cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Haro Tik Tok 💓💓

@Abdi_Wiz_Kid34 🇯 ‌🇴 ‌🇮 ‌🇳 👇 🇺 ‌🇸  👇👇👇👇👇👇👇 @Haro_Tik_Tok @Haro_Tik_Tok Follow On Facebook 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/abdi.musama.9 @Abdi_Wiz_Kid34

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
179
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

🌿🌿አንድአንዴ በሕይወታችን የሚደርሰው ችግር ከባድ ከመሆኑ የተነሳ የሚያጠፋን ይመስለናል። 🌱🌱ተስፋ ያስቆረጠኝ በተደጋጋሚ የሚደርስብኝ ችግር ሳይሆን፤ የምቋቋምበት አቅም ማጣቴ ነው። 🌿🌿ሁሌም ይቺ አለም የማዝንበትን የማለቅስበትን ምክንያት ትፈጥርልኛለች። የሰለቸኝ ነገር ቢኖር ይሄ ብቻ ነው። 🌱🌱አይምሮዬ በተለያዩ ሀሳቦች ተሞልቷል እንዴትስ አድርጌ ትኩረቴን ልሰብስብ? 🌿🌿በችግሮቼ ባህር ውስጥ ጠልቄ ለመውጣት ስታገል ራሴን አየሁት እናም ሰምጬ አለመቅረቴ አስደነቀኝ። @Abdi_Wiz_Kid34
نمایش همه...
አባ ቁዳማ ሆይ! ከእናቴ ጋር የአስር አመት ሴት እህት አለች። ሲበዛ ትወደኛለች አካባቢዬን ለቅቄ ወደ ፍልሚያው አደባባይ ለመሄድ ስዘጋጅ ስለምትናፍቀኝ ቶሎ ትመለሣለህ አይደል?! ብላ ስማ ነበር የሸኘችኝ። ስታገኛት አላህ አንቺን የኔ ምትክ ስላደረገሽ እናቴን አደራ ሰላም በልልኝ። ብዙም ሳይቆይ የሸሃዳ ቃሉን ከአፉ አወጣ ላ ኢላሃ ኢለላህ ሙሀመዱን ረሱሉላህ እስትንፋሱ ተቋረጠ። . . . ከዘመቻው መልስ ወደ ሪቃህ መንደር አቀናን በቀጥታ ወደ ልጁ እናት ቤት አመራሁ። ወደ መንደራቸው እንደዘለቅኩ አንዲት ታዳጊ ህፃን አላፊ አግዳሚውን በማስቆም ወንድሜን አላያችሁትም? እያለች ትጠይቃለች። የሰዎቹ ምላሽ ሁሉ አናውቅም ሆነ በመጠየቅ ተራዬ ደረሰና "እባክህን ወንድሜን አላየኸውም ሁሉም ሰው እኮ ወደ ቤቱ ተመለሰ የኔ ወንድም ብቻ ነው የቀረው" እያለች በእምባ ታጅባ ተንሰቀሰቀች። እንባ እየተናነቀኝ አረጋጋኋትና ከበሩ ፊት ለፊት አባ ቁዳማ የሚባል ግለሰብ ቆሟል ሰላምታ ልኳል ብለሽ ለእናትሽ ንገሪልኝ አልኳት። ቀኝ እግሯ ገና ወደ ቤት እንደገባ እናቷ ከውስጥ በቅፅበት ወጣች። አንደበቷ ነዲድ እሳት እየተነፋ አባ ቁዳማ ሆይ! የመጣከው መርዶ ልታሰማኝ ነው ወይስ ብስራት ልትነግረኝ?! ልቤ በፍርሃት ተናጠ ንግግሯን ቀጠለች "አንተ በሰላም ወደቀየህ እንደተመለስከው ልጄም በሰላም ተከትሎህ ከመጣ መርዶ ነጋሪዬ ነህ። በፍልሚያው መስክ ሸሂድ ሆኖ መስዋቱን ከነገርከኝ አበሳሪዬ ነህ" አለችኝ። የጀነት መለያ ከፊቷ የሚነበበው የሪቃዋ ታጋይ "አብሽሪ በእርግጥም ትመኚው የነበረው ጉዳይ ፍፃሜውን አግኝትዋል" አልኳት። በደስታ ብዛት እንባ ያቀረሩት ዓይኖቿ የሚገድባቸው ስላጡ በጉንጮቿ ላይ ያለ ማንም ከልካይ ይንኳለለኩ ገቡ "የውመል ቂያማ የኸይር ስራ ማሟያ ስንቄ ላደረገልኝ አምላክ አላህ ወሰን ለሌለው ክብሩ ወሰን የሌላው ምስጋና ይድረሰው" ብላ ወደ ውስጥ ገባች። ያቺ እንደ እንቡጥ አበባ የፈካች ታዳጊ ህፃን ማናገር ፈለግኩ ወደኔ መጣች "ወንድምሽ በቅድሚያ ሰላም በልልኝ ከዚያም እናቴን አደራ ብሎሻል ብዬ መልእክቴን ሳልጨርስ ከልጅቱ አፈትልኮ የወጣ ጩኸት ጆሮዬን አርገበገበው። ብቸኝነት ዋጣት። የምትሳሳለት ወንድሟ ላይመለስ ተለይቷታል። በራሷ የሀዘን ዓለም ውስጥ ጠለቀች ትቢያ በበዛበት መሬት ላይ በደረቷ ወደቀች። ከዕድሜው አንፃር የማይጠበቅ ታላቅ ገድል የሰራ ወንድሟን ለመገናኘት የናፈቀች ይመስል ፀጥ አለች። ለሪቃዋ እንስት ያ ሸሂድ ልጇ እንድሰጥለት ያዘዘኝን በደም የረጠበ ልብሱን አስረክቤ ሀዘን ልቤን እያደማው አካባቢውን ለቀቅኩ። ══════════════════ ምንጭ:- كتاب: مشارع العشاق ══════════════════ ፅሑፎቼን አንብቦ ለሌላ በሚያካፍል ሰው ላይ ሁሉ የአላህ እዝነት ይስፈን """""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""" Like ☑ Comment ☑ Share ☑ ኢኽላስ - ታማኝነት - ትጋት - ስኬት """""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""" https://t.me/Haro_Tik_Tok
نمایش همه...
Haro Tik Tok 💓💓

@Abdi_Wiz_Kid34 🇯 ‌🇴 ‌🇮 ‌🇳 👇 🇺 ‌🇸  👇👇👇👇👇👇👇 @Haro_Tik_Tok @Haro_Tik_Tok Follow On Facebook 👇👇👇👇

https://www.facebook.com/abdi.musama.9

@Abdi_Wiz_Kid34

╭─┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅─╮ የጀግኖች ገጠመኝ ╰─┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅─╯ ጌታዬ ሆይ! ብዕሬን እንደ ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ ሠይፍ የሰላ አድርግልኝ! Mahi Mahisho "ለጂሃድ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ አገልግሎት የምትሰጥ ግመል ለመግዛት ሪቃህ ወደተሰኘች መንደር ዘለቅኩ። በመንደሯ ውስጥ የምትገኝ አንድ ቦታ ተቀምጬ ሳለሁ አንዲት ሴት እኔ ወዳለሁበት አቅጣጫ መጣች "አቡ ቁዳማ ሆይ! ባለቤቴ ሲሞት በስነ ምግባሩ ትሁት የሆነ ልጅ ትቶልኝ አልፏል ቁርዓንን በወጉ የተማረ በፈረስ ግልቢያ የተካነ በቀስት ውርወራ ድንቅ ብቃት ያለው ለሊቱን በኢባዳ ቀኑን በፆም የሚያሳልፍ ዕድሜው ከአስራ አምስት ያልዘለለ ልጅ ነው። ከአንተ ጋር ወደ ፍልሚያው ሜዳ አብሮህ ይሄድ ዘንድ እጠይቅሀለው። ለኢስላም ልቅና ስትል የጠየቅኩህን እንድታሟላልኝ ስል አጥብቄ እማፀንሃለው። የአብራኬን ክፋይ ከመዝመት እንዳትከለክለው" ብዙም ሳንቆይ ከባልደረቦቼ ጋር ሆኜ ከሪቃህ መንገድ ወጣን። መስለመቱብኒ አብዱልመሊክ የሚባለው ምሽግ አካባቢ ስንደርስ አባ ቁዳማ ሆይ አንድ ጊዜ ጠብቀኝ የሚል ድምፅ ከኋላዬ ተሰማኝ። ግርማ ሞገስን የተላበሰ የፈረሰኛ ጥሪ ነው። ባልደረቦቼን ወደ ፊት እንዲጓዙ ነግሬ ድምፁን የሰማሁትን ሰው መጠበቅ ጀመርኩ። ፈረሰኛው ወደ እኛ ተጠጋና አቀፈኝ "ካንተ ለመጎዳኘት ያልከለከለኝ ምኞቴን ባዶ ያላደረገው ጌታ ወሰን ለሌለው ክብሩ ወሰን የሌለው ምስጋና ይድረሰው" አለ። "ወደ ፍለወሚያው ሜዳ የመሄድ ጉጉት ያለህ ትመስላለህ" አልኩት። እንደ ሙሉ ጨረቃ በሚንቦገበገው ፊቱ ወደ ዘመቻ የመሄድ ጉጉቱ ጣራ የነካ መሆኑን ያሳብቅበታል። የፊቱ ገፅታ በድሎት ተቀማጥሎ ያደገ ይመስላል። አባት አለህን? በማለት ጠየቅኩት "ከአንተ ጋር ወደ ፍልሚያው አደባባይ ለመሄድ የማኮበኩበው ወላጅ አባቴ ያገኘውን የሸሂድነት ፀጋ እኔም እንድጋራ በመሻት ነው አባ ቁዳማ ሆይ! ምርጥ ፈረሰኛና ድንቅ ቀስት አስወንጫፊ ነኝ። የእድሜዬን ማነስ ተመልክተህ እንዳትመልሰኝ የሪቃዋ እናቴ በፍፁም እንዳልመለስ ቃል አስገብታ ነው የላከችኝ። እሳት የሚንቀለቀልበት ፍልሚያ ውስጥ ገብተህ ጀርባህን ለበደለኞች ፈፅሞ እንዳትሰጥ የአባትህና የደጋግ የአላህ ባሪያዎችን ጉርብትና በመሻት ትግልህን እስክትሰዋ አሊያም በድል እስክታጠናቅቅ ተፋለም ብላኛለች። በመጨረሻም ደረቷ ላይ አስጠግታ "ጌታዬ ሆይ! ይህን ብርቅዬ ልጄን የልቤ መርጊያና መዓዛዬ የዓይኔ ማረፊያ ለኢስላም የበላይነት ወዳንተ ልኬዋለው" ብላ አላህን በጥልቀት ተማፅናዋለች" አለኝ። ይህን ንግግር ከዚህ ልጅ አንደበት ስሰማ ዓይኔ የእንባ ዘለላን አንጠባጠበ። የልጁ ቁንጅናና ለጋነት፣ የአብራክ ክፋይዋን ለኢስላም የበላይነት ከመገበር ያላንገራገረችው የሪቃዋ እንስት ሶብር ሲበዛ አስገረመኝ። እየተንሰቀሰቅኩ አለቀስኩ። አሁን ጉዞ ጀምረናል። ልጁ በደስታ ስሜት ፊቱ ፈክቷል። ቅልጥፍናውና ፍጥነቱ ሲበዛ ይማርካል። በጉዞ ምክንያት በድካም የዛለ ሰውነታችንን ለማሳረፍ ስንሻ የእርሱ ሰውነት ገና ጉዞ የጀመረም አይመስልም። አንደበቱ በዚክር የታጠረ ነው። የትዕቢተኞቹ መንደር እስክንደርስ እኛን ከመኻደም ፈፅሞ አልተቆጠበም። ማገዶውን እየቆሰቆሰ ማፍጠርያ ዳቦ ይጋገርልን ይዟል። ዳቦውን ጋግሮ ከጨረሰ በኋላ እረፍት ለመውሰድ ተጋደመ። በጥልቅ እንቅልፍ ውስጥም ሰጠመ። ከየት አቅጣጫ እንደሆነ የማይታወቅ በደስታና ፈገግታ የታጀበ ሳቅ ሰማን። ወደ ኋላችን ስንዞር የዚያ ልጅ ጥርሶች የተፈለቀቀ ጥጥ መስለዋል። በእንቅልፍ ልቡ የብርሃን ፈገግታ ይረጫል። ከእንቅልፉ ነቃና ያየውን ህልም ያጫውተን ጀመር "ውበቱን ቃላት ተከማችተው ቢተባበሩ ሊገልፁት የማይችሉት አረንጓዴ አፀድ ውስጥ ነበርኩ። በዚያ ለምለም መስክ ከከበሩ ማዕድናት የተሰራ ግዙፍ ቤት ውስጥ እንዳሻኝ እቦርቃለሁ። ውስጡ ዓይንን በሚያስለመልም የወርቅ አይነቶች አጊጧል። የአንፀባራቂው ቀለማት መብዛት በደስታ ይከንፋል። ከምድራዊው ማዕድናት ጋር ለማመሳሰል እየሞከርኩ ነው እንጂ በንግግር ፈፅሞ አይስተካከልም። በቅፅበት ከፊት ለፊቴ ዓይንን ስቦ የሚያስቀምጥ መጋረጃ ተከፈተ። ግርዶሹን የሚከፍቱትን እንስቶች ተመለከትኩ። ውበታቸው ጨረቃን ያስክዳል። የዓይናቸው ጥራት ከበስተጀርባ ያለው አካላቸውን ያሳያል። እንኳን ደህና መጣህ አሉኝ። በጥድፍያ ከመካከላቸው ለአንዷ እጄን ለመዘርጋት ዳዳሁ እኔ ላንተ አይደለሁም አለችኝ። እርስ በርሳቸው እየተንሿኮኩ ይህ እኮ የተወዷጇ ዓይናኡል መርዲያ ባለቤት ነው ሲባባሉ ሰማሁ። አላህ ይዘንልህ ወደ ፊት ተራመድ አሉኝ። መራመድ ጀመርኩ ከበላይ በወርቅ የተንሸቆጠቆጠ ግዙፍ ሰገነት ተንጣሏል። ሰማያዊ ቀለም እየረጩ ልስላሴያቸው ከሐር በላይ የሆኑ የተለያዩ አልጋዎች በረድፍ ተደርድርዋል። አልጋው ላይ ጥብቅ እንስት በክብር ተቀምጣለች። ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ ይሁንብኝ የቤቱንና የእንስቷን ውበት ለማየት የበቃው ዓይኔ ለረጅም ጊዜ ብቆይ ኖሮ በውበታቸው ኃይል በጠፋ ነበር። አዕምሮዬም ከሰጠመበት ድንቅ ሀሳብ መመለስ በተሳነው ነበር። ብርሃን በሚረጨው ዓይኗ ወርውራ ተመለከተችኝ አንተ የአላህ ባለሟል ሆይ! አንተ የኔ ነህ እኔም ያንተ ነኝ አለችኝ። ልቤ ነጠረች እጄን ዘርግቼ ወደ ደረቴ ላስጠጋት ስፍጨረጨር ትክክለኛው የቀጠሮ ጊዜ ዛሬ አይደለም አብሽር ታገስ ነገ ከዙሁር ሰላት በኋላ ተዘጋጅ ብላ በትህትና እጄን መለሰችው" ህልሙን ካደመጥን በኋላ ጎናችንን ከመሬቱ ለጥፈን ተኛን። ጎህ ቀዶ ሲነጋ ፈረሶቻችንን እየጋለብን ወደ ማይቀረው ፍልሚያ ገሰገስን። የብስራት ነጋሪ ድምፆች ከየ አቅጣጫው አስተጋቡ ለጀነት የተሞሸሩ ባሎቻቸውን አበሰሩ። ከጥቂት ሰዓታት በኋላ የጠላት ኃይሎች አድማሱን እንደወረሩ አንበጣዎች ተሰለፉ። ያ ልጅ ሰልፉን ሰንጥቆ ገባ። የእብሪተኞችን ገላ እንደ ዱባ ያፈርጠው ይዟል። ልዩ የጦር ጥበብን ተክኗል። በጋለው የጦር መስክ ውስጥ ጠልቆ ባለንጣዎቹን እምሽክ ድቅቅ ማድረግ ጀምሯል። ከሙስሊሞች መካከልም ቁጥራቸው የበዛ ሰዎች ተሰውተዋል። ጦርነቱ ሰክኖ ሁለቱም ኃይሎች በየፊናቸው ሙታኖቻቸውን ለማንሳት ይሯሯጣሉ። መስኩ በደም ተጥለቅልቋል። የሰውነት አካሎች ተቆራርጠው ወድቀዋል። አድማሱ ላይ አሞራዎች ያንዣብባሉ። በደም ዥረትና በአቧራ የተለወሱ ፊቶች በርክተዋል። ማንነታቸው መለየት ሲበዛ ያዳግታል። ተዘርረው በወደቁ ፈረሶች መሃል አንድ ድምፅ ያስተጋባል። ድምፁ ወደ ሚመጣበት አቅጣጫ አመራሁ። የሸፈነውን አቧራና ያካበበውን የረጋ ደም እየጠረግኩ ስመለከተው የዚያች የሪቃዋ እንስት ልጅ መሆኑን አወቅኩ። እንባዬ ቀደመኝ አይዞህ አልኩት "ህልሜ እውን ሆነ" አለኝ። ከዓይኖቹ የሚረግፉ የእንባ ዘለላዎችን እና ከጉንጩ ላይ ፈሶ የደረቀ ደሙን በልብሴ እየጠረኩ አላህ ፊት በምስክርነት አስታውሰኝ እባክህ እንዳትረሳኝ አልኩት። "ያ አባ ቁዳማ! ትላንት በህልሜ የተመለከትኳት የጀነት ኮረዳ እኔን የራሷ ለማድረግ ነፍሴ ከአካሌ የምትለይበት ጊዜ እየጠበቀች ነው። ወላሂ አሁን በስተጀርባዬ በኩል ቆማለች ቅዠት ሳይሆን እውን የሆነ እይታ ነው። እርሷም ቸኩላለች እኔም ቸኩያለሁ። አላሁ ተዓላ ወደ ሀገር በሰላም ከመለሰህ ይህን በደም የሾቀ ልብሴን ለሪቃዋ እናቴ አድርስልኝ የጣለችብኝንም አደራ በአግባቡ እንደተወጣሁ ንገራት።
نمایش همه...
Palestine profile pic ❹ @Haro_Tik_Tok
نمایش همه...
نمایش همه...
የአላህ ስጦታ ለባሮች ከቀረቡ ታላላቅ የአላህ ሥጦታዎች መካከል ረመዳን ወር ግዙፉ ነው። በዚህ ጊዜ አላህ ለባሮቹ ያለው ፍቅር የሚገዝፍበት፤ ባሮቹ ወደርሱ እንዲመለሱ የሚያቀርባቸው በርካታ ዕድሎች አስገራሚ ሆኖ እናገኘዋለን። አላህ ባሮቹን የሚያናግርበት መንገድ፣ ባሮቹ ምንም ዓይነት ጥፋትና ወሰን ማለፍ ቢያከናውኑና ትዕዛዛትን ችላ ቢሉ ወደርሱ እንዲመለሱ ነው የሚጠራቸው። እያንዳንዱ የግዴታ ሰላት በረመዳን እንደሰባ የግዴታ ሰላት ይቆጠራል፣ ቀኑን በጾም ማታውን በሰላት ያሳለፈ ሰው ከወንጀሉ ምሕረትን ያገኛል። ሁሉንም ሌሊቶች አላህ ባሮችን ከእሳት ነጻ ይልበታል። የአላህ ቸርነትና ልግሥና በነዚህ ብቻ አይቆምም። በየለይለቱል ቀድር ሥጦታ ደግሞ ለየት ያለ ሽልማት ይዞልን ይመጣል። ይህችን ሌሊት እንደምናቀው በረመዳን የመጨረሻ ሌሊቶች ውስጥ ትገኛለች። በዚህች ሌሊት የአላህ ባሮች በተለያዩ አምልኮዎች ካሳለፉት ምንዳቸው የሚሆነው ከአንድ ሺሕ ወር በላይ እንዳደረጉት ይቆጠርላቸዋል። ከዚያ በላይ ይልቃል! ‹‹መወሰኛይቱም ሌሊት ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ? መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት።›› (አል-ቀድር፣ 2-3) ፍጡራንን የሚወደው፣ አዛኙና ቸሩ ጌታችን አላህ እነዚህን ሁሉ ካስገኘልን በኋላ ምን ማለት እንችላለን?! ይህን የአላህ ውድ ሥጦታና ግዙፍ ዕድሎች ተጠቅመን ከእሳት ነጻ መሆን የለብንም?! ሳንጠቀምበትና ወደ አላህ ሳንመለ ስበት ልንተወው አይገባም። ተከታዩ ሐዲሥ ይህን ሐሳብ ይገልጽልናል። መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡- ‹‹ረመዳን ገብቶ ምሕረትን ሳያገኝበት ያለፈው ሰው አፍንጫው መሬት ላይ ይታሽ (ውርደት ያግኘው)!›› ቲርሚዚ ዘግበውታል (5/550 ቁጥር 3545) ሓኪም (1/734 ቁጥር 2016) አሕመድ(2/254 ቁጥር 7444) በረመዳን ወር ያልሠራ ሰው መቼ ነው የሚሠራው? በረመዳን ምሕረት ያላገኘ ሰው መቼ ነው ምሕረትን የሚያገኘው? ይህ ወር የይቅርታ፣ የምሕረትና የአላህ ሥጦታ የሚገኝበት ወር ነው። @Haro_Tik_Tok @Abdi_Wiz_Kid34
نمایش همه...
Remedan vibes💜 @Haro_Tik_Tok @Abdi_Wiz_Kid34
نمایش همه...
🇵🇸🇵🇸 በነገራችን ላይ ፍልስጢናዊያን 14 ሰአት ከ59 ደቂቃ ያህል ከፆሙ ቡሀላ ነው መግሪብ ደርሶ የሚያፈጥሩት😁 @Haro_Tik_Tok @Abdi_Wiz_Kid34
نمایش همه...
- 7 | رمضان. 🌙 " صَلَّىٰ عَليكَ اللهُ يا مَن ذِكرهُ شرحَ الصُّدورَ وطيَّبَ الآفاقَا " ﷺ ..💚 : اللهم صل وسلم وبارك على من كان بنا رحيماً . @Haro_Tik_Tok @Abdi_Wiz_Kid34
نمایش همه...