cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

پست‌های تبلیغاتی
4 453
مشترکین
+124 ساعت
+37 روز
+2730 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን፣ ሰው ሠራሽ የነዳጅ እጥረት በሚፈጥሩ ነዳጅ ማደያዎች ላይ ጠንካራ ርምጃዎችን እንዲወስድ የሚያስችለውን ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቶ ለሚንስትሮች ምክር ቤት ማቅረቡን አስታውቋል። ባለሥልጣኑ፣ ሰው ሠራሽ የነዳጅ እጥረት በሚፈጥሩ ማደያዎች ላይ እስካኹን የሚወስደው ርምጃ ማደያዎቹን ከማሸግ የዘለለ አልነበረም። አዲሱ አዋጅ ግን፣ ባለሥልጣኑ በነዳጅ ማደያዎች ባለቤቶች ላይ የእስራትና የገንዘብ ቅጣት እንዲጥል የሚፈቅድ እንደኾነ ተገልጧል። ረቂቅ አዋጁ ተግባራዊ የሚኾነው፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካጸደቀው ነው። የነዳጅ ግብይት እስከ ጎረቤት አገራት በተዘረጋ ኮንትሮባንድ የተተበተበ እንደኾነ ተደጋግሞ ተነግሯል። @tikfahethiopia
نمایش همه...
3👍 2😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
ደንበኞች ከትንሳኤ በዓል ዋዜማ ጀምሮ ኃይል ቆጣቢ አጠቃቀምን ተግባራዊ እንዲያደርጉ አገልግሎቱ ጠየቀ በትንሳኤ በዓል ዋዜማና ዕለት የኃይል መዋዥቅና መቆራረጥ ለመቀነስ፤ ከተከሰተም አፋጣኝ ምላሽ ለመሰጠት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ። እንዲያም ሆኖ ሊያጋጥም የሚችለውን የኃይል መዋዠቅና መቋረጥ ለመቀነስ በውጭ ንግድ ላይ ከተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች በስተቀር ሌሎች ሁሉም የከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች ከዋዜማው ከቀን 7 ሰዓት ጀምሮ እስከ በዓሉ ዕለት ድረስ ከዋናው ግሪድ የሚጠቀሙትን ኤሌክትሪክ እንዲያቋርጡ አገልግሎቱ ጥሪ አቅርቧል። ደንበኞች በቤት ውስጥ የሚገለገሉባቸው የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች ኃይል ቆጣቢና ለአደጋ የማያጋልጡ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ እና የኤሌክትሪክ ኃይል ጭነት በማይበዛበት ሰዓት በተለይ ከምሽቱ 4፡00 እስከ ንጋቱ 11፡00 ባሉት ጊዜያት እንዲጠቀሙ ጠይቋል። የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ደግሞ በዓሉ ሲደርስ የሚኖረውን አላስፈላጊ ወረፋ ለማስቀረት እንዲችሉ ከወዲሁ የሚበቃቸውን ያህል የኤሌክትሪክ ኃይል አስቀድመው እንዲገዙ (ካርድ እንዲሞሉ) አገልግሎቱ መክሯል። @tikfahethiopia
نمایش همه...
👍 12
" ኢራቅ ውስጥ ለግብረ ሰዶማዊነት ቦታ የለም " - ሞህሰን አል-ማንዳላዊ የኢራቅ ፓርላማ የግብረ ሰዶናዊነት / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ተግባርን ከ10 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስር የሚቀጣ አዲስ ሕግ አርቅቋል። በአዲሱ ሕግ ጾታቸውን የቀየሩ ሰዎች ከ1 እስከ 3 ዓመት እርስ ቤት ይወረወራሉ። እንዲሁም፦ - ግብረ ሰዶማዊነት / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚያበረታቱ፣ የሚያስተዋውቁ፤ - ሴተኛ አዳሪነትን የሚያራምዱ - ጾታ ለመቀየር ቀዶ ህክምና ሚያደርጉ ዶክተሮች - ሆን ብለው ልክ #እንደ_ሴት_የሚሆኑ ወንዶች እና " በሚስት መለዋወጥ " ላይ የተሠማሩ ሰዎች እስራት ይጠብቃቸዋል ፤ ዘብጥያም ይወርዳሉ። የኢራቅ ፓርላማ ተጠባባቂ አፈጉባኤ ሞህሰን አል-ማንዳላዊ ፥ " ይህ አዲስ ሕግ የህብረተሰቡን የሞራል / የግብረገብ / የስነምግባር መዋቅር ለመጠበቅ ያለመ ነው " ብለዋል። " በኢራቅ ውስጥ ለግብረ ሰዶማዊነት ቦታ የለም " ያሉት አል-ማንዳላዊ ፥ " ይህ የኢራቅ ምድር የነቢያት፣ የንፁህ ኢማሞች ፣ የጻድቃን እንዲሁም ቅዱሳን ምድር ነው " ነው ሲሉ ተናግረዋል። ፎቶ፦ ፋይል #Iraq @tikfahethiopia
نمایش همه...
👍 17 1
Photo unavailableShow in Telegram
🌴 ሆሳዕና በአርያም 🌴 እንኳን አደረሳችሁ የ “ሆሳዕና በአርያም”  በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ ዛሬ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡ ሆሳዕና በአርያም ከፋሲካ በፊት ያለው እና የዐቢይ ጾም የመጨረሻው ሣምንት ሲሆን÷ “አቤቱ እባክህ አሁን አድን፣ አቤቱ እባክህ አሁን አቅና፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ብሩክ ነው” የሚሉ ትርጉሞችም እንዳሉት የዕምነቶቹ አባቶች ያስተምራሉ። የዕምነቶቹ ተከታዮች በሆሳዕና በአርያም በዓል መሪው ተመሪውን ዝቅ ማለትን ያስተማረበት እና ተመሪውም የሚመራውን ጨርቁን እያነጠፈ እና ዘንባባ እየጎዘጎዘ ያከበረበት የትህትና እና የፍቅር በዓል ተደርጎ የሚወሰድ ነው፡፡ ሆሳዕና በአርያም ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ በተለይም÷ አረጋውያን፣ ሴቶች፣ ወንዶች፣  ወጣቶች እና ሕጻናት “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፣ ሆሳዕና በዓርያም” በማለት በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው፡፡ @Tikfahethiopia
نمایش همه...
👍 4 1
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ተገለጸ። ከሶስት ዓመት በፊት የደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) በቢሯቸው ከታዩ አንድ ወር አልፏቸዋል ተብሏል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የዩንቨርሲቲው አስተዳድር አመራር አባል  "ፕሬዝዳንቱ ከመጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ. ም ጀምሮ በስራ ላይ አይተናቸው አናውቅም" ሲሉ ለአል ዐይን አማርኛ ዘጋቢ ነግረውታል። "ፕሬዝዳንቱ ንጉስ ታደሰ ከተጠቀሰው ቀን አንስቶ የት እንደሄዱ እና መቼ እንደሚመለሱ አናውቅም" ሲሉም እኝህ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አመራር ነግረውናል። ይሁንና ፕሬዝዳንቱ በቢሮ መታየት ካቆሙ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ባልታወቁ ሀይሎች መታገታቸውን ሰምተናል ሲሉም አክለዋል። የሰማን ሸዋ ዞን ፖሊስ፣ ኮማንድ ፖስት፣ ትምህርት ሚንስቴር እና የደብረብረሀን ከተማ ፖሊስ ስለ ደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ ፕሬዝንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) ጉዳይ ምላሽ እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።ከቤተሰብም የተገኘ መረጃ የለም። የፌደራል መንግሥት ከአንድ ዓመት በፊት የክልል ልዩ ሀይሎችን "መልሼ አደራጃለሁ" የሚል ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ግጭት የተከሰተው። ግጭቱ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተካሄደ ሲሆን ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉን ተከትሎ በአማራ ክልል ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል። ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የታወጀው ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት የተራዘመ ሲሆን ይህ አዋጅ ሊጠናቀቅ ከሁለት ወራት ያነሰ ጊዜ ቀርቶታል ሲል አል ዓይን አማርኛ ዘግቧል። ፕሬዝደንቱ ከወር በፊት ከመኖሪያ ቤታቸው ታግተው እንደተወሰዱ በዚህ ቻናል ላይ መዘገቡ ይታወሳል። @Tikfahethiopia
نمایش همه...
👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
በዓልን ምክንያት በማድረግ የእሁድ ገበያዎች ሳምንቱን ሙሉ አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉ ተነግሯል የትንሳዔ በዓልን አስመልክቶ 188 የእሁድ ገበያዎች ሳምንቱን ሙሉ አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስውቋል፡፡ በዓልን አስመልክቶ የምርት እጥረት እንዳይከሰት በመዲናዋ የሚገኙ 188 የእሁድ ገበያዎች በመደበኛነት ቅዳሜ እና እሁድ የሚካሄደውን የእሁድ ገበያዎች፤ ሳምንቱን ሙሉ እንዲካሄዱ መደረጉን የቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሰውነት አየለ ተናግረዋል፡፡ ይህም በዓልን አስመልክቶ የሚፈጠር የምርት እጥረት፣ ህገ ወጥ ንግድን እና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት እንደሚረዳ ተነግሯል፡፡ የእሁድ ገበያዎቹ የትራስፖርት አገልግሎት ላይ መጨናነቅ የማይፈጥሩት ተለይተው መሆኑን አንስተው፤ በእነዚህ የገበያ ቦታዎች ላይ የገበያ ዋጋ ጥናት በቢሮ በየ 3 ቀኑ የሚከናወን እና የዋጋ ተመን እንደሚዘጋጅ እና የክትትል ስራ እንደሚከናወን ተጠቁሟል፡፡ @Tikfahethiopia
نمایش همه...
👍 3
የናይጄሪያ ጦር ወታደሮቹ መገደላቸውን ተከትሎ የበቀል እርምጃ እንደሚወስድ ዛተ የናይጄሪያ ጦር ባለፈው ሳምንት በኒጀር ማዕከላዊ ግዛት የሰላም ተልዕኮ ላይ እያለ በደፍጣ ውጊያ ለተገደሉት ስድስት ወታደሮች የበቀል እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል። ወታደሮቹ ባለፈው አርብ በሽሮሮ አካባቢ በሚገኘው ካራጋ መንደር “በተዋጊ ፓትሮል” ላይ በነበሩበት ወቅት በጦር ኃይሉ “አሸባሪዎች” ተብለው በተፈረጁ ታጣቂ ቡድኖች ጥቃት ደርሶባቸዋል። የጦሩ መግለጫ እንዳመለከተው በርካታ ጥቃት አድራሾች መገደላቸውን እና ሌሎችንም እየተከታተልን እንገኛለን ነው። ጦረ በወታደሮቹ ላይ የደረሰውን ጥቃት እንደሚበቀልም ቃል ገብቷል። የተገደሉት ወታደሮች ሁለት ከፍተኛ መኮንኖች እና ሌሎች አራት ወታደሮች እንደሚገኙበት ሰራዊቱ ገልጿል። በጥቃቱ ወቅት ሁለት መኮንኖች ቆስለዋል። የመከላከያ ሰራዊቱ አንድ መኮንን ታፍኖ መወሰዱን ከአካባቢው የወጡ ዘገባዎች ቢያመላክቱም ማረጋገጥ ግን አልተቻለም። ከጥቃቱ ጀርባ ማን እንዳለ ግልፅ ባይሆንም በአካባቢው ሽፍቶች በመባል የሚታወቁት የታጠቁ ወንበዴዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በደረሰባቸው ጥቃቶች የጸጥታ ሃይሎችን ኢላማ አድርገዋል ተብሏል። ናይጄሪያ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ከፍተኛ የአፍሪካ የፀረ-ሽብርተኝነት ጉባኤ በመዲናይቱ አቡጃ ስታስተናግድ ቆይታለች። በነዳጅ ዘይት በበለጸገው ደቡባዊ ዴልታ ግዛት በተቀናቃኝ ማህበረሰቦች መካከል ለተፈጠረው ግጭት ሲዋጉ የነበሩ 16 ወታደሮች ከተገደሉ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ይህው የአድፍ ጥቃት መከሰቱን መረጃዎች አመላክተዋል።ናይጄሪያ ለእገታ ገንዘብ ለመቀበል በሚል ከፍተኛ የአፈና ማዕበል የተስፋፋባት ሲሆን የተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች እያንሰራሩ ይገኛሉ። @Tikfahethiopia
نمایش همه...
3👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ ለአምስት ዓመታት ከአትሌቲክስ ታገደች:: የ21 ዓመቷ የመካከለኛ ርቀት አትሌት ለአምስት ዓመታት መታገዷን የገለጠው አትሌቲክስ ኢንቴግሪቲ ዩኒት የተባለው ተቋም ነው። ተቋሙ በቀድሞው ትዊተር በአሁኑ ኤክስ ሰሌዳው ላይ በለጠፈው መግለጫ አትሌቷ ምርመራ ከተደረገላት በኋላ ቅጣት ማስተላለፉን አሳውቋል። የዓለም አትሌቲክስ አካል የሆነው ይህ ተቋም ባወጣው መግለጫ፣ አትሌቷ ሁለት የተከለከሉ ንጥረ-ነገሮችን መውሰዷን አምናለች ብሏል። ዘርፌ፤ ቴስቶስቴሮን የተባለውን እና ኢፒኦ የተሰኘውን አትሌቶች በደማቸው ውስጥ የበለጠ ኦክሲጅን እንዲኖር የሚያደርግ ንጥረ ነገር መውሰዷን አምናለች። ዘርፌ በቶኪዮ ኦሊምፒክስ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ስምንተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል። @Tikfahethiopia
نمایش همه...
የመስተንግዶ ባለሙያዎች የአለባበስ ኮድ መመሪያ ዝግጅት በመጠናቀቁ በቅርቡ ፀድቆ ተግባራዊ ይሆናል ተባለ፡፡ በሆቴሎች የሚሠሩ ሴት የመስተንግዶ ባለሙያዎች ከሀገሪቱ ባሕል ውጪ የሆነውን አለባበሳቸውን ለማስተካከል የሚያስችል የአለባበስ ኮድ መመሪያ ዝግጅቱ በመጠናቀቁ በቅርቡ ፀድቆ ተግባራዊ እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ። የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሣው (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በአንዳንድ ሆቴሎች የሴት መስተንግዶ ሠራተኞች አለባበስ ከሀገሪቱ ባሕል ወጣ ያለ ነው። ይህን ለማስተካከል የሚረዳ የመስተንግዶ ባለሙያዎች የአለባበስ ኮድ መመሪያ ዝግጅቱ ተጠናቆ ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት እንዲፀድቅ በመላኩ መመሪያው በከተማዋ ካቢኔ በቅርቡ ፀድቆ ተግባራዊ እንደሚደረግ ይጠበቃል ብለዋል። ለቱሪስቶች መስተንግዶ ሲሰጥ የሀገራችንን ባሕልና እሴት በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት ያሉት ኃላፊዋ፤ በሆቴሎች ያለው የመስተንግዶ ባለሙያዎች አለባበስ ሥነ-ሥርዓቱን የጠበቀ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል። ሂሩት (ዶ/ር)እንዳመላከቱት፤ አሁን ላይ የመስተንግዶ ባለሙያዎች በተለይም ሴቶች በአንዳንድ ሆቴሎች አማካኝነት ሥነ-ሥርዓቱን ያልጠበቀ አለባበስ እንዲለብሱ ይገደዳሉ። ድርጊቱ ከሴት ልጅ መብት አኳያ ክብርን ያልጠበቀ እና አሳፋሪ ነው ብለዋል። መመሪያው ፀድቆ ሥራ ላይ ሲውል በሆቴሎች የሚሠሩ የመስተንግዶ ባለሙያዎች ወጥ የሆነ ዓለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የአለባበስ ኮድ እንዲከተሉ ይደረጋል ያሉት ኃላፊዋ፤ ይህም የኢትዮጵያን ባሕልና ወግ ያልጠበቀ የአለባበስ ሥነ ሥርዓትን ለመቆጣጠር እንደሚያስችል አስረድተዋል። አሁን ላይ በአንዳንድ ሆቴሎች የሚታየውን ከባሕል ያፈነገጠ የመስተንግዶ ባለሙያዎች አለባበስ መስተካከል እንዳለበት የከተማው ነዋሪዎች ጥያቄ እንደሚያቀርቡ ገልጸው፤ መመሪያው ሲፀድቅ የሁሉንም ጥያቄ እንደሚመልስ አብራርተዋል። ሕጉ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣትም ጭምር ያለው በመሆኑ መመሪያውን በሚተላለፉ ላይ ቅጣት እንደሚጣል ጠቁመዋል። የአለባበስ መመሪያውን ለማውጣት ቢሮው ሁለት ዓመት ሲሠራ መቆየቱን ተናግረው፤ ሕጉ ከፀደቀ በኋላ ወደ ርምጃ እንደሚገባ አመላክተዋል። ሕጉ እስኪፀድቅ የቁጥጥር ሥራ የሚሠራ ሲሆን በሚደረገው ክትትልና ድጋፍም አሁን ላይ ለውጦች መኖራቸውን ተናግረዋል። በቱሪዝም ዘርፉ ውድድር በዓለም አቀፍ ይዘት ያለው በመሆኑ ደረጃውን ያልጠበቀ መስተንግዶ የሚሰጥ ከሆነ ቱሪስቶች ተመልሰው እንደማይመጡ የሚገልጹት ሂሩት (ዶ/ር)፤ በሆቴሎች መልካም መስተንግዶ እንዲሰጥ ለማስቻል ቢሮው በየዓመቱ ሁለት ሺህ ለሚደርሱ በሥራ ላይ ላሉ መስተንግዶ ሰጪ ባለሙያዎች ሥልጠና እንደሚሰጥ አስታውቀዋል። በከተማዋ ያሉ ዓለም አቀፍ ሆቴሎች የመስተንግዶ ባለሙያዎቻቸው አለባበስ ጥሩ መሆኑን ጠቅሰው፤ በመጠኑ ከሴት የመስተንግዶ ባለሙያዎች የፀጉር አያያዝ ሥነ-ሥርዓት ጋር በተያያዘ የማይፈቀዱ ነገሮች በአንዳንድ ሆቴሎች የሚታዩ በመሆኑ እንዲሻሻሉ ክትትል ይደረጋል ብለዋል። Via EPA @Tikfahethiopia
نمایش همه...
👍 2 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጲያዊቷ አትሌት ከ10 ዓመታት በፊት ያሸነፈችበትን የቦስተን ማራቶን 100 ሺ ዶላር እስካሁን ድረስ አልተሰጣትም የ36 ዓመቷ ኢትዮጲያዊቷ አትሌት ብዙነሽ ዲባ የረጅም ርቀት አትሌት ስትሆን እኤአ በ2014 በቦስተን ማራቶን ብታሸንፍም በአሸናፊነቷ ሊሰጣት ይገባ የነበረው 100 ሺ ዶላር እስካሁን እንዳልተሰጣት ከሲቢኤስኒውስ ኒውዮርክ ጋር ባደረገችው ቆይታ ተናግራለች። በወቅቱ በውድድሩ ብዙነሽ ዲባ ሁለተኛ ወጥታ የነበረ ቢሆንም አንደኛ የወጣችው አትሌት ውድድሩ ከተደረገ ከሁለት ዓመት በኃላ በ2016 በዶፒንግ አበረታች መድኃኒት በመውሰድ ያገኘችው ውጤት ተሰርዞ አንደኝነቱን አትሌት ብዙነሽ ዲባ አግኝታለች። ኑሮዋን በአሜሪካ ያደረገችው አትሌቷ የሁለት ልጆች እናት ስትሆን ዳግም ወደ ልምምድ መመለሷን ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል። አትሌቷ በካሊፎርኒያ ዓለም አቀፍ ማራቶን፣ በሳንዲያጎ ማራቶን፣ በሎስ አንጀለስ ማራቶን፣ በግራንድ ማ ማራቶን፣ በቦስተን ማራቶን እና በቲዊን ሲቲ ታ ማራቶን አሸናፊ ነች። በኒውዮርክ ሲቲ ማራቶን ሶስት ጊዜ ምርጥ አስር ሆና አጠናቃለች። Via:Dagu @Tikfahethiopia
نمایش همه...
👍 4 1😢 1