cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

የስኬት መንገድ አሐዱ ሬድዮ 94.3

በስኬት መንገድ ላይ እያንዳንዷ እርምጃችን ወደ ግባችን ታቀርበናለች!!

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 760
مشترکین
-224 ساعت
-97 روز
-1730 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

አስተማሪ አጭር ታሪክ .! አንድ ቤተሰብ ውስጥ አባት ከሞተ በኋላ የሚመገቡት እስኪያሳስባቸው ድረስ ይቸገራሉ ። አንድ ጌጣጌጥ መሸጫ ሱቅ ያለው ዘመድ አላቸው እና እናትየው ለልጇ ያላትን ለረጅም ጊዜ የተቀመጠ የአንገት እና የጣት ዳይመንድ ጌጥ ሰጥታው እዛ ሱቅ ሄዶ እንዲሸጠው ትሰጠዋለች፡፡ ልጁ የተባለው የዘመድ ጌጣ ጌጥ ሱቅ ሄዶ እናቱ እንደላከችው አስረድቶ እንዲገዛው ይጠይቃል፡፡ ሰውየውም ከመረመረው በኋላ "አሁን ገበያው ወድቋል ትንሽ ግዜ ጠብቀን በጥሩ ዋጋ እንሸጠዋለን፡፡" ብሎ ይመልስለትና የተወሰነ ገንዘብ ከሰጠው በኋላ ለልጁም እስከዛው በየጊዜው እየመጣ እዛው ሱቅ ስራ እንዲሰራ ያደርጋል ። ልጁ በየግዜው እየሄደ የጌጣጌጥአሰራር ጥበብ ተካነ ፡፡ የገበያም እውቀት አካበተ በስራውም ታዋቂም ለመሆን ቻለ ፡፡ ይሄኔ ባለሱቁ "የሆነ ግዜ ልትሸጠው አምጠተኸው የነበረውን ጌጥ አሁን አምጣው አሁን ገበያው ጣራ ነክቷል እና ታተርፋላችሁ ፡፡ ብሎ ይልከዋል ፡፡ ልጁ እንደተባለው እቤት ሄዶ ጌጣጌጡን በአይኑ በማየት ብቻ አርቴፊሻል ሆኖ ያገኘዋል፡፡ ወደ ሱቅ ይመለሳል ፡፡ባለቤቱ ይጠይቃል "ዳይመንዱስ ?" ልጁም "አርቴፊሻል ነው ግን እያወክ ያን ጊዜ ለምን አልገርከኝም ?አሁንስ ለምን ላከኝ?ሲል ጠየቀው፡፡ ዘመዱም "ያን ጊዜ ለረጅም ዘመን ዳይመንድ ነው ብላችሁ ያመናችሁትን ነበር ይዘህ የመጣኸው ፡፡ያለምንም እውቀት፤ ባዶህን እና በሙሉ እምነት ብቻ ! በሰዓቱ ባለህበት ሁኔታ ልክ ያልሆነ ነገር ለማስረዳት ይከብዳል፡፡ ምናልባት ላታምኑኝ ትችሉ ነበር ፡፡ምናልባትም ባለመግባባት የሚፈጠሩ የቃላት ልውውጥ አሁን ላይ መጥፎ ስሜት ሊያሳድርብን በቻለ ነበር ።" ብሎ በትህትና መለሰለት፡፡ እንዲህ ያለ የላቀ ስብዕና ባለቤትና ነገሮችን በብዙ አቅጣጫ የምናይበት ህሊና ይስጠን፡፡
نمایش همه...
የማንነትህ መለኪያ ስኬት አይደለም “በቅርጫ ኳስ ጨዋታ ዘመኔ 9 ሺህ ኳሶችን ሞክሬ ስቼአለሁ፡፡ 300 ውድድሮችን ተሸንፌአለሁ፡፡ ባስቆጥረው ቡድኔን ለዋንጫ የሚያበቃውን ኳስ እንድወረውር አምነው ሰጥተውኝ ስቼ አውቃለሁ፡፡ በሕይወቴ ደግሜና ደጋግሜ ወድቄአለሁ፡፡ ለዚህ ነው ስኬታማ የሆንኩት” - Michael Jordan አብዛኛው ሰው ውስጡን የሚነዳው አንድ ጥማት አለው፡፡ ይህ ጥማት የተመሰከረለትና ጥንቅቅ ያለ ስኬታማ ሆኖ ለመታየት ያለው ጥማት ነው፡፡ “እንደዚህ ባደርግ፣ ይህኛውና ያኛው ነገር ቢኖረኝ፣ እዚያኛው ደረጃ ብደርስ ኖሮ … እረካና ሙሉ ስኬት ውስጥ እገባ ነበር” የሚል የውስጥ ጩኸት በብዙ ሰዎች ውስጥ ሲያስተጋባ ይሰማል፡፡ ስለዚህም፣ አንዳንድ ሰዎች ይህንን ጥማት ለማርካት ምንም ነገር ከማድረግና የትኛውንም ድንጋይ ከመፈንቀል አይመለሱም፡፡ የዚህ አመለካት ምንጩ፣ “ሙሉ ማንነት እንዲኖረኝ በኑሮዬ ስኬታማ መሆን አለብኝ” የሚለው አመለካከት ነው፡፡ የዚህ አመለካከትና የሕይወት ዘይቤ ውጤቱ ደግሞ “ስውር” ፍርሃት ነው፡፡ ሙሉ ማንነት እንዲኖረው ስኬታማ መሆን እንዳለበት ያመነ ሰው አለመሳካትን፣ ስህተትንና መውደቅን እጅግ የሚፈራ ሰው ነው፡፡ የሚሰራው ማንኛውም ስራ ስኬታማ የመሆኑና ያለመሆኑ ጉዳይ ከማንነቱ ዋጋ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ባለማወቁ ምክንያት ለብዙ ስነ-ልቦናዊ ጥቃት ራሱን ያጋልጣል፡፡ የአንድ ሰው ማንነት የሚለካው በተሳካለትና ባልተሳካለት ነገር ከሆነ፣ ለዚያ ሰው ሩጫ ማቆሚያ፣ ለውድድሩም መጨረሻ የለውም፡፡ ይህ አይነቱ የሕይወት ዘይቤና አመለካከት የሚያስከትለው ዋነኛ መዘዝ የመውደቅ ወይም ስኬት የማጣት ፍርሃት ነው፡፡ ከዚህ የተዛባ የማንነት መመዘኛ ቀውስ ለመውጣት በስኬት ላይ ያለንን አመለካከት መቃኘት አስፈላጊ ነው፡፡ 1. ስኬት ዘርፈ-ብዙ ነው ለምሳሌ፣ አንድ ሰው በስራው ወይም በንግዱ አለም የተዋጣለት ሆኖና ያሰበው ደረጃ ደርሶ፣ በማሕበራዊውም ሆነ በቤተሰባዊው ኑሮው የተበላሸ ሁኔታ ውስጥ ራሱን ሊያገኘው ይችላል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ፣ አካላዊም ሆነ ስሜታዊ ጤንነቱን ችላ ብሎ እውቀትን ወይም ንብረት ሲሰበስብ የሚኖር ሰው በቀኑ መጨረሻ “ስኬታማ ነኝ” ብሎ እንዲናገር የሚያደርገው ነገር ምንድን ነው? ስለዚህም፣ ስኬት የብዙ መሰረታዊና አስፈላጊ እውነታዎች ጥርቅም ነች እንጂ አንድ ገጽታ ብቻ የላትም፡፡   2. ስኬት የሂደት ጉዳይ ነው ስኬት የአንድ ጊዜ ክስተት ሳይሆን የሂደት ጉዳይ ነው፡፡ ስኬት፣ “አንድ ደረጃ ካልደረስኩ አልረጋጋም” ማለት ሳይሆን ጉዞውን በመጀመራችንና በሂደት ላይ በመሆናችን መርካትና መረጋጋት ማለት ነው፡፡ ዘርፈ-ብዙ የሆነው የስኬት ምስጢር ዘርፈ-ብዙ የሆነ ጥረትና ትጋት ይጠይቃል፡፡  ስኬታማ ሰው በሁሉም አቅጣጫ በአንድ ጊዜ ጥሩ ደረጃ ላይ የደረሰ ሰው ነው ብሎ ማሰብ ከእውነት እንድንርቅ ያደርገናል፡፡ 3. ስኬት ተለዋዋጭ ነው ትናንት ቀለል ያለው ሁኔታ ዛሬ ከበድ ሲል፣ ዛሬ የጨመረው ሁኔታ ነገ ሊቀንስ፣ ዛሬ የተነሳሳውና የጋለው ፍላጎት ነገ ቀዝቀዝ ሊል ይችላል፡፡ እንደ ሁኔታውና እንደ እለቱ ስሜት ጥረቱን የሚቀያይር ሰው እንደዚያው አይነት ውጤትን ያተርፋል፡፡ እንደ እለቱ ሁኔታና ስሜት ሳይሆን ከዓላማው አንጻር የሚሰራ ሰው ደግሞ ከዚያው አንጻር ስኬታማ ይሆናል፡፡ ይህ በፍጹም የማይለወጥ  ሕግ ነው፡፡
نمایش همه...
"የጉንዳኖች ፍልስፍና" ጉንዳኖች ሲጓዙ መንገድ ብትዘጋባቸው ከጉዟቸው አይገቱም፤ሌላ መንገድ ፈልገው ጉዟቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ከተስፋ መቁረጥ ጋር ፈጽሞ አይተዋወቁም፡፡ ጉንዳኖች ለመጪው ጊዜ ይዘጋጃሉ፡፡ በበጋ ወቅት ለክረምት ጊዜ የሚሆናቸውን ቀለብ ያከማቻሉ፡፡ በዝናብ ወቅት ወደ ውጭ ሳይወጡ ክረምቱን ለማሳለፍ  የቻሉትን ያህል ዝግጅት ያደርጋሉ፡፡ በክረምት ወቅት ነገ በጋ እንደሚመጣ ወይም ብራ እንደሚሆን እርግጠኞች ናቸው፡፡ ክረምቱ ለረዥም ጊዜ እንደማይዘልቅ ያውቃሉ፡፡ በጋውን በብሩህ ተስፋ ይጠብቃሉ፡፡ ጸሃይዋ ብጭ ስትልም ተግተልትለው ይወጣሉ፡፡ ጉንዳኖች ከአካላቸው ክብደት 20 እጥፍ የሚልቅ ነገር መሸከም ይችላሉ፡፡ ፈጣንም ናቸው፡፡ ሁልጊዜ በሥራ ተጠምደው ነው የሚታዩት፤ ምንጊዜም በእንቅስቃሴ ላይ ናቸው፡፡ መሰራት ያለበትን ሁሉ በትጋት ይሰራሉ፡፡ ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነጋቸውም ያስባሉ - መኖሪያቸውን ይገነባሉ፤ቀለባቸውን ይሰንቃሉ፡፡ የሰው ልጅ ታዲያ ከጉንዳኖች ህይወት ምን ይማራል? በአሜሪካ የሞቲቬሽናል አባት የሚባለው ጂም ሮን፣ ከጉንዳኖች ለህይወት ስኬት የሚጠቅሙ አራት መመሪያዎችን መቅሰም እንችላለን፤ ይላል፡፡ "የጉንዳኖች ፍልስፍና" ሲልም ሰይሞታል፡፡ አራቱ የስኬት መመሪያዎች የሚከተሉት ናቸው፡- •  ምንጊዜም ተስፋ አትቁረጡ •  ሁልጊዜም ለነገ ወይም ለወደፊቱ አስቡ •  አዎንታዊ ብሩህ ተስፋ ይኑራችሁ •  የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ
نمایش همه...
የራእይ ጉልበት! ታዋቂው ጸሐፊ ስቲቨን (Stephen Covey)  First Things First በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ ስለአንድ ቪክቶር (Viktor Frankl) ስለሚባል የአውስትራያዊ የስነ-ልቦና ባለሞያ ታሪክ ይናገራል፡፡ ይህ የስነ-ልቦና ባለሞያ ከናዚ (ጀርመን) የሞት ካምፕ የተረፈ ሰው ነው፡፡ ቪክቶር በናዚ የሞት ካምፕ ውስጥ ታሽገው ከነበሩ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ በሞት ሲያልፉ አንዳንዶቹ ግን እንዴት ያንን ለሞት የሚዳርግ ሁኔታ አሸንፈው ሊወጡ እንደቻሉ በምርምር ደረሰበት፡፡ በጥናቱ ብዙ ነገሮችን ተመልክቷል - የጤንነታቸው ሁኔታ፣ የቤተሰባቸው ሁኔታ፣ ብልህነታቸው፣ ችግርን የመቋቋም ብቃት እና የመሳሰሉት፡፡ በመጨረሻ የደመደመው፣ ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዱም እንኳን ለእነዚህ ሰዎች በሕይወት መኖር ምክንያት እንደልሆነ ነበር፡፡ በዚያ ከባድ ሁኔታ ውስጥ በሕይወት የቆዩት ሰዎች አንድ የጋራ ነገር ነበራቸው፡፡ ይህ ነገር የወደፊት ራእይ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች በሕይወት የመኖርን ነገር ጠንክረው እንዲይዙ ያደረጋቸው ብቸኛውና ጉልህ የሆነው ምክንያት በፊታቸው ገና ያላከናወኑት ራእይ እንዳላቸው የማመናቸው ሁኔታ ነበር፡፡ ጸሐፊው እንደ ቬትናም እና የመሳሰሉት ብዙ የጦር ምርኮኞች በስቃይ በሚታጎሩባቸው ካምፖችም ውስጥም ተመሳሳይ ሁኔታ እንደታየ ይናራል፡፡ አሳማኝ እና ወደፊት ላይ ያተኮረ ራዕይ ብዙዎቹን በህይወት እንዲኖሩ ያደረጋቸው ዋና ሃይል ነበር (ምንጭ፡- Stephen Covey, First Things First, p 103)፡፡ •  አንድ ሰው የሚሞተው ጤናው ሲጠፋ ብቻ አይደለም … ራእይ ሲጠፋም ጭምር ነው! •  አንድ ሰው የሚከስረው ስራ ሲበላሽ ብቻ አይደለም … የራእዩ ሁኔታ ሲበላሽም ጭምር ነው! •  አንድ ሰው ብቸኝነት የሚሰማው ሰው ሲርቀው ብቻ አይደለም … ራእይ ሲርቀውም ጭምር ነው! •  አንድ ሰው ተስፋ የሚቆርጠው ሁኔታዎች አልታይ ሲሉት ብቻ አይደለም … ራእይ አልታይ ሲለውም ጭምር ነው! •  አንድ ሰው ውዳቂ የሚሆነው ስለወደቀ ብቻ አይደለም … ራእዩን ሲጥል ጭምር ነው! . . . እያለ እውነታው ይቀጥላል፡፡ ይህ እውነታ እንደሚያሳየን አንድ ሰው ምንም እንኳን በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ሲያልፍ የዚያን ሁኔታ ውጤት መቅመሱ ባይቀርም፣ የመጨረሻውን ውሳኔ ከሚያስተላልፉትና በብርታትና በደካማነት መካከል ከሚወስኑት ሁኔታዎች መካከል አንጋፋው ራእይ የመኖሩና ያለመኖሩ ጉዳይ ነው፡፡ አሁን ከምታልፉበት አስቸጋሪና ተስ አስቆራጭ ነገር ባሻገር እንድትሄዱ ሊያደርጋችሁ የሚችል ዋነኛው የፈጣሪ ስጦታ ራእይ ይባላል፡፡  ራእያችሁን አግኙና እሱን በመኖር አሁን ያለውን ከባድ ዘመን አሳልፉት!
نمایش همه...
የማንነትህ መለኪያ ስኬት አይደለም “በቅርጫ ኳስ ጨዋታ ዘመኔ 9 ሺህ ኳሶችን ሞክሬ ስቼአለሁ፡፡ 300 ውድድሮችን ተሸንፌአለሁ፡፡ ባስቆጥረው ቡድኔን ለዋንጫ የሚያበቃውን ኳስ እንድወረውር አምነው ሰጥተውኝ ስቼ አውቃለሁ፡፡ በሕይወቴ ደግሜና ደጋግሜ ወድቄአለሁ፡፡ ለዚህ ነው ስኬታማ የሆንኩት” - Michael Jordan አብዛኛው ሰው ውስጡን የሚነዳው አንድ ጥማት አለው፡፡ ይህ ጥማት የተመሰከረለትና ጥንቅቅ ያለ ስኬታማ ሆኖ ለመታየት ያለው ጥማት ነው፡፡ “እንደዚህ ባደርግ፣ ይህኛውና ያኛው ነገር ቢኖረኝ፣ እዚያኛው ደረጃ ብደርስ ኖሮ … እረካና ሙሉ ስኬት ውስጥ እገባ ነበር” የሚል የውስጥ ጩኸት በብዙ ሰዎች ውስጥ ሲያስተጋባ ይሰማል፡፡ ስለዚህም፣ አንዳንድ ሰዎች ይህንን ጥማት ለማርካት ምንም ነገር ከማድረግና የትኛውንም ድንጋይ ከመፈንቀል አይመለሱም፡፡ የዚህ አመለካት ምንጩ፣ “ሙሉ ማንነት እንዲኖረኝ በኑሮዬ ስኬታማ መሆን አለብኝ” የሚለው አመለካከት ነው፡፡ የዚህ አመለካከትና የሕይወት ዘይቤ ውጤቱ ደግሞ “ስውር” ፍርሃት ነው፡፡ ሙሉ ማንነት እንዲኖረው ስኬታማ መሆን እንዳለበት ያመነ ሰው አለመሳካትን፣ ስህተትንና መውደቅን እጅግ የሚፈራ ሰው ነው፡፡ የሚሰራው ማንኛውም ስራ ስኬታማ የመሆኑና ያለመሆኑ ጉዳይ ከማንነቱ ዋጋ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ባለማወቁ ምክንያት ለብዙ ስነ-ልቦናዊ ጥቃት ራሱን ያጋልጣል፡፡ የአንድ ሰው ማንነት የሚለካው በተሳካለትና ባልተሳካለት ነገር ከሆነ፣ ለዚያ ሰው ሩጫ ማቆሚያ፣ ለውድድሩም መጨረሻ የለውም፡፡ ይህ አይነቱ የሕይወት ዘይቤና አመለካከት የሚያስከትለው ዋነኛ መዘዝ የመውደቅ ወይም ስኬት የማጣት ፍርሃት ነው፡፡ ከዚህ የተዛባ የማንነት መመዘኛ ቀውስ ለመውጣት በስኬት ላይ ያለንን አመለካከት መቃኘት አስፈላጊ ነው፡፡ 1. ስኬት ዘርፈ-ብዙ ነው ለምሳሌ፣ አንድ ሰው በስራው ወይም በንግዱ አለም የተዋጣለት ሆኖና ያሰበው ደረጃ ደርሶ፣ በማሕበራዊውም ሆነ በቤተሰባዊው ኑሮው የተበላሸ ሁኔታ ውስጥ ራሱን ሊያገኘው ይችላል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ፣ አካላዊም ሆነ ስሜታዊ ጤንነቱን ችላ ብሎ እውቀትን ወይም ንብረት ሲሰበስብ የሚኖር ሰው በቀኑ መጨረሻ “ስኬታማ ነኝ” ብሎ እንዲናገር የሚያደርገው ነገር ምንድን ነው? ስለዚህም፣ ስኬት የብዙ መሰረታዊና አስፈላጊ እውነታዎች ጥርቅም ነች እንጂ አንድ ገጽታ ብቻ የላትም፡፡   2. ስኬት የሂደት ጉዳይ ነው ስኬት የአንድ ጊዜ ክስተት ሳይሆን የሂደት ጉዳይ ነው፡፡ ስኬት፣ “አንድ ደረጃ ካልደረስኩ አልረጋጋም” ማለት ሳይሆን ጉዞውን በመጀመራችንና በሂደት ላይ በመሆናችን መርካትና መረጋጋት ማለት ነው፡፡ ዘርፈ-ብዙ የሆነው የስኬት ምስጢር ዘርፈ-ብዙ የሆነ ጥረትና ትጋት ይጠይቃል፡፡  ስኬታማ ሰው በሁሉም አቅጣጫ በአንድ ጊዜ ጥሩ ደረጃ ላይ የደረሰ ሰው ነው ብሎ ማሰብ ከእውነት እንድንርቅ ያደርገናል፡፡ 3. ስኬት ተለዋዋጭ ነው ትናንት ቀለል ያለው ሁኔታ ዛሬ ከበድ ሲል፣ ዛሬ የጨመረው ሁኔታ ነገ ሊቀንስ፣ ዛሬ የተነሳሳውና የጋለው ፍላጎት ነገ ቀዝቀዝ ሊል ይችላል፡፡ እንደ ሁኔታውና እንደ እለቱ ስሜት ጥረቱን የሚቀያይር ሰው እንደዚያው አይነት ውጤትን ያተርፋል፡፡ እንደ እለቱ ሁኔታና ስሜት ሳይሆን ከዓላማው አንጻር የሚሰራ ሰው ደግሞ ከዚያው አንጻር ስኬታማ ይሆናል፡፡ ይህ በፍጹም የማይለወጥ  ሕግ ነው፡፡ http://t.me/psychologypages
نمایش همه...
نمایش همه...
Serve Global | Home

Our organization is founded to uphold the spirit of serving to a new level of prominence by advocating its noble cause and facilitate the means to achieve its desired result.

1. ገንዘብህን በብልሃት አስተዳድረው! ብዙ ሰዎች ገንዘብ ማግኘት ይችላሉ፣ ነገር ግን ሁሉም ሰው እንዴት በትክክል ማስተዳደር እንዳለበት አይማርም።  የፋይናንስ ብልህነት (Financial intelligence) የሚጀምረው በገቢና ወጭህ መካከል ያለውን ልዩነት ከመረዳት ነው። ከምታወጣው የበለጠ ገቢ እንዳለህ አረጋግጥ ፣ ይህም  የበለጠ ሀብታም ያደርግሃል ። 2. መጀመሪያ ራስህ ላይ ኢንቨስት አድርግ!  ብዙ ሰዎች  የሚያገኙትን ገንዘብ የሚያውሉት እዳቸውን ለመክፈል ነው። ብልህ ሰው ግን ሁልጊዜ ከሚያገኘው ገቢ ውስጥ   - ኮርሶችን ለመውሰድ - መጽሐፍት ለመግዛትና - ልምድ ለመውሰድ ያውላል።  3. ቁጠባ እና ኢንቨስት ማድረግ የተለያዩ ናቸው! መቆጠብ ግዴታ እና ጥሩ ልማድ ተደርጎ ይቆጠራል። ነገር ግን ገንዘብህን ከዋጋ ግሽበቱ በበለጠ በሚያድግበት ነገር  ላይ ኢንቨስት ማድረግ ያስፈልግሀል።  መቆጠብ የገንዘብን የመግዛት አቅም ሲያዳክም ኢንቬስትመንት ግን የገንዘብን ዋጋ ይጨምራል። 4. በአንድ የገቢ ምንጭ ላይ ብቻ ጥገኛ አትሁን! ብዙ ሰዎች በአንድ የገቢ ምንጭ ላይ ብቻ ጥገኛ ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ከሆንክ በፍፁም ሀብታም መሆንና የገንዘብ ነፃነት ላይ መድረስ አትችልም። ተጨማሪ ገንዘብ የምታገኝበት ሌላ አማራጭ ሊኖርህ ይገባል።   5.  ሪስክ በመውሰድ ብልህ ትሆናለህ! በህይወትህ ሪስክ እስካልወሰድክ ድረስ ማደግ አትችልም።  በህይወት ውስጥ አንዳንድ እድሎች የህይወትህን  አቅጣጫ የመቀየር አቅም ስላላቸው ሪስክ መውሰድ አለብህ።  6. ማንኛውም ሰው የገንዘብ እውቀት ሊኖረው ይገባል! በዓለም ዙሪያ ያለው የትምህርት ሥርዓት የሚያሳዝነው ነገሩ  ለገንዘብ መሥራትን የሚያስተምር መሆኑ  ነው። የትምህርት ስርዓቱ ገንዘቡን እንዴት ማግኘት፣  ማስተዳደር እና ጠብቆ ማቆየት እንደሚቻል በጭራሽ አያስተምርም። ማንኛውም ሰው ሀብትን እንዴት መፍጠር እንደሚቻል  መማርና የፋይናንስ ነፃነትን ለማግኘት እቅድ ማውጣት አለበት።   7. አስተሳሰብ ሁሉም ነገር ነው! ደሃ  አባቴ ሁልጊዜ እንዲህ ይለኝ  ነበር "ይህን ለመግዛት አንችልም "ሀብታም አባቴ  ግን "እንዴት መግዛት እንደምችል?" ያስተምረኛል። . በዚህ መንገድ አፍራሽ አስተሳሰብህን  ወደ አወንታዊ  አስተሳሰብ ቀይረው።  ይህን ስታደርግ በእርግጠኝነት ግብህን ለማሳካት መንገዶችን ታገኛለህ።  የአንተ አመለካከት እና አስተሳሰብ ከሁሉም በላይ አስፈላጊ ነው። ማንኛውንም ነገር ለማድረግ የመጀመሪያው እና ዋናው ነገር በራስህ ማመን ነው።  8.  ከአንተ የበለጠ ብልህ በሆኑ ሰዎች ራስህን ከበብ! ‘በክፍሉ ውስጥ በጣም ብልህ ሰው ከሆንክ፣ የተሳሳተ ክፍል ውስጥ ነህ።’ የሚል በጣም ታዋቂ አባባል አለ። ብልህ መሆን ከፈለግክ ከአንተ የበለጠ ብልህ በሆኑ ሰዎች እራስህን ከበብ። 9. ስሜቶችህን ተቆጣጠር! ስሜትህን መቆጣጠር በማትችልበት ወቅት ሁኔታው  በጣም የከፋ ይሆናል። ይህ መመሪያ በግል እና በሙያ ህይወትህ  ልትተገብረው የሚገባ ነው። ስኬታማ ቀን ይሁንልን 🙏🙏🙏
نمایش همه...
የነፃነት ጉዞ! ፨፨///////፨፨ የእውቀት ውሱንነት፣ የመረጃ እጦት፣ የብስለት ማነስ፣ የተነሳሽነት ችግር፣ በእራስ የመቆም ፍራቻ የነፃነታችን ዋነኛ ፀር ናቸው። የወረደ ህይወት እንድንኖር፣ በየጊዜው ለፈተና እንድንጋለጥ፣  ህይወታችን አቅጣጫ እንዲያጣ፣  ከአምናው ከካቻምናው የተሻለ ስፍራ እንዳንገኝ የሚያደርገን ትልቁ ነገር የእውቀት ማነስ ነው። አላዋቂ ይፈራል፣ አላዋቂ በሃሳቡ ብቻ ነገሮች የሚቀየሩ ይመስለዋል፤ አላዋቂ ነገሮች ሁሉ በምኞት እንዲከናወኑለት የሚጠብቅ አይነት ሰው ነው። እውቀትህ የነፃነትህ መሰረት ነው፤ መረዳትህ ትልቁ የስኬትህ በር ነው። አንብብ፣ ተማር፣ ቁጭ ብለህ አስተማሪ ታሪኮችን አዳምጥ፣ ጊዜ ሰተህ የሚገነቡህን ተግባራት ፈፅም። ነፃነት በአንዴ የሚመጣ አይደለም፤ ነፃነት ከተወሰኑ መፅሃፍትና ንግግሮች ቦሃላ የሚከሰት አይደለም። የሚሰሩህን፣ የሚያንፁህን፣ ለምትገነባው ህንፃ መሰረት የሚሆኑህን መፅሐፍት ያለማቋረጥ ልታነብ ይገባል። አዎ! ጀግናዬ..! የነፃነትህ ጉዞ ለእውቀት ባለህ ጥማት የሚፈፀም ነው፤ የስኬትህ ሚስጥር እራስህ ላይ ለመስራት ቆራጥ የመሆንህ ነው። አዲስ ተዓምር የለውም፤ እያንዳንዱን የምታደርጋቸውን ነገሮች ከለውጥና እድገትህ ጋር አያይዛቸው፤ የከፍታህ፣ የስኬትህ ግብዓት አድርጋቸው። ብዙ ነገር ባወክ ልክ ብዙ በሮች እየተከፈቱልህ ይመጣሉ፣ ማንነትህን በሚገባ ትረዳለህ፣ ቀጣዩ እርምጃህ አያስፈራህም፣ የወደፊት መዳረሻህ አያስጨንቅህም፣ በባዶ ተስፋ የምትኖርበት ምክንያት አይኖርም። ተማር፣ አንብብ፣ እወቅ ካንተም በላይ የብዙዎችን ህይወት መቀየር ጀምር። የለውጥ ፍራቻ ትልቆቹ ምክንያቶች የእውቀት ውሱንነትና ውድቀት ናቸው። ሳታውቀው በምትጀምረው የትኛውም ስራ ስኬታማ የምትሆንበት መንገድ አይኖርም። ጉዞህን ከመጀመርህ በፊት ስለጉዞው ምንነት መጠየቅ፣ ማወቅና መረዳት ይኖርብሃል። አዎ! የቻይናዎችን አባባል አስታውስ "ስለመንገዱ ማወቅ ከፈለክ የሚመለሱትን ጠይቅ።" አንተ ልትጓዝበት የምትፈልገው መንገድ ቢያስፈራህ፣ ቢያስጨንቅህ፣ ጉዞህን ለመጀመር ደጋግመህ የምታመነታ ከሆነ ያለምንም ቅድመሁኔታ ካንተ በፊት በጉዞው ላይ የተሳተፉ ሰዎችን ጠይቅ፣ ከእነርሱ ተማር፣ የእነርሱን የጉዞ ታሪክ አጥና፣ መውሰድ የሚገባህንም ትምህርት ውሰድ። እወቀት ለተጠማት ሁሌም ቅርብ ነች፤ ጥበብና ብስለት ለሚፈልጋቸው ዘወትር ዝገጁ ናቸው። እራስህን በእራስህ ብቁ ካላደረክ ማንም አንተን ብቁ ሊያደርግህ የሚመጣ አካል አይኖርም። እያንዳንዳችን የገዛ ሃላፊነታችንን የመውሰድ ግዴታ አለብን። ካንተ በላይ እንደሆኑ የምታስባቸው አብዛኞቹ ሰዎች አንተ የማታውቀውን ያውቃሉ፣ አንተ የማታደርገውን ያደርጋሉ፣ አንተ የምትፈራውን እነርሱ ይደፍራሉ። የእውቀት ጥማትህን ጨምር፣ በየጊዜው እራስህን ማደስህን ቀጥል፣ በጥበብ በማስተዋል ወደ ወሳኙ የህይወት ግብህ በልበሙሉነት ተጓዝ። ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን!
نمایش همه...
ያለፈ ማንነትህን እርሳው! የኃላ ታሪካችንን ዘወትር እያሰብን የምንብሰከሰክ ከሆነ አንለወጥም። ባለፈው ታሪካችን የወደቅንባቸውና ያልተሳኩልን ነገሮች የአሁን ማንነታችን ሊሆኑ አይገባም። በጊዜ ውስጥ መቆጣጠር የምትችለው ነገር አሁንን ብቻ ነው። ያለፈው አልፏል። አሁን ላይ ኑር!!!
نمایش همه...
አንድ ፈረሰኛ ወደ አንድ ከፍተኛ ተራራ ይጓዝ ነበር፡፡ ወደ ተራራው ወገብ ላይ ሲደርስ አንድ ምስኪንና አንድ እግሩ ሽባ የሆነ ሰው እንዳቅሙ ቋጥኙን እየቧጠጠ ለመውጣት ሲፍጨረጨር ያገኛል፡፡ ፈረሰኛው፤ "ወዳጄ፤ ይህን የሚያህል ተራራ እንዲህ ተንፏቀህ የሚገፋ አይደለም፡፡ ስለዚህ እንደምንም ፈረሴ ላይ ላውጣህና አፈናጥጬ ዳገቱ ጫፍ ላይ ላድርስህ?" ሰውዬው፤ "እግዚአብሔር የባረከህ ሰው ነህ! ግን ሥጋቴ እንዳላጣብብህ ነው፡፡ ለማፈናጠጥ ይበቃል ብለህ ነውን?" ፈረሰኛው፤ "እንደምንም ተጣበን እንወጣዋለን እንጂ በዚህ ሁኔታ በፍፁም ጥዬህ ብሄድ ግፍ ይሆንብኛል፡፡ ሰው እንኳ ባይኖር ተራራውም ይታዘበኛል፡፡ ስለዚህ ና ውጣ ግዴለህም፡፡" ሰውዬው፤ "ፈጣሪ ምስክሬ ነው፤ ለእኔ የተላክ ውድ አዳኝ መልዐክ ነህ፡፡ አምላክ ውለታህን ይክፈልህ!" ፈረሰኛው ተሸክሞ ፈረሱ ላይ አስቀመጠውና ተራራውን ተያያዙት፡፡ ጥቂት እንደሄዱ ግን፤ ሰውዬው "ወዳጄ፤ ቅድም እንደፈራሁት በጣም ተጣበናል፡፡ ብወርድልህ ይሻላል፡፡" ፈረሰኛው፤ "እንደሱማ አይሆንም፡፡ ባይሆን የተወሰነውን ዳገት እኔ በእግሬ ልሞክረው፤ አንተ ፈረሱን ያዝ" አለውና ፈረሱን ሰጥቶት ወረደ፡፡ ሰውየው እየጋለበ ዳገቱን እየወጣ እየራቀ ሄደ፡፡ ፈረሰኛው በእግሩ ዳገቱን ተያያዘው፡፡ ሆኖም ባለፈረሱ እየራቀ ሄደ፡፡ ፈረሰኛው ሥጋት እየገባው በተቻለው ፍጥነት ሊከተለውና ሊጠጋው ቢሞክርም ሰውዬው ፈረሱን ይብስ አፈጠነው፡፡ ፈረሰኛው መጣራት ጀመረ፡፡ ወይ የሚለው ግን አጣ፡፡ ሰውዬው ፈረሱን ይዞ ሊጠፋ መሆኑ ለፈረሰኛው ገባው፡፡ “አንተ ሰው፤ ግዴለም ፈረሱን ይዘኸው ትሄዳለህ፡፡ ግን አንድ ነገር ቆም ብለህ ስማኝ እባክህ፡፡ እንደማልደርስብህ ታውቃለህ፡፡ ጆሮህን ብቻ አውሰኝ?” ሲል ለመነው፡፡ ሰውዬው ርቀቱን በደንብ ካረጋገጠ በኋላ፤ “እሺ ምንድነው ልትነግረኝ የፈለከው?” ፈረሰኛውም፤ “ወዳጄ፤ መቼም አንድ ቦታ ወርደህ ከሰው መቀላቀልህ አይቀርም፡፡ አደራህን ይሄን አሁን እኔን የሰራኸኝን ነገር ለማንም ሰው እንዳትነግር፡፡ አለበለዚያ ደግ የሚሰራ ሰው ይጠፋል!” #ምንጭ:- "ታሪክና ምሳሌ" ከክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.