cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

TIKVAH-ETHIOPIA BACKUP

ይህ የቲክቫህ (ተስፍ) ኢትዮጵያ #BACKUP ቻናል ነው (ዋናው ቻናል በማናውቀው ምክንያት #ከተቋረጠ ወይም #ከጠፍ) ሁሉንም የቲክቫህ መረጃ እና መልዕክቶች በዚህ ቻናል ማግኘት ይችላሉ። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
7 737
مشترکین
-724 ساعت
-397 روز
-26730 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" የመኪና እቃ የተሰረቀባችሁ በአካል ቀርባችሁ ንብረታችሁን ምረጡ " - ፖሊስ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በከተማይቱ የመኪና እቃ ስርቆት ወንጀል ስጋትን ለመቀነስ ሕግን መሰረት ያደረገ ኦፕሬሽን በልደታ ፤በአራዳ እና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አዋሳኝ ወረዳዎች ላይ መስራቱን አሳውቋል። ፖሊስ በተለምዶ ሱማሌ ተራ በሚባለው አካባቢ ባካሄደው ኦፕሬሽን ፦ ➡ 528 ልዩ ልዩ ፍሬቻዎችን ፣ ➡ 187 ስፖኪዮችን ፣ ➡ 113 የመኪና መብራቶች ፣ ➡ 172 የዝናብ መጥረጊያ በአጠቃላይ 33 ልዩ ልዩ በድምሩ 1 ሺ 269 አይነት የመኪና እቃዎችን መያዙን አስታውቋል፡፡ የተሰረቁ የመኪና እቃዎችን ሚገዙና የሚያሻሽጡ 89 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ መቀጠሉን ገልጿል። በተለያየ ጊዜ የመኪና እቃ የተሰረቀባቸው ግለሰቦች ፦ ° በልደታ ፣ ° በአራዳ ° በአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎቸው በመቅረብ  ንብረታቸውን መምረጥ እንደሚችሉም ፖሊስ አስታውቋል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ፥ በከተማው ለመኪና እቃ ስርቆት መስፋፋት ልዩ ልዩ ምክንያቶች ቢኖሩም በተለይ ወንጀለኞችን በማደራጀትና በማሰማራት የመኪና እቃ የሚያሰርቁ እና የተሰረቁ እቃዎችን የሚገዙ ህገ-ወጦች ለወንጀሉ መስፋፋት ዋና ምክንያት ናቸው ብሏል። #AddisAbabaPolice @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ስቅለት በክርስትና አስተምሮ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለ በደል ያለ ጥፋት ንጹሕ እና ጻድቅ የኾነውን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰቀሉበት ዕለት ነው። ዕለቱ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ዂሉ መድኀኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልዕልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የሚታሰብበት ታላቅ ቀን ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን #በስግደት እና #በጾም የሚታሰብ ሲሆን በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረትም በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች ታስቦ ይውላል፡፡ በተለይ ደግሞ ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከንጋታው ጀምሮ እስከ ማምሻው በዕለቱ የተፈጸሙትን ክስተቶች በሰዓት ከፍላ በልዩ መንፈሳዊ ሥርዓትና በስግደት ታከብረዋለች ፦ ✝ ዓርብ ጠዋት ዓርብ ጠዋት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ፊት በፍርድ አደባባይ መቆሙ ይታሰባል። የካህናት አለቆችና ሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ ፤ አስረውም ወሰዱት ፥ ለገዢው ለጰንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት። ✝ በ3 ሰዓት ጲላጦስ በወቅቱ በነበረው ሕዝብ ግፊት መሠረት ወንጀለኛውን በርባንን ከእስር አስፈትቶ በምትኩ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠበት ፤ አካሉ እስኪያልቅም 6,666 የገረፉት ከሊቶስጥራ - ቀራኒዮ እርጥብ መስቀል አሸክመው የወሰዱበት ነው። ✝ በ6 ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስን እጆቹን እና እግሮቹን ቸንክረው በቀራንዮ ጎልጎታ ተራራ በ2 ወንበዴዎች መካከል የተሰቀለበት ነው። ✝ በ9 ሰዓት በእምነቱ አስተምሮ ይህ ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ከሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ የለየበት ወደ ሲዖል ወርዶም የታሠሩትን ሁሉ ያስፈታበት ነው። ✝ 11 ሰዓት ዮሴፍ እና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብር እና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር የቀበሩበት ነው። (Tikvah Ethiopia Family) @tikvahethiopia
نمایش همه...
👍 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#Urgent ዶ/ር ቤቴል ገርማሞ ትባላለች። ገና የመመረቋን ደስታ ሳታጣጥም እንደቀልድ ለ " ቶንሲል ህመም " በሚል ምርመራ ስትደረግ ያልጠበቀችውን መጥፎ ዜና ተረድታለች። ዶክተሯ የደም ካንሰር በአይነቱ ደግሞ " acute lymphoblaatic leukemia " የሚባል እንዳለባት በፓቶሎጂ ምርመራ ተረጋገጠባት። የጥቁር አንበሳ ሜዲካል ቦርድም አፋጣኝ የሆነ የመቅኒ ንቅለ ተከላ እንዲደረግላት መወሰኑን ከቤተሰቦቿ መረዳት ተችሏል። የደም ካንሰር ምንም እንኳን እጅግ አጣዳፊ እና አስደንጋጭ ቢሆንም በጊዜ ከታከመ እና የመቅኒ ንቅለ ተከላ በማድረግ የመዳን እድል ያለው በሽታ ነው። መላው ኢትዮጲያዊያ የዚህችን ምስኪን እና ወደፊት ህዝቧን በሞያዋ የምታገለግል ሀኪም ህይወት እንዲታደግ ጥሪ ቀርቧል። ዶ/ር ቤቴል በወላይታ ዞን በዴሳ በምትባል ከተማ ተወልዳ ያደገች እና በቤተሰቦቿ እና በአከባቢው ማህበረሰብ እንደምሳሌ ምትጠቀስ ብርቱ ሴት ናት። እንደአብዛኛው ኢትዮጲያዊ ቤተሰብ አቅማቸው እሷን ለማሳከም የሚበቃ አይደለም። ስለሆነም አቅም ያላችሁ ሁሉ ድጋፋችሁ ታደርጉ ዘንድ ቤተሰቦቿ ተማፅነዋል። በስልክ ደውሎ ለማነጋገር በ0913922441 ላይ መደወል ይቻለል። Dr Bethel Germamo Ganebo ➡️ የባንክ አካውንት CBE 1000105102384 @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮ ቴሌኮም ተናፋቂው የትንሳኤ በዓል ፋሲካ እንደ ሁልጊዜው ደምቆ እንዲፈካ በፍጥነት ግንኙነት የበዓል ድባቡን ለማቅለም ልዩ የትንሳኤ ጥቅል ከ ኢትዮ ቴሌኮም እስከ 25% ቅናሽ የተደረገባቸውን የትንሳኤ ጥቅል በተለያየ የጊዜ ገደብ አማራጮች ማቅረባችንን በደስታ እንገልጻለን! ጥቅሎቹን በቴሌብር ሱፐርአፕ ከተጨማሪ 10% ስጦታ ጋር እንዲሁም በማይ ኢትዮቴል፣ አርዲ ቻትቦት ወይም በ*999# ይግዙ፤ ለሚወዷቸውም በስጦታ እያበረከቱ መልካም ምኞትዎን ይግለጹ! መልካም የትንሳኤ በዓል ! ተጨማሪ መረጃ ፦ https://t.me/telebirr https://t.me/ethio_telecom #Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
በአዲስ አበባ ከተማ የወጣው የመሬት ሊዝ  ጨረታ ተራዘመ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ  ፤ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ በሌሎችም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል። በዚህም ከሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 24/2016 ዓ/ም ድረስ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ሲከናወን ቆይቷል። ነገር ግን የጨረታ ሰነድ ሽያጩ ከ28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 09/09/2016 ዓ/ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት መራዘሙ ተነግሯል። ተጫራቾች ፦ - የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ፣ - ሲፒኦ፣ - የግንባታ አቅም ማሳያ ማስረጃ፣ - ሰነዱን ለመግዛት በቴሌ ብር የከፈሉበት ስሊፕ - ሌሎች መያያዝ ያለባቸዉ እና በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን በመጨመር የጨረታ ሰነዶችን በኤንቨሎፕ በማሸግ ግንቦት 09/2016 ዓ/ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አከባቢ ኤም ኤ (MA) ህንፃ ላይ በሚገኘው የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ተብሏል። ጨረታው ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 12/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ ለተከታታይ 9 የስራ ቀናት በቦሌ ክ/ከተማ አስተደዳር አዳራሽ  እንደሚከፈት ተገልጿል። የጨረታው ዝርዝር👇 https://t.me/tikvahethiopia/87112 @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#Kenya በጎረቤት ኬንያ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 188 ደርሷል። ካለፈው መጋቢት ጀምሮ በደረሰው አውዳሚ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 188 መድረሱን የሀገር አስተዳደር ሚኒስቴር አሳውቋል። እስካሁን ያልተገኙ በርካታ ሰዎች መኖራቸውም ተገልጿል። በኬንያና ሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች በተከታታይ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ የብዙ ሰዎች ህይወት እየጠፋ ሲሆን የከፍታ ቦታዎች መናድም ነዋሪዎችን ካለመጠጊያ አስቀርቷል፡፡ መንገዶችን ድልድዮችን እና ሌላም የመሰረተ ልማት አውታሮችን ውድሟል። #VOA @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" ' እኔ ሰርቂያለሁ ስሜን ግን ለጥፏል ' የሚል ይምጣና ይክሰሰኝ ካሳውን እንከፍላለን "  - አቶ አቤ ሳኖ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ከዋልታ ቴሌቪዥን ቆይታ አድርገው ነበር። በዚህም ወቅት ፥ መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ/ም በሲስተም ችግር ምክንያት በተፈጠረው እክል ተዘርፎ የተወሰደውን ባንኩ ገንዘብ  እያስመለሰ መሆኑንና ከ801 ሚሊዮን ብር የቀረው 25 ሚሊዮን ብር መሆኑን ገልጸዋል። በዕለቱ 30 የባንኩ ሰራተኞች በግብይት ላይ መሳተፋቸውን ተከትሎ አሁን ላይ ከስራ ታግደው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን ገልጸዋል። በሌላ በኩል ፥ ባንኩ በምን የሕግ አግባብ ነው ሰዎች ነጻ ሆኖ የመገመት መብታቸው ተጥሶ ፎቷቸው የተሰራጨው ? የሰዎችን ምስል ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዴት አሰራጨ በሚል ተጠይቀዋል። አቶ አቤ ፤ " እኛ ዛሬም ድረስ ወንጀለኛ ናቸው የሚል ቃል አልወጣንም። ይሄን ገንዘባችንን ወስደዋል መልሱ ነው ያልነው መውሰዳቸውን 101% እናውቃለን " ሲሉ ገልጸዋል። " ዛሬ ያለንበት ሁኔታ እና መጀመሪያ ላይ የነበረው ይለያያል። እሁድ የነበረው ታሪክ ' ባንኩ ማን ብር እንደወሰደበት አያውቅም ' የሚል ነው በተለይ ሶሻል ሚዲያ ላይ ሲቀለድ ነበር እኛ ግን ' እናውቃለን መልሱ ስንል ' ነበር ምላሹ ' አያውቅም ' የሚል ነበር በኃላ 1 ሳምንት ሰጠን በተደጋጋሚ አስጠነቀቅም እንዲመልሱ ከዛ ስም እና ፎቷቸው እዲወጣ ወደማድረጉ ገባን " ብለዋል። " ምስል አታሰራጭ የሚል በህገ-መንግስቱ አልተገለጸም። ሲቀጥል 15 ሺህ ሰው በኮንቬንሽናል ህግ ሊፈታ የሚችል ችግር አይደለም " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " naming and shaming የሚል ህግ አለ ገንዘብ የወሰደውን ሰው ስሙን አውጥቶ ያያችሁት ንገሩትና ይመልስ ነው ያልነው " ብለዋል። " ነጻ ሆኖ የመገመት መብቴ ተነክቷል " የሚል ካለ ይክሰሱንና ካሳ ይጠይቁ ሲሉ ገልጸዋል። አቶ አቤ " ' እኔ ሰርቂያለሁ ስሜን ግን ለጥፏል ' የሚል ይምጣና ይክሰሰኝ ካሳውን እንከፍላለን " ሲሉ ተናግረዋል። " ያደረግነው ነገር በተወሰነ ደረጃ ወቀሳ ሊቀርብበት የሚችል ነገር ነው። ለችግሩ መፍትሄ ግን ያደረግነው ብቻ ነበር። ነገሩ ከህግም ከፖሊስም አቅም በላይ ነው ይሄን ሁሉ ሰው ማሰር አይችሉም፤ ፍርድ ቤት ይሄን ሁሉ ሊዳኝ አይችልም። የህግ ጥያቄ ቢነሳም ትክክለኛው መፍትሄ ያደረግነው ብቻ ነበር እሱንም አማራጭ ስላልነበረን ነው ያደረግነው ያን ማድረጋችን ህዝቡ እንዲያውቀው ሆኖ የወሰደው ሁሉ ተሰልፎ መጥቶ መለሰ " ብለዋል። " ገንዘቡ የህዝብ ነው እያስመለስን የቀረው ከ801 ሚሊዮን ብር 25 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው ፤ የማሰባሰቡ ስራ 96.8 በመቶ ደርሷል " ሲሉ አሳውቀዋል። " ምንም እንኳን ልጆች ቢያጠፉም ወላጆች መጥተው አርመዋልና የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ጨዋ ነው ፤ አሁንም አዋቂ አለ ፣ የሚያስትምር አለ፣ ሽማግሌ አለ፣ ጨዋ ወላጅ አለ ማለት እፈልጋለሁ " ሲሉ ለቴሌቪዥን ጣቢያው ተናግረዋል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
👍 1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" በየጊዜው ወጣቶች የምገብርበት የጦርነት ምዕራፍ መዘጋት አለበት " - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በኩል ዛሬ መልዕክት አሰራጭተው ነበር። በዚህም ፤ " የህዝባችን ሁለንተናዊ መብትና ጥቅም ከማረጋገጥና አስተማማኝ ከማድረግ የሚቀድም ሌላ አጀንዳ የለንም " ብለዋል። " የህዝባችን ጥቅምና መብት የሚያረጋግጥ መንገድ ሁሉ እንጓዘዋለን " ያሉት አቶ ጌታቸው " ጉዞው እንዲሳካ የህዝቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነው " ሲሉ አክለዋል። ፕሬዜዳንቱ ፤ " ከሚገባው በላይ ያበረከተ ህዝብ በቅንነትና ታማኝነት ማገለገል ይገባል " ሲሉም ገልጸዋል። " ህዝቡ ከጦርነትና ጦርነት ወለድ ችግሮች በማላቀቅ ወደ አስተማማኝ ሰላም እንዲሸጋገር መስራት ይገባል " ሲሉም አስገንዝበዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " በየጊዜው ትኩስ ሃይል የሆኑትን ወጣቶች የምንገብርበት የጦርነት ምዕራፍ ተዘግቶ ፤ የልማትና የእድገት ፍላጎታችን እንዲሳካ መስራት አለብን " ብለዋል። #TikvahEthiopiaFamilyMekelle @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
እነ ቀሲስ በላይ ክስ እስኪመሰረትባቸው በእስር ይቆያሉ። የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በነ ቀሲስ በላይ መኮንንና ሌሎች 2 ተጠርጣሪዎች ላይ የክስ መመሥረቻ 15 ቀናት ፈቅዷል። በሀሰተኛ ሰነድ ከአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ከ6 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ለማውጣት ሙከራ አድርገዋል ተብለው የተጠረጠሩትና በቁጥጥር ስር የዋሉት ቀሲስ በላይ መኮንንና 2 በወቅቱ አብረዋቸው የነበሩ ግለሰቦች ዛሬ ለ3ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። በዚህም ፍርድ ቤት ለዐቃቤ ሕግ 15 ቀናት የክስ መመስረቻ ፈቅዷል። ተጠርጣሪዎች ክሱ እስኪመሰረት ድረስ ባሉበት ማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ፍርድ ቤት አዟል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር በዓሉን ምክንያት በማድረግ እስከ 25% ቅናሽ የተደረገባቸውን ማራኪና ውብ የመመገቢያ ጠረጴዛዎቻችንን በመግዛት ልዩ የአብሮነት ጊዜ ያሳልፉ! የዘመናዊነት ተምሳሌት! አድራሻችን፦ 1. ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251 995 27 2727 / +251 911 51 6843 2. ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251 957 86 8686 3. ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251 993 82 8282 👉 Telegram:  https://t.me/yonatanbt_furniture 👉 Facebook:  https://www.facebook.com/profile.php?id=100087238034736 👉 TikTok: https://www.tiktok.com/@yonatanbtfurniture 👉 Instagram: https://www.instagram.com/yonatanbtfurniture/
نمایش همه...