cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ርቱዓ ሃይማኖት (ዘኦርቶዶክስ) ✞

በዚህ ቻናል የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ፅሁፎች የሚለቀቁ ሲሆን ከነዚህ ውስጥም በጥቂቱ ✅ ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞች ✅ የተለያዩ አስተማሪ ፅሁፎች ✅ በብዛት በኦርቶዶክስ ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ✅ እንዲሁም በተደጋጋሚ ለኦርቶዶክሳውያን ግልፅ ያልሆኑ ነገሮች ማብራሪያ ይቀርባል እና ሌሎችም ሀይማኖታዊ ፅሁፎች ይቀርባሉ::ለማንኛውም አስተያየት እና ጥያቄዎች @kalbcha

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
531
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

< +ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን >> "እኛክርስቲያኖች ነን ቤተክርስቲያን ደግሞ የክርስቲያን ቤት ናት ታዲያ ቤተክርስቲያን በእኛ ስም ከተጠራች ከተሰየመች በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስም ብትሰየም ጥፋቱ ምንድነው አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ክርስቲያን አይደሉም ?) _ የሽቶ ጠርሙስ የሰበረችውና ሽቶ በጌታ እግር ላይ ያፈሰሰችው ሴት ታሪክ ወንጌል በተነበበት ሁሉ ስሟ ይነሳ ከተባለ ስለ ክርስቶስ ሲሉ አንገታቸው ስለተሰበረው ደማቸው ስለፈሰሰው "ስለነ ቅድስት አርሴማ ስለቅዱስ ጊወርጊስ ስለ ሰማዕታቱ ወንጌል በተነበበት ሁሉ ቢነገር ጥፋቱ ምንድነው የሽቶ ጠርሙስ ከመስበር አንገት መስበር አይበልጥም ን ? ሽቶ ከማፍሰስ ደም ማፍሰስ አይበልጥምን !?) #መ/ር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ )
نمایش همه...
+ ዘኬዎስ አጭር ባይሆን + ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት በኢያሪኮ እያለፈ ያለውን ክርስቶስን ለማየት ተቸገረ:: ሕዝቡ ብዙ ነውና የቆሙት ሁሉ ጌታን ከማየት ከለሉት:: የሾላ ዛፍ ላይ ወጥቶ ጌታን ለማየት ሲሞክር ጌታ አሻቅቦ አየው:: እሱ ዛፍ ላይ ጌታን ሊያይ እንጂ ሊታይ አልወጣም:: ጌታ ሊታዩ ከሚሞክሩ ይልቅ ሊያዩት የሚሹትን ይወዳልና ዘኬዎስን ጠራው:: ከምድር ቆመን ዓይናችንን አንጋጥጠን ማረን የምንለው ጌታ ዘኬዎስን ከምድር ሆኖ ወደ ላይ እያየ ና ልማርህ አለው:: "ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛል" አለው:: ጌታ ወደ ቤቱ ገባ:: ለዘኬዎስ ቤት መዳን ሆነለት:: ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ኖሮ ከሰዎች ጋር እየተጋፋ ጌታን ያይ ይሆናል እንጂ በጌታው ዓይን ለመታየት የሚያበቃ ትጋት አያሳይም ነበር:: ምናልባትም ሰዎችን ገለል በሉ እያለ በኩራት ሲጋፋ ከአንዱ ጋር ሲጣላ ሊቆይ ይችል ነበር:: ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ከዛፍ ላይ አይወጣም ነበር:: ዘኬዎስ አጭር ባይሆን የሠራዊት አምላክ ወደ ቤቱ አይገባም ነበር:: በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ንጉሥ በቤቱ ወንበሮች ላይ የተቀመጠው ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት ነው:: የዘኬዎስ ነፍስ የዳነው በቁመቱ ማጠር ነበር:: እግዚአብሔር የመዳኑን ቀን የቆረጠለት ቁመቱን ሲያሳንሰው ነበር:: በምድር በመጽሐፍ ቅዱስ በሰማይ በሕይወት መዝገብ ስሙ የተጻፈው ዘኬዎስ አጭር በመሆኑ ነው:: ስለ ቁመት የማወራ እንዳይመስልህ:: እግዚአብሔር ለነፍሳችን መዳን የሚያሳጥርብን ብዙ ነገር አለ:: እንደ ዘኬዎስ ቁመትህ አጭር ባይሆን የሚያጥርህ ነገር ግን አይጠፋም:: ይሄ ጎደለኝ የምትለው ከሰዎች አነስኩበት የምትለው ነገር አንዳች ነገር የለም? እሱን ማለቴ ነው:: ይሄ ይጎድለኛል ከሰው አንሳለሁ እያልክ አትማረር:: እጥረትህ መክበሪያህ ነው:: ጉድለትህም መዳኛህ ነው:: እግዚአብሔር ያጎደለብህ የመሰለህ ነገር ወደ ዛፍ እንድትወጣ ምክንያትህ ይሁን:: በጉድለትህ እንደ ዘኬዎስ ከፍ በልበት:: ያኔ ሰዎች አንተን አንጋጠው ከማየት ውጪ አማራጭ አይኖራቸውም:: ፈጣሪ በፍቅሩ ይይህ እንጂ ሰዎች ወዳንተ ያዘነብላሉ:: በቤትህ መዳን ይሆንልሃል:: ከዚያም ስላጠረህ ስለጎደለህ ነገር ፈጣሪህን ስታመሰግነው ትኖራለህ:: እመነኝ አንዳንድ ጉድለቶች እድሎች ናቸው:: ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ይሄኔ በሾላው ዛፍ ጥርሱን እየፋቀ ይቀር ነበር:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ግንቦት 23 2014 አዲስ አበባ ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ! በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
نمایش همه...
#መድኃኔ_ዓለም "እርሱ በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደሆነ እናውቃለን" (ዮሐ 4÷42) ኢየሱስ ማለት መድኃኒት ማለት ነው መድኃኒትነቱ በጥቂት ሰዎች ብቻ የተገደበ፤እንደነ ኢያሱ በእስራኤል ዘሥጋ ማዳን ብቻ የተገለጠ ሳይሆን፤በሥጋ፣ በመንፈስና በነፍስ ማዳን ላይ የተመሠረተ ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጠ፤ ያውም ከአዳም ጀምሮ እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ለሚነሳው ትውልድ ሁሉ የሆነ ማዳን ነው፡፡ ስለዚህም መድኃኒትነቱ ውሱን እንዳልሆነ ለማጠየቅ ˝ኢየሱስ˝ የሚለው በምልኣት ሲገለጥ ˝የዓለም-መድኃኒት˝ ብለን እንጠራዋለን፡፡ ዓለም ማለት ዘመድ፤ ዘመደ ፍጥረት ፤ሰማይ ከነግሡ ምድር ከነልብሱ፤ሰማይ ከነደመናው ምድር ከነጉተናው ማለት ሲሆን ሁሉን የጠቀለለ ስም ነው፡፡ በሊቃውንቱ ሃያ ዓለማት እና ሃያ አየራት እንዳሉ ይገለጣል፤ሃያ ዓለማት የሚባሉትም ዘጠኝ ዓለመ እሳት፤አምስት ዓለመ ምድር፤አራት ዓለመ ማይ እና ሁለት ዓለመ ነፋስ ናቸው፤(9+5+4+2=20)፤አየራቱም በዚህ ልክ ናቸው ይላሉ (ቅዳሴ.ማር አንድምታ)፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሰቀል ዓለሙን ሁሉ ለማዳን ነው ሲባል ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን በአዳም ምክንያት ተረግሞ የነበረውን ዓለም ለሰው ልጆች በግዛት መልክ ተስጥቶ የነበረውን ሁሉ ዓለም ለመባረክ መሆኑንም ማወቅ ያስፈልጋል፤ለአዳም "ከሰማይ በታች ከምድር በላይ ያለውን ሁሉ ብላ ጠጣ ግዛ ንዳ" (ዘፍ 1÷29-31) ተብሎ መሰጠቱ ይታወቃል፤ይህም በረከት ነው፡፡ አዳም ያልታዘዘውን ዕፀ በለስ በልቶ ሲረገም ደግሞ የእርሱ የሆነው ሁሉ አብሮ ተረግሟል፤ ♦ለዚህም "ካንተ የተነሣ ምድር የተረገመች ትሁን" (ዘፍ 3÷17) የሚለው ቃል ማረጋገጫችን ነው፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስም፡- ♦"ምድርም አለቀሰች ረገፈችም ፤ዓለም ደከመች ረገፈችም፤የምድርም ሕዝብ ታላላቆች ደከሙ" በማለት በኢየሩሳሌም ምርኮ አንፃር የነበረውን የዓለምን ስቃይ አመልክቶናል (ኢሳ 24÷4)፡፡ ነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤልም፡- ♦"ወሶበ ዐለወ አቡነ አዳም ኮነ ፍናዊሁ ለዓለም መብእሰ ወጐጻጒጸ" "አዳም ትእዛዙን ባፈረሰ ጊዜ የዚህ ዓለም ጎዳናው ጒድጓድ ሆነ፤ጠባብ ያነሰ የከፋ መከራው የበዛ፤ ፃር ጋር የተመላ ሆነ" (ዕዝ.ሱቱ 5÷2)፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም፡- ♦ "ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ" (ሮሜ 5÷12)፡፡ ጌታችንም ለሐዋርያት ሲያስተምር፡- ♦"ርእዮ ለዓለም በማእሰረ ኃጢአት እንዘ ይትኀጐል፤ፈቂዶ ይፈውስ ትዝምደ ሰብእ…." "ዓለም በኃጢአት ማሰሪያ ተይዞ ሲጎዳ አይቶ የሰውን ባህርይ የሰውን ነገድ ይፈውስ ዘንድ …" ብሏል (ትምሕርተ ኅቡአት)፡፡ ስለዚህ ለአዳም የተሰጠ ዓለም በአዳም ምክንያት የተረገመ ሆኖ ነበር፤ ዓለማችን በአዳም ምክንያት መከራንና ሞትን ተቀብላ አስተናገደች፤ይህ መርገም ለዓለም አንዲወገድላት ሌላ ሁለተኛ አዳም ያስፈልግ ነበር፤ እሱም "የዓለም መድኃኒት" መሆን አለበት፤ሁለተኛው አዳም ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጣ፤ ዓለምን በደሙ ፈሳሽነት አጠባት፤ በሰው ውስጥ የሚገኙትን አራቱን ባህርያት አደሳቸው፤ ተረግማ የነበረችው ምድር በጌታ ደም ታጥባ ፋሲካን አደረገች ("ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተኀፂባ በደመ ክርስቶስ" እንዲል ቅ.ያሬድ)፤ ክርስቶስ መርገማችንን ቀበረልን፤ ልጅነታችንን መለሰልን!!! ዛሬ በዚህ ደም ታጥበን ነጽተን መንግሥቱን እንጠባበቃለን ፍቅሩንና መከራውን እያሰብን ቁስሉንና ሞቱን እያስታወስን እንማፀናለን ለዓለም ቤዛነት መስቀል ላይ የተፈተተው ጌታ ዛሬም እንደማይተወን እናምናለን ስለዚህም እንዲህ እያልን እንለምነዋለን፦ መድኃኔ ዓለም ሆይ! • 6,666 ጊዜ ስለተገረፈው ጀርባህ • ስለተቸነከሩት እጆችህና እግሮችህ • ስለተወጋው ጎንህ • ስለ ቅዱስ ሥጋህና ስለ ክቡር ደምህ • በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ስለወለደችህ ስለ እናትህ ስለ ማርያም ብለህ ይቅር በለን!!! አሜን!!! መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው (ኢ/ር) የመካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የመጽሐፍ መምህር
نمایش همه...
نمایش همه...
"እመቤቴ" ዘማሬ እንዳለ ሻውሌ አዲስ ዝማሬ Ethiopian orthodox new mezmure

ያሎት አስተያየቶች እና ጥያቄ በቴሌግራም

https://t.me/E_M_A_Y

ይላኩልኝ Subscribe to my channel on

https://youtube.com/channel/UCtrUFY0_kANLXS0JsnSJ5Gg

Follow me on Telegram

https://t.me/E_M_A_Y

Follow me on Facebook

https://www.facebook.com/kirubel.wassie

#tikus TUBE #zehabesha #deruzehareru #tikusmereja #mike show #mereja

ያልሰማህ ስማ የሰማህም ላልሰማ አሰማ !!!!
نمایش همه...
#ጀሃድ_አወጁ!!☝️☝️☝️ ሁላችሁም ኦርቶዶክሳዊያን ይሄነን ቮይስ ስሙ!☝️ እኛ እራሳችሁን እንድትጠብቁ እና እንድትጠነቀቁ እንጅ ግደሉ ሚል አምላክ ስለሌለን እንደ እነሱ ገጀራ አናነሳም! የክርስቲያን ዝርያት በሙሉ የተዋሕዶ ልጅ ሆነ ፕሮቴስታንት የሆነ ሁሉ ይዳረስ ይስማ በክርስቲያን ላይ በሙሉ ነው እያወጁ ያሉት! ማንኛውም ሰው በቴሌግራም አካውንት ላለው ኦርቶዶክስ በሙሉ ሸር ያድርግ!!! ለበለጠ መሰል መረጃዎች በቴሌግራም ሊንኩን በመጫን ተከታተሉ👉 t.me/DebteraMedia
نمایش همه...
3.80 KB
፨ ተዓምረ ማርያም ገና አልተጨረሰም! በቤተ-ክርስቲያናችን የቅዳሴው መገባደጃ ላይ ዲያቆኑ "ነአኹቶ"ን ጨርሶ ካህናት ከገቡ በኋላ ትምርተ ወንጌል ሳይሰበክ ካህኑ "ተዓምሪሃ ለእግዝዕትነ ማርያም..... " ብሎ የእመቤታችን ያደረገችውን ተዓምር በቀኑ መሠረት ያነባል ምዕመኑም በፅሞና ከተቀመጠበት ተነስቶ በክብር ያዳምጣል።ተዓምሯ ቢነገረው ቢነገረው ለማይሰለቸው ህዝብም እመቤታችንም ተዓምሯን ሳይሰለቻት ታደርግለታለች በስሟ ለሚተማመነው ሁላ በዘርፋፋ ቀሚሷ ዛሬም ታሳፍረዋለች ምልጃዋ ጣዕሟ ፍቅሯ ሁላ ለሞት ስንቅ ታደርግለታለች።ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም እንደተናገረው እናት የወለደቻትን ልጅ በማታድንበት የፍዳ እና የበቀል ሰዓት መሸሸጊያ ትሆናቸዋለች። የስጋን ደዌንም በስሟ ትፈውስኛለች ብሎ ላመነ ሁሉ በልጇ ባያምን እንኳ ዛሬም ትፈውሰዋለች.....ለዚህም ተዓምረ ማርያም አላለቀም አልተጨረሰም.......በስሟ ለሚያምኑትም ምልጃዋ ተዓምሯ ለልጅ ልጅ ነው። .. የሔዋን የሚጎዳ ማሠሪያዋ በአንቺ የተቆረጠላት እመቤቴ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ ... እግዚአብሔር በብሩሕ ደመና ተጭኖ በማኅፀንሽ ያደረ እመቤቴ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ ... እኔ ለምእመናን ወንጌልን የማስተምርለት የጌታዬ እናቱ እመቤቴ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ ... እኛ ከምንወደው እርሱም ከሚወድደን ከልጅሽ ዘንድ ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን ዘንድ ለምኚልን’ /መቅድመ ተአምረ ማርያም/ ሠናይ ሌሊት🙏 @retua21 @retua21
نمایش همه...
Repost from N/a
01:46
Video unavailableShow in Telegram
ተዓምረ ማርያም ገና ተጽፎ አላለቀም። ሁላችሁም ሼር አድርጉት። @ApostolicSuccession
نمایش همه...
3.78 MB
ዮሐንስ 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴⁴ በነገው ኢየሱስ ወደ ገሊላ ሊወጣ ወደደ፥ ፊልጶስንም አገኘና፦ ተከተለኝ አለው። ⁴⁵ ፊልጶስም ከእንድርያስና ከጴጥሮስ ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበረ። ⁴⁶ ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ፦ ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል አለው። ⁴⁷ ናትናኤልም፦ ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን? አለው። ፊልጶስ፦ መጥተህ እይ አለው። 👉“ፊልጶስ- ጌታ ሆይ፥ አብን አሳየንና ይበቃናል አለው።” — ዮሐንስ 14፥8 ዕረፍቱ ኅዳር አሥራ ስምንት ቀን ነው በሀገረ አፍራቅያ ተዘቅዝቆ ተሰቅሎ ተገርፎ ነፍሱን ሰጥቷል! በረከቱ በሁላችንም ላይ ይደርብን አሜን! 6. በርተሎሜዎስ ፦ ባለ አትክልት ወይም ተክል የማጠጣት ሥራ ያለበት ልጅ ማለት ነው በር እና ሎሜዎስ በር ልጅ ሎሜዎስ አትክልት "ተ" ትርፍ ነው ብለው መተርጉማን ያትታሉ ምሥጢሩ ትምህርቱን እንደ ውሃ ሰውነታቸውን እንደተክሉ ልቡናቸውን እንደምድሩ አድርጎ ማስተማሩን ይገልጻል • አንድም ወይን ማለት ነው ፤ ዕለቱን ወይን ተክሎ ለመሥዋዕት አድርሷልና ወደ ባህር ተጥሎ ሰማዕትነት ተቀብሏል ዕረፍቱ መስከረም ፩ (1) ቀን ነው 7. ቶማስ ፦ ቶማስ ማለት በመተርጉማን አገላለጽ ፀሐይ ማለት ነው ሌላ ስሙ ዲዲሞስ ነው ዲዲሞስ በግሪክ ቶማስ በዕብራይስጥ ሲሆን ቀጥታ ትርጉሙ መንታ ማለት ነው ሰዱቃዊ ነበር (ትንሣኤ ሙታንን አያምንም ነበር) “ስለዚህ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርት፦ ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ አለ።” — ዮሐንስ 11፥16 ዮሐንስ 14 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴ ወደምሄድበትም ታውቃላችሁ፥ መንገዱንም ታውቃላችሁ። ⁵ ቶማስም፦ ጌታ ሆይ፥ ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን? አለው። ⁶ ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። ⁷ እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር። ከአሁንም ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል አለው። ዮሐንስ 20 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁶ ከስምንት ቀን በኋላም ደቀ መዛሙርቱ ደግመው በውስጥ ነበሩ፥ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበረ። ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው። ²⁷ ከዚያም በኋላ ቶማስን፦ ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው። ²⁸ ቶማስም፦ ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት። ²⁹ ኢየሱስም፦ ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው። ዕረፍቱ ግንቦት 26 በጦር ተወግቶ ነው 8.ማቴዎስ፦ • መቅረጫ ማለት ግብር መሰብሰቢያ ማለት ሲሆን ፤ ቀራጭ ማለት ግብር ሰበሳቢ ማለት ነው • ማቴዎስ በዚህ ሥራ ይተዳደር የነበረ ሰው ነበር • ማቴዎስ ማለት ‹‹ኅሩይ እመጸብሐን፤ ከቀራጮች የተመረጠ›› ማለት መሆኑን መተርጉማን አስቀምጠዋል • የቀድሞ ስሙ ሌዊ ነበር ፤ ሌዊ ማለትም ‹‹ኅሩይ›› የተመረጠ የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው • የአባቱ ስም እልፍዮስ/ዲቁ ሲሆን ፤ የእናቱ ስም ካሩትያስ ይባላል (‹‹የእልፍዮስ ልጅ ሌዊን አየና…›› ማር 2፡14) • ነገዱ ከነገደ ይሳኮር ነው • ወንጌሉን የጻፈው በ 41/42 ዓ.ም እንደሆነ ይገመታል • የጻፈበት አገር በፍልስጥኤም ጀምሮ በህንድ ፈጽሞታል • ቋንቋ በእብራይስጥ ጽፏል • ቁጥሩ ከ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ነው • ዕረፍቱ ጥቅምት ዐሥራ ሁለት ቀን ብስባራ በምትባል አገር በሰማዕትነት ነው ጸሎቱ በረከቱ አማላጅነቱ በሁላችንም ላይ ይደርብን፤ አሜን! 👉9.ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ ማለት ነው ያዕቆብ ማለት አእቃጺ አኀዚ ማለት ነው (ሐተታ እንዳለፈው) ዕረፍቱ የካቲት 10 ቀን በድንጋይ ተደብድቦ ነው የተገደለው በቀላውዴዎስ ቄሣር ዘመን ሲሆን የሞተው በኢየሩሳሌም ነው የገደሉትም አይሁድ ናቸው በረከቱ በሁላችንም ላይ ይደርብን 👉10.ታዴዎስ ልብድዮስ ልብድዮስ ማለት "ልብደ ሠሪ" ማለት ነው አንድም "ልበ ድዮስ" ካህነ አምላክ ማለት ነው ታዴዎስ ማለት "ዘርዕ ወማዕረር ፤ ዘርና መከር" ማለት ነው አንድም መምህረ "አሕዛብ ወሕዝብ" ማለት አንድም መሥዋዕት ማለት ነው ዕለቱን ስንዴ ዘርቶ አድርሷልና ሌላ ስሙ ይሁዳ ነው አባቱም ያዕቆብ የሚባል ነው “የያዕቆብ ይሁዳም፥ አሳልፎ የሰጠውም የአስቆሮቱ ይሁዳ ናቸው።” — ሉቃስ 6፥16 “የአስቆሮቱ ያይደለ ይሁዳ፦ ጌታ ሆይ፥ ለዓለም ሳይሆን ራስህን ለእኛ ልትገልጥ ያለህ እንዴት ነው? አለው።” — ዮሐንስ 14፥22 የያዕቆብ ልጅ ይሁዳ (ሐዋ 1፥13) ዕረፍቱ ሐምሌ 2 ቀን ነው በረከቱ በሁላችንም ላይ ይደርብን! 👉11. ቀነናዊው ስምዖን ፦ ስምዖን ማለት "እግዚአብሔር ሰማኝ" ማለት ነው 1. ከአሥራ ሁለቱ ነገድ አንዱ 2. ሽማግሌው ስምዖን ፦ሉቃ 2፥25-35 3. የአስቆሮቱ የይሁዳ አባት ስምዖን ይባላል 4. የጴጥሮስ የቀድሞ ስሙ ስምዖን ነበር 5. የዮሴፍ ልጅ ስምዖን 6. ለምጻሙ ወይም ፈሪሳዊው ስምዖን (“ኢየሱስም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ፥”) 6. — ማቴዎስ 26፥6 7. ቀነናዊው ስምዖን 8. ቀሬናዊው ስምዖን ፦ “ሲወጡም ስምዖን የተባለው የቀሬናን ሰው አገኙ፤ እርሱንም መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት።” 8. — ማቴዎስ 27፥32 8. 9. ቁርበት ፋቂው ስምዖን ፦ “እርሱ ቤቱ በባሕር አጠገብ ባለው በቍርበት ፋቂው በስምዖን ዘንድ እንግድነት ተቀምጦአል፤ ልታደርገው የሚገባህን እርሱ ይነግርሃል።” 9. — ሐዋርያት 10፥6 9. ቀነናዊ ቃሉ አረማይክ ሲሆን ቀናተኛ ማለት ነው በዚያ ዘመን የሮምን መንግሥት አጥብቀው የሚቃወሙ ቡድኖች ቀነናውያን (ቀናተኞች) ይባላሉ ምሥጢሩ "እስመ ቅንዓት ቤትከ በልዐኒ"ከሚለው ይገባል ይህም ቀነናዊ ስምዖን በሌላ ስሙ ናትናኤል ነው ትርጉሙም "የእግዚአብሔር ስጦታ " ማለት ነው “ናትናኤልም፦ ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን? አለው። ፊልጶስ፦ መጥተህ እይ አለው።” — ዮሐንስ 1፥47 ዮሐንስ 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴⁸ ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ፦ ተንኰል የሌለበት በእውነት የእስራኤል ሰው እነሆ አለ። ⁴⁹ ናትናኤልም፦ ከወዴት ታውቀኛለህ? አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ ፊልጶስ ሳይጠራህ፥ ከበለስ በታች ሳለህ፥ አየሁህ አለው። ⁵⁰ ናትናኤልም መልሶ፦ መምህር ሆይ፥ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ አለው። በሌላ መልኩ ቀነናዊ ማለት ቃናዊ ለማለት ሲሆን ናትናኤል የቃና ሰው መሆኑን ለመግለጽ ነው ዕረፍቱ ሐምሌ 10 ቀን ነው አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ ሰማዕትነት ተቀብሏል በረከቱ በሁላችንም ላይ ይደርብን! 👉“በገቡም ጊዜ ወደሚኖሩበት ሰገነት ወጡ፥ ጴጥሮስና ዮሐንስም፥ ያዕቆብም፥ እንድርያስም፥ ፊልጶስም፥ ቶማስም፥ በርተሎሜዎስም፥ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም፥ ቀናተኛ የሚባለው ስምዖንም፥ የያዕቆብ ልጅ ይሁዳም።” — ሐዋርያት 1፥13 የሐዋርያት የመጨረሻ ስም ዝርዝር ይህ ነው! ማትያስ በአስቆሮቱ ይሁዳ ምትክ ገብቶ እስኪሾም ድረስ የ አሥራ አንዱ ሐዋርያት ዝርዝር ይህ ነው።።።። በረከታቸው በሁላችንም ላይ ይደርብን!!! መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው (ኢ/ር) የመካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የመጽሐፍ መምህር
نمایش همه...
#ጉባኤ_ሐዲስ_ኪዳን #የአሥራ_አንዱ_ሐዋርያት_ስምና_ታሪክ_ይህ_ነው https://t.me/+43txasWGPhc1NGU0 1. ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን • ሀገሩ በገሊላ ባህር ቤተ ሳይዳ ነው • አባቱ ዮና ሲሆን ነገዱ በአባቱ ከነገደ ሮቤል በእናቱ ነገድ ከነገደ ስምዖን ነው • የቀድሞ ስሙ ስምዖን ነበር ፤ ስምዖን ማለት እግዚአብሔር ሰማኝ ማለት ነው ይህም የእናቱን ነገድ ያስታውሳል ፤ እናቱ ከነገደ ስምዖን ናት • ጴጥሮስን ከመጠራቱ በፊት ኮንኮርዲያ (ጴርጴቱዋ) የምትባል ሴት አግብቶ ይኖር ነበር • ጌታ በአረማይክ ኬፋ ብሎ ጠርቶታል፤ በግሪክ ጴጥሪ/ጴጥሮስ፤ በግእዝ ኰኲሕ ፤ በአማርኛ ዐለት/ድንጋይ ማለት ነው • የሐዋርያት አለቃ ነው “የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።” — ማቴዎስ 16፥19 • የተጠራው ከዓሣ አጥማጅነት ነው ማቴ 4፡18 • በእምነት የተፈተነበት ማቴ 14፡28-30 ማቴዎስ 14 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁸ ጴጥሮስም መልሶ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተስ ከሆንህ በውኃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ አለው። ²⁹ እርሱም፦ ና አለው። ጴጥሮስም ከታንኳይቱ ወርዶ ወደ ኢየሱስ ሊደርስ በውኃው ላይ ሄደ። ³⁰ ነገር ግን የነፋሱን ኃይል አይቶ ፈራ፥ ሊሰጥምም በጀመረ ጊዜ፦ ጌታ ሆይ፥ አድነኝ ብሎ ጮኸ። ³¹ ወዲያውም ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘውና፦ አንተ እምነት የጎደለህ፥ ስለምን ተጠራጠርህ? አለው። • ትርጓሜ የጠየቀ ማቴ 15፡ 14 &15 ማቴዎስ 15 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁴ ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ አለ። ¹⁵ ጴጥሮስም መልሶ፦ ምሳሌውን ተርጕምልን አለው። • ክርስቶስነቱን የመሰከረ ማቴ 16፡16፤ዮሐ 6፡69 • ዓለት ፤ የቤተ ክርስቲያን መሠረት የተባለ “እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።” — ማቴዎስ 16፥18 • ሰይጣን ተብሎ የተሰደበ ማቴ 16፡23 • በታቦር ተራራ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው ብሎ የተናገረ ማቴ 17፡4 • ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት ብሎ የጠየቀ ማቴ ማቴ 18፡21 • ሁሉን ትተን ተከተልንህ ምን እናገኛለን ብሎ የጠየቀ ማቴ 19፡27 • አልክድህም ብሎ የፎከረ ነገር ግን ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ የካደ ፤ በንስሐ የተመለሰ ማቴ 26፡35 • በማኅበሩ መካከል ቆሞ የተናገረ ሐዋ 1፡15 ጀምሮ • የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ከተቀበሉ በኋላ በሕዝቡ መካከል ቆሞ ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገረ ሐዋ 2፡14 • በጥላው ይፈውስ ነበር ሐዋ 5፡12 • ሙት ያስነሣ ነበር ሐዋ 9፡40 • ሁለት መልእክታት አሉት • ሐምሌ 5 ቀን 67 ዓ.ም (68 እና 69 የሚሉም አሉ) ተገርፎ ከዚያም ተዘቅዝቆ ተሰቅሎ ያረፈበት ቀን ነው • የሞቱን ሁኔታ በተመለከተ ጌታ አስቀድሞ ነግሮታል ዮሐንስ 21 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁸ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ አንተ ጐልማሳ ሳለህ ወገብህን በገዛ ራስህ ታጥቀህ ወደምትወደው ትሄድ ነበር፤ ነገር ግን በሸመገልህ ጊዜ እጆችህን ትዘረጋለህ፥ ሌላውም ያስታጥቅሃል ወደማትወደውም ይወስድሃል አለው። ¹⁹ በምን ዓይነት ሞት እግዚአብሔርን ያከብር ዘንድ እንዳለው ሲያመለክት ይህን አለ። ይህንም ብሎ፦ ተከተለኝ አለው።" በረከቱ በሁላችንም ላይ ይደርብን! 👉 2. እንድርያስ የጴጥሮስ ወንድም • እንድርያስ ማለት ቀጥታ ትርጉሙ ‹ጠንካራ› የሆነ ማለት ነው • በመተርጉማን አገላለጽ ደግሞ ከሥራው አንጻር ‹ተባዕ ለመስቀል› መከራ ለመቀበል የሚጨክን ማለት ነው • አንድም "በኩር" ማለት ነው አስቀድሞ ለጌታ ያደረ ነውና ብለው ገልጸውታል ፤ • ከዮሐንስ ወልደ ዘብዴዎስ ጋር ሆኖ የጌታን ማደሪያ ጎብኝቷል ዮሐ 1፡37 • አስቀድሞ የዮሐንስ መጥምቅ ደቀ መዝሙር ነበር • እስከ ሀገረ በላእተ ሰብእ ድረስ ድረስ ደርሶ አስተምሯል፤ • የቁስጥንጥንያን ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው የቁስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስ እንደሆነ ታሪክ ጸሐፊው አውሳብዮስ ይናገራል። • እረፍቱ ታኅሣሥ 4 በመስቀል ተሰቅሎ በድንጋይ ተደብድቦ ነው፡፡ • በ 80 ዓ.ም እንደሞተ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ይነግረናል • ሁለቱም ወንድማማቾች ከዓሣ ማጥመድ ወደ ሰውን ማጥመድ ተጠርተዋል በረከታቸው ይደርብን🙏 3. ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ ፦ በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት የታወቁ 3 ያዕቆቦች አሉ 1. ያዕቆብ እኁኁ ለእግዚእነ (የጌታ ወንድም ያዕቆብ) 2. ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ (የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ) 3. ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ ያዕቆብ ማለት "የሚይዝ ፤ የሚያሰናክል" ማለት ነው የመጀመሪያው ያዕቆብ "ሰኰና ኤሳው-ኤሳውን ተረከዝ" ይዞ ስለተወለደ "አእቃጺ አኀዚ" ተብሏል “ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ፥ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር፤ ስሙም ያዕቆብ ተባለ። — ዘፍጥረት 25፥26 • ይህ ሐዋርያው ያዕቆብ ሰኰና ወንጌልን ይዞ ሲያስተምር ኖሯልና አኀዚ ወዲህም የመናፍቃንን ትምህርት ያሰነካክላልና አእቃጺ ይባላል • የምሥጢር ሐዋርያት ተብለው ከሚጠሩት ውስጥ አንዱ ነው ዕረፍቱ ሚያዝያ 17 ቀን የተገደለው በሰይፍ ነው በሰይፍ የገደለውም ሄሮድስ ነው “የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው።” — ሐዋርያት 12፥2 4.ዮሐንስ ወልደ ዘብዴዎስ ፦ ሦስት ዮሐንሶች አሉ 1. ዮሐንስ መጥምቅ 2. ዮሐንስ ማርቆስ 3. ዮሐንስ ወንጌላዊ ዮሐንስ ወልደ ዘብዴዎስ ፣ ወልደ ነጎድጓድ፣ ሐዋርያ፣ ወንጌላዊ በአነርጌስ፣ፍቁረ እግዚእ፣ንጹሕ ፣ ድንግል፣ታኦሎጎስ(ነባቤ መለኮት)፣አቡቀለምሲስ እየተባለ ይጠራል። እመቤታችንን በመስቀል ሥር በእናትነት ተቀብሏል ዮሐንስ 19 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁶ ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን፦ አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ አላት። ²⁷ ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን፦ እናትህ እነኋት አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት። ዕረፍቱ ጥር 4 ቀን ነው ፤ ተሠውሯል ፤ ሥጋው በምድር አልተገኘም ማቴዎስ 16 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²¹ ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር። … ²⁸ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ እዚህ ከሚቆሙት ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ። “ስለዚህ፦ ያ ደቀ መዝሙር አይሞትም የሚለው ይህ ነገር ወደ ወንድሞች ወጣ፤ ነገር ግን ኢየሱስ፦ እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ? አለው እንጂ አይሞትም አላለውም።” — ዮሐንስ 21፥23 5. ፊልጶስ • ፊልጶስ ማለት መፍቀሬ አምላክ ማለት ነው "አምላኩ የሚወደው አምላኩን የሚወድ" ማለት ነው • አንድም "ረያጼ አፍራስ ፣ አኀዜ ኲናት" (ፈረስ የሚገራ የሚጋልብ ጦር የሚይዝ) ማለት ነው። #ሦስት ፊልጶሶች አሉ፦ 1. ሄሮድስ ፊልጶስ 2. ሐዋርያው ፊልጶስ 3. ወንጌላዊው ፊልጶስ (ከሰባቱ ዲያቆናት አንዱ)
نمایش همه...
ነቅዐ-ጥበብ

ነቅዕ ንጹሕ ዘእምአንቅዕተ ሕግ

یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.