cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

LOVE ✌ HOPE ❤

In This Channel u can get #New music #old music #tiktok videos #Artist pics #Modern dasig #HD pics👇👇 Just join @Henaa_21

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
Advertising posts
549مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

نمایش همه...
Join Us 🀄️➠@qdamawiyan
نمایش همه...
ጥላሁን ገሰሰ ኧረ እንዴት አርጌ ልተዋት...🎵 መልካም ምሽት ይሁንላችሁ! 🙌❤️ @qdamawiyan
نمایش همه...
نمایش همه...
የንጉሡ ልደት #Ethiopia | ዛሬ ሐምሌ 16 ቀን 1884 ዓ.ም ከራስ መኮንን ወልደሚካኤልና ከወ/ሮ የሺእመቤት ዓሊ ጋምቾ ከሐረር ከተማ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ኤጀርሳ ጎሮ በተባለች ቦታ ልጅ ተፈሪ ተወለዱ፡፡ አባታቸው የአፄ ምኒልክ የአክስት ልጅ ናቸው፡፡ እናታቸው ወ/ሮ የሺእመቤት ዓሊ ከተፈሪ በፊት ስድስት ልጆች ወልደው የነበረ ቢሆንም፤ሁሉም እንደተወለዱ ሞተውባቸዋል፡፡ አሁንም ሰባተኛውን ልጅ ተፈሪን ለመውለድ ሁለት ወራት ቀርቶኛል ብለው ሲያስሱ ድንገት በከባድ ምጥ ይያዙና ፈጣኑ ተፈሪ በተረገዙ በሰባተኛው ወር ይወለዳሉ፡፡ ልጅ ተፈሪ እንደተወለዱ ቤተዘመድ “እናቱ ካዩት እንዳተለመደው ይሞታል” በማለት ህፃኑን እናቱ ሳያዩት ይዘውት ይሄዳሉ፡፡ ይህ ክስተት በባህላዊ አገላለፅ “ሾተላይ” የሚባል ሲሆን፤ ሰው ላይ ሊኖር የሚችለው ኃይለኛ የዓይን ጨረር ሌላ ሰው ላይ ሲያርፍ እስከሞት የሚያደርስ ጉዳት እንደሚያስከትል ይታመናል፡፡ በሳይንሳዊ ገለፃ ደግሞ የእናት ወይም የኣባት የደም አይነት RH Negative ሆኖ የሌላኛው RH Positive ይሆንና የሁለቱ ወላጆች ደም ሳይጣጣም ሲቀር የሚከሰት ችግር ተደርጎ ይገለፃል፡፡ በዚህ ምክንያት ህፃኑ ተፈሪ ከእናቱ ወዲያው መለየት ነበረበትና ከወላጆቹ ቤት ወጥቶ ዘመድ ቤት ማደግ ይጀምራል፡፡ እናቱ የህፃኑን ሁኔታ በመልዕክት ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ፤ በድጋሚ አርግዘው ነበርና ከ20 ወራት በኋላ መጋቢት 6 ቀን 1886 ዓ.ም በዚሁ በወሊድ ምክንያትህይወታቸው አለፈ፡፡ [ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ደግሞ በመጻፋቸው ከዚህ የተለየ ይጽፋሉ] ልጅ ተፈሪ የእናትን ጣዕም ሳያውቀው ቀረ፡፡ ከህፃንነቱ ጀምሮ የአጎቱ የደጃዝማች ብሩ ሓይለማርያም ባለቤት ወ/ሮ ትሰሜ አባይርጋ ከእምሩና ከልጃቸው ጋር አሳደጉት፡፡ በዚያም ሳሉ አባታቸው ራስ መኮንን የፈረንሣይኛ ትምህርት እንዲማሩ መምህር ቀጠሩላቸውና ልጅ ተፈሪ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ አደጉ፡፡ በ10 ዓመታቸው በ1894 ዓ.ም ከሐረር ወደ አዲስ አበባ መጥተው ለመጀመሪያ ጊዜ ከአፄ ምኒልክ ጋር ተገናኝተው ተዋውቀው/ ተመልሰው ወደ ሐረር ሄዱ፡፡ አባታቸው ራስ መኮንን በ1898 ዓ.ም ህዳር 10 ቀን የደጃዝማችነት ማዕረግ ሰጥተው “ጋራ ሙለታ” የተባለውን አውራጃ ሾሟቸው:: “ተከታይ ልጀ ደጃዝማች ተፈሪ ነው” ብለውም ለመኳንንቶቻቸው ይፋ አደረጉ፡፡ ልጅ ተፈሪ በ14 ዓመታቸው የደጃዝማችነት ማዕረግ እንዳገኙ ወዲያው በ1898 ዓ.ም መጋቢት 13 ቀን አባታቸው ራስ መኮንን ሞቱ፡፡ በዚህ ጊዜ አፄ ምኒልክ ተፈሪን ከሓረር ወደ አዲስ አበባ ኣስመጥተው ደጃዝማችነታቸው እንዴፀና ቀረብ የሚለውን የሰላሌን ግዛት ሾሟቸው፡፡ ተፈሪ ግን ለተሰጣቸው ግዛት ሌላ እንዴራሴ ወክለው በኢትዮጵያ ብቸኛ ትምህርት ቤት በነበረው በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት ገብተው ሐረር እያሉ የጀመሩትን ትምህርታቸውን ቀጠሉበት፡፡ ከዚያም በ1899 ዓ.ም የባሶ በጌምድር/ ግዛትን፡ ቀጥሎ በ1900 ዓ.ም ሲዳሞን ተሾሙ፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላም ሲዳሞን ትተው የኣባታቸውን ግዛት ሰፊውን ሐረርጌንና አውራጃዋን እንዲያስተዳድሩ ተደረገ፡፡ የሐረርጌ ህዝብም በደስታ ተቀበላቸው:: በ1903 ዓ.ም በሐምሌ ወር የንጉስ ሚካኤልን የልጅ ልጅ ወ/ሮ መነንን አግብተው መኖር ጀመሩ፡፡ ደጃዝማች ተፈሪ በ19 ዓመታቸው ወ/ሮ መነንን ኣግብተው በ1905 ዓ.ም የመጀመሪያ ልጃቸውን ልዕልት ተናኘወርቅን ወለዱ፡፡ ከምኒልክ ሞት በኋላ ስልጣን የያዘው እያሡ በ1907 ዓ.ም ደጃዝማች ተፈሪን ከሐረርጌ ግዛት ሽሯቸው ወደአዲስ አበባ መጥተው እንዲቀመጡ ተደረገና ወዲያው የከፋን ግዛት ሾማቸው፡፡ ሆኖም ደጃዝማች ተፈሪ አልሄዱበትም፡፡ ተፈሪ የአውሮፓ ቋንቋ የሚያውቁ፣ ከአውሮፓውያኑ ጋር ያለአስተርጓሚ በቀጥታ የሚነጋገሩ ጨዋ፣ ዝምተኛ ... እየተባሉ ቆዩ፡፡ በ1909 እያሱ ከስልጣን ተወግዶ ዘውዲቱ ሲነግሱም በወቅቱ አዲስ አበባ የነበሩት ደጃዝማች ተፈሪ ራስ በሚል ማዕረግ ኣልጋወራሽ ሆነው የራስ ወርቅ አሰሩ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ንጉሠ ነገስት እስከሆኑበት እስከ 1923 ዓ.ም ድረስ በተከታታይ ልዑል አስፋወሰንን፣ ልዕልት ዘነብወርቅን፣ ልዕልት ፀሐይን፣ ልዑል መኮንንን እና አቤቶ ሳህለስላሴን ወልደዋል፡፡ *** (ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘ ኢትዮጵያ እንኳን ለ130ኛ የልደት በዓልዎ አደረሰን! እርስዎና ቀደምት አባቶቻችን ዓለምን ያስደነቀ ሥልጣኔና ስርዓት ገንብታችሁ የኢትዮጵያን ስም ከፍ አድርጋችሁ በዓለም አቀፍ መድረክ አስጠርታችኋል:: ካለ እርስዎና ንጉሠና ንግሥተ ነገሥታት እናትና እባቶቻችን ታሪክ ሀገራዊ ክብር የለንም! @qdamawiyan
نمایش همه...
#ሰውየው አንድ ትልቅ በሬ አርዶ የብረት ምድጃውን ለኩሶ ለልጁ እንዲህ አለው "የምንወዳቸውንና የምናከብራቸውን ጎረቤቶቻችንን #አብረውን እንዲበሉ ሄደህ ጥራቸው ።” #ልጁ ወደ ጎዳና ወጥቶ እንዲህ ሲል መጮህ ጀመረ “እባካችሁ የአባቴ ቤት በእሳት ስለተያያዘ ለማጥፋት እርዱን ድረሱልን!" ከጥቂት ጊዜ በኋላ ጥቂት ሰዎች መጡ ሌሎቹ የእርዳታ ጩኸቱን እንዳልሰሙ ሆነው ቀሩ ። የመጡ ሁሉ ግን በሉ ጠጡ ። #ባየው ነገር የተደናገጠው አባት ወደ ልጁ ዞሮ እንዲህ አለ "የመጡትን ሰዎች እኔ አላውቃቸውም ከዚህ በፊትም አይቼአቸው አላውቅም ስለሆነም ወዳጆቻችን ቤተሰቦቻችንና የሥራ ባልደረቦቻችን የት አሉ?" #ልጁም "ከቤታቸው ወጥተው የመጡት ሰዎች ቤታችን ላይ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት ጩኸት ሰምተው ሊረዱን እንጂ በቤታችን የተዘጋጀውን ፓርቲ ሊካፈሉ አይደለም ። ግብዣችንና እንግዳ ተቀባይነታችን የሚገባው ለእነዚህ ዓይነቶቹ ነው" አለ ። #ሁሉም የምትወዷቸውና የምታከብሯቸው ሰዎች እውነተኛ ወዳጆቻችሁ ላይሆኑ ይችላሉ ። እውነተኛ ወዳጅ ማለት በተቸገራችሁና የእነርሱ ድጋፍ በሚያስፈልጋችሁ ጊዜ ፈጥነው ከጎንዎ የሚገኙ ናቸው ። ስለዚህ አንዳንድ ጊዜ ስለእርስዎ የሚጨነቁትን እውነተኛ ሰዎች ለማወቅ ጥረት ያድርጉ ። #ሼር በማድረግ ተባበሩን🙏 @qdamawiyan
نمایش همه...
እረኛዬ ምዕራፍ 4 ክፍል 1
نمایش همه...