cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ፍኖተ ኦርቶዶክስ

የኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ሥርዓት እና አስተምህሮ የጠበቀ #ትምህርተ_ሃይማኖት ይሰጣል፡፡ በተለይ #ጥያቄዎቻችሁ መልስ ያገኛሉ ። መንፈሳዊ ትምህርት በመማር የሕይወትን ማዕድ ይቋደሱ ለመቀላቀል 👇👇ይጫኑ @finoteorthodox @finoteorthodox

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 406
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
-130 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
#ሰበር_ዜና ፨፨፨፨፨፨፧፨ ፨፨፨፨፨፨ ጥር 14 በሕገ ወጥ መንገድ በመሾማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ከተወገዙት መካከል አንደኛው ዛሬ የካቲት 5/2015 ዓ.ም የይቅርታ ደብዳቤ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት አስገቡ።
نمایش همه...
#Update ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ልኡክ በትናትናው እለት ከመንግሥት ጋር ባደረጉት ውይይት መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም #ሙሉ_በሙሉ የተቀበለ ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ እሁድ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ/ም እንዲካሔድ የተወሰነው ሀገር ዓቀፍ እና ዓለም አቀፍ የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም መወሰኑን ቅዱስ ሲኖዶስ አሳውቋል። (ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል) Credit : EOTC TV
نمایش همه...
ሰበር ዜና!! ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ትላንት ምሽት የመንግሥት ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል " ወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ " ን አስመልክቶ የተሰጠው የሰልፍ ክልከላ መግለጫ እንደማይቀበል አሳውቋል። ቅዱስ ሲኖዶስ የትላንቱ የመንግስት መግለጫ " መንግሥት አሁንም ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ለማውደምና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት የታወጀ አዋጅ መሆኑን በጽኑ እንድናምን አድርጎናል " ብሏል። ቅዱስ ሲኖዶስ መንግስት ከአጉል እልከኝነቱ ወጥቶ ፦ - ከሕገ ወጦቹ ግለሰቦች ጋር በመተባበር በአደባባይ እየፈጸመ ያለውን የሕግ ጥሰት ዛሬን ጨምሮ በቀጣዮቹ ፪/ሁለት/ ቀናት ውስጥ እንዲያቆም እና ሕግ እና ሥርዓትን እንዲያስከብር - በኃይል የወረራቸውን መንበረ ጵጵስና እና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ለቆ ለቤተክርስቲያኒቱ ሕጋዊ መዋቅር እንዲያስረክብ፣ - ያለአግባብ ያሠራቸውን ካህናት እና ምእመናን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ፣ - ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ለፈፀመው በደል በአደባባይ ይቅርታ እንዲጠይቅ፤ - በካህናት እና ምእመናን ላይ ለደረሰው ሞት እና የአካል ጉዳት ተገቢውን ካሳ እንዲክስ እና የወደሙ ንብረቶቿን እንዲጠግን በጥብቅ ጠይቋል። መንግሥት ድርሻው ሰልፉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት ብቻ መሆኑን ያሳሰበው ቅዱስ ሲኖዶስ " ዛሬም ቢሆን መንግሥት ቆም ብሎ በማሰብ ከእኛ ከአባቶች ጋር ሃይማኖታዊ ፣ ቀኖናዊ እና መንፈሳዊ የአስተዳደር ሥርዓታችንን ባልጣሰ መልኩ ለመነጋገር እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ጥረት ካደረገ በውይይት ለመፍታት መንፈሳዊ በራችን ክፍት መሆኑን እናሳውቃለን " ብሏል። (ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)    
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#አዋጅ_አዋጅ_አዋጅ_ለሕዝበ_ክርስቲያን_በሙሉ #ጾመ_ነነዌ ➛ ጥር 29/2015 ዓም (feb, 6/2023GC) #ዐቢይ_ጾም ➛ የካቲት 13/2015 ዓም (feb, 20/2023 GC) የሚገባ መሆኑን እንድታውቁት!!!
نمایش همه...
ጥር 22 ቀን በግብፅ አገር ከአቅማን ከተማ የከበረና የገነነ የመነኰሳት ሁሉ አባት በገዳም ለሚኖር እንደ ኮከብ የሚያበራላቸው አባት እንጦንስ የእረፍቱ መታሰቢያ ነው። #የአባ_እንጦንስ_ምክሮች ✞ ከዕለታት በአንድ ቀን አባ ፓምቦ አባ እንጦስን "ማድረግ ያለብኝ ነገር ምንድን ነው?" ብሎ ይጠይቃል።አባ እንጦስም እንዲህ ሲል መለሰለት "በራስህ ጽድቅ አትታመን፤ላለፈው አትጨነቅ፤ይልቁኑ አንደበትህንና ሆድህን ግዛ።" ✞ አባ እንጦስ በአንድ ወቅት እንዲህ አለ፦ "በዚች ምድር ላይ ስንኖር ህይወታችንንም ሆነ ሞታችን ከባልጀራችን ጋር ነው። ወንድማችንን ገንዘብ ካደረግነው እግዚአብሔርን ገንዘብ እናደርጋለን፤ ወንድማችንን ካስቀየምነው ግን በክርስቶስ ላይ ኃጢአትን እናመጣለን።" ✞ በአንድ ወቅት አንድ ወንድም አባ እንጦስን "ጸልይልኝ" በማለት ይጠይቃል። እንጦስም "አንተ ራስህ ጥረት የማታደርግና ወደ እግዚአብሔር የማትጸልይ ከሆነ እኔም ሆንሁ እግዚአብሔር ምህረት ልናደርግልህ አንችም" አለው። ✞ እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው  ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ። ✞ ኃጢአታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል፤ ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል። ✞ ብዙ ጊዜ ሰዎች ብልህ ነን እያሉ ይሳሳታሉ። ነገር ግን ብልህ የሚባሉት ብዙ የተማሩና ብዙ ያነበቡ ብዙ የሚናገሩ ብቻ አይደሉም። ይልቁንም ጠቢባን የሚባሉት ጥብብት መጥበቢት ብልህ ነፍስ ያላቸው፤ የእግዚአብሔርንና የሰይጣንን ለይተው ለእግዚአብሔር ሆነው የሚኖሩ ናቸው። ፍጹም ምልዓተ ኃጢአትንና ከጦር ይልቅ የሚወጉ የኃጢአት እሾሀቸውን የነቀሉ ናቸው ጠቢባን። ✞ ጠቢባንስ እግዚአብሔርን ያለጥርጥር በሙሉ ልብ የሚያምኑት፤ አምነውም እንደ ፈቃዱ የተከተሉት፤ በክንፈ ጸጋ ተመስጠው ከልብ በሚወጣ ውዳሴ ከእርሱ ጋር ተዋሕደው የሚኖሩ ናቸው። የነፍሳቸውን ረብሕ ጥቅም አውቀው ዕለት ዕለት ያንን የሚለማመዱ በእውነት ጠቢባን እነዚህ ናቸው። ✞ የጋለ ብረትን ለመቀጥቀጥ የሚነሣ ሰው አስቀድሞ በብረቱ ምን ለመሥራት እንዳሰበ መወሰን አለበት፤ መጥረቢያ፥ ሰይፍ፥ ወይስ ማጭድ? እኛም በምን ዓይነት የሕይወት መስመር ፍሬ ለማፍራት እንዳሰብን አስቀድመን ልቡናችንን ማዘጋጀት አለብን፡፡ ✞ ዘወትር በዐይንህ ፊት ፈሪሃ እግዚአብሔር ይኑር፤ ሕይወትና ሞት የሚሰጠውን አዘክረው፡፡ ዓለምንና በዓለም ያለውን ሁሉ ጥላው፤ ከሥጋ የሚመጣውን ደስታና ሰላም አትሻ፤ ለዚህኛው ኑሮ ሙትና ለእግዚአብሔር ሕያው ሁን፤ ለእግዚአብሔር ቃል የገባኸውን አትርሳ፤ ያም በፍርድ ቀን ካንተ ይፈለግብሃል፡፡ ረኀብን በጸጋ ተቀበለው፤ ተጠማ፥ ተራቆት፥ ንቁና በሐዘን የምትኖር ሁን፡፡ በልቡናህ አልቅስና ጩኽ፤ ለእግዚአብሔር የምትመች መሆን አለመሆንህን ፈትን፤ ሥጋህን ቀጥተህ ነፍስህን ታድናት ዘንድ፡፡ ✞ የቱንም ያህል በመከራ ቢወድቅብህ የቱንም ያህል በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ብታልፍ ይህንን ለጌታዬ ለመድኃኒቴ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስል እቀበላለሁ በል። ቀላል ይሆንልሀል። የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ኃይል ነውና። በእርሱ ማእበሉ ፀጥ ይላል ሰይጣንም ይሸሻል። ✞ ለተወሰን ጊዜ ለሀይማኖት መከራከር፤ ጠበቃ መሆን፤ መዋጋት ብሎም መሞት አይከፋም ሁልጊዜ ለሀይማኖት መኖር ግን ከሁሉ የበለጠ መስዋእትና ክብር ያለው ህይወት ነው፡፡ (#ከተለያዩ_ጽሑፎች_የተሰበሰቡ)
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
"በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፣ በማንነቷ፣ በሉዓላዊነቷ፣ በአንድነቷ፣ በዓለም አቀፋዊነቷ ድርድር  የለም። የቤተክርስቲያንን መብትና ጥቅም ማስከበር የእኛ የአባቶች ድርሻ ነው። ምዕመናን በተለይም ወጣት ልጆቻችን የቤተክርስቲያናችሁን ድምጽ መስማትና ማክበር ይኖርባችኋል።"                 ብፁዕ አቡነ አብርሃም    የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና         የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ምንጭ: የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
"በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፣ በማንነቷ፣ በሉዓላዊነቷ ፣ በአንድነቷ፣ በዓለም አቀፋዊነቷ ድርድር የለም። የቤተክርስቲያንን መብትና ጥቅም ማስከበር የእኛ የአባቶች ድርሻ ነው። ምዕመናን በተለይም ወጣት ልጆቻችን የቤተክርስቲያናችሁን ድምጽ መስማትና ማክበር ይኖርባችኋል።" ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ምንጭ: የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ ከታፍኑበት ተፈተዋል። ማኅበረ ቅዱሳን
نمایش همه...
የጅማ ደብረ ኤፍራታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በሌሉበት አይመረቅም! የጅማ ኦርቶዶክሳውያን በዛሬው ዕለት ለዓመታት የለፉባትንና ቅዳሴ ቤቷ ይከበራል ተብሎ በተጠበቀው የቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን ሲጠብቁ ቢውሉም ከአባታቸው ጋር ሳይገናኙ ቀርተዋል። የጅማ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በስፍራው ስለማይገኙ ቆሞሳት ባርከው ቤተ ክርስቲያኗ ትመረቅ ቢባሉም ምዕመናኑና ማኅበረ ካህናቱ እሳቸው የደከሙበትን ቤተ ክርስቲያን በሌሉበት አናስመርቅም፤ ይህ የኛ ቀን ነው፤ በእግዚአብሔር ቀን አባታችን ባሉበት እናስመርቃለን፤ የሠራነው የእግዚአብሔርን ቤት ነው ለምን ተፈተንን አንልም ብለዋል። የቤተ ክርስቲያኑ ምርቃት ወደ ሌላ ቀን መዘዋወሩንም  የደብሩ አስተዳዳሪና አሠሪ ኮሚቴው ለሕዝበ ክርስቲያኑ ይፋ አድርገዋል። ነገ በዓለ ንግሷ በቀድሞ ቤተ ክርስቲያን (በመቃኞ) ተከብሮ ይውላል። በተያያዘ ብፁዕነታቸው በዚህ ሰዓት አዲስ አበባ ገብተዋል።
نمایش همه...