cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

መንፈሳዊ ታሪኮቻችን

🙏ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን 🙏 ለጥያቄው አስተያየት ለመስጠት @yeEnateneg @yeEnateNeg @yeEnateNegላይ ይቻላል ለአገልግሎታችን መቃናት የሁላችንም ትብብር ያስፈልጋል 🙏 ስለማይነገር ስጦታው የድንግል ማርያም ልጅ የልዑል እግዚአብሔር ስም ዛሬም ዘወትርም የተመሰገነ ይሁን 🙏

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
233
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

🌼🌸ፀሎት እንዲሰለቸው 🌺🌸 ሰው ሌላ ነገር ምንም ሲያደር አይሰለቸውም አይደከምም ነገር ግን ገና ለፀሎት ሲነሳ ይልፈሰፍሳል። በአንድ አባታችን ሆይ ላይ አራቴ አምስቴ ያዛጋል አንድ አባታችን ሆይ ለማለት ሁለት ሰዓት የቆምን እስኪመስለው ድረስ የደክመዋል ሰው በፀሎት ከበረታ አጋንንትን ድል ስለሚነሳ በፈተና ከሰው መራቅ የማይርቀው አጋንንት ደግሞ ሰው እሱን ድል የሚነሳበትን መሳሪያ ሲይዝ በቶሎ በተለያየ መንገድ ያስጥለዋል ለዚህም ነው ብዙ ሰው ቤቱን ሁሉ አሳምሮ ሰርቶ የፀሎት ቤቱን የሚዘነጋው። ሰው ያለ ፀሎት የሚኖረው ኑሮ አይደለም ። ምክንያቱም ሰው ያለ ፆምና ያለ ፀሎት እንኳን አለምን ይቅርና የራሱን የስጋ ፍቃድ ለነፍሱ ማስገዛት አይችልም ። እለት እለት በፀሎት ህይወት መትጋት ፅናቱና ብርታት ቢጠየቅም ፍፃሜው ግን የተወደደ ነው ከሞት በኃላ ዋጋ ያላት ነፍስም በፆም የበረታች በፀሎት የተገኘ በሀይማኖት የፀናች ናት ። እለት እለት መፀለይና ማመስገን ዋጋው ብዙ ነው ። 1ተሰ 5:17-18 ሳታቋርጡ ፀልዩ በሁሉ አመስግኑ በፀሎት ሁልጊዜ የምንፈልገውን እናገኛለንና ። ሜቴ 21:22 አምናችሁም በፀሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ አላቸው ። የኛ የብዙዎችን ችግር ካልተያዝን ምንም ግድ የሚለን ነገር የለም። ፀበል እንዳለም ትዝ የሚለን ስንያዝ ብቻ ነው። ሰው ሁሌ ባለጋራ ጠላት አለው ይህውም ዲያቢሌስ ነው። እንዳንፀድቅ ተከብረን እንዳንኖር ደስተኛ ሰኬታማ እንዳንሆን በተለያየ መንገድ ይፈትነናል። ለዚሁም መድሀኒቱ ፆምና ፀሎት ሰለሆነ ይሄን ጋሻ ካልያዝን ከመውደቅ አንድንም። 1ኛጴጥ 5:8በመጠንኑሩ ንቁም ባለጋራችሁ ዲያቢሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና።በዓለም ያሉት ወንድሞቻቾሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ፀንታችሁ ተቃወሙት። 🇪🇹🇪🇹ዘማሪ ዲ/ን ፀጋዬ አሰፋ 💐💐@yegnaefta 💐💐
نمایش همه...
እግዚአብሔርን ማየት ለምትፈልጉ
نمایش همه...
11.60 MB
نمایش همه...
I am yordi on TikTok. To download the app and watch more videos, tap:https://m.tiktok.com/invitef/download?username=muser&platform=more

TikTok

ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡- #ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡ #ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29 #ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡ #ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡ #አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡ #ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡ #እሁድ- ዳግም ትንሳኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡ 🌸@MenfesawiTarikochachn🌸
نمایش همه...
ጌታችን ለወንበዴው <<በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ > የሚል ልመና እውነት እውነት እልሃለሁ ፤ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ ብሎ ወዲያውኑ :መልስ ሰጠ በኃጢአተኞች ሰዎች ፊት የመሰከረለትን ወንበዴ፧ በመላእክት ፊት እመሰክርልሃለሁ አለው ። በግራ ያለው ወንበዴ ሲሰድበው ዞሮ በቁጣ ሳያየው በትዕግስት ሰምቶ ዝም ያለው ጌታ የቀኙ ማረኝ ሲለው ግን ከአፉ ተቀብሎ ወደ እርሱ ዞሮ መለሰለት ፡ከቁጣ የራቀ ምህረቱ የበዛው አምላክ :ክፉ ስራችንን ለማሰብ ሲዘገይ ማረኝ ስንለው ግን ለመማር ይፈጥናል <የራበው ሰው ለምግብ የጠማው ሰው ለመጠጥ እንደሚቸኩል ክርስቶስ ይቅር ለማለት ይቸኩላል ስለዚህ ወደ ወንበዴው ዞሮ "እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው ! ይህንን ምህረት ተስፋ አድርገን << ጌታ ሆይ ወደ ቀኙ ወንበዴ ዘንበል ባለው ራስህ አጋንት በኃጢአት በትር የመቱትን ራሴን ቀና አድርግልኝ እያልን እንጸልያለን ! #ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
نمایش همه...
ሰይጣን ፡- ሞት ሆይ ፤ እስቲ ንገረኝ አንተን የሚያገለግልህና የሚያመልክህ ማን ነው? እኔን ግን ነገሥታት ሳይቀሩ እንደ አምላክ ያመልኩኛል! ሞት ፡- ሞታቸውን እንደ መልካም ነገር የሚናፍቁኝና የሚጠሩኝ ብዙዎች ናቸው ፤ አንተን ግን ፈልጎ የጠራህም የሚጠራህም የለም፡፡ ሰይጣን ፡- ብዙ ሰዎች በሥራቸው እንደሚጠሩኝና እጅ መንሻም እንደሚያቀርቡልኝ አላስተዋልክም እንዴ? አይ ሞት! ሞት ፡- ስምህ እኮ የተጠላ ነው አይ ሰይጣን! ሁሉ ይረግምሃል ፤ ስምህን ልታነጻውና መጠላትህን ልትሸሽገው አትችልም፡፡ ሰይጣን ፡- ጆሮህ ሳይደፈን አይቀርም ፤ ሰዎች በአንተ ላይ ምን ያህል በምሬት እንደሚጮኹ አትሰማም እንዴ? ይልቅ ብትደበቅ ሳይሻልህ አይቀርም…›› ​የሞትና የሰይጣን ክርክር ረዥም ነው ፤ ክርክሩ ከሲኦልም ጋር ይቀጥላል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ከሁሉ በመጨረሻ :- ‹‹አንድ ልብ ሆነው የነበሩትን ሞትና ሰይጣንን የከፋፈላቸው እርሱ የተመሰገነ ይሁን ፤ ተከፋፍለን የነበርነውን እኛንም አንድ ልብ ያደረገን እርሱ የተመሰገነ ይሁን›› ብሎ ውብ ድርሰቱን ያጠናቅቃል፡፡ ​‹አንበሳ ሲያረጅ የዝንብ መጫወቻ ይሆናል› እንደሚባለው ሞት በአሟሟቱና በመዋረዱ የተነሣም እኛ ክርስቲያኖች እጅግ ንቀነው ‹መውጊያህ የታለ?› እያልን መዘበት የጀመርን ሲሆን ሰማዕታቱ ደግሞ እንኳንስ ሊፈሩት የአንገታቸውን ኮሌታ ለመታረድ እየሰበሰቡ በደስታ የሚጠጡት ጽዋ ሆነላቸው፡፡ ስንቱን እንዳላስለቀሰና በጣር እንዳላስጨነቀ ዛሬ ሙቱ ሞት ተንቆ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ለፍትሐት ጸናጽልና ከበሮ ይዛ የምትዘምርበት ፣ በኀዘን ፈንታ ማኅሌት የምትቆምበት ፣ እየተደገሰ ከነዳያን ጋር የሚበላበት ክስተት ሆኖ አረፈው፡፡ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ሚያዝያ 28 2012 ዓ ም ሕማማት - ገጽ 500
نمایش همه...
+ በርባን ይፈታልን + ሕዝቡ ‹በርባን ይፈታልን! ክርስቶስ ግን ይሰቀል!› ማለታቸውን ስንሰማ መቼም ሁላችንም ማዘናችንና ‹ምን ዓይነት ክፉዎች ናቸው?!› ብለን መውቀሳችን አይቀርም፡፡ ወዳጄ ሆይ! እባክህን እስቲ አይሁድንና ጲላጦስ ለአፍታ እንተዋቸው! አንተ ብትሆን ኖሮ ከጌታና ከበርባን ማናቸውን ትፈታለህ? የእስክንድርያው ትምህርት ቤት ዲን የነበረው ሊቅ ‹‹በሥጋው ክፉ ነገርን የሚሠራ ሁሉ በርባንን ፈትቶ ክርስቶስን አሰረው ፤ መልካም ነገርን የሚያደርግ ደግሞ ክርስቶስን ፈትቶ በርባንን አስሮታል›› ይላል፡፡ ወዳጄ ሆይ! አንተ በሰውነትህ ላይ ፈትተህ የለቀቅከው ማንን ነው? በርባንን ነው ወይንስ ጌታን ነው? በርባንን ፈትተኸው ከሆነ ዛሬውኑ በንስሓ ተመልሰህ ፈጣሪህን በሰውነትህ ውስጥ አክብረው፡፡ ‹በርባንን የፈታሁት እኮ ወድጄ አይደለም! ሁኔታዎች አስገድደውኝ ነው› ብለህ እንደ ጲላጦስ ለራስህ ይቅርታ ማድረግና እጅህን መታጠብ አይበጅህም፡፡ ይልቅስ አሁኑኑ ጌታህን ፈትተህ በርባንን የተባለ ኃጢአትን ስቀለው! ያን ጊዜ የክርስቶስ መሆንህ ይታወቃል፡፡ ‹‹የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ምኞቱ ጋር ሰቀሉ›› ተብሎ ተጽፎአልና፡፡ (ገላ. ፭፥፳፬) ሕዝቡ ‹በርባን ይፈታ› ብለው ቢጮኹም ሁሉም ለበርባን ፍቅር አላቸው ማለት አይደለም፡፡ ሊቃነ ካህናቱ ባያባብሏቸው ኖሮ በዚያች ዕለት ሊያስፈቱት የሚፈልጉት ሌላ እስረኛ ዘመድ ያላቸውም ሰዎች መኖራቸው አይቀሬ ነው፡፡ ሆኖም ሊቃነ ካህናቱ ለጌታችን ካላቸው ጥላቻ የተነሣ ሕዝቡን ተለማምጠው በርባን እንዲፈታ አስደረጉ፡፡ ዛሬ በርባንን አግኝተን ‹በርባን ሆይ ማን ነው ያስፈታህ?› ብለን ብንጠይቀው ምናልባትም ‹የሰው መውደድ ይሥጥ ማለት ነው! የሚወደኝ ሕዝብ ነዋ ጮኾ ያስፈታኝ!› ማለቱ የማይቀር ነው፡፡ ሆኖም ሊቃነ ካህናቱና ተከታዮቻቸው ግን ‹በርባን ይፈታ› ብለው የጮኹት ለበርባን ፍቅር ኖሯቸው ሳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በነበራቸው ጥላቻ ምክንያት ነው፡፡ ስለዚህ በርባንን ከሞት ፍርድ አድኖ ያስፈታው ሕዝቡ ሳይሆን ጌታችን ነበር፡፡ ጌታችን በዚያች ዕለት የበርባንን ሞት ወስዶ የእርሱን ሕይወት ለበርባን ሠጠው ፤ የበርባንን ሰንሰለት አስፈትቶ እርሱ ታሰረ ፤ ከበርባን ጓደኞች ጋር በርባን ሊሰቀል በነበረበት ቦታም ተሰቀለ፡፡ ወዳጄ ሆይ! ልብ ብለህ ከተረዳኸው በርባን እኮ አንተው ነህ! ለበርባን ከተደረገለት ለአንተ ያልተደረገ ነገር ካለ እስቲ ንገረኝ! እንደ በርባን ክርስቶስ ሞትህን ወስዶ ሕይወቱን ፣ እስራትህን ወስዶ ነጻነትን አልሠጠህምን? ይህንን ያደረገውም ለአንተ ብቻ ሳይሆን ለአዳም ልጅ ሁሉ ነው ፡- ‹‹የእስረኛው በርባን (ወልደ አባ) መፈታቱ አምላካዊ ምሥጢርን የሚያስታውስ ነው፡፡ በኃጢአቱ ምክንያት በሲኦል ውስጥ ታሥሮ የነበረው አዳምን በአዳኙ መሰቀል ምክንያት መድኃኒት አግኝቶ ነጻ መውጣቱን ያስታውሳል›› / ‹‹እስመ ተፈትሕዎቱ ለወልደ አባ ሙቁሕ ያዜክር ምሥጢራተ አምላካዊ ያሌቡ ግዕዛነ አዳም ዘኮነ ሙቁሐ ውስተ ሲኦል በእንተ ኃጢአቱ ወረከበ መድኃኒተ በስቅለተ መድኅን›› እንዲል፡፡ በዚያች የዕለተ ዓርብ ረፋድ ላይ ያስፈታውን የማያውቀው ይህ ወንበዴ ሰንሰለቱ ተፈትቶ ወደ ቤቱ ሲሔድ ጌታችን ግን ለመከራና ለመስቀል ተሠጠ፡፡ እውነቱንስ ለመናገር እኛ ክርስቲያኖች በርባን በመፈታቱ ላይ ላዩን ብናዝንም ውስጥ ውስጡን ግን ደስ ብሎናል! ‹‹…በርባን ቢሰቀል ኢየሱስ ቀርቶ ምን ይጠቅመናል ሽፍታ ሞቶ እንኳን ኢየሱስን ሰቀሉት የሞቱን መድኃኒት …›› ብለው መሪጌታ ፍቅሩ ሣህሉ በበገናቸው ጨርሰውታል፡፡ (#ሕማማት ) ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
نمایش همه...
🕯``ነገር ግን እርሷን የተዋጉ ጥቂቶች ለዝምታና ቶሎም ለመረሳት ተላልፈው ተሰጥተዋል። የወጓት ቤተ ክርስቲያን ግን ከሰማይ በላይ ከፍ ከፍ ብላለች።``🕯 ^ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ^ "ከቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ ብርቱ (ጠንካራ) ምንም የለም። ይህችውም ከሰማይ ከፍ ያለች ከምድርም ይልቅ የሰፋች ናት። አታረጅም ነገር ግን ዘወትር ታበራለች።" … " ቤተ ክርስቲያን በዘመናት ሁሉ ትሰፋለች። መታሰቢያዋም የሚጠፋ (የሚሞት) አይደለም።" … "ቤተ ክርስቲያን በስንቶች ውጊያ ተደርጎባት ነበር? አልተሸነፈችም እንጂ። የተዋጓት አላውያን ፣ የጦር መሪዎች ፣ ነገሥታቱስ ምን ያህል ናቸው? የተማሩና ኃይልን የተሞሉ ጎበዞች ሐዲሲቷን ቤተ ክርስቲያን በብዙ ጎዳናዎች ተዋግተዋት ነበር። ሊነቅሏት ግን አልቻሉም። ነገር ግን እርሷን የተዋጉ ጥቂቶች ለዝምታና ቶሎም ለመረሳት ተላልፈው ተሰጥተዋል። የወጓት ቤተ ክርስቲያን ግን ከሰማይ በላይ ከፍ ከፍ ብላለች። ቤተ ክርስቲያንን ድል ከማድረግስ ፀሐይን ማጥፋት (ማጨለም) ይቀላል። ሰው ሆይ! ከቤተ ክርስቲያን የሚበልጥ ኃያል ምንም የለም። ከሰው ብትጣላ ወይ ታሸንፋለህ አልያም ትሸነፋለህ። ቤተ ክርቲያንን ግን ብትጣላ፣ ታሸነፍ ዘንድ የሚቻልህ አይደለም። እግዚአብሔር ከሁሉ ይልቅ ኃያል ነውና። እግዚአብሔር መሥርቷታል፣ እንግዲህ ማን ሊነቀንቃት ይችላል? "
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.