የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
رفتن به کانال در Telegram
2 640
مشترکین
+124 ساعت
+27 روز
+5230 روز
آرشیو پست ها
ነሐሴ ፯ (7)
#ጽንሰታ_ለእግዝእትነ_ቅድስት_ድንግል_ማርያም_ወላዲተ_አምላክ
ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ የምታበራ የብርሃን እናቱ እግዝእትነ ማርያም በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ነሐሴ ፯ ተፀነሰች፡፡
እንኳን ለባህሪያችን መመኪያ፤ ለቊስላችን የመድኃኒት ሙዳይ፤ ለድኅነታችን መጀመሪያ፤ ለንጽሕናችን መሠረት ለመላእክት እህት ለነቢያት ትንቢት፣ ለሐዋርያት ሞገስ፣ ለሰማዕታት አክሊል፣ ለደናግል መመኪያ፣ ለእኛ ለኃጥአን መመኪያ፣ ለነፍሳችን ነፍስ ለሆነችው፣ ስሟን ጠርተን ከማንጠግባት ክብሯን ስንናገር ያሳነስን መስሎን ለምንሳቀቅላት ከቅድስት ሥላሴ ዘንድ ባለማል ለሆነችን ለቅድስተ ቅዱሳን ለንጽሕተ ንጹሐን ለቅድስት ድንግል ማርያም የጽንሰት በዓል እንኳን አደረሳችሁ፡፡
ዓለም ሳይፈጠር አስቀድሞ በሕሊና አምላክ ታስባ ትኖር የነበረች እመቤታችን የተነገረላት ትንቢት ሊፈጸም የአባት የእናቷ የቅድመ አያቶቿ ራእይ ሊተረጐም ጌታ የፈቀደበት ጊዜ ሲደርስ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ኢያቄምን ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች ደግ ልጅም ትወልዳለች አለው፡፡
ክብርት እናቱን እናት አድርጎ ለሰጠን ለመድኀኔዓለም ክርስቶስ ክብርና ምስጋና ይግባው!
በቃልኪዳኗ በምልጃዋ ይማረን።
ማስታወቂያ
👉የምዝገባው ቀን እስከ ነሐሴ 9 ድረስ ነው። በሥልጠናው ላይ እነዚህ የተመለመሉ አባላትና መሠልጠን የሚፈልጉ አባላት በሙሉ መሳተፍ ይችላሉ።
👉 ምዝገባው በጽ/ቤት የሚካሔድ ይሆናል
👉 ሥልጠናው በተገኙ አባላት ነሐሴ 10 ይጀምራል
اکنون در دسترس! پژوهش تلگرام ۲۰۲۵ — مهمترین بینشهای سال 
