cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
34 647
مشترکین
-1524 ساعت
+817 روز
+27030 روز
آرشیو پست ها
Photo unavailableShow in Telegram
በጎርፍ የተከበበውን ኬንያዊ ህፃን በአስደናቂ ሁኔታ መታደግ መቻሉ ተነገረ ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ 120 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ያታ ከተማ በጎርፍ ለብቻው የታገተው የአምስት አመት ልጅ በፖሊስ ሄሊኮፕተር ህይወቱን መታደግ ተችሏል። የህፃኑ ልጅ "የውሃው መጠን መጨመር ሲጀምር ወላጅ አባቱ ጥለውት መሄዳቸውን" ፖሊስ ተናግሯል። የልጁን ቦታ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በመጠቀም የተቆጣጠረው አለማቀፉ የሰብአዊ እርዳታ በጎ አድራጎት ሴንተር ለፖሊስ ያሳወቀ ሲሆን ሄሊኮፕተሩን ከናይሮቢ በመላክ የነፍስ አድን ስራው ተግባራዊ ሆኗል። ህፃኑን በጀልባ ለማዳን የተደረገው የመጀመሪያ ሙከራ ምቹ ባልሆነ የአየር ሁኔታ ምክንያት ሳይሳካ መቅረቱን የኬንያ ቀይ መስቀል አስታውቋል። አክለውም “ሕፃኑ ለረጅም ጊዜ በጎርፉ ተከቦ በመቆየቱ የነፍስ አድን ስራው ከተከናወነ በኃላ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሆስፒታል ተወስዷል። ከቀናት በፊት በኬንያ እና በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ እና  ውድመት አስከትሏል። በኬንያ የጎርፍ አደጋው በ 23 የሀገሪቱ 47 አውራጃዎች ተመዝግቧል ፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎችን በጎርፍ እንዲከበቡ ምክንያት ሆኗል። የጎርፍ አደጋ ከተከሰተ ውዲህ ከ188 በላይ ሰዎች መታደጉን የኬንያ ቀይ መስቀል አስታውቋል። የጎርፍ አደጋው ተከትሎ 11 ሺ 2 መቶ 6 አባወራዎችን ከመኖሪያ ቀያቸው ሲያፈናቅል 27 ሺ 7 መቶ 16 ሄክታር መሬት ውሰጥ የነበረ ምርትን አውድሟል።ከ4,800 በላይ የቤት እንስሳትን መሞታቸውንም የኬንያ ቀይ መስቀል ይፋ አድርጓል። በሚሊዮን ሙሴ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
👍 23 5👏 4🥰 1😁 1😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ የሚገኙ የሰባት አገራት ኢምባሲዎች የትግራይን ግዛቶችን "አወዛጋቢ ቦታዎች" በሚል ቃል መግለጣቸውን የትግራዩ ተቃዋሚ ሳልሳዊ ወያነ  ኮነነ ፖርቲው፣ "አወዛጋቢ" የተባሉት አካባቢዎች "በኃይል የተያዙ የትግራይ ግዛቶች እንጅ ውዝግብ የተነሳባቸው አይደሉም" ብሏል። ኤምባሲዎቹ የትግራይ ግዛቶችን በኃይል የያዙ ኃይሎች በመውጣታቸው አስፈላጊነት ላይ አጽንዖት እንዲያደርጉ ፓርቲው ጠይቋል። የአሜሪካ፣ ብሪታንያ፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያንና ጃፓን ኢምባሲዎች፣ በሰሜን ኢትዮጵያ "ውዝግብ ባለባቸው አካባቢዎች" የተፈጠረው አዲስ ውጥረት እንዳሳሰባቸው ቅዳሜ እለት ባወጡት መግለጫ መግለጣቸው አይዘነጋም። #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
😁 15👍 13 2💯 1
Photo unavailableShow in Telegram
ቦትስዋና የዩናይትድ ኪንግደም ስደተኞችን እንድትቀበል የቀረበላትን ጥያቄ ውድቅ አደረገች የቦትስዋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለደቡብ አፍሪካ የቴሌቭዥን ጣቢያ እንደተናገሩት የብሪታንያ መንግስት ከእንግሊዝ የተባረሩ ስደተኞችን ለመቀበል ሀገሪቱ ፈቃደኛ መሆን አለመሆኗን መጠየቃቸውን ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ይህ ጥያቄ መቼ እንደቀረበላቸው ከመናገር ተቆጥበዋል።የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት በቦትስዋና፣ አርሜኒያ፣ አይቮሪ ኮስት እና በኮስታ ሪካ ሩዋንዳ ስደተኞችን ለመቀበል የተስማማችበትን እቅዱን ለመድገም እንደሚፈልግ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በብሪቲሽ ፕሬስ ላይ ያልተረጋገጡ ዘገባዎች መውጣታቸው ይታወሳል። በኒውዝሮም አፍሪካ በተሰኘ ፕሮግራም ላይ በተደረገ የስልክ ቃለ ምልልስ ሚኒስትሩ ሌሞጋንግ ክዋፔ እንደተናገሩት ቦትስዋና የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ጉዳይ ሚኒስትር በ‹‹ዲፕሎማቲክ ቻናል›› በኩል የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ አድርጋለች ብለዋል። ክዋፔ ቦትስዋና ከብሪታንያ የሚመጡ ስደተኞችን መቀበል አትችልም ምክንያቱም የራሷን የኢሚግሬሽን ጉዳዮች እያስተናገደች ነው ብለዋል። "የብሪታንያ መንግስት እነዚህን ሰዎች በአገራቸው እንዲኖሩ ስለማይፈልግ በሩቅ አገር እንዲቀብሩአቸው ይፈልጋል ሲሉ ተደምጠዋል። በራሳችን ቀጠና ያለውን ችግር እየፈታን በመሆኑ ያልተፈለጉ ስደተኞችን ከሌላ ሀገር መቀበል ለቦትስዋና ፍትሃዊ አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል። በሌላ በኩል የዩናይትድ ኪንግደም ፓርላማ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ የሚሰደዱበትን መንገድ የሚከፍተውን አወዛጋቢውን ህግ በማፅደቁ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣናት ያለቸውን ስጋት አንስተዋል። ስደተኞች ወደ እንግሊዝ በህገ ወጥ መንገድ እንዳይገቡ ለማድረግ ያለመ የሩዋንዳ ሴፍቲ ወይን የጥገኝነት እና ኢሚግሬሽን ህግ ለወራት ከዘለቀው አለመግባባት በኃላ ሰኞ እለት ፀድቋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ቱርክ በጋራ በሰጡት መግለጫ የእንግሊዝ መንግስት እቅዱን እንደገና እንዲያጤነው ጠይቀዋል። ይህ ህግ በሰብአዊ መብቶች ላይ "ጎጂ ተጽእኖ ይኖረዋል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ህጉ "የስደተኞች ስምምነትን መጣስ" ነው ሲሉ አክለዋል ። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
👍 17 1👏 1😁 1🤔 1
በሀረር ከተማ ቤተሰቦቹ ቤት ተከራይተው ከሚኖሩ አዛውንት የኤቲኤም ካርድ ላይ ገንዘብ የሰረቀው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ በሀረር ክልል ሀረሪ ከተማ አቦከር ወረዳ ቤተሰቦቹ ቤት ተከራይተው ከሚኖሩ የ65 ዓመት አዛውንት የ20 ዓመቱ ወጣት የኤቲኤም ካርዳቸው በመዉሰድ ገንዘብ ማዉጣቱን የአቦከር ወረዳ ፖሊስ አስታውቋል። የአቦከር ወረዳ ፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ዘይዶን ቶፊቅ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ግለሰቡ ከተቀማጭ ሂሳባቸው ላይ የኤት ኤም ካርድ በመጠቀም የስርቆት ወንጀሉን ፈጽሟል ።የግድ ተበዳይ የ65 ዓመቱ አዛውንት ካሳ ከኢንሹራንስ ብር እንደሚከፈላቸው ከቀረቤታቸው አንጻር ይነግሩት እንደነበር ፖሊስ አስታዉቋል፡፡ በዚህ ሁኔታም ሰሞኑን 120ሺ ብር እንደሚገባላቸው እና ገንዘቡ ሲገባም መግባቱን ያሳውቁታል። አዛውንቱ እና የ20 ዓመት ወጣቱ በቀረቤታቸው የተነሳም የኤቲኤም የሚስጥር ቁጥራቸውን ወጣቱ ያውቃል።የግድ ተበዳይ በሂሳባቸው ገንዘቡ እንደገባላቸው ካረጋገጡ በኃላ ቤታቸው በመግባት የኤቲኤም ካርዳቸውን በመስረቅ ከባንክ 120ሺ ብሩን አውጥቶ ወስዷል። አዛውንቱም ብሩ ስለገባላቸው ወደ ባንክ ሄደው ከሂሳባቸው ላይ ገንዘብ ለማውጣት ሲጠይቁ ብሩ ሙሉ በሙሉ በኤትኤም እንደወጣ ሲነግሯቸው ከባንክ ሰራተኞቹ ጋር ውዝግብ ውስጥ እንደገቡ ኮማንደሩ ተናግረዋል።ባንኩም ጉዳዩን ለፖሊስ ይጠቁማል ፖሊስም በደረሰው ሪፓርት መሰረት ማጣራት አድርጎ ብሩን ያወጣው ግለሰብ የ20 ዓመት ወጣቱ መሆኑን ካረጋገጠ በኃላ በቁጥጥር ስር አውሎታል ። ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በማጣራት ለሚመለከተው የፍትህ አካል እንደሚያቀርብ እና ማንኛውም ሰው የባንክ ወይም የኤትኤም ካርድ የሚስጥር ቁጥርን ለሶስተኛ አካል ማሳወቅ እንደሌለበት  ኮማንደር ዘይዳን ቶፊቅ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በምህረት ታደሰ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
👍 27👎 3 3🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
የናይጄሪያ ትምህርት ቤት በተማሪዎች ብሽሽቅ እና የጉልበተኞች ጥቃት የተነሳ መዘጋቱ ተሰማ የናይጄሪያ ባለስልጣናት በዋና ከተማይቱ አቡጃ የሚገኘውን በአንዳንድ ተማሪዎቹ ላይ በተፈፀመው የጉልበተኝነት ድርጊት ከፍተኛ ደረጃ ያለው ትምህርት ቤት እንዲዘጋ መደረጉን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።በሊድ ብሪቲሽ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ተማሪዎች እኩዮቻቸውን ሲያጠቁ የሚያሳዩ በርካታ ቪዲዮዎች በማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭተዋል። ቪዲዮዎቹ መጋራታቸዉን ተከትሎ የሰላ ትችት የፈጠረ ሲሆን የተናደዱ ወላጆች ትምህርት ቤቱን ማክሰኞ እለት ሲወረሩ ታይተዋል።የትምህርት ቤቱ ባለስልጣናት ጉዳዩን ለመመርመር ለማስቻል ለሶስት ቀን መዘጋቱን አስታዉቀዋል፡፡የትምህርት ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት ካቢሩ ሙሳ ለፓንች የዜና ድረ-ገጽ እንደተናገሩት የሀገሪቱ የሴቶች ጉዳይ ሚኒስትር ኡጁ ኬኔዲ-ኦሀኔዬ ትምህርት ቤቱ እንዲዘጋ ትዕዛዝ ሰጥተዋል። ትምህርት ቤቱ ባወጣዉ መግለጫ ላይ የጉልበተኝነት ድርጊት "በጥልቅ አሳስቦኛል" በማለት በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ምርመራ ለማድረግ ቃል ገብቷል።እ.ኤ.አ በ2007 የተቋቋመው ትምህርት ቤት ከናይጄሪያ የትምህርት ስርዓት ጋር የተዋሃደ የብሪቲሽ ስርዓተ ትምህርት ይሰጣል።በናይጄሪያ ውስጥ በጣም ውድ ከሚባሉት ትምህርት ቤቶች አንዱ እንደሆነ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በኤደን ሽመልስ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
👍 20😁 13 1🤯 1
Photo unavailableShow in Telegram
በቀሲስ በላይ ሁለት መኖሪያ ቤቶች በብርበራ የተገኘ የጦር መሳሪያ ህጋዊነት የማረጋገጥ ስራ እየሰራ መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ መርማሪ ፖሊስ በተሰጠው የ7 ቀን ጊዜ ውስጥ የምስክሮችን ቃል መቀበሉን፣ በተጠርጣሪዎች እጅ ላይ የተገኘ ኤሌክትሮኒክስ ምርመራ እንዲደረግ ለሚመለከተው ተቋም መጠየቁን፣ የቴክኒክ ምርመራ እንዲሰጠው በደብዳቤ መጠየቁን አስታውቋል። በተጨማሪም በቀሲስ በላይ ሁለት መኖሪያ ቤቶች ላይ ብርበራ ማድረጉንና በብርበራ የተገኘ የጦር መሳሪያ ህጋዊነት የማረጋገጥ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጿል፤ ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ገልጾ መርማሪ ፖሊስ የ14 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል። ቀሲስ በላይ መኮንንን ጨምሮ ሌሎቹም ተጠርጣሪዎች በ6 ጠበቆች ተወክለው ችሎት የቀረቡ ሲሆን ደንበኞቻቸውን ተጨማሪ በእስር ለማቆየት የሚያስችል አይደለም በማለት ተከራክረዋል። የግራ ቀኝ ክርክሩን የተመለከተው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ለጊዜው በማለፍ ለፖሊስ የ8 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ፈቅዷል።
نمایش همه...
👍 26😁 17 8😱 5👏 2
የግሪክ ዋና ከተማ አቴንስ ከሳሃራ በረሃ በተነሳ ብርቱካናማ አቧራ መሸፈኗ ተሰማ ከሰሃራ በረሃ የተነሳ አቧራ ብርቱካናማ ጭጋግ በአቴንስ ከተማ ላይ መሸፈኑ ተሰምቷል። ከ 2018 ጀምሮ በግሪክ ከተከሰቱት በጣም አስከፊ ክስተቶች መካከል አንዱ መሆኑን የመንግስት ባለስልጣናት ገልፀዋል። በመጋቢት ወር መጨረሻ እና በሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ ግሪክ በተመሳሳይ ጭጋግ ተሸፍና ነበር ፤ በተመሳሳይ የስዊዘርላንድ እና የደቡብ ፈረንሳይ አካባቢዎችን ይሸፍኑ ነበር። የግሪክ የአየር ሁኔታ አገልግሎት እስከ ሩዕቡ ምሽት ሰማዩ ይጸዳል ተብሎ ይጠበቃል ብሏል። በበርካታ የአገሪቱ አካባቢዎች የአየር ጥራት ብክለት የተመዘገበ ሲሆን እሮብ ጠዋት በአቴንስ የከተማዋ ምልክት የሆነው አክሮፖሊስ በአቧራ ምክንያት አይታይም ነበር። ደመናው እስከ ተሰሎንቄ በስተሰሜን ክፍል ድረስ ሸፍኗል። የአተነፋፈስ ችግር ያለባቸው ግሪካውያን ከቤት ውጭ የሚያሳልፉትን ጊዜ እንዲገድቡ፣የመከላከያ ጭንብል እንዲጠቀሙ እና አቧራው እስኪያጠራ ድረስ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ከማድረግ እንዲቆጠቡ የመንግስት ባለስልጣናት አሳስበዋል። የሰሃራ በረዓ በዓመት ከ60 እስከ 200 ሚሊዮን ቶን የማዕድን አቧራ ይለቃል። አብዛኛው አቧራ በፍጥነት ወደ ምድር ይመለሳል። ነገር ግን አንዳንድ ጥቃቅን ቅንጣቶች ብዙ ርቀት ሊጓዙ የሚችሉ ሲሆን አንዳንዴም አውሮፓ ይደርሳሉ። በተለይ በደቡባዊ ግሪክ ያለው ከባቢ አየር ከአቧራ እና ከከፍተኛ የሙቀት መጠን ጋር ይመዘገብበታል። የሜትሮሎጂ ባለሙያው ኮስታስ ላጎውቫርዶስ የአየር ሁኔታውን ከማርስ ፕላኔት ጋር አወዳድሮታል። የእሳት አደጋ መከላከያ አገልግሎት እንዳስታወቀ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 25 ሰደድ እሳት ተፈጥሯል።አንድ የእሳት አደጋ በቀርጤስ ደሴት የባህር ኃይል ሰፈር አቅራቢያ ያጋጠመ ሲሆን የሙቀት መጠኑ ከ 30 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ ከፍ ብሏል ።ነዋሪዎች ከቤታቸው ለቀው እንዲወጡ መደረጉን የአካባቢው ዘገባዎች ያመላክታሉ። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
👍 13😱 8🥰 5 3🤔 2🔥 1
👍 1
በአዲስ አበባ ጠሮ መስኪድ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ እየተገነባ ያለ የግለሰብ መኖሪያ ፣ አፈርና ድንጋይ ተደርምሶ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት ሰዎች በቤታው ተኝተው የነበሩ ናቸው፡፡ ዛሬ ሚያዚያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት 11 :00 ሰዓት ላይ በአዲስ ከተማ  ወረዳ 12 ልዩ ቦታዉ ጠሮ መስኪድ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ እየተገነባ ያለ የግለሰብ መኖሪያ የግንባታ ግብዓት አፈርና ድንጋይ ተደርምሶ በአቅራቢያው ያለ መኖሪያ ቤት ላይ በመናዱ በቤታቸዉ ተኝተዉ የነበሩ ሰባት ሰዎች ህይወታቸዉ ማፉን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታዊቃል፡፡ የሟቾቹን አስከሬን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋልማስረከባቸው የኮሚሽኑ የሕዘብ ጋኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ አና ቴሌቪዢን የተናሩ ሲሆን የአደጋዉን መንስኤ ፖሊስ ምርመራ እያካሄደ ይገኛልም ብለዋል። በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን እና የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛዉ እንዲሁም የክፍለ ከተማዉ አመራሮች በአደጋዉ ስፍራ ተገኝተዉ በአካባቢዉ ተመሳሳይ አደጋ እንዳያጋጥም የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ አቅጣጫ አስቀምጠዋል መሄዳቸውንም ለማወቅ ቸለናል። በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ በኮንስትራክሽን ስራ የሚደርስ አደጋን ለመከላከል አስፈላጊዉ የደህንነት መስፈርቶችን ጠብቆ መስራት አስፈላጊ መሆኑን  ኮሚሽኑ አሳስቧል። በትግስት ላቀዉ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
😢 41👍 15💔 7 5
Photo unavailableShow in Telegram
የመኖሪያ ህንፃ ተደርምሶ 7ሰዎች ህይወታቸው አለፈ በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ ጠሮ መስኪድ አካባቢ የመኖሪያ ህንፃ ተደርምሶ የ 7ሰዎች ህይወት አልፏል ። የወረዳው አስተዳደር አይዳ አወል እንደተናገሩት ፤ ምሽት 5ሰዓት ባጋጠመው አደጋው ህይወታቸውን ያጡት ቤቶቹ የመፍረስ አደጋ ሲጋረጥባቸው ከጀርባ የነበሩ ቤቶች ላይ ወድቀው ነው መባሉን ዳጉ_ጆርናል ሰምቷል። በአደጋው ህይወታቸውን ስላጡ ፣ ስለ ወደመ ንብረት እና ሌሎች ጉዳቶች ተጨማሪ መረጃ አልተሰጠም ። #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
😢 12👍 4 2😱 1🤬 1
በእንግሊዝ አንዲት እናት የወለደቻት ልጅ በሆስፒታል ውስጥ እንደተቀየረችባት ማወቋን ተናገረች አንዲት እንግሊዛዊት እናት በሆስፒታል ውስጥ የወለደቻት ሕፃን የራሷ ልጅ እንዳልሆነች ካወቀች በኋላ በጣም ፍርሃት እንደተሰማት ተናግራለች። የ22 ዓመቷ ማሂሲ ቤት ሴት ልጇን ኢዛቤልን በወለደችበት በእንግሊዝ ዶርሴት በሚገኘው ሆስፒታል ውስጥ ይህው አስደንጋጭ ክስተት እንጋጠማት ተናግራለች። ቤት አዲስ የወለደቻትን የልጇን ዳይፐር ለመለወጥ ስትሞክር ወንድ ልጅ እንደሆነ ባወቀች ጊዜ አንዳች ችግር እንደተፈጠረ ተረድታለች። ቤት ይህንን ሕፃን ጡት ማጥባት እችል ነበር ወይም የገዛ እናቱ ልጇ የሌለበት ባዶ አልጋ ላይ ልትነቃ ትችላለች የሚለው ነገር ሲያሳስበኝ ነበር ብላለች።ኢዛቤልን ከወለደች በኋላ ብዙም ሳይቆይ አዋላጆች ሕፃኗ የፎቶቴራፒ ሕክምና እንደሚያስፈልጋትና በልዩ የሕፃናት ማቆያ ውስጥ መቆየት እንዳለባት ለቤዝ አሳውቀዋል። አዋላጇ ወደ ቢሮ እኔን አስጠርተው ኢዛቤል ስላለችበት ሁኔታ ነገሩኝ የፎቶ ቴራፒ ህክምናዋን ጨርሰው ያስወጧት መስሎኝ ነበር ስትል ቤት ተናግራለች። ነርሶች ህፃኗ ብዙ ታለቅስ ስለነበር ለተወሰነ ጊዜ እዚያ እንድቆይ እና ቁጭ እኔን እንደምትመስል ነገሩኝ። ከወሊድ ከሁለት ቀን በኋላ ስለነበርኩ ምንም ነገር አልጠየቅኩም እናም ህፃኑን ወደ አልጋዬ ይዤ ተመለስኩ ብላለች። ቤዝ የጨቅላዋን ዳይፐር ልትቀይር ስትሞክር ሴት ልጇ ሳትሆን ወንድ ልጅ እንደሆነ አውቃለች። እናትየው ስትናገር በዛው “ቅጽበት የሰጠሁት ምላሽ አንድ ሰው ልጄን እንደሰረቀኝ ተናግሬያለሁ” በማለት ታስታውሳለች። ከአራት ዓመታት የመካንነት ህክምና በኋላ ይህ ድርጊት ተከሰተብኝ ብዬ የወለድኳትን ልጄን ያጣሁ  መስሎኝ ነበር ስትል አክላለች። ቤተ አዋላጆቹ በስህተት ህጻናቱን ማቀያየታቸውን የተናገረች ሲሆን ነገር ግን የሌላኛው ልጅ እናት ሁኔታውን ተረድታ እንደሆነ ግልፅ አላደረገችም።የሌላኛዋ ልጅ እናት ተኝታ የነበረ ሲሆን ከእኔ የተለየ የማዋለጃ ክፍል ውስጥ ስለነበራች ምን እንደተፈጠረ አላውቅም ስትል ገልጻለች።ስህተቱ እንዴት እንደተከሰተ ሆስፒታሉ ምርመራ ማድረግ ጀምሯል። በዶርሴት ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የአዋላጅ ዳይሬክተር የሆኑት ሎሬይን ቶንጌ እንደተናገሩት “በተፈጠረው ጉዳይ በጣም ተጸጽተናል በምርመራ ሂደታችን እናት እንድትረዳን መልሳ እንድታነጋግረን እናሳስባለን ብለዋል። የወላጆችን እና የህፃናት ደህንነት ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው እናም ለተጎዱ ቤተሰቦች ሙሉ ድጋፍ ለመስጠት ቁርጠኞች ነን ሲሉ አክለዋል። የህፃናቱ ጾታ ተመሳሳይ ቢሆን የመቀያየራቸው ነገር  የማይቀር ይሆን ነበር። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
👍 26😁 5😢 5🤔 4🤯 2👎 1 1
Photo unavailableShow in Telegram
የምስራቅ ጎጃም ዞን ኮማንድፖስት ከሰርጉ ላይ የታገተ ሙሽራን አስለቀኩ አለ የምስራቅ ጎጃም ዞን ኮማንድፖስት ከሰርጉ ላይ የታገተ ሙሽራን ማስለቀቁን ዳጉ ጆርናል ካሰራጨዉ መግለጫ ላይ ተመልክቷል። በኮማንድፖስቱ ስር የሚገኘው ክፍለ ጦር በስፍራዉ የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን ወደሚገኝበት ጎንቻ ወረዳ ባርጃኖ ቀበሌ ተሰማርቶ በወሰደው ርምጃ 20 የቡድኑን አባላት ደምስሻለሁ ያለ ሲሆን ፤ 14 ሲቆስሉ ፣ ሦስት ደግሞ ተማርከዋል ብሏል። በዚሁ ዘመቻ ሦስት ኤ ኬ ኤም ፣ ሰባት የቃታ መሳርያ ፣ ከአርሶ አደሩ ዘርፎ ሊያርዳቸው የነበሩ አምስት በሬዎችን በቁጥጥር ስር አውያለሁም ብሏል። በተጨማሪም ታጣቂዉ ቡድን በእስር ቤት አጉሮ ሲያሰቃያቸው የነበሩ ዜጎችንም ማስለቀቁን አስታዉቋል። ከእስረኞቹ መሐል አንዱ የሆነው ሙሽራው ደመቀ ሚኒሊክ የተባለዉ ግለሰብ ጥር 12/2016 ዓ/ም  ቤተ-ዘመድ ተሰብስቦ የጋብቻ ስነ-ስርአቱን እያካሔደ ባለበት ሰዓት በጽንፈኛው ታግቶ ከወንድሙ ጋር ለእስር ተዳርጓል ብሏል።  በዚህ ወቅትም የሙሽራው አባት ከደገሱት ሰርግ ላይ ልጃቸው በጽንፈኞቹ ታግቶ ሲወሰድ ተበሳጭተው ራሳቸውን አጥፍተዋል ማለቱንም ዳጉ ከመረጃዉ ተመልክቷል። በትናንትናው እለትም ክፍለጦሩ ባደረገው ሰምሪት  "ታጋቹ ሙሽራን ጨምሮ ሌሎች አብረውት ታስረው ሲገረፉ እና ጀርባቸው በእሳት እየተጠበሰ ሲሰቃዩ የነበሩ ዜጎች ነፃ አዉጥቻለሁ" ብሏል። #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
😁 46👍 30😢 5 3👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ከሰሞኑ በቤተክርስቲያን ዉስጥ ሲተኩስ የታየዉን የፌዴራል ፖሊስ አባል ተከትሎ ኮሚሽኑ መተዳደሪያ ህግና አሠራር ውጭ ነዉ ሲል አስታወቀ 👉🏼 የፖሊስ አባሉም ይህንን ተግባር እንደፈፀመ ወዲያውኑ በቁጥጥር ሥር ዉሏል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በማህበራዊ የትስስር ገጹ ላይ ካሰራጨዉ መግለጫ ዳጉ ጆርናል እንደተመለከተው ፖሊስ ከየትኛውም ሃይማኖት፣ ብሄር እና ፖለቲካ  ወገንተኝነት የፀዳ እና ብዛህነትን እሴቱ ያደረገ ሕዝባዊ ተቋም መሆኑን ገልጿል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሃይማኖቶች ብዛህነትን የሚያከብርና የሚያስከብር በእኩልነት ለሁሉም ሙያዊ አገልግሎት የእየሰጠ ያለ ተቋም ሆኖ ሳለ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ አዲስ የፖሊስ አባላትን ለመመልመል ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ የተላከ የፖሊስ አባል ምክትል ሳጂን ታመነ ዱባለ ጥር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ኬቾ ወዜ ቅዱስ ባለወልድ ቤተክርስቲያን  በመገኘት የደንብ ልብሱን እንደለበሰ ሃይማኖታዊ መዝሙር በመዘመር እና በሕዝብ ፊት ጥይት እየተኮሰ በማህበራዊ ሚዲያ ሰሞኑን የሚሰራጨው ቪዲዮ ከተቋሙ መተዳደሪያ ህግና አሠራር ውጭ እንደሆነ መግለጫው ወቅሷል። አባሉም ይህንን ተግባር እንደፈፀመ ወዲያውኑ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ   በቁጥጥር ሥር አውሎት የፈፀመው ድርጊት በተቋሙ ሕገ ደንብ መሠረት በሕግ አግባብ እያጣራ እንደሚገኝ መግለጫው አመላክቷል። ፖሊስ የሁሉም አገልጋይ ሆኖ ሳላ አባሉ እምነቱን በግል መከተል እየቻለ ነገር ግን መንግስት ፀጥታ እንዲያስከብር ያስታጠቀውን የጦር መሣሪያ ከፍተኛ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ፍፁም የፖሊስን ዲሲፕሊን በጣሰ መልኩ የፈፀመው ተግባር በሕግ የሚያስጠይቅ ስለሆነ ተቋሙ ሕግ ፊት እንደሚያቀርበው በመግለጫው መጥቀሱን ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል። #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
👍 59👎 36👏 10😁 8 5😢 4
የሩሲያ ምክትል መከላከያ ሚኒስትር ጉቦ ተቀብለዋል በሚል በቁጥጥር ስር ዋሉ የሩሲያ ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር ጉቦ በመቀበል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሀገሪቱ ከፍተኛ የምርመራ አካል አስታውቋል። የምርመራ ኮሚቴው እንዳስታወቀው ቲሙር ኢቫኖቭ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ እና ምርመራ እንደተደረገባቸው ይፋ አድርጓል። እ.ኤ.አ በ 2016 በመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ የተሾሙት የ47 ዓመቱ ኢቫኖቭ ለሩሲያ ወታደራዊ መሠረተ ልማት ፕሮጄክቶች ኃላፊ ነበሩ። የማህበረሰብ አንቂዎች በሩሲያ መከላከያ ውስጥ ከፍተኛ የሙስና ድርጊትን አለ በሚል ሲነቅፉ ቆይተዋል። እ.ኤ.አ በ 2022 በሟቹ የተቃዋሚ መሪ አሌክሲ ናቫልኒ የተመሰረተው የፀረ-ሙስና ፋውንዴሽን ኢቫኖቭን በሩሲያ በተያዘው የዩክሬን ግዛቶች ውስጥ በግንባታ እቅዶች ውስጥ በሙስና ተሳትፈዋል ሲል ከሰዋል። በተለይም የዩክሬን የወደብ ከተማ በሆነችው ማሪፖል ከሚገነቡት የግንባታ ፕሮጄክቶች ትርፍ እንዳገኙ ገልጿል፣ ሩሲያ ዩክሬንን ሙሉ በሙሉ መውረሯን ተከትሎ  የኪየቭ አብዛኛው የመሰረተ ልማት አውታሯ በሩሲያ የቦምብ ጥቃት ወድሟል። የምርመራ ኮሚቴው ኢቫኖቭን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ይግለፅ እንጂ ምክትል ሚኒስትሩ ስለተሰነዘረባቸው ክስ ምን ምላሽ እንደሰጡ አልታወቀም ። ኢቫኖቭ በቁጥጥር ስር የዋሉበት የሩሲያ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ በአንቀጽ 290 ክፍል 6 በጉቦ ተጠረጠርጥረው ሲሆን ተከሳሹ ከአንድ ሚሊዮን ሩብል በላይ ገንዘብ የተቀበለ እንደሆነ በከፍተኛ የገንዘብ መቀጮ እና እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስራት ይቀጣል ይላል። ኢቫኖቭ ቀደም ሲል የሞስኮ ክልል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ።የወቅቱ የመከላከያ ሚኒስትር ሰርጌ ሾይጉ ለአጭር ጊዜ የሞስኮ ገዥ ሆነው ባገለገሉበት ወቅት የሾይጉ የቅርብ አጋር መሆን መቻላቸው ይነገራል። የእስር ሂደቱ በሩስያ የአስተዳደር ልሂቃን አባል ላይ ያልተለመደ ርምጃ የሚያመለክት ሲሆን ብዙዎቹ ስልጣናቸውን በመጠቀም ሰፊ የግል ሃብት ያካበቱ እንደሆኑ ይታመናል። የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ለፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስቀድሞ ስለ እስሩ ተነግሯቸው ነበር ብለዋል። ኢቫኖቭ በዩናይትድ ስቴትስ ፣ በዩናይትድ ኪንግደም እና በአውሮፓ ህብረት ማዕቀብ  የተጣለባቸው ሲሆን በማዕቀቡም የጉዞ እገዳ እና የንብረት እገዳ ተጥሎባቸዋል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
👍 23🔥 3 2😁 2
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ቼልሲ በሌላ የለንደን ቡድን ከሶስት በላይ ጎሎች ተቆጥረውበት በፕሪሚየር ሊጉ ተሸንፎ አያውቅም ። መድፈኞቹ 5 ግቦችን ማስቆጠር ችለዋል 😯 #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
🔥 39👍 17👎 10🥰 6😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
ካይ ሀቨርትዝ የቀድሞ ቡድኑ ላይ በማስቆጠር ደስታውን አክብሯል 🥶 በ2021ዱ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ማንችስተር ሲቲ ላይ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሮ ቼልሲ ዋንጫ ማንሳቱ ይታወሳል 😬 #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
😁 27👏 10👍 5 2
Photo unavailableShow in Telegram
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ  ጨዋታ ተጠባቂ ጨዋታ       አርሰናል 5-0 ቼልሲ ⚽️ ትሮሳርድ ⚽️⚽️ ዋይት ⚽️⚽️ ሀቨርትዝ ጎሎቹን ለመመልከት 👉 @mikoethio #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
😁 12👍 11🔥 4
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ            አርሰናል 3-0 ቼልሲ ⚽️ ትሮሳርድ ⚽️ኋይት ⚽️ ሀቨርት ጎሎችን ለመመልከት 👉 @mikoethio #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
23😁 5👍 3👏 3👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ         አርሰናል 1-0 ቼልሲ ⚽️ ትሮሳርድ ጎሎችን ለመመልከት 👉 @mikoethio #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
👍 22 3
ተጠባቂ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አርሰናል ከ ቼልሲ ማን ያሸንፋልAnonymous voting
  • አርሰናል (መድፈኞቹ)
  • ቼልሲ (ሰማያዊዎቹ)
0 votes
👍 20👎 8
የእስራኤል ባለስልጣናት አስታራቂዎችን እያጠቁ ነዉ ስትል ኳታር ወቀሰች የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማጅድ አል-አንሷሪ አንዳንድ የእስራኤል ሚኒስትሮች ኳታርን በጋዛ ጦርነት ድርድር ላይ ስውር ዓላማ እንዳላት አድርገዉ መናገራቸዉ ስህተት ነዉ ሲሉ ወቅሰዋል፡፡"በእኛ የሽምግልና ጥረታችን እና በጋዛ የሰብአዊነት ስራን በደንብ ከሚያውቁት የእስራኤል ባለስልጣናት እንዲህ ያሉ መግለጫዎች መዉጣታቸዉ በጣም አበሳጭቶናል ብለዋል፡፡ አስታራቂውን አካል ማጥቃት ቁርጠኝነትን አያሳይም። ከእስራኤላውያን ወገኖቻችን እያገኘን ያለነው ግን ይህንን ነው ፤ድብቅ ዓላማ እንዳለን ተከስሰናል። ግን ይህ ከእውነት የራቀ ነው። ይህንን ግጭት ለማስቆም ብቸኛው መንገድ ሽምግልና ነው ሲሉ አክለዋል፡፡ በጋዛ ያለውን እልቂት ለማስቆም እና የእስራኤል ምርኮኞችን ለመመለስ ሂደቱ ላይ እምነት ከሌለ የሽምግልናዉን የተሳካ ውጤት ለማየት በጣም አስቸጋሪ እንደሚሆን ይሰማኛል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ አል-አንሷሪ አክለውም “የኳታር የሽምግልና ጥረቶች እስከቀጠሉ ድረስ፣ የሐማስ የፖለቲካ ቢሮ በዶሃ መገኘቱን የሚያረጋግጥ ምንም ምክንያት የለም። ይህ ቢሮ የተከፈተው ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በመቀናጀት - በሁለቱም ወገኖች መካከል ለሽምግልና ዓላማ ነው ብለዋል። እስካሁን ድረስ በዚህ ረገድ የተለወጠ ነገር የለም” በማለት ተናግረዋል፡፡የኳታር ጠቅላይ ሚንስትር ሼክ መሀመድ ቢን አብዱራህማን ቢን ጃሲም አል ታኒ ቀጠናዊ ውጥረቶችን በማርገብ እና የእስራኤል በጋዛ ላይ ያደረሰችውን አውዳሚ ጦርነት ለማቆም መስራታቸውን ቀጥለዋል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማጅድ አል አንሳሪ ተናግረዋል። በሌላ በኩል በካን ዮኒስ በሚገኘው ናስር ሆስፒታል በጅምላ መቃብር ውስጥ ቢያንስ 35 ተጨማሪ አስከሬኖች መገኘታቸውን የሲቪል መከላከያ ሰራተኞች ገልፀዋል፡፡ በአጠቃላይ በሆስፒታሉ የተገኙ አስከሬኖች ቁጥር ቢያንስ 310 ደርሷል።በካን ዮኒስ የተገደሉት ፍልስጤማውያን ዘመዶቻቸዉን ለማግኘት በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የእስራኤል ወታደሮች ከተማዋን ለቀው ከወጡበት ጊዜ አንስቶ የአስከሬን ፍለጋ ናስር ሆስፒታል ዉስጥ በትጋት እየፈለጉ ይገኛል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
👍 25👎 3
አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ በፀጥታ ሀይሎች ተያዘ አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ በዛሬው እለት አመሻሹን ሚያዚያ 15ቀን 2016ዓ.ም ወደ እስራኤል ሊያቀና በነበረበት ወቅት ላይ በፀጥታ ሀይሎች መያዙን የአርቲስቱ የቅርብ ምንጮች ገልፀዋል። ጉዳዩን አስመልክቶ የአርቲስቱ የቅርብ ወዳጅ በማህበራዊ ትስስር ገፁ "ያያ ዘልደታ" ጉዳዩን አስመልክቶ ተከታዩን አስፍሯል። " ዛሬ ከመሽ ዕብደት በሕብረት የተሰኘውን አዲሱን ትያትር ለማሳየት ወደ ሃገረ እስራኤል ለመሄድ ዝግጅቱን ጨርሶ እነሆ አሁን ከመሸ ከኤርፖርት ተይዞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ተወስዷል::" ሲል አስታውቋል። እስከ አሁን ባለው ሂደት ከመንግስት አካላት ስለ ጉዳዩ የተሰጠ ምላሽም ሆነ ማብራሪያ የለም። #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
🤔 6
በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ዉስጥ የፍልስጥኤም ድጋፍ እየተስፋፋ መምጣቱ ተነገረ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች እየበረታ የመጣውን የተማሪዎች ተቃውሞ ለማብረድ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው።እስራኤል በጋዛ የምታካሂደውን ጦርነት የተቃወሙ ከ100 በላይ የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተቃውሞውን ወደሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እያሰፋው ነው ተብሏል። ፖሊስ ትናንት ምሽት በኒውዮርክ ዩኒቨርሲቲ የነበረውን ተቃውሞ ለማስቆም በመግባት በርካታ ተማሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተገልጿል።በየል፣ በርክሌይ፣ ማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (ኤምአይቲ) እና ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተማሪዎች ማደሪያቸውን በዳስ አድርገው ተቃውሟቸውን እያሰሙ ሲሆን፥ ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ከውጭ እንግዶች እንዳይገቡ በሩን ዝግ አድርጓል። 108 ተማሪዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ያደረገው ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲም የገጽ ለገጽ ትምህርት አቁሟል።ተማሪዎቹ እስራኤል በጋዛ ላይ የምትፈጽመውን ድብደባ ዩኒቨርሲቲዎቻቸው እንዲያወግዙ እንዲሁም ለእስራኤል የጦር መሳሪያ ከሚያቀርቡ ኩባንያዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያቋርጡ ጠይቀዋል።የፍልስጤም ደጋፊዎች በእስራኤል ላይ ተቃውሟቸውን ሲገልጹ ያስተላለፏቸው “ጸረ ሴማዊ መልዕክቶች” ግን እስራኤላውያን ተማሪዎችን ስጋት ውስጥ መጣሉን ነው አሶሼትድ ፕርስ የዘገበው። አይሁዳውያን ተማሪዎች የፍልስጤሙ ሃማስ አሁንም ድረስ እስራኤላውያንን አግቶ መያዙንና ከ1 ሺህ 100 በላይ እስራኤላውያንን ህይወት መቅጠፉን ያነሳሉ።ቁጥራቸው አነስ ይበል እንጂ እስራኤላውያን ተማሪዎችም በኮሎምቢያ እና ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ድምጻቸውን አሰምተዋል ተብሏል።ዩኒቨርሲቲዎቹ የተማሪዎቹን ጥያቄ ለመመለስ ከመሞከር ከመሆን ይልቅ ተማሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል ላይ መጠመዳቸው ተቃውሞውን እያስፋፋው መሆኑ ተገልጿል። በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች እየተስፋፋ ስለመጣው የተማሪዎች ተቃውሞ የተጠየቁት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፥ ጸረ ሴማዊ ይዘት ያላቸው መልዕክቶች መተላለፋቸውን ተቃውመዋል።ፕሬዝዳንቱ “በፍልስጤም ምን እየተካሄደ እንደሆነ የማያውቁ” ያሏቸውን ወገኖችም ተቃውመዋል።የእስራኤል ዋነኛ አጋር በሆነችው አሜሪካ የጋዛው ጦርነት ከተቀሰቀሰ ጀምሮ በርካታ የአደባባይ ተቃውሞዎች ቢደረጉም ዋሽንግተን በቴል አቪቭ ዙሪያ የማይነቃነቅ አቋም እንዳላት የ26 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ በማጽደቅ አሳይታለች። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
👍 52🕊 15👎 2 2👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ሀሰተኛ የህክምና ማስረጃ በመጠቀም ወንድማችን ታሟል በማለት ሲያጭበረብሩ የነበሩ አምስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ በደቡብ ኢትዮጵያ ወላይታ ሶዶ እና በ በተለያዩ ወረዳዎች በመዘዋወር ታማሚ በማስመሰል የማጨበርበር ተግባር ሲፈጽሙ የነበሩ  ግለሰቦች በህብረተሰቡ ጥቆማ መያዛቸውን ፖሊስ አስታዉቋል። በማጨበርበር ድርጊቱ የተሰማሩት ተጠርጣሪዎች አብዛኛዎቹ ወጣቶች ሲሆኑ  ከተለያዩ አከባቢዎች በመምጣት ሀሰተኛ የህክምና ማስረጃ በማዘጋጀት  ወንድማችን በህመም እየተሰቃየብን ነው በማለት መኪና በመከራየት ሲያጭበረብሩ መገኘታቸዉ ተገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ  ከአስራ ዘጠኝ ሺህ ብር በላይ ከህብረተሰቡ በማጨበርበር መሰብሰባቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ሀይሌ ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በሳምራዊት ስዩም #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
👍 22 6
በትግራይ ክልል የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ተጀመረ የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ በዛሬው ዕለት መጀመሩን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡ በዚህ የክትባት ዘመቻ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ዕድሜያቸው ከ 10 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ይከተባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢንስቲትዩት በክትባት መከላከል የሚቻሉ በሽታዎች ቅኝትና ምላሽ ቡድን መሪ አቶ ሚኪያስ አላዩ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዢን ተናረዋል፡፡ በኢትዮጵያ በክትባት እጥረት ምክንያት የሚመጣ የፖሊዮ በሽታ ከ2019 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች በመከሰቱ ፖሊዮን ጨርሶ የማጥፋት ጉዞን አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡ እንደ ሀገር እ.ኤ.አ 2021 እና 2022 አዲሱን የፖሊዮ ክትባት በመጠቀም የተካሄዱ ሁለት ዙር ሃገር አቀፍ የክትባት ዘመቻዎች በጥሩ ተሞክሮነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን ያነሱት አቶ ሚኪያስ በአንዳንድ የሃገሪቱ አካባቢዎች በጸጥታ ችግር ዘመቻዉ ሳይካሄዱ መቅረቱን አንስተዋል፡፡ በትግስት ላቀዉ #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
👍 17😁 6 1
Photo unavailableShow in Telegram
በመላዉ አለም በየእለቱ በተደጋጋሚ የሚጠራዉ ቃል ምንድነዉ? ስንል ባሳለፍነዉ ቅዳሜ ወደእናንተ ላደረስነዉ ጥያቄ መላሾቻችን እና የ 100 ብር የሞባይል ካርድ አሸናፊዎች ታዉቀዋል። በዚህም መሰረት ጫላ መኮንን - ከሰበታ እና የኃላሸት ሸፈራው -ከችሎት መድሃኒያለም የጥያቄዉ መላሾቻችን ናቸዉ። ስለተሳትፎአችሁ እና ዳጉ ጆርናልን የመረጃ ምርጫችሁ እያመሰገንን ቀጣይ ተሸላሚ የሚያደርጉ ጥያቄዎችንም ወደእናንተ የምናደርስ ይሆናል። #ዳጉ_ጆርናል
نمایش همه...
👏 17 6👍 4🤔 3