cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

አል ሁዳ

ይህ ቻናል ➥ቁርአን ➥ሀዲስ ➥የሰለፎች ንግግር የሚያገኙበት ቻናል ነው

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
204
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-17 روز
-230 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
。 ከዚህም በተጨማሪ ታታሪነታቸው፣ አዛኝነታቸው፣ ቁም ነገረኝነታቸው፣ ጀግንነታቸውና የትላልቅ ስብዕና ባለቤት መሆናቸው ይታወቃል። ዳዕዋዎቻቸውና ድርሳኖቻቸው ብዙ ጊዜ ትኩረታቸው ተውሂድ ላይ ነው። ሰዎች ከአላህ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማጠንከር እንደሚገባቸው አበክረው ያስተምራሉ። "ቅድሚያ ለዐቂዳ! ምክንያቱም ዛሬ የኢስላማዊው ዓለም ውዝግብና ዝቅጠት መንስዔው ለጉዳዩ ተስማሚ የሆነ አስኳል መጥፋት ነው። እሱም ጥርት ያለው ዓቂዳ!" ይላሉ ገናናው ሸይኽ ፈውዛን! ከፃፏቸው ድርሳናት መካከል፦ "አትተህቂቃት አልመርዲያ" ማስተርስ በሰሩበት ወቅት በውርስ ክፍፍል ርዕስ ላይ የፃፉት ድርሳን ነው። “ኢርሻድ ኢላ ሰሒሂል ኢዕቲቃድ" "ሙለኸሰል ፊቅሂይ" "አልበያን" "ሸርሁል አቂደቲል ዋሲጢያ" "አቂደቱ ተውሂድ" "ሚን አዕላሚል ሙጀዲዲን" "አደያኡ ላሚዕ" ና ሌሎችንም መፅሀፍት ለሙስሊሙ ህብረተሰብ አበርክተዋል። ከተማሩባቸው ሸይኾች መካከል ሸይኽ ቢን ባዝ፣ ሸይኽ አብዱረዛቅ አል ዓፊፊ ፣ ሸይኽ ሙሀመድአሚን ሺንቂጢ፣ ሸይኽ አብደላህ ቢን ሁመይድ፣ ሸይኽ ሷሊህ ቢን ኢብራሂም ፣ ሸይኽ ሀሙድ ቢን አቅላን፣ ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህና ሌሎችም ይገኛሉ። 。 ሊቃውንት ስለርሳቸው ዝና ሲናገሩ! ሸይኽ ቢን ኡሰይሚን ታመው “ያ ሸይኽ ማን ቀድሞ እንደሚሞት አይታወቅም። ከርስዎ በኋላ አላህ እድሜ ሰጥቶን ከቆየን ማንን እንጠይቅ? ማነው የፊቅህ ሊቅ?” ተብለው ሲጠየቁ "ሸይኽ ሷሊህ አልፈውዛንን ጠይቁ። እርሱ እጅግ የላቀ ግንዛቤ ያለው የፊቅህ ጠቢብና የዲን ባለቤት ነው።” ታሪክ የማይረሳው የምስክርነት ቃል። “ሸይኽ ፈውዛን ከምርጥ ሊቃውንት ውስጥ አንዱ ነው።” ሸይኽ ቢን ባዝ። ድምፃቸውን የፈለገ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ያገኘዋል። https://telegram.me/qteloch "እጅግ የበቁ ሊቅ ሸይኽ ሳሊህ ቢን ፈውዛን። የትልቆቻችን ታላቅ። በዓቂዳ፣ በመንሀጅና በፊቅሂ መመለሻ የሆኑ አዋቂ። የዘመኑ ምጡቅ ጠቢብ ፤ የሰለፎች ቅሪት።… በዚህ ዘመን ይህ ስም የሚገባቸው እሳቸው እንደሆኑ አምናለሁ።” ሸይኽ ሱለይማን አርሩሀይሊ እኔም ልደመምና እንዲህ ልበል “እርስዎ በዚህ ባይተዋር ዘመን የእውቀትን ችቦ ያበሩ ፣ በጣፋጭ አንደበትዎ ወደ ልከኛው መንገድ የሚጣሩ ታላቅ ባለውለታ ናችሁ። እውነትም የሰለፎች ቅሪት። ሸማሲያ ተነስቶ ሪያድን አልፎ አለምን እያበራ ያለ ኮከብ ናችሁ።"
نمایش همه...
የሸማሲያው ተራራ፣ የሪያዱ ችካል! Fuad kheyredin ***** "የዘመኑ ምጡቅ ጠቢብ ፤ የሰለፎች ቅሪት።… በዚህ ዘመን ይህ ስም የሚገባቸው እሳቸው እንደሆኑ አምናለሁ።” ሸይኽ ሱለይማን አርሩሀይሊ https://telegram.me/qteloch ሸይኽ ሷሊህ ቢን ፈውዛን ቢን ዓብደላህ አል ፈውዛን ይባላሉ። ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን በ1354 በወርሃ ረጀብ 1ኛው ቀን በመካከለኛዋ ምስራቅ ሱዑዲያ ምድር ቀሲም ክልል ውስጥ ተወለደ። የተወለደበት ከተማ ልዩ ስሟ "ሸማሲያ" ትሰኛለች። የዚህች ስፍራ የዕፅዋት ልምላሜ ውበት የብዙዎችን አይን ያረካል። ሙቀት ከሚለኩሰው ጠራራ ፀሀይ ጋር በአረንጓዴ ቀለም ገፅታዋን ያሳመረች ስፍራ መመልከት ለነዋሪዎቹ ከምስጢር አዘልነቱ አልፎ ተዓምር አለው። በተለይ የተምር ዛፎችና የስንዴ አዝርዕቶች። ፈውዛን የልጅነት ህይወቱን ከአብሯ አደጎቹ ጋር በዚህች ሞቃታማ ስፍራ የመስክ ስጋጃ ላይ ፋንኗል። ከጓደኞቹ ጋር አቧራ ላይ እየተዘረገፉ መጫወት፣ በንፁህ አየር ውስጥ እየተሯሯጡ መፈንደቅ ለፈውዛን ደስታን የሚያጭር ነገር ቢሆንም ሮጦ ሳይጠግብ ወላጅ አባቱ ዱንያን መሰናበቱ እጅግ ያሳዝነዋል። በጨዋታ መሀል እንደፊተኛው ያልሆነ፣ በረዶ የተቀላቀለበት ቀዝቃዛ ፈገግታ ይከተለዋል። አብሯ አደጎቹም በግርምት ይመለከቱታል። ምን እያስታወሰ ይሆን? 。 በዚያች ሰፈር ጥላ ስር አንዲት መስጂድ አለች። ፈውዛን ከሚኖርበት ቤተሰብ ቤት እምብዛም አይርቅም። በመስጂዱ ቅጥር ውስጥ ዘወትር የማይጠፉ፣ ነጫጭ ፀጉሮች አናታቸውና ፂማቸው ላይ የተነሰነሰባቸው ኢማም አሉ። ሸይኽ ሀሙድ ቢን ሱለይማን አት-ተላል ይባላሉ። ህፃናትን ሰብስበው ቁርአን ያቀራሉ።በተለያዩ ግሳፄያቸውም ትውልድ ይቀርፃሉ። በትጋታቸው ብዙዎች ያወሷቸዋል። ከእናቶቻቸው የተወለዱ ልጆችን በቁርአን አስተምህሮ ደግመው ይወልዷቸው ነበር። ፈውዛንም እዚያ መስጂድ ውስጥ ተሰብስበው ቁርአን ከሚቀሩት ልጆች ውስጥ አንዱ ነበር። ስለኚህ ሸይኽ፣ ፈውዛን ታላቅ ሰው ከሆነ በኋላ “እጅግ የመጠቁ ሃፊዝ ፣ ድምፀ መረዋ ነበሩ።” ብሎ መስክሯል። 。 ያለመምህር የበቀለ ትልቅ ስብዕና የለምና ፈውዛን ከልጅነቱ ጀምሮ የህይወቱን ዓላማ በማሳወቅ የኮተኮቱት ሰዎች አሉ። እነዚህ መምህሮች በፈውዛን ልብ ውስጥ ትልቅ ቦታ አላቸው። ባለውለታነታቸውንም አይረሳውምና በሀሳቡ ብቻ ሳይሆን ከአንደበቱ ደጅ ፣ ከብዕሩ ጠብታ አይጠፉም። በአስራዎቹ እድሜ ላይ ሸማሲያ ላይ የተከፈተ ትምህርት ቤት ውስጥ ገብቶ ተማረና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ቡረይዳ በምትገኘው "ፈይሰልያ" ትምህርት ቤት ውስጥ አጠናቀቀ። በፈውዛን የዒልም ቆይታ ሸይኽ ኢብራሂም ቢን ደይፈላህ ለመነሻ እውቀቶች ትልቅ አስዋፅኦ ነበረው። "ስርዓተ ትምህርቱ ያፀደቀው ብቻ ላይ ሳይገደብ ለተማሪዎቹ በዓቂዳም በፊቅሂም በርካታ ጠቃሚ እውቀቶችን ያስተምር ነበር። በርሱ ብዙ መልካም ነገሮች ተገኝቷል። የእውቀት በሮችን ከፍቶልን አነሳስቶናል። አላህ መልካሙን ይመንዳው።" ይላል የትናንቱ ደረሳ የዛሬው ሊቅ ፈውዛን። 。 ታጋይነቱ ለእውቀት ካለው ጉጉት ያስታውቃል። ቅሌን ጨርቄን ማለት አልለመደበትም። በቂርአት ጉዞው ለአፉ ምክንያት፣ ለእግሩም እንቅፋት አላደረገም። ሊቃውንት ያሉበትን ደጃፍ ያንኳኳል። ተቀምጦ ብዙ ይቀራል፣ ያዳምጣል። ዛሬ ትልቅ ሰው ሆኖ “እውቀት ፈላጊዎች እጅግ እንዲጠነክሩና እንዲታገሉ እመክራለሁ” ይላል እውቀት በሚፈስበት አንደበቱ። ለእውቀት የተነሳ ሰው ዝለት ሊጠናበትም ይሁን ጉልበቱ ሊብረከረክበት አይገባም። 。 ቡረይዳ ከተማ ላይ የዒልም ማዕከል ተከፍቶ እነ ሸይኽ አብዱረዛቅ አልዐፊፊና ሸይኽ ሳሊህ ቢን አብዱራህማን ሲያስተምሩ ፈውዛን ግንባር ቀደም ተማሪ ነበር። የተለያዩ የፊቅሂ፣ የዐቂዳ፣ የኡሱልና ሌሎችም ዘርፎች ላይ በጥልቀት በበቁ ምሁራን ይሰጥ ስለነበር የእውቀት ጥማቱ ዕለት ዕለት አዲስ ነው። በትኩስ ወጣት መንፈስ የታጠቀውን ወኔ በጥበብ ላይ እንጂ በሌላ ተራ ነገር ላይ ማድረግ አልፈለገም። በማዕከሉ ከሚሰጠው የሸሪዓ ስርዓተ ትምህርት በተጨማሪ ሸይኽ አብዱላህ ቢን ሁመይድ በሚያስተምሩበት የእውቀት ማዐድ ላይ ተድጦ ከሸይኽ አብዱላህ ቢን ሁመይድ አንደበት የሚርከፈከፉ ጥበብ ያዘላቸው ደርሶችን በማዳመጥ ይማራል። ለዚህ ደግሞ ቆራጥነት ያስፈልጋል። “በእውቀት ማዕከሎች ውስጥ ብዙ ጓደኞች ነበሩኝ። አብዛኞቹ በተለያዩ ምክንያቶች አቋርጠዋል። ከፊሉ በሲሳይ ፍለጋ ፣ ከፊሉ በሌላ ምክንያት አቋርጠዋል። አብረውኝ የቆዩ እምብዛም ናቸው።” ይላል ይህ ትልቅ ሰው። 。 ፈውዛን ቡረይዳ ከተማ ከሚገኘው “መዕሀድ አል-ዒልሚይ” በ1377 ዓ·ሂ ተመርቆ ከወጣ በኋላ ወደ "ሪያድ" ከተማ አቀና። ሪያድ ላይ "ኩሊየተ ሸሪዓ" (የሸሪዓ ኮሌጅ) ውስጥ ገብቶ በሸይኽ ቢን ባዝ፣ በሸይኽ ሙሀመድ አሚን አሺንቂጢና በትላልቅ ሊቃውንት የመማር እድሉን አገኘ። ከሸሪዓው ኮሌጅ ውስጥ የሚመረቁበት የመጨረሻው አመት ላይ የፈውዛንን ብቃትና የእውቀት ጥማት የተመለከቱት ሀላፊዎች የነህውና የሌሎች ዘርፎች አስተማሪ እንዲሆን አደረጉት። ፈውዛን በፊቅሂ ዘርፍ የማስተርስ አልፎም የዶክተርነትን ደረጃ ተጎናፀፈ። ከዚያም በተማሪዎቹ የተከበረ ፣ በዒልሙ ከፍታ ቁንጮ ካሉት በክብር የሚሰለፍና በሚያገለግለው ማህበረሰብ ዘንድ ግርማው የላቀ ሊቅ ሆነ።( ሊቅ ሆነዋልና በክብር ልጥራቸው) 。 ሸይኽ ፈውዛን በተለያዩ ኮሌጆችና የእውቀት ማዕከሎች ላይ በተማሪነት ህይወታቸው የሰበሰቡትን ጥበቦች መስጂድ ለታዳሚው ያስጨብጣሉ።መስጂድ ውስጥ ማስተማር ከጀመሩ ከ35 ዓመት በላይ ሆኗቸዋል። በሸሪዓ ኮሌጅ ላይ፣ ኡሱሉ ዲን ኮሌጅ ላይ መዕሃድ አልዒልሚ ላይ በአስተማሪነት ታጭተው አስተምረዋል። መዕሀድ አል-ዓሊ ላይ ሃላፊ ተደርገውም ተሹመው ነበር። የሳውዲ ቋሚ የፈትዋ ሰጭ ኮሚቴ አባልም ናቸው። 。 ሲያስተምሩ ስክነታቸው ለጉድ ነው። የአቀራረብ ስልታቸው እጅግ ይማርካል። ስርዓቱን ጠብቆ እንደበጋ የወንዝ ጅረት ፈሰስ ይላል። ያለማጋነን ከአንደበታቸው ማር ይዘንባል። ያውም ለስለስ ያለ ማር። መተናነሳቸውን የማይወድላቸው ሰው የለም። እንደ ጭስ በባዶነት የሚንጠራሩ ተራ የዘመናችን ሰው እንዳይመስሉህ። እጅግ በጣም አዋቂ ቢሆኑም "እውቀቴ ትንሽ ነው። ደካማ ነኝ" የሚል ቃል ከአንደበታቸውም ይሁን ከብዕራቸው ሰፈር አታጣም። በአንድ መድረክ ላይ ለርሳቸው ቃለ መጠይቅ የሚያደርገው ሰው “የዛሬው እንግዳችን ከኡማው ጠቢቦች አንዱ የሆኑት ፣ ሁሌም የሚሰጧቸውን ትምህርት ለማድመጥ የምትጠባበቋቸው ትልቅ ሰው! በፊቅህ ብትሉ ፣ በአቂዳ ብትሉ ፣ በተፍሲር ብትሉ ልዩ ሊቅ ናቸው።…” እያለ ካወደሳቸው በኋላ "ያልደረስኩበት ደረጃ ላይ ስለሰቀላችሁኝ እጅግ አሳፍራችሁኛል (ሀፍረት ተሰምቶኛል)። እኔኮ ልክ እንደናንተ አንድ እውቀት ፈላጊ እንጂ ሌላ አይደለሁም። ምናልባትም ከናንተ ውስጥ እጅግ የላቀና የተከበረ ሰው ሊኖር ይችላል።” ብለው የመተናነስን ትርጉም በተግባር ያስተማሩን ሸይኽ ናቸው።
نمایش همه...
ከቁርአን ጋር ያለኝን ቅርበት አጠናሁና ምድቤን እዚህ አያ ውስጥ አገኘሁት😭 وَقَالَ الرَّسُولُ يَا رَبِّ إِنَّ قَوْمِي اتَّخَذُوا هَٰذَا الْقُرْآنَ مَهْجُورًا መልክተኛውም «ጌታዬ ሆይ! ሕዝቦቼ ይህንን ቁርኣን የተተወ ነገር አድርገው ያዙት» አለ፡፡
نمایش همه...
وَمَنْ أَعْرَضَ عَن ذِكْرِى فَإِنَّ لَهُۥ مَعِيشَةًۭ ضَنكًۭا وَنَحْشُرُهُۥ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ أَعْمَىٰ «ከግሣጼዬም የዞረ ሰው ለእርሱ ጠባብ ኑሮ አለው፡፡ በትንሣኤም ቀን ዕውር ኾኖ እንቀሰቅሰዋለን፡፡
نمایش همه...
قَالَ إِنَّمَآ أَشْكُوا۟ بَثِّى وَحُزْنِىٓ إِلَى ٱللَّهِ وَأَعْلَمُ مِنَ ٱللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ «ጭንቀቴንና ሐዘኔንና የማሰሙተው ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ ከአላህም በኩል የማታውቁትን ነገር ዐውቃለሁ» አላቸው፡፡
نمایش همه...
   «  የአላህ መልክተኛ አንድ ቀን ከባድ ህመም ላይ ነበሩ ሁለት መልአክቶች መጥተው አንደኛው ከራሳቸው በኩል አልደኛው ደግሞ ከእግራቸው በኩል ተቀመጠ  በእግራቸው በኩል የተቀመጠውም መላኢካ በራስ ኩል ላለው እንዲህ አለ « ሙሃመድ ታሟል እና ምን ትመለከታለህ ምን ሁኖ ነው  (ምን ትላለህ ) ? » አለ ሌላኛው መላኢካም «በረሱሉ ላይ ተደግሞባቸዋል» ሌላኛው መላኢካም « ማነው ታዲያ የደገመባቸው» ብሎ ጠየቀ « የደገመባቸው የሁዲዮ ለቢድ ኢብኑል አዕሶም ነው! » « ታዲያ እሺ የተደገመባቸው ድግምቱ የት ነው » ሲል ጥያቄውን ደገመው መላኢካውም   « የነ እገሌ ቤተሰብ ጋር አንድ የጉድጓድ ውሃ አለ በውስጡ ቋጥኝ አለ ከቋጥኙ ስር ነው ድግምቱ የተቀበረው አለ»  መላኢካዎቹም ወደዚያች ጉድጓድ ሄዱና ጉድጓዱ ውሃው  እንዲደርቅና ከቋጥኙ ስር ጥቅልል ያለ ነገር እንዲወጣ አድርገው አቃጠሉ!  ከዛ የተድበለበለ ነገር ውስጥ ጥቅልል ገመድ ክሮች አሉ በክሮቹም ላይ 11 የሚሆን ቋጠሮዎች ተቋጥረው ነበር!  በዚህም ግዜ ሙዐወዘተይኖች ሱረቱል ፈለቅ እና ሱረቱንናስ ወደ መልክተኛው ተወረዱ!  ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እያንዳንዱን አንቀፅ ባነበቡ ቁጥር እያንዳንዱ ቋጠሮ ተራ በተራ ተፈታ ¹ (ዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ) አነስ ኢብኑ ማሊክም እንዲህ አለ « የሁዶች ለመልክተኛው ዐለይሂሰላም ትንሽ ምግብ ሰርገው በንግድነት ጋበዟቸው በተመገቡት ምግብም ምክንያት ለከባድ ህመም ተጋለጡ  ሶሃቦችም መልክተኛው የደነበሩበት ክፍል ገብተው ነበር ጅብሪል ሙዐወዘተይኖችን ይዞ መጥቶ አነበበባቸው ከዚያም ቡሃላ ረሱሉ ጤነኛ ሁነው ወደ ሶሃቦቻቸው ተቀላቀሉ! »② ①አስባበ ኑዙል ሊልዋሂዲይ ገፅ 410 ② ጠበራኒይ «ዱዓእ»  በሚለው ኪታባቸው 335
نمایش همه...
2
🌤「 ዱ ን ያ 」🌍 ▭▬▭▬▭▬▭▬ ✅:ወህብ ኢብኑ ሙነበህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦ ዱንያ እና አኺራህ ልክ 2 ሚስቶች እንዳሉት ወንድ ናቸው። አንዷን ሲያስደስት ፤ ሌላኛዋ ትቆጣለች። جامع العلوم والحكم【2/203
نمایش همه...
የሽርክ አደጋ    ከአላህ ውጪ ያለን ማንኛውንም አካል እየተገዛ ወይም እያመለከ የሞተ ሰው የእሳት ነው ። ዱንያ ላይ ሳለ ከአላህ ጋር ሌላን አካል ያጋራ ወይም ሽርክን የፈፀመ  ሰው በየትኛውም ዘመንና ቦታ ላይ ቢገኝም  ይህ ሰው ካፊር ፣ሙሽሪክ ነው በፍፁም ሙስሊም አይደለም !
نمایش همه...
ምናልባት አአንተ በምታሰራጨው መልክት አንዱ ይጠቀም ይሆናል። ዙበይድ አል-ኩፊ እንዲህ አሉ፡- «አንዲትን ቃል ሰማሁ አላህም በሷ ለሰላሳ አመታት ጠቅሞኛል።» ሲየር አዕላም አኑበላእ (6/297) @tewhidnasuna
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.