fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

ኮሮጆ bags 💼 & Gift shop 🎁

ኮሮጆ bags 💼 & Gift shop 🎁

رفتن به کانال در Telegram

👉plexiglass 👉engraving 👉orginal cosmotics 👉 natural face products like Kesil 👉Gift packages 📞0942410512 metis_bag 🏠🏠 Megenagna 3M Mall 1st floor

نمایش بیشتر
1 896
مشترکین
-324 ساعت
-57 روز
-2930 روز
آرشیو پست ها
✍ #መጥፎ #የእግር #ሽታን #እንዴት #ማስዎገድ #ይቻላል ? 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን 👉 👉 #መጥፎ የእግር ጠረን በራስ የመተማመን ስሜትን ከማጥፋቱም በተጨማሪ ሰዎች ጋር ተቀላቅለን ጥሩ የሆነ ማህበራዊ ህይወትን እንዳናካሂድ እንቅፋት ይሆናል፡፡ በአብዛኛዉ ጊዜ መጥፎ የእግር ሽታ የሚያመጡ ነገሮች በቀላሉ ሊታከሙ/ሊወገዱ የሚችሉ ናቸዉ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ላይ የእግር ሽታዉ በቀላሉ የማይጠፋና ለረጅም ጊዜ ሊቆይ ስለሚችል የህክምና ባለሙያ እርዳታ ያስፈልጋል፡፡ የህክምና ባለሙያዉ የሽታዉን መንስኤ ካረጋገጠ በኃላ አስፈላጊዉን ህክምና እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡ 👉 👉 #መጥፎ የእግር ጠረን መንስኤዎች 📌 ባክቴሪያ 📌 ፈንገስ እንፌክሽን 📌 ከመጠን በላይ ላብ (Hyperhidrosis) 📌 እግርን የማናፈስ ልምድ ከሌለ 📌 የእግር ንጽህናን የማይጠበቅ ከሆነ 📌 ለረጅም ሰአት አየር የማያስወጣ ጫማ መጫመት 👉 👉 #መፍትሄዎች 📌 እግርዎን በቀን ሁለት ጊዜ በፀረ-ባክቴሪያ ሳሙና መታጠብ ፣ የእግር ካልሲዎችን/ሹራቦችን ቶሎ ቶሎ በመቀየርና እንዲሁም ጫማን በመቀያየር የእግር ላይ ባክቴሪያ እድገትን መቀነስ ይቻላል፡፡ 📌 የችግሩ መንሳኤ ፈንገስ ከሆነ ፓውደር ወይም መድሃኒቶችን በመጠቀም ሊታከም ይችላል። 📌 ለተወሰኑ ጉዳዩች የቆዳ ህክምና ባለሙያዎች መዳኒቶችን ሊያዙ ይችላሉ። 📌 የቤት ውስጥ ውህዶችን መጠቀም 📌 የእግር ጥፍራችንን በየግዜው መቆረጥ 👉 👉 #የቤት ውስጥ መፍትሄዎች 📌የእሬት ፈሳሽ ከሚያስገኛቸው በርካታ ጥቅሞች ውስጥ አንዱ ፈንገስን ማጥፋት እና የእግር ላበትን በማስተካከል መጥፎ ጠረንን ለማስወገድ ፍቱን መድሀኒት ነው። አጠቃቀሙ፦ የእሬት ቅጠልን በመሰንጠቅ ከውስጡ ያለውን ዝልግልግ ፈሳሽ በማውጣት ለአንድ ሳምንት ማታ ማታ እግራችን በደንብ ከታጠብን በሁዋላ ፈሳሹን ተቅብቶ መተኛት እና ጧት መታጠብ 📌 ቲማቲም ቲማቲምን ከሁለት ሰንጥቀን እግራችንን ከታጠብን በሁዋላ በቲማቲሙ ውስጠኛ ክፍል ማሽት እና ጧት መታጠብ ይህንን ለ 1 ሳምንት መጠቀም ...የእግር ላበት መብዛት እና ፈንገስን እስከወዲያኛው መሸኜት እንችላለን 📌 እርሾ እርሾ ወይም ሶድየም ባይካርቦኔት ለእግር ሽታ ፍቱን መድሃኒት ነው። በላባችን ውስጥ የሚገኘውን የኬሚካል ንጥረ ነገር በመቀየር ባክቴርያ እንዳይበራከት ያደርጋል። ሙቅ ውሃ ውስጥ እርሾውን ከጨመርን በኋላ እግራችንን ከ15-20 ደቂቃ ውሃ ውስጥ መጨመር። ለአንድ ሳምንት እንዲህ እያደረግን መቆየት አለብን። ካልሆነም ጫማ ከማድረጋችን በፊት ጫማና ካልሲያችን ውስጥ እርሾ በትንሹ ጣል ማድረግ እንችላለን። 📌 ላቫንደር ዘይት ላቫንደር ዘይት ጥሩ ሽታ ከመኖሩም በላይ በባክቴሪያ ገዳይነቱ ይታወቃል። በጸረ ኦክሲዳንት እና ጸረ ፈንገስ ባህሪው ይታወቃል። እግራችንን ዘይቱ ጠብ የተደረገበት ሙቅ ውሃ ውስጥ በመጨመር በሽታውን ማስወገድ እንችላለን። ከ15-20 ደቂቃ እግራችንን መዘፍዘፍ ይኖርብናል። በቀን ሁለቴ ማድረግ ያስፈልጋል። 📌 አቸቶ አቸቶ አሲዲክ ይዘት ስላለው ባክቴሪያዎች እንዳይራቡ ያደርጋል። የትኛውም አይነት አቸቶ ያገለግላል። አንድ ግማሽ ብርጭቆ አቸቶ እና 8 ብርጭቆ ሙቅ ውሃ በማቀላቀል እግራችንን ከ10-15 ደቂቃ መዘፍዘፍ በቂ ነው። በመጨረሻም የአቸቶውን ጠረን ለማጥፋት እግራችንን በሳሙና መታጠብ እንችላለን። 📌 ቤቢ ፓውደር ቤቢ ፓውደር ወይንም ታልከም ፓውደር ላባችንን መጦ እግራችንን በማድረቅ ከመጥፎ ጠረን ይከላከልልናል። እግራችን ወይም ጫማሽን ውስጥ በትንሹ በቀን ሁለት ወይም ሶስት ግዜ በመርጨት መጥፎ ጠረን መከላከል እንችላለን። 📌 ዝንጅብል ዝንጅብል የባክቴሪያ እድገትን እና ጎጂ ንጥረ ነገሮችን በመከላከል ይታወቃል። መካከለኛ ትልቀት ያለው ዝንጅብል ካደቀቅን በኋላ ከ10-15 ደቂቃ ሙቅ ዉሃ ውስጥ እንዘፈዝፋለን። ከዛም ዝንጅብሉን ከውሃው አጥልለን አውጥተን እግራችን ላይ እንቀባለን። ከመተኛችን በፊት ማድረጉ ይመከራል። ለሁለት ሳምንት መደጋገም ያስፈልጋል። 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ‼️ ሌሎች እንዲጠቀሙበት በቅንነት ሼር ያድርጉ!! @DrJano @DrJano @DrJano @DrJano

✍#የሴቶች #የወሲብ #ፍላጎት #ማጣት #በምን #ምክንያት #ይመጣል? 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ 🔵 #መንስኤዎቹ 🔹 የሆርሞን መቀነስ 🔹 ከዚህ ቀደም ብልት አካባቢ ቀዶ ህክምና ካደረጉ 🔹 ተደጋጋሚ ለጨረር የመጋለጥ እድል ከነበረ 🔹 በተደጋጋሚ ለማህጸን ኢንፊክሽን የመጋለጥ እድል ከነበረ 🔹 የማህፀን ፈሳሽ መቀነስ 🔹 የማህጸን እጢ 🔹 ድብርት 🔹 ጭንቀት 🔹 ስለግንኙነት መጥፎ አስተሳሰብ መኖር 🔹 በግንኙነቱ ደስተኛ አለመሆን 🔵 #ምልክቶቹ 🔹 የስሜት መዛባት 🔹 ፍላጎት አለመኖር 🔹 የሴት ብልት መድረቅ 🔹 ወሲባዊ እርካታ አለማግኘት 🔹 በግንኙነት ወቅት የህመም ስሜት መሰማት 🔵 #ህክምና 🔹 የሆርሞን ማስተካከያ መድሀኒት መውሰድ 🔹 የስነልቦና ህክምና 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ‼️ ሌሎች እንዲጠቀሙበት በቅንነት ሼር ያድርጉ!! @DrJano @DrJano @DrJano @DrJano

የቀይ ሽንኩርት የጤና ጥቅሞች! ********************* 1.የፀጉር እድገትን ያበረታታል 2.የደማችንን የስኳር መጠን ያስተካክላል 3.ካንሰርን ይከላከላል 4.በልብ በሽታ የመያዝ እድላችንን ይቀንሳል 5.በሽታ የመከላከል አቅማችንን ይጨምራል 6.የአፉችንን ጤና ይጠብቃል 7.የቆዳችንን ጤና ይጠብቃል መልካም ቀን!! “ጤና ይብዛልዎ” 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ‼️ ሌሎች እንዲጠቀሙበት በቅንነት ሼር ያድርጉ!! @DrJano @DrJano @DrJano @DrJano

✍️ #የሆድ #ህመም #እንዲሰማን #የሚያደርጉ #ምክንያቶች #ምንድንናቸው? 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #ሁሉም ሰው በህይወቱ ከአንድ ጊዜ በላይ የሆድ ህመም ያጋጥመዋል፡፡ የሆድ ህመም በጣም በብዛት የሚታይና ሁሉንም ሰው የሚያጠቃ ችግር ነው። ምንም እንኳን የሆድ ህመም በየጊዜው የሚከሰት ነገር ቢሆንም ዋናው ነገር ከጀርባው ያለውን ምክንያት አውቆ እራስን መጠበቅ ነው፡፡የሆድ ህመምን ከሚያመጡ ነገሮች መካከል የሚከተሉት በብዛት የሚታዩት እና ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ 👉👉 #መንስኤዎች 🔹 የምግብ አለመፈጨት (Indigestion) 🔹 የሆድ ድርቀት (Constipation) 🔹 ኢንፌክሽን 🔹 የወር አበባ 🔹 የምግብ አለርጂ 🔹 የፈስ (ጋዝ ) እና የሰገራ መጠራቀም 🔹 የጨጓራ ቁስለት 🔹 የወተት አለመፍጨት ችግር (Lactose intolerance) 🔹 የሃሞት ጠጠር (Gallstones) 🔹 የኩላሊት ጠጠር (Kidney stones) 🔹 የአሲድ ከጨጓራ ወደ ላይ መመለስ (Gastroesophageal reflux disease (GERD) 🔹 የትርፍ አንጀት በሽታ (Appendicitis) 🔹 የምግብ መመረዝ (Food Poisoning) 🔹 የተለያዩ ሆድ ውስጥ የሚኖሩ ረቂቅ ህዋሳት – አሜባ፣ ጂያርዲያ 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ‼️ ሌሎች እንዲጠቀሙበት በቅንነት ሼር ያድርጉ!! @DrJano @DrJano @DrJano @DrJano

✍ #የደም # አይነትዎን #መሰረት #ያደረገ #የአመጋገብ #ስርአት 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩#የሰው ልጅ የደም አይነት ማወቅ የሚቻለው በቀይ የደም ሕዋሳት ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ገሮችን በመመርመር ነው ፡፡ በዚህም መሠረት የደም አይነት ኦ(0) ፣ ኤ(A) ፣ ቢ(B) ፣ኤቢ(AB) ተብለው በአራት ይከፈላሉ፡፡ የተመገብነው ምግብ ጨጓራ ላይ ከተፈጨ በኋላ በአንጀት ውስጥ አልፎ የተወሰኑ ውህደቶች ከተከናወኑ በኋላ በደም አማካኝነት ወደ ሰውነት ይሰራጫል በዚህም ሂደት ውስጥ ምግብ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ንጥረ ነገሮች ከደማችን ጋር ኬሚካላዊ ውህደትን ይፈጥራሉ፡፡ ⏩ #ኦ(O) #ደም #አይነት #የአመጋገብ #ስርዓት የዚህ የደም ባለቤቶች ዓሳ ፣ቀይ ስጋ ፣ዶሮ ፣ስኳር ድንች ፣አትክልት እና ፍራፍሬ መሳሰሉ ምግቦችን እነዲያዝወትሩ ይመከራል ፡፡ በዚያውም ልክ እንደ እንቁላል፣ የወተት ተዋፀኦች ፣ስንዴና ባቄላን ከገበታቸው ማስወገድ ይገባቸዋል ፡፡ ⏩ #ኤ(A) #ደም #አይነት #የአመጋገብ #ስርዓት የዚህ የደም ባለቤቶች ፖም፣አቮካዶ፣ሰላጣ፣ካሮት ፣ነጭ ሽንኩት ፣ባቄላ ፣እርጎ፣የስንዴ ዳቦ ና ፓስታ እንዲመገቡ ይመከራል ፡፡ በዚያውም ልክ እንደ እንቁላል፣ ስጋ እና ሌሎች የእንስሳት ተዋፀኦችን ከገበታቸው መስወገድ ይገባቸዋል ፡፡ ⏩ #ቢ(B #ደም #አይነት #የአመጋገብ #ስርዓት የዚህ የደም ባለቤቶች እንደ ቀይ ስጋ፣አሳ ፣እርጎ ፣አይብ ፣ወተት ፣ሙዝ ፣አረንጓዴ ቅጠል ያላቸው አትክልቶች ፣ወይን ፣አናናስ ተስማሚ ከሚባሉ ምግቦች መካከል ሲጠቀሱ እንደ ዶሮ ፣ ስንዴ ቲማቲም እንዲሁም ለውዝ እንዳይመገቡ ይመከራል ፡፡ ⏩ #ኤቢ(AB) #ደም #አይነት #የአመጋገብ #ስርዓት የዚህ የደም ባለቤቶች ስጋ እና ሌሎች የእንስሳት ተዋፀኦዎችን መፍጨት ቢችሉም የጨጓራቸው አሲድ መጠን ዝቅተኛ በመሆኑ ምክንያት የተመገቡት ምግብ በስብ መልክ ይከማቻል ፡፡ ፍራፍሬዎች ፣አረንጓዴ ቅጠል ያላቸው አትክልቶች ፣ሀብሀብ፣ ወይን ፣ቱና ምግቦችን ማዘውተር ተገቢ ሲሆን በቆሎ፣የበሬና አሳማ ስጋ እንዲሁም ከአልኮል ና ቡና መራቅ ያስፈልጋል ፡፡ ✔ #በአብዛኛው ህብረተስብ ላይ የአመጋገብ ስርአታቸው ከደም አይነት ጋር ተዛማጅነት የለውም ነገር ግን የደም አይነቶን መሰረት ያደረገ የአመጋገብ ስርአት መኖር አላስፈላጊ ከሆነ የጤና ችግር እና አላስፈላጊ የሰውነት ክብደት እንዳይከሰት ያድርጋሉ !! 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ‼️ ሌሎች እንዲጠቀሙበት በቅንነት ሼር ያድርጉ!! @DrJano @DrJano @DrJano @DrJano

✍ #ብጉር 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #ብጉር በቆዳ ላይ የሚገኙ የፀጉር ቀዳዳዎች በቅባት እና በሞቱ የቆዳ ሴሎች ሲሞሉ ወይም ሲደፈኑ የሚከሰት የቆዳ ችግር ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ብጉር ነጭ ወይም ጥቁር ጫፍ አንዳንዴም ቀያይ ነጠብጣቦች በቆዳ ላይ ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ነጠባጣቦቹ መጠናቸው ሊለያይ ይችላል፤ ህመም ሊኖራቸውም ላይኖራቸውም ይችላል፡፡ ብዙውን ጊዜ ብጉር በፊት ላይ የሚወጣ ቢሆንም በአንገት፣ ደረት፣ ትከሻ እና ጀርባም ላይ ሊወጣ ይችላል፡፡ ⏩ #ብጉር በማንኛውም ሰው ላይ ሊያጋጥም የሚችል ነው፡፡በአብዛኛውን ግን ብጉር በጉርምስና ወይም በወጣትነት እድሜ ውስጥ ያሉት ላይ ይበረታል፡፡ በሂህ ጊዜ የመጣ ከሆነ እድሜ በጨመረ ቁጥር እየቀነሰ ሲመጣ ጥቂቶች ላይ ግን አብሮአቸው ይኖራል፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ግን አንዳንድ ጊዜ ብጉር በሆርሞን ችግር ምክንያት ህፃናት ላይ ሊታይ ይችላል፤ በእርግዝናም ወቅት የመከሰት እድል አለው፡፡ ⏩ #ምልክቶቹ 🔺 ነጭ/ ጥቁር ጫፍ ያላቸው ነጠብጣቦች 🔺 ትናንሽ ቀያይ ህመም ያላቸው ነጠብጣቦች 🔺 ቀያይ ጫፍ ላይ ትንሽ መግል ያላቸው ነጠብጣቦች 🔺 ተለቅ ያሉ ጠጣር ህመም ያላቸው እብጠቶች 🔺 ህመም ያላቸው መግል የያዙ ከቆዳ ስር ያሉ እባጮች ⏩ #ብጉር #መንስኤው 🔺 ቅባትማ የቆዳ አይነት መኖር 🔺 የፀጉር ቀዳዳዎች በቅባት እና በሞቱ ሴሎች መዘጋት 🔺 ባክቴሪያዎች 🔺 የአንዳንድ ሆርሞኖች ስራ መጨመር (ለምሳሌ Androgen) ⏩ #ብጉር ቅባት አመንጪ እጢዎች (Sebaceous gland) በሚበዙበት የቆዳ ክፍል አካባቢ ነው የሚወጣው፡፡ እነዚህም ፊት፣ ግንባር፣ ደረት፣ የላይኛው የጀርባ ክፍል እና ትከሻን ያጠቃልላል፡፡ ⏩ #የፀጉር ቀዳዳዎች ከቅባት አመንጪ እጢዎች ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ የእነዚህ ቀዳዳዎች ግርግዳ ሲያብጡ ነጣ ያለ አናት ይኖራቸዋል፤ ወይም ደግሞ አናታቸው ክፍት ከሆነ ሲጠቁር ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ቀዳዳዎቹ በባክቴሪያ እና ቅባት ይሞላሉ፡፡ ⏩ #ቀያይ ከፍ ከፍ ያሉ ውስጣቸው ነጭ የሆኑ ነጠብጣቦች የሚፈጠሩት ደግሞ የፀጉር ቀዳዳዎች በቅባት ከመዘጋታቸው በላይ በባክቴሪያ ሲጠቁ ነው፡፡ ⏩ #ብጉርን #ምን #ሊያባብሰው #ይችላል? 🔺 የሆርሞን መለዋወጥ ወይም መዛባት 🔺 አንዳንድ መድሐኒቶች 🔺 አመጋገብ (የተጠበሱ ምግቦች፣ በካርቦሀይድሬት የበለፀጉ ምግቦች) 🔺 ጭንቀት ወይም ውጥረት 🔺 ሸካራ ሳሙና መጠቀም እና በጣም የሞቀ ውሃ መጠቀም 🔺 የፀጉርና ቆዳ መጠበቂያ ውጤቶች በተለይ በውስጣቸው የሚያሳክክ ንጥረ ነገር የያዙ ከሆነ ⏩ #ተጋላጭነት #የሚጨምሩ #ሁኔታዎች 🔺 የጉርምስና የእድሜ ክልል 🔺 የሆርሞን መዛባት 🔺 የዘር ተጋላጭነት 🔺 ቅባትማ ነገሮችን በቆዳ ላይ መጠቀም 🔺 ቆዳን የሚፈገፍጉ (የሚፈትጉ) ነገሮች 🔺 ጭንቀት ⏩ #ብጉርን #መከላከል #ይቻላል? 🔺 ብጉርን በዘላቂነት መከላከል ባይቻልም እንዳይባባስ የሚወሰድ እርምጃዎችና ጥንቃቄዎች ግን አሉ። ከነዚህም መካከል፦ 🔺 በዝግታ ወይም በጣም ሳያሹ መታጠብ ለቆዳዎ ጤንነት አስፈላጊ ነው። በጣም ማሸት፣ መጥረግ፣ መፈተግ ወይም መፈግፈግ ተገቢ አይደለም። 🔺 በጣም እንዳያልብዎ መጠንቀቅ። ላብ እንዲያልበን የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎች ካደረግን በኋላ ወዲያው መታጠብ። 🔺 ፀጉርዎ ቅባት ካለው ወይም ከበዛበት መታጠብ 🔺 ጭንቀትን አለማብዛት 🔺 አንዳንድ የፀጉር መንከባከቢያ ምርቶችን መጠቀም ማቆም፤ እንደ ጄል፣ ክሬምና የመሳሰሉት 🔺 ፊትዎን ቶሎ ቶሎ ከመንካት መቆጠብ 🔺 ለስላሳ የኮተን ልብሶችን መጠቀም፤ በተለይ ከቆዳ ጋር ንክኪ ያላቸው ከሆነ 🔺 ከቅባት እና ኬሚካል ጋር ያለዎትን ግንኙነት መቀነስ ለምሳሌ እንደ ፔትሮሊየም ያሉትን 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ‼️ ሌሎች እንዲጠቀሙበት በቅንነት ሼር ያድርጉ!! @DrJano @DrJano @DrJano @DrJano

✍ #መጠነኛ #የሆነ #የኩላሊት #ጠጠርን #እንዴት #በቤት #ውሰጥ #ማከም# ይቻላል 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #የኩላሊት ጠጠር በኩላሊት ዉስጥ ትናንሽና ጠንካራ የሆኑ ማዕድናት ሲጠራቀሙ የሚመጣ ችግር ነዉ፡፡ ጠጠሮቹ የተሰሩት ከማዕድናትና አሲድነት ካላዉ ጨዉ ነዉ፡፡ የኩላሊት ጠጠር መነሻ መንስኤ ብዙ ሲሆኑ በየትኛዉም የሽንት መተላለፊያ መስመር ዉስጥ ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ ⏩# ብዙዉን ጊዜ የኩላሊት ጠጠሮች የሚከሰቱት ሽንት በሚወፍርበት/ concentrated/ በሚሆንበት ወቅት ሲሆን ይህ ማዕድናቱ እንዲረጉና እንዲጣበቁ እድል ይፈጥርላቸዋል፡፡ ⏩ #መጠኑ አነስተኛ የኩላሊት ጠጠር እንዴት በቤት ውስጥ ማከም ይቻላል ከዚህ በታች በዝርዝር እናያለን 🔺 1 #ውሃ #መጠጣት በቀን ከ6-10 ብርጭቆ ውሃ መጠጣት 🔺 2 #የሎሚ #ጭማቂ #መጠጣት ሎሚ በውስጡ ሲትሬት ስላለው ካልሽየምን ለመሰባበር ይረዳል በተጨማሪም የካልሽየም እድገት ይቀንሳል 🔺 3#አፕል #መመገብ አፕል በውስጡ ሲትሪክ አሲድ ስላለው ካልሽየም እንዲሟሟ ያደርጋል 🔺 4#ክብደትን #መቆጣጠር ወፍራም ሰዎች ለኩላሊት ጠጠር ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ በተለያዩ ሜታቦሊክ በሆኑ ህመሞች ጋር ተያይዞ ለምሳሌ ኮልስትሮል ከፍተኛ የደም ግፊት 🔺 5 #ስኳራማ #እና ካፊን #ያላቸው #መጠጦች #መተው እነዚህ መጠጦች ለኩላሊት ጠጠር ተጋላጭነትን ይጨምራሉ 🔺 6# ከመጠን #በላይ #ቪታሚን #ሲ #አለመውሰድ 🔺 7 #የጨው #መጠንን #መቀነስ ከመጠን በላይ ሶዲየም ወይም የገበታ ጨው መጠቀም የካልሽየም መውጣት በሽንት ውስጥ ስለሚጨምር ለኩላሊት ጠጠር ያጋልጣል 🔺 8 #የፕሮቲን #መጠንን #መቀነስ ከእንሰሳት የምናገኛቸው የፕሮቲን ለምሳሌ ስጋ አሳ ለኩላሊት አጋላጭ ናቸው በመጠኑ መጠቀም ተገቢ ነው 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ‼️ ሌሎች እንዲጠቀሙበት በቅንነት ሼር ያድርጉ!! @DrJano @DrJano @DrJano @DrJano

ፅንስ ማስወረድ በመድሀኒት https://youtu.be/IMmhgBd0MXY ሙሉ ቪዲዮውን ለመመልከት ምስሉን ወይም ሊንኩን ይጫኑ!!

🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ™ 🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ

🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ™ 🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ

🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ™ 🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ

🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ™ 🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ

🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ™ 🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ

🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ™ 🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ

🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ™ 🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ

🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ™ 🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ

🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ™ 🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ

🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ™ 🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ

🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ™ 🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ

🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ™ 🎶 @TeshayMusic | ፀሀይ