cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን

پست‌های تبلیغاتی
3 200
مشترکین
+424 ساعت
+147 روز
+18230 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ምዘናውን ሲያስተባብሩ ያገኘናቸው የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የአራዳ እና ቂርቆስ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተስፋዬ አሰፋ በበኩላቸው እንደገለፁት መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ምዘናውን መውሰዳቸው በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ለውጥ እንዲመጣ እና ለአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ውጤታማነት እንደሚጠቅም ተናግረዋል፡፡ የምዘናው ዝግጅትም ጥሩ እንደሆነ ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ፈተናው በጥራት መዘጋጀቱን የገለፁ ሲሆን በምዘናው ሂደት ላይም ከአመራሩ እና አስተባባሪዎች ጋር በመናበብ ምዘናው መካሄዱን ገልጸዋል፡፡ ምዘናውን ሲወስዱ ያገኘናቸው አንዳንድ መምህራን ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት በተከታታይ እንዲህ አይነት ምዘናዎች ቢሰጡ እውቀታችን ለማስፋት ጠቃሚ እንደሚሆን እና በምን አይነት ደረጃ ላይ እንዳሉ የሚያስገነዝብ መሆኑን ጠቅሰዋል፤ በተጨማሪም መምህራንን የሚያነቃቃ በመሆኑ ለወደፊቱ ራሳቸውን በእውቀት እንዲያዳብሩ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
نمایش همه...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ምዘና ጠቀሜታው የጎላ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ (ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በዛሬው ዕለት ለ18591 መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ የጽሁፍ ፈተና ሰጠ፡፡ ምዘናው በ15 የፈተና ጣቢያዎች የተሠጠ ሲሆን በምዘና ጣቢያው የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ እንደተናገሩት የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ ምዘና ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ እና ተማሪዎችም የተሻለ ትምህርት እንዲያገኙ አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለዋል፡፡ በዚህም በዛሬው ዕለት በግልና በመንግስት ት/ቤቶች ያሉ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ምዘናውን እንደወሰዱ ጠቁመው በምዘናው ሂደትም በጥሩ ሁኔታ መከናወኑን ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም የጽሁፍ ምዘና ያለፉ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የማህደረ ተግባር ምዘና ወስደው ሲጠናቀቅ ውጤታቸው እንደሚገለፅ አስታውቀዋል፡፡
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ለ18591 መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ የጽሁፍ ፈተና በነገው ዕለት ይሰጣል፡፡ (ሚያዚያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ለ18591 መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ የጽሁፍ ፈተና በነገው ዕለት እንደሚሠጥ አስታወቀ፡፡ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ እንደተናገሩት ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ለ5ኛ ጊዜ የሚሰጠው የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ ፈተና አላማው የመምህራኑንና የትምህርት ቤት አመራሩን ብቃት በማረጋገጥ የትምህርትን ተገቢነትና ጥራትን ማረጋገጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በነገው ዕለት የሚሰጠው ፈተና በ36 የሙያ አይነቶች በ3 የማስተማሪያ ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣በአፋን ኦሮሞ እንዲሁም በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች በ15 የፈተና ጣቢያ የሚሰጥ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አክለውም እንደገለጹት ፈተናውን ለማስፈጸም 1003 የፈተና አስፈጻሚዎች ይሳተፋሉ፤እነዚህም መዛኞች/ፈታኞች፣ሱፐርቫይዘሮች አስተባባሪዎች መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ ይህ የጽሁፍ ፈተና ከተጠናቀቀ በኋላ የማህደረ ተግባር ምዘና/ፈተና ይከናወናል፤ በመጨረሻም ውጤቱ እንደሚገለጽ አስታውቀው ለተፈታኝ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች መልካም የፈተና ጊዜን ተመኝተዋል፡፡ #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
نمایش همه...
ዛሬ የከተማ አስተዳደራችን ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉበት የትራንስፎርሜሽናል ዕቅድ ዝግጅት ወርክሾፕ ማካሄድ ጀምረናል። በወርክሾፑ አዲስ አበባን ዓለም አቀፍ ተመራጭ ከተማ ለማድረግ በሚያስችሉ በተመረጡ ስድስት አጀንዳዎች ላይ ስልጠና የሚሰጥ እና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ዝግጅት የሚከናወን ሲሆን በስልጠናው ዓለም አቀፍ የዘርፉ ባለሙያዎች ለአመራራችን ስልጠናዎችን ይሰጣሉ። ሃገራችንን ለማበልጸግ በሁሉም ዘርፍ ያለ እረፍት መስራታችን ተጠናክሮ ቀጥሏል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ
نمایش همه...
ምዘናው በፈቃደኝነት ለተመዘገቡ 18 ሺ 591 ለሚሆኑ መምህራንና የትምህርት አመራሮች ሃሙስ ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም በተመረጡ የመፈተኛ ጣቢያዎች እንደሚሰጥ እንዲሁም በምዘናው ወቅትም ተመዛኞች ስልክም ሆነ ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክስ ግብአቶች ይዘው ፈተና ክፍል መግባት እንደማይችሉ ፣ ተመዛኞች የታደሠ መታወቂያ ይዘው መገኘት እንደሚጠበቅባቸው ፣ ተመዛኞች ፈተናው ከመጀመሩ በፊት 1:00 ሠዓት ቀደም ብለው (1:30) ላይ የምዘና መስጫ ቅጥር ግቢ ውስጥ መገኘት እንዳለባቸው እና አርፍዶ መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ ፣ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አድማሱ ደቻሳ ፣ የባለስልጣን መስራቤቱ ማኔጅመንት አባላት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳና አባላት ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እንዲሁም የሁለቱም ተቋማት የክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ምንጭ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
نمایش همه...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

ለመምህራንና ለትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና በከተማ አቀፍ ደረጃ ግንቦት 1 ቀን የሚሰጥ መሆኑ ተገለጸ፡፡ (ሚያዚያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮና የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በጋራ በመሆን የሚሰጠውን ከተማ አቀፍ የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና አፈጻጸምን አስመልክቶ ውይይት አካሂደዋል፡፡ ምዘናው መንግስት ለትምህርት ጥራትና መሻሻል ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በተሻለ ለመምራት የሚያስችል መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ቁልፍ ሚና ያላቸው አካላት በመሆናቸው ምዘና መደረጉ ተገቢና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ዋነኛው ሂደት ነው ብለዋል፡፡ ዶክተር ዘላለም አያይዘውም ፈተናውን በተሳካ መልኩ ለማካሄድ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ በበኩላቸው ምዘናው የመምህራንን የሙያ ብቃት ለማሳደግና እውቅና ለመስጠት ከማስቻሉም በላይ መምህራንና የትምህርት አመራሩን በበቂ ስነ-ልቦና ለማስተማርና ለመምራት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡ የምዘናውን አካሄድ ውጤታማ ለማድረግም የትምህርት አመራሩና የክፍለከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊዎች ለተፈታኞች የሚሰጡ ቅድመ ምዘና ገለጻዎች ላይ በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡
نمایش همه...
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በ2016 ዓ.ም የሙያ ብቃት ምዘና ለሚመዝኑ መዛኞች፣ሱፐርቫይዘር እና አስተባባሪዎች ኦረንቴሽን ሰጠ፡፡ (ሚያዚያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የኮልፌ ቀራንዮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግንቦት 1/2016 ዓ.ም ለሚሰጠው የመምህራንና የትምህርት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና ለሚመዝኑ መዛኞች፣ሱፐርቫይዘር እና አሰተባባሪዎች ኦረንቴሽን መስጠቱን ገለጸ፡፡ የቅ/ጽ/ቤቱ የመምህራንና የትምህርት አመራር ሙያ ፈቃድ ምዘና ባለሙያ የሆኑት አቶ ይድነቃቸው ደበል የውይይት ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን መዛኞች ስራቸውን ውጤታማ በሆነ መልኩ ተግባርና ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማስቻልና የተሟላ ግንዛቤ ኖሯቸው ስራውን እንዲሰሩ ለማድረግ መድረኩ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመድረኩ በቀረበው ሰነድ ላይም ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ምንጭ፡- የኮልፌ ቀራንዮ ቅ/ጽ/ቤት #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ፅዱ ጎዳና ኑሮ በጤና ለ'ጽዱ ኢትዮጵያ'
نمایش همه...
እናስታውስዎ (ሚያዚያ 28 ቀን 2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የባለስልጣኑ ራዕይ፡- • በ2022 በአገር አቀፍ ደረጃ ብቁ እና ተወዳዳሪ ተቋማትና ባለሙያ ተፈጥሮ ማየት፤ የባለስልጣኑ ተልዕኮ፡- • በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ተቋማትን ጥራት፣ ተገቢነትና በኢንዱስትሪው መሪነት የባለሙያዎች የሙያ ብቃት በምዘና በማረጋገጥ ደረጃውን የጠበቀ ብቁና ተወዳዳሪ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም እና ባለሙያ መፈጠሩን ማረጋገጥ ነው፡፡ የባለስልጣኑ እሴቶች፡- • ለትምህርትና ስልጠና ጥራት ቅድሚያ መስጠት • ሙያ ስነምግባር • የላቀ ምዘና • በጋራ መስራት • በዕውቀትና በእምነት መስራት • ተጠያቂነት • ለህግ መገዛት • የላቀ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት የባለስልጣኑ ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች፡-  የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ጥራትና ተገቢነት  የላቀ የሙያ ብቃት ምዘና #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
نمایش همه...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እና አበባ የማድረግ ስራችን አካል በሆነው የነገዋ የሴቶች የተሀድሶ እና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ሰልጣኞች ጋር የትንሳኤ በዓልን አብረን አክብረናል፡፡ የትንሳኤ በዓልን አብረን ለማሳለፍ የጋበዝናቸው እንግዶች በማዕከሉ በስልጠና ላይ ለሚገኙ ለሁሉም እህቶቻችን የስራ እድል በመፍጠር አብረውን ለመስራት ቃል የገቡ ሲሆን እነዚህን ልበ ቀና ባለሃብቶች በሰልጣኝ ሴት እህቶቻችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ፡፡ አዲስ አበባችንን ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት የሁሉም ከተማ የማድረግ ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡ ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ
نمایش همه...