cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

🇪🇹✝️የኦርቶዶክስ ንግስ በአላት ✝️🇪🇹

ትምህርተኦክቶዶክስ በዚህ ቻናል ከተለያዩ ምንጮች የምናገኛቸዉን አስተማሪ ብለን ያሰብናቸውን #ሀይማኖታዊ ትምህርቶች #ስብከቶች #ታሪኮች #መዝሙሮች#የቤተክርስትያን ዜናዎች#ሀይማኖታዊ ፊልሞች ወ.ዘ.ተ የምናቀርብ ይሆናል ለሌሎች በማጋራት የበኩልዎን እንዲወጡ በልሉል እግዚአብሄር ስም እንጠይቃለን። #ትምህርተኦርቶዶክስ @tmhrteorthodox

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 692
مشترکین
-124 ساعت
-67 روز
+1730 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

​​እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ #መዝ. 86፥1 “መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፡- መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮችናቸው” ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም በእመቤታችን ልደት ምክንያትዛሬ ደስ ሆነ፡፡ በግንቦት 1 ቀን 5ሺ ከ5መቶ የመከራው ዘመን ሊያልቅ 15 ዓመታት ሲቀሩት/ ሊባኖስ በሚባል ተራራ ከፀሐይ  የምታበራ ሴት ልጅ ተወለደች፡፡ ይህቺውም ፍጥረት ሁሉ ደቂቀ አዳም ሁላቸው ተስፋ ሲያደርጓትና ሲጠባበቋት የነበረች የድኅነታቸው ምልክት እመቤታችን ናት፡፡ ሶሪያዊው ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬምም  “አክሊለ ምክሕነ ወቀዳሚተ መድኀኒትነ፡፡ወመሠረተ ንጽሕነ ኮነ በማርያም ድንግል:- የመመኪያችን ዘውድ የደኅንነታችን  መጀመሪያ የንጽሕናችንም መሠረት በድንግል ማርያም ሆነልን” በማለት መናገሩ ስለዚህ ነው፡፡ አክሊል ምክሐነ አላት ይህም አክሊል የወዲህኛው፣ ምክሕ የወዲያኛው ነው። ከነገሥታት መካከል እንደ ዳዊት የከበረ የለም። ምንም እንኳን ቅዱስ ዳዊት የከበረ ቢሆን የመመኪያችንን ዘውድ ማምጣት አልተቻለውም፡፡ ወቀዳሚተ መድኀኒትነ አላት፡- ቀዳሚተ የወዲህኛው መድኀኒት የወዲያኛው ነው፡፡ከመሳፍንት ወገን የሚሆን ኢያሱ ምንም የስሙ ትርጓሜ መድኃኒት ቢሆን የደኅንነታ መሆን አልተቻለውም፡፡ ወመሠረተ ንጽሕነ አላት:- መሠረት የወዲህኛው፤ ንጽሕ የወዲያኛው ከነቢያተ እግዚአብሔር ወገን የሚሆን ኤልያስ በድንግልና በንጽሕና መኖሩ የሚታወቅ ነው፡፡  ነገር ግን ምንም ንጹሕ ድንግል ቢባል የንጽሕናችንመሠረት መሆን አልተቻለው። የመመኪያችን ዘውድ፣ የደኅንነታችን መጀመሪያ፤ የንጽሕናችን መሠረት ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፤” በማለት ተናግሯል። በእርሷ ምክንያትነት መድኀኒዓለም  የሚፈጽምልንን ካሳነቢያትና የቀደሙ አበው ሁሉ  የእርሷን መወለድ በናፍቆት ሲጠባበቁ ነበር። ከነቢያት አንዱ የሆነ  ኢሳይያስም “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርዘርን ባያስቀርልን  ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንነ  እንደ ጎሞራም በመሰልነ ነበር፡፡” በማለት መናገሩ በእርሷ መገኘት  ከጥፋት መዳናችንን ሲገልጽ ነው፡፡  #ኢሳ 1፥9 የቦንጋ ፈ/ሕ/አቡነ ተክለሃይማኖት የበገና ት/ቤት ትምህርት ክፍል ። https://t.me/sratebetkrstyane
نمایش همه...

✝ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙሮችን በድምፅ / በኦድዮ ለማግኘት ከስር ( ክፈት ) ሚለውን ይጫኑ።
نمایش همه...
ክፈት
ለመ🀄️ላ🀄️ል
Free FaceSwap🤖
Best DeepNude🙈
نمایش همه...
💒 ስርዓተ ቤተ-ክርስቲያን 💒
⛪️ የኦርቶዶክስ ንግስ በአላት ⛪️
✝ መንፈሳዊ ትምህርት ✝
✝ ኪነ ጥበብ ብቻ ✝
✝ በማለዳ ንቁ !፪ ✝
✝ ታሪክ ዘ ኢትዮጵያ ✝
💠 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 💠
✝ ትንሳኤ ዘኢትዮጵያ ✝
✝ ዘ ተዋሕዶ ✝
🌷Harmee Tewaahidoo🌷
✝ ቤተ_ልሔም ~ Betelehem
✝ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ✝
💒 ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር 💒
💒 መዝሙረ ማህሌት 💒
🇨🇬  ደጉ ሳምራዊ  ✝
💒 ኑ በብርሀኑ እንመላለስ 💒
🔔 የተዋሕዶ መዝሙሮች 🔔
💠 በዓላት 💠
🖱መንፈሳዊ ፊልም 🖱
🖱መንፈሳዊ ግጥም 🖱
📯 ጥያቄዎች 📯
🔔 መዝሙር 🔔
🛰 EOTC Bot 🛰
🛰 Bot Official 🛰
█     ✞    𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒     ✞     █
🔔 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙሮች 🔔
‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
🏆 የተ҈ ዋ҈ ህ҈ ዶ҈   ቻናሎች መገኛ 🏆
📌 ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ 📌
📩 ለመመዝገብ 📩
Free FaceSwap🤖
Best DeepNude🙈
Photo unavailableShow in Telegram
نمایش همه...
💒 ስርዓተ ቤተ-ክርስቲያን 💒
⛪️ የኦርቶዶክስ ንግስ በአላት ⛪️
✝ መንፈሳዊ ትምህርት ✝
✝ ኪነ ጥበብ ብቻ ✝
✝ በማለዳ ንቁ !፪ ✝
✝ ታሪክ ዘ ኢትዮጵያ ✝
💠 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 💠
✝ ትንሳኤ ዘኢትዮጵያ ✝
✝ ዘ ተዋሕዶ ✝
🌷Harmee Tewaahidoo🌷
✝ ቤተ_ልሔም ~ Betelehem
✝ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ✝
💒 ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር 💒
💒 መዝሙረ ማህሌት 💒
🇨🇬  ደጉ ሳምራዊ  ✝
💒 ኑ በብርሀኑ እንመላለስ 💒
🔔 የተዋሕዶ መዝሙሮች 🔔
💠 በዓላት 💠
🖱መንፈሳዊ ፊልም 🖱
🖱መንፈሳዊ ግጥም 🖱
📯 ጥያቄዎች 📯
🔔 መዝሙር 🔔
🛰 EOTC Bot 🛰
🛰 Bot Official 🛰
█     ✞    𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒     ✞     █
🔔 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙሮች 🔔
‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
🏆 የተ҈ ዋ҈ ህ҈ ዶ҈   ቻናሎች መገኛ 🏆
📌 ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ 📌
📩 ለመመዝገብ 📩
Free FaceSwap🤖
Best DeepNude🙈
🔴 #ማክሰኞ_የትምህርት_እና_የጥያቄ_ቀን ይህ ቀን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰኞ በተናገረው ባደረገው ላይ አይሁድ ጥያቄ ያቀረቡበት እርሱም መልስ በመስጠት ያስተማረበት ዕለት ነው በዚህም ምክንያት የጥያቄ እና የትምህርት ቀን በመባል ይታወቃል፡፡ ሰኞ ቀን ጌታችን በረገማትን በለስ  መድረቅ ሐዋርያት ሲደነቁ እምነት ያለው ሰው ሁሉን ማድረግ እንደሚችል ያስረዳበት ዕለት ነው፡፡ ‹‹ ማለዳም ሲያልፉ በለሲቱን ከሥርዋ ደርቃ አዩአት ጴጥሮስም ትዝ ብሎት መምህር ሆይ፥ እነሆ፥ የረገምሃት በለስ ደርቃለች አለው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ በእግዚአብሔር እመኑ እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት። እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም። ››ማር 11፥20-26 እያለ ያስተማረበት ዕለት ስለሆነ የትምህርት ቀን ይባላል ሌላው ይህ ዕለት ጌታችን  ሰኞ ዕለት  ካደረጋቸው ነገሮች ተነስተው አይሁድ ጥያቄ ያቀረቡበት ዕለት ነው ‹‹ ወደ መቅደስም ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሎች ወደ እርሱ ቀረቡና በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? አሉት። ኢየሱስም መልሶ፦ እኔ ደግሞ አንዲት ነገር እጠይቃችኋለሁ፤ እናንተም ያችን ብትነግሩኝ እኔ ደግሞ እነዚህን በምን ሥልጣን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ፤ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይ ወይስ ከሰው? አላቸው። . . . ›› /ማቴ 21 ፥23- 27/ ይህ ጥያቄ ጌታችን ሲያደርጋቸው የነበሩ ተአምራትና ድንቅ ድንቅ ሥራዎች የካህናት አለቆችን ስላስቀኗቸው ጌታችንን ከሮማ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋር ለማጋጨት የቀረቡት ጥያቄ ነበር ጌታችን በቤተ መቅደስ የነበረውን ገብያ ስለበተነው የነጋዴዎቹን  መደባቸውን ስለገለበጠ ነጋዴን ማባረርና መደብን ማስለቀቅ መንግሥታዊ ሥራ ነውና በማን ሥልጣን አደረከው ብለው ጠየቁት ጌታችን ‹‹በራሴ ሥልጣን›› ቢላቸው ጸረ መንግሥት አቋም አለው በማለት ከሮማ መንግሥት ዘንድ ለማሳጣት ነበር ዕቅዳቸው ጌታችን ግን የፈሪሳውያንን ጠማማ አሳብ ስለሚያውቅ ‹‹የዮሐንስ ጥምቀት ከየት ነው? ከሰማይ ነው ወይስ ከምድር?›› ሲል ጠይቋቸዋል፡፡ ጌታችን ፈሪሳውያን ላቀረቡለት ጥያቄ ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጠም ምክንያቱም ጥያቄው ለከሳሾቹ ዓላማ መሳካት አመቺ ሁኔታን ስለሚፈጥር ጥያቄውን በጥያቄ መልሶላቸዋል፡፡ እነርሱም ‹‹ከሰማይ ነው›› ቢሉት ‹‹ለምን አላመናችሁበትም?›› እንዳይላቸው፤ ‹‹ከሰው ነው›› ቢሉት ደግሞ ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ አባት ይፈሩት፣ እንደ መምህር ያከብሩት ነበርና ሕዝቡ እንዳይጣሏቸው ስለፈሩ ‹‹ከወዴት እንደ ሆነ አናውቅም›› ብለው መለሱለት፡፡ እርሱም ‹‹እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም›› አላቸው ከዚህ ታሪክ የተነሳ ይሄ ቀን የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡ https://t.me/tmhrteorthodox
نمایش همه...
🇪🇹✝️የኦርቶዶክስ ንግስ በአላት ✝️🇪🇹

ትምህርተኦክቶዶክስ በዚህ ቻናል ከተለያዩ ምንጮች የምናገኛቸዉን አስተማሪ ብለን ያሰብናቸውን #ሀይማኖታዊ ትምህርቶች #ስብከቶች #ታሪኮች #መዝሙሮች#የቤተክርስትያን ዜናዎች#ሀይማኖታዊ ፊልሞች ወ.ዘ.ተ የምናቀርብ ይሆናል ለሌሎች በማጋራት የበኩልዎን እንዲወጡ በልሉል እግዚአብሄር ስም እንጠይቃለን። #ትምህርተኦርቶዶክስ @tmhrteorthodox

​​​​ሥርዓተ ጸሎት ሰሙነ ሕማማት ከሰኞ እስከ ዕሮብ  ካህናት እያዜሙ እየሰገዱ እኛም እየተቀበልን እያዜምን የምንሰግድበትን   ሥርዓት ለማውቅ እና ለመፈፀም ከስር ያንብቡ ❖ የጸሎተ ሐሙስና የዕለተ ዓርብ ሥርዓተ ጸሎት 👉 ከሰኞ ጀምሮ እስከ ዓርብ ድረስ ባሉት ቀናት ውስጥ  በመጀመሪያ ዲያቆኑ ቤተ ክርስቲያኑን ሦስት ጊዜ ዞሮ ደወል ካሰማ በኋላ መቶ አምሳው ዳዊት ይታደልና ይደገማል፡፡ የሰባት ቀናት ውዳሴ ማርያምና አንቀጸ ብርሃን  እስከ ይዌድስዋ  ድረስ ታድሎ ይደገማል፡፡ ከዚያም “እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ አግዚአብሔር በፍሥሓ ወበሰላም” ተብሎ አቡነ ይደገምና  በዐራቱም ወንጌላት መሠረት ለእያንዳቸው በእየዕለቱና  ሰዓቱ የተመደበውን አቡነ ካህናቱ በቀኝና በግራ እየተፈራረቁ  ይመራሉ፡፡ ካህናቱና ሕዝቡም ይቀበላሉ፡፡ በመቀጠል፡- (ትእዛዝ፡ ሕዝቡ በጸሎት በተሰበሰቡ ጊዜ ጠዋት ወይም በ3፣ በ6፣በ9፣ በ11ሰዓተ መዓልት መጀመሪያ ሕዝቡ እየሰገዱና እየተከተሉ እንዲህ ይበሉ፡፡ ) ✥ "ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም ፡፡" ✥ "አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም፡፡" ✥ " ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም፡፡ " ✥ " ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ፤ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኰቴት ፡፡" ትእዛዝ፡ በዚህ ጊዜ ካህኑ እየተከተሉ አቡነዘበሰማያት ይድገሙ ። ይህን የላይኛውን ጸሎት እያመላለሱ ከአቡነ ዘበሰማያት ጋር 12 ጊዜ ይበሉ ❖ " ለአምላክ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡ ❖ "ለሥሉስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡ ❖ "ለማሕየዊ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡ ❖ "ለዕበዩ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡ ❖"ለእዘዙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡ ❖ "ለመንግሥቱ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡ ❖ "ስለልጣኑ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡ ❖ "ለኢየሱስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡ "ለክርስቶስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡ ❖ "ለሕማሙ  ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡ ❖ "ለመስቀሉ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡ " ትእዛዝ፡- ይህ ሦስት ጊዜ እየተመላለሰ ይባላል፡፡በመጨረሻም የሚከተለውን ሦስት ጊዜ እያመላለሱ ይበሉ፡፡ ❖ "ለከ ይደሉ ኃይል፣ ወለከ ይደሉ ስብሐት ወለከ ይደሉ አኰቴት ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለመ ዓለም" ትእዛዝ፡- ካህኑ ‹ጸልዩ በእንተ ጽንዓ ዛቲ . . .› ብሎ በሚያነብ ጊዜ በየምዕራፉ "እግዚኦ ተሳሃለነ" እየተባለ ይሰገዳል፡፡ ትእዛዝ፡- ከዚህ ሁሉ በኋላ ሕዝቡ የሚከተሉትን ጸሎት በግራና በቀኝ ይበሉ፤ "ክርስቶስ አምላክነ፤ ዘመጽአ ወሐመ በእንቲአነ በሕማማቲሁ ቤዝወነ፤  ንሰብሖ ወናልዕል ስሞ ኅቡረ፤ እስመ ውእቱ ገብረ መድኃኒተ በዕበየ ሣህሉ" (በዐርብ) ዘሐመ ወሞተ በእንቲአነ ይባላል፡፡ ትእዛዝ፡- ቀጥሎም ሕዝቡ በሁለት ክፍል ሆነው የሚከተለውን ጸሎት ሁለት ጊዜ በመከታተል አንድጊዜ በማስተዛዘል ይበሉት፡፡ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤#ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤ #አብኖዲ  ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን #ናይን፣ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን ፤ #ታዖስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤ #ማስያስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤ #ኢየሱስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤ #ክርስቶስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤ #አማኑኤል ናይን፣ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤ #ትስቡጣ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን ትእዛዝ፡- ከዚህ በኋላ ኪርያላይሶን አርባ አንድ ጊዜ ይባላል፡፡ ይኸውም  በአንድ ወገን 20 ጊዜ በሌላው ወገን 21 ጊዜ በጠቅላላው 41 ጊዜ ኪርያላይሶን  ኪርያላይሶን  ኪርያላይሶን  እየተባለ ይሰገዳል፡፡ በመጨረሻ ጊዜ፡- ✥ ስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ (እናመልከው ዘንድ ለፈጠረን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል)፡፡ ✥ ስብሐት ለማርያም እመ አምላክ እግእዝትነ ወመድኃኒትነ (እመቤታችንና መድኃኒታችን ለሆነች ለአምላክ እናት ለማርያም ምስጋና ይገባል)፡፡ ✥ ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ ዕፀ መድኃኒት ኃይልነ ወፀወንነ(ኃይላችን መጠጊያችን ለሆነ ድኅነት ለተገኘበት ለክርስቶስ ምስጋና ይገባል)፤፤ ጸሎተ ሃይማኖትን ሐመ  እስከ ሚለው ድረስ መድገም ነው፡፡  /ከሰኞ እስከ ረቡዕ ይባላል/ #ሼር https://t.me/tmhrteorthodox
نمایش همه...
🇪🇹✝️የኦርቶዶክስ ንግስ በአላት ✝️🇪🇹

ትምህርተኦክቶዶክስ በዚህ ቻናል ከተለያዩ ምንጮች የምናገኛቸዉን አስተማሪ ብለን ያሰብናቸውን #ሀይማኖታዊ ትምህርቶች #ስብከቶች #ታሪኮች #መዝሙሮች#የቤተክርስትያን ዜናዎች#ሀይማኖታዊ ፊልሞች ወ.ዘ.ተ የምናቀርብ ይሆናል ለሌሎች በማጋራት የበኩልዎን እንዲወጡ በልሉል እግዚአብሄር ስም እንጠይቃለን። #ትምህርተኦርቶዶክስ @tmhrteorthodox

የሰሙነ ሕማማት ሰኞ፡- መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.11፤11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ደኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡ በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡ አንጽሆተ ቤተ መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፦ ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በስድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና 5ሺ ከ5መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው #ሼር https://t.me/tmhrteorthodox
نمایش همه...
🇪🇹✝️የኦርቶዶክስ ንግስ በአላት ✝️🇪🇹

ትምህርተኦክቶዶክስ በዚህ ቻናል ከተለያዩ ምንጮች የምናገኛቸዉን አስተማሪ ብለን ያሰብናቸውን #ሀይማኖታዊ ትምህርቶች #ስብከቶች #ታሪኮች #መዝሙሮች#የቤተክርስትያን ዜናዎች#ሀይማኖታዊ ፊልሞች ወ.ዘ.ተ የምናቀርብ ይሆናል ለሌሎች በማጋራት የበኩልዎን እንዲወጡ በልሉል እግዚአብሄር ስም እንጠይቃለን። #ትምህርተኦርቶዶክስ @tmhrteorthodox

❤ ሌሎችም ከዛፍ ጫፍ ጫፉን እየቈረጡ በመንገድ ላይ ያነጥፉ ነበር። ይኽም ዘንባባ ብዙ ምሳሌ ያለው ነው፤ ይኸውም በእስራኤል ያለው ሰሌን፣ ተምር፣ ዘይት ነበርና ያነን ቈርጠው አመስግነውታል፤ ይኽም ምሳሌነት ያለው ነው፤ ይኽም ሰሌን እሾኻማ እንደኾነ ትእምርተ ኀይል ትእምርተ መዊእ አለኽ ሲሉ ነው፤ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ እንደማያቃጥለው ባሕርይኽ አይመረመርም ሲሉ ነበር፡፡ ♥ ዳግመኛም ከሰሌን ዝንጣፊ ጋር ተመሳሳይ ተምር ይዘዋል ይኽም ተምር ልዑል ነው አንተም ልዑለ ባሕርይ ነኽ ሲሉ፤ ፍሬው አንድ እንደኾነ አንተም ዋሕደ ባሕርይ ነኽ ሲሉ፡፡ በእሾኽ የተከበበ ነው ባሕርይኽ አይመረመርም ሲሉ ነበር፡፡ ♥ የዘይት ዛፍ ነው ቢሉ ዘይት ጽኑዕ እንደኾነ ጽኑዐ ባሕርይ ነኽ ሲሉ፤ ብሩህ ነው ብሩሀ ባሕርይ ነኽ በትምህርትኽም የሰውን ልቡናን ታበራለኽ ሲሉ፤ ዘይት መሥዋዕት እንደሚኾን መሥዋዕት ትኾናለኽ ሲሉ ነበር፡፡ ♥ “የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር” በማለት በአርያም መድኀኒት እንደኾነና እግዚአብሔር አብ “የምወድደው ልጄ ይኽ ነው” ብሎ መስክሮለት የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስን የሚያርቅ በረከተ ሥጋን በረከተ ነፍስን የሚያድል መኾኑን ኹሉም መሰከሩለት፡፡ ♥ በእጅጉ የሚደንቀው የ40 ቀን የ80 ቀን ሕጻናት የፈጠራቸው ጌታ በአህያና በውርንጫ ተቀምጦ ባዩት ጊዜ በንጹሕ አንደበታቸው አንደታቸው ረቶላቸው ጌታን ዘንባባ በመያዝ ሲያመሰግኑ በእጅጉ ይደንቅ ነበር፤ ነገር ግን ጸሐፍት ፈሪሳውያን ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን? አሉት፤ ኢየሱስም፦ እሰማለሁ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ የሚለውን ቃል ከቶ አላነበባችሁምን? በማለት በሕጻናት እንደሚመሰገን የነርሱም ጌታ መኾኑን ከዳዊት መዝሙር በመጥቀስ ነገራቸው፡፡ ♥ ሊቁ ያዕቆብ ዘሥሩግ ሰለዚኽ ምስጢር ሲገልጸው ፡- “ፍቅርኽ ከዘባነ ኪሩብ አውርዶ በአህያ ጀርባ ላይ እንድትቀመጥ አስገደደኽ፡፡ ብዙ ዐይንና ብዙ ገጽ ካላቸው ከሰራዊተ መላክእት ይልቅ በዲዳዋ አህያ ትመሰገን ዘንድ ወደደክ፡፡ በሰማይ ሰራዊት ሠረገላ ተቀምጠኽ ክብርኽን ማሳየት አልወደድክም፤ በውርንጫላይቱ ላይ ተቀምጠኽ ወደ ሰማይ ሰራዊት መኼድን መረጥክ እንጂ፡፡ በአርያም እሳታውያን የሚኾኑ ኪሩቤል ያመሰግኑኻል፤ በምድርም ሕፃናት ይዘምሩልኻል፡፡ በአርያም ብርሃናውያን መላእክት በብርሃን ክንፋቸው መንገድኽን ያነጥፉልኻል፤ በምድርም ደቀ መዛሙርትኽ ልብሳቸውን አንጥፈው መንገድኽን አስተካከሉ፡፡ ወዮ! አርያማዊ ሲኾን ምንም ሳይንቀን ይጐበኘን ዘንድ ከአባቱ መጣ፡፡ ርሱም በገዛ ፈቃዱ ሰው እስከ መኾን ደርሶ መጣ፡፡ በአህያ ላይ ተጭኖም ይጐበኘን ዘንድ መጣ፡፡ ነቢዩ ዘካርያስ የመንፈስ ቅዱስን እንዚራ ይዞ በደስታ ትንቢትን ለመናገር ይቻኰላል፡፡ እየደረደረም የጽዮንን ልጅ ይጠራታል፡፡” በማለት አስተምሯል፡፡ ♥ የምስጋና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያዋና በውርንጫዋ ላይ ተቀምጦ ሕፃናትን ጨምሮ ዘንባባ ሰሌን በያዙት ኹሉ “ሆሣዕና በአርያም” እየተባለ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበትን ታላቁን በዓል ከኹሉም ዓለም አስበልጣ በታላቅ ክብር የምታከብርና የምታስተምረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ♥ ይኸውም ታላቁ የምስጋና ዕለት ሊደርስ ሲቃረብ ስንዱዋ እመቤት አስቀድማ በቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ የቊርባን ምስጋና፦ ✍ “ቦአ ኀቤሃ እግዚአ አጋዕዝት ወመናፍስት እንዘ ይጼዐን ዕዋለ አድግ ትሑት…” (የአጋዕዝትና የመናፍስት ጌታ በተዋረደ አህያ ግልገል ተቀምጦ ወደ ርሷ ገባ፤ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ብሩክ ነው፡፡ አንተም የአማልክት አምላክ የእስራኤልም ንጉሥ እግዚአብሔር ቡሩክ ነኽ እያሉ ለሚያመሰግኑ ሕፃናት ኹሉ ጌትነቱን አሳየ፤ የሆሳዕናን ዑደት ለነርሱ ለደቀ መዛሙርቱ አሳየ፤ ቡርክ ርሱ በታላቅ ቃል እየጮኻችኊ ሆሣዕና በአርያም በሉ አላቸው፤ ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሳዕና በአርያም፤ ከመድኀኒትነቱ የተነሣ ከዚኽ አስቀድሞ ያልተደረገ ከዚኽም በኋላ የማይደረግ ተአምራትንና መንክራትን አሳየ፤ ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሳዕና በአርያም... ) በማለት መድኀኒትነቱን ስትሰብክ፤ ካህናትና ምእመናንም በአንድ ድምፅ በዚያ ዘመን የምስጋና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በተመሰገነበት በዚኽ ልዩ ምስጋና “ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም” እያሉ በመዘመር፤ ፈጣሪያቸው ክርስቶስን ያመሰግናሉ። 💥 ከዚያም በዋዜማው፦ ✍ “በዕምርት ዕለት በዓልነ ንፉሑ ቀርነ በጽዮን ወስብኩ በደብረ መቅደስየ እስመ ይቤ ዛቲ ዕለት በዓለ እግዚአብሔር ሆሣዕና በአርያም ቡሩክ አንተ ንጉሠ እስራኤል” 👉 (በታወቀች በበዓላችን ዕለት በጽዮን መለከትን ንፉ፤ በመቅደሴ ተራራም ስበኩ ይኽቺ ዕለት የእግዚአብሔር በዓል ናት፤ በአርያም መድኀኒት የተባልኽ የእስራኤል ንጉሥ አንተ ቡሩክ (መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስን የምታርቅ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስን የምታድል) ነኽ) በማለት ልዩ ምስጋናዋን ጀምራ እስከ ሌሊቱ ድረስ በልዩ ምስጋና እየሰበከችው በኋላም ቤተ መቅደሱን በውርጫዋ ተቀምጦ እንደዞረ በአራቱ መኣዝን የጌትነቱ ወንጌል እየተነበበ፤ ካህናቱን ምእመናንም በእጃቸው የዘንባባ ዝንጣፊን ይዘው “ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም” እያሉ ያመሰግኑታል፡፡ ✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ተጻፈ መልካም በዓል ይኹንልን። https://t.me/tmhrteorthodox
نمایش همه...
🇪🇹✝️የኦርቶዶክስ ንግስ በአላት ✝️🇪🇹

ትምህርተኦክቶዶክስ በዚህ ቻናል ከተለያዩ ምንጮች የምናገኛቸዉን አስተማሪ ብለን ያሰብናቸውን #ሀይማኖታዊ ትምህርቶች #ስብከቶች #ታሪኮች #መዝሙሮች#የቤተክርስትያን ዜናዎች#ሀይማኖታዊ ፊልሞች ወ.ዘ.ተ የምናቀርብ ይሆናል ለሌሎች በማጋራት የበኩልዎን እንዲወጡ በልሉል እግዚአብሄር ስም እንጠይቃለን። #ትምህርተኦርቶዶክስ @tmhrteorthodox

[በዓለ ሆሣዕና] ✍በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (በድጋሚ የተለጠፈ) ♥ ሆሣዕና ማለት የዕብራይስጥ ቃል ነው፤ “ሆሻአና” ሲባል ትርጒሙም “አቤቱ አኹን አድን” ማለት ነው፤ ይኽ በዓለ ሆሣዕና ከ9ኙ ዐበይት የጌታ በዓላት ውስጥ ሲኾን ክንፋቸው ትእምርተ መስቀል የሚሠራው ኪሩቤል ሱራፌል በፍርሀት በረዐድ ኹነው ዘፋኑን የሚሸከሙት ጌታ በትሕትና ኾኖ ጀርባዋ ላይ ትእምርተ መስቀል ባለባት በአህያና በውርንጫይቱ ተቀምጦ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት፣ የዘካርያስ ትንቢት የተፈጸመበት፣ ሕዝቡ ዘንባባ ይዘው የዘመሩበት፣ ሕፃናት በንጹሕ አንደበታቸው ሆሣዕና ብለው ያመሰገኑበት ታላቅ በዓል ነው፡፡ ♥ ይኽም ታሪክ በ4ቱ ወንጌላት ላይ ሲጻፍ በማቴ 21፡1 ላይ “ወደ ኢየሩሳሌምም ቀርበው ወደ ደብረ ዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ፥ ያንጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከ” ይላል፡፡ ♥ ቤተ ፋጌ ማለት የበለስ ቤት ማለት ሲኾን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ በሚወስደው መንገድ አቅራቢያ ያለች ትንሽ መንደር ናት፤ ኹሉን ዐዋቂ የኾነው ጌታም ጴጥሮስንና ዮሐንስን “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ” በማለት እንደ ማዕምረ ኅቡአትነቱ (የተሰወረውን ዐዋቂነቱ) በመንደሯ ውስጥ ስለታሰሩት አህያና ውርንጫ አስቀድሞ ይነግራቸዋል፡፡ ♥ በተናቀች ግርግም በቤተልሔም በተወለደ ጊዜ ላምና አህያ ትንፋሻቸውን እንደገበሩለት፤ አኹንም በሰዎች በተናቀች አህያ በጌትነት ተቀምጦ እንዲመሰገንባት መርጧታል፡፡ ❤ በልደቱ ማንም ያልገባባት የማይገባባት የሕዝቅኤል የታተመች መቅደስ የተባለች ዘላለማዊት ድንግል እመቤታችንን እንደመረጠ ዛሬም በሆሣዕና ማንም ሰው ያልተቀመጠበት ውርንጫ እንዲያመጡ አዘዘ። ♦ ከዚያም “ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ፤ ወዲያውም ይሰዳቸዋል” በማለት የኹሉ ጌታ ርሱ መኾኑን አመለከታቸው፤ በተሰጣቸው ሥልጣነ ክህነት የሕዝቡንም የአሕዛቡን ኀጢአት የማሰር የመፍታት ሰማያዊ ሥልጣነ ክህነት የተሰጣቸው ሐዋርያትን የሕዝብ ምሳሌ የኾነችውን አህያይቱንና የአሕዛብ ምሳሌ የኾነችው ውርንጫዋንም እንዲያመጡ አዟቸዋልና። ♥ ሊቁ ጀሮምም፡- “ደቀ መዛሙርቱ አህያይቱንና ውርንጫይቱን ለመፍታት ኹለት ኾነው መላካቸው ለሕዝብም ለአሕዛብም መላካቸው ያመለክታል፡፡” ይላል። ♥ ሊቁ አምብሮስ፡- “አህያየቱን ለመፍታት ማንም አይከለክላችኁም ብሎ መላኩ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጣቸው የማሰር የመፍታት ሥልጣን ሰማያዊ መኾኑን ያመለክታል፡፡” በማለት ልዩ ምስጢርን አስተላፎበታል። ♥ አምጥተው “ልብሳቸውንም በእነርሱ ላይ ጫኑ”፤ በአህያዋና በውርንጫዋ ላይ ኮርቻ ሳይኾን ልብስ ማድረጋቸው ኮርቻ ይቈረቊራል ልብስ ግን አይቈረቊርምና የማትቈረቊር ሕግ ሠራኽልን ሲሉ። ዳግመኛም ልብስ በአካል ያለውን ኀፍረት እንዲሰውር አንተም በደላችንን የምትሰውርልን ይቅር ባይ ነኽ ሲሉ በማለት መተርጉማን ይተነትናሉ፡፡ በተጨማሪም ልብስ በልጅነት ይመሰላልና የተገፈፍነውን የጸጋ ልብሳችን (ልጅነትን) ትመልስልናለህ ሲሉ ነው፨ ♥ ቅዱስ ኤፍሬም ይኽነን ሲተረጉም "ልብሳቸውን አውልቀው ያነጠፉለት ሰዎች አሮጌውን ማንነታቸውን ትተው ዐዲሱን ልብስ ክርስቶስን መልበሳቸውን ያስረዳል። ሐዋርያ ጳውሎስ “አሮጌውን ሰውነት አስወግዳችሁ አዲሱን ሰው ልበሱት” እንዳለው (ኤፌ.4፣23) ይኸውም ጥምቀት ነው" ይላል። ♥ ከኢየሩሳሌም እስከ ቤተ መቅደስ 16 ምዕራፍ ሲኾን መተርጒማነ ሐዲስ በትርጓሜ ወንጌል ላይ እንደሚገልጹት 14ቱን ጌታ በእግሩ ሲኼድ 2ቱን በአህያዋ፤ በውርንጫዋ 3 ጊዜ ቤተ መቅደሷን ዞሯል፡- 14ቱ በእግሩ መኼዱ የ10ሩ ቃላት 4ቱ የ4ቱ ኪዳናት ምሳሌ፡፡ 2ቱ በአህያዋ መጓዙ የፍቅረ እግዚአብሔርና የፍቅረ ቢጽ፤ 3ቱን በውርንጫዋ ተቀምጦ ቤተ መቅደሱን መዞሩ የ3ትነቱ የአንድነቱ ምሳሌ ነበር፡፡ ♥ ጌታ ንጉሠ ነገሥት ሲኾን፤ ኪሩቤል ሱራፌል ዙፋኑን በፍርሀት በረአድ የሚሸከሙት 24ቱ ካህናተ ሰማይ ዙፋኑን በፍርሀት የሚያጥኑለት ርሱ በትሕትና የዋህ ኾኖ በተናቁት በአህያና በውርንጫይቱ ላይ ተቀመጠ፤ ይኽም የተናቁትን ሊያከብር እንደመጣና፤ በየዋሀን ምእመናን ልቡና እንደሚያድር ለማሳወቅ በነርሱ ተቀመጠ። በተጨማሪም መተርጉማን እንዳመሰጠሩት በአህያ የተቀመጠ አባሮ እንደማይዝ ሸሽቶ እንደማያመልጥ ርሱም ካልፈለጉት እንደማይገኝ ከፈለጉት እንደማይታጣ በምስጢር አመለከታቸው፡፡ ♥ በተጨማሪም አህያ ሲፈጥራት በጀርባዋ ላይ ትእምርተ መስቀል ያላት ናትና ትእምርተ መስቀል ያለባት እእርሷ እንድትፈታ ማዘዙ ከ5 ቀን በኋላ በመስቀል ተሰቅሎ በሲኦል የታሠሩትን የሰው ልጆችን ነጻ ሊያወጣ መጥቷልና አህያን መርጧታል፨ ♥ ቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ፡- ስለዚኽ ነገር በትርጓሜ ወንጌሉ ላይ “እነዚኽ እንስሳት መላውን የሰው ልጅ ይወክላሉ፡፡ ኹለቱም አህያ መኾናቸውም የሰው ልጅ ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት የነበረውን አኳኋን የሚያስረዳ ነው፡፡ ምክንያቱም አህያ በኦሪቱ ዘንድ ንጹሕ እንስሳ አይደለችም፤ ብዙ ክብደት ያላት የማትወደድ እንስሳ ናት፤ ደካማ ናት፡፡ ሰውም እንደተናገርን ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት እንዲኽ ነበረ፡፡” በማለት አመስጥሯል፡፡ ♥ ሊቁ ቅ. ቄርሎስ ዘእስክንድርያም፡- “ፈጣሬ ኵሉ እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ጠቢብ አድርጐ ፈጥሮት ነበር፡፡ ማሰብና ማሰላሰል የሚችል ፍጥረት አድርጐ ፈጥሮት ነበር፡፡ ሰይጣን ግን አታለለው፡፡ ምንም እንኳን ሰው በሥላሴ አምሳል ቢፈጠርም መልኩን አበላሸው፡፡ ፈጣሬ ኵሉ እግዚአብሔርን ማወቅ ተሳነው፡፡ ክፉው ሰይጣን ሰውን እንስሳ እስኪመስል ድረስ ክብሩን አዋረደው፡፡ መዝሙረኛው ዳዊት፡- “ሰውስ ክብሩን አላወቀም፤ የሚጠፉ እስሳትን መሰለ” ያለውም ስለዚኹ ነው (መዝ.49፡12)፡፡ በመኾኑም አህያይቱ ክብራቸውን አጥተው ተዋርደው የነበሩትን እስራኤል ዘሥጋን ትመስላለች፡፡ እስራኤል ከሕጉ ጥቂት ነገርን ያውቃሉ፡፡ ከነቢያትና ከቅዱሳንም ትንሽ ያውቃሉ፡፡ ከኹሉም በላይ ደግሞ ወደ አሚን የሚጠራቸውን ክርስቶስን አልታዘዙትም፡፡ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” ሲላቸውም እንደ አህያይቱ በድንቁርና ተይዘው እንደነበረ ሲገልጥላቸው ነው፡፡ ውርንጫይቱ ደግሞ አሕዛብን ትወክላለች፡፡ ውርንጫ እኽልን ለመጫን እንደማታገለግል ኹሉ አሕዛብም ማኅደረ እግዚአብሔር ከመኾን ርቀው ነበርና፡፡” በማለት ገልጿል፡፡ ♥ ያን ጊዜ ከሕዝቡም እጅግ ብዙዎች ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ ይኽንም ማድረጋቸው ስንኳን አንተ የተቀመጥኽባት አህያ መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ነበር። እንስሳዋ እንኳን ጌታ ቢቀመጥባት እንዲህ ክብር ያገኘች ከሆነ ያደረባቸው ቅዱሳንማ የሚገባቸው ክብር ምን ያህል ይሆን? ይልቁኑ 9 ወር ከ5 ቀናት በማሕፀኗ የተሸከመችው ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነሥቶ ሰው የሆነውን አምላክ የወለደችው የቅድስት ድንግል ማርያም ክብርማ እጅጉን ታላቅ ነው። ❤ ጌታ የተቀመጠባት አህያ በክብር ወደ ኢየሩሳሌም እንደገባች ጌታ ያደረባቸው ምእመናን ደግሞ በታላቅ ክብር ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ይገባሉ።
نمایش همه...
🇪🇹✝️የኦርቶዶክስ ንግስ በአላት ✝️🇪🇹

ትምህርተኦክቶዶክስ በዚህ ቻናል ከተለያዩ ምንጮች የምናገኛቸዉን አስተማሪ ብለን ያሰብናቸውን #ሀይማኖታዊ ትምህርቶች #ስብከቶች #ታሪኮች #መዝሙሮች#የቤተክርስትያን ዜናዎች#ሀይማኖታዊ ፊልሞች ወ.ዘ.ተ የምናቀርብ ይሆናል ለሌሎች በማጋራት የበኩልዎን እንዲወጡ በልሉል እግዚአብሄር ስም እንጠይቃለን። #ትምህርተኦርቶዶክስ @tmhrteorthodox

ሆሣዕና የዐብይ ጾም ስምንተኛ እሑድ(ሳምንት) ሆሣዕና ከጌታችን አምላካችን ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከኢየሩሳሌም ወደ  ቤተ መቅደስ ለመግባት በፈለገ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ፊታችው ባለው ሀገር "ሂዱና አህያ ከውርጭላዋ ጋራ ታስራ ታገኛላችው ፈታችው እምጡልኝ። 'ምን ታደርጋላችሁ?'  የሚላችሁ  ሰው  ካለ  'ጌታቸው  ይፈልጋቸዋል'  በሉ"  ብሎ  ላካቸው  ከዚህ  በኋላ  ደቀ  መዛሙርቱ እንዳዘዛቸው  ሄደው  ፈተው  አመጡለት  በዚያም  የተሰበሰቡት  ሁሉ  በአህዮች  ላይ  ልብሳቸውን  ጎዘጎዙለት  ጌታችንም በሁለቱ  አህዮች  ላይ  ተቀመጠ  ከሌሎቹ  እንስሳት  አህዮችን  መርጦ  በአህዮች  ተቀምጧል፡ አህዮች  በመጽሐፍ  ቅዱስ ብዙ ታሪክ አላቸውና። ✅የበልአም አህያ የመልአኩን ክብር ለመግለጥ አፍ አውጥታ ተናግራለች። (ዘሁል 22+28) ✅ጌታችን በተወለደ ጊዜ አህዮች ከከብቶች ጋር በበረት እስትፋሳቸውን ገብረዋል። (ቅዳሴ ማርያም) የሆሣዕና እህዮች ከሁሉ ተመርጠው አምላካችን ተቀምጦባቸዋል: 'ለምን የተዋረዱት አህዮችን መረጠ?' ቢባል:- ፩. ደመናን አዝዞ : ነፋስን ጠቅሶ : በእሳት  መንኮራኩር ላይ የሚረማመድ አምላክ ሲሆን ነገር  ግን የመጣው ትሕትናን  ለማስተማር : የትሕትና  ጌታ  መሆኑን  ለመግለጽ ነውና በአህያ ተቀመጠ። ፪.  ትንቢቱን  ለመፈጸም  <<አንቺ  የጽዮን  ልጅ  ሆይ  እጅግ  ደስ  ይበልሽ  አንቺ  የኢየሩሳሌም  ልጅ  ሆይ  እልል  በዪ  እነሆ  ንጉሥሽ  ጻድቅና አዳኝ  ነው  ትሁትም  ሁኖ  በአህያም  በውርንጭላቱ  ላይ  ተቀምጦ  ወደ  አንቺ  ይመጣል  ሰረገላውንም  ከኤፍሬም ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም ያጠፋል>> ብሎ ዘካርያስ ትንቢት ተናግሮ ነበርና ለመፈጸም ነው። ዘካ ፱÷፩ ፫.  ምሳሌውን  ለመግለጽ ምሳሌ-  ቀድሞ  ነቢያት  ዘመነ  ጸብእ  ከሆነ  በፈረስ  ተቀምጠው  ዘገር  ነጥቀው  ይታያሉ  ዘመነ  ሰላም  ከሆነ  በአህያ ተቀምጠው መነሳንስ ይዘው ይታዩ ነበርና ጌታችንም ዘመነ ሰላም ነው ሲል በአህያ ተቀምጦ መጥቷል። ፬.  ምሥጢሩን  ለመግለጽ ምሥጢር-  በአህያ  የተቀመጠ  ሸሽቶ  አያመልጥም  አሳዶም  አይዝም  እሱም  ካልፈለጋችሁኝ  አልገኝም  ከፈለጋችሁኝ አልታጣም ሲል በአህያ ተቀምጦ መጥቷል። ህድግት የእስራኤል ምሳሌ ህድግት ቀንበር መሸከም የለመደች ናት= እስራኤልም ህግ መጠበቅ ለምደዋልና እዋል  የአህዛብ  ምሳሌ እዋል  ቀንበር መሸከም አልለመደችም=አህዛብም ህግ መጠበቅ አልለመዱምና  (አንድም)  ህድግት  የኦሪት  ምሳሌ ህድግት ቀንበር መሸከም እንደለመደች=ኦሪትም የተለመደች ህግናትና እዋል  የወንጌል ምሳሌ እዋል  ቀንበር መሸከም አልለመደችም=ወንጌልም ያልተለመደች አዲስ ህግ ናትና በሁለቱም ላይ መቀመጡ ኦሪትንም ወንጌልንም የሰራሁ እኔ ነኝ ሲል ነው፡፡ ከኢየሩሳሌም እስከ ቤተ መቅደስ ፲፮ ምእራፍ ነው ፲፬ቱን ምእራፍ በእግሩ ሂዶ ሁለቱን ምእራፍ በአህያይቱ ሂዷል በውርጭላይቱ ሁኖ ፫ ጊዜ ቤተ መቅደሱን ዙሯል ፲፬  ምእራፍ የአስርቱ  ትእዛዛትና  የአራቱ ኪዳናት ምሳሌ፤ አስሩ  ምእራፍ የአስርቱ ትአዛዛት፣ አራቱ  ምእራፍ የአራቱ ኪዳናት ምሳሌ ነው፣ አራቱ  ኪዳናት የሚባሉት እነዚህ ናቸው፦ ኪዳነ  ኖህ  :  ክህነተ  መልከ  ጼዴቅ  :ግዝረተ  አብርሀም  እና ጥምቀተ ዮንሐስ ናቸው፡፡ በአህያይቱ  ላይ ልብሳቸውን አንጥፈውለታል:: ልብስ  በአካል ያለውን ነውር ይሸፍናል አንተም ከባቴ አበሳ ነህ  ሲሉ። በአህያዋ  ላይ  ኳርቻ  ሳያደርጉ  ልብስ  አንጥፈውለታል :- ኳርቻ  ይቆረቁራል  ልብስ  አይቆረቁርም  የማትቆረቁር  ህግ ሰራህልን  ሲሉ  ነው።  ስለምን ልብሳቸውን አነጠፉለት ቢባል ? በእዩ  ልማድ ነው ፡ እዩ  የተባለው  ሰው  በእስራኤል  ላይ  ሲነግሥ  እስራኤል  ልብሳቸውን  አንጥፈውለት  ነበረና  በዚያ  ልማድ አንጥፈውለታል እኩሌቶቱ ደግሞ ዘንባባ አንጥፈውለታል ። 🌴 በዕለተ  ሆሳዕና  እስራኤላውያን  ለምን  የዘንባባ  ዝንጣፊ፤  የቴምር  ዛፍ  ዝንጣፊ  እና  የወይራ  ዛፍ  ዝንጣፊ  ይዘው  ዘመሩ?  (ማቴ. ፳፩÷፩-፲፯፣  ማር. ፲፩÷፩-፲፣  ሉቃ.  ፲፱÷፳፱-፴፰፣  ዮሐ. ፲፪÷፲፪-፲፭) የዘንባባ ዝንጣፊ ✅ ዘንባባ የድል ምልክት የደስታ መግለጫ የምስጋና መስጫ ነው፡፡ ✔️ይስሃቅ  በተወለደ  ጊዜ  አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል። ✔️ይስሐቅም ያእቆብን በወለደ ጊዜ    አምላኩን በዘንባባ አመስግኗል። ✔️እስራኤል  ከግብጽ  በወጡ  ጊዜ  በዘንባባ  ንሴብሆ  እያሉ  እህተ  ሙሴ  ማርያም  ከበሮ  እየመታች  አምላካቸውን አመስግነዋል፡፡ ✔️ዮዲት  እስራኤልን  እየገደለ  ያስቸገረው  ሆለፎርኒስን  አንገቱን  ቆርጣ  በገደለችው  ጊዜ  እስራኤል  ዮዲት  መዋኢት  ዮዲት ኀያሊት  ብለው በዘንባባ አመስግነዋታልና። ✅ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ✅ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው። ✅ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ✅ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው። ✅ዘንባባ  የነፃነት  ምልክት  ነው  ከባርነት  ነፃ  የምታወጣን  አንተነህ  ሲሉ  ነው  አኛም  ይህን  በማሰብ  ዘንባባ  ይዘን ሆሳእና  በአርያም  እያልን እለቱን  እናስባለን፡፡ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ ✅የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ህይወታችንን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ✅ የቴምር  ፍሬ  የሚገኘው  ከዛፉ  ከፍታ  ላይ  ነው:-  አንተ  አምላካችን  ልዑለ  ባህሪ  ነህ  ከፍ  ከፍ  ያልክ  አምላክ  ነህ  ሲሉ ነው። ✅ የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው። ✅ የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው። የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ✅ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡ ✅ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ✅ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ✅ በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና። ከፊት ከኋላ ያሉት "ሆሣዕና በዓርያም ለዳዊት ልጅ መድኀኒት መባል ይገባዋል" እያሉ አመስግነውታል የምስጋና ጌታም በአህዮች ተቀምጦ ወደ መቅደስ ገብቷል። በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች፦ -ዕብ ፱፥፲፩ እስከ ፍጻሜ -፩ጴጥ ፬፥፩-፲፪ -ሐዋ ፳፰፥፲፩ እስከ ፍጻሜ ምስባኩም፦ መዝ፰፥፪ "እመ አፈ ደቂቅ ወሕጻናት አስተዳሎከ ስብሐተ በእንተ ጸላኢ ከመትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ" "ከሕጻናት አንደበት ምስጋናን አዘጋጀህልኝ፡፡ ስለ ጠላትና ቂመኛን ለማጥፋት" ወንጌሉም፦ ዮሐ፭፥፲፩-፲፫ ቅዳሴ ፦ ዘጎርጎርዮስ (ነአኵቶ)[በዕዝል ዜማ] https://t.me/tmhrteorthodox
نمایش همه...
🇪🇹✝️የኦርቶዶክስ ንግስ በአላት ✝️🇪🇹

ትምህርተኦክቶዶክስ በዚህ ቻናል ከተለያዩ ምንጮች የምናገኛቸዉን አስተማሪ ብለን ያሰብናቸውን #ሀይማኖታዊ ትምህርቶች #ስብከቶች #ታሪኮች #መዝሙሮች#የቤተክርስትያን ዜናዎች#ሀይማኖታዊ ፊልሞች ወ.ዘ.ተ የምናቀርብ ይሆናል ለሌሎች በማጋራት የበኩልዎን እንዲወጡ በልሉል እግዚአብሄር ስም እንጠይቃለን። #ትምህርተኦርቶዶክስ @tmhrteorthodox