cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

TM አዶናይ ቃልን በቃል

ስለ ፍቅር ስለ ሰው ስለ ተፈጥሮ ስለ ማነኛውም ነገር በግጥም በፅሁፍ በምትፈልጉት አቀራረብ የሚነገርበት ምርጥ አዲስ ቻናል ነው ተቀላቀሉ በቻናሉ ላይ ያሎትን ሀሳብ እና አስተያየት ለመስጠት ይሄን ይጫኑ @TameBlackman

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
133
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

🍃🌹🍃………✍ 🍃🌹#Tm አዶናይ ቃልን በቃል 🍃🌺🍃🌺🍃 -------------------////---------------------- ♨️ ቅኔ❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ↪️ምነው ብታስጠሪኝ እኔን አስታውሰሽ፣ እደጅ ተቀምጬ እቤቴ ሳመሽ።😘😘😁😁😁 ↪️አፈኛ ይሏታል ባላወቁት ነገር፣ ውልውሉን ይዛ ነው እሷ እምትናገር።💰💰💰 ↪️አንገት የለሽም ወይ አዙሮ የሚያይ፣ ሲመሽ ብር ብለሽ ትሄጃለሽ ወይ።💰💰💰 ↪️ያቺን ጠይም አሽከር ልቤ እንዲያ ሲወዳት፣ ትላንት በዘነበው በራሰው ወሰዳት።😇😇😇😂 ↪️እቃ ከመንገድ ላይ ለምን አኖራችሁ፣ ወጥ አወጣ ስትል ሰበረችላችሁ።👯‍♂👯‍♂ ↪️አሁን ምን ያረጋል ነገር መለቃቀም፣ ባባቷ ያልሆነ ባያት ምን ልጠቀም።😳😳😳 ↪️አብረን ተቀምጠን መልካችን አንድ ነው፣አሁን እኔ እና አንቺን የሚለየን ማን ነው።❤️❤️❤️💋💋💋😘😍😘 ✍kalenebekal Tm አዶናይ 📖📖📖 🍃🌺🌸🌹🍃 @kalenebekal @kalenebekal @kalenebekal @kalenebekal 🍃🌸🌺🌼 -----------------////------------------------ °°°^^🍃🌹🍃🌸🍃🌹🍃°°°°
نمایش همه...
🍃🌹🍃………✍ 🍃🌹#Tm አዶናይ ቃልን በቃል 🍃🌺🍃🌺🍃 🎵🎵🎵🎵🎶🎶🎶🎶🎶 -------------------/////--------------------- ከኔ መለየትሽን ልቤ ባይፈልግም መልካም ምኞቴን ግን ልነፍግሽ አልፈቅድም ፍቅሬ አልጥምሽ ብሎ አንቺ ብትጨክኚ ወድጄሻለሁና ዬትም ጤና ሁኝ🎶🎶🎶🎶 ✍kalenebekal Tm አዶናይ 🎶🎶🎶🎶🎶 🍃🌹🌸🌹🍃 @kalenebekal @kalenebekal @kalenebekal @kalenebekal 🍃🌺🌼🌺 --------------------////--------------------- °°°^^🍃🌹🍃🌸🍃🌹🍃°°°°
نمایش همه...
🍃🌹🍃………✍ 🍃🌹#TM አዶናይ ቃልን በቃል 🍃🌺🍃🌺🍃 ሕይወት በምርጫዎች የተሞላችው እንዴት ነው? ----------------------////------------------- ♨️ ምግብ አብዝተን ስንበላ ወፍራም የመሆንና ጤናን የማጣት ምርጫን መረጥን ማለት ነው፣ መጠጥ አብዝተን ስንጠጣ በነጋታው ጠዋት ራስ ምታት እንዲይዘንና ቀስ በቀስ የጤና ወታወክ እንዲደርስብን መረጥን ማለት ነው፣ ጠጥተን ካሽከረከርን በሚፈጠረው አደጋ የመሞት አሊያም ሰው የመግደል ምርጫን መረጥን ማለት ነው፣ ሰዎችን በሕመማቸው ጊዜ ካስታመምናቸው እኛም ስንታመም ተመሳሳዩን አገልግሎት ለማግኘት መረጥን ማለት ነው፣ ለሌሎች ሰዎች ማሰብ ካቆምን ሌሎችም እንዳያስቡልን መረጥን ማለት ነው። ♨️ ምርጫዎች ሁሉ የራሳቸው ጣጣ አሉዋቸው። ምርጫዎችን ለመምረጥ ነፃ ብንሆንም ቅሉ ከዚያ በኋላ ምርጫችን እኛኑ ይቆጣጠረናል። እኩል ያለመሆን እኩል ዕድል ነው ያለን። መምረጡ የኛ ፋንታ ነው። ሕይወት የፈለግነውን ዓይነት ቅርፅ እየሰራ ከሚኖር ሸክላ ሰሪ ጋር ትነፃፀራለች። እኛም ሕይወታችን የፈለግነውን ቅርፅ እንዲይዝ መምረጥ እንችላለን። ✍kalenebekal TM አዶናይ 📚📖📖📖📖📚 🍃🌺🌸🌹🍃 @kalenebekal @kalenebekal @kalenebekal @kalenebekal ----------------////------------------------- °°°^^🍃🌹🍃🌸🍃🌹🍃°°°°
نمایش همه...
🍃🌹🍃………✍ 🍃🌹#Tm አዶናይ ቃልን በቃል 🍃🌺🍃🌺🍃 ---------------------////-------------------- 🌼🌼 ኢድ ሙባረክ🌼🌼 ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1, 442ኛው ለታላቁ ኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!!! በዓሉ የሰላም የፍቅር የአንድነት የመተሳሰብ እንዲሁም የጤና በዓል ይሁንሎት!!!! መልካም በዓል!!! መልካም በዓል!!! መልካም በዓል!!! ኢድ ሙባረክ🙏🙏🙏🙏 ኢድ ሙባረክ🙏🙏🙏🙏🙏 ኢድ ሙባረክ🙏🙏🙏🙏🙏🙏 ✍kalenebekal Tm አዶናይ ኢድ ሙባረክ 🍃🌺🌼🌹🍃 @kalenebekal @kalenebekal @kalenebekal @kalenebekal 🍃🌸🌺🌼 --------------------////--------------------- ኢድ ሙባረክ🙏🙏🙏🙏 °°°^^🍃🌹🍃🌸🍃🌹🍃°°°°
نمایش همه...
🍃🌹🍃………✍ 🍃🌹#Tm አዶናይ ቃልን በቃል 🍃🌺🍃🌺🍃 🍃🌼ያሮጌው ባልሽ ዘፈን🌼 -----------------/////--------------------- አግብተሻል አሉ፣ የናጠጠ ሀብታም ባለብዙ ዝና፤ ባለብዙ ካዝና፣ ብር እሚተነፍስ ዶላር እሚሸና፣ እኔ ግን ድሃ ነኝ፣ አብረሽኝ ብትውይ አብሬሽ ባመሽም እንደ አዲሱ ባልሽ አበል አልከፍልሽም። ግን እወድሻለሁ!!!❤️❤️❤️ ✍kalenebekal Tm አዶናይ 📚📖መስፍን ወንድወሰን📖📚 🍃🌹🌸🌹🍃 @kalenebekal @kalenebekal @kalenebekal @kalenebekal 🍃🌺🌼🌺 --------------////--------------------------- °°°^^🍃🌹🍃🌸🍃🌹🍃°°°°
نمایش همه...
🍃🌹🍃………✍ 🍃🌹#Tm አዶናይ ቃልን በቃል 🍃🌺🍃🌺🍃 🍃🌼ሙጣጭ ንስሃ🌼🍃 ---------------------////-------------------- የበደልኩሽ በደል፣ ቀን እየቆጠረ የሰራሁት ስራ ይገፋኝ ጀመረ፣ በበደልኩሽ በደል ንስሃ ሳልገባ፤ እንደ ጎርፍ ወሰደኝ ያለቀስሽው እንባ።😭😭😭 ✍kalenebekal Tm አዶናይ 📚📖ጀማል ሰይድ📖📚 🍃🌹🌸🌹🍃 @kalenebekal @kalenebekal @kalenebekal @kalenebekal 🍃🌺🌼🌺 -------------------////---------------------- °°°^^🍃🌹🍃🌸🍃🌹🍃°°°°
نمایش همه...
🍃🌹🍃………✍ 🍃🌹#Tm አዶናይ ቃልን በቃል 🍃🌺🍃🌺🍃 ------------------////----------------------- ሕይወት ደስታና ጭፈራ ብቻ አይደለችም፣ ሕመምና ስቃይም ጭምር ናት። ያልተጠበቁ ነገሮች በድንገት ይከሰታሉ። ሳይታሰብ ሁሉም ነገር ግልብጥብጡ ይወጣል። መጥፎ ክስተቶች ጥሩ ሰዎች ላይ ይከሰታሉ። ወላጆቻችንን አሊያም የምንወለድበትን ሁኔታ መምረጥ አንችልም። ኳሷ ወደ ማትፈልጉት አቅጣጫ ተወርውራ ከሆነ ከልብ አዝናለሁ። ሆኖም አሁን ካላችሁበት ሁኔታ ተነስታችሁ ሕይወታችሁን እንዴት ለመቀጠል አስባችኋል? በማማረር ወይስ ኳሷን ካለችበት አንስታችሁ ወደ ምትፈልጉት አቅጣጫ በመወርወር ከኳሷ ጋር መሮጥ? ይህን የመወሰን ምርጫው የናንተ ነው። ቀኑ ፀሀያማና የጠራ ከሆነ ሀይቁ ላይ በተለያየ አቅጣጫ የሚንሳፈፉ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ መርከቦችን ማየት ይቻላል። ምንም እንኳን ነፋሱ የሚነፍሰው ወዳንድ አቅጣጫ ቢሆንም፣ መርከቦቹ የሚነጉዱት በተለያየ አቅጣጫ ነው። አቅጣጫው የሚወሰነው ደግሞ እንደ ሸራ አወጣጠራቸው ነው። በሕይወታችንም ላይ እንዲሁ። የነፋሱን አቅጣጫ መወሰን ባንችልም፣ የምንሄድበትን አቅጣጫ የመወሰኑ ምርጫ የራሳችን ነው። መልካሙን ሁሉ ተመኘሁላችሁ!!! ✍kalenebekal Tm አዶናይ 📚📖📖📖📖📚 🍃🌺🌸🌹🍃 @kalenebekal @kalenebekal @kalenebekal @kalenebekal -----------------////------------------------ °°°^^🍃🌹🍃🌸🍃🌹🍃°°°°
نمایش همه...
🍃🌹🍃………✍ 🍃🌹#Tm አዶናይ ቃልን በቃል 🍃🌺🍃🌺🍃 ገንዘብ የማይገዛቸው ነገሮች ------------------////----------------------- ገንዘብ አፍ አውጥቶ ቢያወራ ኖሮ መቼም ቢሆን ትርጉም የሚሰጥ ነገር አይናገርም። ሁሉም ሰው ዋጋ እንዳለው መስማቱ የተለመደ ነው። የዚያን አይነቱን ቋንቋ የሚናገሩት ሰዎች በእርግጥም ራሳቸውን ለሽያጭ ያቀረቡ ናቸው። ምግባር ያላቸው፣ ሀቀኞችና ትክክለኛ እሴቶች ያሏቸው ሰዎች ራሳቸውን አይሸጡም። ↪️💰 ገንዘብ፦ 💰ጨዋታን እንጂ ደስታን፣ 💰አልጋን እንጂ እንቅልፍን፣ 💰መፅሀፍን እንጂ እውቀትን፣ 💰ሰዓትን እንጂ ተጨማሪ ጊዜን፣ 💰ጊዜያዊ ወዳጅን እንጂ ጓደኛን፣ 💰የክት ልብስና ጌጣጌጥን እንጂ ውበትን፣ 💰ምግብን እንጂ የምግብ ፍላጎትን፣ 💰መጠለያን እንጂ ቤትና ቤተሰብን፣ 💰መድሃኒትን እንጂ ጤናን፣ 💰ቀለበትን እንጂ ትዳርን……አይገዛም። ✍kalenebekal Tm አዶናይ 📚📖📖📖📖📚 🍃🌺🌸🌹🍃 @kalenebekal @kalenebekal @kalenebekal @kalenebekal ------------------////----------------------- °°°^^🍃🌹🍃🌸🍃🌹🍃°°°°
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.