የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
رفتن به کانال در Telegram
2 636
مشترکین
+124 ساعت
+167 روز
+5630 روز
آرشیو پست ها
የጰራቅሊጦስና የሰኔ ሚካኤል እጩ ዘማርያን መሆናችሁን እናሳውቃለን።
ወደ ገዳሙም ደርሶ ከልጆቹ መነኰሳት ጋራ የመንፈቀ ሌሊትን ጸሎት አደረገ። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ብዙ ጊዜ ወደርሱ እየመጣ ያነጋግረው ነበር። እርሱም የመድኃኒታችንን እግሩን ያጥበው ነበር እጣቢውንም ይጠጣ ነበር ጌታችንም ብዙ ምሥጢራትን ገለጠለት ትንቢቶችንም ተናገረ።
ከዚህም በኋላ ፈጽሞ በአረጀ ጊዜ ሐምሌ ሰባት ቀን ተኛ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መጥቶ እያረጋጋው በእርሱ ዘንድ ተቀመጠ። ብፁዕ አባ ሲኖዳም ጌታችንን እንዲህ አለው ጌታዬ ፈጣሪዬ ልዩ ሦስትነትህንና ጌትነትህን ስለሚነቅፉ ከሀድያን ወደ ጉባኤው እሔድ ዘንድ እንዲጠሩኝ ሊቀ ጳጳሳቱ ወደ እኔ ልኳልና እንደቀድሞው ታጸናኛለህን።
ጌታችንም በጸጋና በጥዑም ቃል እንዲህ ብሎ መለሰለት ወዳጄ ሲኖዳ ሆይ ሌላ ዕድሜ ትሻለህን። እነሆ ዕድሜህ ሁሉ መቶ ሃያ ዓመት ከሁለት ወር ሁኖሃል ዕድሜህ ዘጠኝ ዓመት ሲሆን አስኬማን ለበስኽ ከዚያ በኋላ መቶ ዐሥራ አንድ ዓመት ከሁለት ወር ኖርኽ አሁንስ ድካምህ ይብቃህ ይህንንም ብሎ ጌታችን በክብር ዐረገ።
በዚያንም ጊዜም የቅዱሳን አንድነት ማኅበር ወደርሱ መጡ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ዳግመኛ አየው ልጆቹንም ክብር ይግባውና ለጌታዬ ለኢየሱስ ክርስቶስ እሰግድ ዘንድ አንሱኝ አላቸው አንሥተውትም ሰገደለት። ከዚህም በኋላ ዳግመኛ እንዲህ አላቸው ወደ እግዚአብሔር አደራ አስጠብቅኋችሁ ነፍሴም ከዚህ ከደካማው ሥጋዬ የምትለይበት ጊዜ ደርሷል እኔም ለአባታችሁ ለዊዳ እንድትታዘዙ አዝዛችኋለሁ ከእኔ በኋላ ጠባቂያችሁ እርሱ ነውና አላቸው።
ለልጆቹም ይህን በተናገረ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመረጥሁህ ሲኖዳ ሆይ ብፁዕ ነህ ቸርነቴም ይደረግልሃል በሕይወትህ ዘመን ሁሉ አንተ የምወደውን ሥራ ሠርተሃልና እንግዲህ ወደ ዘለዓለም ተድላ ታርፍ ዘንድ ወደእኔ ና አለው። ሐምሌ 7 ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎትና ምልጃ ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።https://t.me/finotebirhan12
🔴#ስንክሳር ግንርቦት_7
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ግንቦት ሰባት በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያኛ የሆነ የከበረ አባት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_አትናቴዎስ_ሐዋርያው አረፈ፣ ቅዱስ አባት የባሕታውያን አለቃ የሆነ መስተጋድል #አባ_ሲኖዳ ልደቱ ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አትናቴዎስ_ሐዋርያዊ
ግንቦት ሰባት በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያኛ የሆነ የከበረ አባት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ሐዋርያዊ አትናቴዎስ አረፈ።
ይህም ቅዱስ ሐናፊ ከሚባል የእስ*ላም ነገድና ከአረማ*ውያን ተወላጅ ነው ይባላል። እርሱም ከመምህር ከሚማሩ ሕፃናት ጋራ እያለ እርስ በርሳቸው በመጫወት ሥርዓተ ቤተክርስቲያን እየሠሩ ከእነርሱ ውስጥ ዲያቆናትን ኤጲስቆጶሳትንም ሲያደርጉ እሊያን የክርስቲያንን ልጆች አይቶ ጨዋታቸው ደስ ስለአለው ከእሳቸው ጋራ በጨዋታቸው አንድ ይሆን ዘንድ የክርስቲያንን ልጆች ለመናቸው። እነርሱም አንተ አረ*ማዊ ነህና ከእኛ ጋራ አትደመርም ብለው ከለከሉት እርሱም ክርስቲያን እሆናለሁ አላቸው እነርሱም ደስ ተሰኙበት።
ያን ጊዜም ወስደው በሊቀ ጳጳሳት አምሳል አደረጉት ከበታቹም ወንበር አድርገው ይሰግዱለት ጀመር። በዚያን ጊዜም ሊቀ ጳጳሳት አባ እለእስክንድሮስ በዚያ አለፈ የክርስቲያን ልጆች ሲጫወቱ በአያቸው ጊዜ አብረውት ላሉ ይህ ሕፃን ከፍ ከፍ ያለችና የከበረች ሹመትን ይሾም ዘንድ አለው አላቸው።
አባቱም በሞተ ጊዜ ወደ አባ እለእስክንድሮስ መጣ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቀው። ከዚህም በኋላ የአባቱን ገንዘብ ሁሉ ወስዶ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ሰጥቶ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርትና ሕግ ሥርዓትንም ከአባ እለእስክንድሮስ ዘንድ እየተማረ ኖረ እርሱም ተወዳጅ ልጅ አደረገው።
ከዚህም በኋላ ዲቁና ሾመው የመንፈስ ቅዱስንም ጸጋ የተመላ ሆነ። የከበረ አባት እለእስክንድሮስም በአረፈ ጊዜ ይህን አባት አትናቴዎስን በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ሾሙት። ከዚህ አስቀድሞ ግን የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ኤጲስቆጶሳት ስብሰባ በተደረገ ጊዜ አባ እለእስክንድሮስ ከዚህ ዓለም ሳይለይ ይህም አትናቴዎስ ከእሳቸው ጋራ ተሰብስቧል። የጉባኤውም ጸሐፊ አድርገውት በኒቅያ ከተማ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ከእሳቸው ጋራ ሠራ።
ጻድቁ ቈስጠንጢኖስ በሞተ ጊዜ አርዮ*ሳዊ ልጁ ሁለተኛው ቈስጠንጢኖስ ነገሠ አርዮ*ሳውያንም በዙ ይህንንም አባት አርዮ*ሳዊው ንጉሥ ከመንበረ ሢመቱ አሳደደው በእርሱም ፈንታ ጊዮርጊስ የተባለ ከሀዲ ሰው ሾመ።
ከዚህም በኋላ ብዙ ጊዜ ሲአሳድዱትና ሲመልሱት ኖረ። በስደቱም በአንዲት ምዕራባዊት አገር በአለ ጊዜ በዚያ የጣዖት ቤት አለች። በዚያችም የጣዖት ቤት ብዙ ሕዝቦች በውስጧ ይሰበሰባሉ። ለዚያችም የጣዖት ቤት በውስጧ የሚሠሩ ብዙ የሰይጣን ሥራዎች አሏት። እርሱም የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመነው ያቺንም የጣዖት ቤት አፍርሶ የአገር ሰዎችን ሁሉ እግዚአብሔርን ወደማወቅ መለሳቸው።
ይህንንም አባት አምስት ጊዜ አሳደዱት የሹመቱም ዘመን አርባ ሰባት ሲሆን ዐሥራ አምስቱን ዓመት በስደትና በእሥራት ነው ያሳለፈው። ይህንንም አባት ብዙ መከራና ድካም መሰደድም ስለደረሰበት ሐዋርያዊ ተብሎ ተጠራ።
በሚሞትበትም ጊዜ በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን ባገኝ ይህን የጣዖት ቤት ያፈርስ ዘንድ በፊቱ እኔ እየሰገድኩ እለምነዋለሁ። ይህም አባት ከአረፈ በኋላ ንጉሥ ልኮ ያንን የጣዖት ቤት አስፈረሰው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ታላቁ_አባ_ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
ዳግመኛም በዚህች ቀን ቅዱስ አባት የባሕታውያን አለቃ የሆነ መስተጋድል አባ ሲኖዳ ልደቱ ነው።
ይህም ቅዱስ በግብጽና በአክሚም አውራጃ ስሟ ስንላል ከምትባል ሀገር ከላይኛው ግብጽ ነበር። ስለእርሱም የመላእክት አምሳል የሆነ አባ ሐርስዮስ ትንቢት ተናገረለት። እርሱም ስለ ገዳም አገልግሎት ከመነኰሳት ጋር ሲሔድ የዚህን የቅዱስ ሲኖዳን እናት ውኃ ለመቅዳት ወጥታ አገኛት: ወደርሷ ሒዶ ሦስት ጊዜ ራሷን ሳማትና እንዲህ አላት ዜናው በዓለሙ ሁሉ የሚሰማ የስሙ መዓዛ ከሽቱ የሚጥም የሆነ የሆድሽን ፍሬ እግዚአብሔር ይባርክ።
እነዚያ መነኰሳትም በአዩት ጊዜ አድንቀው አባታችን አንተ የሴት ፊት ማየት ከቶ አትሻም ነበር ዛሬ ግን ከሴት ጋራ ትነጋገራለህ አሉት። ልጆቼ ሆይ ሕያው እግዚአብሔርን የእግዚአብሔርን ምሕረት ተስፋ የሚያደርግ ዓለሙ ሁሉ የሚጣፍጥበት ከዚች ሴት የሚወጣ የጨው ቅንጣት አለ አላቸው።
አንድ በገድል የጸና ጻድቅ ሰው መነኰስ ነበረ እርሱም መልሶ አባ ሐርስዮስን እንዲህ አለው እግዚአብሔር ሕያው ነው አንተ ራሷን ትስም ዘንድ ወደዚያች ሴት በቀረብክ ጊዜ በእጁ የእሳት ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ በዙሪያዋ አየሁት፡፡ ራሷንም በሳምካት ጊዜ ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጁ ሆይ ሰላምታ ይገባሃል ሲልህ ደግሞም ከዚች ሴት የሚወለደው የተመረጡ ቅዱሳንን ሁሉ ልባቸውን ደስ ያሰኛል ወልደ እግዚአብሔርም ከርሱ ጋር ብዙ ጊዜ ይነጋገር ነበር ሲል ሰማሁት አለ።
በግንቦት ሰባት ቀን ይህ ቅዱስ አባ ሲኖዳ ተወለደ በአደገም ጊዜ አባቱ በጎች ስለነበሩት ለልጁ ለሲኖዳ እንዲጠብቃቸው ሰጠው ይህ ሲኖዳም ምሳውን ለእረኞች ሰጥቶ እስከ ማታ ድረስ ይጾም ነበር። በሌሊትም ከውኃ ዐዘቅት ውስጥ ወርዶ በዚያ ቁሞ እስቲነጋ ድረስ ሲጸልይ ያድር ነበር። በክረምትም ሆነ በቊር ሰዓት እንዲሁ ያደርግ ነበር።
አባቱም የሲኖዳ እናት ወንድም ወደ ሆነው ወደ አባ አብጎል እጁን በላዩ ጭኖ ይባርከው ዘንድ ወሰደው። አባ አብጎልም በአየው ጊዜ የሕፃኑን እጅ አንሥቶ በራሱ ላይ አድርጎ ሲኖዳ ሆይ ባርከኝ ለብዙ ሕዝብ ታላቅ አባት ትሆን ዘንድ የሚገባህ ሁነሃልና አለው: አባቱም በአባ አብጎል ዘንድ ተወው።
ከዕለታትም በአንዲቱ ቀን አባ አብጎል እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ ሰማ እነሆ ሲኖዳ ለዓለሙ ሁሉ አርሲመትሪዳ የባሕታውያን አለቃ ሁኖ ተሾመ። ይህም ሲኖዳ ለዓለሙ ሁሉ ብርሃን እስከሚሆን በበጎ አምልኮ ያለ ማቋረጥ በጾምና በጸሎት በስግደትና በመትጋት ታላቅ ተጋድሎ መጋደልን ጀመረ።
ከዚህም በኋላ በአንዲት ቀን ለአባ አብጎል የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና የኤልያስን አስኬማ የሠለስቱ ደቂቅን ቆብና የመጥምቁ ዮሐንስን ቅናት አመጣለት። እንዲህም አለው እንድትጸልይና የምንኵስና ልብስ ለሲኖዳ እንድታለብሰው እማዚአብሔር አዝዞሃል። ያን ጊዜም አባ አብጎል ተነሥቶ ጸለየ የምንኵስና ልብስንም አለበሰው።
ከዚህም በኋላ ተጋድሎውን አበዛ፡፡ ለመነኰሳት፣ ለመኳንንት፣ ለሕዝባውያንና ለሴቶች ለሰዎች ሁሉ መመሪያ የሚሆን ሥራትን ሠራ። በኤፌሶንም የሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ ስለ ከሀዲው ንስጥሮስ በተደረገ ጊዜ ከማኅበሩ አባት ከሊቀ ጳጳሳት ቄርሎስ ጋራ ወደ ጉባኤው ሔደ ንስጥሮስም ከክህደቱ ባልተመለሰ ጊዜ አውግዘው ለይተው አሳደዱት።
ከዚህ በኋላም ወደ ሀገራቸው በመመለሻቸው ጊዜ መርከበኞች ከሊቀ ጳጳሳቱ ጋራ አትሳፈርም ብለው አባ ሲኖዳን ከለከሉት እርሱም ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ማለደ። ወዲያውኑም ደመና መጥታ ተሸከመችውና አባ ቄርሎስ በመርከቡ ውስጥ እያለ በበላዩ በአንጻሩ አደረሰችው። አባቴ ሆይ ሰላም ለአንተ ከአንተ ጋራ ላሉትም ይሁን ብሎ ሰላምታ አቀረበ፡፡ በመርከብ ያሉት ሁሉም ላንተም ሰላም ይሁን በጸሎትህም አትርሳን አሉት። እጅግም አደነቁ ለሚፈሩት ይህን ይህል ጸጋ የሚሰጥ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።
በዚህችም ቀን ቅድስት ዲላጊ ከአራት ልጆቿ ጋራ ምስክር ሆና አረፈች፡፡ እነርሱም ሱርስ ኀርማን ያአፋ ናቸው። ይችም ቅድስት በክብር ባለቤት ክርስቶስ ሃይማኖት የጸናች ናት።
መኰንኑ አርያኖስም ሀገረ አስና በደረሰ ጊዜ ልጆቿን እየነዳች ተቀበለችው በፊቱም ቁማ አርያኖስ ሆይ ሰማይንና ምድርን በውስጣቸው ያለውን በፈጠረ በክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ የማምን ክርስቲያን ነኝ አለችው።
ልጆቿም እንደርሷ እኛ ክርስቲያን ነን እያሉ በግልጽ ጮኹ። መኰንኑም ሰምቶ ቁጣን ተመላ ራሳቸውንም በሰይፍ ቆረጠ ምስክርነታቸውንም ፈጽመው ነፍሶቻቸውን ወደ ክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ መላእክት ወሰዱ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#እናታችን_ቅድስት_ሰሎሜ_ዘወረብ
በዚህችም ዕለት ደግሞ ንጽሕናን ቅድስናን ድንግልናን ገንዘብ ያደረገች ተሐራሚት ሰሎሜ አረፈች። ይችም ቅድስት ወረብ ከሚባል አገር ናት ወላጆቿም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ናቸው በበጎ አስተዳደግም አሳደጉዋት። በአደገችም ጊዜ እርሷ ሳትፈቅድ አንድ መኰንን አጭቶ በሠርግ አገባት። ያን ጊዜም አምላካዊ ኃይል ከልክሎት ወደርሷ መቅረብ አልቻለም አባለ ዘሩ ተቀሥፎአልና።
በእንደዚህም እያለች ራሷን ሠውራ በሌሊት ሔደች በእግዚአብሔር ኃይል አመለጠች። ቅዱሳን በአሉበት ሁሉ በመዞር በጾም በጸሎት ተወስና ዕውነተኛ መንገድን ጌታ ይመራት ዘንድ በቀንና በሌሊት ስትማልድ ኖረች።
ጌታችንም ልመናዋን ሰምቶ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም አደረሳት የመላእክት የሆነ አልባሰ ምንኲስናን በአባ ዮሐንስ ከማ እጅ ለብሳ የሰውን ልብ የሚያስደነግጥ ጽኑ ገድልን ተጋደለች።
በጾም በጸሎት በተመሰገነ ገድል ሁሉ የፍጹማን አባቶችን ጐዳና ተጓዘች። በመጽሐፈ ገድሏ እንደ ተጻፈ ብዙዎች ድንቆች ተአምራትንም እስከ ማድረግ ደርሳ ከዚህ በኋላ በሰላም አረፈች።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን።https://t.me/finotebirhan12
🔴#ስንክሳር ግንቦት_6
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ግንቦት ስድስት በዚህች ቀን የእስክንድርያ ቄስ የከበረ አባት #አባ_መቃርስ አረፈ፣ ከግብጽ ደቡብ ዳፍራ ከሚባል አገር የከበረ #አባ_ይስሐቅ ምስክር ሆኖ አረፈ፣ #ቅድስት_ዲላጊ ከአራት ልጆቿ ጋራ ምስክር ሆና አረፈች፣ ንጽሕናን ቅድስናን ድንግልናን ገንዘብ ያደረገች #ተሐራሚት_ሰሎሜ አረፈች።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_መቃርስ
ግንቦት ስድስት በዚህች ቀን የእስክንድርያ ቄስ የከበረ አባት አባ መቃርስ አረፈ። ይህም ቅዱስ በአባቱ በሚቀድመው በታላቁ በክቡር አባ መቃርስ ዘመን ለአስቄጥስ ገዳም አባት ሁኖ ብዙ ትሩፋትን ሠራ።
ስለእርሱም እንዲህ ተባለ አንዲት ዘመሚት ነክሳው ገደላት ከዚህም በኋላ ተጸጽቶ ነፍሱን ገሠጻት ስለ ዘመሚቷም ሞት በበረሀ ወደአለ ወንዝ ወርዶ ሥጋውንም ለዘመሚት ገልጦ እንደዝልጉስ እስኪሆን በዚያ ስድስት ወር ኖረ። ከዚህ በኋላ ወደበዓቱ ተመለሰ መቃርስ እንደሆነም ማንም አላወቀውም።
አንድ ጊዜም እየጸለየ አምስት ቀን አምስት ሌሊት ቆመ ልቡም ወደ ሰማይ ተመስጦአል ሰይጣናትም እስከ ተቃጠሉ ድረስ ይቺ ትጋትና ተጋድሎ ከሠራው ትሩፋት ሁሉ ትልቃለች አሉ። አንድ ጊዜም የረዓይትን ቦታዎች ሊያይ ወዶ ወደ በረሀ ውስጥ ገባ ዐሥር ቀኖችም እየተጓዘ ኖረ። በሚመለስም ጊዜ ምልክት ሊሆኑት መንገዱን እንዳይስት ለምልክት የሚያኖራቸው ሸንበቆዎች ከእርሱ ጋራ ነበሩና በየመንገዱ ተከላቸው።
በደከመም ጊዜ ጥቂት ሊያርፍ በምድር ላይ ተኛ። ተኝቶ ሳለም እነዚያን ሸንበቆዎች ሰይጣን ነቀላቸው አሥሮም በቅዱስ መቃርስ ራስጌ አኖራቸው። በነቃም ጊዜ አያቸውና ወዲያውኑ አጣቸው አደነቀ እንዲህ የሚልም ቃልን ሰማ።
መቃርስ ሆይ ሃይማኖት ካለህ አታወላውል በሸንበቆዎችም አትታመን የእስራኤልን ልጆች በበረሀ ሲመራቸው የነበረ የብርሃን ምሰሶ እርሱ እንደሚመራህ እመን እንጂ አትጠራጠር። ወዲያውኑ የብርሃን ምሰሶ አይቶ ተመለሰ።
ከዚህም በኋላ በጎዳና ሳለ ተጠማ እግዚአብሔርም ከበረሀ ላሞች አንዲቷን ልኮለት ወተቷን ጠጥቶ ረካ ወደ በዓቱም ተመለሰ።
በአንዲት ቀንም ጅብ ወደርሱ መጥታ ልብሱን ይዛ ትስብ ጀመር እርሱም እስከ ዋሻዋ ተከተላት። ሦስት ልጆቿን አወጣችለት በአያቸውም ጊዜ ዕውሮች ሁነው አገኛቸው ከልቡናዋም አሳብ የተነሣ ያቺን ጅብ አደነቃት። ግልገሎቿንም ይዞ በዐይኖቻቸው ውስጥ ምራቁን ተፋ፡፡ አዳኝ በሆነ በመስቀል ምልክትም አማተበባቸው ያን ጊዜ ድነው ከእናታቸው ኋላ ሮጡ ጡቷንም ጠቡ ከዚህ በኋላም ወደ በዓቱ ተመለሰ እርሷም የበግ አጐዛ አመጣችለት እርሱም ተቀብሎ በላዩ እየተኛ እስከሚአርፍበት ጊዜ በእርሱ ዘንድ አኖረው።
በአንዲት ጊዜም ደግሞ ልብሱን ለውጦ በሕዝባዊ አምሳል ሆኖ ወደ አባ ጳኵሚስ ገዳም ሔደ በታላቁም ጾም ሳይበላ ሳይጠጣ አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ቆመ። የሚሠራውንም እንደቆመ ይታታ ነበር እንጂ አይቀመጥም። መነኰሳቱም አባ ጳኩሚስን ይህን ሰው ከእኛ ዘንድ አውጣው ሥጋ የለውምና አሉት አባ ጳኵሚስም ሥራውን ይገልጥልኝ ዘንድ እግዚአብሔርን እስከምለምነው ታገሡኝ አላቸው። በለመነውም ጊዜ የእስክንድርያው መቃርስ እንደሆነ እግዚአብሔር አስረዳው።
በዚያን ጊዜም አባ ጳኵሚስና መነኰሳቱ ሁሉ ወደርሱ ሒደው እጅ ነሱት ከእርሱም ቡራኬ ተቀብለው ደስ ተሰኙበት ወደቤተ መቅደስም ከእሳቸው ጋራ አስገቡት። በገዳሙ ውስጥም በሥራቸው በመመካት በባልንጀሮቻቸው ላይ የሚታበዩ የዚህን ቅዱስ አባት የአባ መቃርስን ጸጋውን አይተው ትሑታኖች ሆኑ። ከዚህ በኋላም ወደ በዓቱ ወደ አስቄጥስ ገዳም ተመለሰ።
በእስክንድርያ አገርም ዝናብ በተከለከለ ጊዜ ዝናብን እንዲያወርድ አንበጣንም እንዲአጠፋ ወደ እግዚአብሔር አብሮት ለመጸለይ ወደርሱ ይመጣ ዘንድ ሊቀ ጳጳሳት አባ ጢሞቴዎስ እየማለደ ላከበት። ያንጊዜም ተነሥቶ ወደ እስክንድርያ አገር ሔደ ሕዝቡም በታላቅ ደስታ ተቀበሉት በልቡም ጸለየ ብዙ ዝናብም ዘነበ ከዝናብ ብዛት የተነሣ ምድሪቱ ትጠፋለች ብለው እስቲአስቡ ድረስ ሁለት መዓልት ሁለት ሌሊት እየዘነበ ኖረ። እጅግም ፈርተው አባታችን ሆይ ዝናቡን አስወግዶ በልክ ይሆን ዘንድ እንዳንጠፋ ስለ እኛ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ ብለው ለመኑት ያንጊዜም ጸለየ ዝናቡም በርቶ በእግዚአብሔር ቸርነት ፀሐይ ወጣላቸው።
ይህም አባት ብዙ ታላላቅ ትሩፋቶችን ሠርቷል እግዚአብሔርም በእጆቹ ድንቆች ተአምራትን ገለጠ ርኵሳን አጋንንት ያደሩባቸውንና ብዙዎች በሽተኞችን አዳናቸው። ይህ አባትም የሠራቸውን በጎ ሥራዎች ሊቆጥራቸው የሚችል የለም አንድ ሰው በጎ ሥራ እንደሠራ የሰማ እንደሆነ ሰውዬው እንደሠራው እስከሚሠራ አይተኛም።
የክብር ባለቤት ስለሆነ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም ክብር ምራቁን ሳይተፋ ስልሳ ዓመት ኖረ። መቶ ዓመት ከሆነውና ተጋድሎውን ከፈጸመ በኋላ በበጎ ሽምግልና አረፈ፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ይስሐቅ_ጻድቅ
በዚህች ቀን ከግብጽ ደቡብ ዳፍራ ከሚባል አገር የከበረ አባ ይስሐቅ ምስክር ሁኖ አረፈ። ለዚህም ቅዱስ በሌሊት ራእይ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጾለት የሰማዕትነትን አክሊል ትቀበል ዘንድ ጣዋ ወደሚባል አገር ሒድ አለው።
ከዚያም በነጋ ጊዜ ከመሔዱ በፊት አባትና እናቱን ሊሰናበታቸው ተነሣ። ሁለተኛም የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ ከአገሩ እስከ አወጣውና ሀገረ ጣዋ እስካደረሰው ድረስ እነርሱ በላዩ እያለቀሱ አልለቀቁትም።
በደረሰም ጊዜ መኰንኑን በዚያ ከውሽባ ቤት አገኘው ከዚያም በወጣ ጊዜ በክብር ባለቤት በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ የማምን እኔ ክርስቲያን ነኝ ብሎ በመኰንኑ ፊት በግልጽ ጮኸ።
ከኒቅዩስ ሀገርም እስኪመለስ ቅዱሱን ወስዶ እንዲጠብቀው ከወታደሮች አንዱን አዘዘው ከዚያ ወታደርም ጋራ ቅዱስ ይስሐቅ አልፎ ሲሔድ በመንገድ ዳር የተቀመጠ አንድ ዕውር የእግዚአብሔር ቅዱስ ሆይ ይቅር በለኝ ዐይኖቼንም አድንልኝ ብሎ ለመነው። አባ ይስሐቅም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ስለዚያ ዕውር ለመነው ያን ጊዜም ዐይኖቹ ተገለጡ። ይህንንም ድንቅ ተአምር ወታደሩ አይቶ የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ የክርስቲያን ወገን ሆነ።
መኰንኑም በተመለሰ ጊዜ ያ ወታደር በመኰንኑ ፊት የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ በመታመን ሰማዕት ሁኖ አክሊል ተቀበለ።
ከዚህም በኋላ መኰንኑ ቅዱስ ይስሐቅን ጽኑ ሥቃይን አሠቃይቶ ወደ ሀገረ ብህንሳ ሰደደው በዚያም አሠቃዩት። በመርከብም ሲወስዱት የጽዋ ወኃን ለመናቸው ከቀዛፊዎችም አንዱ አንድ ዐይኑ የታወረ ውኃን በጽዋ ሰጠው የከበረ ይስሐቅም ያን ውኃ በላዩ ረጨ ዐይኑም ድና እንደ ሌላዪቱ ሆነች።
ጽኑ ሥቃይን የሚአሠቃዩት የብህንሳ ሀገር ሰዎችም ይህን ድንቅ ሥራ በአዩ ጊዜ ወደ መኰንኑ ወሰዱትና ብትገድለውም ብትተወውም አንተ ታውቃለህ አሉት። መኰንኑ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ ወዲያውኑ አዘዘ የከበረች ራሱንም ቆረጡት የምስክርነት አክሊልንም ተቀበለ።
በዚያም ምእመናን ሰዎች ነበሩ የአባ ይስሐቅንም ሥጋ በሠረገላ ጭነው በበሮች እያሳቡ ዳፍራ ወደተባለ አገሩ አደረሱት ያሻግሩትም ዘንድ መርከብ ባላገኙ ጊዜ ተሸክመው አሻግረው ወደ ቤቱ አደረሱት። ቤቱንም አፍርሰው በስሙ ቤተ ክርስቲያን አድርገው ሠሩዋት ሥጋውንም በውስጥዋ አኖሩ ከእርሱም የሚያስደንቁ ብዙዎች ተአምራት ተገለጡ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_ዲላጊና_አራት_ሴት_ልጆቿ
🔴#ስንክሳር ግንቦት_5
#ቅዱስ_ኤርምያስ_ነቢይ
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ግንቦት አምስት በዚች ቀን የካህኑ ኬልቅዩ ልጅ ታላቅ ነቢይ ኤርምያስ አረፈ። ይህም እውነተኛ ነቢይ የአሞጽ ልጅ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ሦስት ዓመቱ ማስተማር ጀመረ።
ከዚያም በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን ዐሠራ አንዱ የሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥቱ እስከሚፈጸም በአምስተኛው ወር ኢየሩሳሌም እስከ ተማረከችበት ጊዜ ያስተምር ነበር።
ስለ ራሱ እንዲህ ሲል ራሱ ተናገረ የእግዚአብሔር ቃል ወደኔ መጣ እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ "በእናትህ ማሕፀን ሳልፈጥርህ ወደድኩህ ከእናትህም ማሕፀን ሳትወጣ መረጥኩህ ለአሕዛብም መምህር አደረግሁህ አለኝ።" ይህም ነቢይ የእግዚአብሔርን አምልኮና ሕጉን በመተዋቸው እንዲህ ሲል የእስራኤልን ልጆች ገሠጻቸው። ተጠበቁ ንስሐም ግቡ የእግዚአብሔር ቁጣው በላያችሁ እንዳይመጣ።
ሁለተኛም እንዲህ ብሎ አስረዳቸው ወደ ፈጣሪያችሁ እግዚአብሔር ካልተመለሳችሁ ያለዚያ የከላውዴዎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን በላያችሁ እርሱ ያሥነሣዋል ይማርካችኋልም እንደቃሉም ሆነ። ሁለተኛም ሕዝቡ ተማርከው ሰባ ዘመን እንደሚኖሩ ትንቢት ተናገረ።
ደግሞ የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ለኩነተ ሥጋ እንደሚመጣና መከራ እንደሚቀበል የአስቆሮቱ ይሁዳ እንደሚሸጠውና ሠላሳ ብር እንደሚወስድ ተናገረ። ስለ ብዙ ሥራዎችም ተናገረ አይሁድ ግን ሊገድሉት ወደው ገርፈው አሥረው በጒድጓድ ውሰጥ ጣሉት እግዚአብሔርም አዳነው። እርሱ ግን ስለእነርሱ ይለምንና ይማልድ ነበር እግዚአብሔርም ስለ እርሳቸው ወደእኔ አትማልድ እነርሱ ከክፋታቸው አይመለሱምና አለው።
ናቡከደነጾርም የኢየሩሳሌምን ሕዝብ በማረከ ጊዜ ከእሳቸው ጋራ አልማረከውም። ነገር ግን ከምርኮ የቀሩት ወደ ግብጽ አገር ወሰዱት የግብጽን ሰዎች ሲያጠፉአቸው የነበሩ በግብጽ ወንዞች የሚኖሩ አራዊትን በእርሱ ጸሎት እግዚአብሔር አጠፋቸው።
ከዚያም ወደ ባቢሎን አገር ወሰዱት በዚያም የእስራኤል ልጆች ከምርኮ እስኪመለሱ ትንቢት እየተናገረ ሕዝቡን ሲአስተምር ኖረ። የትንቢቱ ወራትም በተፈጸመ ጊዜ አይሁድ በደንጊያዎች ወገሩት ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። https://t.me/finotebirhan12
የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት
የደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ት/ቤት የተመሰረተበትን 55 ተኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል ከዛሬ ግንቦት 4/2015 ጀምሮ እስከ ግንቦት 21/2015 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ዝግጅቶች ያከብራል የክብረ በዓሉን የማብሰሪያ (መክፈቻ) መርሐ ግብር በዛሬው እለት ጀምረዋል።
በዚህምየጽ/ጽ/ሐ/ጎላ ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት እንኳን አደረሳችሁ አገልግሎታችሁ ለፍሬ ለበረከት እንዲሆን እንመኛለን።
ፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት
🔴#ስንክሳር ግንቦት_5
#ቅዱስ_ኤርምያስ_ነቢይ
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ግንቦት አምስት በዚች ቀን የካህኑ ኬልቅዩ ልጅ ታላቅ ነቢይ ኤርምያስ አረፈ። ይህም እውነተኛ ነቢይ የአሞጽ ልጅ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ሦስት ዓመቱ ማስተማር ጀመረ።
ከዚያም በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን ዐሠራ አንዱ የሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥቱ እስከሚፈጸም በአምስተኛው ወር ኢየሩሳሌም እስከ ተማረከችበት ጊዜ ያስተምር ነበር።
ስለ ራሱ እንዲህ ሲል ራሱ ተናገረ የእግዚአብሔር ቃል ወደኔ መጣ እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ "በእናትህ ማሕፀን ሳልፈጥርህ ወደድኩህ ከእናትህም ማሕፀን ሳትወጣ መረጥኩህ ለአሕዛብም መምህር አደረግሁህ አለኝ።" ይህም ነቢይ የእግዚአብሔርን አምልኮና ሕጉን በመተዋቸው እንዲህ ሲል የእስራኤልን ልጆች ገሠጻቸው። ተጠበቁ ንስሐም ግቡ የእግዚአብሔር ቁጣው በላያችሁ እንዳይመጣ።
ሁለተኛም እንዲህ ብሎ አስረዳቸው ወደ ፈጣሪያችሁ እግዚአብሔር ካልተመለሳችሁ ያለዚያ የከላውዴዎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን በላያችሁ እርሱ ያሥነሣዋል ይማርካችኋልም እንደቃሉም ሆነ። ሁለተኛም ሕዝቡ ተማርከው ሰባ ዘመን እንደሚኖሩ ትንቢት ተናገረ።
ደግሞ የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ለኩነተ ሥጋ እንደሚመጣና መከራ እንደሚቀበል የአስቆሮቱ ይሁዳ እንደሚሸጠውና ሠላሳ ብር እንደሚወስድ ተናገረ። ስለ ብዙ ሥራዎችም ተናገረ አይሁድ ግን ሊገድሉት ወደው ገርፈው አሥረው በጒድጓድ ውሰጥ ጣሉት እግዚአብሔርም አዳነው። እርሱ ግን ስለእነርሱ ይለምንና ይማልድ ነበር እግዚአብሔርም ስለ እርሳቸው ወደእኔ አትማልድ እነርሱ ከክፋታቸው አይመለሱምና አለው።
ናቡከደነጾርም የኢየሩሳሌምን ሕዝብ በማረከ ጊዜ ከእሳቸው ጋራ አልማረከውም። ነገር ግን ከምርኮ የቀሩት ወደ ግብጽ አገር ወሰዱት የግብጽን ሰዎች ሲያጠፉአቸው የነበሩ በግብጽ ወንዞች የሚኖሩ አራዊትን በእርሱ ጸሎት እግዚአብሔር አጠፋቸው።
ከዚያም ወደ ባቢሎን አገር ወሰዱት በዚያም የእስራኤል ልጆች ከምርኮ እስኪመለሱ ትንቢት እየተናገረ ሕዝቡን ሲአስተምር ኖረ። የትንቢቱ ወራትም በተፈጸመ ጊዜ አይሁድ በደንጊያዎች ወገሩት ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። https://t.me/finotebirhan12
ቅዱስ ሲኖዶስ በ3ኛ ቀን ውሎው
በተለያዩ ጉዳዮች ውሳኔ አሳልፏል።
ግንቦት ፬ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
""""""""""""""""""""
ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) ዕለታዊ ማብራሪያ የሰጡት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በሦስተኛ ቀን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በተመለከተ ውሳኔ ማሳለፉን ገልጸዋል።
በዚህም ብፁዕ አቡነ ዲዎስቆሮስ የደቡብ ትግራይ ማይጨው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊና መተከል ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቀደም ሲል ያገለግሉባቸው በነበሩ አህጉረ ስብከቶች አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ ጉባኤው ወስኗል።
ጉባኤው በዛሬው ውሎው እንዲነጋገርበት ተይዞ የነበረው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ጉዳይ የጉባኤው የመጨረሻ አጀንዳ እንዲሆን የአጀንዳ ሽግሽግ አድርጓል።
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) በሰጡት ዕለታዊ ማብራሪያ ጉባኤው የዋልድባ ዳልሻህ ኪዳነምሕረት ማህበረ ደናግል ገዳምን በተመለከተ፣ የያዘው አጀንዳ ላይ መወያየቱን እና ለውሳኔ በይደር መቆየቱን አረጋግጠዋል።
EOTC TV
ነው፡፡
ከዚህ በኋላም አባታችን ተክለ ሃይማኖት ሦስት የብርሃን አክሊሎችና የወርቅ ዘውድ ተቀዳጅቶ ተገለጠለት፡፡ የብርሃን ልብሶችን ለብሶ የመስቀል ምልክት ያለው በትርም ተመርኩዞ ፊቱም እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ መጣና ወደ አባታችን መልከ ጼዴቅ ቀርቦም "ልጄ ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን" አለው፡፡ አባታችን መልከ ጼዴቅም መልሶ "የእግዚአብሔር ሰላም ከአንተ ጋር ይሁን አንተ ማነህ አለው፡፡ "እኔ ከእናቴ ማኀፀን ጀምሮ መድኃኒዓለም የመረጠኝ ተክለ ሃይማኖት ብሎም የሰየመኝ ፍሰሐ ጽዮን ነኝ" አለው፡፡ ያንጊዜም ከእግሩ በታች ወደቅሁ ከኔ ጋር የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ አነሣኝ አቡነ ተክለ ሃይማኖት "የዳሞት ንጉሥ ሞተለሚ እንዴት እንዳደረገው የጣዖት ማምለኪያዎችን እንዴት እንዳጠፋ ብዙ ሰዎችን በክርስቶስ እንዴት እንደአሳመነ" ያን ጊዜ ነገረኝ፡፡
ስለዚህም "እግዚአብሔር አከበረኝ ከፍ ከፍ አደረገኝ፤ የብዙዎችም አባት አደረገኝ፤ ልጄ ሆይ አንተም ጸንተህ ተጋደል የብዙዎች አባት ትሆናለህ፤ እግዚአብሔር ለመጋደል ያበርታህ ሰላምንም ይስጥህ"፡፡ ይህንም ብሎ ከእርሱ ተሠወረ፡፡ ከርሱ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ አባታችን መልከ ጼዴቅ መጣና ወዳጄ ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን" አለው፡፡ መልከ ጼዴቅም "አንተ ማነህ" አለው፡፡ "እኔ የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ" አለው፡፡ ያን ጊዜም ከእግሩ በታች ወደቀ፡፡ ጌታችንም እጁን ይዞ፡፡ አነሣውና "ጽና አትፍራ" አለው፡፡ ያን ጊዜም እናቱ ድንግል ማርያም፣ ከቅዱስ ሚካኤልና ከቅዱስ ገብርኤል፣ ከሱራፌልና ከኪሩቤል ጋር ከነቢያት፣ ከሐዋርያት ጋር፣ ከጻድቃንና ከሰማዕታት ጋር መጣች መድኃኔዓለምም አባታችን መልከ ጼዴቅን "ከእናትህ ማኀፀን ጀምሮ በምስክር ሁሉ ፊት መረጥሁህ ካህንም አደረግሁህ ዛሬም የብዙዎቹ አባት አደርግሃለሁ፡፡ ኃጢአተኞችንም የምትመልስ ትሆናለህ፡፡ ያልጠቆረ ብሩህ አክሊልና በሰው እጅ ያልተሠሩ የብርሃን ልብሶችን እሰጥሃለሁ፡፡ ርስትህ ከአጥማቂዬ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ይሁን፤ ሹመትህም ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይና ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ጋር ይሁን፣ ስምህም የኔ ምሳሌ በሆነው መልከ ጼዴቅ ይሁን" አለው፡፡
የመጀመሪያው በጥምቀት የተሰጠው ስሙ ኀሩየ ወልድ (በወልድ የተመረ) የሚል ነበርና ያን ጊዜም ቁመታቸው እስከ ሰማይ የሚደርስ ብርሃናቸው እንደ ፀሐይ የሚያበራ፤ ሦስት የወርቅ መስቀሎችን ሰጠው" በላያቸው ላይ ውጣ" አለኝ፤ እኔም በእያንዳንዳቸው ላይ ሦስት ጊዜ ወጣሁ እስከ አርያምም አገቡኝ፡፡ በዚያም የእግዚአብሔርን መንበር አየሁ፡፡ በአንድነት በሦስትነት የሚኖር የዘመናት ጌታም በላይ ተቀምጧል፡፡ ይህም ነገር እጅግ ድንቅ ነው ወልድ በምድር ላይ ከእርሱ ጋራ እየተነጋገረ ሳለ በአርያም ደግሞ በሦስትነቱ ተቀምጦ አየሁ፡፡ ጌታም ሥርዓትህ እንዲሁ እንዳየኸው ይሁን፤ እስከ ዕለት ዕረፍትህም ድረስ ስለ ገድልህ ጽናት የሚሆን ሰጥቼሃለሁ" አለው፡፡ በጸሎቱ የተማጸነውን እንደሚምርለትና ሌላም ብዙ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡ "እኔም ከአንተ አልለይም፣ መላአክቶቼም ይጠብቁሃል" አለው፡፡ መልከ ጼዴቅም ይህንን በሰማ ጊዜ በፊቱ ሰገደ፡፡ "አቤቱ ለእኔ ለኃጢአተኛው አገልጋይህ ይህን ሁሉ ክብር የሰጠኸኝ ጌታ ሆይ መንግሥትህ ይባረክ" አለው፡፡ ጌታችንም ባርኮት በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ፡፡
አባታች መልከ ጼዴቅ እንደዝህ በብዙ ተጋድሎ ሲኖሩ ዕረፍታቸው ሲደርስ ትንሽ በተቅማጥ በሽታ ታመሙ ያንጊዜም ጌታችን እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ከቅዱሳን መላእክቶች ጋር መጣች፡፡ መላእክትንና ቀደምት አባቶችን፣ ነቢያትንና ሐዋርያትን፣ ጻደቃን ሰማዕታትን፣ ቀሳውስትና ዲያቆናትን፣ ደናግልና መነኮሳትን፣ ወንዶችንና ሴቶችን ሕፃናትንም ምስክሮች አድርጎ አቆመ፡፡ ሄሮድስ ያስገደላቸው 144,000 ሕፃናት ከአለቃቸው ከቅዱስ ቂርቆስ ጋር መጡ፡፡ "በእኔና በአንተ መካከል እነዚህ ሁሉ ምስክሮች ይሁኑ፤ ስምህን የጠራ፣ መታሰቢያህን ያደረገ፣ በእጅህ የተጠመቀ፣ በቃልህ የተናዘዘና በእጅህ የተሳለመ ምሬልሃለሁ፤ የገድልህን መጽሐፍ የጻፈውና ያጻፈውን ምሬልሃለሁ ከአንተም ጋር ርስት እሰጠዋለሁ፤ የቤትህ ልጆች መንግሥተ ሰማያትን ከአንተ ጋር ይውረሱ" አለው፡፡ ዳግመኛም "ለምህረት ያልጠራኋትን ነፍስ ለመሳለምም ሆነ ለመባረክ ወይም ለመናዘዝ ወደ አንተ አላቀርብም፤ ከኃጥአንም ወገን አንተ ስለ እነርሱ ከለመንኸኝ እምርልሃለሁ" ብሎ ቃል ኪዳን ገባላቸው። አባታችንም በዚህች ቀን ነፍሳቸው ከስጋቸው ተለየች።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ዮሐንስ_ሊቀ_ጳጳሳት
በዚህች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሀያ ዘጠነኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ አረፈ። እርሱም ከእስክንድርያ አገር ነው ከታናሽነቱም በአስቄጥስ በአባ መቃርስ ገዳም መንኲሶ በተጋድሎ ኖረ።
ከእርሱ አስቀድሞ የነበረ አባ አትናቴዎስም በአረፈ ጊዜ አዋቂዎች ኤጲስቆጶሳት ሕዝቡም ሁሉ መረጡት። ወስደውም በግድ ተሾም አሉት እርሱ ግን አልፈለገም የክርስቶስን መንጋ እንዳይተው ሌላ ተሹሞ በክርስቶስ መንጋዎች ላይ ጥፋት እንዳያመጣ ብዙ ልመናዎችን ለመኑት አዋቂዎች ኤጲስቆጶሳትና መምህራን ሁሉ አጽንተው ሲለምኑት በአየ ጊዜ ፈራ ይህ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ ይሆን ብሎ አሰበ።
ከዚህም በኋላ ሊቀ ጵጵስና ሾሙትና በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር ላይ ተቀመጠ። ስለ መንጋዎቹም ጥበቃ አሰበ ደግሞ ስለ ትምህርት መጻሕፍትንም ስለ ማንብበ በቀናች ሃይማኖትም የሚያጸናቸው ሆነ ምሁራን ካህናትንም ኤጲስቆጶሳትን አድርጎ ሾማቸው።
በዚያ ወራትም ስሙ ዘይኑን የሚባል እግዚአብሔርን የሚፈራ ደግ ንጉሥ ነበረ። ይህንንም ቅዱስ ስለረዳው ሥልጣኑ በሀገሮች ላይ ተዳረሰ የቀናች ሃይማኖትም በግብጽ አገሮች ሁሉ ላይ ተዘረጋች።
በዚያም ወራት ስንዴና ወይን ዘይትም የተመሉ ብዙ እንቅቦችን ለአብያተ ክርስቲያናትና ለገዳማት ለፍላጎታቸው ንጉሥ ዘይኑን ላከ። ለዚህም አባት ዘመኑ ሁሉ ጸጥታና ሰላም ሆነ። ጌታችንም በሥራው ሁሉ ተደሰተለት ከዚህም በኋላ በቸርነቱ ጐበኘውና ጥቂት ታመመ በሹመቱም ስምንት ዓመት ከኖረ በኋላ በሰላም አረፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።https://t.me/finotebirhan12
#🔴ስንክሳር ግንቦት_4
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ግንቦት አራት በዚህች ቀን ኢትዮዽያዊ ጻድቅ #አቡነ_መልከ_ጼዴቅ_ዘሚዳ ዕረፍታቸው ነው፣ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ዮሐንስ አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_መልከ_ጼዴቅ_ዘሚዳ
ግንቦት አራት በዚህች ቀን ኢትዮዽያዊ ጻድቅ አቡነ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ ዕረፍታቸው ነው፡፡ እኚህ ጻድቅ ከከበሩና ነገሥታት ከሆኑት ወገን በአገረ ጐጃም ኢናይ በምትባል ቦታ የካቲት አሥራ ስድስት ቀን ተወለዱ፡፡ ልደታቸውም እንዲህ ነበር፡፡
ንጉሥ አምደ ጽዮን ምስረነዓዳን ወለዱ፣ ምስረነዓዳም በዝራምበሳን ወለደች፣ በዝራምበሳም ፍሬጽዮንን ወለደ፣ ፍሬጽዮንም መልከ ጼዴቅን ወለደ የእናታቸውም ስም ቅድስት ዓመተ ማርያም ነው፡፡ በተወለዱም ጊዜም በአባትና በእናታቸው ቤት ታላቅ ደስታ ሆነ እግዚአብሔር ለብዙዎች አባት አድርጎ መርጦአቸዋልና፡፡
ለትምህርት በደረሱም ጊዜ መዝሙረ ዳዊት ይማሩ ዘንድ አባትና እናታቸው ለመምህር ሰጧቸው ፡፡ እርሳቸውም አምቢ ብለው ወደ አባትና እናታቸው ቤት ተመለሱ ፡፡ ፈረስ ጋላቢም ሆኑ፡፡ ደግሞ እኚህ ጻድቅ በጐለመሱ ጊዜ አባትና እናታቸው መልኳ የምታምር ሚስት አጩላቸው፡፡ የአባታቸውንም ሹመት የንጉሥ ሠራዊት አለቃ ሆነው ተሾሙ፡፡ በልባቸውም ሰሎሞን እንደተናገረው "ከፀሐይ በታች ያለው ሁሉ ከንቱ እንደሆነ አሰቡ" "በምድር ላይ ቋሚ የፀና ሕይወት የለምና" ይህንም ብለው ከአባትና ከእናታቸው ቤት ተሰደዱ፡፡ የእግዚአብሔርም መልአክ እየመራቸው ቅጽሮ ወደሚባል አገር ደረሱ የበሩም ጠባቂዎች አባታችን መልከ ጼዴቅን ከተሸከሟቸው ሁለት የወርቅ ልብሶች ጋር አቆሙአቸው "አትሻገር ተመለስ" አሏቸው፡፡ ያ የበር ጠባቂ የሆነ ሰውም "ለሌላው እስከምመለስ ጠብቀው" አላቸው ይህን ብሎም ይረዷቸው ዘንድ ጓደኞቹን ሊጠራ ሄደ የሚመራው መልአክም መልከ ጼዴቅ "ከወርቅህ ጋር ከዚህ ሂድ" አላቸው ልብሶቻቸውንም ተሸክመው ሄዱ፡፡ ይመራቸው የነበረ የእግዚአብሔር መልአክም እነዚህን የበርሃ ጠባቂዎች እንደ ድንጋይ የፈዘዙ እንደበድን የደነዘዙ አደረጋቸው፡፡ መናገርም ተሳናቸው፡፡
ከዚህ በኋላም የኢዮስያስ ቦታ ወደ ሆነችው ደጋዳሞት ደብረ ምዕራፍ ደረሱ፡፡ ከአባታችን ኢዮስያስ ቀጥሎ (በኋላ) በተሾሙት በአባታችን በአቡነ አሮን እጅ በዚያ መነኰሱ እርሳቸው አስቀድመው በስውር መንኩሰው ነበርና፡፡ አባታችን አቡነ አሮን ንዑድ ክቡር ለሚሆን መልከ ጼዴቅ የምንኩስናን ልብስ አለበሳቸው፡፡
ከዚህም በኋላ አባትና ወንድሞቹ ዘመዶቹም ኤናይ ከምትባል አገሩ እየፈለጉ መጡ፡፡ በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ተሰወራቸው አላገኙትም አባታችን አሮንንም ይዘው "ልጃችን አባት እናቱን እጮኛውንና ሹመቱን ትቶ ወደ አንተ መጥቷልና ስጠን" አሉት፡፡ አባታችን አሮንም ቅዱስ መልከ ጼዴቅ እንደመነኰሰ ነገራቸው፡፡ ያን ጊዜም አባትና እናቱ ወንድሞቹና ዘመዶቹ ታላቅ ለቅሶን አለቀሱ አዘኑ "ወዮልን ወዮልን ክብራችን ፈርሶአልና ኃይላችንም ተሽሮአልና ወልደን እንደ አልወለድንም ሆነናልና" አሉ፡፡ ከአባታችን ከአቡነ አሮን ጋር አስታረቋቸው አባቱም ያን ጊዜ "የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን" አለ አስቀድሞ ቅዱሳንን ሲጎበኝና ለነዳያን ሲራራላቸው ባየሁ ጊዜ ይህ ልጅ መነኩሴ እንደሚሆን በልቤ አስብ ነበር፡፡ ትተውትም ወደ አገራቸው ሄዱ፡፡ ከዚህ በኋላም የእግዚአብሔር መልአክ ክቡር መልከ ጼድቅን በዚያ ወስዶ ደብረ መድኃኒት አደረሳቸው፡፡ በዚያም ከቀሲስ አስጢፋኖስ የዳዊትን መዝሙርና የመጻሕፍትን ቃል እየተማሩ ተቀመጡ፡፡ ፈጥነውም ጨረሱ መንፈስ ቅዱስ በእርሳቸው ላይ ይናገራልና፡፡
ከዚህ በኋላ ከትንሽ ዋሻ ገቡ የአምላካቸውን የክርስቶስን መከራ በማሰብ በዚያ ገብተው ቀንና ሌሊት ዘግተው በረደኝ ፀሐይ ልሙቅ፣ ጨለመኝ ብርሃን ልይ ሳይሉ በጸሎት ብቻ ዘግተው በመኖር ራሳቸውን በችንካር እያቆሰሉና ጭንቅላታቸውን እያተሉ ትሉን ለሰማይ አእዋፍ ይመግቡ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ወልድ የተገረፈውን ግርፋት እያሰቡ በየቀኑ እስከ ሦስት ሺህ ድረስ ይሰግዳሉ፡፡ ሰውነታቸውንም እንዲሁ ይገርፋሉ፡፡ የክርስቶስን መቸንከር እያሰቡ እጅና እግራቸውን፣ ወገብና ደረታቸውን በብረት ቸንክረው መከራውን ያስባሉ፡፡
ጎኑ በጦር መወጋቱን አስበው አጥንታቸው እስኪሰበር ድረስ ጎናቸውን ወጉ፤ ሐሞትና ከርቤ መጠጣቱን አስበው እርሳቸውም መራራ ይጠጡና እንክርዳድን ይመገባሉ፤ ሞቱን አስበው ደም እንባን ያነባሉ፤ ብፁዕ መልከ ጼዴቅ በቀንና በሌሊት በጾምና በጸሎት ይጋደሉ ዘንድ ጀመሩ፡፡ የዳዊትን መዝሙር በየቀኑ ሦስት ጊዜ ይጸልዩ፣ እየተጋደሉም አርባ መዓልትን ቆዩ፤ ሌሊትም ራቁታቸውን ማቅ ብቻ ለብሰው ከባህር ውስጥ ይቆማሉ፡፡ በነጋም ጊዜ ወደ በዓታቸው ይመለሳሉ፡፡ በየዓመቱም አራት ጊዜ እንዲህ ያደርጋሉ፡፡ በየዓመቱም አርባ ቀን እህል ሳይበሉ ወይን ሳይጠጡ፣ ከቅጠልና ከእንጨት ፍሬ ከሣርም ፍሬ የፅዋው ቁመት በትንሽ ጣት ልክ ከተሰፈረ ጥቂት ውኃ በስተቀር እንደዚህ እየተጋደሉ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በደብረ መድኃኒት ሰባት ዓመት ኖሩ፡፡ የእግዚአብሔርም መልአክ ይጠብቃቸው ነበር፡፡ በእንደዚህ ዓይነቱ ተጋድሎ የክርስቶስን መከራ እያሰቡ ነቢያትን፣ ሐዋርያትን፣ ሰማዕታትን ደናግል መነኰሳትን መስለው ሁሉን እያከናወኑ እያለ የወዳጆቹን መከራ የማይዘነጋ፣ የሰውን የድካሙን ዋጋ ፈጽሞ የማያስቀር አምላክ ሠራዊተ መላእክትን አስከትሎ መጥቶ "መገረፍህ ስለ እኔ መገረፍ ይሁንልህ፤ የደምህ መፍሰስ ስለ እኔ ደም መፍሰስ ይሁንልህ፤ መቸንከርህም ስለ እኔ መቸንከር ይሁንልህ፤ ሞትህም ስለ እኔ ሞት ይሁንልህ" ብሎ ቃል ኪዳን ገባላቸው፡፡ "ከዚህ ቦታ መጥቶ የተሳለመውን እምርልሃለሁ ነፍሱ በአንተ ቃል ኪዳን የማይማር በአንተ ቦታ ለመሳለምም፣ ንሰሐ ለመግባትም ሆነ ለመቀበር አላቀርብብህም፣ መጥቶም የተቀበረውን ሥጋውን አፈር አይበላውም" የሚል እጅግ ድንቅ ቃል ኪዳን መድኃኒዓለም ሰጣቸው እስከ ዕለተ ምጽዓትም ሲታይ ይኖራል፡፡ በደጃቸው የተቀበረ ሰው አይበሰብስም፡፡
የእግዚአብሔር መልአክ አባታችን መልከ ጼጼቅን "በግራሪያ አገር ወደምትገኝ የቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ደብር ወደሆነች ወደ ደብረ ሊባኖስ ሂድ" አለው፡፡ አባታችን መልከ ጼዴቅም በዚህ መልአክ ትዕዛዝ ሄዱ ደብረ ሊባኖስ ደረሱና በዚያ እያሉ ቅዱሳንን እጅ ነሷቸው ከንቡረ ዕድ እንድርያስ ጋርም ተቀመጡ፡፡ ትንሽ ዋሻ በዓትን ሰጡዋቸውና "ትዕዛዛቱን ለመጠበቅ እግዚአብሔር ያጽናህ የገድልህንም ፍጻሜ ይሰጥህ" አላቸው፡፡ አባታችን እንድርያስ በእሱ ላይ በባረከ ጊዜም አባታችን መልከ ጼዴቅ ወደ በዓቱ ገብቶ ምስጋና ጸሎትና ስግደት ተግቶ ያዘ፡፡ እንደ መጀመሪያውም ታስሮ እያለ በየለቱ እስከ ሦስት ሺህ ስግደት ይሰግድ ነበር፡፡ ደሙም በምድር ላይ እስከሚፈስ ድረስ መንታ በሆነ የገመድ ጅራፍ ሰውነቱን ይገርፍ ነበር፡፡ እንባውም እንደክረምት ነጠብጣብ ይፈስ ነበር፤ የዓይኑ ብሌን እስኪገለበጥ ድረስ ያነባ ነበር፡፡ የሥጋውንም ቁስል እንደ መርፌ ሰርስሮ ወደ ውስጥ አካሉ እስኪገባ ድረስ በማቅ ፀጉር ይሰቀስቅና ይደመድም ነበር፡፡ እንዲህ ሆኖ መከራ ሲቀበልም ከእግዚአብሔር ምሥጋና ዝም አይልም ሥራውንም ፈጽሞ ያደንቅ ነበር፡፡ "ጌታ ሆይ የተኛሁትን አንቃኝ የደከምሁትን አበርታኝ የጨለምሁትን እኔን አብራልኝ" ይል ነበር፡፡ ይህንንም የሚለው ለራሱ ብቻ አይደለም ስለዓለም ሁሉ ነበር እንጅ እሱስ በኢየሩሳሌም ከሐዋርያት ጋርና በዓርያም ካሉ ከሱራፌል ጋር በክህነት የሚያገለግል ፍጹም ንጹሕና ጻድቅ ሰው
በኢየሩሳሌም ከሐዋርያት ጋርና በዓርያም ካሉ ከሱራፌል ጋር በክህነት የሚያገለግል ፍጹም ንጹሕና ጻድቅ ሰው

የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel):

የእግዚአብሔር መልአክ አባታችን መልከ ጼጼቅን "በግራሪያ አገር ወደምትገኝ የቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ደብር ወደሆነች ወደ ደብረ ሊባኖስ ሂድ" አለው፡፡ አባታችን መልከ ጼዴቅም በዚህ መልአክ ትዕዛዝ ሄዱ ደብረ ሊባኖስ ደረሱና በዚያ እያሉ ቅዱሳንን እጅ ነሷቸው ከንቡረ ዕድ እንድርያስ ጋርም ተቀመጡ፡፡ ትንሽ ዋሻ በዓትን ሰጡዋቸውና "ትዕዛዛቱን ለመጠበቅ እግዚአብሔር ያጽናህ የገድልህንም ፍጻሜ ይሰጥህ" አላቸው፡፡ አባታችን እንድርያስ በእሱ ላይ በባረከ ጊዜም አባታችን መልከ ጼዴቅ ወደ በዓቱ ገብቶ ምስጋና ጸሎትና ስግደት ተግቶ ያዘ፡፡ እንደ መጀመሪያውም ታስሮ እያለ በየለቱ እስከ ሦስት ሺህ ስግደት ይሰግድ ነበር፡፡ ደሙም በምድር ላይ እስከሚፈስ ድረስ መንታ በሆነ የገመድ ጅራፍ ሰውነቱን ይገርፍ ነበር፡፡ እንባውም እንደክረምት ነጠብጣብ ይፈስ ነበር፤ የዓይኑ ብሌን እስኪገለበጥ ድረስ ያነባ ነበር፡፡ የሥጋውንም ቁስል እንደ መርፌ ሰርስሮ ወደ ውስጥ አካሉ እስኪገባ ድረስ በማቅ ፀጉር ይሰቀስቅና ይደመድም ነበር፡፡ እንዲህ ሆኖ መከራ ሲቀበልም ከእግዚአብሔር ምሥጋና ዝም አይልም ሥራውንም ፈጽሞ ያደንቅ ነበር፡፡ "ጌታ ሆይ የተኛሁትን አንቃኝ የደከምሁትን አበርታኝ የጨለምሁትን እኔን አብራልኝ" ይል ነበር፡፡ ይህንንም የሚለው ለራሱ ብቻ አይደለም ስለዓለም ሁሉ ነበር እንጅ እሱስ
ቅዱስ ሲኖዶስ በ2ኛ ቀን ውሎው የተከፋፈለ ሲኖዶስ እንደሌለ እና ከዚህ ሐሳብ ውጪ የሆነ አካል ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት ውጪ የሆነ መሆኑን በመግለጽ መንግሥትን የሚያነጋግሩ ል ዑካን ሰይሟል።
በቅዱስ ሲኖዶስ በትግራይ ያሉ አባቶችና አባላቱን በአካል የሚያነጋግሩ ብፁዓን አባቶች ተመርጠው ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።
የ2015 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት የሁለተኛው ቀን ውሎን አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባባቢዋ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ማብራሪያ ሰጡ።
ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) ዕለታዊ ማብራሪያ የሰጡት ብፁዕነታቸው በሁለተኛው ቀን በነበረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ
ሁለት ርዕሰ ጉዳዮች መወያያየቱን ገልጸዋል።
ቅዱስ ሲኖዶስ በቀዳሚነት በሀገር ሰላም ዙሪያ በተነሳው ርዕሰ ጉዳይ ጉባኤው ብዙ ሲወያይ ከቆየ በኋላ በመጨረሻም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሁሉን ማድረግ ትችላለች ምእመናንም የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ድምጽ ይሰማሉ የሚለው ሐሳብ አሸንፎ በዚህ ጉዳይ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስን ወክለው የሚሰሩ ሦስት ብፁዓን አባቶች ተመርጠው የሀገር ሰላምን በተመለከተ ረዥም ርቀት በመሔድና ከሚመለከተው አካል ጋር ሁሉ በመነጋገር በሀገር ሰላም ዙሪያ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉና አሁን ካለንበት መከራ የምንወጣበትን መፍትሔ እንዲያመጡ ተመርጠዋል።
በቀጣይነት በወቅታዊ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ችግር አስመልክቶ በትግራይና በኦሮሚያ አህጉረ ስብከት የነበሩትን ችግሮች መነሻ በማድረግ
ሀ) በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት የትግራይ አባቶችና አባላቱን በአካል የሚያነጋግሩ ብፁዓን አባቶች ተመርጠው ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።
_ በተጨማሪም ተቋርጦ የነበረው በጀት እንዲለቀቅ
_ የማጽናኛ መርሐ ግብር እንዲካሄድና በተቻለ መጠን አስቸኳይ እርዳታ እንዲደረግ በጉባኤው ተወስኗል።
ለ) በጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም የተከሰተውን የቤተ ክርስቲያን ፈተና በተመለከተ
ሰፊ ውይይት ከተደረገ እና ወደ መግባቢያ ሐሳቦች መደረሱን ገልጸው
በስድስት አኅጉረ ስብከቶች ምንም ዓይነት የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እየተሰጠ አለመሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ የደረሰውን መረጃ መነሻ በማድረግ
የማያዳግም የመፍትሔ ለመስጠት ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው ከሦስቱ ብፁዓን አባቶች ጋር አራት ብፁዓን አባቶችን ተጨማሪ በማድረግ
በቀጥታ የነበረው ችግር ሙሉ በሙሉ መቀረፉንና ከአንድ ሲኖዶስ ውጪ ሌላ አለመኖሩን ለመንግሥት አካላት በጋራ ሔደው የተደረሰበትን ስምምነት ተገቢውን መረጃ እንዲሰጡ
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስን
ብፁዕ አቡነ ሩፋኤልን
ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስን
ብፁፅ አቡነ ሳዊሮስን
ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስን
እና ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስን
በመመደብ እነዚህ ሰባት ብፁዓን አባቶች በአንድ ላይ ከመንግሥት ጋር በመነጋገር ፍጹም በሆነ የመግባባት ስምምነት መፈጠሩን ገልጸው ከእንግዲህ በኋላ የተከፋፈለ ሲኖዶስ እንደሌለ እና ከዚህ ሐሳብ ውጪ የሆነ አካል ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት ውጪ የሆነ መሆኑን በአንድነት ለመንግሥት እንዲያሳውቁ መወከላቸውንም ገልጸዋል።
በቀጣይም ያሉንን የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮች በዚህ መልኩ በመግባባትና በመተማመን በመፍታት በሀገርና በቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሰላምና አንድነትን በማያዳግም ሁኔታ የሚያውጅ ቆይታ ይሆን ዘንድ መላው ሕዝበ ክርስቲያን በጸሎት አስቡን በማለት ብፁዕነታቸው አባታዊ መልእክታቸውንና ቡራኬአቸውን በመስጠት
የሁለተኛውን ቀን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሎ አጠር ባለ መልኩ ገልጸውልናል።
EOTC TV
ነው፡፡
ከዚህ በኋላም አባታችን ተክለ ሃይማኖት ሦስት የብርሃን አክሊሎችና የወርቅ ዘውድ ተቀዳጅቶ ተገለጠለት፡፡ የብርሃን ልብሶችን ለብሶ የመስቀል ምልክት ያለው በትርም ተመርኩዞ ፊቱም እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ መጣና ወደ አባታችን መልከ ጼዴቅ ቀርቦም "ልጄ ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን" አለው፡፡ አባታችን መልከ ጼዴቅም መልሶ "የእግዚአብሔር ሰላም ከአንተ ጋር ይሁን አንተ ማነህ አለው፡፡ "እኔ ከእናቴ ማኀፀን ጀምሮ መድኃኒዓለም የመረጠኝ ተክለ ሃይማኖት ብሎም የሰየመኝ ፍሰሐ ጽዮን ነኝ" አለው፡፡ ያንጊዜም ከእግሩ በታች ወደቅሁ ከኔ ጋር የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ አነሣኝ አቡነ ተክለ ሃይማኖት "የዳሞት ንጉሥ ሞተለሚ እንዴት እንዳደረገው የጣዖት ማምለኪያዎችን እንዴት እንዳጠፋ ብዙ ሰዎችን በክርስቶስ እንዴት እንደአሳመነ" ያን ጊዜ ነገረኝ፡፡
ስለዚህም "እግዚአብሔር አከበረኝ ከፍ ከፍ አደረገኝ፤ የብዙዎችም አባት አደረገኝ፤ ልጄ ሆይ አንተም ጸንተህ ተጋደል የብዙዎች አባት ትሆናለህ፤ እግዚአብሔር ለመጋደል ያበርታህ ሰላምንም ይስጥህ"፡፡ ይህንም ብሎ ከእርሱ ተሠወረ፡፡ ከርሱ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ አባታችን መልከ ጼዴቅ መጣና ወዳጄ ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን" አለው፡፡ መልከ ጼዴቅም "አንተ ማነህ" አለው፡፡ "እኔ የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ" አለው፡፡ ያን ጊዜም ከእግሩ በታች ወደቀ፡፡ ጌታችንም እጁን ይዞ፡፡ አነሣውና "ጽና አትፍራ" አለው፡፡ ያን ጊዜም እናቱ ድንግል ማርያም፣ ከቅዱስ ሚካኤልና ከቅዱስ ገብርኤል፣ ከሱራፌልና ከኪሩቤል ጋር ከነቢያት፣ ከሐዋርያት ጋር፣ ከጻድቃንና ከሰማዕታት ጋር መጣች መድኃኔዓለምም አባታችን መልከ ጼዴቅን "ከእናትህ ማኀፀን ጀምሮ በምስክር ሁሉ ፊት መረጥሁህ ካህንም አደረግሁህ ዛሬም የብዙዎቹ አባት አደርግሃለሁ፡፡ ኃጢአተኞችንም የምትመልስ ትሆናለህ፡፡ ያልጠቆረ ብሩህ አክሊልና በሰው እጅ ያልተሠሩ የብርሃን ልብሶችን እሰጥሃለሁ፡፡ ርስትህ ከአጥማቂዬ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ይሁን፤ ሹመትህም ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይና ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ጋር ይሁን፣ ስምህም የኔ ምሳሌ በሆነው መልከ ጼዴቅ ይሁን" አለው፡፡
የመጀመሪያው በጥምቀት የተሰጠው ስሙ ኀሩየ ወልድ (በወልድ የተመረ) የሚል ነበርና ያን ጊዜም ቁመታቸው እስከ ሰማይ የሚደርስ ብርሃናቸው እንደ ፀሐይ የሚያበራ፤ ሦስት የወርቅ መስቀሎችን ሰጠው" በላያቸው ላይ ውጣ" አለኝ፤ እኔም በእያንዳንዳቸው ላይ ሦስት ጊዜ ወጣሁ እስከ አርያምም አገቡኝ፡፡ በዚያም የእግዚአብሔርን መንበር አየሁ፡፡ በአንድነት በሦስትነት የሚኖር የዘመናት ጌታም በላይ ተቀምጧል፡፡ ይህም ነገር እጅግ ድንቅ ነው ወልድ በምድር ላይ ከእርሱ ጋራ እየተነጋገረ ሳለ በአርያም ደግሞ በሦስትነቱ ተቀምጦ አየሁ፡፡ ጌታም ሥርዓትህ እንዲሁ እንዳየኸው ይሁን፤ እስከ ዕለት ዕረፍትህም ድረስ ስለ ገድልህ ጽናት የሚሆን ሰጥቼሃለሁ" አለው፡፡ በጸሎቱ የተማጸነውን እንደሚምርለትና ሌላም ብዙ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡ "እኔም ከአንተ አልለይም፣ መላአክቶቼም ይጠብቁሃል" አለው፡፡ መልከ ጼዴቅም ይህንን በሰማ ጊዜ በፊቱ ሰገደ፡፡ "አቤቱ ለእኔ ለኃጢአተኛው አገልጋይህ ይህን ሁሉ ክብር የሰጠኸኝ ጌታ ሆይ መንግሥትህ ይባረክ" አለው፡፡ ጌታችንም ባርኮት በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ፡፡
አባታች መልከ ጼዴቅ እንደዝህ በብዙ ተጋድሎ ሲኖሩ ዕረፍታቸው ሲደርስ ትንሽ በተቅማጥ በሽታ ታመሙ ያንጊዜም ጌታችን እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ከቅዱሳን መላእክቶች ጋር መጣች፡፡ መላእክትንና ቀደምት አባቶችን፣ ነቢያትንና ሐዋርያትን፣ ጻደቃን ሰማዕታትን፣ ቀሳውስትና ዲያቆናትን፣ ደናግልና መነኮሳትን፣ ወንዶችንና ሴቶችን ሕፃናትንም ምስክሮች አድርጎ አቆመ፡፡ ሄሮድስ ያስገደላቸው 144,000 ሕፃናት ከአለቃቸው ከቅዱስ ቂርቆስ ጋር መጡ፡፡ "በእኔና በአንተ መካከል እነዚህ ሁሉ ምስክሮች ይሁኑ፤ ስምህን የጠራ፣ መታሰቢያህን ያደረገ፣ በእጅህ የተጠመቀ፣ በቃልህ የተናዘዘና በእጅህ የተሳለመ ምሬልሃለሁ፤ የገድልህን መጽሐፍ የጻፈውና ያጻፈውን ምሬልሃለሁ ከአንተም ጋር ርስት እሰጠዋለሁ፤ የቤትህ ልጆች መንግሥተ ሰማያትን ከአንተ ጋር ይውረሱ" አለው፡፡ ዳግመኛም "ለምህረት ያልጠራኋትን ነፍስ ለመሳለምም ሆነ ለመባረክ ወይም ለመናዘዝ ወደ አንተ አላቀርብም፤ ከኃጥአንም ወገን አንተ ስለ እነርሱ ከለመንኸኝ እምርልሃለሁ" ብሎ ቃል ኪዳን ገባላቸው። አባታችንም በዚህች ቀን ነፍሳቸው ከስጋቸው ተለየች።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ዮሐንስ_ሊቀ_ጳጳሳት
በዚህች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሀያ ዘጠነኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ አረፈ። እርሱም ከእስክንድርያ አገር ነው ከታናሽነቱም በአስቄጥስ በአባ መቃርስ ገዳም መንኲሶ በተጋድሎ ኖረ።
ከእርሱ አስቀድሞ የነበረ አባ አትናቴዎስም በአረፈ ጊዜ አዋቂዎች ኤጲስቆጶሳት ሕዝቡም ሁሉ መረጡት። ወስደውም በግድ ተሾም አሉት እርሱ ግን አልፈለገም የክርስቶስን መንጋ እንዳይተው ሌላ ተሹሞ በክርስቶስ መንጋዎች ላይ ጥፋት እንዳያመጣ ብዙ ልመናዎችን ለመኑት አዋቂዎች ኤጲስቆጶሳትና መምህራን ሁሉ አጽንተው ሲለምኑት በአየ ጊዜ ፈራ ይህ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ ይሆን ብሎ አሰበ።
ከዚህም በኋላ ሊቀ ጵጵስና ሾሙትና በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር ላይ ተቀመጠ። ስለ መንጋዎቹም ጥበቃ አሰበ ደግሞ ስለ ትምህርት መጻሕፍትንም ስለ ማንብበ በቀናች ሃይማኖትም የሚያጸናቸው ሆነ ምሁራን ካህናትንም ኤጲስቆጶሳትን አድርጎ ሾማቸው።
በዚያ ወራትም ስሙ ዘይኑን የሚባል እግዚአብሔርን የሚፈራ ደግ ንጉሥ ነበረ። ይህንንም ቅዱስ ስለረዳው ሥልጣኑ በሀገሮች ላይ ተዳረሰ የቀናች ሃይማኖትም በግብጽ አገሮች ሁሉ ላይ ተዘረጋች።
በዚያም ወራት ስንዴና ወይን ዘይትም የተመሉ ብዙ እንቅቦችን ለአብያተ ክርስቲያናትና ለገዳማት ለፍላጎታቸው ንጉሥ ዘይኑን ላከ። ለዚህም አባት ዘመኑ ሁሉ ጸጥታና ሰላም ሆነ። ጌታችንም በሥራው ሁሉ ተደሰተለት ከዚህም በኋላ በቸርነቱ ጐበኘውና ጥቂት ታመመ በሹመቱም ስምንት ዓመት ከኖረ በኋላ በሰላም አረፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።https://t.me/finotebirhan12
#🔴ስንክሳር ግንቦት_4
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ግንቦት አራት በዚህች ቀን ኢትዮዽያዊ ጻድቅ #አቡነ_መልከ_ጼዴቅ_ዘሚዳ ዕረፍታቸው ነው፣ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ዮሐንስ አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_መልከ_ጼዴቅ_ዘሚዳ
ግንቦት አራት በዚህች ቀን ኢትዮዽያዊ ጻድቅ አቡነ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ ዕረፍታቸው ነው፡፡ እኚህ ጻድቅ ከከበሩና ነገሥታት ከሆኑት ወገን በአገረ ጐጃም ኢናይ በምትባል ቦታ የካቲት አሥራ ስድስት ቀን ተወለዱ፡፡ ልደታቸውም እንዲህ ነበር፡፡
ንጉሥ አምደ ጽዮን ምስረነዓዳን ወለዱ፣ ምስረነዓዳም በዝራምበሳን ወለደች፣ በዝራምበሳም ፍሬጽዮንን ወለደ፣ ፍሬጽዮንም መልከ ጼዴቅን ወለደ የእናታቸውም ስም ቅድስት ዓመተ ማርያም ነው፡፡ በተወለዱም ጊዜም በአባትና በእናታቸው ቤት ታላቅ ደስታ ሆነ እግዚአብሔር ለብዙዎች አባት አድርጎ መርጦአቸዋልና፡፡
ለትምህርት በደረሱም ጊዜ መዝሙረ ዳዊት ይማሩ ዘንድ አባትና እናታቸው ለመምህር ሰጧቸው ፡፡ እርሳቸውም አምቢ ብለው ወደ አባትና እናታቸው ቤት ተመለሱ ፡፡ ፈረስ ጋላቢም ሆኑ፡፡ ደግሞ እኚህ ጻድቅ በጐለመሱ ጊዜ አባትና እናታቸው መልኳ የምታምር ሚስት አጩላቸው፡፡ የአባታቸውንም ሹመት የንጉሥ ሠራዊት አለቃ ሆነው ተሾሙ፡፡ በልባቸውም ሰሎሞን እንደተናገረው "ከፀሐይ በታች ያለው ሁሉ ከንቱ እንደሆነ አሰቡ" "በምድር ላይ ቋሚ የፀና ሕይወት የለምና" ይህንም ብለው ከአባትና ከእናታቸው ቤት ተሰደዱ፡፡ የእግዚአብሔርም መልአክ እየመራቸው ቅጽሮ ወደሚባል አገር ደረሱ የበሩም ጠባቂዎች አባታችን መልከ ጼዴቅን ከተሸከሟቸው ሁለት የወርቅ ልብሶች ጋር አቆሙአቸው "አትሻገር ተመለስ" አሏቸው፡፡ ያ የበር ጠባቂ የሆነ ሰውም "ለሌላው እስከምመለስ ጠብቀው" አላቸው ይህን ብሎም ይረዷቸው ዘንድ ጓደኞቹን ሊጠራ ሄደ የሚመራው መልአክም መልከ ጼዴቅ "ከወርቅህ ጋር ከዚህ ሂድ" አላቸው ልብሶቻቸውንም ተሸክመው ሄዱ፡፡ ይመራቸው የነበረ የእግዚአብሔር መልአክም እነዚህን የበርሃ ጠባቂዎች እንደ ድንጋይ የፈዘዙ እንደበድን የደነዘዙ አደረጋቸው፡፡ መናገርም ተሳናቸው፡፡
ከዚህ በኋላም የኢዮስያስ ቦታ ወደ ሆነችው ደጋዳሞት ደብረ ምዕራፍ ደረሱ፡፡ ከአባታችን ኢዮስያስ ቀጥሎ (በኋላ) በተሾሙት በአባታችን በአቡነ አሮን እጅ በዚያ መነኰሱ እርሳቸው አስቀድመው በስውር መንኩሰው ነበርና፡፡ አባታችን አቡነ አሮን ንዑድ ክቡር ለሚሆን መልከ ጼዴቅ የምንኩስናን ልብስ አለበሳቸው፡፡
ከዚህም በኋላ አባትና ወንድሞቹ ዘመዶቹም ኤናይ ከምትባል አገሩ እየፈለጉ መጡ፡፡ በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ተሰወራቸው አላገኙትም አባታችን አሮንንም ይዘው "ልጃችን አባት እናቱን እጮኛውንና ሹመቱን ትቶ ወደ አንተ መጥቷልና ስጠን" አሉት፡፡ አባታችን አሮንም ቅዱስ መልከ ጼዴቅ እንደመነኰሰ ነገራቸው፡፡ ያን ጊዜም አባትና እናቱ ወንድሞቹና ዘመዶቹ ታላቅ ለቅሶን አለቀሱ አዘኑ "ወዮልን ወዮልን ክብራችን ፈርሶአልና ኃይላችንም ተሽሮአልና ወልደን እንደ አልወለድንም ሆነናልና" አሉ፡፡ ከአባታችን ከአቡነ አሮን ጋር አስታረቋቸው አባቱም ያን ጊዜ "የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን" አለ አስቀድሞ ቅዱሳንን ሲጎበኝና ለነዳያን ሲራራላቸው ባየሁ ጊዜ ይህ ልጅ መነኩሴ እንደሚሆን በልቤ አስብ ነበር፡፡ ትተውትም ወደ አገራቸው ሄዱ፡፡ ከዚህ በኋላም የእግዚአብሔር መልአክ ክቡር መልከ ጼድቅን በዚያ ወስዶ ደብረ መድኃኒት አደረሳቸው፡፡ በዚያም ከቀሲስ አስጢፋኖስ የዳዊትን መዝሙርና የመጻሕፍትን ቃል እየተማሩ ተቀመጡ፡፡ ፈጥነውም ጨረሱ መንፈስ ቅዱስ በእርሳቸው ላይ ይናገራልና፡፡
ከዚህ በኋላ ከትንሽ ዋሻ ገቡ የአምላካቸውን የክርስቶስን መከራ በማሰብ በዚያ ገብተው ቀንና ሌሊት ዘግተው በረደኝ ፀሐይ ልሙቅ፣ ጨለመኝ ብርሃን ልይ ሳይሉ በጸሎት ብቻ ዘግተው በመኖር ራሳቸውን በችንካር እያቆሰሉና ጭንቅላታቸውን እያተሉ ትሉን ለሰማይ አእዋፍ ይመግቡ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ወልድ የተገረፈውን ግርፋት እያሰቡ በየቀኑ እስከ ሦስት ሺህ ድረስ ይሰግዳሉ፡፡ ሰውነታቸውንም እንዲሁ ይገርፋሉ፡፡ የክርስቶስን መቸንከር እያሰቡ እጅና እግራቸውን፣ ወገብና ደረታቸውን በብረት ቸንክረው መከራውን ያስባሉ፡፡
ጎኑ በጦር መወጋቱን አስበው አጥንታቸው እስኪሰበር ድረስ ጎናቸውን ወጉ፤ ሐሞትና ከርቤ መጠጣቱን አስበው እርሳቸውም መራራ ይጠጡና እንክርዳድን ይመገባሉ፤ ሞቱን አስበው ደም እንባን ያነባሉ፤ ብፁዕ መልከ ጼዴቅ በቀንና በሌሊት በጾምና በጸሎት ይጋደሉ ዘንድ ጀመሩ፡፡ የዳዊትን መዝሙር በየቀኑ ሦስት ጊዜ ይጸልዩ፣ እየተጋደሉም አርባ መዓልትን ቆዩ፤ ሌሊትም ራቁታቸውን ማቅ ብቻ ለብሰው ከባህር ውስጥ ይቆማሉ፡፡ በነጋም ጊዜ ወደ በዓታቸው ይመለሳሉ፡፡ በየዓመቱም አራት ጊዜ እንዲህ ያደርጋሉ፡፡ በየዓመቱም አርባ ቀን እህል ሳይበሉ ወይን ሳይጠጡ፣ ከቅጠልና ከእንጨት ፍሬ ከሣርም ፍሬ የፅዋው ቁመት በትንሽ ጣት ልክ ከተሰፈረ ጥቂት ውኃ በስተቀር እንደዚህ እየተጋደሉ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በደብረ መድኃኒት ሰባት ዓመት ኖሩ፡፡ የእግዚአብሔርም መልአክ ይጠብቃቸው ነበር፡፡ በእንደዚህ ዓይነቱ ተጋድሎ የክርስቶስን መከራ እያሰቡ ነቢያትን፣ ሐዋርያትን፣ ሰማዕታትን ደናግል መነኰሳትን መስለው ሁሉን እያከናወኑ እያለ የወዳጆቹን መከራ የማይዘነጋ፣ የሰውን የድካሙን ዋጋ ፈጽሞ የማያስቀር አምላክ ሠራዊተ መላእክትን አስከትሎ መጥቶ "መገረፍህ ስለ እኔ መገረፍ ይሁንልህ፤ የደምህ መፍሰስ ስለ እኔ ደም መፍሰስ ይሁንልህ፤ መቸንከርህም ስለ እኔ መቸንከር ይሁንልህ፤ ሞትህም ስለ እኔ ሞት ይሁንልህ" ብሎ ቃል ኪዳን ገባላቸው፡፡ "ከዚህ ቦታ መጥቶ የተሳለመውን እምርልሃለሁ ነፍሱ በአንተ ቃል ኪዳን የማይማር በአንተ ቦታ ለመሳለምም፣ ንሰሐ ለመግባትም ሆነ ለመቀበር አላቀርብብህም፣ መጥቶም የተቀበረውን ሥጋውን አፈር አይበላውም" የሚል እጅግ ድንቅ ቃል ኪዳን መድኃኒዓለም ሰጣቸው እስከ ዕለተ ምጽዓትም ሲታይ ይኖራል፡፡ በደጃቸው የተቀበረ ሰው አይበሰብስም፡፡
የእግዚአብሔር መልአክ አባታችን መልከ ጼጼቅን "በግራሪያ አገር ወደምትገኝ የቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ደብር ወደሆነች ወደ ደብረ ሊባኖስ ሂድ" አለው፡፡ አባታችን መልከ ጼዴቅም በዚህ መልአክ ትዕዛዝ ሄዱ ደብረ ሊባኖስ ደረሱና በዚያ እያሉ ቅዱሳንን እጅ ነሷቸው ከንቡረ ዕድ እንድርያስ ጋርም ተቀመጡ፡፡ ትንሽ ዋሻ በዓትን ሰጡዋቸውና "ትዕዛዛቱን ለመጠበቅ እግዚአብሔር ያጽናህ የገድልህንም ፍጻሜ ይሰጥህ" አላቸው፡፡ አባታችን እንድርያስ በእሱ ላይ በባረከ ጊዜም አባታችን መልከ ጼዴቅ ወደ በዓቱ ገብቶ ምስጋና ጸሎትና ስግደት ተግቶ ያዘ፡፡ እንደ መጀመሪያውም ታስሮ እያለ በየለቱ እስከ ሦስት ሺህ ስግደት ይሰግድ ነበር፡፡ ደሙም በምድር ላይ እስከሚፈስ ድረስ መንታ በሆነ የገመድ ጅራፍ ሰውነቱን ይገርፍ ነበር፡፡ እንባውም እንደክረምት ነጠብጣብ ይፈስ ነበር፤ የዓይኑ ብሌን እስኪገለበጥ ድረስ ያነባ ነበር፡፡ የሥጋውንም ቁስል እንደ መርፌ ሰርስሮ ወደ ውስጥ አካሉ እስኪገባ ድረስ በማቅ ፀጉር ይሰቀስቅና ይደመድም ነበር፡፡ እንዲህ ሆኖ መከራ ሲቀበልም ከእግዚአብሔር ምሥጋና ዝም አይልም ሥራውንም ፈጽሞ ያደንቅ ነበር፡፡ "ጌታ ሆይ የተኛሁትን አንቃኝ የደከምሁትን አበርታኝ የጨለምሁትን እኔን አብራልኝ" ይል ነበር፡፡ ይህንንም የሚለው ለራሱ ብቻ አይደለም ስለዓለም ሁሉ ነበር እንጅ እሱስ በኢየሩሳሌም ከሐዋርያት ጋርና በዓርያም ካሉ ከሱራፌል ጋር በክህነት የሚያገለግል ፍጹም ንጹሕና ጻድቅ ሰው
🔴#ስንክሳር ግንቦት_3
#ቅዱስ_ያሶን_ሐዋርያ
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ግንቦት ሦስት በዚች ቀን ጌታ ከመረጣቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የሆነ ሐዋርያው ቅዱስ ያሶን አረፈ። ይህም ቅዱስ ከሐዋርያት ጋራ ወንጌልን በሰበከ ጊዜ ብዙ መከራዎችን በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተቀበለ ድንቆች ተአምራትንም አደረገ በሃምሳኛው ቀን ከሐዋርያት ጋራ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሏልና።
ትውልዱም ከጠርሴስ አገር ነው ከጠርሴስም ሰዎች አስቀድሞ አመነ ሐዋርያ ጳውሎስም ከተጠራና ከአመነ በኋላ በብዙ አገሮች ተከትሎ በወንጌል ትምህርት አገለገለው በተሰሎንቄ ከተማም ከጳውሎስ ጋራ ይዘው በመጐተት ከተሰሎንቄ ገዢ ዘንድ አቀረቡአቸው።
ከዚህም በኋላ በጠርሴስ አገር ቅዱስ ጳውሎስ ኤጲስቆጶስነት ሾመው የወልደ እግዚአብሔርንም ቤተ ክርስቲያን በመልካም አጠባበቅ በቅንነት ጠበቀ። ምእመናንን በቀናች ሃይማኖት ከአጸናቸውና በጎ ምግባርን ከአስተማራቸው በኋላ ከዚያ ወደ ምዕራብ አገር ሒዶ በውስጥዋ የከበረ ወንጌልን አስተማረ። ስሟ ኮራኮራስ ወደምትባል ደሴትም ደርሶ በውስጧ ወንጌልን ሰበከ እግዚአብሔርንም ወደማወቅ መለሳቸው በዲያቆናት አለቃ በሰማዕታትም መጀመሪያ በከበረ ሐዋርያ እስጢፋኖስ ስም በውስጧ ቤተ ክርስቲያን ሠራላቸው።
የዚያች አገር ገዥም በአወቀ ጊዜ ይዞ ከእሥር ቤት አስገባው በዚያም ሰባት ወንበዴዎችን አግኝቶ ሃይማኖትን አስተማራቸው በክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው። ከዚያም በኋላ በመኮንኑ ፊት ቁመው እኛ ክርስቲያን ነን በክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን ብለው ጮኹ። መኰንኑም ዝፍትና ዲን በተመላ ምጣድ ውስጥ አግብቶ አቃጠላቸው የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ ያሶንን ከእሥር ቤት አውጥቶ ብዙ አሠቃየው ነገር ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰበትም። የንጉሡም ልጅ ከቤቷ መስኮት ሁና አይታ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነች ልብሶቿንና ጌጦቿን አውጥታ ለድኆችና ለምስኪኖች ሰጠችና ከዚያም በሐዋርያው በያሶን አምላክ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ታመነች አባቷም ሰምቶ እንዲአሥሩዋት አዘዘ እንዳዘዛቸውም አደረጉ። በጢስም አፍነው አሠቃዩዋት ደግመውም አራቈቷትና አባቷ በፍላፃ ነደፋት ነፍሷንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠች።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ ያሶንን ወደ ደሴት ሰደደው በደሴትም ውስጥ ያሠቃየው ዘንድ መኰንኑ ከሠራዊቱ ጋራ አብሮ በመርከብ ተሳፈረ እግዚአብሔርም ከሠራዊቱ ጋራ በባሕር አሠጠመው።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ ያሶን ወንጌልን እያስተማረ ብዙ ዘመናት ኖረ። ሁለተኛም ሌላ መኰንን ተሾመ ቅዱስ ያሶንንም ይዞ በምጣድም ውስጥ ድኝና ዝፍት ሰም መልቶ ነበልባሉ ወደ ላይ እስቲወጣ ድረስ ከበታቹ አነደደ ቅዱስ ያሶንንም በውስጡ ጨመረው። የክብር ባለቤት ጌታችንም አዳነው ምንም ምን ጉዳት አልደረሰበትም መኰንኑም ይህን ድንቅ ሥራ አይቶ በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቤተሰቡ ሁሉ ከሀገር ሰዎች ሁሉ ጋራ አመነ። ሁሉንም አጥምቆ የከበረ የወንጌልን ሕግና ትእዛዝ አስተማራቸው አብያተ ክርስቲያንም ሠራላቸው በውስጣቸውም ብዙ ድንቆች ተአምራትን አደረገ ብሩህ በሆነ ገድሉ ጌታችንን ደስ ካሰኘውና ካገለገለው በኋላ በበጎ ሽምግልና አረፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን።https://t.me/finotebirhan12
اکنون در دسترس! پژوهش تلگرام ۲۰۲۵ — مهمترین بینشهای سال 