cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Addis Powerhouse

A Feminist Media committed to amplifying women’s voices and creating participatory spaces for women in Ethiopia.

نمایش بیشتر
أثيوبيا7 420انگلیسی134 872دسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
1 899
مشترکین
+124 ساعت
-17 روز
+730 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

የአይዳሚያ ሴቶችን የንቅናቄ ታሪክ እና የትግል ጉዞ የቃኘንበት ዘጋቢ ፊልም አሁን ተለቋል! ሙሉውን በዩትዩብ ገፃችን ታገኙታላችሁ። 👇🏾 https://youtu.be/sUtRvZeEu5c?si=950RDVCrXCMhNxF-
نمایش همه...
የአይዳሚያ ንቅናቄ | የሴቶች ትግል፣ የህዝብ ነፃነት

ይህ ዘጋቢ ፊልም በደቡብ ኢትዮጵያ ላይ በምትገኘው ወላይታ ሶዶ፣ አራት ቆራጥ ሴቶች ስለመሰረቷት አይዳሚያ የምትባል ንቅናቄ ታሪክ እና የትግል ጉዞን የሚቃኝ ነው፡፡ እነዚህ ሴቶች ከሕዝባቸው ጥያቄ እና ከራሳቸውን ሕልም በመነሳት፣ የጋራ ድምጻቸውን ወደ አቅም በመቀየር፣ ሴት ልጅ በማህበረሰብ ጉዳዪች ላይ እንድትሳተፍ ፈር ቀዳጅ የሆኑ ስራዎችን ሲሰሩ አንደቆዩ በዝርዝር ያሳያል። ይህ በእህትማማችነት የተቃና የመብት ትግል የአይዳሚያ ሴቶች ታሪክ ነው። እንደምትወዱት ተስፋ እናደርጋለን። This documentary explores the history and struggle of the Aydamiya movement, founded by four determined women in Wolayta Sodo, southern Ethiopia. It shows in detail how these women, starting from their people's demands and their own dreams, turned their collective voice into power. This is the story of Aydamiya women's struggle for rights through sisterhood. We hope you are inspired by it.

6
በዛሬዋ አጅሪት ፖድካስታችን የፋይናንስ እና ቴክኖሎጂ ለዉጦች ለሴቶች ምን ይህል ቅርብ ናቸው ሚለውን እየተጫወትን ቆይተናል፡፡ Let us know your thoughts 👇🏾 Part Seven: Women’s Digital Financial Freedom
نمایش همه...
እኛን ያገናዘበ ለውጥ | የገንዘብ እና የፋይናንስ ቴክኖሎጂ ነፃነት

ለዚህ season የመጨረሻዋ በሆነችው የአጅሪት ፖድካስት ክፍላችን ስለገንዘብ እና የፋይናንስ ቴክኖሎጂ አቅርቦት፣ ተደራሽነት እና እውቀት እንጫወታለን። አክለንም ስለሴቶች የባንክ እና ሌሎች የፋይናንስ ዘርፎች ውስጥ ያላቸው የውሳኔ ሰጭነት፣ እና ተጠቃሚነት የፌሚኒስት መነፅራችንን አድርገን ከዛሬዋ አጅሪታችን ሊያ ዳንኤል እና እንግዳችን ሀዊ ዳዲ ጋር በመሆን ቃኝተናል፡፡ ቪድዮን ከወደዳችሁት like, follow, share and subscribe ማረግ እንዳትረሱ። በዚህ ክፍልም ሆነ season ባጠቃላይ በነበሩን ክፍሎች ላይ በተወያየንባቸው ጉዳዮች ዙርያ ማንኛውንም አይነት ጥያቄ ወይንም አስተያየት ካላችሁ ከስር ፃፉልን፣ ለመመለስ ዝግጁ ነን!

7
ሴቶች እና ፖለቲካ በሚል ርዕስ አዲስ የአጅሪት ፖድካስት ክፍል ይዘን መጥተናል። ሙሉዉን ክፍል በዩትዩብ ገፃችን ያገኙታል👇🏾 Part Six: Politics and Feminism
نمایش همه...
ሴት በማጀቱ፥ ወንድ በችሎቱ | ሴቶች እና ፖለቲካ

በዚች አጀሪት ፖድካስት ክፍላችን ሴቶች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ወስጥ ስላላችው ትሳትፎ እና ስለሚሰጣቸው ቦታ፣ ፖለቲካ ውስጥ ያሉ ሴቶች የግል እና ማህበራዊ ሕይወት፣ አያይዘንም የፖለቲካ አክቲቭስም ምን አይነት ገፅታዎች ሊኖሩት እንደሚችሉ ተጫውተናል። የዛሬዋ አጅሪታችን ጽዮን እንግዳዬ ከራሷ የፖለቲካ ገጠመኞች ተነስታ እንግዳችን እና የዞን ዘጠኝ የፖለቲካ አክቲቭስት ቡድን መስራች አባላት መሃከል ካለችው ሶልያና ሽመልስ ጋር እየተወያየች ቆይታለች። ቪድዮን ከወደዳችሁት like, follow, share and subscribe ማረግ እንዳትረሱ። በተወያየንባቸው ጉዳዮች ዙርያ ማንኛውንም አይነት ጥያቄ ወይንም አስተያየት ካላችሁ ከስር ፃፉልን፣ ለመመለስ ዝግጁ ነን!

5👏 2👍 1
Have you ever wondered what a local grassroots women’s movement in Ethiopia looks like? Meet Aydamiya, a movement based in Wolayita and rooted in sisterhood, solidarity and resistance. Full documentary will premiere on July 6, 2025 on the Addis Powerhouse YouTube page. Aydamiya Women’s Movement
نمایش همه...
አይዳሚያ ንቅናቄ | የሴቶች ትግል፣ የህዝብ ነፃነት

በደቡብ ኢትዮጵያ ላይ በምትገኘው ወላይታ ሶዶ እምብርት ላይ አራት ቆራጥ ሴቶች ከሕዝባቸው ጥያቄ እና ከራሳቸውን ሕልም በመነሳት፣ አይዳሚያ የምትባል ንቅናቄ ለሴት እህቶቻቸው አበርክተዋል፡፡ ንቅናቄው ወላይታ ውስጥ የሴቶችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ለማጎልበት ሲባል አባታዊ ስርአት ላይ በማመጽ የተመረኮዘ ቢሆንም፣ ፣ የፍትህ ጥያቄዎቻቸው በወላይታ ሶዶ ማንነት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ስራቸው ውጤታማ ሊሆን ችሏል፡፡ ይህ የንቅናቄያቸው ታሪክ በመብት ትግላቸው ዉስጥ ያሳለፏቸዉን ጥቃቶች፣ እስር፣ ብሎም እስከ ሞት ድረስ ያጋለጧቸዉንከባባድ ፈተናዎች በአብሮነት እና በእህትማማችነት እንዴት እንደተቋቋሙ ያወሳል፡፡ ከነሱ ጋር በቆየንበት ጊዜ የሰራነው ገላጭ ፊልም በቅርብ ይለቀቃል። ዮትዮብ ላይ ይጠብቁን።

10
በሴቶች መሃል ያለን ግንኙነት በራሳችን አንደበት የምንቃኝባት የአጅሪት ፖድካስት ተለቃለች። “ሲጀመር ሴቶች ይግባባሉ እንዴ” እና “እኔ ከሴት ጋር ጓደኛ መሆን አልችልም” ለሚሉ ሰዎች መላክ ይቻላል። ሙሉዉን ክፍል በዩትዩብ ገፃችን ያገኙታል👇🏾 Part Five: Being a Girls' Girl (Female Friendships)
نمایش همه...
እህቴ መድኃኒቴ | "ብሮ ኮድን" በኛ መዝገበ ቃላት

በዚች የአጅሪት ፖድካስት ክፍል ሁለት ሴት ጓደኛሞች በብዛት ስለሴቶች ግንኙነት ማህበረሰባችን ያለውን አመለካከት እና እውነተኛውን የእህትማማችነት/ የሴቶች ሴት (girls’s girl) የመሆን ትርጉም ከራሳቸው ሕይወት፣ ከንቅናቄያቸው እና ከየተለያዩ ጥናቶች ተነስተው ያወጋሉ። በ popular culture (በሚድያ ፣ ፊልሞቻች/ ዘፈኖች፣ እና እውቅና ያላቸው ሰዎች በሚመሯቸው ባህሎች) ውስጥ ሴቶች ግንኙነቶች የሚሳሉባቸው እና እንዲጫወቱ የምፈቀዱላቸው ገፀ-ባህሪዎችን ዳሰን፣ ወደራሳችን ዓለም እንጋብዛቹሀለን። የዛሬዋ አጅሪት ማህሌት ውብሸትስትሆን፣ አብራት በፀሎትከፈለኝ ትቆያለች። ቪድዮን ከወደዳችሁት like, follow, share and subscribe ማረግ እንዳትረሱ። በርዕሳችን ላይ ወይም በተወያየንባቸው ጉዳዮች ዙርያ ማንኛውንም አይነት ጥያቄ ወይንም አስተያየት ካላችሁ ከስር ፃፉልን፣ ለመመለስ ዝግጁ ነን!

7🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ፈረስና ሌሎች የሜትር ታክሲ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ስለአገልግሎት አሰጣጣቸው፣ በተለይም ከጾታዊ ጥቃት ጋር በተያያዘ ለቀረበላቸው ቅሬታ በጎ ምላሽ ይሰጣሉ ብለን በትግስት ስንጠብቅ ቆይተናል። ሆኖም እስካሁን በይፋ የሰጡት ምላሽ የለም። በመሆኑም የራሳችንን ደህንነት ለማስጠበቅ ታሪካችንን እንመዘግባለን፣ የሚጮኸውን ዝምታቸውንም በማስረጃ እንሰብራለን። ይህንን ጉዳይ በተመለከተ መረጃ በማሰባሰብ ሂደት ላይ ተሳታፊ ለመሆን ከዚህ ቀደም የሜትር ታክሲ ስትጠቅሚ ማንኛውም አይነት ፆታዊ ጥቃት ደርሶብሽ ካወቀ ታሪክሽን አጋሪን። ያንቺ ድምፅ የእህትሽ መዳኛ ሊሆን ይችላል። በጋራ ስንጮህ እንደመጣለን። Link to the survey ታሪክሽን እዚህ አጋሪን ✍🏾
نمایش همه...
15🔥 3👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
Empowering women in finance! Government, financial institutions, mobile operators, NGOs, and tech firms all have a responsibility to bridge the gender gap in digital finance. From setting clear targets for account ownership to offering financial products designed for women's needs and supporting female leadership within their organizations, they can create a more inclusive financial system. Let's #CloseTheGap! Source: Making Ethiopia's Financial Sector Work For Women: March 2024, World Bank’s Africa Gender Innovation Lab (GIL) and National Bank of Ethiopia (NBE)
نمایش همه...
👍 5
ምግብ ማብሰል ፦ ለሴቶች ብቻ የተመደበ ስራ ወይስ ሁሉም መማር ያለበት ሙያ? ሙሉዉን ክፍል በዩትዩብ ገፃችን ያገኙታል | subscribe to our channel and leave a comment 👇🏾 Episode Four (part two): Healthy Relationships
نمایش همه...
“አያድርስ፥ የባል ቢስ” | ጤናማ የፍቅር ግንኘት

በሁለተኛዋ የአጅሪት ክፍል አራት ቆይታችን በወንዶች እና በሴቶች መሃከል የሚገኘው የፍቅር ግንኙነትን በፌሚንስት መነፅራችን እየመዝነን መወያየታችንን ቀጥለናል። አክለንም ዕድሜ፣ ውበት ፣ ፀባይ፣ ገንዘብ ወዘተ በማኅበረሰቡ፣ ብሎም በአባታዊ ስርዓት ውስጥ ምን አይነት ፆታዊ ተፅዕኖ ይዘው እንደሚመጡ በሰፊው ውይይት እናድርገናል። የዛሬዋ አጅሪታችን ቃልኪዳን አስማማው ውይይቱን ከተጋባዥ እንግዶቻችን እስከዳር ታደሰ እና በፍቃዱ ሀይሉ ጋር ታደርጋለች። እንደሁሌም ጥያቄያችሁን ለመመለስ ዝግጁ ነን፣ አስተያየታችሁን ከስር አስቀምጡልን!

4
Photo unavailableShow in Telegram
Ethiopian women are significantly underrepresented in leadership positions within financial institutions. They make up 26% of the workforce in financial institutions, and only 5% hold decision-making roles. In private commercial banks, women's representation is (nearly) 30% in lower management and less than 10% in senior positions. Women hold ONLY 15% of board director roles in commercial banks. This disparity underscores a critical gap in gender equality at the top. The National Bank of Ethiopia targets 25% female representation in senior management by 2025. Currently, only three institutions meet this goal, with a sector average of just over 12.5%. Alarmingly, six institutions have no women in executive roles at all. Let's push for greater gender equality in leadership! It's time to close the gap and ensure more women hold senior positions in financial institutions. Source: Making Ethiopia's Financial Sector Work For Women: March 2024
نمایش همه...
👍 3 3
Photo unavailableShow in Telegram
Compared to women, men KNOW significantly more about mobile money The gender gap in mobile money awareness has surged from 1% in 2017 to 14% by 2022. 48% of women who own phones but lack mobile money accounts reported needing to learn how to use mobile money as a significant obstacle. To address this issue, we need to improve women's financial literacy, increase access to DFS education, and create targeted outreach programs. This will empower women with the knowledge and tools they need for financial independence. Numbers speak louder than words! #Closethegendergap Source: Making Ethiopia's Financial Sector Work For Women (2024), World Bank’s Africa Gender Innovation Lab (GIL) and National Bank of Ethiopia (NBE)
نمایش همه...
3
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.