Change ||| የአስተሳሰብ ለውጥ |||
کانال بسته
Transformation of Mind to transform the society (በሀሳብ ልዕልና የሚያምን ማህበረሰብ መፍጠር)
نمایش بیشتر1 882
مشترکین
-524 ساعت
-67 روز
-3230 روز
آرشیو پست ها
የስኬት ጉዞ
የምትፈልገው ነገር ምን ያሳጣሃል? ምንስ ያህል ሌላ ነገሮች ብታጣ መቀጠል ትችላለህ? ለማጣት ምን ያህል ዝግጁ ሆነህ ታውቃለህ? ይሄ መራራ የህይወት እውነታ ነው።
ስለስኬት ሲወረ ስለሚሰጠህ እንጂ ስለሚያሳጣህ ሲወራ ብዙ አይታይም። ይህ የስኬትን የመጨረሻው የሽልማት ህይወት በመናፈቅ እድሜያቸው የተለያዩ ነገሮች በመሞከር ተላላ ሆነው ብዙዎች ከመንገድ አስቀርቶል። ነገር ግን በየትኛው መስክ ላይ ስኬታማ መሆን የሚፈልግ ግለሰብ ሊዘነጋው የማይገባው ጉዳይ በመንገዱ ላይ ብዙ ነገሮች እንደሚያጣ ነው።
ሰዎች ከጉኑ ከመሆኑ ይልቅ እንቅፋት ሲሆኑብህ፤ ነገሮች መልካቸው ሲቀያዮሩብህ፤ ወዳጅ የውድቀትህ ጉድጎድ ሲቆፍርብህ፤ የቅርብ ሰዎች የውደቅት ምላሳቸው ሲዘረጉብህ፤ ምንም ነገር በህይወታቸው አሳክተው የማያውቁ ሰዎች የትችት ዶፍ ሲያዘቡብ ብዙ ብዙ የምላስ ጅራፎች አቅምህ ሲያደክሙት እናም ደግሞ ነገሩ ከስኬቱ ይልቅ ውደቀት አካራከሩ ሳይሆንብ የምታልፋው ጉዳና እንደሆነ አትርሳ። እኒህ ልብን የሚያዝሉ ማንነትህ በአለት ላይ የሚገነቡህ ናቸው። በጉን ብቻኝነትን፤ ከኃላ አይሆንም የሚሉ ሰዎች ድምጿች ሲከተሉህ፤ ከፊትህ ጭላንጭል የሆነ ተስፋ ተመልክተህ የምትቀጥል ግለሰብ መሆን አለብህ። ይህንን ጫንቃቸው መሸከም የሚችሉ ህይወት የክብር ስኬት ካባ ያላብሳቸዋል።
✍ህልመኛው
🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት
✨መልካም ቀን ይሁንልን❤️❤️
join and follow our channel
👉 Share Share Share 👈
https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
✨መልካም ቀን ይሁንልን❤️❤️
join and follow our channel
👉 Share Share Share 👈
https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
የትም ፍጂው ትውልድ!
ገንዘብ ደስታን ይገዛልም አይገዛምም። ገንዘብ መምጫው መንገድ ልክ የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው የሆነበት ዘመን ላይ ነን ያለነው። በአንድ ጉራ ገንዘብ ደስታ አይገዛም የሚሉ እንዳሉ ሁሉ በሌላው ደግሞ ገንዘብ ደስታ ይገዛል የሚሉ ተበራክተዋል። ለእኔ ግን ትልቁ ጥያቄ ገንዘብ ደስታ መግዛቱ ሆነ አለመግዛቱ ሳይሆን ደስታ ብለን የምንጠራው ጉዳይ እንዳለንበት የህይወት ምዕራፍ ይላያያል። በብዛት በዚህ ዘመን ፍላጎታችን ማግኛት ነው ደስታ ብለን የምንጠራው ጉዳይ ። ነገርግን ፍላጎት ጅማሬ እንጂ ፍፃሜ የሌለው ነገር ነው። ስለዚህ አሁን ባለህበት ደረጃ ያስፈልገኛል ያልከው ፍላጎት ስታገኝ ለጊዜው ደስታኛ ትሆን እና ሌላ ከፍ ያለ ነገር ታማትራለህ። እናም እውር እውር እንደሚመረው ልክ እንዳዛ ገንዘብ በፍላጎት ከተመራ መምጣቱ ብቻ እንጁ እንዴት መጣ የሚለው ሀሳብ የማይሆንበት ትውልድ እናበዛለን።
የትም ፍጪው ትውልድ ሲበዛ ደግሞ ገንዘብ እንዴትም ብሎ ይምጣ እንጂ በምን አይነት መንገድ መጣ የሚለው ጥያቄ አያሳስበው። ሁሉም ሀብታም ሌባ እና አጭበርባሪ አይደለም፤ ሁሉም ድሃ ደግሞ ሰነፍ እና ጠንክሮ የማይሰራ አይደለም። የስኬት አንዱ መለኪያ ሊሆን ቢችል ነው እንጂ ገንዘብ ሁሉም አይደለም።
በዘር፣ በፆታ ፣ በቀለም እና ሀይማኖት የተከፈለ ትውልድ በበዛበት በዚህ ዘመን ብሂሉ ቀድሞ መገኛት ሆኖል። እኔ እንዴት በምንም አምታትቼ ላገኝ እንጂ ሌላው ሰው ላይ የሚፈጥራው ነገር አይተያኝም በዝቶል። ስለዚህ የምትገዛው ደስታ ብቻ በገንዘብ አይተን አመጣጡ ግን ከሌላው ሰው አጨበርብሮ፤ ለሀሰት ቆሞ እና ሌላም ልክ ያልሆነ መንገድ ሲመጣ የገዛሀው ደስታ እንጂ የሌላው የፈጠርከው ችግር አይታይህም። የአንተ ቤት እንዲሞላ የሌላው ቤትም ሆነ ህይወት መጉደል የለበት።
በትክክለኛው መንገድ ገንዘብ ሲመጣ ለሚያስፈልጉ ነገሮችም ትጠቀማለህ፤ በዙሪያ ላሉ ሰዎች በረከት ትሆናለህ፤ ለአቅመ ደካሞች መርደት ትችላለህ፤ በእድሜ የገፉ ሰዎች ትጦርበታለህ። ግን ይሄ ሁሉ የሚሆን የምታገኛው ገንዘብ አመጣጡ ልክ ሲሆን ነው። እንደዘመኑ አንዳንድ ሰዎች እጃቸው በደም ተዘፍቀው፤ ሀገሪቱ በዘር እና በሀይማኖት ከፋፍለው፤ ለሰዎች በመርዳት የበግ ለምዳቸው እንዲጠበቅ የሚጥሩ እንዳትሆኑ። የምትሰጠው ነገር መምጫው መንገድ ትክክለኛው ሲሆን የምትሰጠው ነገር ለምትሰጠው ሰው በረከት ይሆናል ነገርግን በተቀራኒው ከሆነ ደግሞ መርገም ነው የሚሆነው።
✍ህልመኛው
🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት
✨መልካም ቀን ይሁንልን❤️❤️
join and follow our channel
👉 Share Share Share 👈
https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
🙏አመስጋኝነት…
አመስገኝ ነኝ የጎደለ ነገር ያለኝ፤ አመስገኝ ነኝ ወቶ መግባት ትልቁ የዕለት በረከት እንደሆነ የገባኝ፤ አመስገኝ ነኝ የጤና ሀብት እና የመኖር ውድነት የገባኝ፤ አመስገኝ ነኝ የዕለት እንጀራ የተሰጠኝ፤ አመስገኝ ነኝ የጣሁት ትንሽ ነገር የለኝ ብዙ ነገር የማያደበዝዝብኝ፤ አመስገኝ ነኝ ነገ የተሻለ ነገር እንደሚሆን አምኝ የምንቀሳቀስ ሰው ነኝ፤ አመስገኝ ነኝ ባልከፈልኩት ኦክስጂ በተሰጠኝ ውድ እስትንፈስ ለአላማ ምድር ላይ እንዳቆየኝ የተገነዘብኩኝ፤ ለምን ላማር፣ ለምንስ ብዬ የነፍሴ ሰላም ባልሆኑልኝ እና መቁጣጠር በማልችለው ነገሮች ስብሰለሰል እና ስጨነቅ ልኑር፤ ለምንስ ነው መጨመር በማልችለው ጉዳይ ነገር ላይ ጊዜ የማጠፈው፤ ለምንስ በጎደኝ ሰዎች የተነሳ መኖር የለብኝ ልበል፤ መኖር የፈጣሪ ሌላ የፍቅር መግላጫ ነው እና ለማን ብዬ ምንስ ይሉኛል ብዬ ሰው ለማስዳሳት ልጨነቅ፤ አየህ የምታመሰግነው ለሰጠህ ትንሽ ነገር ነው። ትንሹ ስታከበር ትልቁ የህይወት በር ይንኮኮል።
አመስጋኝነት ፈጣሪ ያየልህ ቀጣዩ በረከት መክፈቻ ቁልፍ ነው። እናም ከአሁን በኃላ መቆጣጠር የማትችላቸው ነገሮች ለፈጣሪ ተውለት። ቀንህን ስትጀምርም ሆነ ስትጨርስም በምስገና ይሁን!!!
✍ህልመኛው
🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት
✨ሰናይ ምሽት ይሁንልን❤️❤️
join and follow our channel
👉 Share Share Share 👈
https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
ለመላው የሙስሊም እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1446 ኛው ለዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ ይሁንልን።
🕋ኢድ ሙባረክ
🙏 ቴክቶክ አካውንታችን ፎሎ ያድርጉ፡ https://vm.tiktok.com/ZM6a5oBDe/
join and follow our channel
https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
ለትዝብት ያህል
የጲላጦስ ዘመን ትውልድ በርባን በኢየሱስ ለመቀየር የማያመነታ እንደሆነ ስታውቅ ትፈራለህ። ከፈሪሳውያን ይልቅ ያ ለሆሳዕና ዘንባባ የወጣው የኢያሩሳሌም ህዝብ ክፉ መሆኑ ታውቃለህ። ልቡ የሚወላውል፤ ሆይ ሲባል ሆይ የሚል ስለሆነ ነው። የበሉበት ወጪት ሰባሪ ፤ የጎረሳቸውን ነካሽ ናቸው።
በዲያር 30 እንደመሸጥ፤ በወዳጅ እንደመተው ባዶ እንደመሆን ከባድ ያለ ስሜት ያለ አይመስለኝም። ይሄ በጲላጦስ ዘመን ያለ እውነታ አሁንም ያለ ነው።
አንዳንዴ እውነት ከአብዛኛው ጋር አለመሆኑ ሲገባ ለምን ብለህ መጠየቅ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑ ይገባሃል። የዚህ ዘመን ባለእውነተኞች ዘመን ቢቀየርም ሰው ግን ያው ነው።
ይህም የምለው ለዚህ ዘመን ባለ እውነት ኖሪዎች ወዳጅም፣ ከእጃችሁም የበለው ለመክዳት እና በእናታ ላይ ለመቀየር ሰከንድ አይፈጅባቸው። የተሻለ ከመጣ ለመተው ዝግጁ ናቸው። የተሻለ ማለት ለአፈ ቀለጤ ማለቴ ነው። ክብር ስትለው ትቢያ ለሚለው ገለለ በልለት፤ ከተገባቸው በርባን ጋር ይኑሩ። ዋጋ ለማሳውቅ ብለህ እንዳትደክም፤ ያልተመቸው መሄድ እንደሚችል አሳውቃቸው። ክብር ለእነዚያ ባለእውነቶች
የዚህ ዘመን የበርባኖች ነፃነት በንፆዎች ላይ በደረሰ በደል ነው።
✍ህልመኛው
🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት
✨መልካም ቀን ይሁንልን❤️❤️
join and follow our channel
👉 Share Share Share 👈
https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
ለእኔ ትልቁ ወዳጅም ሆነ ጠላቴ እራሴ ነኝ!
ትልቁ ጠላቴ ሆነ ወዳጄ ውስጤ ነው ያለው። ከውጪ ያለው ወዳጅም ይሁን ጠላት አጋዥ እንጂ ዋነኛ አይደለም። ለዚህም ነው ብዙ ሰዎች የሚዘነጉት ጉዳይ የሆነው? ስለዚህ ውጪ የውስጥ ክፍተት የምታይበት ነው።
ይህን እዉነት እንደኮሶ የወሰዱት የህይወት አስቀየሚ ገፆች ማለፍ የሚችሉበት አቅም ያገኛሉ። ጠንካራ መሆን ምርጫ ሳይሆን ግዴታ መሆኑ ያውቃሉ። ብቻኝነት እንደ መጥፎ እድል ሳይሆን እንደ ጥሩ አጋጣሚ ነው የሚያዩት። ቢወደዱ ሆነ ቢጠሉ፤ ቢከበሩ ሆነ ቢዋረዱ፤ ቢመቻቸው ሆነ ባይመቻቸው፤ ወደፊት ከመቀጠል ውጪ አማራጭ እንደሌለ ያውቃሉ። ህይወታቸው በትልቁ የመወሰን አቅም ያለው እራሳቸው እንደሆነ ስለሚያውቁ ተገቢው ትጋት ስለሚያደርጉ በመጨረሻም ህይወት ስኬት ስትሸልመቸው ይታያሉ።
✍ህልመኛው
🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት
✨መልካም በዓል ይሁንልን❤️❤️
join and follow our channel
👉 Share Share Share 👈
https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
# ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳዔ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የፍቅር፣ የመተሳሰብ፣ የመቻቻል፣ አንተ ትብስ የምንባባልበት፣ ለሌለው የምናካፍልበት፣ የተጣላ የሚጣረቅበት... ይሁንልን። በተለይ ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጲያን ሰላም ያድርግልን።
መልካም የትንሳዔ በዓል ይሁንላችሁ ❤️❤️❤️
join and follow our channel
https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
☪ ለመላው የሙስሊም እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447 ኛው ለኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ ይሁንልን።
🌙ኢድ ሙባረክ
🙏 ቴክቶክ አካውንታችን ፎሎ ያድርጉ፡ https://vm.tiktok.com/ZM6a5oBDe/
join and follow our channel
https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
መለየት በረከት ነው!!
መለየት ሞት ብቻ ሳይሆን የለውጥ አንዱ ሂደት ነው። ቀድሞ የነበረህ አንዳንድ ህብረቶች ህይወት ወደምትፈልገው ለውጥ ውስጥ የማያስገቡህ ከሆነ እየተወዳዱ ቢሆን መለየት ነው። ከምታውቀው ከለመድከው እና ከገደበህ ምቾት ይልቅ ድካም፣ ልፋት እና ለማወቅ ጥረት የሚፈልግህ ቦታ ላይ መገኛትን የመሰለ ነገር የለም።
ባለህበት መርገጥን፤ አርቆ አለማየትን፤ በቆየ እና በጃጀ አመለካከት ወደፊት ከመጎዝ ይልቅ ትላንት እንደትርክት ብቻ መውራት ከሚመርጥ ህብረት እራስህ መለየት በረከት ነው። ህይወት የምትመከትበትን መነፅር፤ አለምን የምትረዳበት መንገድ ከሚገድብ፣ ከምሬት እና ከሰበበኝነት ካባ ከማያወጣው ህብረት መለየት ምነኛ በረከት ነው። አስተዋዮች የሚውሉበት ህብረት ነገሮች የሚያጤኑበት መነፅር የሚሰራው እንደሆነ ስለሚያውቁ መለየት ካለባቸው ነገሮች ለመለየት ምን ይሉኛል የማያጠቃቸው ናቸው።
✍ህልመኛው
🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት
✨ሰናይ ሰንበት ይሁንልን❤️❤️
join and follow our channel
👉 Share Share Share 👈
https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
🧩 ቅምሻ ሀሳቦች
ነፃ ምሳ ምድር ላይ የለም። ነገርግን ነፃ የሆነ ምሳ ካገኛህ ዋጋው አንተ ስለሆንክ ነው ምግቡ ነፃ የሆነው፤ ቢገባህ ይሄ የብዙህ ነገሮች እስር ቤት ነው።
✍ህልመኛው
🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት
✨ሰናይ ቀን ይሁንልን❤️❤️
join and follow our channel
👉 Share Share Share 👈
https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
እንኳን ለ130 ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ። አባቶቻችን በአንድነት ንደው እንደጣሉት የእነሱ ዘመን ፋሽስት እኛ ደግሞ የዚህ ዘመን ፋሽስት የሆነብን ዘረኝነት እና ጥላቻ በፍቅር የምናሸንፍበት የልባችን አድዋ ይሁንልን።
ፈጣሪ ሀገራችን ከክፉ ይጠብቅልን!
🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት
join and follow our channel
👉 Share Share Share 👈
https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
🧠አእምሮ ማበልፀግ
አስቸጋሪ ጊዜ የልብ ጓደኛ ማን እንደሆነ ብቻ ሳይሆን ምን አይነት ሰው እንደሆንክ ታውቅበታለህ። ለራስህ የሰጠሀው ከፍተኛ ይሁን ዝቅተኛ እሳቤ ይፈተናል። ገላባው ከፍሬው ይለያል፤ መቀጠል የማይገባው ሽንፍላ ይወገዳል። ከሰዎች እኩል ከአንተ መቀረፍ ያለበት ነገር ይቀርፋል። ይሄ ነው የህይወት መንገዷ።
✍ህልመኛው
🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት
✨ሰናይ ምሽት ይሁንልን❤️❤️
join and follow our channel
👉 Share Share Share 👈
https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
ፍርሃትህን ተጋፈጠው!!!
የወደከው በፍርሃት የተነሳ ነው እንጂ አቅም አንሶ ወይም ስለማትችል አይደለም። ፍርሃት አቅምህ አሽመድምዶ እራስህ አሳንሰህ እንድታይ ያደርግሀል። ነገርግን እውነታው ያ አይደለም። ፍርሃት እንዳይሰማ የማይቻል ቢሆንም ፍርሃትህ የህይወት መሪ አለማድረግ እና አለማደመጥ የአንተ ድርሻ ነው። ፍርሃቱ እየለብህ ማድረግ የለብህ ነገር መፈፀም አለብህ። ልጅ እያለ ትምህርት ቤት የምናውቀውነ ነገር ፊት ላይ ወታህ ለሌሎች አቅርብ ስንባል የሚይዘን ፍርሃት እና ብርክ ብርክ ይለን ነበር። ከዚህም አልፎ የምናውቀው ነገር ሁሉ ይጠፋብን ነበር። ፈርተን ስናወራ እና ሲስቁብን የበሰ ከዚህ በኃላ ፊት ወጥቼ አናወራም እንል ነበር። እናም አሁን በህይወታችን ብዙ ነገሮች መሞከር አቆምን ምክንያቱም በልጅነታችን እንደተሳቀብን አሁን ብንወድቅ ወይም ብንሳሳት ይስቁብኛው ብለን ስለምናስብ።
ፍርሃትህን አሸንፈው። ምክንያቱም ብዙ ህልሞች የሞቱት በፍርሃት መሆኑን እወቅ። ሩቅ የሚያስጎዝ አቅም አሳስሮ የሚያስቀምጥህ ፍርሃት የተበለ ነቀዝ ነው። ምን ይሉኝ ይሆን ብለህ አትስብ? የሚሉት ይላሉ ግን መኖር አለብኝ ብለህ የምታስበው ኑር። ደፋር ሁን፤ ፍርሃት እንኳን ዙሪያህ ቢከብህም። አንተ የሚወቅስህ እና አትችልም የሚልህ አብዛኛው ጊዜ ምንም ነገር ሞክሮ የማያወቅ የመቀመጥ ንጉስ፣ የጥላቻ አለቃ የሆነ ሰው ነው። ተዋቸው የሉትን ይበሉ። ዛሬ እኳ ነው ዳዴ የምትለው ከሆነ ጊዜ በኃላ ምን ያህል እርቀት ከእነሱ እንደሚኖርህ አስብ።
በህልምህ አትቀልድ፤ በህልምህ አታሹፍ፤ መከፈል የለበት ዋጋ ከፍለህ መድረስ የለብህ ነገር ጋር ድረስ። ፍርሃት ተጋፈጠው፤ እንደምትችል እመን። አሁን ጀመሪ ነህ። ማንንም አልሰማህ ሲልህ አይዞህ ሁሉም ከመውደቅ ነው መራመድ ቀላል የሆለት። ምን ይሉኛ የሚለው ፍርሃት ከብዙ ነገር ወደኃላ እንዳስቀረህ ስታስብ ልትቆጭ ይገባል። ዋናው ፈጣሪ የሚከብርበት ሰው የማይጎዳ ነገር ከሆነ ለምን ብለህ ነው የምትሳቀቀው። ሰው ፊት ወተህ ማቅረብ ስትጀምር ስትንቀጠቀጥ፣ የሌለብህ መንተባታብ ስንተተባተብ፤ አይገርም ነገሩ ሳታውቀው ቀርታህ አይደለም። ነገር ግን ፍርሃት ስላለሸንፈከው ነው። አየህ ትክክል ነው ወይ ያልኩት ብለህ ስትጨነቀ የባሰ ምንም እንደማያውቀው ሰው ትሆናለህ። እና ፍርሃት ያስመለጠ ብዙ ዕድሎች እንዳሉ አይሰማህም። ስለዚህ ፍርሃት ህልምህ ከመግደሉ በፊት አንተ ተጋፈጠው።
✍ህልመኛው
🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት
✨ሰናይ ምሽት ይሁንልን❤️❤️
join and follow our channel
👉 Share Share Share 👈
https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
ብርታትህን ይፈተናል!
በህይወት መኖር አጎጊ ከሚያደርጉ ነገሮች መካካል ብርታትህን የሚፈትኑ ጉዳዮች ናቸው ብዬ አምናለሁ። በህይወት ቁርጠኛ እና የአላማ ሰው ነኝ ስትል፤ መሆንህን እንድታሳይ የሚመጡብህ ፈተናዎች ይኖራሉ። ታላቅነት ሊያወጡ የቀረቡልህ የህይወት ፈተናዎች እንደ መሰናክል ካየህ በነበርክበት ቦታ ትቀጥላለህ። ነገርግን ምርጫ መገፈጥ ከሆነ አንተ የማታውቀው ጠንካራ ማንነት ታገኛዋለህ።
ህይወትህ በመልካም ከሚቃኙ ነገሮች መካከል በጥበብ ተግዳሮቶች ማለፍ አንዱ ነው። የማይገል ችግር ጠንካራ ያደርጋል እንደሚባለው ልክ እንደዚያ በህልምህ ጉዞ መሃል የሚያገጥሙህ ነገሮች የሚሰብሩህ ሳይሆን የሚሰሩህ፤ የሚያስቀሩህ ሳይሆን የሚያሻግሩህ፤ የሚያዋርዱህ ሳይሆን የሚያከብሩህ መሆናቸው ተረዳ። ሁሌም ከትልልቅ ድል በፊት ትልልቅ ተግዳሮቶች እና የማይተለፉ የሚመስሉ ነገሮቸ አሉ።ከባድ ችግሮች እና ፈተናዎች ተገፍጠህ ካለፍክ በኃላ የሚጠብክ የድል ዋንጫ እንደላ እወቅ። እነዚህ ነገሮች በድል እና በአሸነፊነት ማለፍ ብርታትህን እና አቅምህን ይጨምረዋል። ከአሸነፊትህ እና ድል አድራጊት የሚወጣ ለሌሎች የሚሆን ትምህርት እና ጥበብ ይኖራል። ንግግር ብቻ ሳይሆን ህይወትህም የሰዎች ህይወት መቀየር ይጀምራል።
✍ህልመኛው
🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት
✨ሰናይ ምሽት ይሁንልን❤️❤️
join and follow our channel
👉 Share Share Share 👈
https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
📌 የጭንቀቴ ምክንያት
በህይወት በየደረስክበት ደረጃ የተሰጡህ ነገሮች እንዳሉ ሁሉ ያልተሰጠህ ነገር አለ። ብዘ ጊዜ የጉደለህ ነገር ካለቸው ጋር ብቻ የምታወዳድረው ከሆነ ህይወትህ እርባነ ቢስ ያደርገዋል። ይሄ ደግሞ አቅም አሽመድምዶ ጤናህንም ያቃውሰዋል። አሁን የሌለህ በዛሬ በተሰጠህ ነገር ትጋት ስታደርግ ስለምትደርስበት ብዙ መጨነቅ ለውጥ አያመጣም። የተሰጠህ ከማንኮሰስ እና ካለመጠቀም ውጪ ምንም የምትፈጥረው አዲስ ነገር የለም። ህይወት የከለከለህ አንተ ደግሞ እንደህፃን ልጅ ካልሆነ ብለህ የምታለቃቅስበት ጉዳይ ወድቆ መፈራገጥ ለመላላጥ እንደሚለው ነው የሚሆንብህ። ያለህን ነገር ሲደመር ጥረትህ እና የፈጣሪ በረከት የምትመኛው እንድታገኝ ያደርግሃል።
✍ህልመኛው
🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት
✨ሰናይ ምሽት ይሁንልን❤️❤️
join and follow our channel
👉 Share Share Share 👈
https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
ፀሀይ ስትወጣ
በፍጥነት ከፈትኩኝ፣ በርና መስኮቴን
ጨለማውን ሄደ ፥ ብርሐን ሞላ ቤትን።
…
ቤት ብርሃን ሲሆን
ያስገባሁት ፀሀይ ፥ እንዳይወጣ ሠጋሁ
መስኮትና በሬን ፈጠን ብዬ ዘጋሁ
…
በርና መስኮቴን
ፈጥኜ ስዘጋ ቤቴን ፅልመት ዋጣት
ጨለማው በየት ፥ ገባ ፀሀዪ በየት ወጣ?
✍ከsocial media መንደር
🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት
✨ሰናይ ምሽት ይሁንልን❤️❤️
join and follow our channel
👉 Share Share Share 👈
https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
⛳️በትዕግስት የተሰነቀ ፤ በድርጊት የተሰተረ፤ በፅናት የተገመደ እና በእርጋታ የተቃኛ ግብ የሚያስጎመጅ ውጤት ያስገኛል።
✍ ህልመኛው
🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት
✨ሰናይ ምሽት ይሁንልን❤️❤️
join and follow our channel
👉 Share Share Share 👈
https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
⏱ጊዜ መግዛት ወይስ እራስን መግዛት
ጊዜ በያትኛውንም መልኩ መግዛት አይቻልም። ይህ ስል ተጨማሪ ጊዜ መግዛት አንችልም ለማለት ነው። ጊዜ የሚገዛው እራስን በመግራት ነው። ጊዜ የሚገዛ ነገር ስላልሆነ በተሰጠ ጊዜ የምንስራው ስራ ነው ጊዚያችን በአግባቡ ተጠቅመናል ወይም አባክነናል የሚያስብለን። ስለዚህ ከጊዜው ጋር ሳይሆን ጉዳዩ እራሳችን ከመግዛት ከመቆጣጠር ጋር ነው።
"ጊዜና አየር ተዝቀው የማያልቁ ሀብት ቢሆኑም፣ አየርና ጊዜ ያላቀበት ህይወት ሞት ደጁን ያንኳኳል።"
"ጊዜና አየር ነፃ መሆናቸው ርካሽ ስለሆኑ ሳይሆን ለህይወት ከሁሉም ውድ የሆኑ ቅመሞች በመሆናቸው ነው።"
✍️ዶ/ር ምህረት ደበበ
🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት
✨ሰናይ ሰንበት ይሁንልን❤️❤️
join and follow our channel
👉 Share Share Share 👈
https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ።
#ከተራ
join and follow our channel
👉 Share Share Share 👈
https://t.me/+TCPWUsY-p8t5rBTt
