2 938
مشترکین
+124 ساعت
-87 روز
-830 روز
آرشیو پست ها
ቲክቶክ «አምስት ደቂቃ ብቻ ልይ» ብላችሁ ከፍታችሁት ሳይታወቃችሁ ሰዓታትን የሚውጥ አደገኛ ወጥመድ ነው።አፕልኬሽኑ ራሱ የተሰራው አእምሮን በፈጣን ደስታ እያደነዘዘ ሰውን ስክሪን ላይ ጠፍሮ ለማስቀረት ነው።
ትልቁ አደጋው ጊዜ ማባከኑ ብቻ ሳይሆን፦
- አእምሮ ረዘም ላሉና ትዕግስት ለሚጠይቁ ሥራዎች እንዳይዘጋጅ ያደርጋል።
- የሌሊት እረፍትን በማዛባት የቀን ንቃትን ያጠፋል።
- የሌሎችን የተጋነነ ኑሮ እያሳየ በራስ ሕይወት ላይ ስንፍናን ይዘራል።
በማይረቡ ቪዲዮዎች ላይ በከንቱ የሚፈሰው እያንዳንዱ ሰከንድ ነገ የማይመለስ የዕድሜያችሁ ውድ ካፒታል ነው። ስልኩን እናንተ ካልገዛችሁት፣ እሱ ሕይወታችሁን በከንቱ ይገዛዋል፤ ስለዚህ ወይ ገደብ አበጁለት፣ አለበለዚያ ሙሉ በሙሉ ሰርዛችሁ በሰላም ኑሩ!
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1
🕌 የደሴ መስጂደ አስ-ሱና የእርዳታ ጥሪ!
ዛሬ የምናበረክተው የነገውን የዕውቀት ብርሃን ለማስፋት ነው!
በአላህ ፈቃድ የሚተላለፍ የዒልም ብርሃን፤ ከዱንያ ሕይወታችን በኋላም የሚቀጥል ሰደቀተል ጃሪያ ነው!
📢 ለዓለም ዙሪያ ለምትገኙ ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሙሉ የተላለፈ የኸይር ጥሪ!
በደሴ ከተማ የሰለፊዮች ዐይን ፣ የሱና ብርሃን መፍለቂያ እና የቁርአንና የሸሪዓ ዕውቀት መማሪያ የሆነችው መስጂደ አስ-ሱና ዛሬ በእናንተ እገዛ የሚታሰብ ታሪክ ለመሥራት በር ከፍታለች!
በቅርብ ጊዜ ይህ መስጂድ በትንሽ ቦታ፣ ቆርቆሮ በቆርቆሮ በትንሽ ቦታ ላይ ፣ በትንሽ አቅምና በታላቅ ተስፋ ተጀመረች። በሸይኽ መሐመድ መኪን መሪነት የተለያዩ ቂርኣቶች፣ የዳዕዋ ፕሮግራሞች፣ የዒልም ደርሶችና የኮርስ ትምህርቶች ሲሰጡባት ቆይተዋል።
በዚያ ትንሽ ቦታ ውስጥ የአላህ ቃል ተነብቧል፤ የነቢዩ ﷺ ሱና ተምሯል፤ የዒልም ተማሪዎች ተቀምጠዋል፤ የብዙ ሕፃናትም ልብ በቁርአን ብርሃን እንዲበራ ጥረት ተደርጓል።
ነገር ግን፣ አልሐምዱ ሊላህ! ዛሬ በዚህች መስጂድ የሚቀሩ ሕፃናት ቁጥር እጅግ ጨምሯል። ይህ የሚያስደስት የኸይር ዜና ቢሆንም፣ የሚማሩበት ቦታ መድረሳ ጠባብ በመሆኑ ትልቅ ፈተና ሆኗብናል።
ዛሬ በዚያ ጠባብ መድረሳ ውስጥ የሚቀመጡት ሕፃናት የነገው የኡማችን ተስፋዎች ናቸው። ከእነርሱ መካከል የቁርአን ሐፊዞች፣ የሐዲስ ዕውቀት ተሸካሚዎች፣ የሱና ጥሪ አስተላላፊዎችና ለእስልምና የሚጠቅሙ የዒልም ሰዎች ሊወጡ ይችላሉ።
እነዚህ ሕፃናት የአላህን መጽሐፍ በሰፊ ቦታ፣ በተመቻቸ አካባቢና በተሻለ የመማሪያ ሁኔታ እንዲማሩ ማድረግ የእኛ የዛሬ ኃላፊነት ነው።
⚠️ ወዳጆቻችን ሆይ! የዚህ ታላቅ ኸይር ተባባሪዎች እንሁን!
የመስጂደ አስ-ሱናን የመማሪያ ቦታ ለማስፋፋት፣ ሕፃናቱ የሚቀሩበትን መድረሳ ለማሻሻልና የቁርአንና የሱና ትምህርት የበለጠ እንዲስፋፋ ለማድረግ የእናንተን ድጋፍ እንሻለን።
አንዳንዶቻችን ብዙ ልናዋጣ እንችላለን፤ ሌሎቻችን ደግሞ ትንሽ ልናዋጣ እንችላለን። ነገር ግን በአላህ ዘንድ የሚቀበለው በቁጥር ብቻ የሚለካ ሳይሆን በኢኽላስና በመልካም ዓላማ የሚመዘን ነው።
በትንሽ አቅማችሁ ትልቅ ለውጥ ማምጣት ትችላላችሁ!
አንድ ሕፃን በእናንተ ድጋፍ ቁርአንን በትክክል ቢያነብ፣ አንድ ተማሪ ትክክለኛ የዲኑን ዕውቀት ቢያገኝ፣ አንድ ልጅ የተማረውን ዕውቀት ለሌሎች ቢያስተላልፍ፣ የእናንተ እገዛ በዚህ መልካም ሥራ ውስጥ ድርሻ እንዲኖረው አላህ ሊያደርግ ይችላል።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«إِذَا مَاتَ الْإِنْسَانُ انْقَطَعَ عَنْهُ عَمَلُهُ إِلَّا مِنْ ثَلَاثَةٍ: إِلَّا مِنْ صَدَقَةٍ جَارِيَةٍ، أَوْ عِلْمٍ يُنْتَفَعُ بِهِ، أَوْ وَلَدٍ صَالِحٍ يَدْعُو لَهُ».
“የሰው ልጅ በሞተ ጊዜ ሥራው ይቋረጣል፤ ከሦስት ነገሮች በስተቀር፦ የሚቀጥል ሰደቃ፣ ከእርሱ የሚጠቀምበት ዕውቀት፣ ለእርሱ ዱዓ የሚያደርግ መልካም ልጅ።”
📚 ሰሒሕ ሙስሊም፣ 1631
ወንድሞችና እህቶች ሆይ! ዛሬ በመስጂድ ማስፋፊያ ላይ የምናዋጣው ገንዘብ የዛሬ ድጋፍ ብቻ አይደለም። በዚያ ቦታ ቁርአን ሲነበብ፣ የአላህ ዲን ሲማር፣ ልጆች ሲያድጉና የሚጠቅም ዕውቀት ሲተላለፍ፣ አላህ ከምሕረቱ ድርሻ እንዲያደርግልን የምንሻበት ታላቅ እድል ነው።
እኛ እዚህ ምድር ላይ ለዘላለም አንኖርም። ነገር ግን በኢኽላስ የተሠራ መልካም ሥራ አላህ ከተቀበለው፣ ከሞታችን በኋላም የምንጠብቀው የኸይር ምክንያት ሊሆን ይችላል።
ስለዚህ ዛሬ የምንችለውን እናድርግ፤ የምንችለውን እናዋጣ፤ ሌሎችም እንዲሳተፉ እንጋብዝ። ምናልባት በእኛ የተነሳ የአላህ ዲን የሚማሩ ልጆች ቁጥር ይጨምር ይሆናል።
⚠️ዛሬ የእናንተ ድጋፍ የእነዚህ ሕፃናት ተስፋ ነው!
🌍 በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በዓለም ዙሪያ ለምትኖሩ ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን፦ በዚህ የኸይር ሥራ ላይ የቻላችሁትን ያህል ድጋፍ እንድታደርጉልን በአላህ ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የምትሰጡት ትንሽ ቢመስልም አትናቁት። የምታደርጉት ድጋፍ በአላህ ፈቃድ ለብዙ ሕፃናት የዒልም መንገድ ሊያመቻች ይችላል። ካልቻላችሁ ደግሞ ይህን ጥሪ ለሌሎች በማድረስ ተባበሩን። የኸይርን መንገድ የሚያመለክትም ከሠሪው ምንዳ ያገኛል።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🏦 የመስጂደ አስ-ሱና የባንክ ሂሳቦች
💳 1. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)
1000469830277
💳 2. ዘምዘም ባንክ
0005649620101
💳 3. ሂጅራ ባንክ
1000030300001
📌 ከላይ የተጠቀሱት የባንክ ሂሳቦች በመስጂደ አስ-ሱና ስም የተመዘገቡ ናቸው።
ስለ መስጅዱ ሙሉ መረጃ ለማገኘትና ለመጠየቅ
ስልክ፦+251914718693
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
📣 ይህን መልእክት ሼር በማድረግ ለመስጂደ አስ-ሱና ማስፋፊያ የሚያግዙ ወንድሞችና እህቶች እንዲደርሱ እንርዳ!
🕌 በመስጂደ አስ-ሱና — ላይ የማናደርገው የዛሬው ድጋፋችን፣ የነገው የዒልም ብርሃን ያሰፋል!
⭕️👉የደሴው ፕሮግራም ተጀምሯል
🎤ሸይኽ ዒማም ሰዒድ (ሀፊዘሁሏህ)ገብተዋል
https://t.me/Sobabilalmesjid?livestream=7999dc7c2d359e4b1c
✨ የደስታችን ተካፋይ ይሁኑ!
— ታላቅ የኒያ እና የዳዕዋ ፕሮግራም ✨
በአላህ ፈቃድ በደሴ ከተማ ልዩና ታላቅ የኒያ እና የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቶልዎታል!
📅 ቀን፦ እሁድ — ጥቅምት 1 / 2019 ዓ.ል
💢 ቦታ፦ ደሴ — መስጂደ አስ-ሱና
⏰ ሰዓት፦ ከጧቱ — 2:30
🎙 በፕሮግራሙ ላይ የሚገኙ የተከበሩ ዑስታዞች፣ ሸይኾችና ወንድሞች፦
1) ሸይኽ ሙሐመድ መኪን
2) ሸይኽ ሙሐመድ አሚን
3) ሸይኽ ሙሐመድ ኋዛል
4) ሸይኽ ሙሐመድ ሰዒድ
5) ሸይኽ ሐሰን አሊ
6)ሸይኽ አሕመድ አወቀ
7) ሸይኽ ጀማል ዘሀቢ
8) ሸይኽ ይማም ሰዒድ
9) ሸይኽ ሰዒድ ሙሐመድ ሚጢቆሎ)
10)ሸይኽ አብዱልአዚዝ
11)ሸይኽ በድሩዲን ዩሱፍ
12) ሸይኽ ሑሴን ኡመር
13) ሸይኽ ሐሰን ነጃሽ
( ከወንዲሞች)
14) ወንድም ሙርሰል ሰዒድ
15) ወንድም ኢዘዲን ሻፊ
16) ወንድም አቡ ሹራ
17) ወንድም አቡ ሒበቲላህ
18) ወንድም አቡ ሐፍሷ (ይማም)
19) ወንድም አሊ ሰዒድ
20) ወንድም አቡ ኢምራን
(እንዲሁም ሌሎች በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው ዑስታዞችና ወንድሞች ይገኛሉ)
📢 ልዩ ጥሪ፦
ይህንን መልእክት ለሌሎች በማጋራትና በዕለቱ በአካል በመገኘት የዚህ ታላቅ በረካና ደስታ ተካፋይ ይሁኑ!
📌 ለሁሉም እንግዶች ጥሪያችን ክፍት ነው!
ቻናልhttps://t.me/yedesse_selfyochi_yedewa_channel
ግሩፕhttps://t.me/yedesse_selfyochi_group
ሼር ይደረግ‼
✨ የደስታችን ተካፋይ ይሁኑ!
— ታላቅ የኒያ እና የዳዕዋ ፕሮግራም ✨
በአላህ ፈቃድ በደሴ ከተማ ልዩና ታላቅ የኒያ እና የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቶልዎታል!
📅 ቀን፦ እሁድ — ጥቅምት 1 / 2019 ዓ.ል
💢 ቦታ፦ ደሴ — መስጂደ አስ-ሱና
⏰ ሰዓት፦ ከጧቱ — 2:30
🎙 በፕሮግራሙ ላይ የሚገኙ የተከበሩ ዑስታዞች፣ ሸይኾችና ወንድሞች፦
1) ሸይኽ ሙሐመድ መኪን
2) ሸይኽ ሙሐመድ አሚን
3) ሸይኽ ሙሐመድ ኋዛል
4) ሸይኽ ሙሐመድ ሰዒድ
5) ሸይኽ ሐሰን አሊ
6)ሸይኽ አሕመድ አወቀ
7) ሸይኽ ጀማል ዘሀቢ
8) ሸይኽ ይማም ሰዒድ
9) ሸይኽ ሰዒድ ሙሐመድ ሚጢቆሎ)
10)ሸይኽ አብዱልአዚዝ
11)ሸይኽ በድሩዲን ዩሱፍ
12) ሸይኽ ሑሴን ኡመር
13) ሸይኽ ሐሰን ነጃሽ
( ከወንዲሞች)
14) ወንድም ሙርሰል ሰዒድ
15) ወንድም ኢዘዲን ሻፊ
16) ወንድም አቡ ሹራ
17) ወንድም አቡ ሒበቲላህ
18) ወንድም አቡ ሐፍሷ (ይማም)
19) ወንድም አሊ ሰዒድ
20) ወንድም አቡ ኢምራን
(እንዲሁም ሌሎች በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው ዑስታዞችና ወንድሞች ይገኛሉ)
📢 ልዩ ጥሪ፦
ይህንን መልእክት ለሌሎች በማጋራትና በዕለቱ በአካል በመገኘት የዚህ ታላቅ በረካና ደስታ ተካፋይ ይሁኑ!
📌 ለሁሉም እንግዶች ጥሪያችን ክፍት ነው!
ቻናልhttps://t.me/yedesse_selfyochi_yedewa_channel
ግሩፕhttps://t.me/yedesse_selfyochi_group
ሼር ይደረግ‼
እውን ሰው ስለሌለ ነው ሙስሊም የማይሽሾመው?
~
በሃገር አቀፍ ደረጃም ይሁን በአንዳንድ ክልሎች ቁልፍ የሹመት ድልድል ላይ ሊስተካከል ያልቻለ፣ ዛሬም ድረስ የቀጠለ ሙስሊሞችን ማግለል ይታያል። ይሄ ማንም የሚታዘበው ሐቅ ነው።
ታዲያ ሙስሊሞች ይህንን ጉዳይ በማንሳት ቅሬታቸውን ሲገልፁ ተደጋግሞ የሚነሳ በቅጡ ያልተፈተሸ አንድ ግልብ ምላሽ አለ። ይሄውም "ሙስሊሙ ከፖለቲካ ወይም ከትምህርት ስለሚርቅ ነው ይሄ የሚሆነው" የሚል ነው። አዎ ከፖለቲካውም ከትምህርቱም የሚርቀው ሙስሊም ቀላል አይደለም። ለዚህ ብዙ ምክንያቶች አሉ። ይሄ ራሱን ችሎ የብቻው መታየት ያለበት ጉዳይ ነው።
ነገር ግን "ሙስሊሙ ከፖለቲካ ወይም ከትምህርት ስለሚርቅ ነው ይሄ የሚሆነው" ማለት በቅጡ ያልተፈተሸ ሰነፍ ድምዳሜ ነው። ይህንን የዋህ ምላሽ ማን እንደጀመረው እንጃ የሚያስተጋባው ብዙ ነው። ያልተማረው ብቻ ሳይሆን ቀለም የቀመሰውም ጭምር ቁም ነገር ብሎ ሲቀባበለው ይደንቀኛል። አግላዮቹ አካላት የሚሾሙት ሙስሊም ጠፍቶ ተቸግረው እንጂ እነሱ ከፍተው አይደለም የሚል አንድምታ ያለው አፍ ማስያዣ ነው ይሄ ምላሽ። እውነታው ፈፅሞ እንደዚያ አይደለም። በሃገር ደረጃም ይሁን በክልል ወይም ከዚያ በታች ባሉ እርከኖች ላይ ቀላል የማይባል የተማረ ሙስሊም አለ። ሙስሊም የማይሾሙት ፈልገው ስላጡ አይደለም። በጭራሽ!
እውነትነት የሌላቸው ምክንያቶችን መደርደር ለሴረኞች ጥሩ ሰበብ ማቀበል ነው። ችግሩ አጋጣሚ እንዳይመስላችሁ። በአብዛኛው የታቀደበት ነው። ታች ወርዳችሁ ሙስሊም በዝ የሆኑ ወረዳዎችን ጭምር መታዘብ ትችላላችሁ። በቂ የተማረ ሙስሊም ባለበት ሁኔታ የሙስሊም አመራሮች ቁጥር ግን የለም ባይባልም በጣም የሳሳ ነው። እዚች ሃገር ውስጥ ከላይ ከምናየው በላይ በህቡእ የሚንቀሳቀሱ ስውር እጆች አሉ። ለውጥ ለማምጣት ትግል ያስፈልጋል እንደምትሉኝ አስባለሁ። እውነት ነው። ያልሆነ ምክንያት መደርደር ግን ትግል አይደለም። ይሄ ለሴረኞች ዱላ ማቀበል ስለሚሆን ብናስተውል መልካም ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ሰለፊ የሆነ አካል ለሰዎች የሚያሰራጨውን ነገር ሊጠነቀቅ ይገባል። የቢድዓ ባለቤቶችን ቂርዓት፣ ትምህርት ወይም ቻነል ማስተዋወቅና ማሰራጨት ሰዎች ወደ እነርሱ እንዲገቡ፤የተሳሳተ አቂዳና መንሐጅ እንዲወስዱ በር ሊከፍት ይችላል።
ስለዚህ ሰለፊ የሆነ አካል ሰለፊ የሆኑ መሻይኾችን፣ኡስታዞችን ፣ዳዒዎችን ያስተዋውቃል። ሰዎችም ወደ ተሳሳተ መንገድ እንደይገቡ ጥንቃቄ ሊያደርግ ሲገባ በየ ሚድያ አውታሮቹ የሙኻሊፎችን ፣ድምፅ፣ቪድዎ፣ኦዲዮ፣ቻነል በሆነ ባልሆነ ምክንያት ላይክ እና ሼር ሊያደርግ አይገባም። የሚያሰራጨው ነገር ለራሱም ሆነ ለሌሎች አካላት አማና መሆኑን ሊውቅና ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል።
አንተ ሱና ላይ ደፋ ቀና የምትል ሱና ወዳድ ወንድሜ ሆይ “የምታሰራጨውን አረጋግጥ፤ ለሰዎች ሐቅን አስተላልፍ፣ ለራስህም ሆነ ለሌሎች ወደ ጥመት የሚያደርስን በር በሙሉ ዝጋው።
አንሷር ሙሐመድhttps://t.me/ansuar_muhammed_0088
ባለፈው የየመን ስትራቴጂክ የወደብ ከተማ መኻ ስትያዝ ስሟን እንኳ አስተካክሎ መጥራት የማይችለው የሺዐ ፈረስ እንደ ጉድ ሲቦርቅ ነበር። ይሄው መኻ ከተማ በሱኒዮች እጅ ቁጥጥር ስር ውላለች፣ አልሐምዱ ሊላህ አወለን ወኣኺራ። ደግሞ "ሑሢዮች የአሜሪካና የእ$ራኤል መድሃኒት ናቸው" ይላሉ። ሑሢኮ ባበል መንደብን እንደተቆጣጠረ ከሳዑዲ መርከቦች በስተቀር የአሜሪካንና የእ$ራኤልን ጨምሮ የየትኛውንም ሃገር መርከብ እንደማይነኩ በግልፅ ነው የተናገሩት። እስካሁን በሑሢ ጥቃት የሞተ አንድ አሜሪካዊ፣ አንድ እ$ራኤላዊ የለም። ይልቁንም የየመን ሱኒዮችን ነው የፈጀው። የየመን መስጂዶችን ነው ያጠቃው።
ይሄው በአህለ ሱና መስጂዶች ላይ የሚያደርሱትን ተመልከቱ። እነዚህ ዐቂዳቸውን የሸጡ የሺዐ ፈረሶች ግን የሶሐባ መሰደብ አይገርማቸው፣ የመስጂዶች መደፈር አያማቸው። እንዲሁ ከነፈሰው ጋር መንፈስ ነው መታወቂያቸው። ደግሞ "ሳዑዲም ውስጥ ሶሐባ የሚሳደቡ ሺዐዎች አሉ" ይላሉ። አዎ ሺ0ዎች አሉ። እስኪ ሑሢዮች እንደሚያደርጉት ባደባባይ ይሳደቡና ተመልከቷቸው። አንጠልጥለው ነው የእጃቸውን የሚሰጧቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
እውነቱን ለመናገር፣ በአሁኑ ወቅት በንቃት የምከታተላቸው የቴሌግራም ቻናሎች ከአምስት እንኳ አይበልጡም። ቴሌግራም እንደ ቀድሞው ማራኪነቱ ቀርቶ እጅግ አሰልቺ መድረክ እየሆነ መጥቷል።
በተለይ "ዋቭ" በሚል ሰበብ የሚለጠፉት የቻናል ማሳደጊያ ማስታወቂያዎች ቻናሎችን ከመረጃና ዕውቀት ማዕከልነት ይልቅ ወደ አደባባይ ልመና ቀይረዋቸዋል። በዚያ ላይ አስር አድሚን ተሹሞበት፣ እንደ ሰፈር ስብሰባ እያንዳንዱ ሰው የፈለገውን እየረጨ የሚወጣበት የተዘበራረቀ ጓዳ ሆነዋል።
ሐቂቃ ኢኽላስ እና የሚጨበጥ ጠቃሚ ይዘት ያለው ሰው እንዲህ ዓይነት የቁጥር ብዛት አያስጨንቀውም። ያለ ምንም ማስታወቂያ በይዘታቸው ጥንካሬ ብቻ ከዜሮ ተነስተው በአስር እና በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ተከታዮችን ያፈሩ ብዙዎች አሉ።
ቻናል ማስተዳደር ቀላል ነገር ሳይሆን ትልቅ አማናና ኃላፊነት ነው። የቁጥር መብዛት ሳይሆን ተከታዮቻችሁን ማክበር እና ለነሱ
የሚመጥን ጥራት ያለው ነገር ማቅረብ ይቅደም።ይዘታችሁ ይመስክርላችሁ፤ ተከታይ በራሱ ይመጣል!
t.me/AbuSufiyan_Albenan
⛔በርካታ ወጣቶች የተፈተኑበት
የዘመናችን በሽታ አሏህ ይጠብቀን
🎙በኡስታዝ ኸድር አህመድ
🚫 ራስን በራስ ማርካት
https://t.me/Multeka_Selefiyin
✅ለወጣቶች የተላለፈ አደራ
ከታላቁ ነብይ ትዳርን መስርቱ
🎙በኡስታዝ ኸድር አህመድ
https://t.me/Multeka_Selefiyin
