cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ኢስላም ሚዲያ

ኢስላሚክ ሚዲያ አላማዉ ኡማዉን በሀቅ ለማገልገል ነዉ ከተዛቡ ዉሸት ከሆኑ ዜናዎች ማራቅ ነዉ ትክክለኛ መረጃ ለማድረስ እንተጋለን

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

★ #አስቾካይ_የእርዳታ_ጥሪ! እኔ ስሜ አንዋር ሁሴን አባ ዱራ የተባልኩ የ20 ዓመት ወጣት የ1 ዓመት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ስሆን፣ ላለፉት 3 አመታት አፒላስቲክ አኒሚያ(Aplastic Anemia) ተብሎ በሚጠራው የደም በሽታ በመያዜ የአጥንት መቅንዬ ሙሉ በሙሉ ደም ማምረት አቁሟል። በመሆኑም የጥቁር አንበሳ ሃኪሞች ወደ #ውጭ_ሄጄ እድታከም በቦርድ ወስነዋል። ለህክምናውም ከወላጆቼ አቅም በላይ የሆነ 2,500,000 ብር በላይ ያስፈልገኛል።በመሆኑም ውድ ወገኖቼ እህቶቼ ወንድሞቼ በአቅማቹ እንድትረዱኝ እማፀናችዋለሁ። ★የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ(CBE) 1000337570918 ★የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ(COOP) 1000077415096 ስልክ ቁጥር-09 39 50 46 54 @Alhamdumuredu
نمایش همه...
ፍልስጤም ክፍል 1 ✍ አብዲ ኢኽላስ ብዙዎቻችን በአሁን ሰዓት ፍልስጤም ላይ በወራሪዋ እስራኤል እየደረሰ ባለው ጥቃት ተቆጥተናል። ነገር ግን ትክክለኛ የፀብ ምክንያታቸውንና የታሪኩን አነሳስ ስንቶቻችን እናውቃለን?? ለዛሬ በክፍል 1 ፅሁፋችን የነገሩ ጥንስስ ከየት እንደሚጀምር ለማየት እንሞክራለን : ጉዳዩ ሚጀምረው ከኡስማንያ ስረወ መንግስት መውደቅ ጋር ተያይዞ ነው። በዘመኑ መቀመጫውን ቱርኩ ያደረገው የኡስማንያ ኢስላማዊ እምፓየር በምዕራበውያን ተሸንፎ ወደቀ ፣ ከዛም አልፎ በክፉ የአውሮፓ ባለ ስልጣናት አማካይነት ኡስማንይ የሆኑ አስተሳሰቦችና አስተዳደሮች ለታሪክ እንዳየወተርፉ ተደርገው መፈራረስ ጀመሩ በዚህ ምክንያት ከጥንት ጀምሮ በነ አርጦግሮል እና በሌሎችም ሲቀባበል የመጣው ታላቁ ኢስላማዊ አገዛዝ ለከሀድያን እጅ ሰጠ በዚህ ግዜ እንደ እንግሊዝ ጣልያንና መሰል ያሉ ሀገራት ኢስላማዊ ግዛቶችን መቆጣጠርና ማፈራረስ ጀመሩ። በዚህ ወቅት ነበር ታላቋ ፍልስጤም አይናቸው የገባችው። ፍልስጤም በሰዓቱ እጅግ በተዋበ ተፈጥሮአዊ ፀጋ ያሸበረቀች ከመሆኗ በላይ በግብፅ በኩል አፍሪካን እና መካከለኛውን አረብ የምታገናኝ ብቸኛ ሀገርም ነበረች። ሙስሊም ሀገራት አፍሪካዊ እና አረባዊ ሀይላቸውን በማቀናጀት ጠላት ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩባት ቅድስት ስፍራም ነበረች። ለዚህ ነው እንግዲ አውሮፓውያን በአፍሪካዊቷ ግብፅ እና በፍልስጤም መሀል ግንብ ካልተገነባ ሙስሊሞች አንድ ላይ የሚሆኑበት እድል ሰፊ ስለሚሆን አንችላቸውም በማለት ለሙስሊም ጠላት የሆኑትን እና ለምዕራባውያን ምች የነበሩትን አይሁዳውያንን (እስራኤልን) ፍልስጤም እና ግብፅ መሀል ማስፈር ያስፈለጋቸው። የሙስሊም አገዛዝ መውደቁን ተያይዞ ፍልስጤምን እንዳሻት ታደርግ የነበረችው እንግሊዝ አይሁዳውያንን ማስፈር ጀመረች። ፍልስጤሞች የቱ ጋር ተሸወዱ? ብክፍል 2 ሀተታችን ይቀጥላል ... ✍ አብዲ ኢኽላስ 👉 @Alhamdumuredu
نمایش همه...
የወንድም ነጃ ዋበላ የድጋፍ ማሰባሰቢያ አካውንት ይፋ ሆነ የአካውንት ስም:— ነጃ ዋበላ ሰኢድ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:— 1000399619533 #share @Alhamdumuredu @Alhamdumuredu @Alhamdumuredu
نمایش همه...
ስም➤ነጃ ዋበላ የስራ ቦታ➤መርካቶ ምዕራብ ሆቴል አካባቢ መኖሪያ አድራሻ➤አሸዋ ሜዳ የትዳር ሁኔታ➤ያገባ የሁለት ልጆች አባት ሲሆን በአሁኑ ወቅት ባልተቤቱ በእርግዝና ላይ ትገኛለች ነጃ የዚህን ቤተሰብ ጉሮሮ ለመሸፈን ፣ ባልተቤቱም በቀዶ ጥገና ነው የምትወልደው ስለተባለ ፣ ወቅቱ የረመዷን የፃም ወር ስለሆነ ፣ የቤት ኪራይ እና ሌሎችም ወጪዎች ስለሚጠብኩት ኑሮን ለማሸነፍ ሲታገል ስራቸውም ቢሆን በአግባቡ መስራት የነበረባቸውን ስራ ዘንግተው እጅግ በሚያሰቅቅ መልኩ ከዘረፋ ባልተናነሰ ሁኔታ በአላህ በአላህ ኧረ ልጆቼ ኧረ ልጆቼ እያላቸው ሲያሰቃዩት አይተናል ተመልክተናል ስለዚህ ሁላችንም የአቅማችንን ለመርዳት እንዘገጃጅ #ምስሉንም #ሐሳቡንም #መመካከሩንም ሼር ማድረጋችንንም አንዘንጋ @Alhamdumuredu @Alhamdumuredu @Alhamdumuredu
نمایش همه...
1.54 MB
ዑመር ድንገት ነቢ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤት ሲገባ እሳቸው መሬት ላይ ከተነጠፈ ጂባ ላይ ተኝተዋል። ከዘንባባ ቅጠል በተወተፈ ትራስ የተንተራሱት ነቢይም ከግርጌያቸው አንድ ግንድ አለ። ዑመር የነቢን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰውነት አትኩሮ ሲያይ የጂባው ቅርፅ ሰውነታቸው ላይ ሰንበር አውጥቶ ተመለከተ። ጠንካራው ዑመርም ለቅሶ ጀመረ። «ዑመር! ምን ያስለቅስኃል?» ነቢ ጠየቁት። «ያ ረሱለሏህ! የሮም እና የፐርሺያ ንጉሳን ከነክህደታቸው እንዲ ተደላድለው ሲኖሩ አንቱ ነቢይ ሁነው እንዴት...!» «ዑመር ሆይ! ዱንያ ለነሱ አኪራ ለኛ ብትሆን አይሻለንም? እነሱ እኮ መጠቃቀምያቸው ዱንያ ላይ የተደረገላቸው ህዝቦች ናቸው» በእርስዎ ሰበብ አንድ ሰው ቢቶብት ወይም ባለበት ጠንካራ አቋም ላይ ቢፀና ከፍተኛ አጅርን ይጎናፀፋሉ እባክዎ ለወዳጅ ዘመድዎ ሼርና ፎርዋርድ በማድረግ ያዳርሱ በቻናላችን በሚሰጡ ትምህርቶች ተሳታፊ ለመሆን ይህን ይጫኑና ጆይን ይበሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇 @Alhamdumuredu @Alhamdumuredu @Alhamdumuredu
نمایش همه...
ስለ ኢትዮጵያ አልቅሱ!😢😢😢 ሁላችሁም ሼር አድርጉት❗️❗️ - አስተዋይ፣ ትልቅ ሰው የጠፋባት። - ሰው ለሰው እባብ የሆነባት። - እባቦች ግን የተፋቀሩባት። - ገላጋይ አስታራቂ የጠፋባት። - ከሰው ሚዛን ይልቅ የሸቀጥ ሚዛን የበዛባት። - በቁስል ላይ ጋሪንጣ ሰዳጅ የሞላባት። - በገለባ ላይ እሳት ጫሪ የበዛባት። - ለብር ሲል ህሊናውን የሸጠ የሚኖርባት። - ትልቁ ትንሽ የሆነባት። - ጠበኞችን ገላጋይ የሌለባት። - ግጭት ናፋቂ የበዛባት። - የሰው ደም የጠማው የሚኖርባት ። - ለህሊናው፣ ለሃገሩና፣ ለፈጣሪው የማይታመን የሰፈረባት። - መንፈሳዊው ተኩላ፣ ተኩላው መንፈሳዊ የሆነባት።-ግራ አጋቢ ነገር። - ጅቦች ከበጎች ጋጥ የከተሙባት። - ንቦችና ጉንዳኖች መሪ ባገኙበት ሰአት ሰው የሆነ መሪ የጠፋባት የሰው ልጅ እንደ በግ በየቀኑ እሚታረዱባት ሀገር ሆናለች፤ ኢትዮጵያ። ✅ @Alhamdumuredu @Alhamdumuredu @Alhamdumuredu
نمایش همه...
#ምናለ_በረመዷን_እንኳ_አደብ_ብትይዙ አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካትሁ ጀሚዐን #መቼ_ነው_ግን #ደሴ_ላይ_ህግ_ሲከብር_ለቅፅበት_ያክል_እንኳን_የምናየው😭😭😭😭😭😭😭 እነሆ እደሚታወቀው ከ 3 አመታት በፊት በሸዋበር መስጅድ አሸባሪው የወሀብያ ቡድን ግርግርና ረብሻን በመፍጠር ከሙሰኛ የመንግስት አካል ጋር ሆኖ ሙስሊም ሱፍያዎችን ከመስጅዱ በማባረርና እስካሁን ድረስ 6 ወንድሞቻችንን ጉቦ በመስጠት ረመዷንን በስር ቤት እንዲያሳልፉ ማድረጋቸው ሳያንስ በቃለ ጉባኤ ስምምነት 👉 የደሴ ከተማ እስልምና ጉዳይ ፣ የደ/ወ ዞን እስልምና ጉዳይና የ1ኛ ፖሊስ ጣቢያ እኒስፔክተር አቶ ጌታቸው እንድሁም ሌሎችም ባለስላጣኖች በተገኙበት የሸዋበር መስጅድ ነባር ኮሚቴ ቢሮ ከነሰነዱ ለመስጅዱ መፍትሔ እስኪገኝ ድረስ ተብሎ በቃለ ጉባኤ ተስማምተውና ተፈራርመው እንዲታሸግ መደረጉ ይታወቃል። ሆኖም አሸባሪው የወሀብያ ቡድንም መሰሎቻቸው የፌደራል መጅሊስን ቢሮ ሰብረው ማህተም እንደሰረቁት ሁሉ ( #ሚያዚያ 8 / 2013) የሸዋበር መስጂድ ነባር ኮሚቴዎች ቢሮ የነበረውን ቃለ ጉባኤውን ጥሰው ቢሮውን ሰብሮ በመግባት የተለያዩ ሰነዶችንና መረጃዎችን በመዝረፍ ላይ ይገኛሉ። መንግስትም ህግ ሲጣስ እያየ እንዳላየ የሚያልፈው ነገር በጣም እያገራረመን ነው #መንግስት_በአስቸኳይ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ጥያቄዎች በአስቸኳይ ምላሽ ይስጥልን 1, መንግስት በአስቸኳይ በበደል ለታሰሩ ወንድሞቻችንና አባቶቻችን አስቸኳይ እልባት ይስጥልን 2, በህገ ወጥ መልኩ በዘራፊው የወሀብያ መንጋ የተዘረፉ መስጅዶችን ወደ ነባሩ ሙስሊም ይመልስልን 3, በህገ_ወጥ መልኩ ወሀብያዎች እያቀሳቀሱት ያለውን ድርጊታቸውን በማስቆም እርምጃ እንደወስድልን እንጠይቃለን 4, ደሴ ከተማ ላይ ፍትሀዊ የሆነ አሰራር እንዲኖር ኪራይ ሰብሳቢ አካላቶችን መንጥሮ ሊያወጣ ይገባል #ሸዋበር_መስጂድ_የፖለቲካ_ማራመጃና_የማንም_መፈንጫ_ሳይሆን_የሙስሊሞች_ኢባዳ_ማድረጊያ_ቤት_ነውና_ወደ_ባልተቤቱ_ይመለስ ሁላቺንም ሸር በማድረግ እንድንሳተፍ በአሏህ ስም እንጠይቃችሗለን https://t.me/assunah_jemea/1438
نمایش همه...
,አስ_ሱናህ ጀመዓ ⇄ AS_SUNNAH JEMEA

💞ታላቁ የአሏህ መልእክተኛ የኛ ነብይﷺ ማግኘት ለቻለ ሰው ለኢፍጧርም ሆነ ለ ሰሁር ተምርን አብሮ መጠቀምን የተሻለ እንደሆነ ማስተላለፋቸው ለምን ነው? °------------------------------------------------° 📋ይሔውልህ የዛሬ ዘመን ሳይንቲስቶች የነብያችንንﷺ ንግግር በሙሉ ድምፅ ድጋፍ አድርገው የጥናታቸውን ውጤት አስቀምጠዋል። 💎10 (አስር) ወሳኝ የተምር ታላላቅ ጥቅሞች👇 🕯1,የሆድ ድርቀት ለመከላከል 🕯2,የልብ ህመም ለመከላከል 🕯3,ከአኒሚያ ህመም ለመጠበቅ 🕯4,አለርጂክ ለመከላከል 🕯5,ለስንፈተ ወሲብ ችግር 🕯6,ለአጥንት ጤናና ጥንካሬ 🕯7,ለከፍተኛ ሀይልና ብርታት ምንጭነት 🕯8,ተመጣጣኝ ክብደት ለማግኘት 🕯9,የአንጀት ካንሰር ለመከላከል 🕯10,ለጤናማ የነርቭ ስርአት እኖዳቹሀለን ነብየ ያንቱ ያደረገን አሏህ ምስጋና ይገባው #ለወንድም_እህትህ_ሸር_አድርግላቸው 👉 @Alhamdumuredu @Alhamdumuredu👈
نمایش همه...
'ሱፍዩን' ለማጥቃት ሲፈለግ በቅድሚያ ስሙ አህባሽ ይባላል። በወሀቢ እሳቤ አህባሽ የሆነ ደሙ ሳይቀር ሃላል ነውና የሚደረግበት ጥቃትና በደል እንደ ፅድቅ የሚቆጠር ይሆናል። ከስር የምትመለከቱት Screenshot የፍል ውሃ መስጂድ ኮሚቴዎች የሚዘውሩት ገፅ ላይ እንዳስነበቡን ኢማሙን አህባሽ ካሏቸው በኋላ ከኢማምነት ሊያባርሩ ሞክረዋል። እኒህን ኢማም ለአመት ያክል ደሞዝ ከልክለዋቸዋል። ይህን ሲያደርጉም ለሙስሊሙ አንድነት እየሰሩ ነውና ከፋፋይ የሚላቸው ወሀቢ አይኖርም። ይህን ቀድመው ያዩት ሙፍቲያችን አትረብሽ ሲሉት "ከፋፈሉን" ብሎ ያለቀሰና ክብረ ነክ ስድቡን ሲያወርድባቸው የነበረ መንጋ ዛሬ አቂዳ እየለየ ሱፍዩ ላይ ጥቃት እያደረሰ ነው። ልክ ረመዳን አንድ ብሎ ሸይጧን ሲታሰር፣ ሰው ቀልቡን ወደአላህ ለማስጠጋት ወደ መስጂድ በተጠጋበት "አህባሽ" ባሏቸው የፍልውሃ መስጂድ ኢማም ሸይኽ አስራርን ተከትሎ ላለመስገድ ሌላ የወሀቢ ኢማም ለመተካት በተደረገ ሙከራ የመጀመሪያው ተራዊህ ሶላት በሚያሳዝን ሁኔታ ሳይሰገድ እንዲበተን አድርገዋል። ረመዳን ሁለት ላይ በተራዊህ ሶላት ሰዓት ችግር አልተፈጠረም። ከሶላት ወጥቶ ከተበተነ በኋላ ትላንት ለኢማሙ ሲከላከሉ የነበሩ ወጣቶች ከመስጂዱ በር ላይ በብረት ተደብድበው ሁለት ልጆች የአካል ጉዳትና ስብራት ደርሶባቸዋል። በዚህ አላበቃም የተደበደቡት ወጣቶች ያለበቂ ምክንያት በአካባቢው የፖሊስ ሃይል እንዲያዙ ተደርገዋል። ሁሉንም የወጣት ጀምዓ አባላት (ሴቶችን ሳይቀር) በክስ የያዙት የመስጂዱ ህገ ወጥ ኮሚቴዎች ይህን በደል የሚያደርሱት ወጣቶቹ ምንም ስላደረጉ ሳይሆን በኢኮኖሚ ጫና ስራቸውን ሊያቆሙ ያልቻሉትን ኢማም ያለተከላካይ በማስቀረት በጉልበት ለማስወገድ እዲመቻቸው የሚደረግ አካሄድ ነው። 'የሱፍይ መስጂድ' ላይ ይህን ሲያደርጉ መጅሊስ ውስጥ ያሉ የወሀቢ ተወካዮች ድጋፍ ያደርጉላቸዋል። ተቋማዊ ውንብድናውን ህጋዊነት ያላብሱላቸዋልና አስደብድበውም የመክሰስ ቁመና ማግኘት ችለዋል። በመቀጠል ሸህ ሰኢድ አህመድ ሙስጦፋ የሚያሰግድበት መስጂድ ላይ ደግሞ ተከታዩ አስነዋሪና አሳፋሪ ድርጊት ይታያል። መስጂዱ የአፍንጮ በሩ አቅሷ መስጂድ ነው። ከዚህ በፊት ሰዎችን ወደመስጂድ ለመጥራት በየመስጂድ የሚገቡ የዳዕዋ ሰዎች በረመዳን እንዳይገቡ ተደርገዋል። ምክንያቱም የዳዕዋ ጀምዐ "በመዝሀብ ኺላፍ አንገባም" ስለሚሉና የወሀቢን አስተምህሮት ስለማይሰብኩ 'አህባሽ' ወይም 'ሱፍይ' ተብለው በመፈረጃቸው ምክንያት ነው። በረመዳን ሁሉም ወደመስጂድ እንዲገባ ሲፈቀድለት እነዚህ የመስጂድ እርግቦች ዱንያን ትተው በመስጂድ ብቻ ለቀናት በሚኖራቸው የኢህቲካፍ ቆይታ ለምግብ ማብሰያና አልባሳታቸውን የሚያስቀምጡበት፣ አካባቢው ያሉ ሙስሊሞችን ወደመስጂድ ከጠሩ በኋላ ከፀሀይ ድካም ተመልሰው ለቀይሉላ አረፍ የሚሉበት ክፍል ነበር። ከስር በምትመለከቱት አሳፋሪ መልኩ ማረፊያ ቤታቸው በሰለፊ ኡስታዞች ትዕዛዝ አገልግሎት እንዳይሰጥ ተደርጓል። ሰው ወደመስጂድ እንዳይጠራ በማድረግም ሆነ የዳዕዋ ሰዎችን ማረፊያ እንደዚህ በማሸግ የሚገኝ ሸይጧናዊ እንጂ ሰዋዊም ሆነ ሃይማኖታዊ ጥቅም አይኖርም። አንድ እንሁን እየተባለ ያለው ከእነዚህ ፀረ ሰላም የፋሺስት አስተሳሰብ አራማጆች ጋር በመሆኑ እስካሁን ብዙ ትዕግስት አድርገን የአባታችንና የሙፍቲያችን ሙስሊሙን አንድ የማድረግ አላማ እንዲሳካ አብረን ታመናል። በሙስሊሙ የውስጥ ችግር ሀገር እንዳይረበሽና በመሃል ምስኪኑ ምዕመን ባለማወቅ አላስፈላጊ መስዋዕትነት እንዳይከፍል ዝም በማለት ብዙ ከፍለናል። ከከፈልነው ክፍያ ታላቁና አሳማሚው ዑለሞቻችን ላይ የራሳቸውን ጥፋት እነሱ ላይ እየቀቡ በሚከስሱ ሰዎች የተደረገባቸው የስብዕና ጥቃት ነው። በተረፈ በየመስጂዱ የሚያለቅሱትን ኢማሞችና ወጣቶች መዘርዘር ይከብዳልና ቤት ይቁጠራቸው። ቀይ መስመር እየታለፈ እንደተለመደው በዝምታ መቀጠል አቋም አልባነት አለፍ ሲልም ወኔ ቢስነት ይሆናል። የሀገርን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ ተሸክሞ የሚንቀሳቀሱ የመንግስት አካላትና ሌሎች የሚመለከታቸው የህግ አካላት መብታችን እየገበርን የምንሸከምበት የትእግስት ጫንቃችን እየተፈተነ ስለሚገኝ በሰፊው ዝምተኛ ሙስሊም ይቅር ባይነትና በብልህ ሸይኾቻችን ደንዳና ትዕግስት ላይ የቆመውን የሕዝበ ሙስሊሙን ሰላም በህግ የበላይነት ላይ በማቆም ህገወጥነትን ልክ እንዲያስግቡ፤ እንዲሁም በየመስጂዱ በአሻጥር እየታሰሩና እየተበደሉ የሚገኙ አባሎቻችን የሚደርስባቸውን እንግልት እንዲያስቆምና ይህን እኩይ ድርጊት መጅሊስ ውሥጥ ተቀምጠው ስፖንሰር የሚያደርጉትን እኩይ ግለሰቦች የሚመለከተው አካል ስርዐት እንዲያስይዝ አበክረን እንጠይቃለን።
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.