fa
Feedback
ኮሮጆ bags 💼 & Gift shop 🎁

ኮሮጆ bags 💼 & Gift shop 🎁

رفتن به کانال در Telegram

👉plexiglass 👉engraving 👉orginal cosmotics 👉 natural face products like Kesil 👉Gift packages 📞0942410512 metis_bag 🏠🏠 Megenagna 3M Mall 1st floor

نمایش بیشتر
1 896
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-47 عوز
-2830 عوز
آرشیو پست ها
✍ #የጥቁር #አዝሙድ #የጤና #ጥቅሞች 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #ጥቁር አዝሙድ ከመቶ በላይ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ይይዛል ከነዚህ መካከል ፕሮቲን ፣ካርቦሃይድሬት፣የስብ አሲዶች ፣ካልሲየም ፣ፖታሲየም ፣ብረት ፣ዚንክ፣ማግኒዥየም ፣ቫይታሚን ኤ፣ቢ፣ሲ በዋናነት ይይዛል፡፡ከዚህ በታች ከበርካታ የጥቁር አዝሙድ ጥቅሞች መካከል የተወሰኑት ተዘርዝረዋል፡፡ 🔺#ለመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን • በዘይቱ ደረትንና ጀርባን ማሸት፤ በቀን ሦስት የሾርባ ማንኪያ መጠጣት እንዲሁም ሁለት ማንኪያ በፈላ ውኃ ውስጥ ጨምሮ በእንፋሎቱን ቤትን ማጠን 🔺#ለራስ ምታት • በጥቁር አዝሙድ ዘይት ግንባርንና በጆሮ አካባቢ ያለውን አካል ማሸት ፤ለሦስት ተከታታይ ቀናት አንድ ሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በባዶ ሆድ መጠጣት 🔺#ለጀርባ ሕመም • የተወሰነ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በጥቂቱ በማሞቅ የታመመውን አካል አጥንትን ዘልቆ እስኪሰማ ድረስ በዘይቱ በደንብ መታሸት በቀን ሦስት ጊዜ አንድ የሾርባ ማንኪያ ዘይት መጠጣት 🔺#ለልብ ሕመም • የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከትኩስ መጠጥ ጋር በተከታታይ መውሰድ ስብን ለማሟሟትና የደም ሥሮችን ለማስፋት ይረዳል 🔺#ለደም ብዛት • ትኩስ መጠጥ ባሰኘው መጠን ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ዘይት ጠብታዎችን ጨምሮ መጠጣት፡፡ በተጨማሪም ገላውን ጥቁር አዝሙድ በመቀባት ቢያንስ በየሳምንቱ አንድ ጊዜ የፀሐይ ሙቀት ማግኘት 🔺#ለጨጓራ አሲድ • አንድ ኩባያ ወተት የአንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በቀን ሦስት ጊዜ መውሰድ 🔺#ለኩላሊት ኢንፌክሽን • አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ በየቀኑ በባዶ ሆድ ለአንድ ሳምንት ጥሬውን መቃም፤ ጥቁር አዝሙድን በሚገባ መፍጨትና ከማር ጋር ቀይጦ በሚገባ ማዋሀድ ከዚያም ሁለት ማንኪያ ከቅይጡ ቀንሶ በአንድ ብርጭቆ የሞቀ ውኃ ውስጥ ጨምሮ በባዶ ሆድ መጠጣት 🔺#ለሐሞት ከረጢት • አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዱቄት፣ ሩብ ማንኪያ የተፈጨ እሬት፣ አንድ ኩባያ ማር ጋር መለወስና ጧትና ማታ መብላት 🔺#ለጉሮሮ ሕመም • የጥቁር አዝሙድ አፍልቶ መጉመጥመጥና አንድ ማንኪያ አዘጋጅቶ ለብ ባለ ውኃ ውስጥ ጨምሮ መጠጣትና በዘይቱም የጉሮሮን ውጫዊ አካል መቀባት በውስጥ ደግሞ መንጋጋን መቀባት 🔺#ለቆዳ ውበት • አንድ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ማንኪያ የወይራ ዘይት ጋር አዋሕዶ ፊትን መቀባት አንድ ሰዓት ቆይቶ በውኃና በሳሙና መታጠብ 🔺#የማስታወስ ችሎታንና ፈጣን የግንዛቤ አቅምን ለመጨመር • አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት፣ 100 ሚሊ ሊትር የፈላ ናና ተክል ጋር ተቀላቅሎ ለአሥር ተከታታይ ቀናት መውሰድ 🔺#ለጭንቀት • አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በባዶ ሆድ መውሰድ ሰዉነትን ያረጋጋል አንድ ትልቅ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ሲኒ ቡና ውስጥ ጨምሮ መጠጣት የአእምሮ ጭንቀትን አስወግዶ መረጋጋትን ያስገኛል !!! ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇 https://t.me/DrJano https://t.me/DrJano

በጥያቄአቹ መሰረት ስለጤናችን የምንወያይበት Dr. Jano የቴሌግራም ግሩፑ ከፍተናል ተቀላቀሉን!! በተጨማሪም ወዳጅ ዘመዶን ወደ ግሩፑ አድ አድርጉ!! 👇👇👇👇 https://t.me/+AShRrcxs3KZhMjlk

✍ #ነስር #ሊያስከትሉ #የሚችሉ #መንስኤዎች #ምንድን #ናቸዉ? 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ 👉👉 #ነስር (epistaxis) ድንገተኛ የሆነ አስደንጋጭ ከአፍንጫ ደም መፍሰስ ሲሆን በአብዛኛው ለከፋ አደጋ የማይዳርግ የሕመም ዓይነት ነው፡፡ነስርን ከሚነሳበት ክፍል በመነሳት በሁለት ይከፈላል፡፡ 1, ከፊተኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (Anterior Nosebleeds) ከአፍንጫ ቀደዳዎች መካከል አካባቢ የሚገኙ የደም ስሮች ሲጎዱ የሚከሰት ሲሆን ከ90 በመቶ በላይ ለሚከሰት የነስር ዓይነት ምክንያት ነው፡፡አብዛኛዉን ጊዜ ህፃናት ላይ ይከሰታል እንዲሁም በቀላሉ መቆጣጠር ይቻላል፡፡ 2, ከኋለኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (Posterior Nosebleeds) በአብዛኘው በዕድሜ በገፉ ሰዎች ላይ ይከሰታል፡፡ ወደ ዉስጥ ካሉ የደም ስሮች የሚመጣ መጠኑ በዛ ያለ ደም ይኖረዋል እናም የተለየ ሕክምና የሚያስፈልገው እና ውስብስብ ነው፡፡ 👉👉 #ነስርን #የሚያመጡ #መንስኤዎች 📌 በአፍንጫ ላይ አደጋ/ አፍንጫ መጎርጎር 📌 የደም ግፊት መጨመር 📌 የደም መርጋት ችግር 📌 የደም ማቅጠኛ መድሐኒቶች 📌 የመተንፈሻ አካላት ህመም 📌 ቀዘቃዛ እና ደረቅ የአየር ንብረት 📌 ለኬሚካል ተጋላጭ መሆን 📌 አልኮል እና በአፍንጫ የሚወሰዱ አደንዛዥ እጽ 📌 እርግዝና 👉👉 #ነስርን #መከላከያ #መንገዶች 📌 በአብዛኛው ነስር የሚከሰተው በቀዘቀዘ እና በደረቅ የአየር ንብረት ስለሆነ አፍንጫ እንዳይደርቅ ቫዝሊን (Petroleum jelly) መጠቀም 📌 አፍንጫዎን በጣትዎ አለመነካካት 📌 የነስር መንስኤ ከሌላ የጤና ችግር ጋር ተያያዥነት ካለው ሐኪም ማማከር 📌 ሲጋራ ከማጨስ መቆጠብ 👉👉 #ነስር #ከተከሰተ #በኋላ #ወደ #ሐኪም #መሄድ #የሚያስፈልገው #መቼ #ነው? 📌 አፍንጫዎን ለ10 ደቂቃ ያህል ይዘው ቆይተው ነስሩ ካልቆመ 📌 ወዲያዉኑ ወዲዉኑ በተደጋጋሚ የሚነስር ከሆነ 📌 ለነስሩ ጋር ተያይዞ ደም ማስመለስ ካለ 📌 ራስ ማዞር ወይንም ራስ መሳት ካለዉ 📌 ከፍተኛ ትኩሳት ካለ 📌 የልብ ምት የሚጨምር ከሆነ እና ለመተንፈስ መቸገር ካለ 📌 ሰውነት ላይ ሽፍታ/መበለዝ ካለ 📌 ከአፍንጫ ሌላ ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች ደም መፍሰስ ካለ 📌 ደምን ለማቅጠን የሚጠቅሙ መድኃኒቶችን የሚወስዱ ከሆነ 📌 የደም መርጋትን የሚያስተጓጉሉ ማንኛውንም ዓይንት ሕመም ካለ 📌 የኬሞቴራፒ ሕክምና በቅርቡ ወስደው ከነበረ 👉👉 #ነስርን #እንዴት #ማቆም #ይቻላል? 📌 ከጭንቅላትዎ ጎንበስ ማለት (ጭንቅላትን ወደ ላይ ቀና ማድረግ የሚፈሰውን ደም ወደ ጉሮሮ በማምጣት ጉዳት ያስከትላል) 📌 ቀጥ ብለው መቀመጥ 📌 ሁለቱም የአፍንጫ ቀዳዳዎች በአውራ ጣት እና በጠቋሚ ጣት ግጥም አድርጎ ለአስር ደቂቃ ይዞ ማቆየት 📌 በአፍ የሚመጣን ደም መትፋት 📌 ነስሩ ካቆመ በኋላ አፍንጫዎን አለመነካካት 📌 ቢያንስ ለ24 ሰአታት ያህል ሞቅ ያሉ መጠጦችን አለመጠቀም 👉👉 #የነስር #በምን ይታከማል? 📌 ደም በሚፈስበት ቦታ የአፍንጫ እስፖንጅ ማስገባት እና ከ 24-48 ሰአት ማቆየት(የሚገባዉም ሆነ የሚዎጣዉም በጤና ባለሙያ እርዳታ ነዉ፡፡) 📌 ለደም መርጋት የሚሆኑ መድሀኒቶች 📌 የተቀደዱ የደም ስሮችን ካሉ በኬሚካል(ሲሊቨር ናይትሬት በመጠቀም) እና በቀዶ ህክምና ማስተካከል ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇 https://t.me/DrJano https://t.me/DrJano

በጥያቄአቹ መሰረት ስለጤናችን የምንወያይበት Dr. Jano የቴሌግራም ግሩፑ ከፍተናል ተቀላቀሉን!! በተጨማሪም ወዳጅ ዘመዶን ወደ ግሩፑ አድ አድርጉ!! 👇👇👇👇 https://t.me/+AShRrcxs3KZhMjlk

በጥያቄአቹ መሰረት ስለጤናችን የምንወያይበት Dr. Jano የቴሌግራም ግሩፑ ከፍተናል ተቀላቀሉን!! በተጨማሪም ወዳጅ ዘመዶን ወደ ግሩፑ አድ አድርጉ!! 👇👇👇👇 https://t.me/+AShRrcxs3KZhMjlk

የእንቅልፍ አተኛኘት አቅጣጫ ጥሩ እና መጥፎ ጎናቸው! 1. በጀርባቸው የሚተኙ! 🔻 ጥቅሙ በጀርባ መተኛት ትራስ አከርካሪን የመደገፍ ሥራውን በትክክል እንዲወጣ ይረዳዋል። በትክክለኛው አለም ሁሉም ሰው ትራስ ሳይጠቀም በጀርባው መተኛት ይፈልጋሉ፤ ይህም አቅጣጫ አንገታችን ነፃ አቅጣጫ ላይ እንዲሆን ይረዳዋል። ከመጠን በላይ/ብዙ ትራስ መጠቀም የአተነፋፈስ ሥርዓትን አስቸጋሪ ያደርገዋል። በጀርባ መተኛት ውበትን ከመጠበቅ አንፃር ይመከራል፤ ሌሊቱን ሙሉ ፊታችን ለንጽህ አየር እንዲጋለጥ በማድረግ ይረዳል። የተጠቀምነው የውበት መጠበቂያ ኮስሞቲክስ በትራሱ እንዳይጠረግ ከማድረጉ በተጨማሪ የፊት መሸብሸብን ወይም መጨማደድን ይቀንሳል። 🔻 ጉዳቱ ማንኮራፋት እና የእንቅልፍ እጦት በጀርባ ተንጋሎ ከመተኛት አቅጣጫ ጋር ይያያዛሉ። በነገራችን ላይ በጀርባ መተኛት ከእንቅልፍ እጦት ጋር በቅርበት የተገናኘ ነው ለዚህም ነው ዶክተሮች በጎን አቅጣጫ በኩል መተኛትን እንደመፍትሄ የሚመክሩት። በጀርባችን በምንተኛበት ወቅት የመሬት ስበት ሃይል የምላሳችን ሥር ወደ አየር ቧንቧ አቅጣጫ እንዲታጠፍ ያስገድደዋል ይህም ሥርዓተ ትንፈሳን በማስተጓጎል ጎረቤትን እንቅልፍ የሚነሳ አስቀያሚ ማንኮራፋት እንዲፈጠር ያደርጋል። ጥሩ እንቅልፍ የሚተኙ እና ጥሩ ያልሆነ እንቅልፍ የሚተኙ ሰዎችን በማነፃፀር የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው፦ ጥሩ ያልሆነ እንቅልፍ የሚተኙ ሰዎች አብዛኛውን የመኝታ ጊዜ የሚያሳልፉት በጀርባቸው እንደሆነ አረጋግጠዋል። 2. በጎናቸው የሚተኙ! 🔸 ጥቅሙ በጎናቸው የሚተኙ ሰዎች በአንድ ላይ! ማህፀን ውስጥ እንዳለ ጽንስ እግራቸውን እጥፍጥፍ አድርገው የሚተኙ እና እግራቸውን ዘርግተው የሚተኙ ሰዎች፤ አብዛኛው ማህበረሰብ በጎን በኩል እንደሚተኙ ሪፓርት ተደርጓል። በእርግዝና ወቅት በግራ ጎን በኩል እንዲተኙ ዶክተሮች ይመክራሉ፤ ምክንያቱም ወደ ልብ ያለውን የደም ፍሰት ስለሚጨምር ነው ይህም ለእናት እና ልጅ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው። በእርግዝና ወቅት በጎን በኩል እንድትተኚ ይመከራል ምክንያቱም በጀርባ በኩል መተኛት የታችኛው ጀርባ ላይ ግፊት ይፈጥራል (በአብዛኛው ፌንት እንድታደርጊ አስተዋጽዎ ያድርጋል)። እንደሚታወቀው በእርግዝና ወቅት በሆድ በኩል መተኛት አይቻልም። 🔸 ጉዳቱ በተመሳሳይ ሁኔታ በግራ ጎን በኩል መተኛት ሆድ እና ሳንባ ላይ ጫና እንዲፈጠር ያደርጋል። ሁሉም በጎናቸው የሚተኙ ሰዎች እንደሚያውቁት በዚህ አቅጣጫ በሚተኙበት ወቅት የእጅ መደንዘዝ ሊያጋጥም ይችላል። ጭንቅላትን እጅ ላይ አስደግፎ መተኛት የተለመደ አቅጣጫ ነው። ነገር ግን በጡንቻ እና ነርቭ ላይ ተጨማሪ ጉዳት ያስከትላል። ጭንቅላትን (አጠቃላይ ሰውነትን) በአንድ እጅ ላይ ማሳረፍ የደም ፍሰትን ይከለክላል በተጨማሪም ነርቭን ወደታች ይጫናል። 3. በሆዳቸው የሚተኙ! 🔹 ጥቅሙ በሆድ በኩል መተኛት ማንኮራፋት እና የእንቅልፍ ችግርን ያስቀራል። ነገር ግን በጣም ጥሩ የሚባለው ጎኑ በሌሊት ሠዓት ቦርጫችን ወደ ውስጥ እንዲገባ ያደርጋል። 🔹 ጉዳቱ በሆድ በኩል መተኛት በአብዛኛው እንደሚታወቀው በጣም አስቀያሚ የሚባል የአተኛኘት አቅጣጫ ነው። የአከርካሪ የተፈጥሮ መንጋደድን በማዛባት ቀጥ እንዲል ያደርገዋል ይህም የታችኛው ጀርባ ህመምን ያስከትላል። ሌሊቱን ሙሉ ጭንቅላትን ወደ አንድ አቅጣጫ አድርጎ መተኛት የአንገት ህመምን ያስከትላል። ይህ የአተኛኘት አቅጣጫ ምርጫዎ ከሆነ ትራስ በመጠቀም ሰውነትዎ በአንድ አቅጣጫ መተኛትም ያለማምዱት። ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇 https://t.me/DrJano https://t.me/DrJano

🔥ሰበር ዜና 🔥 በተለያዮ ትምህርት ቤቶች እና ዮኒቨርሲቲዎች የተሰጡ ፈተናዎችንን ና አጋዥ መፅሀፎች PDFዎች በቀጥታ ለማግኘት የሚረዳ ቻናልን ይቀላቀሉ!! @EthExam @EthExam @EthExam @EthExam ለወዳጆ ሼር ያድርጉ!!

ለእለተ ሰንበት ይዘንላችሁ የቀረብነው ስለእግር ተረከዝ ውበት አጠባበቅ ነው :: ለእግር ተረከዝ ማስዋቢያ በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ ውህዶች: ♤ አዘገጃጀት  የሰሊጥ ዠይት ፦ የሰሊጥ ዘይቱን በእጃችን የተሰነጣጠቀ ተረገዛችንን በመቀባት በደንብ ማሸት - የጥጥ ካልሲ አድርጎ መተኛት ከዛም በሳሙና ታጥቦ ሎሽን ወይም ግሪሲሊን መቀባት  ሎሚና ግሪስሊን ፦ ሙቅ ውሃ መዘፍዘፊያ ውስጥ በመጨመር 1 የሻይ ማንኪያ ጨው ፣2 የሾርባ ማንኪያ ግሪስሊን በማዋሃድ ፣ እግራችንን ለ 10 እስከ 15 ደቂቃ ያህል መዘፍዘፍ ከዛም በእግር መፈግፈጊያ ተረከዛችንን መፈግፈግ እና በንጹህ ውሃ አለቅልቆ ግሪስሊን እና ቫዝሊን አንድ ላይ መቀባት ይህን በሳምንት ሁለቴ መተግበር  የሎሚ ጭማቂ እና ቫዝሊን ፦ ቫዝሊኑንና የሎሚ ጭማቂውን አንድ ላይ በመደባለቅ የተሰነጣጠቀው ተረከዝ ላይ መቀባት ከ15 – 20 ደቂቃ አቆይቶ በሙቅ ውሃ መታጠብ እና ማድረቅ ከዛም የሎሚ ጭማቂ በድጋሚ ቀብቶ ካልሲ አድርጎ ማሳደር እና ጠዋት መታጠብ  ማር እና ቤኪንግ ሶዳ ፦ አንድ የሻይ ማንኪያ ቤኪንግ ሶዳ፣ማር ፣ ሙቅ ውሃ በመዘፍዘፊያ በማድረግ ማዋሃድ ከዛ ከ 15- 20 ደቂቃ ያህል እግራችንን በመዘፍዘፍ በእግር ብሩሽ ማሸት ፣ በንጹህ ውሃ ተለቅልቀን የወይራ ዘይት ወይም ሎሽን መቀባት:: ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇 https://t.me/DrJano https://t.me/DrJano

የወር አበባ (የፐሬድ) ህመም‼️ 🖌ዶ/ር መስፍን ገ/እግዚአብሔር #በፐሬድ_ጊዜ_ለምንድነው_ህመም_የሚኖረኝ ? ✍በዚህ ወቅት ሰውነትዎ ፕሮስታግላንዲን የሚባሉ ኬሚካሎችን ያመነጫል።እነዚህ ኬሚካሎች በምጥ ጊዜ የሚኖረው አይነት የማህጸን ቁርጠት ያመጣሉ። ይህ በወር አበባ ጊዜ የሚከሰት ህመም የጤና ባለሞያዎች ዲስመኖርያ( dysmenorrhea) በማለት ይጠሩታል። ✍አንዳንድ የማህጸን በሽታዎች በወር አበባ ወቅት የሚኖረውን ህመም ያባብሱታል። ይህ ችግር ከሚያባብሱት መካከል ኢንዶመትርዮሲስ፣ የማህጸን ኢጢ እና የማህጸን ኢንፌክሽን ተጠቃሽ ናቸዉ። #የህመም_ስሜቱ_ምን_የመስላል? ✍ የፐሬድ ህመም ያላቸው ሴቶች የታችኛው የሆድ አከባቢ ቁርጠት ይኖራቸዋል። ቁርጠቱ ቀላል ወይም ከባድ ሊሆን ይችላል። በተጨማሪም የጀርባ ወይም በጭን አከባቢ ህመም ሊኖር ይችላል። ህመሙ ፐሬድ እንደጀመረ ወይም ከመጀመሩ ከጥቂት ሰአታት በፊት ሊጀምር ይችላል። ✍ አንዳንድ ሴቶች በተጨማሪ የሚከተሉት የህመም ስሜቶች ይታዬባቸዋል ● ማጥወልወል ● ተቅማጥ ● በጣም ከባድ የድካም ሰሜት ● ራስ ምታት ● ሆድ የመንፋት ስሜት #ጥሩ_ስሜት_እንዲሰማኝ_ማድረግ_የምችለው_ነገር_አለ? ✍ አዎ የሚከተሉት በማድረግ ጥሩ ስሜት እንዲሰማዎ ማድረግ ይችላሉ። ● የፐሬድ መምጣት ምልክቶች እንደጀመሩ ወዲያውኑ እንደ ዲክሎፌናክ የመሳሰሉ የህመም ማስታገሻ ክኒኖችን መዋጥ ይጀምሩ። ከዚያም 2 ወይም ለ 3 ቀናት መውሰድዎን ይቀጥሉ። ● በታችኛው የሆድዎ አከባቢ ላይ የሞቀ ፓድን ወይም ሙቅ ውሃ የያዘ ጠርሙ ያድርጉ ● በመደበኛነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ #ዶክተር_ወይም_ነርስ_ማየት_አለብኝ? ✍ከስር የተዘረዘሩት ምልክቶች ከታዩብዎ ሐኪምዎን ወይም ነርስዎን ያማክሩ ● ህመሙ እየባሰ ከመጣ ● ህመሙ የህመም ማስታገሻ መድኃኒት ካላስታገሰው ● ህመሙ ከፐሬድ ውጪ የሚቀጥል ከሆነ #ላደርጋቸው_የሚገባኝ_ምርመራዎች_አሉን? ✍የርስዎ እድሜ ፣ ሌሎች ተጨማሪ ምልክቶች እና ግለሰባዊ ሁኔታዎች መሰረት በማድረግ ምንአይነት ምርመራ ማድረግ እንዳለብዎት ሐኪምዎ ወይም ነርስ ይወስናሉ። ✍አብዛኛዎቹ ሴቶች የአካል ምርመራ ብቻ ያስፈልጋቸዋል። አንዳንድ ጊዜ ግን ተጨማሪ ምርመራዎች ሊያስፈልጉ ይችላሉ። ለምሳሌ ፦ ● የማህጸን አልትራሳውንድ ● የአባላዘር በሽታዎች ምርመራ እና ● ላፓሮስኮፒ ከሚያስፈልጉ ምርመራዎች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው። #የፐሬድ_ህመም_ህክምናው_ምንድን_ነው ? ✍ህክምናው በመንስኤው ላይ የተመሰረተ ነው። በጣም የተለመዱት ሕክምናዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላል። ● የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች ● የወሊድ መከላከያ ክኒን ወይም ሌላ ዓይነት የወሊድ መቆጣጠሪያዎችን (ሆርሞኖችን) ያጠቃልላል:: ___ ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇 https://t.me/DrJano https://t.me/DrJano

የፊንጢጣ ኪንታሮት ፩. መግቢያ የፊንጢጣ ኪንታሮት ማለት በፊንጢጣ ቬን (Vein) መለጠጥ (Dilation) የሚመጣ የህመም አይነት ሲሆን ሁለት አይነት ናቸው። እነርሱም ውስጣዊ እና ውጫዊ ተብለው ይጠራሉ። ፪. አጋላጭ ሁኔታዎች 👉 ድርቀት (Constipation) 👉 ሽንት ቤት ለረጅም ሰዓት ማማጥ (Sitting on toilet for a long time) 👉 ከመጠን በላይ ውፍረት 👉 እርግዝና 👉 ሆድ ውሰጥ ብዙ ውሃ ፈሳሽ (Fluid) መኖር /Ascites/ ፫. ምልክቶች 🔸 ህመም የሌለው ደማቅ ቀይ ደም በፊንጢጣ መፍሰስ 🔸 ንፍጥ መሰል ነገር በፊንጢጣ መፍሰስ (Mucus Discharge) 🔸 በፊንጢጣ ሥጋ መሰል ነገር መውጣት (Mass per anus) 🔸 በፊንጢጣ ሥጋ መሰል ነገር በሚውጣት ጊዜ የህመም ስሜት (Pain during mass per anus) ፬. መከላከያ መንገዶች 🔹 ጎመን፣ ሰላጣ፣ ቅጠላቅል መጠቀም (More fiber diet and liquid laxatives) 🔹 ሽንት ቤት በተመሳሳይ ሰዓት መጠቀም (Use regular toilet pattern) 🔹 ሸንት ቤት ከቁርስ በኋላ መጠቀም 🔹 ብዙ ውሃ መጠጣት 🔹 ከሽንት ቤት በኋላ መታጠብ 🔹 ለብ ባለ ውሃ የፊንጢጣ አካባቢን መዘፍዘፍ (Use water sitz bath) ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇 https://t.me/DrJano https://t.me/DrJano

በሂርና ሆስፒታል አንድ እናት ሁለት አንድ አካል ያላቸው ህጻናት ወለደች። በምዕራብ ሀረርጌ ጡሎ ወረዳ በሂርና ከተማ በሂርና ሆስፒታል ውስጥ አንድ እናት ሁለት አንድ አካል ያላቸውን ህጻናት መውለዷን
በሂርና ሆስፒታል አንድ እናት ሁለት አንድ አካል ያላቸው ህጻናት ወለደች። በምዕራብ ሀረርጌ ጡሎ ወረዳ በሂርና ከተማ በሂርና ሆስፒታል ውስጥ አንድ እናት ሁለት አንድ አካል ያላቸውን ህጻናት መውለዷን የሆስፒታሉ ሀኪሞች አስታውቀዋል። የሂርና ሆስፒታል ሀኪም ዶ/ር ዳኛቸው ካሳዬ እንደገለጹት እናት በተደረገላት ቀዶ ህክምና ሁለት እግር ያላቸው እና ከወገብ በላይ ሙሉ የራሳቸው አካል ያላቸው መውለዷን አስረድተዋል። በአሁኑ ሰዓት ህጻናቱ በማሞቂያ ክፍል ውስጥ እንክብካቤ እየተደረገላቸው ሲሆን የእናትየው ጤንነትም በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። ይህ አይነት አጋጣሚ በሆስፒታሉ ያልተለመደ ነው ያሉት ሀኪሙ ህጻናቱ ሰገራና ሽንት በጀርባቸው በኩል ስለሚጸዳዱ ቀጣይ ህክምና እንዲያገኙ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል። (OBN Afaan Oromoo, TM) ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇 https://t.me/DrJano https://t.me/DrJano

ኢትዮጵያውያን እናቶቻችን ከሚጠቀሙባቸው ባህላዊ መድኃኒቶች በጥቂቶቹ እናስተዋውቃቹ። ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹን...በየቤታችን ውስጥ እናቶችን ይጠቀሙበታል። 1.ጤና_አዳም ( Ruta chalepensis)፦ ቅጠሉም ሆነ ፍሬው ለሆድ መታወክ ፣ ለቁርጥማትና ለሌሎች መሰል ሕመሞች መድኃኒት ነው። 2.ዳማከሴ (holy basil, tulsi, Ocimum tenuifolium) ለጉንፋን ፣ ለከባድ ራስ ምታት (ማይግሬን) በአፍንጫ ተስቦ የሚወሰድ ፣ ለመተንፈሻ ቧንቧ ችግርና አጠቃላይ ለምች ፍቱን መድኃኒት ነው። 3.ሬት (Aloes)ቅርፊቱ ተልጦ የሚገኘው የውስጡ ዝልግልግ የማር ወለላ የመሰለው ነገር ከሌላ ምግብ ጋር አዋህዶ በመምታት የከሱ ሕፃናት ቢመግቡት ወዲያውኑ ያፋፋቸዋል ፣ ለቁስል ቢቀቡት ወዲያው የመፈወስ ኃይል አለው ፣ ለፎረፎር ቢቀቡት፣ የስኳር በሽተኞችና የደም ግፊት ችግር ያለባቸው ሰዎች አድርቀው ፈጭተው እንደ ሻይ አፍልተው ቢጠጡት የመፈወስ አቅም አለው። 4.የጫት_ቅርፊት ((KhatCutin)፦ ስጋ በልቶ አልፈጭ ብሎት ሆዱ የታወከ ሰው ወቅጦ ቀቅሎ ቢጠጣው ይድናል። 5.አርማ_ጉሳ (Cleome gallaensis)፦ አረንጓዴውን ቅጠል በማድረቅ ወቅጠው እንደ ሻይ ለረጅም ጊዜ በመጠጣት የስኳር ህመምተኞች በደማቸው ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ፈጥኖ የማውረድና የመቀነስ አቅም አለው። ቅጠሉን ደግሞ በአረንጓዴነቱ ወቅጠው ጨምቀው ቢጠጡት ከቁርጥማት የመፈወስ ኃይልና የምግብ አፒታይት የመክፈት ኃይል አለው። 6.ነጭ_ሽንኩርት(Garlic)፦ ለደም ዝውውር ፣ ለጨጓራ ፣ ለውስጥ ካንሰር፣ ለመተንፈሻ አካል፣ ለወሲብ ማነቃቂያነት እና በሰውነት ውስጥ ምግብ እንዲንሸራሸር ፍቱን መድኃኒት እንደሆነ አዋቂዎች በአብነት በመጥቀስ ይናገራሉ። 7.የኮክ_ዛፍ_ቅጠል(Prunus persica)፦ የጋማና የቀንድ ከብቶች በድንገት ሲታመሙም ሆነ ሰዎች በድንገተኛ በሽታ ሲያዙ ከጤና አዳም ጋር ተወቅጦና ተጨምቆ ሲጠጡት ከህመማቸው ይፈወሳሉ። 8.ግራዋ (Vernonia amygdalina) ተመርጦ 7 ቅጠሉ ተቀንጥሶ በሰው እጅ መድኃኒት ለበላ ሰው ቢያጠጡት የመፈወስ ኃይል አለው ፣ እንዲሁም በግራዋ የታጠበ እቃ(እንስራ) ሽታን የሚያመጡ ባክቴሪያዎችን ያጠፋል። ከዚህ በተጨማሪም ግራዋ የተተከለበት ቦታ እባብ ፈፅሞ አይኖርም። 9.የነጭ_ባህርዛፍ_ቅጠሉ (White Eucalyptus globulus) ቅጠሉን በውሃ ተፈልቶ ቢታጠኑት የመተንፈሻ አካል ችግርም ሆነ የትኛውም የጉንፋን ዓይነትን ያለ ኪኒን በሁለት ቀን ውስጥ ፈውስ ያገኛል። 10.ቀይ_ሽንኩርት(Red onion)፦ ለአጠቃላይ ጤንነትና ለደም ዝውውር ጠቃሚ ከመሆኑም ባሻገር የዘር ፈሳሽ እጥረት ላጋጠማቸው ሰዎች በብዛት ለማመንጨት እንደሚያገለግል አባቶች ይናገራሉ ፤ ኮረሪማና ቆንዶ በርበሬ እነዚህ በአንድ ላይ ተቀምመው ለራስ ምታትና ለሆድ ቁርጠት ፍቱን መድኃኒት ናቸው። 11.ዞጓራጋጅ(አማርኛ ስሙን ለጊዜው አላቀውም) ቅጠሉ በእንጨት የሚጠመጠም ሆኖ እንደ አሚቾ ስር የሚያኮርት ሲሆን ይኸው ስሩ ትክትክ ለያዘቸው ሕፃናትና ወባ ለያዛቸው ሰዎች አገልግሎት እንደሚውል አባቶች ይናገራሉ። 12.ኦሞሮ፦ ይህ አረንጓዴ ተክል የእግር ወለምታ ላለባቸውና ሰውነታቸው ተቀጥቅቶ ደም ለቋጠረባቸው ቅጠሎቹን በውሃ ቀቅሎ ቦታውን በቅጠሉና በተቀቀለው ውሃ ደጋግመው ሲያሹት እጅግ ፍቱን መድሐኒት ነው እንዲሁም ሴቶች በወሊድ ወቅት የፈሰሳቸውን ደም ለመተካትና በወር አበባ ጊዜ ተቀቅሎ እንዲጠጡት ይደረጋል። ይህ መድኃኒት የቅጠላቅጠል ዝርያ ሲሆን ለወለደች ሴትና የወር አበባ ያየች ሴት ከአንድ ሣምንት ላላነሰ ጊዜ እየተቀቀለ እንዲጠጡት ይደረጋል። ምክንያቱም ቁርጠትን ይከላከላል፣ሆድ ያጥባል ተብሎ ስለሚታመን ነው። 13.እንስላል(Dill) በውሃ ተቀቅሎ ሲጠጣ የተዘጋ የሽንት ትቦ ይከፍታል። 14.የምድር_እምቧይ_ስሩ /አሚቾው/፡- ተወቅጦ የታመሙ ከብቶች እንዲጠጡት ሲደረግ ከብቶቹ ይድናሉ። 15.መቅመቆ (Rumex abyssinicus)፦ የተባለ ተክል ስሩ ተወቅጦ እንዲደርቅ በማድረግ ዱቄቱ 2 ወይም 3 በሻይ ማንኪያ በውሃ በማፍላት እንዳሻይ ቢጠጣ የደም ግፊት ይቀንሳል። 16.የእንጆሪ_ቅጠል (Berry leaves)በንፅህና ደርቆ ተወቅጦ በሻይ መልክ ተፈልቶ ቢጠጣ የስኳር ህመምን ይቀንሳል። 17.ፌጦ(garden cress)፦ለድንገተኛ ህመምና ውጋት ተወቅጦና ተበጥብጦ በመጠጣት ከህመም መፈወስ ይቻላል። 18.ቀበርቾ /ቾሳ/ (Echinops kebericho) ከስራስር ክፍል የሚመደብ ሲሆን አገልግሎቱም ለድንገተኛ ህመም ፣ ውጋት ወዘተ በማኘክ የሚወሰድ ፈዋሽ መድኃኒት ነው። 19.ጣዝማ ማር፦ ከመሬት ተቆፍሮ የሚገኝ የማር ዓይነት ሲሆን ከነጭ አዝሙድና ኮረሪማ ጋር በመቀላቀል ጠዋት ጠዋት ሁለት ማንኪያ በመውሰድ ከሳል ፣ ከአስም ፣ ከቁርጥማት ወዘተ ህመም መገላገል ይቻላል። ይህንን መድኃኒት የወሰደ አንድ ሰው መድኃኒቱ እንዲሠራ ቢያነስ ከአንድ ሰዓት እስከ አንድ ሰዓት ተኩል ጊዜ ድረስ ሌላ ተጨማሪ ነገር እንዳይጠጣ ይመክራል። 20.ሎሚ( Lemon )ለብዙ ዘመናት ከምግብ መመረዝና ተያያዥነት ካላቸው ሌሎች ምክንያቶች የሚከሰት የሆድ በሽታ ለመፈወስ ሲጠቀሙት የቆየ ባህላዊ መድኃኒት ነው። 21.ልምጭ (Clausena anisata) ከድንገተኛ ህመም ፈዋሽ ሲሆን የጥርስ መፋቂያ ዓይነትና ለብዙ በሽታዎች ፍቱን መድኃኒት ነው፤ከበሽታዎቹም መካከል የአፍንጫ ነስርና ላለበት ሰው ነስሩን ለማስቆም ቅጠሉን በመበጠስና በማሸት ቢያሸቱት ፍቱን መድኃኒት ነው። 22.እንቆቆና_መስመስ(Embelia abyssinica)፦ ለሆድ ትላትልና መሰል በሽታዎች ተፈጭቶና ተበጥብጦ ከኮሶ ጋር በመደባለቅና በመጠጣት ለኮሶ ትልና መሰል የሆድ ህመም መድኃኒት ነው። 23.የጥቁር_ገብስ_አረቄ፡- የጥቁር ገብስ አረቄ ለአስም በሽታ ጠዋት ጠዋት ሁለት መለኪያ ቢወስዱት በሽታውን ማስታገስ ይቻላል። 24.ሰንሰል_እና_አግራ( (Adhatoda schimperiana) ሰንሰል ከሀገር በቀል መድኃኒት ውስጥ የሚካተት ሲሆን ቅጠሉን በመበጠስ ተወቅጦ በሻይ ብርጭቆ አንድ በባዶ ሆድ ሲጠጡበት በወፍ በሽታ ለተጠቃ ሰው ፍቱን መድኃኒት ነው። 25.የእንሰት_ስር(አምቾ) ( zoom out root)፦ ከውስጥ አካሉ የሚገኘው ውሃ እና አሚቾው ተቀቅሎ ደጋግሞ መብላት ከወፍ በሽታ ይፈውሳል እንዲሁም እንዲመግል የተፈለገ የተጎዳ የሰውነት አካልም ሆነ በሰውነት የወጣ ማንኛውም እባጭ መግል ሆኖ እንዲፈነዳ/እንዲወጣ የእንሰት አምቾ ተደጋግሞ ይበላል ፣ የተሰበረ አጥንት በወጌሻ ማጀል ሲያስፈልግ የተሰበረው ቦታ ለማለዘብ (ለማለስለስ) አምቾውን በእርጎ እያማጉ ደጋግሞ መብላት ነው ፣ በጠቦት ሾርባ ደጋግሞ መብላት በመኪናም ሆነ በጦር ሜዳ ስጋው የተቦጨቀ ወይም አጥንቱ ላይ አደገኛ ስብራት ያጋጠመው ቁስሉ እንዲሽር(እንዲጠገን) ያደርጋል። 26.ኮሶ((Hagenia abyssinica)፦የደረቀ የኮሶ ዛፍ አበባ ከእንቆቆና መስምስ ወቅጦ በብርጭቆ በመጠጣት የሆድ ውስጥ ጥገኛ ትላትልን ጠራርጎ ማስወጣት ይቻላል። 27.ሽፈራው_ሞሪንጋ((Moringa stenopetala)፦ይህ የዛፍ ቅጠል የማያድነው በሽታ የለም ይባላል የስኳር መጠንን ይቀንሳል ፣ የደም ግፊትን ይቀንሳል ፣ የደም ዝውውርን ያቀላጥፋል ቅጠሉን.... እንደ ሻይ ተፈልቶ ፣ ዱቄቱ ተወቅቶ በውሃ መጠጣትም ይቻላል ፤ እንዲሁም እንደ ጎመን ቀቅሎ መብላትም ይቻላል። @DrJano

ፅንስ ማስወረድ በመድሀኒት https://youtu.be/IMmhgBd0MXY ሙሉ ቪዲዮውን ለመመልከት ምስሉን ወይም ሊንኩን ይጫኑ!!

የዝንጅብል ሻይ 10 የጤና ጥቅሞች ዝንጅብል ውስጡ ባለው የቫይታሚን ሲ፣ የማግንዚየም እንዲሁም ሌሎች ንጥረ ነገሮች ለጤና ከፍተኛ ጥቅም እንደሚሰጥ ይነገራል። ከእነዚህ መካከል አስሩን እነሆ፦ 1/ ካንሰርን መከላከል ከ 17 በላይ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ዝንጅብል የካንሰር እድገትን የሚያቆም ንጥረ ነገር በውስጡ የያዘ በመሆኑ ከ101 በላይ በሽታዎችን ይከላከላል። 2/ ማቅለሸለሸን ያስቆማል ረጅም ጉዞ ከመጀመርዎ በፊት አንድ ሲኒ የዝንጅብል ሽይ መጠጣት ማስመለስ እና ማቅለሽለሽን የመሳሰሉ ችግሮችን ሊካላከሉ ይችላሉ። 3/ የጨጓራ እና የሆድ ስራን ይሻሽላል ዝንጅብል የምግብ መፈጨት እንዲሁም የሆድ ጤንነትን የማሻሻል አቅም አለው። 4/ የሰውነት መቆጣትን ይቀንሳል የመገጣጠሚያ እና የጡንቻ ችግሮች ካለብዎት ዝንጅብል ፍቱን መድሀኒት መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ። የዝንጅብል ሻይን ከመጠጣት ባለፈ የተቆጡ የሰውነት መገጣጠሚያ አካባቢን በዝንጅብል ማሸትም ጥሩ ማስታገሻ ዜዴ ነው። 5/ የመተንፈሻ አካላት ችግሮችን ይከላከላል ከጉንፋን ጋር ከተያያዙ የመተንፈሸ አካል በሸታዎች ለመፈወስም ያግዛል። 6/ የደም ዝውውርን ያሻሽላል በዝንጅብል ሻይ ውስጥ የሚገኙ ቪታሚኖች፣ ማዕድናት እና አሚኖ አሲድ ለደም ዝውውር መሻሻል ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው ናቸው። 7/ በወር አበባ ጊዜ የሚኖር የሆድ ህመምን ይቀንስል ሴቶች በወር አበባ ጊዜ የሚኖርን የሆድ ህ|መም ለመቀነስ ሞቅ ባለ የዝንጅብል ሻይ ውስጥ ፎጣን በመንከር ሆድ አካባቢ ማሸት የሚሰማቸውን ህመም ለመቀነስ ያግዛል። 8/ በሽታን የመከላከል አቅምን ይጨምራል ውስጡ ባለው ከፍተኛ ንጥረ ነገር ምክንያት በሽታ የመከላከል አቅምን ሊጨምር ይችላል። 9/ ጭንቀትን ያስወግዳል ዝንጅብል ጭንቀትን የማስወገድ አቅም አለው ተብሎ ይነገርለታል ይህም ውስጡ በያዘው ጠንካራ መዓዛ እና ንጥረ ነገሮች ምክንያት ነው። 10/ ለአስም በሸታ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ዝንጅብል ከአስም ጋር የተያያዙ ህመሞችን የመቀነስ ባህሪ አለው። ተጨማሪ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇 https://t.me/DrJano https://t.me/DrJano