለላት፡፡ قَالَتْ إِنِّي أَعُوذُ بِالرَّحْمَٰنِ مِنكَ إِن كُنتَ تَقِيًّا «እኔ ከአንተ በአልረሕማን እጠበቃለሁ፡፡ ጌታህን ፈሪ እንደ ሆንክ (አትቅረበኝ)» አለች፡፡ ✅ተመልከቺ እህቴ የአርአያሽን መርየም ጥግ የደረሰ ኢማን የሞላው ምላሽ : በዛ በረሀ ሰው ዝር በማይልበት: መልከ መልካሙ ጅብሪል በሰው ተመስሎ ገና ሳይቀርባት ባእድ ሰው በመሆኑ ብቻ አላህን ምትፈራ ከሆንክ አትቅረበኝ: በአረህማኑም እጠበቃለው ስትል ክብሯን የጠበቀችው። ታድያ ለምን አንቺስ ብትሆኚ hi እያለ በጓሮ በረ ሚሽሎከለከውን የሸይጣን ጓደኛ : በአረህማኑ እጠበቃለው እያልሽ የመርየምን ሱና ሀይ አታደርጊም !? -------------------- mohammed ebnu seid ----------------------------- 🍀🍀🍀 በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን! ➢👇👇👇 @Haayha
نمایش همه...
〽️ ልበ ሰፊው ሕጻን.....መገሰጫ ይሆን ዘንድ ሰይዲ ማሊክ ኢብን ዲናር በአንድ ህፃን ልጅ በኩል እያለፉ ነበር።ይህ ህፃን መሬት ላይ ያለን አቧራ እየዘገነ ይጫወታል።አንዴ ይስቅና አንዴ ያለቅሳል። ማሊክ ኢብን ዲናር ይህንን ህጻን ሰላም ልበለው አልበለው በሚል አንገራግረው በመጨረሻም ውስጣቸው ውንዲህ ትላቸዋለች °ረሱላችንኮ ህፃን አዋቂውን ሁላ ሰላም ይሉ ነበር ° ረሱላችን ሰላምተኛ እንደነበሩ ሲያስታውሱም ሰላምታ ያቀርቡለታል። ህፃኑም °°በአንተም ላይ ሰላም ይስፈን ያ ማሊክ ኢብን ዲናር°° ብሎ ከነስማቸው ይመልስላቸዋል። ማሊክ ግራ በመጋባት °°አንተ ልጅ ስሜን እንዴት ልታውቅ ቻልክ! °° ብለው ይጠይቁታል። መለሰላቸው °°ማሊክ ሆይ ያ በዐለመል ሩህ(ከስነ ፍጥረት በፊት በነበረው የሩህ ስብስብ) ላይ ያገናኘን ህያው የሆነ ጌታ አሳወቀኝ°° ማሊክ አግራሞታቸው ጨመረ °°አንተ ልጅ እስኪ ንገረኝ የነፍስ እና የዐቅል(ጭንቅላት) ልዩነት ምንድነው?°° °° ነፍስ ማለት ቅድም እኔ ላይ ሰላምታን ከማቀረብ ያገደችህ ኩራተኛ ስትሆን ዐቅል ደግሞ ሰላምታ ማቅረብ እንዳለብህ ያስታወሰችህ ናት °° ማሊክ ኢብን ዲናር ደንገጥ አሉ። °°እሺ የመሬቱን አቧራስ ምን ገዶህ ነው እያቦነንክ የምትጫወትበት?°° ብለው ጠየቁት °°ያ ማሊክ ከአፈር ተፈጥሬአለሁ ወደርሷም ተመላሽ ነኝ፡ታዲያ አሁን ባቦናት ምን ይገርምሃል?°° ማሊክም መለሱ °°ገባኝ ገባኝ ልጄ።እሺ አንዴ እየሳቅህ አንዴ የምታለቅሰውስ ለምንድነው ልጄ?°° °°የአሏህን ምህረት ሳስብ በደስታ እስቃለሁ።አሳማሚ ቅጣቱ በታወሰኝ ግዜም በፍርሃት እንባዬን አፈሳለሁ°° ማሊክ በዚህ ህጻን ልጅ አስተዋይነት እየተደመሙ °° ገና ልጅ አይደለህ እንዴ ምን ያስፈራሃል? ምንስ ያስለቅስሃል°° ብለው በጉጉት አይኖች ጠየቁት አሏህ ይባርክህ አንተ አንባቢ! የህጻኑን መልስ ከልብህ አስተንትን °°ያ ማሊክ እኔ እናቴን አየኋት! አዎ እናቴን እሳት እያነደደች ምግብ ስታበስል አየኋት።ትልቁን ማገዶ አታነደውም ከሥሩ ትናንሽ ማገዶዎችን ብታስቀምጥለት እንጂ°° እኛስ ወጣቶች የጀሀነም ትናንሽ ማገዶ ከመሆን የሚከለክለን ምን ይሆን? ያ አሏህ እዝነትህን! እኛ በዳዮች ነን አንተው ከቅጣትህ ጠብቀን! @tewjihat
نمایش همه...
እህቴዋ ካለ እውቀት አትደርሽም! ውድ እህቴ ሆይ! ኢስላም ከማንኛውም ነገር በፊት ዲናዊ ዕውቀትን በመገብየት ላይ አደራ ይላል፡፡ ምክንቱም የምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ዕውቀትን መሰረት ያላደረጉ ከሆነ ከልማቱ የምንዘፈቅበት አዘቅት ያመዝናል፡፡ አንዳንዴም በኛ ሳይገደብ የኛው የጥፋት ረመጥ ይቀጥልና ሌሎችን እኛ የሰመጥንበት አዘቅጥ ውስጥ እንዲዋኙ የጥፋት ጀልባ እና መቅዘፊያ እንድንሆን ያደርገናል፡፡ ያለነው በዱንያ አለም ነውና ብልሀት እና ጥንቃቄን ከዕውቀት ጋር አጠምረን ካልተጓዝን ወደ ስኬት አንደርስም!! በማስከተል መልዕክቱ እህቴም ልብ ላይ ተፅዕኖ ያሳድር ዘንድ የተወሰኑ መረጃዎችን ከቁርአንና ሀዲስ እያጣቀስኩ መልዕክቴን እቀጥላለሁ... ከቁርአን፦ ስለ እውቀትን ፋይዳዎችና ስለ አዋቂዎች ደረጃ ዓዋቂው አምላካችን ስለ እውቀት ባለቤቶች ከፍ ያለ ደረጃ ዓዋቂዎች በሚገነዘቡት መልኩ እንዲህ ይላል፡- يَرْفَعِ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا مِنكُمْ وَالَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ دَرَجَاتٍ [٥٨:١١] ‹‹«አላህ ከናንተ እነዚያ ያመኑትንና እነዚያ ዕውቀት የተሰጡትን በደረጃ ከፍ ያደርጋል»››(ሙጃደላህ፡11) የዲን ዕውቀትን የቀሰሙ ዓዋቂዎችን አንፀባራቂ ፈርጥነት በአንቀፁ ፍንትው ተደርጎ ተወስቷል፡፡ ታላቁ ሶሃብይና የቁርአን ተፍሲር ዓዋቂ ዓብደላህ ኢብኑ ዓባስ እንዲህ ሲል የቁርአን አያውን የሚያጠናክርና የዓዋቂዎችን ደረጃ የሚያጎላ ንግግር አክሏል፡- «የተማሩ ሰዎች ደረጃ ከተራው ሙዕሚን ሰባት መቶ እጥፍ ይበልጣል፡፡ ከአንዱ ደረጃ ወደ ሌላ ደረጃ ያለው ርቀት የአምስት መቶ ዓመት ርቀት ይሆናል፡፡» በሌላም ቁርአን አንቀፅ አላህ እንዲህ ይላል፡- إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ [٣٥:٢٨] ‹‹«አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው»››(ፋጢር፡28) እንዴታ! የማያውቁትን አካል እንዴት ተገቢውን ፍራቻ ይፈሩታል ጃል! ለዚያም ሲሉ መልዕክተኛው (ﷺ) እንዲህ አሉ፡- ‹ ‹ «ዕውቀትን ቅሰሙ አላህን የምትፈሩት ባወቃችሁት ልክ ነውና፡፡»›› አላህ መልዕክተኛው (ﷺ) እንዲጨምርላቸው እንዲጠይቁት ያዘዘው ብቸኛ ነገር ዕውቀት ነው! ከየት አመጣኸው ትይኝ ይሆናልና ማስረጃውን :- وَقُل رَّبِّ زِدْنِي عِلْمًا [٢٠:١١٤] ‹‹«ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትን ጨመርልኝ በል»›› (20፡114) ለዕውቀቱ ገደብ የሌለው ሁሉን ዓዋቂ ከሆነው ጌታ ቃል ቁርአን ይህን ያክል የጥቂት ጥቂት ግን የገዘፉ መልዕክት ያላቸው አንቀፆች ካየን በተጨማሪ ደግሞ ከተወዳጁ መልዕክተኛ (ﷺ) አይጠገብ ንግግሮች የተወሰኑ እንቋዳሰ ዘንድ ወደ ቀጣይ ደረጃ እንለፍ አላህ ያግዘን… ከሀዲስ፦ ከታላቁ ሶሃብይ ሙአውያ ኢብኑ አቢ ሱፍያን እንደተወራው የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹«አላህ መልካም የሻለትን ሰው የዲን ግንዛቤ ይሰጣዋል» ›› (አል-ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል) ልብ በይ እህቴ! የዲን ዕውቀትና ግንዛቤ አላህ የሚሰጠው መልካም ለሻለትና ለወደደው ነው፡፡ ምንኛ ታላቅ እድል ነው! አላህ ይውደደን! መልካምም ከሻላቸው የዲን ግንዛቤ ከሰጣቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን! በሌላም ሀዲስ ዕውቀትን ከመቅሰም እንዳንቦዝን ፈዘዝ ቀዘዝ ቆረጠኝ ፈለጠኝ አያልን እንዳንዳከም የሚያግዝ ልጅ አዋቂ ሴት ወንድ ሳይሉ ሁሉን ያቀፍ መልዕክት ነብዩ (ﷺ) አስተላልፈውልናል፡- «ዕውቀትን መፈለግ በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዱታ ነው»›› (አልባኒ ሰሂህ ብለውታል) ውድ እህቴ! ሸሪኣዊ ዕውቀትን ከመፈለግ እድሜ ፆታ መሰል ምክንያቶች ፈፅሞ ሊያግዱሽ አይገባም!ሌላው ዒልም የወንዶች ስራ ነው እኔን አይመለከተኝም ብለሽ ራስሽን እንዳትሸነግይ! አደራ እንዳትሳነፊ! በዲናችን ላይ በወርቅ የሚፃፍ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ያለፉ እንስቶችን አትዘንጊ በዚህ ረገድ ታላቋ አርዓያሽ ውዷ እናታችን ዓኢሻ ልትሆን ይገባል፡፡ የሷን ጀብድ የኔ ደካማ ብዕር ለጊዜው ለመግለፅ ከበዳትና በይደር አለፈችው! ሴትነትሽ ክብር እንጂ የደካማነት መገለጫ አይደለም! ይልቁኑ ነቃ ብለሽ ልትተጊ ይገባል፡፡ ራስሽንም ለዚህ ታላቅ ተግባር እንድታዘጋጂ አደራ እልሻለሁ፡፡ ዕውቀት ለመቅሰም በምታደርጊው ጥረት ድካም ብጤ ተሰምቶ ተራራን የመውጣት ያክል ካሰላቸሽ ይህችን ሀዲስ አስታውስሻለሁ፡- ‹«ዕውቀትን ለመፈለግ መንገድ የጀመረ አላህ ወደ ጀነት የሚያስገባውን መንገድ ይመራዋል!» ሙስሊም ዘግበውታል ታዲያ ከዚህ በላይ ብርታት የሚለግስ ማነቃቂያ አለን? ጀነት እኮ ነው! በሌላም ሀዲሳቸው መልዕክተኛው (ﷺ) ሌላ ብስራት አክለውልሻል፡- «ዕውቀትን ለሚፈለግ ሰው መልዕክቶች ክንፎቻቸውን በደስታና በእርካታ ዝቅ ያደርጉለታል» አህመድ ዘግበውታል እንግዲህ ይህች ከውቂያኖስ በመርፌ ተነክራ እንደወጣች ውሃ ስለ ሸሪያዊ ዕውቀት አስፈላጊነት የምትዘክር አጭር ማስታወሻ ናት፡፡በበለጠ ለመገንዘብ ከውድ ጊዜሽ ቆርሰሽ በመስጠት ዕውቀትሽን ለማዳበር እና ዲንሽን ለመገንዘብ እንድትጥሪ የማንቂያ ደውል ለማሰማት ያህል ነው፡፡ አላህ ለጥሪው ጆሮ ከሚሰጡ መልካሞች ያድርግሽ! መሰነባበቻ!… ታላቁ ሶሃብይ ኢብኑ መስዑድ እንዲህ ይላል፡- «ዕውቀት በአላህ ከመወሰዷ በፊት አካብቷት» ይህም ማለት አላህ የእውቀት ባለቤቶችን (ዑለማዎችን) ወደ አኼራ ከመውሰዱ በፊት ማለት ነው፡፡ ወዷ እህቴ! አሁንም እድልሽን ተጠቀሚና ለዒልም ውድ የምትይውን ግዜ ስጪ። በአላህ እርዳታ ስኬት ካንቺ ጋር ትሆናለች። መልካም የዒልም ፍለጋ ጊዜ! ተንቢሀት፦ @tewjihate
نمایش همه...
//ሙስሊም ወንድሙ አደጋ ሲደርስበት መደሰት// «በሙስሊም ወንድምህ መከፋት አትደሰት አሏህ እሱን ይመረውና አንተን ይፈትንሃልና» « ወንድሙን በወንጀል ያነወረ ራሱ ሳይተገበርው ኣይሞትም» የአላህ መልዕክተኛ ሙሀመድ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ሀዲሱን ሳሂህ @Haayha
نمایش همه...
ምን ብታይ ድካሜ አይሎ፣እንደ ሰው ችዬ ባልፀና፤ አያስችለኝም ሲነኩ ያመኛል ገና ለገና! ምን ልሣን ባይኖረኝ ፣ ሚደመጥ ለሁሉ ደርሶ፤ ፊዳ መሆኑ ክብሬ ነው በፍቅር መሞት ስለርሶ! ሰለዋቱላህ ወሰላሙን አለይከ ያ ነብዩላህ!❤️ اللهم صّلِ وسَلّمْ عَلۓِ نَبِيْنَامُحَمد @Haayha @tewjihate
نمایش همه...
ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ (ረዐ) ... የመልካም ትዳር ተምሳሌት* በሞባይል ስልኬ ላይ የባለቤቴን ስም ኸዲጃ ብዬ ነበር save ያደረኩት። ለሷ ግን አልነገርኳትም ነበር። አንድ ቀን ድንገት ስልኬን ስትጎረጉር ኸዲጃ ከምትባል ሴት ጋር በተደጋጋሚ መደዋወሌን ተመለከተች። በንዴት አይኖቿ ቀልተውና ደም ስሯ ተወጥሮ “ኸዲጃ ማን ናት?” አለችኝ። የደነገጥኩ አስመስዬ ዝም ብዬ አየኋት። በዚህን ጊዜ ንዴትዋ ጨምሮ ጮክ ብላ መናገር ጀመረች። አትናገርም? ......... አትመልስልኝም?...... ........................ አንተን መስሎኝ የማናግረው! ............... .......... ማን ናት ኸዲጃ? እያለች የሸሚዜን ኮሌታ ይዛ ትወዘውዘኝ ጀመር። ሳይታወቃት እንቅ አደረገችኝ። ኸ.....ዲ......ጃ ማን ናት? በል ፍጠን ተናገር! ለምን እሷን እራሷን ማን እንደሆነች አትጠይቂያትም? አልኳት እጆቿን ለማስለቀቅ እየሞከርኩ። እሺ እንደሱ ሳይሻል አይቀርም . . . እኔው እራሴ እጠይቃታለሁ በማለት ወደ ኸዲጃ ደወለች። የራሷ ስልክ ሲጠራ ሰምታ ደዋዩን ስታጣራ ባለቤቷ (እኔ) መሆኑን አወቀች። . . . ግራ በተጋባ ሰው ስሜት “ታዲያ ለምን? እኔ ስሜ ኸዲጃ አይደለም” አለች። ባህሪሽ፣ እዝነትሽ፣ ለኔ ማሰብሽ፣ መጨነቅሽ፣ ፍቅርሽ፣ ቤሳ ቤስቲን ሳይኖረኝ እኔን ለማግባት መፍቀድሽ፣ ..................... አንቺ ለኔ በዱኒያ ላይ ያለሽኝ መተኪያ የሌለሽ ሀብቴ ነሽ፡ አንቺ ለኔ ክብሬ፣ ፍቅሬ፣ መሰተሪያዬ፣ የህይወት አጋሬ ነሽ። በአላህ ፍቃድ በፊርደውሰል አእላ ውስጥም ሚስቴ እንድትሆኚ እፈልጋለሁ። . . . እናታችን ኸዲጃ (ረዲየላሁ አንሃ) የፍቅርና የመልካም ትዳር ተምሳሌት ስለሆነች ነው በርሷ ስም የሰየምኩሽ አልኳት። . . . አይኖቿ እምባ እንዳቀረሩ “እሺ በአላህ ፍቃድ ሁሌም መልካም የትዳር አጋርህ ለመሆን እጥራለሁ አንተም ጥሩ በመሆን አግዘኝ” አለችኝ። =============== =========== አንቸኩል!!! ከመጠርጠር እንቆጠብ!!! ምንጭ:- ከፈስቡክ መንደር የተገኘ @Haayha @tewjihate
نمایش همه...
እህቶች ሆይ!! በሚጥል በሽታ የተጠቃች አንዲት ታላቅ ሴት ነበረች — በነብዩ صلى الله عليه وسلم ዘመን ። ነብያችን ዘንድ በመቅረብ ያንገላታትን በሽታ በተመለከተ አላህን እንዲለምኑላት ጠየቀቻቸው ። መልእክተኛውም إن شئت صبرت ولك الجنة وإن شئت دعوت الله أن يعافيك " ከፈለግሽ ታገሺና ላንቺ ጀነት አለልሽ። ከፈለግሽ ደግሞ ጤና እንዲለግስሽ አላህን ልለምንሽ " አሏት ። ይህቺ አኺራዋን ከዱንያዋ— ለዛውም አሳሳቢ ከሆነው ጤናዋ— ያስቀደመች ሴት በሽታዋን በተመለከተ " እታገሳለሁ " አለች ። ልብ በሉ እህቶች! ! "በበሽታው ምክንያት መውደቄን እታገሳለሁ" ነበር አባባሏ! — ይህንን ከባድ በሽታ እታጋሳለሁ ነበር ነገሯ ! ! ነገር ግን ልትታገሰው የከበዳት አንድ ጉዳይ ነበርና ነብዩን እንዲህ ስትል ጠየቀች ፣ " በምወድቅ (በሽታው በሚጥለኝ ግዜ) ሰውነቴ ይጋለጣልና አካሌ እንዳይራቆት አላህን ለምኑልኝ አለች ። አንዳንድ ዘገባዎች ላይ እንደተብራራው ይህቼ ሴት ከነብዩ ዱዓ በሇላ በሽታዋ ቢጥላትም ሰውነቷ በፍፁም አይጋለጥም ነበር— በነብዩ ዱዓ በረካ። ይህች ታላቅ ሴት በበሽታዋ ምክኒያት መደበቅ ያለበት አካሏ ቢጋለጥ እንኳን ነገሩ በፈቃዷ የተከሰተ አይደለምና የምትጠየቅበት ወንጀል አይደለም ። ከዚህም ጋር ጉዳዩ ይህን ያህል አሳስቧት ነበር — አላህን መፍራት ማለት ይሄ ነው! ቀደምት ምርጦቻችንና ተምሳሌቶቻችን እንዲህ ነበሩ!! ታዲያ ምን ነው?!.... አንዳንድ እህቶች በዳዕዋ ስም ተቀባብተው ለጅምላ እይታ መቅረባቸው? ! ምን ነው ታዲያ አንዳንድ እህቶች ተኳኩለውና መደበቅ ያለበትን አካል ገላልጠው አደባባይ መውጣታቸው? ! ኧረ አይበጅም እህቶች !! አላህን ፍሩ! ! ይሄ ገላ ከመፈራረሱ በፊት ይህንን ገላ ወደሰጣችሁ አላህ ተመለሱ! ! ━════ ❁❁❁ ════━ •┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈•  JOIN us↓ ↓ ↓ @tewjihate 🕊...............🍃🌹🍃..................
نمایش همه...
የምእመናን እንስቶች ሞዴል የሆኑት (የረሱል ሚስቶች) ይሄን ቁርአናውይ መርህ እንዲከተሉ ታዘዋል ❗ ትእዛዙ ማንኛዋንም አማኝ እንስት ይመለከታል ፡ ለቁርአን ለአላህ ታዛዥ የሆነች አማኝ እንስት በፍፁም የቁርአንን መመሪያ አትጥስም ❗ ሴት ልጅ ፡- ቤቷ ውስጥ መርጋቷ የቁርንን መመሪያ ተግበራዊ ማድረጓን ያመላክታል ❗ ሴት ልጅ፡- ቤቷ ውስጥ የማትረጋ ከሆነ ደግሞ (የጃሂልያ) የማሃይማንነቱን ዘመን በራሷ ላይ ማንፀባረቋን ነው ሚያሳየው ❗ ሴቶች ሆይ ! ባካችሁ የአላህን ትእዛዝ አትጣሱ ! ስለናንተ ከማንም በላይ አዋቂ የሆነው ጌታችሁ አላህ የመረጠላችሁ ቦታ (ቤታችሁ) ይስፋችሁ ❗ መገላለጥና ብሎም በአደባባይ በየሚዲያው መውጣት ይሄን ቁርአናዊ መርህ የአላህን ትእዛዝ መጣስ ነው ❗ ሴቶች ሆይ ሞዴላችሁን እወቁ ፣ አርአያችሁን እወቁ ❗ የናንተ ሞዴሎች ሊሆኑ የሚገቡት እነዚያ የውዱ ነብያችሁ ሚስቶች ናቸው ❗ እናንተ ከነሱ በበለጠ አላህን ልትፈሩት አትችሉም ❗ እነሱን የሰፋቸው ጎዳና እናንተንም ይስፋችሁ ❗ @Haayha
نمایش همه...
ምድር ላይ ብዙ ነገር ልትወድ ትችላለህ አማኝ ስትሆን ግን ከአላህ የሚበልጥብህ ምንም ነገር አይኖርም። "እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ ይበልጥ የበረቱ ናቸው፡፡" (2፡165) https://t.me/Haayha
نمایش همه...
ሐያእ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሰይጣንን እርምጃዎች አትከተሉ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች የሚከተል ሰው (ኀጢአትን ተሸከመ)፡፡ እርሱ በመጥፎና በሚጠላ ነገር ያዛልና፡፡ በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ ከናንተ አንድም ፈጽሞ ባልጠራ ነበር፡፡ ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያጠራል፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡ ኑር:21 Any comment @Haayhabot ላይ ያገኙናል

ለውዷ እህቴ ውድ ምክር ፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦ በመጽሐፉ ውስጥ መርየምንም ከቤተሰቧ ወደ ምሥራቃዊ ስፍራ በተለይች ጊዜ (የሆነውን ታሪኳን) አውሳ፡፡ فَاتَّخَذَتْ مِن دُونِهِمْ حِجَابًا فَأَرْسَلْنَا إِلَيْهَا رُوحَنَا فَتَمَثَّلَ لَهَا بَشَرًا سَوِيًّا ከእነሱም መጋረጃን አደረገች፡፡ መንፈሳችንምም (ጂብሪልን) ወደርሷ ላክን፡፡ ለእርሷም ትክክለኛ ሰው ሆኖ ተመሰለላት፡፡ قَالَتْ إِنِّي أَعُوذُ بِالرَّحْمَٰنِ مِنكَ إِن كُنتَ تَقِيًّا «እኔ ከአንተ በአልረሕማን እጠበቃለሁ፡፡ ጌታህን ፈሪ እንደ ሆንክ (አትቅረበኝ)» አለች፡፡ ✅ተመልከቺ እህቴ የአርአያሽን መርየም ጥግ የደረሰ ኢማን የሞላው ምላሽ : በዛ በረሀ ሰው ዝር በማይልበት: መልከ መልካሙ ጅብሪል በሰው ተመስሎ ገና ሳይቀርባት ባእድ ሰው በመሆኑ ብቻ አላህን ምትፈራ ከሆንክ አትቅረበኝ: በአረህማኑም እጠበቃለው ስትል ክብሯን የጠበቀችው። ታድያ ለምን አንቺስ ብትሆኚ hi እያለ በጓሮ በረ ሚሽሎከለከውን የሸይጣን ጓደኛ : በአረህማኑ እጠበቃለው እያልሽ የመርየምን ሱና ሀይ አታደርጊም !? -------------------- ----------------------------- 🍀🍀🍀 በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን! 👇👇👇 @tewjihate
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.