fa
Feedback
ኮሮጆ bags 💼 & Gift shop 🎁

ኮሮጆ bags 💼 & Gift shop 🎁

رفتن به کانال در Telegram

👉plexiglass 👉engraving 👉orginal cosmotics 👉 natural face products like Kesil 👉Gift packages 📞0942410512 metis_bag 🏠🏠 Megenagna 3M Mall 1st floor

نمایش بیشتر
1 896
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-47 عوز
-2830 عوز
آرشیو پست ها
ያለመድሀኒት የደም ግፊት ለመቀነስ የሚረዱ በሳይንስ የተደገፉ ዘዴዎች ምንም እንኳ መድኋኒት መውሰድ ግድ የሚሆንባቸው ሰዎች ቢኖሩም ለሁሉም ሰው ግን መድኃኒት መጀመር ላያስፈልግ ይችላል። ይህ ከሐኪሞ ጋር በመወያየት የሚወሰን ሲሆን ያለ መድሀኒት የደም ግፊት ለመቀነስ እንደሚረዱ በሳይንስ የተደገፉ ዘዴዎች እንዳሉ ማወቅና መተግበር ጠቃሚ ነው። በመሆኑም የሚከተሉትን ዘዴዎች ተጠቅመው የደም ግፊቶትን ይቀንሱ ስል እመክራለሁ ። ልብ ይበሉ ፦ በተለይ የኩላሊት ድክመት ፣ የልብ ድካምና ስኳር ካለቦት መድሀኒት ሊያስፈልጎት ስለሚችል እባክዎት ከሐኪሞ ጋር ይመካከሩ። 1ኛ፦ የአተነፋፈስ ዘዴ፡ በየቀኑ አየር ወደ ሳንባች በደንብ ሳብ አርገን ለ 4 ሰኮንድ ያህል በመያዝ ቀስ አርገን ወደ ውጭ መተንፈስ ። ይህን ለአስር ደቂቃ ያህል በየቀኑ መደጋገም ። ዮጋ ኒድራ/Yoga nidra ቪዲዮ ከዩቲዩብ በመመልከት አሰራሩን ማወቅ ይቻላል። ይህ መላ ሰውነታችንን ዘና/relax በማድረግ የደም ግፊት እንዲቀንስ ይረዳል ። 2ኛ፦የጨው መጠንን መቀነስ ፡ በአሁን ሰዓት ብዙ ነገሮች ጨው በብዛት ይይዛሉ፦ ዳቦ ጨው አለው፤ ካች ኣፕ ብዙ ጨው አለው....ወዘተ። ይህም ሳናውቀው የጨው አወሳሰዳችንን ከፍ ያደርገዋል ። ጨው የደም ግፊትን በብዛት ከፍ ከሚያደርጉ ነገሮች ዋንኛው ነው። በመሆኑም በቀን ከሚያስፈልገን 1.5 ግራም አብዝተን ባንጠቀም ይመከራል። ምግቦችን ስናዘጋጅም ሆነ ስንመገብ የጨው መጠናቸውን መመልከት ይኖርብናል ። 3ኛ፦ የደም ግፊትን ለመቀነስ የሚረዱ ምግቦችን ማዘውተር ፡ እንደ ነጭ ሽንኩርት ፣ ሙዝ፣ ቀይ ሽንኩርት ፣ ስትሮበሪ፣ ሰናፍጭ(spinach) የመሳሰሉ አትክልትና ፍራፍሬዎችን መጠቀም የደም ግፊትን ለመቀነስ ይረዳል ። 4ኛ፦የአልኮል መጠጥ መተው /በጣም መቀነስ 5ኛ፦ የኣሳ ዘይትን መጠቀም፡ በብዙ ሳይንሳዊ ጥናቶች የተደገፈ ነው። ከ70 በላይ የሆኑ ጥናቶች የኣሳ ዘይት የደም ግፊትን ለመቀነስ እንደሚረዳ አሳይተዋል ። 6ኛ፦ጭንቀትን መቀነስ፦ ጭንቀት ኮርቲሶልና አድሬናሊን የተባሉ ንጥረ ነገሮችን በመጨመር የደም ግፊትን ከፍ ያደርጋል ።በመሆኑም የጭንቀት መጠንን የሚቀንሱ እንደ ፀሎት ፣ ዮጋ፣ ሜዲቴሽን የመሳሳሉ ዘዴዎችን በመጠቀም የደም ግፊት እንዳይጨምር ማድረግ ይቻላል ። በተለይ የረጅም ጊዜ ጭንቀት ካለቦት መነሻውን ለይተው መፍታት አለቦት። የስነ አእምሮ ወይም የስነ ልቦና ባለሙያ ማማከር ካስፈለጎ ሳያመነቱ ያድርጉት ። 7ኛ፦ ሰፖረት መስራና ውፍረትን መቀነስ፦ ይህን ማድረግ በርካታ የጤና ጥቅሞች ያሉት ሲሆን የደም ግፊትን መከላከልና መቀነስ ከዋነኞቹ ነው። 8ኛ፦ በቂ እንቅልፍ መውሰድ ፦ በቀን ከ7-8 ሰዓት መደበኛ እንቅልፍ መውሰድ የደም ግፊትን ለመቀነስ ሲረዳ የእንቅልፍ እጦት በተቃራኒው የደም ግፊት ከፍ እንዲል ያደርጋል ። በቂ እንቅልፍ በመውሰድ ፣ስፖርት በመስራትና ጨው በመቀነስ የደም ግፊትን እንከላከልም እንቀንስም። ጤናና ሰላም ከናንተ ጋር ይሁን ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት https://t.me/DrJano https://t.me/DrJano

የደም አይነት እና የአመጋገብ ስርዓት 1) የ ኦ (O) ደም ዐይነት አመጋገብ ስርዓት ይህ የደም ዐይነት ከሌሎቹ የደም ዐይነት ቀድሞ የነበረ ጥንታዊ ሲሆን ከእንስሳት አዳኞች የተወረሰ የደም አይነት ነው። የዚህ ደም ባለቤቶች ዓሣ፣ የባህር ምግብ፣ ቀይ ስጋ፣ ጨው፣ ዶሮ፣ ስኳር ድንችና የመሳሰሉትን ምግቦች እንዲያዘወትሩ ይመከራል። በዚያውም ልክ እንቁላል፣ የእንስሳት ተዋፆኦዎች፣ ስንዴና ባቄላን ከገበታቸው ማራቅ አለባቸዉ። 2) የ ኤ (A) ደም ዐይነት አመጋገብ ስርዓት ይህ የሰው ልጆች ወደ እርሻ ሲገቡ በተፈጠረው የአመጋገብ ለውጥ ምክንያት የተከሰተ የደም አይነት ነው። በዚያ ዘመንም የሰው ልጆች ለመኖነት ፊታቸውን ወደ አትክልቶች በማዞራቸው ምክንያት በጊዜ ሂደት እጅግ የዳበረ የምግብ ማላም ስረዓትን አዳበሩ። በአንጀታቸው ውስጥ የሚኙት የባክቴሪያዎች አይነትና ቁጥርም እጅግ ተበራከተ። የዚህ ደም ባለቤቶች ፖም፣ አቮካዶ፣ ሰላጣ፣ ካሮት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ባቄላ፣ እርጎ፣ የስንዴ ዳቦና ፓስታ እንዲመገቡ ይመከራል። ነገር ግን እንቁላል፣ ስጋና ዶሮ ከገበታቸው ማራቅ አለባቸው። 3) የቢ (B) ደም ዐይነት አመጋገብ ስርዓት የጥንቶቹ አዳኞች ወደ ሂማላያስ ተራሮች በመሰደድ እንስሳትንም በማላመድ የአርብቶ አደር ህይወትን በመምራት ሲጀምሩ የተፈጠረ የደም አይነት ነው። ቀይ ስጋ፣ ዓሳ፣ እርጎ፣ ዓይብ፣ ወተት፣ ሙዝ፣ አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልቶች፣ ወይንና አናናስ ተስማሚ ከሚባሉት ምግቦች መካከል ሲጠቀሱ ዶሮ፣ ስንዴ፣ ቲማቲም እንዲሁም ለውዝ እንዳይመገቡ ይመከራል። 4) የ ኤቢ (AB) ደም ዐይነት አመጋገብ ስርዓት ኤቢ የደም አይነት በቅርብ ጊዜ የተከሰተ ሲሆን ከዓለም ህዝብም በአምስትፐርሰንቱ ውስጥ ብቻ ይገኛል። የዚህ ደም ባለቤቶች ስጋና ሌሉች የእንስሳት ተዋፆኦችን መፍጨት ቢችሉም የጨጓራቸው አሲድ መጠን ዝቅተኛ በመሆኑ ምክንያት የተመገቡት ምግብ በስብ መልክ ይከማቻል። ፍራፍሬዎችና አረንጓዴ አትክልቶች፣ ሀብሀብ እና ወይን፣ እንደ ቱና እና ሰርዲን ያሉ የባህር ምግቦችን ማዘውተር ተገቢ ሲሆን ከቦቆሎ፣ የበሬና አሳማ ስጋ እንዲሁም ከአልኮልና ቡና መራቅ ያስፈልጋቸዋል።

ጎንደር ዩኒቨርሰቲ የሕክምና ቡድን ከግንቦት 08 – 15/2014 ዓ.ም የቆየ የዐይን ሕክምና (የዐይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና) ዘመቻ በማክሰኝት ከተማ አድርጓል፡፡ በህክምና ቡድኑ 27647 አጠቃላይ ልየታ ተደርጎ 13727 የመድሀኒት አገልግሎት ሲያገኙ 405 የአይን ሞራ ግርዶሽ እንዲሁም 119 የዐይን ቆብ መቀልበስ ቀዶ ጥገና እንደተደረገላቸው ከአቶ ሰማልኝ አበው (የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ አስተባባሪ) ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ህክምና የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከተለያዩ ቦታዎች ከፎገራ፣ ከሊቦ ከምገም፣ ከበለሳ፣ ከምዕራብና ምስራቅ ደንቢያ ወረዳዎች እንዲሁም ማክሰኝትን ጨምሮ ከምንዝሮ፣ ከእንፍራዝ፣ ከሰብሐ ከተማዎች የመጡ ሲሆን የትራንስፖርት፣ የምግብና የምኝታ ወጪአቸውን ፕሮጀክቱ እንደሸፈነላቸው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ [የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል]

Repost from N/a
ፅንስ ማስወረድ በመድሀኒት https://youtu.be/IMmhgBd0MXY ሙሉ ቪዲዮውን ለመመልከት ምስሉን ወይም ሊንኩን ይጫኑ!!

✍️#የጦጣ #ፈንጣጣ 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥️♥️#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥️♥️ 👉👉 #ከሰሞኑ በዩናይትድ ኪንግደም፣ ፖርቱጋል፣ ስፔን እና ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የጦጣ ፈንጣጣ (Monkeypox) ተከስቷል። በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና መረጃ ስርዓት አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዘውዱ አሰፋ ለአል ዓይን ኒውስ በሰጡት ቃል የተናገሩት ፦" ቫይረሱ ከዚህ በፊት ፈንጣጣ መሰሉ በሽታ ተጠቂ የሌለባቸው ሀገራት ሳይቀር እየተስፋፋ ነው፡፡እንደማንኛውም ሀገር እኛም በቫይረሱ ስርጭት ስጋት አለን። በኢትዮጵያ የመግቢያ እና መውጫ በሮች ላይ የተለመደው ክትትል እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ 👉👉 #መተላለፍያ #መንገድ 📌 የጦጣ ፈንጣጣ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ በሽታ ነው፡፡ 📌 ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው ከሰውነት ፈሳሾች ጋር በመገናኘት ፣ በቆዳ ላይ ለምሳሌ በአፍ ወይም በጉሮሮ፣ በመተንፈሻ አካላት ጠብታዎች እና በተበከሉ ነገሮች ላይ ሊተላለፍ ይችላል። 👉👉 #የበሽታው #ምልክቶች 📌 ራስ ምታት 📌 የጡንቻ ሕመም 📌 ብርድ ብርድ ማለት እና ድካም ያሳያሉ 📌 የንፍፊት እብጠት 📌 ትኩሳት 📌 ትኩሳት ከታየ ከ 1 እስከ 3 ቀናት ውስጥ በሰዉነት ላይ ሽፍታ ይወጣል። ሽፍታዉ ፊት ላይ ጀምሮ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ይስፋፋል። 👉👉 #የጦጣ #ፈንጣጣ #እና #የፈንጣጣ #ልዩነት 📌 በፈንጣጣ እና የጦጣ ፈንጣጣ ምልክቶች መካከል ያለው ዋነኛው ልዩነት የጦጣ ፈንጣጣ የንፍፊት እብጠት ሲያመጣ ፈንጣጣ አያመጣም። 👉👉 #የጦጣ #ፈንጣጣ #ሕክምና 📌 ይህ ነው የተባለ ህክምና ባይኖረውም ነገር ግን የፈንጣጣ ክትባት ለመነከላከል የሚሰጥ ይሆናል፡፡ 👉👉 ያስተውሉ:_ በአፍሪካ የጦጣ ፈንጣጣ በበሽታው ከተያዙት ከ10 ሰዎች ውስጥ 1 ሰዉ ላይ ሞት እንደሚያደርስ ታይቷል። #ሼር በማድረግ መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ በማድረግ ለሰው ልጅ መዳን ምክንያት እንሁን!! #ጆይን 👇 https://t.me/+6X9O71L_Vu1iY2Y0 https://t.me/+6X9O71L_Vu1iY2Y0

#Update የዓለም ጤና ድርጅት Monkeypox ገና ባልታወቀባቸው ሀገራት ክትትሉን በማስፋፋት ተጨማሪ የጦጣ ፈንጣጣ ሊገኝ እንደሚችል ገለጿል። አስካሁን ቢያንስ 92 በበሽታዉ የተጠቁ ሰዎች እና 2
#Update የዓለም ጤና ድርጅት Monkeypox ገና ባልታወቀባቸው ሀገራት ክትትሉን በማስፋፋት ተጨማሪ የጦጣ ፈንጣጣ ሊገኝ እንደሚችል ገለጿል። አስካሁን ቢያንስ 92 በበሽታዉ የተጠቁ ሰዎች እና 28 ተጠርጣሪዎች ቫይረሱ ካልተከሰተባቸው 12 ሀገራት ለአለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ተደርጓል።

ማድያት(ሜላዝማ) ​​ምንድን ነው? ማድያት/ሜላዝማ ​​ ተብሎ የሚጠራው ቡናማ ወይም ግራጫማ ቀለም ያላቸው ቀለሞች (ቀለም) የሚያድጉበት የአዋቂዎች የተለመደ የቆዳ ሁኔታ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ፊቱ ላይ ይከሰታል ፡፡ ብዙውን ጊዜ በሴቶች ላይ በተለይም በእርግዝና ወቅት የሚታይ ነው ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ወንዶችም ሊጠቁ ይችላሉ ፡፡ ሜላዝማ ​​ብዙውን ጊዜ በበጋ ወቅት ይበልጥ የሚታወቅ እና በክረምቱ ወቅት ይሻሻላል ፡፡ ማድያት/ሜላዝማ ​​መንስኤው ምንድን ነው? ትክክለኛው መንስኤ አይታወቅም ፣ ግን በቆዳ ውስጥ ቀለም የሚያመነጩ ህዋሳት (ሜላኖይቲስቶች) በጣም ብዙ ቀለሞችን (ሜላኒን) በመፍጠር ነው ተብሎ ይታሰባል ፡፡ እርግዝናን ጨምሮ እንደ የወሊድ መከላከያ ክኒን ጨምሮ በርካታ ነገሮች ለማድያት መፈጠር አስተዋፅዖ ሊያበረክቱ ይችላሉ ፡፡ አልፎ አልፎ በሆርሞኖች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ሌሎች የሕክምና ችግሮች (እንደ ታይሮይድ ዕጢ ችግሮች ያሉ) እንዲሁም እንደ ፀረ-የሚጥል በሽታ ያሉ ሌሎች መድኃኒቶች ማድያት ሊያስከትሉ ይችላሉ ፡፡ የፀሐይ አልትራቫዮሌት (UV) ብርሃን በብዛት መጋለጥ ማድያት እንዲነሳ ወይም እንዲባባስ ሊያደርግ ይችላል ፡፡ የህም ዋንኛው የማድያት ምክንያት ነው ። ማድያት ​​በዘር የሚተላለፍ ነውን? ሜላዝማ ​​የበሽታው ሁኔታ በቤተሰብ ታሪክ ባላቸው ሰዎች ላይ በጣም የተለመደ ነው ፣ ግን በዘር የሚተላለፍ አይደለ። በ ተወሰነ ደረጃ ተጋላጭነትን ይጨምራል። የማድያት ​​ምልክቶች ማድያት በዙሪያው ካለው ቆዳ የበለጠ ጠቁሮ ይታያል- ጉንጮቹን ፣ ግንባሩን ፣ የላይኛው ከንፈሩን ፣ አፍንጫውን እና አገጩን ይነካል ፡፡ እንደ ፊትለፊት እና አንገት ያሉ ለፀሐይ በተጋለጡ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ላይም ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል ፡፡ ብዙ ሕመምተኞች በማድያት መልክ ይበሳጫሉ ወይ ይጨነቃሉ ፣ ግን የተጎዳው ቆዳ የሚያሳክክም ሆነ የሚያሠቃይ አይደለም ፡፡ ማድያት ​​ሊፈወስ ይችላልን? አጅግ ውጤታማ የሚባል መድኃኒት የለውም ፣ ግን መልክን ሊያሻሽሉ የሚችሉ በርካታ የሕክምና አማራጮች አሉ ፡፡ በእርግዝና ወቅት ማድያት ከተከሰተ ከወሊድ በኋላ ጥቂት ወራቶች ሊጠፉ ይችላሉ እናም ህክምናው አስፈላጊ ላይሆን ይችላል ፡፡ ፅንሱን ሊጎዱ ስለሚችሉ ሃይድሮኮኒኖንና ሬቲኖይድ ክሬሞች በእርግዝና ወቅት መወገድ አለባቸው ፡፡ ቢታከም እንኳ ብዙውን ጊዜ ሕክምናዎቹ ከቆሙ በኋላ ይመለሳል ፡፡ እንዴት መታከም ይችላል? እንደ የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒኖች እና ሆርሞን ቴራፒ ያሉ የታወቁ ቀስቃሽ ነገሮችን ማስወገድ ፡፡ ፀሐይን ማስወገድ እና የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መጠቀም ፡፡ የቆዳ ማንጫ ቅባቶች ፣ ኬሚካል ፒልስ(chemical Peel ) ፣ ማይክሮኔይሊንግ እና ሌዘር ቴራፒ ያሉ አማራጮችን መጠቀም ይቻላል ፡፡ በምርመራ የተረጋገጠ የውስጥ ህመም ካለም ማከም አስፈላጊ ነው። ህክምናው ውጤታማ ለማድረግ ከ 3-6 ወራት ሊወስድ ይችላል። በ ዶ/ር ተስፋማርያም ፀጋዬ የ ቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት

የማደንዘዣ መድሃኒቶች ያለህ! ላለፉት ጥቂት ሳምንታት ሁሉም በሚባል ደረጃ የመንግስት ሆሰፒታሎች በማደንዘዣ መድሃኒቶች እጥረት ምክንያት የኦፕሬሽን አገልግሎት አቁመዋል፡፡ ይህ ችግር መቼ እንደሚፈታ አይታወቅም፡፡ በዚህ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ታካሚዎች በተራዘመ የኦፕሬሽን ቀጠሮ እየተጉላሉ ይገኛሉ፡፡ ሃኪሞችም ብንሆን ስራ ፈተን ሌሎች ብሶቶቻችንን ማዳመጥ ጀምረናል፡፡ እነዚህን መድሃኒቶች ለጤና ተቋማቱ ገዝቶ ማቅረብ ያለበት መስሪያቤት ይህንን ችግር እስቀድሞ በመረዳት ዝግጅት በማድረግ መቅረብ ነበረበት ኣላደረገም፡፡ ለምን? ችግሩ ያለው የት ነው? * የውጭ ምንዛሪ እጥረት፡- ብዙ ሰው ሰበብ የሚያደርገው በውጭ ምንዛሪ እጥረት ነው፡፡ ነገር ግን ለውስኪ፣ ለኮስሞቲክስ፣ እና ለዘመናዊ መኪኖች የዶላር እጥረት ገጥሞን የማያውቅ ለምን ይሆን ለመድሃኒት እና ለህክምና እቃዎች መግዣ እጥረት የሚገጥመን? በምሽት ክበቦች ብንሄድ ሰዎች እጅግ ውድ የሚባሉ ውስኪዎች ሲራጩ እንመለከታለን ፣ ትልልቅ መንግሰታዊ ስብሰባዎች ሲኖሩ በስብሰባው አዳራሽ አካባቢ የሚደረደሩ የV8 እና ሌሎች እጅግ ውድና ዘመናዊ መኪኖች ብዛት ሲታይ መሰረታዊ ፍጆታችንን ያሟላን (ምግብና መድሃኒት) እንመስላለን፡፡ (ቅናት የተቀላቀለበት አስተያየት እንደሆነ ይወሰድ) *ሁሉ አቀፍ ግድ የለሽነት፡- ሃኪሞች፣ የጤና ተቋማቱ ሃላፊዎች፣ በየቢሮው ያሉ ባለስልጣናት ባጠቃላይ በምንቸገረኝነት ተጠፍንገን ዝም ብለናል፡፡ ይህ ችግር የተከሰተው በእንድ አዳር አይደለም፡፡ ለወራት ምናልባትም ለአመት ያህል ሲንከባለል የመጣ ችግር ነው፡፡ በየሆስፒታሉ ያለን ሃኪሞች በበቂ ሁኔታ አልጮህንም፣ ችግሩ ቀጥታ የሚመለከታቸው የየሆስፒታሎቹ ሃላፊዎች አለቆቻቸውን ላለማስቀየም ጸጥ ብለዋል፣ በቀጥታም በተዘዋዋሪም ጉዳዩን የሚሰሙ የጤና ባለ ስልጣናትም ባላየ ባልሰማ ዝም ብለዋል፡፡ መድሃኒቱን ማቅረብ ያለበት መስሪያ ቤትም ቢጠየቅ አሳማኝ የሚመስል ምክንያት አዘጋጅቶ ቁጭ ብሏል፡፡ በኛ አገር በማንኛውም መስክ ሰዎች የሚጠየቁት ሲሰሩ በሚያጠፉ ዜጎች ላይ እንጂ ባልተሰራ ጉዳይ በሚመጣ ቀውስ አይደለም፡፡ አንድ ቀዶ ሃኪም ካቅም በላይ በሆነ ችግር ህይወት ለማዳን ብሎ ግዜው ባለፈበት መድሃኒት ቢጠቀምና ታካሚው ችግር ቢደርስበት ሁሉም በዛ ምስኪን ሃኪም ላይ ጣቱን ይቀስራል፡፡ ይህ ሃኪም ወይም ሰመመን ሰጪ ባለሞያ ለዚህ ሁኔታ እንዴት ተዳረገ ብሎ የሚጠይቅ ማህበረሰብም ሆነ ስርአት የለንም፡፡ በዚህም ምክንያት ዜጎች “ባለመስራት አለመጠየቅን” እንደመፍትሄ ቆጠረውታል፡፡ * የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀም ፖሊሲያችን፡- በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም እውቀትም ባይኖረንም የምንመለከተው ነገር መንግስት የውጭ ምንዛሬን ወደራሱ ለመሳብ የሚጠቀማቸወው ዘዴዎች ሁሉ እየሰሩ አይመስሉም፡፡ ከጊዜ ወደግዜ ዜጎችም የሚያገኙትን ዶላር ከመንግስት እያራቁ ነው የሚገኘው ለምን? ስግብገብ ስለሆኑ? ስግብግብ ነጋዴ ያለው እኛ አገር ብቻ አይመስለንም፡፡ በየአገሩ አሉ፡፡ የመፍትሄ ሀሳቦች ተጠያቂነት፡- የዜጎች ተጠያቂነት ሊኖር የሚገባው በስራ ላይ ለተፈጠረ ስህተት ብቻ ሳይሆን ሃላፊነትን ባለመወጣት ለተፈጠሩ ቀውሶችም መሆን አለበት፡፡ አገሪቱን እና ዜጎችን ከግዜ ወደግዜ ትልቅ ችገር ውስጥ እየከተተ የሚገኘውን ሌብነትንና ሙስናን መንግስት ሳይውል ሳያድር በመግለጫ ሳይሆን በተግባር መዋጋት መጀመር አለበት፡፡ አንዱ የችግሩ ምንጭ ሙስና ስለሆነ፡፡ ኮሚሽን የማይገኝበት ግዢ መፈጸም ወይም አገልግሎት መስጠት በዚህ ዘመን ብርቅ እየሆነ ነው፡፡ የውጭ ምንዛሪ ፖሊሲዎቻችንን መፈተሽ፡- ይህ ጉዳይ በሹመኞች ሳይሆን በሙያው ሊቆች ሊወሰን ይሚገባው ጉዳይ ነው ብለን እናስባለን፡፡ ለግዜው ግን መንግስት ይህንን ግዢ ለሚፈጽመው መስሪያ ቤት በአስቸኳይ ገንዘብ መድቦ ግዢውን እንዲፈጽም ቢያደርግ ወይም ግዢው በቀላሉ ሊከወን የሚችልበትን መንገድ ቢፈጥር፤ በንዝህላልነት የተፈጠረ ችግር ከሆነ መጠየቅ ያለበትን አካል ተጠያቂ ማድረግ፡፡ ለግል መድሃኒትና የህክምና አስመጪ ተቋማትም በቂ የውጪ ምንዛሬ እንዲያገኙ ቢደረግ፤ ያገኙትን ገንዘብ ለሌላ ነገሮች ግዢ አለማዋላቸውን በጥብቅ መቆጣጠር፤ በውጭ አካውንት ያላቸው ዜጎች ውጭ ያላቸውን ገንዘብ መድሃኒት እና የህክምና እቃዎችን እንዲያመጡበትን እና የሚበረታቱበትን አሰራሮችን መፍጠር፡፡ ይህ የመድሃኒት ችግሮቻችንን በከፊል የሚቀንስልን ሲሆን በተጨማሪም ካገር ውስጥ ተመልሶ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ ሊቀንስ እና ለሌላ ጉዳይ ሊዉል ይችላል፡፡ በውጭምንዛሬ አጠቃቀም ጉዳይ ላይ የተሰጠው አስተያየት በእውቀት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን እንዳንድ ተራ ዜጋ (lay man) በስሜት የተሰጠ አስተያት ተደርጎ ይወሰድ፡፡ መቋጠሪያ፡- አብዛኛው ሆስፒታሎች የኦፕሬሽን አገልግሎት አቁመው ዜጎች እየተጉላሉም ጤናቸውም አደጋ ላይ እየወደቀ ነው፡፡ ሰለዚህ የማደንዘዣ መድሃኒቶች የምናገኝበት መንገድ ባስቸኳይ ይፈለግ፡፡ - ዶ/ር መዝገብ ገደፌ - ዩሮሎጂስት https://t.me/DrJano https://t.me/DrJano

በጥያቄአቹ መሰረት ስለጤናችን የምንወያይበት Dr. Jano የቴሌግራም ግሩፑ ከፍተናል ተቀላቀሉን!! በተጨማሪም ወዳጅ ዘመዶን ወደ ግሩፑ አድ አድርጉ!! 👇👇👇👇 https://t.me/+AShRrcxs3KZhMjlk

የእግር ሽታ ለመቀነስ👇👇 💧እግር አብዛኛውን ግዜ ሽታ የሚያመጣው ላብ ነክቶት ያልደረቀ ካልሲ ወይም ጫማ ካደረግን ነው ስለዚህ 💧አንድ ጫማ ከሁለት ቀን በላይ አከታትሎ አለማድረግ 💧ጫማችን እንዲደርቅ በትንሹ 24ሰአት ንፋስ ላይ ማቆየት 💧ካልሲ በየቀኑ መቀየር የካልሲው አይነት ኮተን ቢሆን ጥሩ ነው 💧እግራችንን በ አንቲ ባክቴሪያል ሳሙና (ላይፍ ቦይ መታጠብ) 💧ከታጠብን በኋላ እግራችንን በአግባቡ ማድረቅ 💧ጥፍራችንን መቆረጥ እና ማጽዳት 💧ጠንካራ ቦታዎችን ሞቅ ባለ ውሀ ዘፍዝፎ በእግር መፈቅፈቂያ ማስወገድ አነዚህ ቦታዎች ላብ ሲነካቸው ይሞቀሙቃሉ ለሽታም ያጋልጣሉ 💧ከእነዚህ ጥንቃቄዎች አልፎ ካስቸገረ ግን የህክምና ባለሙያ ማማከር ያስፈልጋል