cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

አዲስ ሪፖርተር - NEWS

🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው ! => በቻናሉ 📌 ፈጣን ፥ 📌 ትኩስ ፥ 📌 ወቅታዊ እና 📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል ! 🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል ! For promotion @Addis_reporter_bot #ADDIS ABABA, ETHIOPIA

نمایش بیشتر
Advertising posts
40 518مشترکین
-1124 ساعت
-947 روز
-46630 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

በዛሬው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ጥያቄ ካቀረቡ የምክር ቤት አባላት መካከል አንዱ የሆኑት ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ፤ ከኮሪደር ልማት ተነሺዎች መካከል “1,135 ሰዎች አሁንም ምትክ ቤት ወይም ቦታ አለማግኘታቸውን” በማንሳት ጥያቄ አቅርበዋል። “1,135 ሰው ማለት ቀላል አይደለም። በዚህ ወቅት፣ በዚህ የኑሮ ውድነት፣ በዚህ ጊዜ ተረጋግቶ የሚኖርበት አጋጣሚ ካልተፈጠረ፤ የሚሰራውን ስራ ሁሉ በዜሮ ድምር የሚያባዛ ነው የሚሆነውና እርሱ ለምን ግምት ውስጥ አልገባም?” ሲሉ ጠይቀዋል። የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት በ90 ቀናት እንዲጠናቀቅ እቅድ እንደተያዘለት በመጥቀስም፤ “የግድ በዚህ ሶስት ወር ውስጥ ስራ ማለቅ አለበት ወይ?” ሲሉ ተጨማሪ ጥያቄ አስከትለዋል። “በጊዜ ተለክቶ ስራ መሰራት አለበት፤ ልክ ነው። አምናም የ90 ቀን እቅድ ተብሎ ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል። ሁልጊዜ ግን በዚህ መልክ በዘመቻ መሰራት አለበት ወይ? የሚል ጥያቄ ይስነሳል” ያሉት ዶ/ር ሲሳይ፤ “ነገሮች በተረጋጋ እና በታቀደ መልኩ እንዲሄዱ ለማድረግ መሰራት የለበትም ወይ?” ሲሉ አስተያየት አዘል ጥያቄያቸውን አስደምጠዋል። ከንቲባ አዳነች ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ የምክር ቤት አባሉ ከጠቀሷቸው የልማት ተነሺዎች ውስጥ “አንድም ሰው ቤት ሳይሰጠው ተነስቶ ሌላ ቦታ የገባ ሰው የለም። በተለይ የመንግስት ቤት ተከራይ፣ የቀበሌ፣ የኪራይ ቤቶች፣ የቤተክህነት ጭምር ማለት ነው” ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ የልማት ተነሺዎችን በዚህ መልኩ የማስተናገድ አካሄድ ሲከተል “ለመጀመሪያ ጊዜ” መሆኑንም ጠቁመዋል። Via:ኢትዮጵያ ኢንሳይደር @Addis_Reporter
نمایش همه...
👍 10😢 5 3
የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች በፍተሻ ኬላዎች አላግባብ ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍሉ እየተጠየቁ ነው ተባለ ለአገር አጠቃላይ የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ ዋነኛ መሆኑ የሚነገርለት የትራንስፖርቱ ዘርፍ በርካታ ፈተናዎች እንደተጋረጡበት ያስታወቀው የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ማህበር ነው፡፡ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ዘውዴ ከዚህ ቀደም የረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች እገታ፤ ዝርፊያ፤ ግድያ እና ሌሎች ጥቃቶችም ሲደርስባቸው እንደነበር ገልጸው፤ አሁን ላይ ግን በአንጻራዊነት መሻሻሎች እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡ ይሁን እንጂ አሁን ላይ አሽከርካሪዎች በሚያቀኑባቸው አከባቢዎች ባሉ የፍተሻ ኬላዎች አላግባብ እንዲከፍሉ የሚጠየቁት ገንዘብ ከፍተኛ መሆኑን እና ይህም በዘርፉ ላይ ችግር እየፈጠረ እንዳለ ተናግረዋል፡፡ ስራ አስኪያጁ እንደሚሉት ከሆነ ተሸከርካሪዎች በሚንቀሳቀሱባቸው ኬላዎች ከ5ሺህ እስከ 30 ሺህ የሚደርስ ገንዘብ እንዲከፍሉ እየተገደዱ ነው፡፡ ዘርፉ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የተለያዩ ፈተናዎች እንደተጋረጡበት ማህበሩ ያስታወቀ ሲሆን፤ የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር በበኩሉ በአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለማስቆም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራው ነው ማለቱ የሚታወቅ ነው፡፡ Via:መናኸሪያ ሬዲዮ @Addis_Reporter
نمایش همه...
👍 7
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ተገለጸ። ከሶስት ዓመት በፊት የደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) በቢሯቸው ከታዩ አንድ ወር አልፏቸዋል ተብሏል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የዩንቨርሲቲው አስተዳድር አመራር አባል "ፕሬዝዳንቱ ከመጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ. ም ጀምሮ በስራ ላይ አይተናቸው አናውቅም" ሲሉ ለአል ዐይን አማርኛ ዘጋቢ ነግረውታል። "ፕሬዝዳንቱ ንጉስ ታደሰ ከተጠቀሰው ቀን አንስቶ የት እንደሄዱ እና መቼ እንደሚመለሱ አናውቅም" ሲሉም እኝህ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አመራር ነግረውናል። ይሁንና ፕሬዝዳንቱ በቢሮ መታየት ካቆሙ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ባልታወቁ ሀይሎች መታገታቸውን ሰምተናል ሲሉም አክለዋል። የሰማን ሸዋ ዞን ፖሊስ፣ ኮማንድ ፖስት፣ ትምህርት ሚንስቴር እና የደብረብረሀን ከተማ ፖሊስ ስለ ደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ ፕሬዝንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) ጉዳይ ምላሽ እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።ከቤተሰብም የተገኘ መረጃ የለም። የፌደራል መንግሥት ከአንድ ዓመት በፊት የክልል ልዩ ሀይሎችን "መልሼ አደራጃለሁ" የሚል ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ግጭት የተከሰተው። ግጭቱ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተካሄደ ሲሆን ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉን ተከትሎ በአማራ ክልል ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል። ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የታወጀው ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት የተራዘመ ሲሆን ይህ አዋጅ ሊጠናቀቅ ከሁለት ወራት ያነሰ ጊዜ ቀርቶታል ሲል አል ዓይን አማርኛ ዘግቧል። ፕሬዝደንቱ ከወር በፊት ከመኖሪያ ቤታቸው ታግተው እንደተወሰዱ በዚህ ቻናል ላይ መዘገቡ ይታወሳል። @Addis_Reporter
نمایش همه...
በዓልን ምክንያት በማድረግ የእሁድ ገበያዎች ሳምንቱን ሙሉ አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉ ተነግሯል የትንሳዔ በዓልን አስመልክቶ 188 የእሁድ ገበያዎች ሳምንቱን ሙሉ አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስውቋል፡፡ በዓልን አስመልክቶ የምርት እጥረት እንዳይከሰት በመዲናዋ የሚገኙ 188 የእሁድ ገበያዎች በመደበኛነት ቅዳሜ እና እሁድ የሚካሄደውን የእሁድ ገበያዎች፤ ሳምንቱን ሙሉ እንዲካሄዱ መደረጉን የቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሰውነት አየለ ተናግረዋል፡፡ ይህም በዓልን አስመልክቶ የሚፈጠር የምርት እጥረት፣ ህገ ወጥ ንግድን እና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት እንደሚረዳ ተነግሯል፡፡ የእሁድ ገበያዎቹ የትራስፖርት አገልግሎት ላይ መጨናነቅ የማይፈጥሩት ተለይተው መሆኑን አንስተው፤ በእነዚህ የገበያ ቦታዎች ላይ የገበያ ዋጋ ጥናት በቢሮ በየ 3 ቀኑ የሚከናወን እና የዋጋ ተመን እንደሚዘጋጅ እና የክትትል ስራ እንደሚከናወን ተጠቁሟል፡፡ @Addis_Reporter
نمایش همه...
👍 4 3
ራይድ በኤሌክትሪክ መኪና የታገዘ የትራንስፖርት አገልግሎት መጀመሩን አስታወቀ ራይድ የአረንጓዴ ትራንስፖርት አገልግሎት አካል የሆነውን የኤሌክትሪክ መኪኖች አገልግሎትን ማስጀመሩን በዛሬው እለት በአድዋ ሙዚየም የተለያዩ ተቋማት ሚንስትሮች፣ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች፣ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የዓለም አቀፍ እና የአህጉራዊ ድርጅት ተወካዮች፣ አምባሳደሮች እና ዘርፉን ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ የሚገኙ ግለሰቦች በተገኙበት ገልጿል፡፡ የራይድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳምራዊት ፍቅሩ የራይድ የትራንስፖርት ዘርፉ ወደ ኤሌክትሪክ መኪኖች የሚያደርገዉን ሽግግር በይፋ በሚጀመርበት በዚህ ቀን እንደገለጹት በሀገራችን የአረንጓዴ ትራንስፖርት ዘርፉን ለማስፋት እየተደረገ ያለዉን ርብርብ ራይድ በርካታ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ወደ አገልግሎት በማስገባት ከቴከኖሎጂው ፈር ቀዳጆች ተርታ ተቀምጧል ብለዋል ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በሞባይል መተግበሪያ እና በጥሪ ማዕከል አማካኝነት ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት በማቅረብ ላይ የሚገኘዉ ራይድ የኤሌክትሪከ መኪኖች ወደመገልገል መሸጋገሩ የተገለፀ ሲሆን ይህ አግልግሎቱ "የራይድ ራዕይ 2030” አንዱ (RIDE'S 3G, Vision 2030) ማስጀመሪያ ጭምር መሆኑም ተነግሯል። እነዚህ የተስላ ብራንድ የሆኑት ከ150 በላይ የኤሌክትሪክ መኪኖች ወደ አገልግሎት የሚገቡበት የመጀመሪያ ዙር የራይድ የአረንጓዴ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ባንኮች፣ የኢንሹራንስ ተቋማት እና የመኪና አስመጪዎች ተሳትፈውበታል ተብሏል ። ራይድ በአሁን ሰአት ከ400 በላይ ለሆኑ ሰዎች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 85 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። Via:በድሬቲዩብ @Addis_Reporter
نمایش همه...
👍 12 3😢 3
በቅርቡ በራሱ ሰራተኞች ጉዳት የደረሰበት የአይደር ሆስፒታል የላብራቶሪ ክፍል አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተነገረ የሆስፒታሉ ዳይሬክተር ዶ/ር አብርሃ ገ/እግዚአብሔር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ማሽኑ በተለያዮ አቅጣጫዎች ውድመት ደርሶበት  ለሁለት ሳምንት ያህል ከአገልግሎት ውጪ እንደነበር ተናግረዋል። ድርጊቱን ፈፅመዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች 4 ግለሰቦች መሆናቸውን እና በቁጥጥር ስር ዉለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ብለዋል። ተጠርጣሪዎቹም ማሽኑ በነበረበት የስራ ክፍል ላይ ተመሳሳይ የስራ ድርሻ የነበራቸው መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል ። እስካሁንም ድርጊቱ ለምን እንደተፈፀመ የተደረሰበት ነገር አለመኖሩን እና አሁንም በምርመራ ላይ እንደሆነ አንስተዋል ። ድርጊቱ የተፈፀመው መጋቢት 21 ለሊት ሲሆን በሚሊዮኖች የሚገመት ዋጋ ያለው የህክምና መሳሪያ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር የሚታወስ ነው። @Addis_Reporter
نمایش همه...
👍 12
የአገር ውስጥ በረራ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንደገለጹት እየተጠናቀቀ ባለው በጀት አመት የአገር ውስጥ ተጓጓዦች ቁጥር 3.5 ሚሊየን ይደርሳል፡፡ ይህ መጠን ከ2015 በጀት አመት አንጻር የ34.6 በመቶ ጭማሪ የሚኖረው ነው፡፡ በቀደመው አመት በአገር ውስጥ በረራ የተስተናገዱት ተሳፋሪዎች 2.6 ሚሊየን እንደነበሩ አቶ መስፍን አስታውሰዋል፡፡ አየር መንገዱ እየሰፋ ያለውን የደንበኞች ቁጥር ታሳቢ በማድረግ የቦሌ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ አሁን በአመት ማስተናገድ ከሚችለው 25 ሚሊየን መንገደኞች ከ4 እጥፍ በላይ ማስተናገድ የሚችል አየር ማረፊያ እና ማስተናገጃ ለመገንባት በዝግጅት ላይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፡፡ ሆኖም ይህ ማእከል የአለም አቀፍ እና በተወሰነ መልኩ የጭነት ማስተናገጃ ሆኖ የሚሰናዳ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልጸዋል፡፡ የቦሌ አየር ማረፊያ እያደገ የመጣውን የአገር ውስጥ በረራ በማሰተናገድ ይቀጥላል ያሉት አቶ መስፍን ; የጥገና እና የጭነት ማእከሉም በቦሌ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡ አየር መንገዱ ለአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ የአየር መንገዶች የጥገና አገልግሎት እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡ ይህንኑ ስራ ለማስፋት ተጨማሪ የመለዋወጫ ማስቀመጫ እና የጥገና ማእከል እየሰራ ሲሆን እስከመጪው ታህሳስ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል:: በተመሳሳይ እጅግ ዘመናዊ የጭነት ማእከል የገነባው አየር መንገዱ ዋነኛ የችነት ማእከሉን በቦሌ እንደሚቀጥል ነው ያስታወቀው፡፡ ከአዲስ አበባ ወደ ቢሾፍቱ 40 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገነባው አዲስ የአየርመንገድ ከተማ ከቦሌ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ ጋር በፈጣን ባቡር እንደሚገናኝ ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል፡፡ @Addis_Reporter
نمایش همه...
የኤርትራ ጦር  ከዛላንበሳና አጎራባች ወረዳዎች ሰዎችን አግቶ እየወሰደ ነው ተባለ የዛላ  አንበሳ ከተማ ከንቲባ ብርሃነ በርሄ ለጣቢያችን እንደተናገሩት ከምስራቃዊ ዞን  ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ታግተዉ ተወስደዋል  ብለዋል፡፡ ከዛላ አንበሳ 26 ሰዎች፣ ከጉለም ወረዳ  50  እንዲሁም ከኢሮፕ 28 ሰው በኤርትራ ሰራዊት እንደተወሰደ  ገልፀው በዚህ ሳምንት ደግሞ ቁጥሩ መጨመሩን ተናግረዋል። አሁን ላይ ዛላንበሳ ከተማን ጨምሮ  ምስራቃዊው ዞን ሙሉ በሙሉ በኤርትራ ጦር ቁጥጥር ስር እንደሆነ የሚናገሩት የከተማዋ ከንቲባ ማህብረሰቡም  ብዙ በደል እና ጥቃት እየደረሰበት ነዉ ብለዋል፡፡ የኤርትራ ጦር  የአካባቢዉን ነዋሪዎቹ በአልጀርስ ስምምነት መሰረት  ኤርትራዊ እንደሆኑ በመግለጽ  በኃይል  እንደተቆጣጠረም ሰምተናል፡፡ የፌድራል መንግስት ምንም አይነት ትኩረት አልሰጠንም የሚሉት አቶ ብርሀነ ዳግም ጦርነት አንፈልግም ግን ደግሞ ማንነታችንን እና ህልውናችንን ሊያስከብርልን ይገባል ብወዋል። በከተማዋ የሚገኙ መሰረተ ልማቶች በጦሩ  ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ ተነስቶ  በከተማው እንዲሁም በአካባቢው ያለው ነዋሪ ለከፋ ችግር እንደተጋለጠም ተናግረዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከ30ሺ በላይ ነዋሪ ተፈናቅሎ በመቀሌ፤ በአዲግራት እንዲሁም በተለያዩ አከባቢዎች በመጠለያ ጣቢያ እንደሚገኝ አቶ ብርሀነ ገልፀዋል፡፡ @Addis_Reporter
نمایش همه...
👍 6👏 4 2
ኪት ቦይድ ላለፉት 270 ቀናት ከደቡብ አፍሪካዋ ኬፕ ታውን እስከ ግብፅ ካይሮ ሲሮጥ ከርሟል። ነገር ግን በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው የፀጥታ ችግር ወደኋላ እያስቀረው እንደሆነ ተናግሯል። ቦይድ ሦስት ጊዜ በሰሜን ኢትዮጵያ በኩል ለማቋረጥ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። አልፎም አንድ ጊዜ የጦር መሣሪያ በያዙ ሰዎች ተይዞ እንደነበር እና ከመታፈን ለጥቂት እንዳመለጠ ተናግሯል። ብሪታኒያዊ-ደቡብ አፍሪካዊው ቦይድ እንዳለው ታጣቂዎች እሱን እና ካሜራ ይዞ የሚከተለውን ማይክል የማፈን ሙከራ እንዳደረጉባቸውም ያስታውሳል፡፡ አሁን ግን ህልሜ ሊከስም ተቃርቧል ብሏል ለቢቢሲ፡፡ @Addis_Reporter
نمایش همه...
👍 5 1🥰 1
ዲ/ን ዕዝራ ኃይለ ሚካኤል ወደ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በይቅርታ መመለሳቸው ተገለጸ። ዲ/ን ዕዝራ ኃይለ ሚካኤል ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን በይቅርታ መመለሳቸውን ቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ማሳወቁ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታውን የተቀበለው ሚያዚያ 9/2016 ዓ/ም ባደረገው ስብሰባ ሲሆን ዲ/ን ዕዝራ ኃይለ ሚካኤል "በምንፍቅና መንገድ ስጓዝ የነበርኩ ስሆን በአሁኑ ወቅት የስህተት መንገዴን አርሜ ወደ እናት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በይቅርታ ልመለስ" ብለው ያቀረቡትን ጥያቄ ተክሎ መሆኑም ተገልጿል። ቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስም ዲ/ን ዕዝራ ኃይለ ሚካኤል በጠየቁት መሠረት በድጋሚ እንዳይበድሉ ምክርና ተግሣጽ ተሰጥቷቸው ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን በይቅርታ መመለሳቸውን አሳውቋል። በቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ተቀባይነት ያገኘው የይቅርታ ጥያቄ እንዳለ ሆኖ በቅዱስ ሲኖዶስ በታዘዘው መሠረት ዲ/ን ዕዝራ ኃይለ ሚካኤል በይፋ ወጥተው በይቅርታ መመለሳቸውንና ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ መጠየቃቸውን የገለጹ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ድርጅት ካስተላለፈው መረጃ ለማወቅ ተችሏል። ከዚህ በተጨማሪም በይቅርታ የተመለሱትን ዲ/ን ዕዝራ ኃይለ ሚካኤልን በምክር የሚያጸኑና በተግሳጽ የሚያቀኑና የሚከታተሉ አባቶች መኖራቸውም ታውቋል። ዲ/ን ዕዝራ ኃይለ ሚካኤል ቀደም ባለ ታሪካቸው ገና በልጅነታቸው ዕድሜ ለዝማሬ አገልግሎት በቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ከቆሙ አገልጋዮች አንዱ እንደነበሩ የሚታወስ ነው። Via:አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ @Addis_Reporter
نمایش همه...
👍 13👏 8😢 2